Monday, May 11, 2015

“የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ” የማኅበረ ቅዱሳን ኅቡእ ድርጅት ነውRead in PDF 

ሰሞኑን የግንቦቱን የሲኖዶስ ስብሰባ ለማወክ ማኅበረ ቅዱሳን “የአዲስ አበባ /ስብከት ገዳማት እና አድባራት ሰንበት /ቤቶች” በሚል ስም ያደራጃቸውን የክፉ ቀን “ቅምጥ ኃይሎች” የመዘምራን ልብስ በማልበስ ለማወክ ሞክሮ የነበረ መሆኑ የሰሞኑ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራ  ከገቢያቸው በላይ ሀብት ባካበቱ አማሳኞች እና ወደ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር በሰረጉ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ” በሚል ርእስ ሜይ 5/2015 ላቀረበው ፕሮፓጋናዳዊ ዘገባ ስምዖን የተባለ ሰው ለብሎጉ የሰጠው አስተያየት እንዲህ ይላል፦  

“የጥቅምትና ግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ ሲመጣ በብሎግ ተጠራርቶ ራስን እያጸደቁ ሌላውን መወንጀል ከአዲስ አበባ //ቤት ያልተጻፉ ሕጎች አንዱ ሆነ መሰለኝ፡፡ በየሰበካ ጉባኤው የሰ//ቤት ተወካይ አለ፡፡ ቅሬታችሁንና ማስረጃችሁን በዛ በኩል ማቅረብ ትችሉ ነበር፡፡ አሁን የያዛችሁት የማኅበረቅዱሳን ተላላኪ መሆንን ነው፡፡ ያሳፍራል፡፡ ከቻላችሁ በራሳችሁ ሳንባ ተንፍሱ፡፡ ቢያንስ ደግሞ አሁን ቅሬታ ተብየውን በመነጽር ታግዞ በወጣቶች ሥም ለማቅረብ እንደሚሞክረው እድሜውን ከቤ. ተጠግቶ የቆይታውን ያህል የረባ መንፈሳዊ እውቀት ሳይጨብጥ ከካሕናት በቀሰመው አድማና አሉባልታ ከሚለካ ወመሽ ሸበቶ ሳይሆን በትክክል በቃለዐዋዲው መሰረት 30 አመት ያልሞላው ተወካይ እንዲናገር አድርጉ፡፡ መናገር መብት ስለሆነ ማንም አይከለክላቸሁም፡፡ የተሞላችሁትን ይዛችሁ ቁረጠው ፍለጠው ስላላችሁ ግን የሚሆን ነገር የለም፡፡ በሰልፍና በመንጋ ሆኖ በጮኸ ሳይሆን እውነት የምትቆመው በማስረጃ ነው፡፡ ለእያንዳንዷ በቤተክርስቲያን ባለች ድክመት ውስጥ ፓትርያርኩ ብቻ ሳይሆኑ ከሰ//ቤት ጀምሮ ያሉ አካላት ተጠያቂ መሆናቸውን አትዘንጉ፡፡ በከዳው ምዕመን፣ በጠፋው ሥርዓት፣ በጎደለው ገንዘብ ሁሉ ይብዛም ይነስም ሁልሽም እጅሽ አለበት፡፡ ወላ ማኅበረ ቅዱሳን ወላ /ተማሪ፡፡ እንደ ጲላጦስ እጅሽን ቀድመሽ ለመታጠብ አትሽቀዳደሚ፡፡ እሱ የቸከና የመነቸከ ከማኅበረ ቅዱሳን የተዋሳችሁት መፈክር ተነቃበት፡፡ ሌላ ሞክሩ፡፡”

