Tuesday, June 16, 2015

የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግስት ዘመን ደብተራዎችና ፈጠራዎቻቸው

Read in PDF

ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ [1000 . ገዳማ]ደርግ እስከ መጣበት ድረስ በኢትዮጵያ ሲገዛ የኖረ መንግሥት ነው። መሠረቱአክሱም ሆኖ እስከ ዛጉዬ ሥርወ መንግሥት [ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመንድረስበአክሱሞች ተይዞ ቆይቷል። የላስታ መንግሥት ዛጉዬ በመባል ይታወቃል "ዘአጕየየመንግስተ አክሱምለማለት ነው። ከዘጠነኛው እስከ አሥራ ሦስተኛው መቶ ክፍለዘመን ገዝቶ አስደናቂ ቅርሶችን አስቀምጦ አልፏል።
 የዛጕየ ዘመነ መንግሥት ማክተም ምክንያቱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መሆናቸውታውቋል። ገድለ ተክለ ሃይማኖት እንደሚለው ላስታዎች መንግሥት አይገባቸውምነበር። ምክንያቱን ሲያቀርብ "የሰሎሞን ዘር ስላልሆኑይላል። ስለዚህ መንግሥትወደ ሰሎሎሞን ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ሲዛወር ክህነትም የአሮን ዘር ወደ ሆኑትወደ ተክለ ሃይማኖት ተዛወረ፣ ከተክለ ሃይማኖት ዘር ውጭ ጳጳስ ወይም እጨጌመሾም እርግማን ነው በማለት ገድላቸው ይደመድማል። ሃይማኖት የፖለቲካ መሳሪያመሆን የጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። አቡነ ተክለ ሃይማኖት "የሰሎሞን ሥርወመንግሥት ወደ ትክክለኛው ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ መመለስ አለበትእያሉሲሰብኩ ኖረው በመጨረሻ ስብከቱ አላዋጣ ሲል የላስታው ንጉሥ በጦር እንዲገደልቀጥተኛ ትዛዝ መስጠታቸውን ገድላቸው ይናገራል።[ገድለ ተክለ ሃይማኖት 241-5 እና  26 ያንቡ]

     የላስታው ንጉሥ ይትባረክ በይኩኖ አምላክ ሲገደል ወሎ ውስጥ ከላስታአንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው "ድግር መጥረቢያላይ የበርካታሰዎች እግር መቆረጡን በአካባቢው ታሪክ ሆኖ ይነገራል። አገሩ "ድግር መጥረቢያ"የተባለበት ምክንያት እግር የተቆረጠበት ቦታ በመሆኑ ነው ይባላል። ይህ ጉዳትያገኛቸው ሰዎች ግን ያች እግር የተቆረጠው "በጸሎት ብዛትመሆኑን ይተረካሉ።ነገሩ የፖለቲካ ጨዋታ ስለሆነ ማለባበስ የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው እንዲህየተባለው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ።
 ሃይማኖትን የፖለቲካ መሳሪያ ማድረግ እንደሚቻል ከአቡነ ተክለ ሃይማኖትየተማሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በአሜሪካ ቁጭ ብለው ደርግን በኢሕዴግሲያስወጉ እንደነበር ይተረክላቸዋል። እርሳቸው ግን አሜሪካ ስለነበሩ እግራቸውበመጥረቢያ ከመቆረጥ ተርፏል። ስለዚህ ስድስት ክንፍ ማውጣት አያስፈልጋቸውምመብረር ከፈለጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከራያቸው በራሪ አካላት አሉ።
    ስድት ክንፍ የወጣላቸው ሰው እግር ስለሌላቸው ነው ተብሏል እናምበክንፋቸው በረው ሄደው 24 ካህናተ ሰማይ ላይ ተደረብው 25 ካህን ሆነውእስከ ዛሬ ድረስ የጌታን መንበር እያጠኑ ነው ተብሏል። አንድ ቀን ሰውየው ክንፍያወጡት በሥጋቸው ነው ወይስ በነፍሳቸው ብዬ ጠይቄ ነበር። በነፍሳቸው ነውተባልሁ። ታዲያ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ነው ክንፉ የበቀለው ብሎ ገድላቸው ለምንይናገራልስላቸው አይ ይቅርታ በሥጋቸው ነው አሉኝ። በሥጋቸው ከሆነ በደብረሊባኖስ ከሚገኘው አጥንታቸው ላይ ክንፋቸውንም አብረን ልናገኘው እንችላለንስላቸው ክንፋቸው ተሰውሯል ብለውኝ አረፉት። ተሠውሯልከሰማይ ወረደየተባለው መስቀልስ እንዴት ነው ስላቸው አዎ ለክብራቸው ነው አሉኝ  ሌላውእውነተኛው አባት ግን ልጄ እንግሊዛዊቷ ንግስት ለአጼ ምኒልክ ባለቤት የሸለሟቸውስጦታ ነው ብለው እውነቱን ነገሩኝ። አዳዲስ ውሸቶች በጥንቱ ውሸት ላይእየተጨመሩ አስቸግረውናል ብለውም አከሉልኝ እኔ ግን የፖለቲካ ጉዳይ ነውእላለሁ።
    መለስና ይኩኖ አምላክ፤ አቡነ ጳውሎስና አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ነጉሥይትባረክና መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ይመሳሰሉብኛል። ይኩኖ አምላክ ተክለሃይማኖት ለዋሉት ውለታ ሲሶ መንግሥት የሰጣቸው ሲሆን፤ መለስም ለአቡነጳውሎስ ይኸው ፕትርክናውን ከአቡነ መርቆርዮስ ቀምቶ አጎናጽፏቸው ይገኛል።ክህነት ከአሮን ዘር ወጣ ማለት ነው? ይትባረክ ድግር መጥረቢያ ላይ፤ መንግሥቱኃይለ ማርያም ዝምባዌ ላይ ወድቀው ቀሩ። ሃይማኖት እስከ አሁን ድረስ የፖለቲካጨዋታውን ሞቅ ሞቅ አርጎታል።  ማህበረ ቅዱሳንም ከዚህ ታሪክ በመኮረጅእየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ፍጻሜውን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል። እያንዳዱን የጨዋታዓይነት ወደ ፊት እመለስበታለሁ። ዛሬ ላሳያችሁ የምፈልገው የሰሎሞናዊው ሥርወመንግሥት ደብተራዎች የፈጠሩትን እና የቤተ ክርስቲያናችን እምነት ያደረጉትንጥንታዊ ተረት ነው።

