Thursday, June 18, 2015

የመጽሐፍ ቅዱስና የመልክአ ሚካኤል አለመግባባትመጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አሳሳቢነት በቅዱሳን አባቶች የተጻፉ የእግዚአብሔር መልእክትናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታቀፉ እና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የሃይማኖትማስተማሪያ ሆነው የኖሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድሳ ስድስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት መመሪያዎችግን ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ናቸው። የአንድ ሰው ሃይማኖቱ ትክክለኛነት ተመዝኖ ሊወገዝምሆነ ሊመሰገን የሚችለው በነዚህ መጻሕፍት መሠረት ነው። ነገር ግን በአሁኑ ዘመን በቤተክርስቲያናችን በቀኖና የማይታወቁና  ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ውጭ የሆኑ መጻሕፍት በቤተክርስቲያናችን ስም ወደ ሕዝብና አገልጋዮች ሾልከው ገብተው ቦታውን በመቆጣጠር፣ በአገሪቱመጽሐፍ ቅዱስ የሌለ እስኪመስል ድረስ ውሸታቸውን አጋነው በማቅረብ አገሪቱን በክለዋል።


መልክዐ ሚካኤል የሚባለው ድርሰት በአጼ ዘራአ ያዕቆብ ዘመን እንደተደርሰ ይገመታል፣መጽሐፉ በየወሩ የሚካኤል ማህሌት በሚቆሙ የቤተ ክርስቲያችን ተቀጣሪዎች በየተራበቅብብሎሽ እየተዜመ ሚካኤል የሚመለክበት፣ የሚመሰገንበት ድርሰት ነው። ይህን መጽሐፍሁልጊዜ በመድገም ወደ ሚካኤል የሚጸልዩ ምእመናንና ደብተራዎች በርካታ ናቸው።የሚካኤል በአል ሲሆን ካህናቱ ሌሊቱን ሙሉ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ ዚቅ የሚባለውን ሌላድርሰት ጨምረውበት ሲዘሉበት የሚያድሩት ይህን ድርሰት ነው። ምእመናን ግን ይህን በቤተክርስቲያን እና በእግዚብሔር ላይ ሲካሔድ የሚያድረውን አመጽ ስለማያውቁ ካህናቱ ረጅምሌሊት ሲጸልዩ በማደራቸው ይደክማቸዋልና ምርጥ ምርጡን፥ ቁርጥ ቁርጡን እንጋብዛቸውበረከታቸውን እንካፈል እያሉ ይሽቀዳደማሉ። በነገው ዕለት በሚከበረው የህዳር ሚካኤል ወደአንዱ ቤተ ክርስቲያን ጎራ በማለት ይህን ድርሰት ማዳመጥ የሚቻል መሆኑን ሳንጠቁምአናልፍም። ነገር ግን በግዕዝ ብቻ ስለሚባል እግዚብሔር እና እነሱ ብቻ ናቸው የሚሰሙትናላይገባችሁ ይችላል። ለሁሉም በመልክአ ሚካኤል እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ያለውንአለመግባባት እንዲህ አቅርበነዋል።


ከመልካ ሚካኤል፦


ሰላም ላአእዛኒከ እለ ያጸምአ ንባበ፣
ወጸሎተ ኩሉ ዘተመንደበ፣
ሚካኤል አቅልል እምላእሌየ እጸበ፣
ከመ ትመአድኒ ውትምህረኒ ጥበበ፣
ረስየኒ ወልደ ርሰይኩከ አበ፤

ትርጉሙ፦

ለጆሮዎችህ ሰላምታ አቀርቫለሁ፤
የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልመናን ያዳምጣሉ፣
ሚካኤል ሆይ ችግሬን አቅልልኝ፣
ምከረኝ እውቀትንም አስተምረኝ፤
አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ፤

ይህ ለሚካኤል የቀረበ ጸሎት እና ምልጃ ቤተ ክርስቲያናችን በተቀበልችው ሰማኒያ አንድመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም ወይንም ይህን ሐሳብ የሚደግፍ ንባብ የለም። ቅዱሳንአባቶቻችን ጸሎታቸውን ያቀረቡት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላእክት አልነበረም። ወደመላእክት ጸሎት ያቀረበ የእግዚአብሔር ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም። የኛደብተራዎች ግን ሚካኤልን እናነግሳለን በሚል ፈሊጥ እግዚአብሔርን ሲያስቀኑ እያደሩየእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊመስሉ ይሞክራሉ። ሚካኤል የእግዚአብሔር ክቡር መልአክአገልጋይና ተላላኪ የመላእክት አለቃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ይህን ማንምአይክድም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማና ጸሎትም ወደ እርሱ መቅረብ እንዳለበት የሚናገርክፍል ፈጽሞ የለም። ደብተራዎች ለሚካኤል የሰጡትን ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማንእንደተሰጠ እንመልከት፤

መጽሐፍ ቅዱስ፦

«ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» መዝ 65፥2 እግዚብሔር በዓለምምሉዕ በመሆኑ የሥጋን ሁሉ ጸሎት መስማት ይችላል። ቁራዎች እንኳ ወደ እግዚአብሔር ከጮኹ ያገሬ ሰዎች ምን ነካቸውና ነው ወደ ሌላ የሚጮኹት? ወይስ ያክብሮት ጩኸት ነው?

