Monday, June 8, 2015

ሰንበት ት /ቤት ለታዳጊ ወጣቶች ወይስ ለፖለቲካ አቀንቃኝ ጎልማሳዎች?ከተውህቦ ምህረ (ባህር ማዶ)
   የሰንበት /ቤት  ወጣቶች በማወቅም ባለማወቅም ለማቅ ዓላማ ሰለባ ሆነዋል።
   ወጣቶች በቤተ ክርስቲያንዋ ጥላ ሥር ከአባቶቻቸው እየተማሩና በቃሉ እየተኮተኮቱ
ማደግ ወይስ ፖለቲካዊ የአቋም መግለጫ ለማውጣት የሚሰበሰቡ?
   የሰንበት /ቤት  አባላት ወደ ጎልማሳነት የእድሜ ደረጃ ሲደረሱ የወጣቶችን ቦታ ለቀው በሌላ  የአገልግሎት መሥመር የሚሰማሩ ወይስ ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ በአርባና በሃምሳ እድሜያቸው የእድሜ ገደብ ይነሳልን እያሉ ቤተ ክርስቲያንን የሚያውኩ?
   ዛሬ የወጣትነት ካባን ደርበው ቃለ አዋዲው ይሻርልን ያሉ አባት-ወጣቶች ነገ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ይታረምልን ለማለት ምን ይገድባቸዋል?
   የሰንበት /ቤት  ማደራጃው ወጣቶች የማቅ አጀንዳ ሰለባ እንዲሆኑ መንገዶችን ማመቻቸት የአደባባይ ምሥጢር ነው።
   የቅዱስ ፓትርያርኩ ጠንካራ አመራርና አቋም የብዙዎችን ሊቃነ ጳጳሳትን ልብ እየማረከ ነው።
   የማቅ ተወካይ አቡነ ማቴዎስ የሚያሳድሙት የጳጳሳት ቡድን እንደተበተነ፤ እርሳቸውም በሥጋትና በተጠንቀቅ እንዳሉ ታውቋል
   ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከፓትርያርኩ ጋር እንደታረቁና አብሮ ለመሥራትም መወሰናቸው ተሰምቷል
   የእነ አቡነ አብርሐምና የእነ አቡነ ዲዮስቆሮስ የፓትርያርኩን አቋም መጋራት ቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ከማስቀደምና ወጣቶችን ወደ ስህተት ጎዳና ከመምራት ይልቅ ከአባቶቻቸው ጋር ሆነው  ለቤተ  ክርስቲያን ሕግ እየታዘዙ እንዲያገለግሉ ከማድረግ
አንጻር መሆኑ ታውቋል። ይኽ ይበል  የሚያሰኝ ነው.
   የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም ለውጥ ለማቅ ክፉኛ አስደንጋጭ ዜና ሆኗል
   ቅዱስ ፓትርያርኩ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የወሰዱት አቋምም ጠንካራ
አመራራቸውንና የአባትነት አደራቸውን በትክክል የሚያንፀባርቅ ነው። ከተለያዩ ታዛቢዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶች ናቸው።

ሰሞኑን የሊቃውንቱ ሁሉ መነጋገሪያ ርእስ የሆነው የማቅ ሰለባ  ስለሆኑት ወጣቶችና በወጣትነስም  ቤተ  ክርስቲያንን ስለሚያውኩ ጎልማሳዎች ነው። የሰንበት ትምህርት ቤት  ዓላማ እንደሚታወቀው  ታዳጊ  ወጣቶች  በቤተ    ክርስቲያን  ሥርዓትና  ቀኖና    ተኩትኩተው፤ የእግዚአብሔር ቃል  እየተማሩ የሚያድጉበት፤  ነገረ መለኮትን የሚያጸኑበት፤  ቤተ ክርስቲያናቸውን ተረካቢ የመሆን ብቃታቸውን የሚያጎለብቱበት ነው። በዚህ መንገድ ብዙዎች ከሰንበት ትምህርት የወጡ ዲያቆናት፤ ካህናትና ጳጳሳት ይገኛሉ። በቃለ  አዋዲ ሕግና  በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትም የጎልማሳነት የእድሜ እርከን ላይ  ሲደርሱ ለተተኪ ታዳጊ ወጣቶች ቦታውን በመልቀቅ ለጎልማሳዎች በተቀመጠው የአገልግሎት መሥመር ይሠማራሉ።

