Saturday, June 20, 2015

የሦስት ሰዎች ጉዳይሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ እየተመራ የሰውን ዘር በሦስት ከፍሎታል።
1. ፍጥረታዊ ሰው 2. ሥጋዊ ሰው 3. መንፈሳዊ ሰው
"ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል‚ 1ቆሮ 2፥14-15። "ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን?‚ 1ቆሮ 3፥3።
ይህ ልዩነት የመጣው በመንፈስ ቅዱስ ምክንያት ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ ነው "ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው‚ ይላል 1ቆሮ 2፥10። ስለዚህ ሰዎች በሦስት የሚመደቡት "የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገሮች‚ ለመረዳትና ለመቀበል ባላቸው ችሎታ ነው።ወደ እነዚህ "የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች‚ ደግሞ ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መግባት አይቻልም። "ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም‚ ቁ 11 እንደተባለ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሲኖር የእግዚአብሔርን ነገር ማወቅ ይቻላል። "እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም‚ ይላል ቁ 12። ስለዚህ ክርስቶስን ያወቅነው ስለተማርን ወይም ልዩ የጭንቅላት ችሎታ ስላለን ሳይሆን እንዲያው ስለተሰጠን ነው።
1 ፍጥረታዊ ሰው
"ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም‚1 ቆሮ 2፥14።
በዚህ ክፍለ ንባብ ፍጥረታዊ ሰው ሊያውቅ ባለመቻሉ አልተወቀሰም። ጥቅሱ በቀላልና በግልጥ ቋንቋ የዚህን ሰው ውስንነት ያመለክትና በመቀጠል የውስንነቱን ምክንያት ያስረዳል። መገለጥ የሚመጥው ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተመለከትን። "ፍጥረታዊ ሰው ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ አልተቀበለምና‚ የተገለጡትን ነገሮች መረዳት አይችልም። እርሱ የተቀበለው "በእርሱ ውስጥ ያለን የሰውን መንፈስ‚ ብቻ ነው። ምንም እንኳ "በሰው ጥበብ‚ ምክንያት ቃላቱን ማንበብ ቢችል፥ መንፈሳዊ ትርጉማቸውን ግን ሊረዳ አይችልም። ለዚህ ሰው መገለጥ የሚባለው ነገር ሞኝነት ነው። "ሊቀበለው‚ ወይም "ሊያውቀው‚ አይችልም።