ታዲያ መነፍቃን ደብተራዎች «የተቸገረን ሁሉ ጸሎት የምትሰማ» በማለት ለሚካኤል የሰጡትከምን አምጥተውት ነው? ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን ሕዝብ በዚህ ክህደት እንዲተባበርየሚደረገውስ ለምንድን ነው? «ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» ሲልየኢትዮጵያን ሕዝብ አይጨምርምን? ሥጋ ሁሉ ካለ ኃጥአንም ሆኑ ጻድቃን ወደ እግዚአብሔርመጸለይ እንዳለባቸው የሚናገር አይደለምን? እንስሳት እንኳ ወደ ማን ማንጋጠጥእንዳለባቸው የሚያውቁ መሆኑን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል።

«እጓለ አንብስት ይጥህሩ ወይመስጡ ወይስእሉ ኀበ እግዚአብሔር ሲሳዮሙ»

«የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮሃሉ፣ ምግባቸውንም ከእግዚአብሔር ይለምናሉ» መዝ103፥21።

«ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጭቶች ለእንስሳትም ምግባቸውን ይሰጣል» መዝ 147፥9


በጣም ትናንሽ የሆኑ የቁራ ጫጭቶች እግዚአብሔርን እንደሚጠሩ በዚህ ቃል ይታወቃል።በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረው ያገሬ ደብተራ ግን ወደ ሚካኤል በመጸለይ የአምልኮዝሙት ይፈጽማል። ይህ እጅግ ያሳዝናል። ችግሬን አቅልልኝ መባል ያለበት እግዚአብሔርነው። ዳዊት «ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም» ብሏል። ችግርን ወደእግዚአብሔር ማቅረብ መፍትሔን ያስገኛል። ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ሲላክ ብቻተልኮውን ይፈጽማል እንጂ እኛ ወደ እርሱ ስለጸለይን ደስተኛ አይሆንም ያለ እግዚአብሔርምፈቃድ አንዳች ነገር ሊያደርግ ይችልም።

«በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ» መዝ 119፥66።

ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ምክርንና እውቀትንይሰጣል፤ እርሱ ልብና ኩላሊትን ይመረምራል፣ ለሁሉም የሚያስፈልገውን ያውቃል፣ ሶሎሞን«ማስተዋልን ስጠኝ» በማለት የለመነው እግዚአብሔርን ነው። የኢትዮጵያ ደብተራዎች ግንየእግዚአብሔርን መለኮታዊ ሥራ ለፍጡር በመስጠት «ሚካኤል ሆይ ምከረኝ እውቀትንአስተምረኝ» እያሉ ወደ ሚካኤል ሲጮሁ ያድራሉ። ሚካኤል ግን ከእግዚአብሔር ሲላክየእግዚአብሔርን ምክር ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያስተምርና ሊናገር ይችላል።በዳንኤል እንደተጻፈው የእግዚአብሔርን ምሥጢር መላእክት ይናገራሉ። ሆኖም ግን ዳንኤልየጸለየው ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላኩ አልነበረም፤ ይህን እራሱ መላኩ እንዲህ ሲልያረጋጣል፦

«እነሆም አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጉልበቴና በእጄም አቆመችኝ። እርሱም እጅግ የተወደድህሰው ዳንኤል ሆይ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል ቀጥ ብለህምቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፣ዳንኤል ሆይ አትፍራ፣ ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቷል እኔም ስለቃልህ መጥቻለሁ» ዳን10፥10-12።

«እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁ»  የሚለው ቃል የመላኩን ዋና ሥራ ያመለክታል፣ «ልብህያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደርግህበት ቀን ጀምሮ»የሚለው ዳንኤል በአምላኩ ፊት እንጂ በመላኩ ፊት አለመውደቁን ያመለክታል። «ቃልህተሰምቷል ስለቃልህ መጥቻለሁ» የሚለው ደግሞ የዳንኤል ጽሎት በጌታ ዘንድ መሰማቱን እናመልሱ በመላኩ እጅ መምጣቱን ይናገራል። እናም ሰው መጸለይ ያለበት ወደ እግዚአብሔርእንጂ ወደ መልክተኛው መሆን የለበትም። ዛሬ ደብተራዎች በቤተ ክርስቲያችን ገብተውበጉልበት የሚያደርጉት ባዕድ አምልኮ ከሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ውጭ ነው።

«አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ»


በዚህ የደብተራዎች አባባል አባታቸው ሚካኤል እንጂ እግዚብሔር አይደለም። እንዲህ ባለእምነት ግን ክርስቲያን ሊሆን አይሞከርም። ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመንየእግዚብሔር ልጆች ናቸው።

«ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድሥልጣንን ሰጣቸው እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከወንድ ወይም ከሥጋ ፈቃድአልተወለዱም» ዮሐ 1፥12-13

«አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና» ማቴ 23፥9

አንድ ሰው ከሁለት አባት ሊወለድ እንደማይችል ሁሉ ክርስቲኖችም አባታቸው አንዱ እርሱምየሰማዩ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት አብ ነው። ከመንፈስና ከውሃ ዳግም የተወለድንሁሉ አባታችን አንድ ነው፤ እርሱም መንፈስ ስለሆነ በመንፈስ ወልዶናል። ታዲያ መናፍቃንደብተራዎች ሁለተኛውን አባት ከየት አመጡት? እንዴትስ ወለዳቸው?  መጽሐፍ ቅዱስሚካኤል አገልጋይና ከኛ ጋር አብሮ የእግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን ይናገራል እንጂየክርስቲያኖች አባት መሆኑን አይናገርም።

«ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋርየኢየሱስም ምሥክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ..አለኝ»  ራእይ 19፥10

በምድር ላይ በመንፈሳዊ ምክር ያሳደጉንን የምናውቃቸውን ቀሳውስትን አባቶች እንላቸዋለን።ይህ ከነርሱ ጋር ስለምንተዋወቅ  ምንም ነውር አይኖረውም ምክንያቱም እነሩሱን[ቀሳውስትን]ስለመንፈሳዊ ሕይወታችን እናማክራቸዋለን እንጂ ወደ እነርሱ እየጸለይን አንሰግድላቸውም።

በሰማይ የሚኖሩ መናፍስትን አባት እያሉ መጥራት መጸለይና መስገድ ግን ባዕድ አምልኮስለሆነ ቅዱሳን የሆኑ መላእክትም አይቀበሉትም። ትሑቱ ሚካኤል «እንዳታደርገውተጠንቀቅ» ይላል እንጂ፤ አይቀበለውም።

አንዳድ ደብተራዎች በተለኮሰው የወንጌል እሳት ምክንያት ማስተዋል ጀምረዋል። አሁንየሚካኤልን ታቦት እናነግሣለን እያሉ ሕዝብ እንዲሰበሰብ የሚያደርጉት ያመት ቀለባቸውንለመሰብሰብ የሚሠሩት ድራማ እንጂ እውነት እንደዚህ ከሐዋርያት እምነትና ሥርዓት ውጭበሆነ ልምምድ ሚካኤልን ለማንገሥ እየሞከሩ አለመሆኑን አውቀውታል። ይህን ምሥጢረገንዘብ የማያውቁ ምእመናን ግን እጅግ ያሳዝናሉ፤ የሚያደርጉትን አያስተውሉምና አምላካችንይግለጥላቸው።

ማንገሥ ምንድር ነው?

ማንገሥ መሾም! ይሁን! ይሁን! ይገባዋል ማለት ነው፤ ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ከተሾመእጅግ ብዙ ዘመን አለፈ፤ እርሱ የመላእክት አለቃ እንጂ የሰው ዘር አለቃ አይደለም። በሰውናበመላእክት በፍጥረት ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው በተዋሕዶ የከበረው የድንግል ልጅ የናዝሬቱኢየሱስ ነው። አምልኮ ክብር ምስጋና ለርሱ ይገባዋል። ሚካኤልን «ማንገሥ» ማለት ምንድርነው? « ማምለክ» የምተለዋን ቃል ዘወር አርገው «ማንገሥ» ይላሉ መናፍቃኑእንዳይንቃባቸው የፈጠሩት ይመስላል። ማንገሥ ማምለክ ነው፤ ሌላ ምንም ትርጉም ሊኖረው አይችልም። እልል እየተባለ የሚሰገደው ለሚካኤል ታቦት አይደለምን? ሚካኤልን በአካልእንደ ዮሐንስ ቢገለጥልን በእውነቱ ዝቅ ብለን ተንበርክከን ልንቀበለው እንችላለን፣ ነገር ግንታቦቱ የሚካኤል ነውና እንስገድለት የሚለው አስተሳሰብ ፍጹም ከሰማኒያ አንዱ መጻሕፍትውጭ ነው።

ሌላ መልክአ ሚካኤል፦

ሰላም ለእመትከ ዘይሜጥን ተራድኦ፣
አኮ ሰንዱነ ወአልባሰ ረፍኦ፣
ሚካኤል ኀቤከ አወዩ በአስተቍዖ፣
ከመ ታድኅነኒ ሥመር እግዚኦ፣
እስመ ኩሉ ይትግህ ከመ ያድኅን ሰብኦ፤