 ተረቱ ባጭር ቃል፦
ትንሽ መነሻ ካገኙ እግራቸውን ወደ ላይ ብለው ውሸታቸውን በመልቀቅ የሚታወቁትየሰሎሞን ሥርወ መንግሥት ደብተራዎች ማፈሪያ የሆነውን ተረት ሲተርቱ እንዲህይላሉ።
   የኢትዮጵያ ንግሥት ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት በሄደችበት ጊዜ[ይህእውነተኛ ታሪክ ነው 1ነገ 10] ከሰሎሞን ጸንሳ መመለሷንና ቀዳማዊ ምኒልክንእንደወለደች ይተረካል። ምኒልክ በተወለደ በሃያ ዓመቱ አባቱን ለመጎብኘት ሄዶነበር። ሲመለስ ልጄን ባዶ እጄን አልሰደውም ብሎ ታቦተ ሚካኤል ከሦስት መቶበላይ የሆኑ ሌዋውያን ከልዩ ልዩ መጻሕፍት ጋር እንዲሰጠው ታዘዘለት። ሌዋውያኑግን በሚካኤል ፈንታ ታቦተ ጽዮንን ሰርቀው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡና ከዚያን ጊዜጀምሮ ታቦተ ጽዮን በኢትዮጵያ እንደምትገኝ ይተርካሉ። የመንግሥታቸው ታሪክ ከዚህእንደሚጀምርና ንጉሥነትም ከይሁዳ ዘር አይወጣም የተባለውን የጌታ ቃል በመጥቀስ"ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳብለው ሰይመው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲገዙበትእንደኖሩ ሁላችን የምናውቀው ጉዳይ ነው። ይህ ያለፈ ታሪክ ዛሬ አይቆጨንም ነገርግን ዛሬ ላይ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያንን መናፍቅ እያሰኘ እያስወገረን ስለሆነየኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀውና ፍርዱን እንዲሰጥ እንፈልጋለን።
አትስረቅ የሚለው ሕግ የተጻፈበት ጽላት የተቀመጠበት ታቦት ተሰርቆ መጣ የሚለውታሪክ የተጋነነ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ታቦት አንድ ብቻ ነው ዘጸ2510-28 የሚካኤል ታቦት አብሮ እንደተሰጠው የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስቃል የለም። በታሪክም በአዋልድ መጻሕፍትም ስለሚካኤል ታቦት የሚናገር አይገኝምከድርሳነ ኡራኤልና ከገድለ ተክለሃይማኖት በቀር።
 በእርግጥ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መጣለችንመጽሐፍ ቅዱስ ስለታቦተ ጽዮንምን ይላል?
                                                        መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታቦት

                                           
   

   የኢትዮጵያው ታቦት
መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ታቦትና የኢትዮጵያውን ታቦት ተመልከቱ

 
ምኒልክና የሰሎሞን ዘመን መራራቅ

1 ሰሎሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ከሁለት ወር ቤተ መቅደሱን ለመስራትመሠረት አኖረ። 1 ነገ 61 2ዜና 31-2
2የቤተ መቅደሱ ሥራ ሶሎሞን በነገሰ 11ኛው ዓመት ወር ተጠናቀቀ።1ነገ 636-37 ሥራው የፈጀው ጊዜ 7 ዓመት ከስድስት ወር ነው።
3በጥቅሉ የራሱን ቤት እና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ 20ዓመት ነው 1ነገ 910 2ዜና 81-8
 ከዚህ በኋላ ነበር ንግሥተ ሳባ የሶሎሞንን ዝና ሰምታ ለመጎብኘት የሄደችውመጽሐፍ ቅዱስ የቤተ መቅደሱን እና የቤቱን ሥራ እንደጎበኘች ይናገራልና ሥራውከተጠናቀቀ በኋላ መሄዷን ለመረዳት አንቸገረም 1ነገ 101-13 2ዜና 91-12
4ንግሥቲቱ ወደ ሶሎሞን ለመድረስ የፈጀባት ጊዜ ምን ያህል እንደሆነባናውቅም በደረሰች ጊዜ ጸነሰች ብለን እንኳ ብናስብ የጽንሱ ጊዜ 9 ወር ነው።
5እንደ ክብረ ነገሥቱ እንደ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ትረካ ቀዳማዊ ምኒልክከ20 ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ 3 ዓመት ቆይቶ ተመልሷል ስለሚልበድምሩ 23 ይሆናል።
 ጠቅላላ ድምር