ይኽ  ሥርዓት የቃለ አዋዲ ሕግ  ብቻ  ሳይሆን የቅዱስ መጽሐፍ መለኮታዊ መመሪያ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደም ዋጋ  የከፈለላትን መንጋ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሲያስረክብ በእድሜ ደረጃ መጠበቅና መሠማራት እንዳለባቸው ቃለ ምዕዳኑን ለሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በግልጽ አስታውቋል።

,   ዖን ሆይ ከእ ይል ትወደኛለህ? አለው አዎ  ሆይ፥ ድወድ አን ታውቃለህ አለው ግልገሎቼ አሰማ አለው ደግ  ዖን ሆይ ትወደኛለህ? አለው አዎ  ሆይ ድወድ አንተ ታውቃለህ አለው።ጠቦቶቼ ጠብ አለው ጊዜ  ዖን ሆይ፥ ትወደኛለህ? አለው ኛ። ትወደኛለህ? ስላለው ጴጥሮ አዘ  ሆይ፥ አን ሁሉ ታው  ድወድ አን ታውቃለህ አለው በጎአሰማ. (ዮሐ.21:15-17)

ግልገሎች ሕጻናትን፤  ጠቦቶች ወጣቶችን፤  በጎች  ከጎልማሳነት እድሜ በላይ ያሉትን ያመለክታል። መለኮታዊ መመሪያ ካስቀመጠልን ሥምሪት ወጥቶ በማይመለከተው መሠማራት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መቃወም ብቻ ሳይሆን እስትንፋሰ መለኮት የሆነውን ቅዱስ መጽሐፍን አለመቀበል ነው። ጥጆችን ከበሬዎች ጋር ማሠማራት ደግሞ ያለ እድሜያቸውና ያለ ጊዜያቸው ውጊያን ማስተማር ነው። ጥጆች እንደ በሬ የሚዋጉበት ቀንድና ልምድ ስለሌላቸው ስብራትና ቁስለት ብሎም መሞትም ሊያጋጥማቸው ይችላል። በሰንበት ትምህርት ቤት  ውስጥ ሆነው ያለእድሜያቸው ታዳጊ ወጣቶች የአእምሮ  መስፋት፤  የማስተዋል፤  የመጠበብና እንደ ዩኒቨርሲቲ ለዘመናት የተከማቸውን የአባቶቻቸውን አሠረ ፍኖትና ትምህርተ ሃይማኖታቸውን እንዳይከተሉ እንቅፋት የሚሆኑ ግለሰቦችን ማየት እጅግ ያሳዝናል። ይኽ በክርስትና ትምህርትና በቤተ  ክርስቲያን ሥርዓት ቀርቶ በዓለሙ ሕግም የሚያስወነጅል ነው። ከሃያ ዓመት በላይ የሆነው ወጣት ከታዳጊ ወጣቶች ጋር  ኢለመንተሪ ስኩል  ገብቶ መማር ሕጉ  አይፈቅድለትም። በአጋጣሚ ሳይማር ኖሮ አሁን መማር ቢፈልግ እንኳ የጎልማሶች ትምህርት ቤት መግባት ወይም ማታ  ማታ  ከሚመስሉት ጋር  መማር የትምህርት ቢሮ  ፖሊሲ  ነው። ታዲያ የዓለሙ ህግ  ይኽ ከሆነ የእግዚአብሔርን ህግ ለማቅ ድብቅ አጀንዳ ብሎ  ለመሻር ይኽ  ዓይነቱ ድፍረት ከሰንበት ትምህርት ቤት እንዴት ጠበቃል?