ትርጉም፦

እርዳታን ለሚሰጥ ለክንድህ ሰላምታ አቀርባለሁ፣
የበፍታ ልብስም ሆነ የልብስ እራፊ አለምንህም፤
ሚካኤል ሆይ በምልጃ ወደ አንተ እጮሃለሁ፤
አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
ሰው ሁሉ ዘመዱን ለማዳን ይተጋልና፤

በቅዳሴያችን ሰዓት "ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ ሥመር እግዚኦ ከመታድኅነነ” አቤቱታድነን ዘንድ ውደድ አቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ እንላለን መባል የሚገባውም እንዲህ ነው።ደብተራዎች ግን ሚካኤልን «እግዚኦ አቤቱ» ታድነን ዘንድ ውደድ ብለውታል። ደብተራዎችየጌታን ለሚካኤል ይሰጣሉ። ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን? ይህ ባዕድ አምልኮ ያለፈ እናየተተወ ነገር ቢሆን ኖሮ ዝም ባልን ነበር፤ ነገር ግን ዛሬም የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ባለበትእና በበአሉ ቀን የሚባለው እና የሚጸለየው ይህ ስለሆነ ምእመናንን ማንቃት ማስጠንቀቅግዴታ ሆኖብናል።

ለቤተ ክህነቱና ለጳጳሳቱ ስናቀርብ እባካችሁ ዝም በሉ ይህን ሕዝብ ታስገድሉናላችሁ ጊዜይፈታዋል ይሉናል። ማህበረ ቅዱሳንን ይህ መታረም አለበት ስንለው መናፍቅ ናችሁ እያለስማችንን ያጠፋል ከዚያም አልፎ በማጅራት መች ያስደበድበናል። በዚህ ምክንያት ስንት የቤተክርስቲያን ልጆች መከራና ችግር ደርሶባቸዋል! ይህ እልከኝነት ግን ችግር አይፈታም።ስሕተታችንን ብናርም ይሻላል እንጂ ስም ማጥፋቱና ማባረሩ አይበጅም።
ሰላም እብል ለመልክአቲከ ኩሎን፣
በበአስማቲሆን፣
ሚካኤል ሥርግው በልብሰ ብርሃን፣
ሠናይ ተአርኮትከ በኩሉ አዝማን፣
ሠራየ ኃጢአት አንተ አርከ ነፍስ መመን፤

ትርጉም፦

ለመልኮችህ በሙሉ በየስማቸው ሰላም እላለሁ፣
ሚካኤል ሆይ አንተ በብርሃን ልብስ የተሸለምክ ነህ፣
በዘመናት ሁሉ ያንተ ወዳጅንት መልካም ነው፣
የአማኝ ወዳጅህን ነፍስ ኃጢአት የምታስተሠርይ አንተ ነህና፤

ኃጢአትን የሚያስተሥርይ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል የኢየሱስክርስቶስ ደም ኃጢአታችንን ያስተሠርይልናል። ደሙ ለዘላለም ሕያው ነው መለኮት ብቻውንየሚሠራውን የኃጢአት ሥርዬት ሥራ ከሚካኤል መለመን ምን የሚሉት ነው? ይህ ክህደትከቤተ ክርስቲያናችን መነቀል አለበት። ሚካኤልን እያመለኩ ሲያስመልኩ የኖሩ ሰዎችፍርዳቸውን እንደሚያገኙ ባንጠራጠርም ዛሬ ግን በቃችሁ ሊባሉ ይገባል።

ሰላም እብል ለአክናፊከ ስፉሐት፤
ምስካቤ ኩሉ ፍጥረት፣ ሚካኤል ክቡር ሊቀ ካህናት፣
አድህነነ እምዕለት እኪት፣
ወባልሃነ እምኩሉ መንሱት፤

ትርጉም፦

ሰፋፊ ለሆኑ ክንፎችህ ሰላም እላለሁ፣
የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ናቸው፣
ሚካኤል ሆይ አንተ የከበርህ ሊቀ ካህናት ነህ፣
ክፉ ከሆነች ቀን አድነን፣
ከጥፋትም ሁሉ ታደገን፤

የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ እግዚብሔር ነው ወይስ የሚካኤል ክንፍ? ሚካኤል የፍጥረት ሁሉመጠጊያ ከሆነ አምላክ ሆኖአል ማለት ነው። ሁለት አምላክ የለም፤ የፍጥረት ሁሉ መጠጊያእግዚአብሔር ብቻ ነው "ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች ረዳታችንና መጠጊያችንእርሱ ነውና” መዝ 33፥20 ተብሎ ተጽፏልና የእግዚአብሔርን ለሚካኤል አንሰጥም።

