Thursday, June 4, 2015

አባ ቀሌምንጦስ ከባንክ ሒሳብ አንቀሳቃሽነት (ፈራሚነት) ታገዱ
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመወዳጀትና በዓላማ በመተሳሰር ድብቅ ዓላማቸውን ውስጥ ለውስጥ ሲሰሩ ቆይተው ወጣቶችንም ለዓመፅ አደራጅተው ፓትርያርኩ ላይ ሴራ ሲጠነስሱ የነበሩት፣ ፓትርያርኩ ከሾሟቸው ሥራ አስኪያጆች ጋር አልሰራም በማለት ሲያቅማሙ ሰነባብተው ትናንት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት የሀገረ ስብከቱን ገንዘብ ለማንቀሳቀስ አልፈርምም ያሉት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ  ሆነው የተመደቡት አባ ቀሌምንጦስ ከፈራሚነት ታገዱ፡፡ በምትካቸውም በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ፈራሚነት ሂሳቡ እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ በእርሳቸው ፊርማ ሥራው ቀጥሏል፡፡


ቅዱስ ፓትርያርኩ አባ ቀሌምንጦስን አክብረው ይሠራሉ በሚል በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ጠቁመው በልዩ ሀገረ ስብከታቸው በረዳት ሊቀ ጳጳስነት የመድቧቸው መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ድረስም ከአባ ቀሌምንጦስ ጋር አብረው በመሄድ አስተዋውቀዋቸዋል፡፡ አንድ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በዚህ መልኩ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ተገኝቶ ከሠራተኞቹና ከአድባራትና ገዳማት አገልጋዮች ጋር ሲያስተዋውቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለታላላቅና አዋቂዎች፣ ከልጆች ጋር ላልዘለሉና ክብራቸውን ለጠበቁ ጳጳሳት እንኳ ያልተደረገ ክብር ነው፡፡

