Monday, June 1, 2015

መፈንቅለ ፓትርያርክ እንዲያደርጉ የታዘዙ የሚመስሉት የሰንበት ተማሪዎች በመናጆነት እስከ መቼ ይቀጥላሉ?

 Read in pdf

በቀሲስ በላይ ዘመነ ስራ አስኪያጅነት በሙስና በተዘፈቀበት ጊዜ ድምፃቸው ያልተሰማውና አሁን በለውጥ ጎዳና ላይ እየተጓዘ የሚገኘውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንቅስቃሴን ለመግታት ውስጥ ለውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው ማቅ ከፊት ለፊት የሚያጋፍጣቸውንና የሚዋጋባቸውን በየራሳቸው ሰንበት ት/ቤት ውስጥ ድክመታቸውን ማየትና ለመፍትሄው መወያየት የተሳናቸውን የሰንበት ተማሪዎችን ይዞ ትግሉን ቀጥሏል፡፡  ማቅ ለአዲስ አበባ የሰ/ት/ቤት አንድነት ሊቀ መንበር ለግቢ ገብርኤሉ “መበለት” አቶ ሄኖክ አስራት፣ አቶ ሄኖክ አስራት ደግሞ ለየአጥቢያው ሰ/ት/ቤት ሊቃነ መናብርት ያወረደው የሁከት እስትራቴጂው ዳዴ እያለ ፓትርያርኩን ለማወክ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ እያየን ነው፡፡

የማቅ ብሎግ ሐራም ይህን እቅድ እንዲህ በማለት አስነብባናለች፦ “የፓትርያርኩን ዳተኝነት በማጋለጥ ፍትህን የሚጠይቁ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዳሉ፡፡” ቅዱስ ፓትርያርኩን እረፍት ለመንሳት እየሞከረ ያለው ማቅ እቅዱን በየአጥቢያው ወዳሉ ሰ/ት/ቤቶች አባላት በማውረድ ከ3 ዓመት በፊት ያቀደውን እቅድ ይፋ እያደረገ ያለ ይመሳላል፡፡ ከዚህ የጥምቀት ተመላሾች ህብረትን ለተሳሳተ ዓላማ ሊጠቀምበት ሲል  ቋሚ ሲኖዶሱ በወሰደው ፈጣን እርምጃ ከተበተነ በኋላ፣ ሰልቱን ወደ ተራ ሰንበት ተማሪ አባላት በማውረድ ለረብሻ፣ ለአደባባይ ላይ ነውጥ በመናጆነት የፈረደበትን “ተሐድሶ መጣብህ” የሚለውን ማስፈራሪያ እየተጠቀመ ይገኛል፡፡

የእያንዳንዱ  አጥቢያ ሰንበት ተማሪ የትኛው አባል ነው በቂ እውቀት ያለው? የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ገልጦ ኦሪት ዘፍጥረትን የሚፈልግ ወጣት የተከማቸበት አይደለም እንዴ? ከበሮ ከመደለቅ ለጥምቀትና ለመስቀል መዝሙር ከማጥናት የዘለለ አላማ ስለሌላቸው እኮ ነው ማቅ መናጆ እያደረጋቸው ያለው! ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ቢያውቁ ኖሮማ ማቅ አይነዳቸውም ራሳቸውንም ችለው ይቆሙ ነበር፡፡ ስላልሆነ ግን ጥያቄያቸውን በቃለ አዋዲው መሠረት ማቅረብ ሲገባቸው አባ ቀሌምንጦስ በሚያመቻቹላቸው የአመፅ መንገድ ህገወጥ በሆነ አካሄድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