ሊቀ ካህናትስ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? "በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠእንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል” የተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ የት ሄዶ ነው ሚካኤል ሊቀካህናት የሆነው? ወይስ የትኛውን መስዋእት አቅርቦ ይሆን? እራሱን ነውን? ወይስ እንስሳትን?መስዋእት ማቅረብ የሊቀ ካህናት ሥራ እንጂ የመላእክት አይደለም። መላእክት ኃጢአትየለባቸውምና መስዋእት ማቅረብ አይጠበቅባቸውም ስለዚህ "ሊቀ ካህናት ካህነ ምስዋዑ”የሚለው ጌታን ብቻ ይመለከታል።

ከክፉ አድነን ብለን መጸለይም ወደ እግዚአብሔር ነው፣ ጌታ "ከክፉ ሁሉ አድነን” ብላችሁጸልዩ ብሎ ሲያስተምረን ወደ ሚካኤል ነውን? ወይስ በሰማይ ወደሚኖረው አባታችን? ይህንጥያቄ አንባቢ ይመልሰው።

ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ሃያ አራት ሰዓት የሚጸልዩ አባቶች አሉን እያለ የሚመካባቸውደብተራዎች የሚጸልዩት ጸሎት ይህን ይመስላል።

ይህን አባባል አሜን ብለን ብንቀበል እንኳ የሚጸለየው ጸሎት ግን ከላይ ያየነውንስለሚመስል ዋጋ የለውም።  የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚጋብዝ እንጂ ኢትዮጵያን ከድህነት፣ከጦርነት፣ ከእርስ በእርስ ንትርክ፣ አውጥቶ ትውልዱን ከስደት የሚያሳርፍ ጸሎት አይደለም።

እንግዲህ በየወሩና በየአመቱ ሚካኤል ሲነግሥ ደብተራዎች ሲዘሉበት የሚያድሩት ማህሌትከዚህ በላይ በጥቂቱ ያየነውን የሚመስል ነው።

ውድ አንባብያን፥ ከዚህ በፊት እንደጠቆምኩት ከላይ ያየናቸው ሰይጣን በየጊዜው ያስገባብን የስህተት ትምህርትች የጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አይደለም። ክቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን አካባቢ ጀምሮ በነገስታቱ ጣልቃ ግብነትና ባልተማሩ ደብተሮች አማካኝነት ሰይጣን ቤተ ክርስቲያናችንን በክሎብናል። እነ አባሰላማ እና ሌሎች ጥንታውያን አባቶች የሰበኳት ክርስትና እንዲህ አይነት መላ ቅጡ የጠፋ ባዕድ አምልኮን ያዘለ አልነበረም።


በዲያቆን ሉሌ

19 comments:

 1. አምላከ ቅዱሳን የክህደት አንደበትህን አጠራር።

  ReplyDelete
 2. ለዲያቢሎስ ዲያቆን ሉሌ
  አቶ ሉሌ፤ የዲያቢሎስ ሎሌ መሆንህን በደንብ አረጋገጥህ። የማታውቀውንና ያልገባህን የእግዚአብሔር አሰራርና ወንጌል( የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል) መክህደት መዝሪያና ለአባትህ ለሳጥናኤል አላማ ማስፈፀሚያ መጠቀምህ የሚጠበቅ ከሰይጣን የተማኸው ነው። አባትህ ሰይጣን የቃሉን ባለቤት እንደፍጡር ሰው ስጋ ለባሽ መሥሎት ቃል እየመዘዘ ክርስቶስን ፈትኖታል። አንተም ለቀቀ ለክ እንደ አሰማሪህ ሰይጣን ቃላት እየመረጥህ የማይጋጭ ማይቃረኑትን በውሸት የሚጋጩ የሚቃረኑ በማሥመሰል እንዳንተው በስጋዊ አይምሮ አሥተሳሰብና ፍላጎት የሚያሔዱ ባገኝ ብለህ የእውነትን መንገድ ለመዋጋት መትጋትህ ማንና የማን መሆንህ ግልፅ ነው። የእግዚአብሐር አሰራርና ቃሉን ለማወቅና ለመረዳዠት ብሎም በእምነት ለመፅናት በመንፈስ ቅዱስ መጎብኘትና የመንፈስ ቅዱስ ገላጭነትን ማግኘት አሥፈላጊ ነው።
  አቶ ሉሌ፦ መዋሸትና ያልሆኑትን እንዲህ ነኝ ማለት የተጣለው የሳጥናኤል መሆኑ የታወቀ ነው። አንተም በሱ ልብ የምትኖርና የምትመላለስ ስለሆን ከቤተክርስቲያን ሳትሆን የሆንህ መሥለህ ውሸትን እየነዛህ እውነትን ለማጥቆር በፅናት ተግተሀል።
  አቶ ሉሌ፦ ለማደናገርና የሐሰት ትምህርትህ እውነት ለማስመሰል ከመዝሙርም ከወንጌልም ጥቂት ቃሎችን ገልፀሃል። ግን በመዝሙር የእግዚአብሔር መላክ በሚፈሩት ዙሪያ እንደሚሰፍርና እንደሚያድናቸውም ተፅፏል። ለምን ይህን አልገለጽኸውም? መልሱ አንድና አንድ ነው። ይኸውም የእግዚአብሔር መላእክትን መፍራት እንደሚገባና ማዳን እንደሚችሉ ስለሚናገር ያንተን ሐሰተኛ ውንጀላ ስለሚያጋልጥ መሆኑ ግልፅ ነው። በተጨማሪም በመፍራት ውስጥ ማክበር አለና ለእግዚአብሔር መላእክት ክብር መሥጠት ተገቢ መሆኑ ሥለሚያሥገነዝብ የአንተ ለምን ክብር ተሰጣቸውና ለምን ተከበሩ ክስ የጠላት የሰይጣን መሆኑ ሥለሚገለጥ ነው። ይህ ብቻ አይደመም። ዳኔልን ያዳነው ( የረዳው)የእግዚአብሔር መላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለማማለድም ሰባ(70) ዘመን የተቆጣሀቸውን እሥራኤልን የማትምራቸው እሥከመቸ ነው ብሎ በልመና ጠይቋል። ታዲያ ለምን አማላጅነትን፤ ማዳንንና መከበርን ለመላእክት ለምን ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ሰጣቸው ብሎ ምቀኝነትና ጠላትነት የሰይጣን መሆኑ የታወቀ ነው። አንተም የሰይጣን ተላላኪ ነህና የሱኑ ሥራ ትሠራለህ።
  ሌላው ሊቀ ካህን ተባለ ብለህ በማይሆን መንገድ ለማጥላላት መሞከርህ የሚያስገርም ነው። የማያምንና የማያስተውል ሁሌም እንደተወናበደና በክህደት ትቢት እንደ ተቅበዘበዘ ያልፋል። የቅዱሳኑን ፀሎት ከእጣኑ ጋር ወደ ሰማይ ያሳረገ የእግዚአብሔር መላእክ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። የሚያሳርግና በእግዚአብሔር ፊት የሚያቀርብ ደግሞ ካህን የሆነ ሊቀካህን ነው። ስለዚህ ሊቀካህን መባሉ የሚገባው እንጂ ሌላ የሚያስቧልት አይደለም። ኬፍ የነበረው ቅዱስ ቤጥሮስ በጎቸን ጠብቅ ተብሎ የእረኝነት ስልጣን ተሰጥቶታል። ታዲያ ክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞ እውነተኛ የበጎች እረኛ ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ ተገልጧልና ለምን እረኛ አደረግኸው ብለህ ክርስቶስን ልትወነጅል ይሆንን?
  ሌላው ከአባትህ የወረስኸው ያልተገባህን ቦታ የተመኘህበት ድርጊትህ ነው። በራዕይ ዮሐንስ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ሰዎች ቅድስና የፍፁምነት ደረጃ ሲደርሱ ያላቸውን ክብር የሚገልጠውን የመላኩን ንግግር ለራስህ ጭምር ማድረግህ በጣም የተለሰነ መቃብር መሆንህን አጉልቶ ያሳያል። ባሪያ ነኝ የምትለዋን ቃልና ንግግር ይዘህ እንዲህ አንተም እራስህን ከመላእክት ክብር ጋር ማነፃፀርህ ምን ያክል ሰይጣን ልብህን በከንቱ እንዳሳበጠው የሚያመላክት ነው። ትርጉሙ ወይም ሚሥጢሩ ይቅርና ዮሐንስ ለመላኩ ለመሥግድ የፈለገው አንድ ጊዜ ሳይሆን ሁለት ጊዜ መሆኑን እዛው በራዕይ ዮሐንስ ተገልጧል። ታዲያ ዩሐንስ በሁለት የተለያዮ ጊዚያት ለመሥገድ የተነሳው ተሳስቶ ነው ሊባል መቸም አይቻልም። ዮሐንስ ለቅዱሳን መላእክት ስግደት እንደሚገባ ስለሚያውቅ ነው። የሚሰገድላቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና የከበሩ በመሆናቸው የክብር ነው። መላኩ እንዳንተና እንደወንድሞችህ የእግዚአብሔር ባሪያ ነኝ ያለው የዮሐንስ ቅድስናና የእምነቱን ፍፁምነት ስለሚያውቅ ነው። በመጽሐፍ "በመላእክት እንከን እንድንፈርድ አታውቁምን?" የተባለው ከዚህ የቅዱሳኑ የእምነት ፍፁምነት የተነሳ ነው።
  ብዙ እንክርዳዶችን የበተንህ ቢሆንም አንድ ልጨምርና ላብቃ። የእግዚአብሔር መላእክት መናፍስት ናቸው። እንደ ሰው ሥጋ የለበሱ አይደሉም። የእግዚአብሔር መላእክት ረቂቃን ናቸው። አገልጋዮቹን ደግሞ መናፍስት ያደረገ የፈጠራቸው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። የእግዚአብሔር አገልጋዮች መናፍት ቅዱሳን መናፍስት ናቸው። በተፃራሪው ደግሞ የቀደመው እባብ የተባለውና የአንተ አባት የተጣው ሳጥናኤልም መናፍስት ነው። ከሳጥናኤል ጋር የተጣሉትም መናፍስት ናቸው። ሆኖም ሳጥናኤል ሐጢያተኛ እርኩስ መንፈስ ነውና የእሱ ሰራዊቶችም እርኩሳን መናፍስት ናቸው። ስለዚህ ሳጥናኤልንና ሰራዊቶቹን መከተልና ተግባራቸውን መፈፀም ባእድ አምልኮና ሐጢያት ነው። እግዚአብሔርን ማምለክና የእሱ የሆኑትን( መላእክትን ጨምሮ) ሀይማኖትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውና የተወደደ ና ጽድቅ ነው።
  የእግዚአብሔርን መላእክት ጣዖት ናቸው ማለት የፈጠራቸውን የጣዖታት አለቃና አምላክ ብሎ ማለትና እግዚአብሔርን መሥደብ ነው። ይቅር ይበልህ! ለሥም አጠራሩ ምሥጋና ይሁንና እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ቅዱስ የእሱ የሆኑትም ቅዱሳን ናቸው።
  የእግዚአብሔር መላእክት ቅዱሳን መላእክትና የከበሩ ናቸው ተብለው ይመሰገኑ ይከበራሉ እንዲ አምላክ ተብለው አይከበሩም። አንተ አትቅጠፍ!በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ሌላ አምላክ የለም።
  አቶ ሉሌ፦ መጽሐፍ ቅዱስ የገባያ ሸቀጥ የሚሸቃቀጥ አይደለምና ሳይገባህ ተሸክመህ አትዙር። ለማስተማር ከመሮጥ እግዚአብሔር ወዳዘጋጃቸው ጠጋብለህ ተማር። አይ ካልህ ቤተክርስቲያንን ለቀቅ አዳራሽህን ጠበቅ ነው። ህግ የለም እንጂ ህግ ቢኖር የሌሎችን አኛ አምነት በእንዲህ አይነት የውሸት ክስ ማጥላላትና መንቀፍ በወንጀል የሚያስጠይቅ ነበር። ግና በንስሀ ካልተመለሥህ የእግዚአብሔር ፍርድ ትጠብቅሃለች።