ሲከበሩ ክብር ያልወደደላቸው አባ ቀሌምንጦስ ግን ድብቅ ዓላማቸው እየጨነገፈ መሆኑ ስላስከፋቸው ቦታውን ለመልቀቅ አስበው የነበረ ቢሆንም የካዛንችሱ ጨፋሪ የሳሪስ አቦው አለቃ ክብሩ፣ እነ ዳዊት፣ ዲያቆን ኃይሉ ጉተታና ታዴዎስ ለምነውና እግራቸው ላይ ወድቀው እንዳስቀሯቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለያየ አጋጣሚ ፓትርያርኩን አልታዘዝ፣ እሳቸው ከሾሟቸው ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ጋር አልሰራም በማለት ሲያንገራግሩ የቆዩ ሲሆን አሁን ለአደረጃጀት ሲባል ከተነሡ የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ጋር ግንባር በመፍጠርና አባ ማቴዎስን መከታ በማድረግ ሥራ የፈቱና ማኅበረ ቅዱሳን በሰንበት ተማሪ ስም ለአመፅ ያደራጃቸውን ወጣቶች እያነሳሱ ቆይተዋል፡፡ አባ ቀሌምንጦስ ላይ አሁን የተወሰደው እርምጃ ተገቢም አስፈላጊም ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባ ማቴዎስ ዘረኛነት መደበቅ እስከማይቻል ድረስ ገሃድ መውጣቱን ቀጥሏል፡፡ ሰውዬው የለየላቸውና ዓይን ያወጣ ዘረኛ መሆናቸው የታየው የእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ የመጽሐፍ መምህር የሆኑት የኔታ አስራት በሊቃውንት ጉባኤ የተወሰነባቸው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዳይሆን በማፈን ነው፡፡ ሊቁ ወደ ደብሩ ተመልሰው ከስብከተ ወንጌል እንዲነሱና በማሕሌት አገልግሎት እንዲወሰኑ የተወሰነ ቢሆንም የሳቸውን ጉዳይ ዘረኛው አባ ማቴዎስና አባ ሉቃስ አፍነው አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ግን እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን ክህደት በጽሑፍ ያስተላላፈው አቶ ሃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ክህደቱን አምኖ ተቀብሎ ክህደቱም በሚዲያ እንዲነገርና እንዲስተባበል ከተወሰነበት በኋላ እስከ ዛሬ ውሳኔው ሳይፈጸም እንዲዘገይና እንዲረሳም ተደርጓል፡፡ ለዚህ መናፍቅና ከሐዲ ዘረኛው አባ ማቴዎስ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግና ሽፋን በመስጠት ከስብከተ ወንጌል መምሪያ ወደአልባሳት መምሪያ እንዲዛወር በማድረግ ፍትሕን በማዛባት በእናት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኑፋቄን ከማረም ይልቅ እንዲጸና በማድረግ ትልቅ በደል በቤተ ክርስቲያን ላይ ፈጽመዋል፡፡ ከሃይማኖት ይልቅ ዘረኛነት ምን ያህል ቤቱን እንደሰራባቸው ይህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መናፍቅና ከሀዲ ሆኖ በወንዙ ልጆች ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንክብካቤ የተደረገለት ኃይለ ጊዮርጊስ ባለፈው መስቀል አደባባይ በተደረገው የሐዘን መርሀ ግብር ላይ ድንጋይ ሲወረውር ተይዞ ለእስር ተዳርጓል፡፡ መስሪያ ቤቱ ጠቅላይ ቤተ ክህነትም ከሥራ ገበታው ላይ በመጥፋቱ ማስታወቂያ አውጥቶበታል፡፡ በዚያ የአመፅ ድርጊት ላይ ሃይለ ጊዮርጊስን ያሰማራው ማቅም ሆነ ሽፋን ሰጪው አባ ማቴዎስ ከመታሰር አላዳኑትም፡፡ ከግብረ ሰዶማዊነት እስከ ድንጋይ ወርዋሪነት ያለው ጉዞው የተሸፈነለት ግን በእነርሱ ነበር፡፡ ይህን የተመለከቱ ብዙዎች ዘረኛው አባ ማቴዎስ በዘረኛነት መርዝ በመለከፍ እውነትን ሐሰት ሐሰትን እውነት በማድረግ ያዛቡትን ፍትህ ሁሉን በፍትሁ የሚዳኘው ጌታ የእርሱን ፍትህ ሰጠ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በአባ ቀሌምንጦስ ላይ የተወሰደው እርምጃ በአባ ማቴዎስ ላይ መደገሙ ሩቅ አይሆንም የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አድሯል፡፡ ምክንያቱም በትክክልና በፍትህ መንገድ ካልሰሩና ሲያከብሯቸው መከበር ካልቻሉ ሥራቸው ያጋልጣቸዋልና ከዚህ የተለየ እድል ፈንታ አይኖራቸውም እየተባለ ነው፡፡

15 comments:

 1. ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ ይሉሃል እንዲህ ነው።

  ReplyDelete
 2. ኧረ ለመሆኑ ማቴዎስ ጳጳስ ነው እንዴ? በዘረኝነት፣ በአድማና በጭካኔው ተወዳዳሪ የሌለው ማቴዎስን ጳጳስ ለማለት ይከብደኛል። ሰው የሚከበረው በስራውና በምግባሩ እንጂ በሹመቱ አይደለም። ጨካኙ ኔሮንም በአንድ ወቅት የሮማ ንጉሥ ነበር። ነገር ግን በታሪክ ያተረፈው በስራ የገለፀውን ያንን ቆሻሻ የጭካኔ ተግባሩን ነው።
  የቤተ ክህነቱ ማቴዎስ ማእረጉን ተገፎ በአቶነት ሊባረር የሚገባው የሽፍቶች አለቃ ነው። ጳጳስ ከመሆኑ በፊት አጭር ካፖርት ለብሶ በአንድ ሆቴል መገኘቱንና ያየነው መሆኑን ይህን አስተያየት ሲያነበው ቦታውን ያስታውሳል። ደግሞ እሱን ብሎ ጳጳስ??