የማህበረ ቅዱሳንን ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካዊ ትግል ለመታገል ሳያውቅ የተሰለፈውና አንድን ፓትርያርክ ስራቸውን እቅዳቸውን ሹመታቸውን የሚቃወም ሰንበት ተማሪ እውነት ሃይማኖታዊ አላማ አለው ማለት ይቻላል? አሁን አሁንማ ድምፁ የማይሰማው ማደራጃ መምሪያው በጥብቅ ሊፈተሽ ይገባል፡፡ ማቅ የሚችለውን ያህል ብዙ ጥይት ተኩሶ ጥይቱን ወደመጨረሱ ስለተቃረበ ወጣቶችን እንደ መጨረሻ ጥይት እየተኮሰ ይገኛል፡፡
እነዚህን ምንም የማያውቁትና ማቅ ከኋላዬ አስልፍበታለሁ ብሎ እንደማንቂያ ደወል ዘወትር የሚጠቀምበትን “ተሐድሶ መጣብህ” ስልት አሁንም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ እንዲህ ተብለው የተቀሰቀሱት ወጣቶች በአብዛኛው ትምህርት ያቋረጡ፣ መሄጃ ያጡ፣ የሰንበት ት/ቤት ሳንቲም የለመዱ፣ ከደጀ ሰላም የማይጠፉ፣ የዘወትር ውሏቸው እዚያው የሆነ ወጣቶች ሲሆኑ ለአደባባይ ነውጥ ሳይጠቀምባቸውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ገጽታ በማይመለከታቸው ጉዳይ ለማደብዘዝ ዳር ዳር የሚሉትን፣ የደብር አለቆች በቅርብ ሊቆጣጠራቸው ይገባል፡፡ አባ ማቴዎስና አባ ቀሌምንጦስም በተልእኮ የሚንቀሳቀሱለትና የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የዘወትር ህልሙ አድርጎ ባለ በሌለ ሃይሉ እየተንቀሳቀሰ ያለው ማቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትከሻ ላይ ሆኖ ሃይማኖትን ተተግኖ እየተንቀሳቀሰበት ያለውን ፖለቲካዊ ትግል እንደ ፓርቲ ተመዝግቦና ፖለቲካዊ ሰውነቱ ታውቆለት ፈቃድ አውጥቶ ቢንቀሳቀስ የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡
 
ለመናጆነት የሚጠቀምባቸው የአጥቢያ ሰ/ት/ቤት ወጣቶችንም ማኅበሩ የብዙ ባለሙያ ስብስብ ነኝ ስለሚለን የሥራ ፈጠራ፣ የሙያ ክህሎት የሥራ እድል ቢፈጥርላቸው የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ እንዲህ ካደረገ ግን መናጆነታቸው ስለሚቀር እንዲህ እንዲሆኑ አይፈልግም፡፡ተረትን የመተረት ካልሆነ በቀር አቅም የለውም እንጂ ቢኖረው ኖሮ መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት  ቢነግራቸውና ከአእምሯቸው ያስወጣውን የጌታን የማዳን ሥራ  ብቻ በልባቸው ቢስልላቸው በየጊዜው ለመልካም ነገር እንደ ችግኝ ይፈሉ ነበር፡፡ እባካችሁ እናንተ የሠንበት ተማሪዎች “የሚያደርስህን ቦታ ሳታውቅ ጉዞ አትጀምር” የሚል ብሂል አለና ወዴት እየሄዳችሁ እንደሆነ አስቡበት፡፡ ገብቶኝ ነው ወይ? ወይስ ወግና ልማድ ልጠርቅ ነው የሰ/ት/ቤት አባል የሆንኩት ልትሉም ይገባል፡፡ ለሁሉም ግን ራሳችሁን ችላችሁ ቁሙ መናጆነታችሁ ያብቃ፡፡

6 comments:

 1. ፍቅረማርያም አበራJune 2, 2015 at 5:44 AM

  ስለ ሄኖክ አስራት!

  የጌታን የማዳን ሥራ እያላችሁ የወንጌሉን ቃል ማንሸዋረሩን እዚያው በአዳራሻችሁ አድርጉት፡፡በአንድ ድንጋይ 2 ወፍ ለመምታት አትሞክሩ፡፡መቼም በዚህ በኩል ከእናንተ ጎን መቆም ክሕደት ብቻ ሳይሆን ውለታ ቢስ መሆንም ነው፡፡በራዥ-ከላሽ መንገዳችሁን መከተል የሚሆን አይደለም፡፡የእናንተ የ‹‹ወንጌል ከኛ በላይ ላሳር›› ጎዳና እነ ፓ/ር ተከስተን፣እነ ፓ/ር ዳዊትን፣እነ አሸናፊ መኮነንን የት እንዳደረሳቸው አይተናል፡፡እጃችሁን ወደላይ-ወደላይ፣ከፍ-ከፍ፣ጌትዬ-ጌታዬ፣ድኜ-ጸድቄያለሁ፣ንጹኃን-ቅዱሳን ነን፣ጌታ ቀብቶናል-ሾሞናል…..የሚል ከሥርዓት ያፈነገጠ መደዴ ጎዳና ገና ከጅምሩ እንዴት እያቀባዠራችሁ እንደሆነ ታውቁታላችሁ፡፡ጊዜ ሲኖራችሁ ስለ ሰ/ት/ቤቶች የእውቀት ደረጃ ራሳችሁን ዳኝነት ከማስቀመጥ ስለዚህና ስለመሳሰሉት ፕሮቴስታንታዊ ቅዠቶችም ጻፉ፡፡