  ReplyDelete
  Replies
  1. aba selamawch ytlkun abat sme ssytan blog matry adrgachut egzabhar amlK ysadkan ysmeta amlak fredun yestach!! tolow nesh geb ynshf kidusen adamta abatowec bmenfes keds tmertaw ysafweten anbw gata fetretw azaz newn bgeza nesh gebw !!

   Delete
  2. HSABEHE MULU BEMULU GELEBA NEW

   Delete
 3. Dn lule selam neh wey ? ene Mk or yelela jele aydelehum just on behalf of my beloved mother church , EOTC, I wish to introduce you sth: the way you understood this religious verse is utterly wrong: The real message of this sacred manuscript is that the arch angel saint Michael is our intercessor and He is always praying for us to get sent the mercy of almighty God to us. And Angels and Saints intercede and intervene for us.of course, we do forgive with one another to establish peace and friendship.Besides, The Holy bible command us to forgive with one another so as to get forgiveness from Almighty God.Note: the arch priest of this world is God, who sent His son to ransom us and absolve our sins by his honored Blood.Please don't spread your misconception among the innocent laity.
  In our EOTC tradition, Priests say: May God absolve your sins: Egziabher yiftah.But not ene fetehuh.

  See you later


  ReplyDelete
 4. ምነው ባዶነታችሁን እና ሀየይመማኖት የለሽነታችሁን እደዘዚህ በገጋሀድ ባተታሰሳዩ ለ አዋቀቂ ቀርተርተቶ ለጨዋ ተረራ ጽሁፍ ነው በደዲየያቀቆን ሉሌ ሳይሆን በደንቀቆረሮ ሉሌ ተብሎ ይስተከካከል ቢየያንስ ቃንቀው እንካ ሀይመማኖት የመሚየያውቅ ሰው ይሆን ነበር ቢያንስ የፈደል ግድፈት ማስተክካከል''''''' ሆዳም ሁላ