  ReplyDelete
 3. አሉባልተኛ የክፋት ስልቻዎች
  የትም ዘለላችሁ፣ የትም ገባችሁ፣ በዚህ አመፀኛና እርኩሰታችሁ መውደቂያችሁ ሲኦል ነው። መዳን ብትፈልጉ፣ ህይወትን ብትሹ ኖሮ ወንጌል በተማራችሁ ከዛም ትንሽ ለህሊናችሁ በተገዛችሁ። አሁን እናንተ ስለዘረኝነት ለመናገር ስትዘባርቁ ትንሽ ሰቅጠጥ አይላችሁም። ዘረኛማ እናን የዚህ ብሎግ ባለቤቶችና አሉባልታ ነዠዎች ናችሁ። የማትታወቁ ሊመስላችሁ ይችላል ስማችሁን ስለምትቀያይሩ ግን ትታወቃላችሁ። በዘረኝነት ተደራጅታችሁ የክርስቶስን ቤተክርስቲያንና ክርስቶሳዊያንን ሰላም ስትነሷት ተው የሚላችሁ የህግ አካል የጠፋው። ዘራችሁን ንገረኝ ብትሉ መናገር ይቻላል። ዘራችሁን ተገን አድርጋችሁ የተኩላ ተግባርን እንደምታራምዱ የታወቀና የተረጋገጠ ነው። አባ ማቲያስ አይደለም የቤተክርስቲያን አባት በዚህ አካሔዳቸው ቄስነትም አይገባቸው።

  ReplyDelete
 4. ይድረስ ለአባ ሰላማ ለመሆኑ የእናንተ ሲኖዶስ የትኛው ነው በእርግጥ ወንድም ፓስተር ምናሴ ቤተክርስቲያኒቱ ብትፈርስ ግ የለህም ምክንያቱም እየሰራሁ ያለኸው ይህኑ በመሆኑ።

  ReplyDelete
 5. በእጅጉ የሚገርመው ነገር ፓትርያሪኩ ጉያ ሰር ተደብቆ ተኩስ እየከፈተ ያለው ሞ ፋራህ ሙሴ እና ይቅርባይ የሰንበት ት/ቤቱና ዘላኑና የመቀሌ ኮሌጅ የጥበቃ ሀላፊ የንበረው ግለሰብ መሆኑን ማውቅ ለአባ ሰላማ እንዴት ተሳናት።የሰንበት ት/ቤት ሰልፉን ያቀናጁ ይቅርባይና ሙሴ አይደሉም ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዘላኑ የጥበቃ ሀላፊ ማን ነው ?ኑረዲን ወይስ መነኩሴው?