በጥጃና በበሬ ምሳሌ ከላይ እንዳየነው ብዙዎች ታዳጊ ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የፖለቲካ አቀንቃኞች በሆኑት ጎልማሳዎች ተበርዘዋል። በትምህርትና በጥበብ፤  በመንፈሳዊ ሕይወትና አገልግሎት ታንጸው ማደግ ቀርቶ ለሰልፍና ሌሎችን ለመኮንን ጊዜን ማጥፋት ሆኗል። በእድሜና በአእምሮ ብስለት የማይመጣጠኑ ወጣቶችና ጎልማሳዎች አብሮ መሰለፍ አደጋ ነው ይሏችኋል ይኽ  ነው። እንደ ሄኖክ  አሥራት ያሉ ዓይን አውጣ ደፋሮች የወጣቶቹን አእምሮ ሸብበው ቃለ  አዋዲውን እንዲቃወሙ ,የእድሜ  ገደብ ይነሳልን.  በማለት ጠየቁ። እንዴት አሳፋሪ  ነው?   የማደራጃ መምሪያው ቸልተኝነትን ተጎናጽፎ የቃለ አዋዲውን መመሪያ ላለማስፈጸም ዝም ስላለ  የማቅን ድብቅ አጀንዳ ይዘው ወደ  አደባባይ ለመውጣት ደፈሩ። ከዓመት በፊት በዕለተ ስቅለት ሕዝቡን ለሰላማዊ ሰልፍ  ቀስቅሶ የነበረ ማቅ  አሁን ደግሞ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን በቤተ  ክርስቲያን ላይ  ሰላማዊ ሰልፍ  እየጋበዘ ነው። በሰልፍ ሁከት ሕዝብን ለዓመጽ መቀስቀስ ይቻል እንደሆነ እንጂ የቤተ ክስቲያንን ድምፅ አይወክልም። የቤተ ክርስቲያን ችግር የሚፈታው በጸሎትና በውይይት ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ  ክርስቲያን ምዕመናን ማቅ  በቅድስት ቤተ  ክርስቲያን ላይ  የዘረጋው ምዝበራና ቅሳጤ በደንብ ስለተረዱ ለዓመጹ ቦታ  የላቸውም። የተባለው ሰልፍም ቢደረግ ሁከት ፈጣሪዎችን ለመለየትና  እርምጃ  ለመውሰድ ይረዳ ይሆናል  እንጂ  ሌላ   ፋይዳ  የለውም

የጋጠወጦቹ  ድፍረት በዚህ ብቻ   አልተገደበም። ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማወክ፤  የተሳካ አመራራቸውንና ቆራጥ አቋማቸውን ጥላሼት ለመቀባት ቃጥተዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ባልተያዘላቸው መርሐ-ግብር በጉባኤያቸው ለምን አልተገኙም ብለው ለመኮነንም ሞክረዋል። ይኽንንም ከቤተ  ክርስቲያን  ሥርዓት አኳያ  ስንመለከተው።  የሥርዓት  ጥሰትና  የቤተ ክርስቲያንን  ሥልጣን ማቃለል ሆኖ   አግኝተንዋል። አንደኛ ቅዱስ ፓትርያርኩ አስቀድሞ ፕሮግራም ሳይያዝላቸው መገኘት አለባቸው ማለት የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣንና ማዕረግ ማቃለል ነው። ሁለተኛ በጉባኤው ላይ የተገኙ የሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ  ጳጳሳት ሥልጣንን አለመቀበልና አለማክበር የሚያሳየው ከቅዱስ ሲኖዶስ  እኩል ራሱን  ያስቀመጠውን ማቅንና አጀንዳውን ነው።

