Tuesday, June 2, 2015

ማኅበረ ቅዱሳን አዲሱ ገበያ የሚገኘውን የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን በተወካዮቹ አማካይነት እየመዘበረ መሆኑ ይፋ እየወጣ ነውበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ እጅግ የተጠናከረ ውንብድና ከሚፈጸምባቸው አድባራት መካከል አንዱና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ተዘፍቆ ያለው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ዘግበን የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ከሰሞኑም ችግሩ ተባብሶ በየትም ቦታ ያልታየ በዕቅድና በዓላማ የማቅን ጥቅም ለማስጠበቅ በህገ ወጥ መንገድ የተመረጠው የሰበካ ጉባኤ አባላት ጉድ ይፋ ሆኗል፡፡

ችግሩ የሚጀምረው ከሰበካ ጉባኤው አመራረጥ ሲሆን፣ በጊዜው ህግወጥ ነው እየተባለ ቢለፈፍም ሰሚ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ የሰበካ ጉባኤው በሕገ ወጥ መንገድ መመረጡ ብቻ ሳይሆን እውቅና የሌለው የሀገረ ስብከቱ ተወካይ በሌለበት ማቅ ጉዳዬን ያስፈጽሙልኛል ብሎ በወከላቸው ሰዎች የተቋቋመ ነው፡፡ ከሰበካ ጉባኤው አባላት መካከል ዶ/ር ኃይሉ የአጥቢያው አባል ያልሆነ፣ ሊቀ መንበሩ ዮናስ ሽፈራው ባለ ሁለት ሚስት እና በሰካራምነቱ የታወቀው ግለሰብ ይጠቀሳሉ፡፡

በጊዜው የድምጽ ቆጠራ ይካሄድ የነበረው ምንም ስራ ሳይኖረው ሃብታሞችን እያታለለ የሚኖረው ወጣት ዮናስ መኮንን ወንድሙን አባሪ አድርጎ ጓደኛውን ወጣት የትናየት ኃይሉን እና ዮናስ ሽፈራውን የሰበካ ጉባኤ አባላት አድርጓቸዋል፡፡ በህንጻ አሰሪ ኮሚቴው ውስጥ ያለው አቶ ይድነቃቸው መኮንን የዋንዛ ፈርኒቸር ሥራ አስኪያጅ ከትዳሩ ውጪ ዱከም ላይ ቅምጥ ያለው ሲሆን፣ በቤቱም ከሰራተኛው ወልዷል ተብሎ ውስጥ ውስጡን ይወራበታል፡፡ ሚስቱ ወንድሟን የሕንጻ አሰሪው ኮሚቴ ዕቃ ግዢ ያስደረገችው ሲሆን እዚያው አጂፕ አካባቢ ባለ 3 ፎቅ ህንጻ እየገነባ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ በሥሩ ያለውን ት/ቤት ማስቀጠል ስላልቻለና ከገቢ ይልቅ ወጪ ስለበዛበት የማቅ አባላትም ቦታውንም ህዝቡንም በማዳከማቸው ት/ቤቱን ከቤተ ክርስቲያኑ አሳልፈው ለማኅበረ ቅዱሳን የጎርጎርዮስ አጸደ ህጻናት አካል ለማድረግ ውስጡን ሲሰሩ ቆይተው በኋላም ለእነርሱ ይከራይ ብሎ አቶ ዮናስ ሽፈራው ተናግሮ ይፋ አውጣው፡፡ መረጃው ወደ ሀገረ ስብከቱ ስለደረሰ አሁን ያለው የሀገረ ስብከቱ አመራር በሬዲዮና በጋዜጣ ጫረታ እንዲወጣ በማለት መመሪያ በመስጠታቸውና ጨረታውም በሚዲያ በመውጣቱ የእነ ዮናስ ህልም ተጨናግፏል፡፡ አንድ የሰበካ ጉባኤ አባል ካሉበት ግዴታዎች አንዱ የአጥቢያውን ልማት ማስፋፋት ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ራሳቸውን አልምተውና ቦታውን አዳክመው ሲያበቁ ለሌላ አካል ለማከራየት መሞከር አሳዛኝና ይሉኝታ ማጣት ነው፡፡