ይህ ሚዛናዊና እውነተኛ አስተያየት ነው፡፡ የሰንበት ት/ቤቶቹ ያቀረቡት አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የእነርሱ ሳይሆን ማቅ ከነአባ ማቴዎስና አባ ቀሌምንጦስ ጋር አብሮ ያዘጋጀው ነው፡፡ የራሳቸው ጥያቄ ቢሆን እንደተባለው በየደብራቸው ማቅረብና ችግሮችን እዚያው መፍታት ይችሉ ነበር፡፡ ካልተቻለም በየደረጃው ወደላይ መምጣት ይችሉ ነበር፡፡ ይህን ሙከራ ሳያደርጉና በየደረጃው አቤት ሳይሉ በቀጥታ ወደ ሲኖዶስ መቅረባቸው ግን አጀንዳው የእነርሱ ሳይሆን የአልታዘዝ ባዩ የማቅ ለመሆኑ በቂ ምስክር ነው፡፡ በስማቸው በተጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደ ገለጹትም ማቅ ካልሆነ በቀር የትኛው የሰ/ት/ቤት ወጣት ነው ፓትርያኩ ለዘረኛውና የአንኮበር ፖለቲካ ባለተስፋ ለሆኑት ለአባ ማቴዎስ በየጊዜው የሚጽፉትን ደብዳቤ የሚከታተለውና የሚረዳው? ደብዳቤው ማቅ ያረቀቀውና ለሰንበት ት/ቤቶቹ የሰጠው ነው፡፡ ይህም አዲስ አይደለም፤ ከዚህ ቀደም በግንቦት 2004 ውግዘት እንዲተላለፍ ለማድረግ ማቅ አንዱን በስሙ ሌላውን ግን በእነዚሁ አስተኳሾቹ ስም በሁለት ፋይሎች ክስ መስርቶ የነበረ መሆኑን ዘግበን እንደ ነበረ ይታወሳል፡፡ በተለይም በአስተኳሾቹ በኩል ከዚህ ቀደም ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ውለታ የዋሉና ዛሬ በሕይወት የሌሉ ታላላቅ ሰዎችንና ለማቅ አመለካከት አንንበረከክም ያሉና በጠቅላይ ቤተክህነትና በተለያዩ ደብሮች ውስጥ እያገለገሉ ያሉትን ሰዎች ለማስወገዝ ያቀረበው ሁለተኛው ክስ ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚታወስ ነው፡፡ አሁንም ማቅ ፊት ለፊት በስሙ ለማቅረብ ያልቻለውን ጉዳዩን በእነዚህ ወጣቶች በኩል ለማቅረብ ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ ነገር ግን እስከ መቼ ነው እነዚህን ንጹሓን ወጣቶች ማቅ መናጆ የሚያደርጋቸው? እስከ መቼስ ነው እነርሱ እንደ ጠፍ ከብት በማኅበረ ቅዱሳን የሚነዱት? ወጣቶቹ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ለማቅ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ቢወግኑ ይሻላል፡፡
ከዚህ በፊትም አበክረን እንዳሳሰብነው ማቅ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ለማራመድ እንደ አስተኳሽ ከሚጠቀምባቸውና በሌላ ስም ካደራጃቸው ቡድኖች አንዱ ይህ የሰንበት ተማሪዎች ተብዬ ቡድን ነው፡፡ ይህን ቡድን የሚመሩና የሚያስተባብሩ ቤተክርስቲያንን ተገን አድርገው የማቅን ጥቅም የሚያስጠብቁ ዋና ዋና መሪዎች የሚከተሉት ሲሆኑ የርክበ ካህናቱን ዋዜማ ሰልፍ ሲያስተባብሩ ታይተዋል፡፡ እነርሱም፦ አቶ ሳሙኤል የያሬድ አካባቢ ተወካይ፣ አቶ ዋሲሁን የመሓል አራዳ ተወካይ፣ አቶ ሄኖክ አስራት የግቢ ገብርኤል ተወካይና የአመራሩ ሊቀመንበር፣ የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ሰ/ት/ቤት ሊቀመንበር ወጣት መንክር ግርማ ናቸው፡፡