  1ቆሮ 1፥18 እና 23 እንደተገለጠው ከመለኮታዊ መገለጥ ከፊሉ "ለፍጥረታዊ ሰው ሞኝነት‚ ነው። "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለ እኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው‚ "እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው‚ እዚህ የተገለጠው ብታሪክ ስለታወቀው የክርስቶስ ሞት ብቻ ሳይሆን ከዚያም የበለጠ ነገር ነው። ያም በእርሱ በኩል የተደረገውን ዘለዓለማዊ ግንኙነት የሚያጠቃልልና በጸጋው በኩል መዋጀታችንን የሚያሳይ መለኮታዊ መገለጥ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነገሩት ግብረ ገባዊ መርሆዎችና ብዙዎች ሃይማኖታዊ ትምህርታዊው ሰው ሊገባው በሚችል ደረጃ ይገኛሉ። "የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች‚ መኖራቸውን እንኳን ሳያውቅ ከእነዚህም ምንጮች በመቅዳት አንደበተ-ርቱዕ እና ከልቡ የሚያገልግል ሰባኪ ሊሆን ይችላል።
 ሰይጣን በአስመሳይ ዘዴው የሚገልጣቸው "ጥልቅ ነገሮች‚ ራእይ 2፡24 "የዲያብሎስ ትምህርቶች‚ 1ኛ ጢሞ 4፥1፡2 እንዳሉት እና እነዚህንም ነገሮች "ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም የሌሎችን ድምጽ አያውቁምና‚ ዮሐ 10፥5 እንደተባለ እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ እንደማይቀበላቸው ተጽፏል። ሆኖም እነዚህ የሰይጣን "ጥልቅ ነገሮች‚ ለታወረው "ተፈጥሮአዊ ሰው‚ በጣም ምቹ ናቸው። ስለዚህም ይቀበላቸዋል የዘመናችን የስሕተት ሃይማኖቶች ሁሉ የዚህን መግለጫ እውነትነት ያረጋግጣሉ።ያልዳነ ሰው ምንም እንኳ "በሰባዊ ጥበብ‚ ሁሉ የሰለጠነና ሃይማኖተኛ ቢሆን ለወንጌል የታወረ ነው 2ቆሮ 4፥3። ይህ ሰው የ እምነት አንቀጽ አውጣ ቢባል "የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገሮች‚ የሚገልጠውን የመስቀሉን ነገር እውነተኛ ትርጉም በመዝለል ከመሠረታዊው ትምህርት ለየት ያለ "አዲስ ትምህርተ መለኮት‚ ያወጣል። የመስቀሉ የኃጢአት መስዋእት ምትክነት ለእርሱ "ሞኝነት‚ ነው። "ፍጥረታዊ ሰው‚ እንደመሆኑ መጠን ውስንነቱ እንዲህ እንዲሆን ያስገድደዋል። ሰብአዊ ጥበብ ሊረዳው አይችልም ምክንያቱም "ሰው በጥበቡ እግዚአብሔርን አያውቅምና‚ በሌላ በኩል ደግሞ "የእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ‚ ለተቀበለው ሰው ወሰን የሌላቸው "የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች‚ እንዲያው (በነጻ)ተሰጥቶታል። ስለዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ መንፈስ ቅዱስን ስለተቀበለ ሰማያዊዉን መገለጥ ሊማር ይችላል። የተማረ አእምሮ በጣም ይረዳል ይባል ይሆናል፤ ነገር ግን በውስጥ ያለው መምህር (መንፈስ ቅዱስ) ካልኖረ የተገለጡትን የ እግዚአብሔር ነገሮች መንፈሳዊ ትርጉም ለመረዳት የሰለጠነ አእምሮ ምንም ለማድረግ አይቻልም።
   ሰው "በዚህች ዓለም ጥበብ‚ እጅግ ስለመጠቀ በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ የሚያቀርባቸው አስተያየቶች ጠቀሜታ ይኖራቸዋልየሚለው ግምት አያሌ ክፉ ነገር ፈጥሯል። "ፍጥረታዊው ሰው‚ በዚያ ሁሉ እውቀቱና ቅንነቱ በመንፈስ የሚገለጡ ነገሮችን የሚያያቸው እንደ "ሞኝነት‚ ነው። ሳይንሳዊ እውቀት ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ትክክለኛ ዝምድና ያለውንና በውስጥ የሚኖርን መንፈስ ሊተካ አይችልም። ያለ መንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደት አይኖርም "የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች‚ አይታወቁም። ዳግም ያልተወለደ አንድ አስተማሪ አስፈላጊዎቹ የደኅንነት እውነቶች ያሉበትን የእግዚአብሔር ቃል በገሃድ አልቀበልም ካለ እነዚህ እውነቶች ባብዛኛው በተማሪው እንደ ዋጋ ቢስ በመቆጠር ይጣላሉ። የዘመናችን የዩንቭርስቲዎችና የኮሌጆች ተማሪዎች የጎላ ስሕተት ነህ ነው።
