Thursday, June 25, 2015

የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊ የሆኑት የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ሕንጻ አሰሪ ዕቃ ግዢና ሰንበት ት/ቤት ሊቀመንበር ጥፋታቸውን አመኑበደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በሙስና ቅሌት ምክንያት የተነሳው ውዝግብ ተካሮ ቀጥሏል፡፡ የደብሩ አስተዳደር ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ለሀገረ ስብከቱና ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት ችግሩን በማሳወቅ ጭምር የሄደበት አማራጭ በመጨረሻ ላይ ውጤት እያስገኘለት መጥቷል፡፡ በቀን 12/10/2007 ዓ.ም በወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት፦ የደብሩ አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የህግ ክፍል ተወካዮች፣ የህንጻና ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች የወረዳው የፍትህ ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ እስካሁን ሲያድበሰብሱ የቆዩትን የሙስና ወንጀሎች አምነዋል፡፡ በቅድሚያ የህንጻ አሰሪው ዕቃ ግዢ የሆነው አቶ በለጠ ደሳለኝ (ጉዳ) በራሱ አንደበት ከዚህ ቀደም የዘገብነውን ለደብሩ በስጦታ የተገኘውን ባለአንድ ፎቅ ቤት በ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር መሸጡን አምኗል፡፡ እንዴት ተሸጠ? ለማን ተሸጠ? የሚሉት የህግ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ የሚያገኙ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ስጦታውን ካበረከቱት ወገኖች እጅ ካርታውን የተረከበው እስጢፋኖስ ኃይሉ ነው፡፡ 

ከሀገረ ስብከቱ የተወከሉት አፈ መምህር ይህን ሲሰሙ ከመገረም አልፈው እንዲህ ዓይነቱ ትልቅ ስጦታ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስና ስራ አስኪያጅ ሳያውቁ መሸጥ እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን እንኳን ለእነዚህ አካላት ሊያሳውቁ ከደብሩ አስተዳደር ደብቀው በህገወጥ መንገድ መሸጣቸው አሳዝኗል፡፡ የሚገርመው ይህን አሻጥር የሕንጻ አሰሪው ሊቀመንበር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተገኑ እንዴትና ለማን እንደተሰጠ አላውቅም በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴው ሥእል የማሳሉን ጉዳይም ለሌላ ተግባር ለማዋል አስቦት እንደነበረ ጭምር ተናዟል፡፡

ሌላው የደብሩ ሰ/ት/ቤት አመራር ተወጥረው ስለተያዙ ለጥቁር አንበሳ ሰጠን ያሉት 75 ሺህ ብር ለደብሩ በእጅ የተጻፈና ማሕተም ብቻ ያረፈበት ደብዳቤ በመስጠት ብሩን በአካባቢው ለሚገኙ ነዳያን በነፍስ ወከፍ ማደላቸውን ገልጠዋል፡፡ ይህም ብዙዎችን አስቋል፡፡ በፊት ለጥቁር አንበሳ ሰጠን ሲሉ እንዳልነበር አሁን ግን ለነዳያን ነው ብለውት አረፉ፡፡ ሆስፒታሉ መጠየቁ ስለማይቀር ያን ተከትሎ ከሚመጣባቸው መዘዝ ለማምለጥ የፈጠሩት ዘዴ ነው፡፡

በዚሁ ስብሰባ ላይ ጉዳዩን አቅጣጫ ለማስለወጥ ደብሩን ለመናፍቃን አሳልፈን አንሰጥም ብሎ ሲፎክር የነበረው አቶ ይድነቃቸው የእርሱን ጉድ ለመሸፈን በሚል አስጸያፊ ስድብ ተሳድቦ የነበረ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ በድርጊቱ መጸጸቱን ለፍትህ አካላቱ ገልጿል፡፡

በዚሁ ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎችን በእጅጉ ያሳቀው ሌላው ክስተት ጉዳዩ ሙስና ሆኖ እያለ የሃይማኖት ለማስመሰል  እገሌ ይወገዝልን የሚል አቤቱታ የያዘ ለዚያውም የአንድ ቤተሰብ አባላት ማለትም አቶ ሙሉዓለም፣ ሚስታቸውን ጨምሮ እቤት የሚውሉ 3 ሴቶች እና 2 ወንዶች የሰንበት ተማሪዎች እና አንድ ጫት ቃሚ ወንድማቸውን ጨምሮ የቤተሰቡ አባላትን ስምና ፊርማ የያዘ ወረቀት ሲቀርብ ሁሉም በሳቅ ሞቷል፡፡ እንዲህ ያለው ጥያቄ የሙስናው ጉዳይ እየታየ ባለበት ሰዓት መቅረቡ ማቅ “ተሐድሶ መናፍቅ” የሚለውን ዕድሜ ማራዘሚያውንና የመጫወቻ ካርዱን ሁሌ እንዲህ ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባና አቅጣጫ ማስቀየሪያ ሲፈልግ የሚጠቀምበት ስልት መሆኑን አስመስክሮበታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንኳን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየመጣ ያለውን ለውጥ ተከትሎ በለውጡ ጥቅሜ ተነካ ብሎ ስላሰበ ተሐድሶ መናፍቅ ማለቱን ቀጥሏል፡፡ የራሱን አማሳኞች እንደጻድቃን ቆጥሮ ዝም ሲል በሚቃወሙት ላይ ግን ይህን ስም እየለጠፈ አገር ይያዝልኝ እያለ ነው፡፡

ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ከህግ ክፍል ተወክለው የመጡ አባት የሲኖዶሱን ክብር በመግለጽ ሲኖዶስ ያላወገዘውን ሰው ማንም እየተነሳ ተሐድሶ መናፍቅ የማለት አቅም መብትና ሥልጣን እንደሌለው አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም የአቶ ሙሉዓለም ቤተሰብ ለማይመለከተው አካል የቀረበ የውግዘት ጥያቄ በፈገግታ ታልፏል፡፡

ሌላው አስገራሚ ነገር በዚሁ ስብሰባ ላይ አሁን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለማተራመስና 25ሺህ ወጣቶችን ሰልፍ አስወጥተን እንቃወማለን ብሎ በቋሚ ሲኖዶስ ፊት የተናገረውና ማቅ ተቃውሞን እንዲያደራጅለት በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ስም የሾመውና ተልእኮ የሠጠው ሄኖክ አስራትን አለ ደብሩ በዚህ ስብሰባ ላይ አስርገው በማስገባት ከደብሩ አስተዳደር በኩል የቀረበውን እውነት ማስተባበል ተስኖት አንድም ቃል ትንፍሽ ሳይል በመጣበት እግሩ ተመልሶ ሄዷል፡፡ ሄኖክ አስራት በጆሮው የማቅ አባላትና ደጋፊዎች በዘረፋ መሰማራታቸውን እንዳመኑ ሲሰማ ምን ተሰምቶት ይሆን? ለዚህስ ጉዳይ እንደተለመደው ዩኒፎርም አስለብሶ ለአመፅ ያደራጃቸውን ወጣቶች መቼ ይሆን ይዞ የሚወጣው? የሚለው ያጓጓል፡፡ ሄኖክ አስራት ማቅን የሚቃወሙትን በተለይ ማቅን ስለተቃወሙት ብቻ አማሳኝ ለማለት የሚቀድመው እንደሌለ ከዚህ ቀደም ታዝበናል፡፡ አሁን እነዚህን በማስረጃ የተደገፈ ሙስና የፈጸሙትንና ጥፋታቸውንም ያመኑትን አማሳኞች ጉዳይ በጆሮው ሰምቶ ምን ይል ይሆን? 

በአጠቃላይ በሙስናው የተዘፈቁትና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሲንቀሳቀሱ የቆዩት አማሳኞች አፍረውና አንገት ደፍተው ጉዳያቸው ወደፊት የሚታይ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ አሁን እያደረጉ ያሉትን ሁከት ቀስቃሽ ተግባር እንዲያቆሙ ከከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡ 

የቤተ ክህነቱ ተወካይም ሆኑ የፍትሕ አካላቱ ጉዳዩን በተገቢው መንገድ የተመለከቱት መሆኑ ደስ ያሰኛል፡፡ በደብሩ አስተዳደር በኩልም ማንም አይደርስበትም ብለው እንደ ልባቸው ሲፋንኑ የነበሩትን እንዲህ ባጭር ጊዜ ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ መደረጉ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ መሆኑንና ጽዋው ሲሞላ ማንም ከፍትሁ እንደማያመልጥ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ በሌሎችም ደብሮች ተመሳሳይ ተግባር እየፈጸሙ ያሉ ወደልባቸው እንዲመለሱና ንስሐ እንዲገቡ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ እግዚአብሔር በቤቱ ውስጥ ፍትሕ ሲዛባ እውነት በሐሰት ስትተካ ዝርፊያና ቅሚያ ሲሰለጥን እውነተኞች ሲገፉና ቀማኞችና ሐሰተኞች ሲፋንኑ ዝም ብሎ አያይም ይፈርዳል፡፡ ስለዚህ ያ ከመሆኑ በፊት በተሰጠን የንስሓ እድል እየተጠቀምን ከክፉው መንገድ እግራችንን ብንመለስ መልካም ነው፡፡ ደብሩ እዚህ ያደረሰውን ጉዳይ ሀገረ ስብከቱ ግለሰቦቹ በሕግ ተጠያቂ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት፡፡
ደብዳቤውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ 

