Tuesday, June 30, 2015

ስለግብረ ሰዶማዊነት ከአየርላንድ ምን እንማራለን?
                    ምንጭ፡-የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ብሎግ
 
ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች ከግብጽ በወጡ ጊዜ እርሱን በማክበርና በመፍራት እንዲያመልኩት በዓላትን ሰጥቷቸዋል፡፡ ከተሰጡት በዓላት መካከል ደግሞ የፋሲካ ፣ የመከርና የዳስ በዓላት የትኛውም እስራኤላዊ ከሚኖርበት ከስደት ምድሩ በመምጣት በእስራኤል ምድር ተገኝተው እንዲያከብሩ አዟቸዋል፡፡ (ዘጸ.23፥14፥17) በእነዚህ የበዓል ወራት የእስራኤል ጎዳናዎች ሁሉ የሚሸቱት እጅግ የተወደደውን የመንፈሳዊነትን ለዛና ዝማሬ ነው፡፡
     
ከጥቂት ዓመታት በፊት በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ጎራ ክርስትናዋን ከፍላ ጎዳናዎቿን በደም ያጨየቀችው አየርላንድ ፤ አሁን በጎዳናዎቿ የተሰማው ነውር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ ግብረ ሰዶምን በወንጀል ህጓ ጠቅሳ በመከላከልና ለጋብቻ ባላት እሴቷ በአገራችን ካለው ሕግና እሴት ጋር እጅግ የተቀራረበ ነበር፡፡ አየርላንድ በወንጀል ህጓ በግልጥ ግብረ ሰዶምን መከልከል ብቻ ሳይሆን ፈጽመው የተገኙትንም ትቀጣ ነበር፡፡

     ነገር ግን ይህን እውነት ለመገልበጥ ከውጪ ያሉት ዜጎቿ ሁሉ፥ አገር ቤት ካሉት ጋር በአንድነት ተሰባስበው ስለግብረ ሰዶም “መልካምነትና ቅዱስነት” አወጉ ፤ አውግተውም ዝም አላሉም ፤ ጋብቻን  “No”፥ ግብረሰዶምን ደግሞ  “Yes” በማለት ድምጽ ለመስጠትና አብላጫ ድምጽ ያገኘው ሕግ ሆኖ ሊጸድቅና ሊደነግጉት፡፡ መልካም ባህልና ሕግ እያላቸው ይህንን በመናቅ ለአለም ክፉና የስህተት መንገድ መገለጫ ሆነው ታዩና ፥ ግብረ ሰዶምን “Yes” ብለው አጸደቁት፡፡
     መልካሙ የጋብቻ እሴቷና ግብረ ሰዶምን የከለከለው የወንጀል ሕጓ እንደመርገም ጨርቅ ማንም ላይነካው ረከሰ፡፡ የቀደመው ትውልድ “የጠበቀውንና ያስተላለፈውን የጋብቻና ሃይማኖታዊ እሴት” አዲሱና እንግዳው ትውልድ በሚበዛ ቁጥር መረዘው፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ጋብቻ የኋላቀርነትና የአላዋቂነት ድርጊት ተደርጎ ግብረ ሰዶም “ትክክለኛና ለሁሉ እንደተገባ ድርጊት” ተቆጥሮ “ይሁንልን ፤ ወደነዋል” በማለት ጸደቀ፡፡ ይህንን ዜና እንደምሥራች ይሁን ሌላ ምንነቱ ባልታወቀ መንፈስ ቢቢሲና አልጀዚራና ሌሎችም አራግበውታል፡፡