ማቅ በአንድ በኩል በቅርቡ በአባይነህ ካሴ አማካይነት በሐራ እንዳስነበበን በአይኤስ የተጎዱ ወገኖችን ምክንያት በማድረግ “አንድነትን ብናጸና” ብሎ ያስተላላፈው መልእክት ጥሩ ሆኖ ሳለ፣ የበቀደሙ ሰልፍ አስተባባሪዎች ግን “10 ሚሊየን ሕዝብ ወጥቷል ተሐድሶ ሰርጎ ገብቷል” ብለው ሰልፍ መውጣታቸው አስገራሚና ወቅቱን ያልጠበቀ፣ የቤተክርስቲያንን ጠላት ሳይሆን ለቤተክርስቲያን በጎ የሚያስቡትን ወገኖች የሚኰንን ጽሑፍ ነው፡፡ ለመዘመር ወጥተው የማቅን ፖለቲካዊ አጀንዳ በማንገብ ተቃውሞ ማሰማትስ መንፈሳዊነት ነው? ወይስ ፖለቲከኛነት? እነዚህ ሰዎች የቤተክርስቲያንን ልጆችና አባቶች ተሐድሶ እያሉ የምእመናን ቁጥር እንዲመናመን አደረጉ፣ አሁን ደግሞ ሌላ 10 ሚሊየን እናስወጣ እያሉን ይሆን? አሁን የምንገኝበት ወቅትስ ይህን የምናስብበት ጊዜ ነውን?
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምላተ ጉባኤ በ2 ቀን ውስጥ ተጠናቋል፡፡ አባ ማቴዎስና አባ ቀሌምንጦስ ሽምቅ ተዋጊ አደራጅተውና ወጣቶችን አስተረባብረው ገና በዋዜማው የፓትርያርኩን መንፈስ ለማደፍረስ ቢሞክሩም ገና ስብሰባው ሲጀመር በመጠናቀቁ የሁሉም ሕልም እልም ብሏል፡፡ ለጥቅምቱም የሲኖዶስ ስብሰባ አምላክ ያውቃል፡፡ እስከዚያው ድረስ የእግዚአብሔር ቃል ሥራውን ከዚህ በበለጠ ይሠራል፡፡ ዘረኞቹ አባ ማቴዎስና አባ ቀሌምንጦስም ሌላ ዕቅድ መንደፋቸው አይቀርም፡፡ ፓትርትርያኩም ለማኅበሩ እኩይ ዓላማና ተግባር ጀርባ እየሠጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን አሁን በያዙት ሁኔታ መምራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ለመሆኑ የአንድ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያንን በርእሰ መንበርነት የሚመሩ ፓትርያክ በልዩ ሀገረ ስብከታቸው  ላይ በዋናና በምክትል ሥራ አስኪያጅነት የሾሟቸውን ሥራ አስኪያጆች የሰንበት ተማሪዎች ያለምንም በቂ ምክንያት መቃወም የጤና ነውን? ከዚህ ይልቅ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሚመለከቱ ችግሮች ላይ ለምን አላተኮሩም? ይህ ሁከት ለመቀስቀስ ማቅ ያቀጣጠለው እሳት ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ ወጣቶቹ ያቀረቡትን የተሐድሶ አጀንዳ ጉዳይም ሲኖዶሱ ቦታም አልሰጠው፤ በመግለጫው ላይም በምንም ዓይነት መልኩ ሳይጠቅሰው ቀርቷል፡፡ ይህም ማቅ በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለማስነሣት የሞከረው አቧራ ሳይጨስ መምከኑን ነው የሚያሳየው፡፡ ደግሞስ ቀድሞው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና በጥቅም ተጋሪዎቻቸው ሙስናና ከፍተኛ በደል ሲፈጸሙ ዝም ብለው በብዙሃኑ ጩኸት ከቦታቸው ሲነሱና የአሁኖቹ ሥራ አስኪያጆች ተተክተው ከጅምሩ ከሞላ ጎደል መልካም ሥራ እየሠሩ ባለበት ሁኔታ ስለሙስና መዘመር ምን ይሉታል? ሙስናውና ዝርፊያው አሳስቧቸው ሳይሆን ማቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየዘረጋ የነበረው መዋቅሩ አደጋ ውስጥ እንደሚወድቅበት ስለሰጉ ነው የሚል ከፍተኛ ግምት አለ፡፡ 