5 comments:

 1. አባ ሰላማዎች ስለምትሰጡን መረጃ በጣም እናመሰግናለን በርቱልን እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን

  ReplyDelete
 2. ይህን ቤተክርስቲያን አውቀዋለሁ የመሀል ሀገር የሆኑ ካ ህናትን ና የሰበካ ጉባዔ አባላት ብቻቸውን መያዝ የሚፈልጉት ጠብ ና የደጀ ሰላም እንጀራ ሁል ጊዜም የማይጠፋበት ነው ።

  ReplyDelete
 3. ወይ ግሩም ተደንቄም አላባራሁ

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች ሰላም እግዚአብሄር ይደረሳችሁ
  አንባብያን መረዳት ማወቅ ያለባቸው ቤተክርስቲያን / ብእንተ እለወሀቡነ ምጽዋተ / እያለች ለምእመናንዋ ጤንነትና ሰላም በጸለየችበት ማህበረ ቅዱሳን በሚባለው ያረጀ ፖለቲካ አቀንቃኝ ማህበር አባል የሆኑትን ሁሉ ሳይሆን በማህብረ ቅዱሳን አመራርነት ያሉት ጥቂጦቹ ቤተክርስቲያንዋን እነደ ጃንጥላ ተጠቅመው ከህግ ተደብቀው ግብር ሳይከፍሉ በንግድ ሥራ ላይ መሰማራት ብቻ ሳይሆን ለካህናት የተፈቀደውን የቤተክርስቲያን አስራት፤ቀዳሜያት፤ አስተዋጽኦ ፤እጣን ጣፍ ሽያጭ፤ የመጻህፍት ሕትመት ሽያጭ እና የመሳሰሉትን ገቢዎች ለራሳቸው ማድረጋቸው /ዳዊት የተራበ ግዜ የካህናት መግብ በላ ይላል ስለተራበ እነዚህ ምሁራን ተርበው ነው ፡፡የተማርንነን ይላሉ የተማረ ደግሞ አማርጦ በመንግስትም በግልም በከፍተኛ ደመወዝ ሊቀጠር ይችላል ግን የስረርቆት ያህል አይሆንም ለቤተክርስቲያን ተብለው በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት የጠቀመጡት ብጹእ ጠቀላይ ሥራ አስኪያጅም ለዚህ መአርግ ካበቃቻቸው ከቤተክርስቲያናቸው ይልቅ ላረጀ ፖለቲካ የሚቀነቅነውን ማቅን ይሻለኛል ብለው ለቤተክርስቲያንዋ መቆም አቅቶአቸው ለባናዳዎች አድረው የበተክርስቲያንዋ ሀብትና ክብር ለወንበዴዎች አሳልፈው ሰጥተው ይኖራሉ ጎንደር ሀገረ ስብከት 4ሚሊዮን ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት 5ሚልዮን ለቤተክህነቱ ሲያስጋበ በቂ አይደለም አንሶዋል ይላሉ ማቆች የቤተክርስቲያን አካል ከሆኑ ስንት አስገቡ ይህ አልበቃ ብሎአቸው ይቅርታ ይደረግልኝ አባባል ነው /ዕውር ሲጠግብ ከመሪው ይጣላል / እንደሚባል የማቅን ግልጽን ስውር ደባ ችለው በየአድባራቱ ሉት አስተዳደሪዎች ለሀገረ ስብከቱ በሚያስገቡት 20 ከመቶ ኑሮአቸው ተንጠላጥሎ መልሰው ቀላቢዎቻቸውን ሙሰኛ ይሉአቸዋል ለዚህም ቤት አለው መኪና አለው ነው ማስረጃው ለቤትማ ዘመናዊ ሕንጻ አስገንብተው ዘመናዊ መኪና የሚነዱት የማህበራ አባወራዎች ከሰማይ በወረደ ገንዘብ ነው ይገርማል ሌቦችን ጻድቆች ጻድቆችን ይህ ባባል ቢከብድም ሌቦች እያሉ ሌብነታቸው ከሚደብቁ ሒሳባቸውን ያሳውቁ እየተሰደቡ ያት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳደሪዎች ፐርሰንት በመክፈል ለጠቅላይ ቤተክህነቱ የጀርባ ድጋፍ ሆነዋል ከዚህ በኃላግን አባ ማቴዎስ ዱላ ይዘው ያስከፍሉ እንደሆነ ይታያል ላለመክፈል በአንድ ቀን ይወስናሉ ሀብታሙ የ20 ካቴድራሎች ያህል ገቢ ያለው ማቅ ምንም ሳይከፍል ለምን / ማቆች ለጠቅላይ ቤተክህነቱ የሚክፈልት ገንዘብ አለዎይ
  ልብ በሉ ለጠቅላይ ቤተክህነት ፐርሰንት ባይከፍሉም ለአባ ማቴዎስና ለአባ ቀሌሚንጦስ እንዲሁም በ50 እና ስልሳ አመታቸው ወጣት በማለት ስነተፈጥሮን የሚቃወሙ እንደብራና ጭንቅላታቸው የተፋቀው የ50 እና 60 ዓመታ አዛውንት የሰንበት ት/ቤት አመራሮች ግን ባዮች ግን ከማቅ በገፍ የሚከፈላቸው ስራ ፈት ናቸው ከየት የመጣ ገንዘብ ነው መንግስት የማይወቀው ቤተክህነት የማይመረምረው ሒሳብ እንዴት ነው የቤተክርስቲያን ማህበር የሚሆነው አሁን አሁን ደግሞ አባሎቻቸውን በየአድባራቱ በሊቀመንበርነት በህናጻ አሰሪነት በተራ ሰበካ ጉባኤ አባልነት በማስመረጥ በዘረፋ ላይ ለመሳማራታቸው የደብረ ሲና እግዚአብሄር ጉዳይ ፤የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል የሰበካ ጉባ አባልና በ50አመቱ የሰንበት ተማሪ ነኝ የሚለው ኮርማው አቶ ዮናስ የደብረ ሲናው ዮናስ ማሳያዎች ናቸው ስለሆነም የማህበረ ቅዱሳን ሒሳብ ይመርመር ይታወቅ ሳይመረመር ሳይታወቅ እንዲሁ ከቀጠለ ግን የዛሬዎች አክራሪ የአይ ኤስ ኤስ ጽንፈኞች ፤ አልቃይዳና ሌሎችም በዚሁ የጀመሩ ናቸው ስለዚህ ዘመናዊ ሂሳብ ስለምንጠቀም ቤተክህነት ሊመረምረን አይገባም የሚለው የጅል ንግግር ይቁም ሐቲአታቸውን በጽድቅ ዘራፊነታቸውን በመጽዋችነት ፖለቲካዊነታቸውን በክርስቲናዊነት እየቀየሩ ቤብሎጉ የሚጽፉላቸውን እንደ እና አቶ አሉላ ጽጉራሙ አውሬ የመሳሰሉ ቢጸ ሀሳውያንም ወደ ህሊናቸው እንዲመለሱ እግዚአብር ልብ ይስጣቸው