ለማወቅ እንደተሞከረው በዚያን ዕለትና ሰዓት   ቅዱስ ፓትርያርኩ ቀደም ሲል  ፕሮግራም የተያዘላቸውን ከኮፕት/ግብፅ  ኦርቶዶክስ ቤተ  ክርስቲያን የመጡ ሊቃነ   ጳጳሳትንና ከሰላሣ የሚበልጡ ወጣቶች ልዑካንን በማስተናገድ ላይ  ነበሩ። የእነዚህ ዓለም አቀፍ እንግዶችና በርካታ ሊቃነ  ጳጳሳት ጽርሐ ጽዮን መንበረ ፓትርያርክ ሞልተው የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይን በሚወያዩበትና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ  ምዕዳንን በሚቀሉበት ሰዓት  ነበረ   በሰንበት ትምህርት ስም  የተሰባሰቡት ወጣቶች በእነ ሄኖክ  አሥራት መሪነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ደጃፍ ቆመው  የጋጠወጥነት   ጩኸታቸውን  ያስተጋቡት።   ይኽም  ከጋጠወጥነት  አልፎ  ማቅ የሚያካሔደውን የሁከት ፈጣሪነት ዓላማንም በግልጽ የሚያሳይ ነው። በመሠረቱ ሥርዓት ባለው መልኩ ቅዱስ ፓትርያርኩን ፕሮግራም ቢያስይዙ ኖሮ  ቅዱስ ፓትርያርኩ በልጆቻቸው ጉባኤ ተገኝተው ለመባረክና ድምፃቸውን ለመስማት ምንም ጊዜም ፈቃደኛ እንደሆኑ እስከ አሁን ካለው ተግባራቸው መረዳት ይቻላል። ለድብቁ አጀንዳቸው የሚያዜሙት ,ሙስና.,አማሳኝነት. ዜማቸው በመሠረቱ የቅዱስ ፓትርያርኩ አቋምና ዓላማ ነው። መልካም አስተዳደር ለማስፈን፤ ሙስናን ለማጥፋት፤ ሕገወጥ የቤተ ክርስቲያን ነጋዴዎችን ወደ  ሕግ እንዲቀርቡ መታገል ቅዱስነታቸው የተነሱበት  መሠረታዊ  ፖሊሲያቸው ነው። በመሆኑም ልጆቻቸው ይኽን  ዓላማቸውን ለመጋራት መነሳታቸው ለቅዱስነታቸው ትልቅ ደስታ ነው። ይሁን እንጂ የቅዱስነታቸው አቋም (ሙስናን ማውገዝ) ለእነርሱ ለአጀንዳቸው መሸፈኛ ብቻ  ስለሆነ በመሥመር አልተገናኙም። የቅዱስነታቸውን መመሪያ የሚቀበሉ ቢሆኑማ ሙስናን ማውገዝ መጀመር የሚችሉት ከማቅ መንደር ነበር። ምክንያቱም ሕገ ወጡ  ነጋዴ፤ የቤተ ክርስቲያን አማሳኝና ሁከት ፈጣሪ ከማቅ የበለጠ ከየት መፈለግ ይቻላል?

ይኽ በእንዲህ እንዳለ ብዙዎች ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ፓትርያርኩን ትክክለኛ አካሔድ በመረዳት መልካም አስተዳደር የማስፈን አቋማቸውን መጋራት ጀምረዋል። አብሮ ለመሥራትም ታጥቀው እንደተነሱ ከሚታዩት ገጽታዎች ለመረዳት ተችሏል። ለምሳሌ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው አቡነ ሳሙኤል ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ልዩነታቸውን ተነጋግረው መስማማት ላይ እንደ ደረሱና አብሮ ለመስራትም እንደወሰኑ ለማወቅ ተችሏል። ይኽ  የቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጠንካራ አቋምና ቅድስና የብዙዎችን ሊቃነ  ጳጳሳት ልብ  እየማረከ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ብዙዎቹ ይናገራሉ። የእነ አቡነ አብርሐምና የእነ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን መመሪያ መቀበል፤  የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ማስቀደምና በተለይም ወጣቶችን ወደ  ስህተት ጎዳና ከመምራት ይልቅ ወጣቶች አባቶቻቸውን በመታዘዝና በመከተል የቤተ ክርስቲያናቸው ተራካቢ እንዲሆኑ ማድረግ መምረጣቸውን እያሳዩ እንደሆነ ታውቋል። አቡነ ማቴዎስና አቡነ ቀለምንጦስ ለማቅ መቆማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን  ሁለቱም የዘረኝነትና የማቅን የሁከት አቋም መደገፋቸው በጳጳሳቱም ዘንድ እየታወቀ መጥቷል። ከቤተ ክርስቲያን ጥቅም ይልቅ የአንድ ማኅበር ደጋፊ መሆናቸው ትልቅ ግምት ላይ ጥሎአቸዋል።