 ቤተ መቅደሱ ከመጀመሩ በፊት የነበረው ይሰሎሞን የንግሥና ዘመን 4 ዓመት 2ወር  
 የቤተ መቅደሱና የራሱ ቤት ሥራ የፈጀው ጊዜ 20 ዓመት  20+4= 24
 ምኒልክ የተጸነሰበት ጊዜ 9 ወር 9+2 = 11 ወር ይሆናል
ምኒልክ ኢትዮጵያ የቆየበት ጊዜ 20 ዓመት እና አባቱ የቆየበት 3 ዓመት 20+3=23
ጠቅላላ ድምሩ 47 ዓመት 11 ወር ይሆናል።  48 አመት ብንለው ይሻላል።
   መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስረዳን ግን ሰሎሞን የነገሰው 40 ዓመት ብቻ እንደሆነናእንደሞተ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሱ መሠረት ምኒልክ የሄደው ሰሎሞን በሞተ 5ኛውዓመት ነው። ታዲያ ሰሎሞን እና ምኒልክ አራባና ቆቦ ሆነው ሳለ እንዴት በሰሎሞንትዕዛዝ ሌዋውያንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ ሊመጣ ቻለነገሩ ተረት መሆኑንእንረዳለን።
 ክብረ ነገሥት በቤተ መቅደሱ ከነበሩት ታቦታት ውስጥ አንዱ የማርያም አንዱየሚካኤል ነበር ይልና የሚካኤልን ውሰድ ቢባል የሚካኤልን በማርያም ሥፍራተክተው የማርያምን ይዘው መጡ ይላል። ማርያም በሰሎሞን ጊዜ ነበረችን? ገና መችተወለደችና ነው ታቦት የሚቀረጽላትበሬው ወለደዎች!
 በመሠረቱ ታቦተ ጽዮን ከሰሎሞን በኋላ 16 ሆኖ በነገሰው በኢዮስያስ ዘመንእዚያው ኢየሩሳሌም እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ታሪኩን እንደዚህእናስተውለው
በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው የታቦተ ጽዮን ታሪክ በማያሻማ መልኩ ወደ ባቢሎንተማረከ የሚል ነው

 ታቦቱ ከመማረኩ በፊት በኢየሩሳሌም እንደነበረ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል"ቅዱሱን ታቦት የእሥራኤል ንጉሥ  የዳዊት ልጅ ሰሎሞን  ባሠራው  ቤት ውስጥአኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም" 2ዜና 35ንጉሥኢዮስያስ የተናገረው   ( ኢዮስያስ ለሰሎሞን አሥራ ስድስተኛ ንጉስ ነበር) ።ከኢዮስያስ በፊት ነግሶ የነበረው ምናሴ  የቤተ መቅደሱን ዕቃ አውጥቶ  በውስጡ ጣኦት አስቀምጦበት እንደነበር  2ዜና 33ላይ ይናገራል። በዚህ ምክንያትካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው በየቤታቸው  ይዞሩ ነበር  ኢዮስያስ "ከንግዲህ ወዲህበትክሻችሁ ሸክም አይሁንባችሁያለው በዚህ ምክንያት ነው።

    የባቢሎን ምርኮ ከኢዮስያስ ዘመን በኋላ [600 .]ተጀምሮ በሴዴቅያስዘመን ተፈጽሞአል። በባቢሎን የምርኮ ዘመን የነበረው ነቢይ ኤርምያስ ነበር።2ዜና3611-23
   ነቢዩ ኤርምያስ ስለታቦቱ በራሱ መጽሐፍም እንዲህ ብሎአል"የግዚአብሔርየቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትምአያስቡትምም አይሹትምም፤ከንግዲህወዲህም አይደረግምምኤር 316። ኤርምያስከኢዮስያስ ጀምሮ እስከ ባቢቢሎን ምርኮ እስከ ሴዴቅያስ የነበረ ነቢይ ነው ኤር11-3 ያንቡ። ኤርምያስ "ከእንግዲህ ወዲህ አይደረግምያለው ታቦቱበባቢሎናውያን እንደሚወሰድ በመንፈስ ቅዱስ ስለተረዳ ነው። ወደ ኢትዮጵያከተወሰደ 330 ዓመት በኋላ እንዲህ ሊናገር አይችልም። ኢዮስያስ ያልነበረን ታቦትበቤተ መቅደስ አኑሩት በትክሻችሁ አትሸከሙት ሊል እንደማይችል ሁሉ ኤርምያስምበዘመኑ የነበረውን ታቦት ትንቢት ተናግሮበታል።     ታቦቱ በሴዲቅያስ ዘመን ወደባቢሎን እንደተወሰደ የሚናገረው  የመጽሐፍ   ቅዱስ ክፍል የሚከተለው ነው።"እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱን ጥቃቅኑን እና ታላቁን ዕቃ ሁሉየግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት እቃ ቤትም  ያለውን ሳጥኑንምሁሉ  ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱእዝራ ካልእ 154

"ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይምን ግናይቱ እንደጠፋ ምስጋናችን እንደቀረ ዘመራዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፋ የሕጋችን ማደሪያ ታቦተ ጽዮንእንደተማረከች አታይምን?" እዝራ ሱቱ 9 23

"ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደ ጠፋች ቀረች ከሷ ጋርም ንዋየ ቅድሳቱተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎናውያን እጅ ወደቅንእዝራ ሱቱ 9 23

    ከዚህ ትምህርት  እንደምንረዳው  መጽሐፍ ቅዱሱና ክብረ ነገስቱ፤ ገ/ተክለሃይማኖት፤ድርሳነ ኡራኤል አለመስማማታቸውን ነው።  ምክንያቱም  ሦስቱ መጻህፍትማለት ክብረ ነገሥት፣ ገድለ ተክለ ሃይማኖት፣ ድርሳነ ኡራኤል፤ በመጽሐፍ ቅዱስላይ በማደም በሰሎሞን ጊዜ ታቦቱ ተሰርቆ መጧል ሲሉ  የእግዚአብሔር ቃልየሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ወደባቢሎን ተማርኳል ይላል። በትውፊት የሚያላክኩደብተራዎችን እንቀባላቸው ብንል እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቀድም መጽሐፍ የለምናዘወር በሉ ለማለት እንገደዳለን። ከላይ የጠቀስሗቸውን ጥቅሶች ለማግኘት የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖናዋ የተቀበለችውን ሰማኒያ አንድ መጽሐፍ ቅዱስይመልከቱ።