  ReplyDelete
 5. Aba selamawoch selam yebzalachu ! betechalachu akem sele mahebere kedusan metefo gon be batri endemetefelegu gelts new mechem ! waga kefayoche enante satehonu weyem yenante aseteyayet mizan lay sayekemet kulalite ena leben yemimeremerew Cheru MEDHANIYALEM new ena temesgen new ! ene ye mahebere kedusanem yenantem abal adelehum ! kefuna degun gen eyeleyew ehedalew enji kemanem ga wegenge alenagerem . Mahebere kedusan gen ye Aserat genzeb ayekebelem . maheber kedusan yemitedaderew be waneganet Abalatu ke gebiyachew lay 2% bemkefel ( Aserat be kurat wechi ) Aserat be kuratachewen le betecherestiyan bekefel sihon lelaw be setota be miyagengewe ena andand gebi masgenga serawochen be meserat new ! be mahbere kedusan amakangenet demo sent yeteresu yegeter Betekrestiyanoch gedamat endeteredu ye Abenet temehert betoch endayebetenu demoz le Astemariwoch eyekefelu le betechrestiyan Gizeyachewen eweketachewen Hiwetachewen chemer mulu le mulu eyesetu EGEZIABHEREN endemiyagelegelu enakalen ! sehtet demo ke sew ayetefam ena yehenen baneresa teru new . Yehuda eko ye Geta dekemezmur hono Leba neber !selezi kefun endemtaganenu andande melkamunem batersu betamsegenu teru new ! beseferut kuna mesefer ayekeremena ! yeleke sele Ashenafi Mekonen ebakachu zm atebelu ! beteley bewech yalu sewoch sebeketun becha eyesemu endayetalelu ! ene beweche yemenor ejeg adenakiw neberkunge !! betam ataly sew new ! ebakachu sewoch ketetalelu buhala krestenan erem belew endayetewu yehone neger medereg alebet ! Tebareku !

  ReplyDelete