   Delete
 6. አባ ሰላማዎች እውነትን በውደዳችሁ፤ ሚዛናዊ ጽሑፍ ማለትም በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ጥሩ ሲሰራ ጥሩ መጥፎ ሲሰራ ጥሩ ማለታችሁ ከእየሱስ ክርስቶስ በቀር እውነተና በር አለመኖሩ በመስበካችሁ ደስ ይበላችሁበማለት ወደ ጉዳዬ ልመለስ
  የአንኮበሩ ውዳቂ ቤተማንግስት አሳድሳለሁ ባዩ የነ አባ ማቴዎስና ቀሌሚንጦስ አካሄድ ውሸት መሆኑ ከ12ኛ ክፍለዘመን ይጀምራል
  1ኛ የሸዋ ወታደር የነበረውና በጦርነት አንድ እግሩ የጣውን ተክለሃይማኖት የተባለው ግለ ሰብ ባህታዊና ጻድቅ አታልሎ በማስመለስ የዛጌ መንግስት ከወሎ ወደ /ሽዋ / ሶሎሞናዊ ዳይናስቲክ በስመለስ በመቻሉ ወታደሩ የጻድቁን አቡነ ተ/ሃይማኖትን ስም በመስጠት የትውልድ ሀገሩ ደብረ አሰቦት በማለት ለጀመረው ውሸት የቤተሰቦቹ ሥም ፍስሃ ጽዮን ፤ እግዚእ ሀረያ ፤ ፀጋዘአብ እነዚህ ሥሞች የአማርኛ ስሞች ናቸው የትግርኛ የተባለው አከባቢ ስሞች ሁሉም እንደሚያውቀው እርገጣቸው ፤ድፋባቸው ፤አደፍርስ ሆኖ እያለ እንዴት ይሆናል፡፤
  2ኛ ሰሎሞን ዳይናስቲክ ከተባለስ ሰሎሞን የአክሱሙ ነው ወይስ ሌላ ሰሎሞን ፈጥረው ነው አጤዎቹ ለውሸትና ታሪክ ለማጥፋት በማቀድ ርእሰ አድባራት መናገሻ ፤ የመናጋሻ አስተዳዳሪ ንቡረ እድ እያሉ እንደሚቀባጥሩት የሚከፋው ደገሞ የጻድቁ አቡነ ተ/ሀይማኖት ሳይሆን የወታደሩ ተ/ሃይማኖት ታሪክ ላይ / ወመጽዑ ሰብአ ጎጃም ተጺእኖሙ … ወተሰጥሙ /ይህ እውነት ከቅዱሳን የሚወጣ ቃል ነው / አሁንም ወደ ቀድሞ የአባቶቻቸው ውሸት በመመለስ የውሸት ፕሮግራማቸው ምላሳቸው በሆነው የሀራ ተዋህዶ ብሎግ እየተደገፉ ያልተደረገ ተደረግ እራሳቸው ያጠፉት ሌላ አጠፋው በተለይ አባ ቀሌሚንጦስ የኢህአደግ ደጋፊ መስሎ ኢሀአደግን ላመጣፋት ለዘመናት በውስጡ የደበቀው ክፉ አላማው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገብቶ እስከ ወጣበት ባለው ወቅት ታውቆባቸዋል ድመት መንኩሳ አመልዋን አትረሳ ፡፡
  ሰው ወደ ኃላ አይወቀስም ሥራ ከጀመረበት ጀምሮ ባለው ጊዜ ግን ይወቀስበታል አባ ቀሌሚንጦስ በስነምግባር ብልሹ ሆነው ከተገኙት ስራ አስኪያጆች ጋር በመሆን የመሀልና የደር ሀገር ብለው የቤተክርስቲያን ልጆችን በመከፋፈል የኔ የሚሉዋቸውን ያለፈተና ሥራ አንዲ ቀጠሩ ሲያደርጉ በስራ አለም ላይ ያልነበሩትን በስራ እንደነበሩ አድርገው ዝውውር ሲፈጽሙ የዳር ሀገር ብለው በራሳቸው አባባል የመጠሩዋቸው አገልጋዮች ደግሞ ከስራቸው እንዲፈናቀሉ ሲያደርጉ ቆይተዋል አሁን ከክፉ ምግባራቸው እንዲመለሱ ቢመከሩም ሴትየላከችው ሞት አይፈራም ሆኖባቸው ተመክረው አልሰማ በማለታቸው በራሳቸው ተባርረዋል / ማንም ሳይፈነቅለው ከድበሩ እንደተፈነቀለው ድጂያ /
  ይጨምሩና በግቦት ስብሰባ ፤ኝጹን ወጣጦችን በውሸት በማነሳሰት ፍላጎታቸው ማማላት ሳይችሉ ሲቀሩ ደግሞ ሀገረ ስብከቱ 50 ሚልዮን ስላለው እሱን ለማጥፋት እኔ ተባረርኩኝ ይላሉ ገንዘቡ ይኑር እንጂ አይጥ ያልበላው ገንዘብ አንበሳ አይበላውም ግን ስለመኖሩ ያቀረቡት መረጃ የለም ተአማኒነት እሳቸው ብቻ ናቸው የሚየውቁት ያቀዱት የዘረኝነት ዓላማ በማቋረጡ ግን ገና ለቅሳሉ አልተዳሌ የክርስቶስን መሰቀል አስበው አያለቅሱ ከዚህ በኃላ ማቴዎስና ቀሌሚንቶስ የክርስቲያኖች አባት ብሎ በሙሉ አፍ መጥራት ይከብዳል አስመሳይ ፤ ውሸታም ፤ ነገር ጠንሻሾች ወገንተ|ኛ መባል አለባቸው የሀይለጂዮርጊስን ግልጽ ክህደት ከሀዲነታቸው ይገልጣል የእየሱስ ክረስቶስን ሥም የሚጠሩትን ተዋህዶ የሚሉት ማቴዎስና ቀሌሚንጦስ የሰዶማዊው እና መናፍቁ ኃይለጂዮርጊስ ክህደት ተሸፍኖ እንዲታለፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ባለቸው ስልጣን ሸፍኖዋል ይሁን እንጂ ማቴዎስና ቀሌሚንጦስ ሊቁን መጋቢ አእመረን መናፍቅ ለማለት እሱ የተማረውን መማር ባይችሉም ማስረጃው መቁጠር ይበቃቸዋል ግረድናቸው በቃ የተባለው አባት ቀሌሚንጦስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ከማቴዎስ የበለጠ ጥቁር ደንጋይስ ከየት አለና የበተክህነት ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ቤሌለው ስልጣን ለአንዳን በእነሱ አጠራር የዳር ሀገር ሰዎች አለቆች ማስጠንቀቂያ የሚጽፈው በየትኛው የቤተክሰርቲያን ህግነው፤ባጭሩ እነዚህ ሰዎች አንድም ቀን እውነት ላይናገሩ እውነቱ ላይሰሩ አድማ እና ድሎታ አድልዎ ብቻ እንደሰሩ ይህች ሀገር ወደኃላ ማስቀረታቸው አንሶ ፤ ይህች ቤተክርስቲያን ሀይማኖትዋ እንዲበረዝ በየገድላቱ በታሪክ ጸሐሀፊዎቻቸው መጥፎ ቃላትና ወሸት በማስገባት ማበላሸታቸው ይብቃ ይባል
  የማቅ አፍ የሂነው ሃራ ተዋህዶም የጅል ለቅሶ መልሶ መላከስ የንተው የማህበሩ ሰዎች ፎቆችና መኪናዎች ኬት የተገኙ ናቸው ስእለት ሰብሳቢኔ እስካላቆምክ ሌባው የማይቀድሰው የማይፈታው የቤተክርስቴን ስጦታዎችን በመዝረፈፍ የከበረው ያንተው ማህበር መሆኑ ማንም ውቃል እኛም አውቀናል እንንተም አውቃቹል አንድ ቀን እውነቱ ያሸንፋል በተናገሩ ሳይሆን በሰሩ ነው አባ ማቴዎስ ጵጵስናው ለዚች ቤተክርስቲያን ነው ለማህበረ ቅዱሳን ማቅ ስእለት፤ አስራት ፤በኩራት እየሰበሰበ የቤተክርስቲያንዋን ጥቅም ለራሱ ሲያደርግ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ሆኖ ባለቀሰ ግን አባ አፈወርቅ መኪኖች የገዛው በዚሁ የሙድዬ ሙጽዋት ገንዘብ አልነበረም ዎይ ይቀጥላል