በሰበካ ጉባኤው ውስጥ የተከሰተውን ሽኩቻና ለወንጌል እንቅፋት የሆኑበት ምክንያቱ ከታወቀ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር መውረድ አለበት በማለት እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ይህን ተከትሎ ሲዘርፉ በልባቸው የያዙትን ምስጢር አሁን መወጣጣት ይዘዋል፡፡ በዚሁ መሠረት፦
·       ህንጻው የሚፈልገውን የንጣፍ ድንጋይ ወለል የሚገዛው በጨረታ ሳይሆን በአቶ ጉዳ አማካይነት በዮናስ ሽፈራው አቅራቢነት ከመስሪያ ቤቱ እንደነበር ይፋ ወጥቷል፡፡
·        አሁንም ህንጻ አሰሪ ኮሚቴው የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ ዕቃ ደግሞ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ አባል ከሆነውና ቤተልሄሙን እያሰራ ካለው፣ ሀገር ፍቅር አካባቢ “ባርና” ከተባለው ከአቶ እስጢፋኖስ ሃይሉ ድርጅት እና አትክልት ተራ የሚገኘው የእስጢፋኖስ ኃይሉ ወንድም የየትናዬት ኃይሉ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት ነው፡፡ ልብ እንበል ያለ አንዳች ጨረታ ከሁለቱ የሠበካ ጉባኤ እና የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ወንድማማቾቹ ሱቅ ነው የሚገዛው፡፡ የሚገርመው ግን ከቤተ ክርስቲያን እየተዘረፈ እዚያው ቤተልሄም እናሰራለን ይባላል፡፡

ይህ ሁሉ ግዢ የሚከናወነው አሁን በግል ህንጻውን እያጣደፈ ያለው ከህንጻው አሰሪ ኮሚቴ ውስጥ የእህቱ ባል  በሆነው ቤቱ ወይራ ሰፈር በሆነው በይድነቃቸው አማካይነት ነው፡፡

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኑ ሙዳየ ምጽዋት ቁልፍ  የሚይዘው የሰበካ ጉባኤው ሊቀመንበር ዮናስ ሽፈራው መሆኑ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱስ ካህናቱስ ይህን ጉዳይ ምን ይሉት ይሆን? ነባር የደብሩ ካህናት አሁን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሱ ይመስላል፡፡ በእርግጥ በደብሩ ውስጥ ወደፊት እንደአስፈላጊነቱ የምንገልጠው የወለዱ ነባር አገልጋይ መነኮሳት ጉዳችን ይወጣል ብለው እነዚህን አማሳኞች እንደሚደግፏቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ ይልቅ አጥቢያው እየደረሰበት ያለውን ችግር ህገወጦችን በመቃወም አቋም ሊይዙ ይገባል፡፡ ልጆች ስለወለዱ ራሳቸውን ሸፍነው አጥቢያውን ለወሮበሎች አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፡፡ እነርሱ የሸፈኑላቸው ጉዳቸው እኮ አሁንም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ እኛ እንደ ማቅ ጥቅም እናስጠብቅበታለን ብለን አናስፈራራበትም፤ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሲባል ግን በፎቶ ተደግፎ ይፋ ሊሆን ይችላል፡፡  

ሰሞኑን በ18/9/2007 ዓ.ም. እስካሁን አብሮ ሲሞዳሞድ የነበረው የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት በቃለ ጉባኤ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያስገባው ደብዳቤ እንደሚያትተው፦
·        ያለጨረታ ዕቃ ግዢ ሲፈጽሙ ነበር፡፡
·        የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም ብቻ የሚያስቀድሙ ናቸው፡፡
·        ሰበካ ጉባኤውን ተግን አድርገው ኦዲት ተደርገው አያውቁም ሲል በሰፊው ያትታል፡፡

የዕቃ ግዢው ኃላፊ አቶ ጉዳ በለጠ ደሳለኝ ከሌላው ጊዜ ይልቅ ገንዘብ የሚያስወጣ የኮሚቴ ስራ ካለ ፈጥኖ የኮሚቴው አባል ሆኖ በመግባት ይታወቃል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከነቤተሰባቸው ኢየሩሳሌም ሄደው የሚሳለሙ፣ ሲኖትራክ ገዝተው የተገለበጠባቸው ናቸው፡፡

ሌላው ሰሞኑን የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የእስካሁኑ አልበቃ ያለው ያለው የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ በ21/9/2007 የደብሩን ሰበካ ጉባኤ ሊቀመንበር ይዞ ያለ ደብሩ ዕውቅና ዝርፊያ ሊፈጽምባቸው ካቀዳቸው ሥራዎች አንዱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሣል ሥእል ጨረታ ሲሆን፣ ጨረታውን በውስጥ ጨርሶ ለአንድ የማቅ አባል ለመስጠት አቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ደብሩ ግን በማገድ በግልባጭም ለሀገረ ስብከቱ አሳውቋል፡፡