እነዚህ በሰንበት ተማሪዎች ስም የተሰባሰቡት ቡድኖች ማቅ ሁከት ለመፍጠርና የሚፈልገውን በግድ ለማስፈጸም ያቋቋማቸው መሆናቸው ከታወቀ ግን ስለምን ዝም ይባላሉ? ከዚህ ቀደም የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን ስማቸውን ሳይሆን ግብራቸውን ተመልክቶና የተቋቋሙበትን ትክክለኛ ዓላማ ተገንዝቦ እንዲበተኑ እንዳደረገ ሁሉ እነዚህን ስብስቦችም መበተን ዕውቅናን መንፈግ ተገቢ ነው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት ካስፈለገም የማኅበረ ቅዱሳን ጣልቃ ገብነት ሳይኖርና በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው አስተባባሪነት በገለልተኛነት ሊቋቋሙ የሚችሉበትንና የማቅ ቀኝ እጅ ሳይሆኑ ለቤተ ክርስያን የሚጠቅሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህን ሊያስቡበት ይገባል እንላለን፡፡ ሰሞኑን ያሳዩት “የውክልና ሰልፍ” በዝምታ ከታለፈ ግን ነገ ከዚህ የከፋ ነገር እንደማያደርጉ ምንም ማስተማማኛ የለም፡፡ ስለዚህ ይህን የማኅበረ ቅዱሳን ኅቡእ ድርጅትና እኩይ ዓላማውን በእንጭጩ መቅጨት ያስፈልጋል፡፡

8 comments:

 1. የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ሰ/ት/ቤት ሊቀመንበር ወጣት መንክር ግርማ በተመለከተ

  ይህ ሰው አባቱ መርጌታ ግርማ(ትንሽ የቤተ ክህነት እውቀት የያዘ ና ውስጥ ለውስጥ ጥንቆላ የሚሰራ ሲሆን ፡ ልጅየው መንክር ደግሞ በስርህ ሁለት ሰው በማስገባት አምስት ሽህ ብር እያስከፈልህ ትበለጽጋልህ የሚባል ፍልስፍና ይዞ የሰውን ሁሉ ገንዘብ ላፍ አርጎ በመብላት ቤተ ክርስቲያን አያሰይኝ ያለ ነበር ይህም ሲሆን ግን የማቅ አባል ነበር አሁንም ተመልሶ በመምጣት የማቅን አጀንዳ ያራግባል


  ቢተው ነኝ ከደብረ ሲና

  ReplyDelete
 2. የሀይለጊዮርጊስ በፖለቲካ ምክንያት መታሰር ይገርማል፡፡የሄኖክ አስራትንም እንጠብቃለን፡፡ከሚለያዩ አንድ ላይ ቢሆኑ ይሻላል፡፡ተሐድሶ አልወድም፡፡ሄኖክና ሀይለጊዮርጊስ የሚሉዋቸው ጭፍን የማኅበረቅዱሳን አጨብጫቢዎችም አይመቹኝም፡፡በተለይ ሄኖክ ለማኅበረቅዱሳን እንደማይመጥን ማኅበረቅዱሳኖችም ያውቃሉ፡፡
  እናንተ ግን የሰው አስተያየት ሳይቀር ዜና አድርጋችሁ ማቅረባችሁ ሼም ነው፡፡ፕሮቴስታንቶች ስትባሉ ኦርቶዶክስን እና ልጆቿን የተቸ ሁሉ ዘሎ ለማቀፍ ትሞክራላችሁ፡፡ኮምፕሌክሳሞች፡፡የሆነ ውስጣችሁ የማይጠፋ የበታችነት ስሜት ስላለባችሁ ሁለት ሱባኤ ተጠመቁ፡፡

  ReplyDelete
 3. ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የሲኖዶስ ጉባዔ በተካሄደ ቁጥር እንደቁራ ጮኾ ማወክ የማኅበረ ቅዱሳን እና ቡችሎቹ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ እባካችሁ የዚህን ማኅበረ ሠይጣንን እኩይ ሥራ ፈጽሞ አታውሩት፡፡