  ReplyDelete
 7. አትፍረዱባቸው እነዚህ ጳጳሳት ነን ባዮች ዘረኛ ግለሰቦች አይሳካላቸውም እንጂ የአንኮበሩ ሥርዓት ተመልሶ በኢትዮጵያዊያን ላይ እንዲጫን የሚፈልጉ የዘመኑ ቂሎች ናቸው። ምኞት አይከለከልም ማለት እንዲህ ነው የዘመኑ ደናቁርት ናቸው።

  ReplyDelete
 8. HIS HOLINESS DID WHAT HE SHOULD DO
  .I AM REALLY PROUD OF HIM. HE IS VERY PATIENT AND A MAN OF DECISION.

  ReplyDelete
 9. ሰላማዎች

  ReplyDelete
 10. ቅድስት ቤ/ን ስትዘክራቸው ከምትኖረው አንዱንዋናው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አባት ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ መሆናቸው ግልጽ ነው
  ይህ ሆኖ እንዳለ ሆኖ ባልጠፋ ሰው ከሙያ ሙያ ከእምነት እምነት የሌላቸውን የቤተ ክርስቲያን ነቀርሳ የሆኑትን መሰግሉ አባ እብርሃምን ሰዶማዊው አባ ሳሙኤልን ሽሮሜዳ ሥላ። ለስብከተ ወንጌል ተልኮ እንደ እነ መሀመድ 7ት ቤት ትዳር መስርቶ የኖረውን አባ ማቴዎስን ጵጵስና መሾማቸው ቤንን ሲያስለቅሳት ይኖራል።

  ReplyDelete
 11. I hate this website , I used to visit at least once a day, not any more. I don't see any progress by the word of God (sharing Gospel) in stead every post talking adversely about MK , Jesus died even to ISIS. If you don't love for others that means your father is Satan. Why don't you pray for MK instead of cursing them in every post? Geta Eyesus le bona yestachew , yebarkachew!

  ReplyDelete
 12. አይ አባ ዶማዎች ሸዋ ላይ ቅማልህን ታራግፍና ቁምጣህን ትቀይርና የሸዋ ሰው አልይ ትላለህ ወራዳ መናፍቅ

  ReplyDelete
  Replies
  1. YOU ARE RIGHT!

   Delete
  2. shewa yemibal hager yelem.

   Delete