  ወደተነሳው ነጥብ ስመለስ ግን መጀመሪያ ነገር ሄኖክ አስራት የግቢ መንበረ - መንግሥት ቅ/ገብርኤል ሳይሆን የታዕካ - ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ሰ/ተማሪ የነበረ ነው፡፡ልጁ ፈጣን፣ለቤተክርስቲያንና ለተዋሕዶ ሃይማኖቱ ቀናኢ መሆኑ አይካድም፡፡


  የዚያኑ ያህል ያደገበት ገዳም በሊቃውንት መፍለቂያነት ታዋቂ ሆኖ ሳለ እሱ ግን ጥልቅ እውቀት የሚጎድለው(ምንም የአብነት ትምህርት አልተማረም)፣ከእሱ በላይ ሰው ያለ የማይመስለው፣እጅግ የቡደንተኝነት መንፈስ የተጸናወተው፣በቀላሉ የአድማ መሳሪያ መሆን የሚችል፣በሥራ ሳይሆን በአድማ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም የሚተጋ፣በሰ/ተማሪነቱ ወቅት የሰ/ት/ቤቱን መብት በጉልበት ለማስከበር አካላዊ ጥቃትንና ማስፈራሪያዎችን ሳይቀር በቢሮ ሰራተኞች ላይ የሚሰነዝር፣ለካሕናት ከፍተኛ ንቀት ያለውና አገልግሎታቸውን እንደኋላቀር የሚመለከት፣ሲበዛ እልኽኛ፣አልኩ-ባይነት የሚያጠቃው፣አለሁ-አለሁ የሚወድ፣ታዳጊዎችን በቀላሉ ለእኩይ ዐላማ ሰብኮ ማሰለፍ የሚችል፣ባስፈለገ ጊዜ ደግሞ የአዞ እንባ እያነባ ብፁዐን አባቶችን ለማሳመን የሚጥር፣ሲበዛ ደፋርና ዐይነደረቅ፣አሉባልታና ቡድንተኝነት ባለበት ሁሉ ቀድሞ የሚገኝ፣ከሁሉም በላይ ግለሰባዊ የአመራርና የአሰራር እንዲሁም የተግባቦት ችግሮቹን በቀላሉ ወደ በላይ አመራሮች በማላከክ የራሱን ሁለንተናዊ ድክመትና እርባና ቢስ የአመራር ሪከርድ ማድፈንፈን የሚችል 40ዎቹን የተሻገረ የሰ/ት/ቤት ወመሽ አመራር ነው--ሄኖክ አስራት!!ስለዚህ እንኳን እንዲህ እንደፈለጉት የሚነዳ ትውልድ ተገኝቶና ቤንዚን የሚያርከፈክፍ እንደ ሐራ አይነት ብሎግ አይዞህ ብሎት ልጁ እንዲያውም እንዲያው ነው፡፡ሁከት ስጦታው ነው፡፡ጥርሱን የነቀለበት፡፡6 ወር ድሮ በሕጻናት ክፍል ኮርስ ወሰደ፡፡ቀሪ እድሜውን ከራሱ የሚፈልቀውን ክፋት በአካባቢው ከሚገኙ ካሕናት ክፋት ጋር እያዛመደ ተሞክሮውን በማስፋት አሁን ላይ ፓትርያርክ ከነወንበሩ፣መንግሥትን ከነዙፋኑ የሚነቀንቅ ምርጥ የአቧሬ ነጠላ ለባሽ ወንበዴ ወጥቶታል፡፡
  የምትቀርቡት ብትመክሩት ጥሩ ነው፡፡ከተሳሰተና እድሜውን ከፈጀበት የአድማ እና ብዙም ያልተሸፋፈነ ዘረኝነተ ራሱን ያላቅቅ፡፡ወደ ቀልቡ ይመለስ፡፡ካለበለዚያ ለራሱም ለሰ/ት/ቤቶች አንድነትም ጉዳት የሚያመጣ ይሆናል፡፡እየሄደበት ያለው ጎዳና ኦርቶዶክሳዊም፣ሥነምግባራዊም፣ሕጋዊም አይደለም፡፡