  ReplyDelete
 5. ዳንኤል ነብይ ይመልስልህ እንዲህ ይልሀል;ይነግርሀል:- ዳን 10፥21"ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሀለሁ ;በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም"።እኔም ከነብዩ ተምሬ ነብዩ ያለውን እየደጋገምኩ "ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም" ሁልጊዜ እላለሁ።እልሀለሁ ።ቢመርህም.ብትናደድም።ከዚህ የበለጠ ምስክርነት ከየት ይምጣልህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Angel service is one wayJune 23, 2015 at 1:53 PM

   Brother Daniel was living before Christ that means he was under law , God is not manifested as a flesh at that time. Now God is manifested through his begotten son Jesus Christ to give us eternal life those of us who took Jesus as our savior we don't need the old testament services we are above law and under God. I don't blame you my brother or sister, I blame the Church because they didn't teach the gospel and lead by the holy spirit . Finally, I am telling you that Saint Michael will only come to if you only take Jesus of the Nazareth as your savior. Bless you!

   Delete
 6. Yoh. Easy8፥3-8"Ke mel'aku ej" tselotachen wede lay endiweta ye mel'aku ej yasfelgal eyaleh new atastewulemen?Zekarias 1፥12-16"mel'aku ke zekarias hehezbu eregna ena nebiy gar eko new ketegagere behuala marachew bilo teyeqe,melsun quter 16 anbebew.ante endemetelew bihon noro,Egziabher ayagebahem yilew neber enji bemelkam ena bemiatsenana qal ayinagerewum neber.ene menetser aladergem Egziabher yimesgen ayene beruh new.esti and titaqe leteyikeh ena bedenb asebebet,"Egziabher eregna new,redat ayasfelegewum,yale mela'ekt metebeq etechal,yale melktegna rasu menger eyechale lemen Mal'akten tebaki melketegna adrgo feterachew?yezih alama kegebah yemelakten amalajenet teqebelaleh,yih kalgebah eske mechereshaw sayigeh tefteh teqeraleh

  ReplyDelete
 7. "Ke mel'aku ej" tselotachen wede lay endiweta ye mel'aku ej yasfelgal eyaleh new atastewulemen?mel'aku ke zekarias hehezbu eregna ena nebiy gar eko new ketegagere behuala marachew bilo teyeqe,melsun quter 16 anbebew.ante endemetelew bihon noro,Egziabher ayagebahem yilew neber enji bemelkam ena bemiatsenana qal ayinagerewum neber.ene menetser aladergem Egziabher yimesgen ayene beruh new.esti and titaqe leteyikeh ena bedenb asebebet,"Egziabher eregna new,redat ayasfelegewum,yale mela'ekt metebeq etechal,yale melktegna rasu menger eyechale lemen Mal'akten tebaki melketegna adrgo feterachew?yezih alama kegebah yemelakten amalajenet teqebelaleh,yih kalgebah eske mechereshaw sayigeh tefteh teqeraleh

  ReplyDelete
 8. መላእክት ነብያት ሐዋርያት በሙሉ ቅዱሳን የዓለም ብርሃን ናቸው።ይህንን ብትቃወም ግን ማቴዎስ 5፥14 ከርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ"እናንተ የዓልም ብርሃን ናቸሁ"።አላቸው ሰለዚህ። ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የዓለም ብርሃን እንዳደረገው ተረድተህ ይቅርታ ጠይቀው ይቅር ይልሃል

  ReplyDelete
 9. ድንቅ ምላሽ ለአላዋቂና አሳሳች መናፍቅ። በዚህ ድረ ገጽ የሚቀርበው ነገር ሁሉ የማይረባና አንድም እውነት የሌለበት ቢሆንም ቅሉ ለእናንተ በዚሁ ተሰማርታችሁ እንደመኖርያ ስለአደረጋችሁት ምንም ማድረግ አይቻልም። የሆኖ ሆኖ የንስህ ጊዜ አልና ጊዜአችሁን አታጥፉ።

  ReplyDelete
 10. ኢትዬጵያን ዋጋ እያስከፈላት ያላው እንዲህ አይነቱ ድርስት ነው

  ReplyDelete
 11. ኢትዬጵያን ዋጋ እያስከፈላት ያላው እንዲህ አይነቱ ድርስት ነው

  ReplyDelete
 12. You wick demon!!! Leave the church.

  ReplyDelete
 13. anten bilo dirset awki. eyefeshah ager bemagmat ante neh waga yasikefelikat

  ReplyDelete
 14. E.O.T.C has false scripitures which are cibtradict with bible. Bible is enough to get eternal life.

  ReplyDelete
 15. Hi guys those who are commenting instead of blaming the blog compare the Bible and dersen mikael or other books.chose the best

  ReplyDelete
 16. God bless you diakon the truth shall prevail. The kingdom of God shall destroy all fox holes the devil is hiding in.

  ReplyDelete