ማህበረ ቅዱሳን ያሳተመው "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋየሚለው መጽሐፍ ግን ታቦቱበሰሎሞን ጊዜ ሳይሆን  በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ወደ ግብጽ በተሰደዱ ካህናተ ኦሪት ለዘመናት ግብጽ ቆይቷል ከዚያም ስደት ሲበዛባቸው ወደ ሱዳን ይዘውት እንደ መጡ፤ ከሱዳን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይዘውት እንደገቡ ይተርካል ።በጣና ቂርቆስ 800መቶ አመት ያህል ቆይቶ  የአክሱም ነገሥታት  ከአይሁድ ነጥቀው  እንደወሰዱትናበአክሱም እንዳስቀመጡት፤ እንዲሁም  በዮዲት ጦርነት ጊዜ ወደ ዝዋይ ተወስዶቆይቶ  ዮዲት ከተሸነፈች በኃላ ወደ አክሱም ተመልሶ  አሁንም በዚያ እንደሚገኝመጽሐፉ ይተርካል።ይህ ትረካ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይመሳሰላል፤ ፍርዱን ግንለአንባቢ እንተወዋለን።

 ማጠቃለያ
ነገሩ የፖለቲካ ጭዋታ መሆኑን ደርሰንበታል፣ እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሕዝባችንንለመግዛት ታቅዶ የተፈለሰፈ ታሪክ መሆኑን ለማንም ግልጥ ነው። መንግሥት ከይሁዳዘር አይወጣም የሚለውን ቃል የሚያከብረው ሕዝባችን የሁዳ መንግሥት በኢየሱስክርስቶስ መወረሱን እርሱም የዘላለም ንጉሳችን መሆኑን ሳይነግሩት ለራስ ሲቆርሱአያሳንሱ እንዲሉ የይሁዳ ዘር እኛ ነን ከሰሎሞን ተወልደናል እናም መንግሥታችንንማንም እንዳይነካ የአሮን ዘር ስለሆንን ክህነትም የኛ ነው ቃሉን መጠበቅ አለባችሁበማለት የጌታን ክብር ሠውረው የራሳቸውን ንግሥና ሲያመቻቹ ኖረዋል። በዚህምክንያት ነው ይህ ተረት እንዲፈጠር የተደረገው።
   ዛሬ ግን የጽድቅ ጸሐይ ወጥታለች። ይህ እንደሃይማኖት ሆኖ የቆየው ታሪክተረት መሆኑን የደረሱበት ከዘር፣ ከፖለቲካ ነጻ የሆኑ፣ ወንጌልን ከእውነት ጋር እንደዝናር የታጠቁ የለውጥ ሐዋርያት ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን አፍርታለች። ለውሸትለጣኦት ለማንኛውም የሥጋ ሥራ ርኅራኄ የላቸውም፣ ለማፍረስና ለመሥራት፤ለመንቀልና ለመትከል እግዚአብሔር ልኳቸዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ማሳመንያቃታቸው፣ ለዘመናት ሲሰብኩት የኖሩት ተረት እየተናደ ከላያቸው ላይ የወደቀባቸውቢጽ ሀሳውያን ግን በጩቤ መዋጋት ጀምረዋል። ሰይፋቸውን ወደ ሰገባቸው ከተውወንጌልን እንዲቀበሉ፤ ኋላ ቀር የሆነውንና ሃይማኖትን የፖለቲካ መሣሪያ አድርጎኢትዮጵያን ወደ ኋላ ሲጎትት የኖረውን ተረት ተረት እንዲጥሉት ጥሪ እናቀርባለን።ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካን ማራመድ ብጥብጥን እንጂ ሰላምን አያመጣም።
 ተስፋ ነኝ

11 comments:

 1. ጉድ ነው! ነገር ከሥሩ ውሀ ከጥሩ ነውና በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለው ዕውቀት ግዙፍና ረቂቅ በመሆኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስህተት ወደ ዓለም ገባ ፍጡሩንም ከፈጣው ነጠለው በመሆኑም
  ፍጡር ለራሱ በሚመቸው መንገድ ለመንጐድ ሙከራ ያደርጋል። ዳሩ ግን መንገዱ ዕንቅፋትና መሰናክል ስለበዛበት ሙከራው ይከሽፋል ሐሳቡም ይከስማል። ሀ/ታላቁ እስክንድር ዓለምን በባህል በቋንቋና በማናቸውም ማኅበራዊ ኖሮ አንድ ለማድረግ ቆርጦ ተነሣ አልተሳካለትም።ለ/ሌሎችም በሌላ መንገድ የራሳቸውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን ሲያሰላስሉ ተሰናከሉ። በሀገራችንም በተለይ ከ14ኛው ምእት ዓመት ጀምሮ አለን አለን የሚሉ ሰዎች ከዕውነት ሳይሁን ከሐሰት ተነስተው ሀይማኖትን አሳበው
  በራሳቸው ውሳኔ ወንድሞቻቸውን ሲገርፉና ሲያስገርፉ ሲጨፈጭፉና ሲያስጨፈጭፉ በከንቱ አለፉ
  እምነትን እያሳበቡ በወንድሞቻቸው ላይ ያደረሱት ግፍ ግን ውሎ አድሮ ሁሉን ተመልካች ረቂቅ ፈጣሪ ሳያቋርጥ ለ15 ዓመታት አብያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥል ሰዎችን በጅምላ የሚገድል አዘዘባቸው።
  አሁንም የአስመሳዮችና አቀናቃኛች ምድር ከረቂቅ አካል የሚመጣላትን ዝናም ተቀብላ መልካም ፍሬ ካላፈራች (ዘቅርብት ለመርግም ወደኃሪታ ለአንድዶ)ናት።