  ReplyDelete
 4. አባ ማቴዎስና አባ
  ቀሌምንጦስ ሽምቅ ተዋጊ አደራጅተውና
  ወጣቶችን አስተረባብረው ገና በዋዜማው
  የፓትርያርኩን መንፈስ ለማደፍረስ
  ቢሞክሩም ገና ስብሰባው ሲጀመር
  በመጠናቀቁ የሁሉም ሕልም እልም
  ብሏል፡፡ ለጥቅምቱም የሲኖዶስ ስብሰባ
  አምላክ ያውቃል፡፡ እስከዚያው ድረስ
  የእግዚአብሔር ቃል ሥራውን ከዚህ
  በበለጠ ይሠራል፡፡ ዘረኞቹ አባ ማቴዎስና
  አባ ቀሌምንጦስም ሌላ ዕቅድ
  መንደፋቸው አይቀርም፡፡ ፓትርትርያኩም
  ለማኅበሩ እኩይ ዓላማና ተግባር ጀርባ
  እየሠጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን አሁን በያዙት
  ሁኔታ መምራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

  ReplyDelete
 5. abbba selamawoch asafariwoch eko nachu.....mekeneyatum weshete tenegerachu ...weshet comment taderegalachu..

  ReplyDelete
 6. መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስብከት በጀመረ በመጨረሻው ዓመት በመቅደስ ተገኝቶ ለሕዝቡና ለደቀመዛሙርቱ ተናገረ፡-ታላቅ ሸክም ማሰር ሰለሚችሉት መሸከም ግን ስለማይወዱት ስለ ጻፎችና ፈሪሳውያን ነበር የተናገረው፡፡

  ለብዙዎች ብዙውን ኀጢአታቸውን በፍቅር የሸፈነው ጌታ ስለ ወንጀለኞች ሲጠየቅ ዝም የሚለው አምላክ ዮሐ.8፥11፣ ሉቃ.7፥47 በቤተ መቅደሱ አደባባይ በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል የእነዚህን ታላላቅ የኦሪት አገልጋዮች በደል መዘርዘር ጀመረ፡፡ ተመክሮ ያልተመለሰን ሰው በአደባባይ ሊወቅሱት ይገባልና ጌታ በቅዱስ ወንጌል እንደተናገረው ቢሰማህ ብቻውን አድርገህ ብቻህን ሆነህ ምከረው ባይሰማህ ካንተ ጋር ሁለት ሆናችሁ ምከረው... እነርሱንም ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት ማቴ.18፥15-17 ብሎ በእግዚአብሔር ጉባኤ ላይም የማይገባ ነገርን አድርገዋልና መገሰጽ ስለሚገባቸው በታላቅ ቃል ገሰጻቸው 1ቆሮ.5፥5 በመጽሐፍ ቃልህ እውነት ነው ተብሎ የተነገረለት መምህር ነውና ዮሐ.17፥17 እነርሱን ከውስጥ እስከ ውጭ ሊገልጹ በሚችሉ የተግሣፅ ቃላት ገሰፃቸው፡፡

  በዘመኑ የነበሩ መምህራን አባቶቻቸው በሠሩት ኀጢአት የተጸጸቱ ለመመሰል አባቶቻቸው የገደሏቸው የነቢያትን መቃብር በኖራ እየለሰኑ ይሠሩና ያሠሩ ነበርና ያንኑ የሠሩትን ልስን መቃብር እየተመለከተ የተለሰነ መቃብር የምትመስሉ ሲል ተናገራቸው ይህ መቃብር ቢከፍቱት ለአፍንጫ የሚከረፋ ለዐይንም የሚከፋ ነገር አይታጣበትም፡፡ ሥጋው ተልከስክሶ አጥንቱ ተከስክሶ፣ እዡ ፈሶ ሲታይ ከውጭ የተለሰነ ውበቱን ያጠፋዋል፡፡ አብረውት እንዳይኖሩ ያስገድዳል በዚህ ረጅም ዕድሜው እንደላዩ ሁሉ ውስጡ አምሮ አያውቅም፡፡ መናፍቅም እንዲሁ ነው መናፍቅም እንዲሁ ነው ባልበላበት ይጮኻል የወንጌል ሰው ለመምሰል ይሞክራል ግን በተግባር የለበትም፡፡ ተመየጢ ተመየጢ ተሃድሶ ቀሳጢ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Asmesay , kelmada. Tenagereh motehal.

   Delete
 7. የማቅ አይ ኤስ ናቸዋ እንኳን አወቅን

  ReplyDelete