እነርሱ እንደፈለጉ ከሰበካ ጉባኤው ጋር ተባብረው የሚዘርፉትን ገንዘብ፣ ካህናቱ ደሞዝ ሲቀበሉ የሚናደዱ፣ ለካህናቱ ኑሮ መሻሻል ግድ የሌላቸው፣ አገልጋዩ በቤት ኪራይ በልጆች ት/ቤት ሲሰቃይ አይተው ልማት በማልማት የገቢ ምንጭ ፈጥሮ እንዲጠቀም ከማድረግ ይልቅ ደብሩን ወንጌሉን ልማቱን የሰውን አመለካከት ጭምር አዳክመውታል፡፡ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ይህን ሁሉ ሲፈጽም ለቤተ ክርሰቲያን ከኔ በላይ ተቆርቋሪ የለም ባዩ ማኅበረ ቅዱሳን ዝም ያለበት ምክንያቱ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ጥቅሙን ስለሚያስከብሩለት ሲሆን፣ የእርሱ ጥቅም እስካልተነካ ድረስ “አማሳኝ” የሚለውን መዝሙሩን እንማይዘምር አስመስክሯል፡፡ የተቃወሙትንና የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለማስጠበቅ ቦታ ያሳጡትን ግን በየአጋጣሚው “አማሳኝ” እያለ ያላዝናል፡፡

በደብሩ ውስጥ የተከሰተውን ችግር ውስብስብነት ስንመለከት የሰንበት ት/ቤት ምክትል ሰብሳቢ፣ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ሀብታሞችን ቤተ ክርስቲያን ላሰራ ነው እያለ የገቢ ምንጭ የፈጠረው ያለ ስራ እዚያው የሚውለው ዮናስ መኮንን፣ ወንድሙ ይድነቃቸው የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ፣ የሚስቱ ወንድም ዕቃ ግዢ፣ ሁለቱ ወንድማማቾች ከሚዘረፈው ገንዘብ ላይ የኤሌክትሪክ ዕቃ የሚያቀርቡት እስጢፋኖስና የትናዬት፣ የቅርብ ጓደኛቸው ዮናስ ሽፈራው ከመስሪያ ቤቱ ዕቃ ያቀርባል፡፡ በዚህም እነዚህ ሰዎች ምን ያህል የተሳሰሩና አደገኛ ሙስናዊ ሰንሰለት የዘረጉ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ ይህ ተጠንቶና ታቅዶ በዓላማ የተመረጠው ሰበካ ጉባኤ አፍራሽ ተልእኮውን የጀመረው ወንጌልን በመስበክ ይህን የጨለማ ስራ ሊገልጥ የሚችለውን የደብሩን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ድራሹን በማጥፋት ነው፡፡

በደብሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በቅድሚያ ሕገወጡንና የማቅ ወኪል የሆነውን የሠበካ ጉባኤ በማፍረስ ሌሎች ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸውን፣ ለስብከተ ወንጌል፣ ለልማት ቅድሚያ የሚሰጡ፣ የማንም ማኅበር ጥገኛ ማኅበር አባል ያልሆኑ፣ በደብሩ ውስጥ ጥሩ ምስክርነት የሚያገኙ ታማኝ ሰዎችን መምረጥ አንዱ መፍትሔ ነው፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ቦታዎች ተሞክሮ ውጤት ያስገኘ በመሆኑ በተለይ ለይድነቃቸውና ለዮናስ ሽፈራው መስሪያ ቤት ደብሩ ደብዳቤ በመጻፍ አንዳንድ ጉዳዮችን ማሳወቅ ቢችል ጥሩ ነው፡፡

7 comments:

 1. ere wegen sele keresetose belen yesewe bedele mezerezer yebekan manewe mitekemewe esti negerugn? akahedu tere aleneberem akahedu hege betekerstiyanene yetebeke ayedelem bele metekese sigeba yegeleseben hatiyate mezerezeru len aletayegnem bichalachu yegelesebochen hatiyate yemetawerubeten mekeneyatem aberachu metekese betechelu legnam yegeban neber ? neger gen tshfun yemiyazegajewe akale yebeka keduse kehone tegeletolete newe biye weyse amelaku azote newe beye lekemete? kalehone gen enegn mane hone newe tysewen bedele menezerezelewe ? social mida almawe memamaer endehone yegebagn amelake yerasachnene bedelenA HATIYATE MEMELEKETE ENEDENECHKLE YEREDAN?

  ReplyDelete
 2. አቤት ውሸት፣ አሉባልታና ስም ማጥፋት ሰትወዱ፣ የዲያብሎስ ቅጥረኞች። የማትረቡ።

  ReplyDelete
 3. make eko chelema new

  ReplyDelete
 4. i know this church especially the Sunday school students are under MK they do not like Gospel. The office people are corrupted. I thank Jesus christ After I went to Another church. I saw Devil in that church.

  ReplyDelete
 5. Why don't u post the word of God instead of ye mender wory?

  ReplyDelete
 6. Hey GAYS!!!! Not Guys....Please leave us alone bother about your wongelawit church.....sineka lash belu enji......ende.....

  ReplyDelete
 7. ይቅር ይበላችሁ

  ReplyDelete