  ReplyDelete
 2. "ስድት ክንፍ የወጣላቸው ሰው እግር ስለሌላቸው ነው ተብሏል እናምበክንፋቸው በረው ሄደው በ24ቱ ካህናተ ሰማይ ላይ ተደረብው 25ኛ ካህን ሆነውእስከ ዛሬ ድረስ የጌታን መንበር እያጠኑ ነው ተብሏል።" (አባ ሰላማ)።
  የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
  የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን።
  "26፤ እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።" (ዘፍ. ም1)። ይላል። በዚህም ቃል መሠረት የሰው ልጅ ፍጥረቱ ዛሬም በሥጋውም ሆነ ወደፊት በትንሳኤ የሚያገኘው ሰውነት ክንፍ እንደሚያኖረው ያስተምረናል። ነገር ግን የሰው ልጅ የክርስቶስን መልክ ይዞ ለዘላለም እንደሚኖር የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። በሰውነታቸው በፍጥረታቸው ክንፍ ይዘው የሚኖሩ መላክቶች እንደሆኑ ግልጽ ነው። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርቱ ወቅት ለወገኖቹ ይሁዳውያን እንደነገራቸው፡ " 12 ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።" (ዩሐ. ም3) ፡ ይላል። በዚህም ቃል መሠረት ማንም የአዳም ዘር በሰማይ ላይ ሆኖ በእውነተኛው መቅደስ በአስሁኑ ሰዓት የሚያገለግል የለም። ምክንያቱም የሰው ልጆች መንፈሳዊ ሰውነትን የሚያገኙት በመጨረሻው ዘመን በትንሳኤ ስዓት ብቻ ነው። በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንዳስተማራቸው፡
  " 51-52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።" (1ኛ ቆሮ. ም15)። ይላል። በዚህም ቃል ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው በሚነሱበት ወቅት ክንፍ አይደርጉም ነገር ግን ክርስቶስ የትንሳኤ በኩር ሆኖ በሶስተኛው ቀን በሚነሳበት ወቅት እንደነበረው መንፈሳዊ ሰውነትን ይሰጣቸዋል። በዚህም ማንም የአዳም ዘር እሳካሁን ትንሳኤንም ያየ ወይም ወደ ሰማይ ወጥቶ የሚኖር የለም። በዚህም አሁንም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንዳስተማራቸው፡" 21 ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።22 ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤" (1ኛ ቆሮ. ም15)። ይላል። በዚህም አሁን እኛ ሁላችን ተራችንን እንጠብቃለን። አብርሃምም በመቃብር ውስጥ ተኝቶ መነሳትን ተርውን ይጠብቃል። እንዲሁም ዳዊትም መበሰበስን አይቶ ትንሳኤን ይጠብቃል። ስለዚህ ዛሬ በራሳችን ጥበብ የምንማረው ትምህርት የእግዚአብሔርን እውቀትም ጥበብን ስለማይሰጠን ዝም ብለን ራሳችን ማታለል ሰለሚሆንብን የእግዚአብሔርን ቃል እንድናስተውለው እግዚአብሔር ይመክረናል። በዚህምእግዚአብሔር በቅዱስ ሰለሞን ላይ አድሮ ዛሬ ሁላችንም የሚመክረን ዝም ብለን በሰዎች ጥበብ ተነድተን ወደ ሞት እንዳንሄድ።"5 እናንተ አላዋቂዎች፥ ብልሃትን አስተውሉ፤ እናንተም ሰነፎች ጥበብን በልባችሁ ያዙ።6 የከበረች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።7 አፌ እውነትን ይናገራልና፥ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ።8 የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ ጠማማ ዘወርዋራም አይደሉም።9 እነርሱ በሚያስተውሉ ዘንድ የቀኑ ናቸው፥ እውቀትንም ካገኙአት ሰዎች ጋር የተስማሙ ናቸው።" (ምሳ. ም8)። ይላል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Raiy 12 lesetitum kinf tesetat yilal ikko.kinf degmo yemitay aydelem indemelaikt siwur newu.timiirt saynorih lerasih anebebku bileh yemittsfewu lekefa sihtet sidargihal.metshaf kidus indanebebn yeminreda bihon noro yih hulu yekrstiyan sectoch yelum neber

   Delete
  2. Igziabhern sewoch indiredut besil inaskemitalen inji bemelkachin yemilewu yesewu lij indigziabiher Awaki,tenagari ina zelalemawi mehonun yemiyasay newu yihn tirgwame kalanebebk /kaltemark fitsum litawukewu atchilim.Belibachewu hasab yemikorutn betatenachewu yilal metshaf kidus.Lezih newu protestant yetebetatenewu