በአንጻሩ ቅዱስ ፓትርያርኩ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን አስመልክቶ የወሰዱት አቋም ምንም እንኳን የዘረፋ ኔትወርክ ሠርተው ሲዘርፉ ለነበሩት አስደሳች ባይሆንም የለወጥ ፍሬ  እያሳዬ ነው። የማቅና በሰንበት /ቤት   ስም  የማቅ ድብቅ ሠራዊቶች ጩኸት ይኽ  የለውጥ  ፍሬ ምክንያት ነው። ምክንያቱም የነጋዴው የማቅ ቅጥፈት በሩ ስለሚዘጋ ስለሚበክን ነው። ከምን ጊዜውም በላይ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ  ክርስቲያን ጠንካራ አቋምና የቅድስና ሕይወት ለው ፓትርያርክ ያገኘችበት ጊዜ ቢኖር አሁን እንደሆነ ማንም የሚመሠክረው ነው። ካህናት፤ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት አባላት በአንድነት ጠንክረው ቢሠሩ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንዋ ለውጥ ያመጣሉ ብለን  ተስፋ  እናደርጋለን።

ይቆየን!

4 comments:

 1. Great article of spiritual advice to the Ethiopian Orthodox Church Sunday School members everywhere from a concerned man of God, who clearly showed his LOVE to the word of God and to his fellow Sunday School young brothers and sisters.
  GOD BLESS OUR CHURCH !!!

  ReplyDelete

 2. ሊቅነትን ተክነሀል እባክህ የእግዚአብሔር ቃል በእድሜ ዘመን ተከፋፍሎ አይቃኝም
  መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ እንዲህ ይላል

  ወደ ዕብራውያን
  5፥12 ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
  ወተት የሚያስፈልጋቸው ወጣኒ ክርስቲያኖች (አዲስ አማኞች) ጠንካራ ምግብ የሚሹ (በእግዚአብሔር ትምህርት የጎለመሱ) ይባላሉእንጂ በእግዚአብሔር ቤት በሰማንያ ቀን የተጠመቀ ሁሉ እኩል የእድሜ ጸጋ ነው ያለው የኔ ሊቅ

  ReplyDelete
 3. "ሠናይ እገሪሆሙ ለእለይዜንዉ ሠናየ ዜና" ከዚህ የበለጠ ፍትሃ ዊ ሚዛናዊ ዘገባ ከየት ይገኛል? ከዚህ ብሎግ ካልሆነ የማቅ ጊዜያዊ እስትንፋስ የሆነቺው ሐራ(የደርግ ወታደሮች) ብሎግማ ዘረኝነትን ጠባብነትን ብሔርተኝነትን ከመስበክ የዘለለ ለቤ/ን የሚጠቅም ዘገባ እንደሌላት ለማወቅ ተችሏል። ስለዚህ አባሰላማዎች እንደዚህ ዓይነቱ ሚዛነዊ ዘገባ ከማስተላለፍ ወደኋላ እንዳትሉ በርቱ ቀጥሉበት

  ReplyDelete
 4. የትኛው መዋቅር ነው ከ30 አመት በላይ ያሉት እንዲያገለግለሉ የሚያረገው?

  ReplyDelete