  ይሕ አስተያየት ሐራ ተዋሕዶ በተባለው ብሎግ እንዲወጣ ነበር ምኞታችን፡፡ይሑንና ብሎጉ የሄኖክ አስራትን ሥም የሚያነሱ አስተያየቶችን ልከን ለማውጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑና ከዚያ ይልቅ የፓትርያርኩን ሥም የሚያጠለሹ አስተያየቶችን ሲያወጣ ሀፍረት የማይሰማው ሆኖ በማግኘታችን እጅግ በማንወደውና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ከሚፈታተኑ ሚዲያዎች አንዱ መሆኑን በደንብ የምናውቀውን አባ ሰላማ ብሎግ ለመጠቀም ተገድደናል፡፡ፍትሐዊ፣ነጻና የማይወግን ሚዲያ በማጣታችን የተነሳ ያልሆነ ሚዲያ በመጠቀማችን የቤተክርስቲያን አምላክ ይቅር እንዲለን እንለምናለን፡፡

  ReplyDelete
 2. ዋአአአአ! መንቀዥቀዥ እንጃ ፈራሁ! ይኸ አጉል አወቅሁ አወቅሁ አለሁ ማለት በኋላ ለትውልድ የሚተርፍ ከባድ እርግማን እንዳያመጣ። ሰው እንኳን በዚህ ክብር ላይ ያለን ሰው እንዳው የእድሜ ባለፀጋ እኮ ይከበራል! በእድሜው ብዙ ያካበተው እውቀት ይኖራል። ከኛ በተሻለ ያውቃል ተብሎም ይከበራል እኮ። ለማንኛውም እውነተኛው ዳኛ አለ በዙፋኑ። ሁሉንም ወደፊት እናያለን። የነገስታት፣ የመኳንንት፣ የመሳፍንት አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው።

  ReplyDelete
 3. ፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ አቋም መግለጫ የተባለው ላይ የሚከተሉት ነጥቦች በጣም አስገርመውኛል፡፡

  እውነት በርግጥ ይኽ የጉባኤው አቋም መግለጫ ከሆነ የተሰበሰቡት በርግጠኛነት መንፈሳውያን የሰንበት ተማሪዎች አይደሉም፡፡ ለምን በሉኝ በደንብ ተመልከቷቸው፡፡ እኔ በተራ ቁጥር ሦስት ላይ ያለውን ነጥብ ለአሁኑ አቀርባለሁ፣ ከዚያ ደግሞ በሌሎቹ ላይ በተከታታ አቀርባለው የሚያስተናግድ ከተገኘ

  3. መልክአ ምድርን መሠረት ያደረገ የሰንበት ት/ቤቶች ትስስር በማጠናከር ሰንበት ት/ቤቶች ባልተቋቋሙባቸው አጥቢያዎች እንዲቋቋሙ፣ በተቋቋሙባቸው ደግሞ የተጠናከረ አገልግሎት እንዲሰጥባቸው ለማድረግ እንሠራለን፤

  ቤተ ክርስቲያን መልክዓ ምድር ይሁን ምን የራስዋ የሆነ የአህጉረ ስብክ አወቃር አላት፣ ይህ የአቋም መግለጫ በቀጥታ በቤተ ክርስቲያኒቱ አደረጃጀት ላይ ከፍተኛ የሆነ መፋለስ ሚያደርስ ነው፡፡ ከዚያም ደግሞ ሀገራችን አሁን የምትከተለው የክልል አከፋፈል መልክዓ ምድርን የተመረጎዘ ሳይሆን ባህልን፣ ቋንቋንና የሕዝብ አሰፋፈርን የተከተለ ነው፣ መልክዓ ምድር የሚለው ምኒልክ መሬቱን እንጅ ሕዝቡን አንፈልግም ያለውን አስተሳሰብ የሚያራምዱ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አቋም ነው፡፡ ለማለት የፈለግሁት ይህ የመንፈሳውያን አስተሳሰብ አይደለም በተለይም የሰንበት ተማሪዎች፣ ይህ ንጹሕ ፖለቲካ ነው እንደውም የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አቃም፡፡ ቤተ ክረስቲያን ስለ መልክዓ ምድር ሳይሆን ማለትም ስለ ወንዝ፣ ተራራ አሰፋፈር ሳይሆን ሕዝብን በቋንቋውና ባለበት ሁኔታ ስለማስተዳደር ነው የምታስበው አሁኖቹ የሰንበት ትምርት ቤት አሰተሳሰብ ማይወክለው አቋም መግለጫ ስለ መልክዓ ምድር ያስባል የማነው ትሉኝ እንደሂነ አሁንም እነዚያው የመዥገሮቹ፣ እየከፋፈሉ አዳዲስ ሀሳብ እያመጡ አባቶችን የሚያውኩት ቡድኖች ሐሳብ ነው፡፡ ነቃ በሉ