   Delete
  3. ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ከተነሳ በኋላ መንፈሳዊ ሰውነት ወይም የማይታይ እንደ ነፋስ ሆኖ ለወገኖቹ እንደ ድሮው በር ክፈቱልኝ ሳይል ቢት ውስጥ ግብቶ መካከላቸው ተገኝቷል። በዚህም ቅዱስ ሉቃስ እንደሚመሰክረው።" 35 እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው።36 ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።37 ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው።38 እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል?39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።" (ሉቃ. ም24)። ይላል።
   በዚህም እነርሱ በሚያዩበት ወቅት ክንፍ አልነበረውም። ነገር ግን መንፈሳዊ ሰውንትን አድርጓል። መላዕክቱች ግን በተፈጥሯቸው ክንፍ አላቸው ለሰው በሚገለጡበት ወቅት እስክ ክንፋቸው ይታያሉ። ነገር ግን ሰው ወደፊት አምላኩን ለመምሰል ነው ጽድቅ የሚሰራው። በዚህም መንፈሳዊ ሰነት ክንፍ የሌለው የክርስቶስን ሰውነት እናገኛለን። በተጨማሪ ደግሞ እግዚአብሔር በቃሉ ሁልጊዜ በምሳሌ ያስተምራል። በዚህም "1 ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ።" (መዝ. ም78)። ይላል። በዚህም ይህንን ቃል በምሳሌ እንዲህ ሲል ተናግሯል።
   " 14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት። " (ዩሐ. ራዕይ ም12)። ይላል። በዚህም ቃል መሠረት እግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ወይም ያዕቆብ ወይም ክርስትያኖች በመጨረሻው ዘመን በመከራው ዘመን የሚሆነውን ነገር እግዚአብሔር አብ ለልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቶስ መላዕኩን ልኮ ለዩሐንስ ወደፊት ቶሎ ይሆን የሚገባውን ነገር ባስወቀው መሠረት ይህንን ቃል ተናግሯል። በዚህም መሠረት ይህች ሴት ታላቅ የንሥር ክንፍ ተሰጣት ማለት ለአንድ ሴት ብቻ የተነገረ አይደለም። በክንፏም የሄደችው ሰማይ ቤት ሳይሆን ወደ ምድር በዳ ከሚመጣው ከመከራው ለመደበቅ ነው የሄደችው። በዚህም ቦታ የምትቆይበትን ጊዜም ለ3 ዓመት ተኩል ማለትም አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ብሎ ገልጾታል። በዚህም ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን አስቀድሞ እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ወደ ተቀደሰችው ምድር በሚመራባት ጊዜ መጀመሪያ ያደረገው ወደ ምድረ በዳ ነው የመራት። በዚህም ቦታ ከእሥራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል። እምቢ ያሉት ቃሉን ሰምተው በእምነት ያላዋሃዱትን ወገኖች ሁሉ እንዲሁ በምድረ በዳ ቀርተዋል። በተመሳሳይ መልኩ ወደፊት በመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስትያንን ወይም ክርስትያኖቹን በመከራው ወራት በሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ይመራቸዋል። በዚህም ቦታ አስቀድሞ በግብጽ ምድረ በዳ ያደረገውን ነገር እንደገና ያደርጋል። በዚህም እንዲህ ሲል ተናግሯል።
   " 6፤ ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።17፤ ከዚያም የወይን ቦታዋን፥ የተስፋ በርም እንዲሆንላት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፤ በዚያም ከግብጽ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ ሕፃንነትዋ ወራት ትዘምራለች። (ሆሴ ም2)። ይላል። ........ይቀጥላል