Sunday, June 28, 2015

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያዘጋጀው ሥልጠና መልካምነትና የማቅ ሴራየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች በቅርቡ የሰጡት ስልጠና እጅግ ግሩምና የተሳካ ሲሆን የአሰልጣኞች አቅምና ችሎታ በግልጽ የተለካበት ነበር ብሎ ማመንና መቀበል ይቻላል፡፡ ሁለገብ ዕውቀት ያላቸው ስራ አስኪያጆች ለቦታው እጅግ የሚመጥኑ ሆነው በመገኘታቸው በተሰብሳቢዎች ደስታም አግራሞትም ሐዘንም የተንጸባረቀበት ጊዜ ነበር፡፡ ደስታው በቤተክርስቲያኒቱ እንደዚህ ዓይነት በዕውቀት የተገነቡና ዘመኑን የዋጁ ልጆችን ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲሾሙ ምን ያህል አርቀው እንዳሰቡ በማስተዋላቸው ነው፡፡ ሐዘኑ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከዚህ ቀደም ለቦታው የማይመጥኑና ስንዴን ከገለባ የማይለዩ ዕውቀት የሌላቸውንና ለሀገረ ስብከቱ የማይመጥኑ ለሊቃውንቱም ክብርን የማይሰጡ ይልቁንም ስደትና መከራ ሲያበዙ በነበሩ ሹመኞች የደረሰው ግፍና በደል ሲታሰብ እጅግ ያንገበግባል፡፡ 

እርግጥ ነው ጥቂት ሥራ አስኪያጆች አንድ ሁለት ሊባሉ የሚችሉ እንደ ወርቅ ተፈትነው ያለፉ አልነበሩም እያልን አይደለም፣ ነበሩ፡፡ እያልን ያለነው የአሁኖቹ ሥራ አስኪያጆች በአመራርና በብስለት በእውነት ተዝቆ በማያልቅ እውቀታቸው ያለፈውን ክፍተትና ቁጭት እየሞሉ ነው፣ ለወደፊቱም ይህን መንገድ በማይከተሉት ዘንድ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን የታወቀ ነው፡፡ ምክንያቱም ሊቀ ማእምራን የማነና መጋቤ ብሉይ አእመረ አሁን ቢመደቡም ለወደፊቱ ነዋሪዎች አይደሉምና ከእነርሱ በኋላ ለሚሾሙ ኀላፊዎች ፈተናው ቀላል አይሆንም፡፡ ይህን የተጀመረውን መልካመ ጅምር የሚያስቀጥሉ ካልሆኑና ወደቀደመው ነገር የሚመለሱ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅ ቀውስ ውስጥ መግባቷ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም አሁን እየታየ ያለውን የፍትሐዊ አሰራር ፍሬ የቀመሱ ሁሉ በኋላ በጄ አይሉምና፡፡ 

Thursday, June 25, 2015

የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊ የሆኑት የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ሕንጻ አሰሪ ዕቃ ግዢና ሰንበት ት/ቤት ሊቀመንበር ጥፋታቸውን አመኑበደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በሙስና ቅሌት ምክንያት የተነሳው ውዝግብ ተካሮ ቀጥሏል፡፡ የደብሩ አስተዳደር ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ለሀገረ ስብከቱና ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት ችግሩን በማሳወቅ ጭምር የሄደበት አማራጭ በመጨረሻ ላይ ውጤት እያስገኘለት መጥቷል፡፡ በቀን 12/10/2007 ዓ.ም በወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት፦ የደብሩ አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የህግ ክፍል ተወካዮች፣ የህንጻና ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች የወረዳው የፍትህ ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ እስካሁን ሲያድበሰብሱ የቆዩትን የሙስና ወንጀሎች አምነዋል፡፡ በቅድሚያ የህንጻ አሰሪው ዕቃ ግዢ የሆነው አቶ በለጠ ደሳለኝ (ጉዳ) በራሱ አንደበት ከዚህ ቀደም የዘገብነውን ለደብሩ በስጦታ የተገኘውን ባለአንድ ፎቅ ቤት በ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር መሸጡን አምኗል፡፡ እንዴት ተሸጠ? ለማን ተሸጠ? የሚሉት የህግ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ የሚያገኙ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ስጦታውን ካበረከቱት ወገኖች እጅ ካርታውን የተረከበው እስጢፋኖስ ኃይሉ ነው፡፡ 