  4. የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ችግሮችን ለማጋለጥ ያስችል ዘንድ ከሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሚደርስ መረጃ የማሰባሰብ ሥርዐት በመዘርጋት የመረጃ ማሰባሰቡን አጠናክረን እንሠራለን፤

  5. በአኹኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አፈጻጸም ላይ ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንን እንቅሰቃሴ ለማስቆም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲያን አካላት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፤

  6. ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስለ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን የቀረበው ማስረጃ ውሳኔ እንዲሰጠው፤ ውሳኔውም ተግባራዊ ይኾን ዘንድ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፤

  8. ከዚኽ ጋር ተያይዞ የመንግሥት የፍትሕ አካላትም ከአጥፊዎች ጋር በመተባበር የሰንበት ት/ቤት አባላትን ከማሰር እና ከማንገላታት እንዲታቀቡ ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን፤

  9. በቃለ ዐዋዲው እና በ1986 ዓ.ም. ሕገ ደንቡ ላይ የተጠቀሰው የሰንበት ት/ቤቶች የዕድሜ ገደብ እንዲነሣልን በድጋሜ እንጠይቃለን፤

  11. የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የቤተ ክርስቲያንን አቅም የሚያዳክሙ አማሳኞች ማስረጃ ተጠናቅሮ በአገሪቱ ሕግ መሠረት እንዲጠየቁልን እንጠይቃለን፤

  12. የቤተ ክርስቲያን የፋይናንስ አሠራር ማእከላዊ እንዲኾን እና በባለሞያዎች የሚታገዝ የክትትል እና የቁጥጥር ሥርዐት እንዲኖረው እንጠይቃለን፤

  13. በአኹኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ስም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል ትምህርት እና መልእክት የሚያስተላልፉ የቴሌቪዥን መርሐ ግብሮች በተቻለ ፍጥነት እንዲዘጉ አልያም በቤተ ክርስቲያን ስም ከመጠራት እና ከመጠቀም እንዲከለከሉ እንጠይቃለን፤

  18. የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ያቀረበው ጥያቄ የኹላችንም አቋም ስለኾነ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠው እንጠይቃለን፡፡

  Gebreweld, from 4-kilo

  ReplyDelete
 4. ፍቅረ ክፋት አበራ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍቅረማርያም አበራJune 4, 2015 at 10:52 PM

   ዳ…ሞት

   Delete
 5. እጅግ ይገርማል
  ለመሆኑ ሙሰኛ አማሳኝ የሚሉት ማቅ ሃያ ዓመት ሙሉ ያለደረሰኝ ቤተ ክርስቲያንን ሲዘርፍ የት ነበሩ
  ማቅ በብልሹ አሰራር ቤተ ክርስቲያን ያለመዋቅር ሲያምስ የት ነበሩ
  ማቅ አሁንም ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው ከ300 በላይ ቅጥረኛ ሲያስተዳድር ት ናቸው፣ ማቅ ሀገረ ስብከት ነው፣ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው ወይስ ምንድን ነው
  ለመሆኑ የማቅ አባላት አልባሌ ስብከት፣ አልባሌ መጽፍ ሲያወጡ የት ነበሩ ሆድ ይፍጀው እን ባሰ ነገር ሲመጣ ይጣል ተብሎ ነውእንጅ ስንት ኑፋቄ ያለው ማቅ ውስጥ መሆኑን ረሱት
  ገብረ ወልድ ጥሩ እይታ ነው የአቋም መግለጫው ምንም መንፈሳዊ ሽታ የለውም
  የሰንበት ተማሪዎቹ ሳይሆን የወሮበሎቹ ነው፡

  ReplyDelete