   Delete
  4. እንዲሁም ለነቢዩ ዳነኤል እግዚአብሔር እንዳመለከተው፡ የመከራው ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው እንደሆነ እንዲህ ሲል ነግሮታል። " 1፤ በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።2፤ በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።3፤ ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።4፤ ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።5፤ እኔም ዳንኤል አየሁ፤ እነሆም፥ ሁለት ሌሎች ቆመው ነበር፥ አንዱ በዚህ በወንዙ ዳር፥ ሌላውም በዚያ በወንዙ ዳር።6፤ አንዱም ከወንዙ ውኃ በላይ የነበረውን በፍታም የለበሰውን። የዚህ ድንቅ ፍጻሜ እስከ መቼ ነው? አለው።7፤ ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ። ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፤ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ። " (ዳን. ም12)። ይላል።
   ይህም የመከራ ቀን በቀን ሲሰላ 1260 ቀን እንደሚሆንም እንዲህ ሲል የተቀደሰው መላእክ ለዩሐንስ ነግሮታል። " 3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።" (ዩሐ. ራዕይ ም11)። እነዚህ ማቅ ለብሰው የሚመጡት ምስክርች ኤልያስና ሄኖክ እንደሆኑ ያስተምረናል፡፤ እነርሱም ከተሰወሩበት የሚወጡት በዚሁ መከራ ዘመን ይሆናል። በተጨማሪም ከላይ ዩሐንስ ታላቁ ዘንዶ ቤተ ክርስትያንን ወይም ሲቷን እንድሚአሳድዳት ተናግሯል። በዚህም ይህንንም ሲያደርግ ምን ያህል ጊዜ እንድሚወስድም እንዲህ ሲል አህንም በወራት ቆጥሮ ነግሮታል።
   " 5 ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።" (ዩሐ. ራዕይ ም13)። ይላል። አርባ ሁለት ወራት ማለት ደግሞ 1260 ቀን ማለት ነው እንዲሁም 3 ዓመት ተኩል ማለት ነው። በዚህም ወራት ታላቁ ዘንዶ " 7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።"" (ዩሐ. ራዕይ ም13)። ይላል። በዚህም ጊዘ ከዚህ መከራ ለመሽሽ ቤተ ክርስትያን ወደ ምድረ በዳ ይመራታል።
   በመቀጠልም እግዚአብሔር ለሴቲቷ ወይም ለቤተ ክርስትያን ወይም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል ተናግሯል። "33፤ እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።34፤ ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።35፤ ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ።36፤ በግብጽ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋር እንደ ተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።37፤ ከበትርም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ፤38፤ ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ፤ ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።" (ሕዝ. ም20)። ይላል።
   በዚህም ቃል ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት ሲል እግዚአብሔር በምሳሌ መናገሩ ነው። በዚህም ይህ ቃል በዩሐንስ ራዕይ ላይ የተመዘገበው ወደፊት የሚሆነውን ነገር ያመለክታል። መቼም ለሁላችን አንዳንድ የእግዚአብሔር ቃል አዲስ ሲሆኑብን የጴንጤ የጀሆቫ ትምህርት ነው ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ማውገዝ አስፈላጊ አይደለም። በመጽሀፉ የተጻፈው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ነገር ግን ከተጻፈው ውጪ ስንማር ነው ማውገዝ ያለብን። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደሚመክረን እኛ እንውቃለን ብለን የምንናገር ሁሉ አንድ ነገር ማስተማር በምንፈልግበት ወቅት በስድብ ሳይሆን መጽሀፉ እንዲህ ይላል ብለን በተቻለን መጠን ማስተማር ይገባናል። ቅዱስ አባቶቻችን ስድብ በመጽሀፍ ላይ ጽፈው አላስተማሩንም። ነገር ግን ስይጣን እውነቱ ሲነገር ደስ ስለማይለው ስድብ ውግዘት ያበዛል። እኔ ጻድቅ ነኝ ይላል። ከዚህ በሽታ እግዚአብሔር ይሰውረን።
   ቃለ ሕይወት ያሰማልን! ወስብሃት ለእግዚአብሔር!   Delete
 3. ለቀቢፀ ተስፋ
  ዲያቢሎስ ከሳሽ ነው። ዲያቢሎስ እውነት በሐሰት የሚቀይር ነው። ዲያቢሎስ ታሪክን የሚያፋልስ የተፃፈውን ሳይሆን ያልተፃፈ የሚያነብ ነው። ዲያቢሎስ እውነታውን ለማጥፋና ቅደም ተከተሉን ለማፈለስ በዚህም እውነቱን ተረትና ውሸት ለማትና ለማደናገር ይተጋል። ብቻ ዲያቢሎስ ገና ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ የእግዚአብሔር የክብሩ ወራሽ የሆኑትን የሰው ልጆች ከአምላካቸው ለመለየት እውነቱን ሐሰት ሐሰቱንም እውነት በማለት ብዙ ውጊያዎችን አድርጓል እያደረገም ነው። የተሸነፉትን በተንኮል አሳችነቱ ጥሏቸዋል። አንተም ቀቢፀ ተስፋ የደም የደያቢሎስ ልጁ ነህና በመንገዱ መሔድህ ሌጊዎንነትህን ያመለክታል።
  እዚህ ከአይምሮህ ፈጥረህና የመልክቱ ትርጉም ሳይገባህ ክደህ ክህደትህን እውነቱን ውሸትና ተረት ለማለት ብዙ ደክመሃል። ግን አለማዊ ለዛውም ክፉ የክፋት ደቀመዝሙር ነህና የወለቀ ጥርስህን ብታስተክል ይሻልሃል። ከዛውጭ ይህ ሁሉ እንክዳድ ውሸትህ በክርስቶስ መንግስ አንዳች ቦታ የላቸውም።
  አንተ የሌለ ታሪክን የቤተክርስቲያኗ ለማስመሰልና የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ መጽሐፍት ያልሆኑትን በቅዱሳን ስዕልና በመጠሪያ ከበር እየተጋረዳችሁ ውሸት በመፃፍ እያሳተማችሁ እንክርዳዳችሁንና ጥፋታችሁን እንደምታራምዱ ከታወቀ ቆየ። ለምሳሌ ገድል ወይስ ገደል የሚለው የኑፋቄ መጽሐፍ ሽፋኑ በቅዱሳን ስዕል የተዘጋጀ የቤተክርስቲየኗ በማስመሰል ነው።
  ስለሆነም የቤተክርስቲያኗ ቅዱሳት መጽሐፍት እውነተኛነት የሚረጋገጠውና ትክክለኛ መልእክት የሚነገረው በቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ አባቶችና መምህራን እንጂ በአንተ በቀቢፀ ተስፋውና በካሃዲያን መናፍቃን ብሉም ባላመኑት አይደለም።
  ዛሬ መጽሐፍ ቅዱሱን የተሸከመው ሁሉ ያወቀና የዳነ እየመሰለው የቃሉ መልእክት ሳይገባቸው ስተው ሲያስቱ ይታያሉ። አንተም ውሸትህንና መናፍቅነትህን ለመደበቅ መጽሐፍ ቅዱስን ከለላ ለማድረግ ተጠቅመሃል። ትናንት እውነት የእግዚአብሔር ቃል የሚነገር ክርስቶስ የሚመለክ መሥሏቸው በሐሰተኛ ክርስቶሳዊያን የተታለሉትን ሳር ሲያስግጣቸው የነበረው የአንተው የሥራ አገር የዲያቢሎስ አገልጋይ የደቡብ አፍሪካው ፖስተር ነኝ ተብየ ነው።
  እናም የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል ሳታውቅና በዲያቢሎስ መንፈስ እየመዘንህ ጥቅስ መጥቀስህ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ተብሎ የተነገረውን እንድናስብና ወግድ አንተ ክፋ እንልሃለን።
  የውሸትህ ዘባተሎ መያዣ መጨበጫ የሌለው ነው። ግን አንዱን ውሸትህንና ከአይምሮህ አንቅተህ የፈርከውን እውሸትህን ልናገር። ንግስት ሳባ ከንጉስ ሰለሞን የወለደችው ምኒሊክ ታቦተ ፅዮንን ይዞ መጣ የሚል ታሪክ በቤተ ክርስቲያን የለም። ይህ የአንተእውነትን ለማጥፋት የፈጠርከውና የፃፍከው ታሪክ ነው።
  ምኒሊክ ይዞት የመጣው ካህናተ ኦሪትንና ስርዓትን እንጂ ታቦተ ፅዮንን አይደለም።
  መጽሐፍቱ ይጋጫሉ ለምትለው የተጋጩብህ ለአንተ እውነትን ለማየት ለማትሻው ለታወርኸው እንጂ እውነትን ለማየት ለሚፈልጉት አይደለም። በመጽሐፍ የማያምኑትን ልብ አሳወረ ለቀው ተብለልና።
  ከስርዎ መንግስት ተነስተህ እስካሁን ባሉት ተነስተህ አንዲቷንና ለክርስቲያኖች ፈፅሞ አንድ ጊዜ በተሰጠችው ሀይማኖትና የክርስቶሶ ቤተክርስቲያን ላይ ጦር ሰብቀህ ዘውግ መዘህ ጥፋትህን ማራመድና መዝራትህ ምን ያክል ተሸከምከው እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ቃልና ታሪክ የተጣላህና የተራራቅህ መሆንህን ያመለክታል። ምክንያቱም እግዚአብሔር በብሉይም ከነገስታት ጋር ነበር በአዲስ ኪዳንም አይደለም ለመንግስት ለሰው ህግም ተገዙ ተብሏል። እንዲህ ሲባል ግን ግፍ ሲፈፀም ዝም በሉ ለጣኦት አምላኪ ዲብ ደብዳቢ ተገዙ ማለት አይደለም።
  ቀቢፀ ተስፋ፦ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖቷን ለአማኞቿ ተወት አድርገህ የራስህን በስልሳ ስድስቶ መጽሐፍ ተደብቀህና በክፉ መንፈስ መገለጥ እያጭበረበርህ ስለምትፈፅመው ክፉ ስራህና እርኩሰትህ ተርክ። ደርሶ ፊጢጥ ለነቀያፋም አልሆነ፤ ለአባትህ ለሳጥናኤልም መዋረድና ከክብር መጣል ነው የሆነ።
  የእውነትን መንገድ ለታጠፍና ልትበጥስ አትችል። የእውነት መንገድ ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. @Damot
   Trash and non sense as usual. Try to discover the truth. Do not bark invain.