ከሀገረ ስብከቱ የተወከሉት አፈ መምህር ይህን ሲሰሙ ከመገረም አልፈው እንዲህ ዓይነቱ ትልቅ ስጦታ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስና ስራ አስኪያጅ ሳያውቁ መሸጥ እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን እንኳን ለእነዚህ አካላት ሊያሳውቁ ከደብሩ አስተዳደር ደብቀው በህገወጥ መንገድ መሸጣቸው አሳዝኗል፡፡ የሚገርመው ይህን አሻጥር የሕንጻ አሰሪው ሊቀመንበር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተገኑ እንዴትና ለማን እንደተሰጠ አላውቅም በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴው ሥእል የማሳሉን ጉዳይም ለሌላ ተግባር ለማዋል አስቦት እንደነበረ ጭምር ተናዟል፡፡

Wednesday, June 24, 2015

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፋሽስት ለተፈጸመባት ግፍና ጭፍጨፋ የኢጣሊያን መንግሥት ካሣ ልትጠይቅ ይገባታል! ክፍል-፩በዲ/ን ኒቆዲሞስ                        (ምንጭ፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

ለኢጣሊያ ምሥራቅ አፍሪካ ጠቅላይ ግዛት
የፕሮቶኮል መዝገብ ቁጥር 9325
አዲስ አበባ ግንቦት 24/1937 ዓ.ም.

ጥብቅ ምስጢር፡- ለጄኔራል ማሌቲ- ደብረ ብርሃን፣
ለክቡር ምክትል ገዥ ኤታማጆር- አዲስ አበባ፣
ለፖለቲካ ጉዳይ ዋና አዛዥ- አዲስ አበባ፣
ለጦር ፍርድ ቤት- አዲስ አበባ፣
ለካራቢኜራዎች ዋና አዛዥ- አዲስ አበባ፡፡
ቁጥር 26609- የደብረ ሊባኖስ ጉዳይ ሙሉ ሓላፊነቱ የእርስዎ እንደሆነ አረጋግጬያለሁ፡፡ የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳትና ዲያቆናት ሁሉም አንድ ሣይቀር በጥይት እንድትፈጇቸው አዝዣለሁ፡፡ ትእዛዝህን በአስቸኳአስፈጽሜያለሁ በሚል ቃል እንድታረጋግጥልኝ ይሁን!
ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒ፡፡
ለዚህ ለዛሬው ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ ሁለት ዐበይት ምክንያቶች ናቸው፡፡ የመጀመሪያው በዚህ ዓመት በአሜሪካዊው ምሁር በፕ/ር ኢያን ካምፔል ‹‹The Massacre at Debre Libanos Ethiopia 1937:- The Story of One of Fascism’s Most Shocking Atrocities›› በሚል ርእስ የተጻፈው መጽሐፍ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የኒው ዮርክ ታይምስ ከሁለት ሳምንት በፊት የአርመን ኦርቶዶክስ ቤ/ን ከመቶ ዓመት በፊት ቱርካውያን በአርመን ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲናት ላይ ላደረሱት ግፍና መከራ የአርመን ቤ/ን መሪና መንፈሳዊ አባት የሆኑት አቡነ አራህም I የቱርክ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል የጠየቁበትና ያሳሰቡበት ሰበር ዜና ነው፡፡
 ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ሰፊ ምርምርና ጥናት በማድረግ የሚታወቁት አሜሪካዊው ምሁር ፕ/ር ኢያን ካምፔል የፋሽስት መንግሥት በኢትዮጵያ ቤ/ን በተለይም ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳትና አገልጋዮች ላይ ያደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋና እልቂት፣ መከራና ሥቃይ በተመለከተ የሚተርከውን መጽሐፍ በቁጭትና በኀዘን ውስጥ ሆኜ ነው ሳነብ የነበርኩት፡፡ 