   በአንድ ወይም በብዙ ሰብአዊ የእውቀት ዘርፎች ጥልቅ እውቀት ያለው አስተማሪ ወይም ሰባኪ ከዚያ እውቀቱ የተነሣ ተመጣጣኝ ተመጣጣኝ በሆነ ችሎታ መንፈሳዊ ነገሮችንም ማስተዋል ይችላል የሚል አጠቃላይ አሳብ አለ። ይህ ስሕተት ነው። አንድ ዳግም ያልተወለደ (ደግሞስ ዳግም ካልተወለደ ሰው በቀር የዳግም የዳም ልደትን መሠረትና እውነታ የሚክድ ማን አለ?)፤ ሁልጊዜም ቢሆን በጣም ቀላል የሆኑትን የመገለጥ እውነቶች መቀበልና ማወቅ ይሰነዋል። ለፍጥረታዊው ሰው እግዚአብሔር እውን አይደለም "በአስተሳሰቡም እግዚአብሔር የለም‚ ስለዚህ ያልዳነ ሰው ከተፈጥሮ በላይ የሆነበትን ነገር ወዲያ እንዲጥል የሚያስገድድ ጭንቅና ሸክም አለበት። የዓለማችን አፈጣጠር አስመልክቶ ላለው ጥያቄ የሚያገኘው ብቸኛ መልስ መሠረት የለሽ የሆነው የአዝጋሚ ለውጥ ፅንሰ-ሐሳብ ነው። ዳግም ለተወለደ ሰው ግን እግዚአብሔር እውነት ነው። እግዚአብሔር ፈጣሪና የሁሉ ጌታ መሆኑን ስለሚያምንም እርካታና ዕረፍት አለው።
  የእግዚአብሔርን ነገሮች የመቀበያና የማወቂያ ችሎታ በትምህርት አይገኝም። ያልተማሩ ብዙዎች ይህ ችሎታ ሲኖራቸው ብዙዎች የተማሩ ግን የላቸውም። ይህ ችሎታ በውስጣችን ከሚኖረው መንፈስ ቅዱስ የሚፈጠር ነው። ይህ ችሎታ በውስጣችን ከሚኖረው ከመንፈስ ቅዱስ የሚፈጠር ነው። ለዚህም ነው ከ እግዚአብሔር እንዲያው የተሰጧቸው ነገሮች ያውቁ ዘንድ ለዳኑት መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው። ያም ቢሆን ከክርስቲያኖችም መካከል አንዳዶቹ ከሥጋዊነታቸው የተነሣ ውስኖች ሆነው ይኖራሉ። ካለማወቅ ሳይሆን በሥጋዊነት ምክንያት እነዚህ ሰዎች ጠንካራ ምግብ ሊመገቡ አይችሉም።
  ያልዳኑትን በተመለከተ በመለኮት ዘንድ ምንም ልዩነት አልተደረገም። ሁሉም "ፍጥረታውያን‚ ተብለዋል። የዳኑትን በተመለከተ ግን ሁለት ደረጃዎች አሉ። በክፍለ-ምንባባችን "መንፈሳዊው‚ ሰው ከ"ሥጋዊው‚ ሰው በፊት 1ቆሮ 3፥1-3 በመጠቀሱ ካልዳነው ሰው ጋር በቀጥታ ይነጻጸራል። ይህ ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም "መንፈሳዊ‚ ሰው መለኮታዊ አላማ ነው። "መንፈሳዊ ሰው‚ 1ቆሮ 2፥15። መሆን ከክርስቲያን የሚጠበቅ ነው። ሆኖም "መንፈሳዊ ሰው‚ መሆን በክርስቲያኖች ዘንድ የተለመደ ነገር አይደለም። በአንጻሩ ደግሞ "ሥጋዊ‚ ሰው አለ። ይህን በሚቀጥለው ጽሑፍ እናየዋለን።
ሥጋዊ ሰው፦ ይቀጥላል--- ከዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተወስደ  


2 comments:

  1. ምንግዜም ግብራችሁ ፕሮቴስታንታዊ ስለሆነ ምንጫችሁም በኩር ከሆኑ መናፍቃን ነው ጥቂት ሥለዚህ ሰው Lewis Sperry Chafer (February 27, 1871 – August 22, 1952) was an American theologian. He founded and served as the first president of Dallas Theological Seminary, and was an influential proponent of Christian Dispensationalism in the early 20th century.

    ReplyDelete
  2. Aba selama we thank you for your good information

    ReplyDelete