   Delete
 4. ልጅ ተስፋ ትዘባርቃለህሳ!!ከሸዋ አቡነ ተ/ሃይማኖትን በፖለቲካ ሥም ነጠቅህ ስታበቃ፣ከትግራይ ታቦተ-ጽዮንን በማኅበረቅዱሳን አስመስለህ ለመንጠቅ ሞከርክ--አቡነ አረጋዊን ደግሞ መቼ ትመለስባቸው ይሆን??!!


  መደምደሚያሕ በቤተ ፕሮቴስታንት የተለመደው ያልደረሱበትን ትውፊት ሁሉ ተረት-ተረት ማለት ሆነ፡፡አማርኛ መቻል፣ጥቂት ምዕራፎችን መጥቀስ፣ከዚህም ከዚያም ታሪኩንም፣ገድለ-ቅዱሳንንም፣ፖለቲካውንም፣መጽሐፍቅዱሱንም ለፕሮቴስታንታዊ ስሜትህ መደጎሚያ ለማዋል ትታትራለህ፡፡ተሐድሶ መሆን ትልቁ ጥቅሙ ‹‹ሁሉን ነገር አውቄ ነው፤ጌታ በራእይ ተናግሮኝ ነው ወደ ቃሉ የመጣሁት›› ለማለት የተመቸ ነውና እንዳሻህ ታወራለህ--እንደ ዶክሌው ፓስተር ዳዊት፡፡መቀበጣጠርህ ላለፉት አመታት በነ ተስፋየ ገብረአብ የለመድነውን ያረጀ ወሬ በአዲስ የብዕር ሥምና በአዲስ አማርኛ ከማለባበስ በቀር የረባ ነገር ስለሌለው የምንለው የለም፡፡ንቆ ማለፍ ነው!!


  የቅድስት ተዋሕዶን በትርጓሜ-ወንጌል ያጌጠና ትውልዶችን የተሻገረ ሥርዓትና ትውፊት እንኳንስ እንደ አንተ ያለ የፕሮቴስታንት-ክልስ አማተር እነ ዮዲት ጉዲት፣ግራኝ፣ሱስንዮስ፣ደርቡሽ፣ፋሺስት ጣሊያንና ደርግም ሞክረውት አልሆነ፡፡አንተ እና መሰሎችህ ግን ቅድስት ቤትክርስቲያን ለሀገርና ለወገን ያበረከተቻቸውን ቁሳዊና መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ ተረት-ተረት ብላችሁ ኢትዮጵያዊውን ትውፊት በምዕራባዊ ሥጋ-መራሽ መንፈስ ካልቃኛችሁ ምሁራዊ ካባ የሚደረብላችሁ አይመስላችሁምና ግፉበት፡፡ማንንም አትጎዱም!የሚያስቀው ግን እናንተ ተረት እየላችሁ የምታጣጥሉዋቸው የሰሎሞናዊ ሥርወ-መንግሥት ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርሶች እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ንብረቶች ተቆጥረው በስስት የሚታዩ የአውሮፓ ላይብራሪዎች ውድ ቅርሶች መሆናቸው ነው!!እቡይ እግረ-ተልሚድ ተስፊቲ ግን ከላይ ከፍ ብለሽ አርእስታቸውን፣ዝቅ ብለሽ ኅዳጋቸውን ሳታይ ነጠላ ንባብ ይዘሽ በመቆንጸል ግዳይ ለመጣል ትታትሪያለስሽ!!ላይሆንልሽ!


  በነገርሽ ላይ ጽሑፍሽ የረባ ሆኖ ጥቂት ቲፎዞዎችሽን ማንጫጫት ከቻለ ገለባ መሆኑን ለማሳየትና የቅድስት ተዋሕዶን ልጆች ካልፎ ሂያጅ አደናጋሪ ለመታደግ ስል ልመለስበት እችላለሁ፡፡ደስ እንዳለኝ!!ለጊዜው ግን ‹‹የተለመደ›› ተብሎ እየታለፈ ስለመሰለኝ እኔም እንደ ሌላው ‹‹የተለመደ የቀሳጢ እሪታ›› ብዬ በግልምጫ አልፈዋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. ENAZEH DEBTARAWOCH ESKAHUN YEWAHUN YE'ETHIOPIA HIZB SIYATALILUNA SIBADILU NOREWAL. TINISH QOYTEW DEGMO 'ABUNA PHAWULOSIM KINF AWUTEW MEKABIR FENKLEW BERARU" ENDAYLUN EFERALEHU. QESOCHACHEN AMANYU METSHAF KIDUSIN ANBIBO ENDAYREDA LEZEMENAT AFNEWUT NEBER, AHUN GIN ANBIBEN EWUNATUN MEREDAT CHILENAL. ENASU GIN EWUNATUN ENDAYREDU SAYTAN AYNACHEWUN CHEFINOBACHAWAL. EGZABHER MENFESAWI AYNOCHACHAWUN YEKFATLACHEW!

  Netsenat

  ReplyDelete