Saturday, June 20, 2015

የሦስት ሰዎች ጉዳይሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ እየተመራ የሰውን ዘር በሦስት ከፍሎታል።
1. ፍጥረታዊ ሰው 2. ሥጋዊ ሰው 3. መንፈሳዊ ሰው
"ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል‚ 1ቆሮ 2፥14-15። "ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን?‚ 1ቆሮ 3፥3።
ይህ ልዩነት የመጣው በመንፈስ ቅዱስ ምክንያት ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ ነው "ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው‚ ይላል 1ቆሮ 2፥10። ስለዚህ ሰዎች በሦስት የሚመደቡት "የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገሮች‚ ለመረዳትና ለመቀበል ባላቸው ችሎታ ነው።ወደ እነዚህ "የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች‚ ደግሞ ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መግባት አይቻልም። "ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም‚ ቁ 11 እንደተባለ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሲኖር የእግዚአብሔርን ነገር ማወቅ ይቻላል። "እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም‚ ይላል ቁ 12። ስለዚህ ክርስቶስን ያወቅነው ስለተማርን ወይም ልዩ የጭንቅላት ችሎታ ስላለን ሳይሆን እንዲያው ስለተሰጠን ነው።
1 ፍጥረታዊ ሰው
"ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም‚1 ቆሮ 2፥14።
በዚህ ክፍለ ንባብ ፍጥረታዊ ሰው ሊያውቅ ባለመቻሉ አልተወቀሰም። ጥቅሱ በቀላልና በግልጥ ቋንቋ የዚህን ሰው ውስንነት ያመለክትና በመቀጠል የውስንነቱን ምክንያት ያስረዳል። መገለጥ የሚመጥው ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተመለከትን። "ፍጥረታዊ ሰው ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ አልተቀበለምና‚ የተገለጡትን ነገሮች መረዳት አይችልም። እርሱ የተቀበለው "በእርሱ ውስጥ ያለን የሰውን መንፈስ‚ ብቻ ነው። ምንም እንኳ "በሰው ጥበብ‚ ምክንያት ቃላቱን ማንበብ ቢችል፥ መንፈሳዊ ትርጉማቸውን ግን ሊረዳ አይችልም። ለዚህ ሰው መገለጥ የሚባለው ነገር ሞኝነት ነው። "ሊቀበለው‚ ወይም "ሊያውቀው‚ አይችልም።

Thursday, June 18, 2015

የመጽሐፍ ቅዱስና የመልክአ ሚካኤል አለመግባባትመጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አሳሳቢነት በቅዱሳን አባቶች የተጻፉ የእግዚአብሔር መልእክትናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታቀፉ እና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የሃይማኖትማስተማሪያ ሆነው የኖሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድሳ ስድስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት መመሪያዎችግን ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ናቸው። የአንድ ሰው ሃይማኖቱ ትክክለኛነት ተመዝኖ ሊወገዝምሆነ ሊመሰገን የሚችለው በነዚህ መጻሕፍት መሠረት ነው። ነገር ግን በአሁኑ ዘመን በቤተክርስቲያናችን በቀኖና የማይታወቁና  ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ውጭ የሆኑ መጻሕፍት በቤተክርስቲያናችን ስም ወደ ሕዝብና አገልጋዮች ሾልከው ገብተው ቦታውን በመቆጣጠር፣ በአገሪቱመጽሐፍ ቅዱስ የሌለ እስኪመስል ድረስ ውሸታቸውን አጋነው በማቅረብ አገሪቱን በክለዋል።


መልክዐ ሚካኤል የሚባለው ድርሰት በአጼ ዘራአ ያዕቆብ ዘመን እንደተደርሰ ይገመታል፣መጽሐፉ በየወሩ የሚካኤል ማህሌት በሚቆሙ የቤተ ክርስቲያችን ተቀጣሪዎች በየተራበቅብብሎሽ እየተዜመ ሚካኤል የሚመለክበት፣ የሚመሰገንበት ድርሰት ነው። ይህን መጽሐፍሁልጊዜ በመድገም ወደ ሚካኤል የሚጸልዩ ምእመናንና ደብተራዎች በርካታ ናቸው።የሚካኤል በአል ሲሆን ካህናቱ ሌሊቱን ሙሉ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ ዚቅ የሚባለውን ሌላድርሰት ጨምረውበት ሲዘሉበት የሚያድሩት ይህን ድርሰት ነው። ምእመናን ግን ይህን በቤተክርስቲያን እና በእግዚብሔር ላይ ሲካሔድ የሚያድረውን አመጽ ስለማያውቁ ካህናቱ ረጅምሌሊት ሲጸልዩ በማደራቸው ይደክማቸዋልና ምርጥ ምርጡን፥ ቁርጥ ቁርጡን እንጋብዛቸውበረከታቸውን እንካፈል እያሉ ይሽቀዳደማሉ። በነገው ዕለት በሚከበረው የህዳር ሚካኤል ወደአንዱ ቤተ ክርስቲያን ጎራ በማለት ይህን ድርሰት ማዳመጥ የሚቻል መሆኑን ሳንጠቁምአናልፍም። ነገር ግን በግዕዝ ብቻ ስለሚባል እግዚብሔር እና እነሱ ብቻ ናቸው የሚሰሙትናላይገባችሁ ይችላል። ለሁሉም በመልክአ ሚካኤል እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ያለውንአለመግባባት እንዲህ አቅርበነዋል።


ከመልካ ሚካኤል፦


ሰላም ላአእዛኒከ እለ ያጸምአ ንባበ፣
ወጸሎተ ኩሉ ዘተመንደበ፣
ሚካኤል አቅልል እምላእሌየ እጸበ፣
ከመ ትመአድኒ ውትምህረኒ ጥበበ፣
ረስየኒ ወልደ ርሰይኩከ አበ፤

ትርጉሙ፦

ለጆሮዎችህ ሰላምታ አቀርቫለሁ፤
የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልመናን ያዳምጣሉ፣
ሚካኤል ሆይ ችግሬን አቅልልኝ፣
ምከረኝ እውቀትንም አስተምረኝ፤
አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ፤

ይህ ለሚካኤል የቀረበ ጸሎት እና ምልጃ ቤተ ክርስቲያናችን በተቀበልችው ሰማኒያ አንድመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም ወይንም ይህን ሐሳብ የሚደግፍ ንባብ የለም። ቅዱሳንአባቶቻችን ጸሎታቸውን ያቀረቡት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላእክት አልነበረም። ወደመላእክት ጸሎት ያቀረበ የእግዚአብሔር ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም። የኛደብተራዎች ግን ሚካኤልን እናነግሳለን በሚል ፈሊጥ እግዚአብሔርን ሲያስቀኑ እያደሩየእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊመስሉ ይሞክራሉ። ሚካኤል የእግዚአብሔር ክቡር መልአክአገልጋይና ተላላኪ የመላእክት አለቃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ይህን ማንምአይክድም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማና ጸሎትም ወደ እርሱ መቅረብ እንዳለበት የሚናገርክፍል ፈጽሞ የለም። ደብተራዎች ለሚካኤል የሰጡትን ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማንእንደተሰጠ እንመልከት፤

መጽሐፍ ቅዱስ፦

«ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» መዝ 65፥2 እግዚብሔር በዓለምምሉዕ በመሆኑ የሥጋን ሁሉ ጸሎት መስማት ይችላል። ቁራዎች እንኳ ወደ እግዚአብሔር ከጮኹ ያገሬ ሰዎች ምን ነካቸውና ነው ወደ ሌላ የሚጮኹት? ወይስ ያክብሮት ጩኸት ነው?

ታዲያ መነፍቃን ደብተራዎች «የተቸገረን ሁሉ ጸሎት የምትሰማ» በማለት ለሚካኤል የሰጡትከምን አምጥተውት ነው? ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን ሕዝብ በዚህ ክህደት እንዲተባበርየሚደረገውስ ለምንድን ነው? «ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» ሲልየኢትዮጵያን ሕዝብ አይጨምርምን? ሥጋ ሁሉ ካለ ኃጥአንም ሆኑ ጻድቃን ወደ እግዚአብሔርመጸለይ እንዳለባቸው የሚናገር አይደለምን? እንስሳት እንኳ ወደ ማን ማንጋጠጥእንዳለባቸው የሚያውቁ መሆኑን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል።

«እጓለ አንብስት ይጥህሩ ወይመስጡ ወይስእሉ ኀበ እግዚአብሔር ሲሳዮሙ»

«የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮሃሉ፣ ምግባቸውንም ከእግዚአብሔር ይለምናሉ» መዝ103፥21።

«ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጭቶች ለእንስሳትም ምግባቸውን ይሰጣል» መዝ 147፥9