Wednesday, July 22, 2015

“ወሐሰት ርዕሰ ዓመፃ” “ሐሰትም የዓመፃ አበጋዝ ናት” (መዝ. 26፥12)“የሐሰት ምስክሮች” ክርስቶስን እሩቅ ብዕሲ ነው፣ ራሱን የአይሁድ ንጉሥ ብሏል ብለው የሐሰት ምስክሮችን በማደራጀት ክርስቶስ ያላለውን ብሏል፣ ያላደረገውን አድርጓል በሚል የሐሰት ክስ ለሞት የሚያበቃ ምንም ምክንያት ያልተገኘበት ሆኖ እያለ፣ ይልቁንም ለታሠሩት ነፃነትን ለተበደሉት ፍትህንና ሰላምን ይዞ መጥቶ እያለ፣ በመልካምነቱ ያልተደሰቱት አይሁድ፣ ለሁሉም ሰው እኩልነትን ስላወጀና ፈሪሳውያን በህዝቡ ላይ ያደርሱት የነበረውን ኢፍትሃዊነትና በደል ስላጋለጠባቸው ነቃብን፣ በሕዝቡ ዘንድ የነበን ክብር ይቀንሳል በሚል ሥጋት የክብር ጌታ በውሸት በጥላቻ ተነሳስተው ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት፡፡ እግዚአብሔር የሐሰትን አደገኛነት ይህን አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት የገለጸለት ንጉስ ቅዱስ ዳዊት ሐሰት መናገርና መመስከር አደገኛ መሆኑን ስለተረዳ፣ ሐሰት የኃጢአት ሁሉ አውራ አበጋዝ ናት አለ፡፡ ሐሰት ታሪክን ስለሚያበላሽና እውነተኞችንና ንፁሃን ስለሚያስገድል “ወሐሰት ርዕሰ ዓመፃ የሐሰት ምስክርነት የኃጢአት ሁሉ ራስ ነው አለ፡፡
        የአገራችን ታሪክ ስንመረምር የተከናወኑ በጎ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል ትልልቅ ስህተቶች ተፈፅመዋል፡፡ በአገራችን የገባው ስህተት እውነትን አስለቅቆ የእውነት ቦታ ነጥቆ ይኖራል፡፡ በሌላው ዓለም ስህተቶች ሲገቡ ተነቅሰው ይወጣሉ፣ በአገራችን ግን ተተክለው ይቀራሉ፡፡ እንዲጸኑና እውነት መስለውና የእውነትን ቦታ ነጥቀው እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡  ለምሣሌ ያህል ብንጠቅስ ዘርዓ ያዕቆብ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የፈጃቸውን ሰማዕታት ማለትም ደቂቀ እስጢፋኖስ የተባሉት ሰማእታት ለእምነታቸው ሰማዕታት ሆነው እያ ነፍሰ ገዳዩ ዘርዓ ያዕቆብ ፃድቅ ስለ ሃይማኖታቸው የሞቱትን ሰማእታት ደግሞ መናፍቃን ብለው ታሪክ አጣመው ፃፉ ደብተሮች ምክንያት እስከ አሁን ድረስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ትልቅ ጠባሳ ሆኖ ንስሃ ትገባበት ሲገባ፣ ጭራሽ በየትኛውም ሃይማኖት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሰ ገዳዩን ፃድቅ እያለች ትገኛለች፡፡ 

ነፍሰ ገዳይ ጻድቅ ሊሆን አይችልም ይህ ሳፋሪ ታሪክ መሆኑ እየታወቀ ርግማንም ሆኖ እያለ ለደቂቀ ዘርዓ ያዕቆብ ክብርና ዝና ሲባል ቤተክርስቲያናችን ዘርዓ ያዕቆብ ፅላት ተቀርፆለታል እየተባለ ይነገራል፡፡ አባይ ማደሪያ የለው …” እንደሚባለው ዘርዓ ያዕቆብ ራሱ መኖሪያው ሲኦል ሆኖ እያለ፣ “ዘፀውአ ስመከ ወዘገብረ ተዝካረከ” እየተባለ በስሙ ብዙ ነገር ይደረጋል፡፡ ዘርዓ ያዕቆብ ራሱ መኖሪያው ሲኦል ነው ስንል የእግዚአብሔር ቃል ሰው መግደል ይቅርና ወንድን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ (1ዮሐ. 3፡15) ስለሚል፣ ከቃሉ ተነስተን ስንመዝነው ዘርዓ ያዕቆብ ሰዎችን ሊያማልድ ቀርቶ የሱ መኖሪያ ሲኦል መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ለክርስቶስ ብሎ የሞተርስቱ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡
የአገራችን ታሪክ ፀሐፊ ተብዎች ግን ፃድቁን ነሰ ገዳይ ብለው እስጢፋኖስ የተባለ ስሙን ቀይረው  የሰይጣን ስም በመስጠት እስጢፋ እያለ ምድረ ደብተራ ምንም ሳይሰቀጥጠው ሰማዕቱን አባ እስጢፋኖስ በማህሌ ፅጌው ሐሳዊ በማለት ሲራገም ያድራል፡፡ እስ በእውነት እናተውል! ሞትን ያህል ነገር ተጋፍጦ ለሃይማኖት መሞት ውሸታም ያሰኛልን? በዚ አጋጣሚ ይህን ታሪክ እንድናስተውልና እንድንረዳ ያደረጉንን እውነተኛ የታሪክ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌን እግዚአብሔር ይባርካቸው እንላለን፡፡ እርሳቸው ቀድመው የደቂቀ እስጢፋኖስን ገድላት ባያወጡልን ኖሮ ማኅበረ ቅዱሳን የጀመረውን የአፄ ዘርዓ ያዕቆብን የተሳሳተ ጻድቅነት ለማጽደቅ የጀመረው ግስጋሴ ባልተገታም ነበር፡፡
በመሠረቱ ታሪክ ለመጻፍ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ እንዳሉት ሦስት የእግዚአብሔር ስጦታዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እነሱም
1ኛ. ተመልካች ልቦና የተረገውን ለማስተዋል
2ኛ. የማያደላ አእምሮ በተደረገው ነገር ለመፍረድ (በእውነት ለመፍረድ ማለት ነው)፣
3. የጠራ የቋንቋ አገባብ ችሎታ ያለው ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ደቂቀ ዘርዓ ያዕቆብ የሆኑት ቆች በዚህ መንገድ የማያስቡ በመሆናቸው የንፁ ሰዎች ታሪክ የማበላሸት አባዜያቸው ጮኾ ያልወጣው መንፈሳቸው እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ታሪክ ሲያጎድፍና ሲያበላሽ ይኖራል፡፡
ከዚህ ቀደም በአባ ሰላማ ብሎግ ላይ እንዲወጣ የላክነውና የወጣው ጽሑፋችን ሁለት ሰዎች የሠሩትን መልካም ሥራና ጥሩ ታሪካቸውን ይዞ ነበር፡፡ እነሱም ሊቀጠበብት ኤልያስና ሊቀትጉሃን ገብረ መስቀል የተባሉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች ናቸው፡፡ እነርሱ በልደታና በኡራኤል ቤተክርስቲያን የሠሩትን የማጣራትና ኦዲት የማድረግ መልካም ሥራ ጠቅሰን ለቤተክርስቲያን ያደረጉት አስተዋፅኦ በታሪክ የማይረሳ መሆኑን መስክረን ነበር፡፡ ይኸውና የሠሩት መልካም ሥራ ፍሬ አፍርቶ በልደታ ቤተክርስቲያን በተፈፀመው ጥፋት ማለትም ሂሳብ ሹሙና ገንዘብ ያዥዋ ሁለቱም በሠሩት ከባድ ጥፋት በሊቀ ጠበብት ኤልያስ ከፍተኛ ጥረት ጥፋተኞቹ በህግ ሊወሰንባቸው ችሏል፡፡ በማህደረ ስብሃት ቅ/ልደታ ቤተክርቲያን የተፈፀመው የሥራ ግድፈት ከባድና ሊደረስበት የማይችል ዓይነትና ውስብስብ በመሆኑ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በጉዳዩ ፍትህ ለማግኘት የተሄደውን ረጅም ርቀትና እልህ አስጨራሽ ትግል ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተገቢውን መሥዋዕትነት የከፈሉ መሆናቸውን  የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በማህደረ ስብሃት ቅ/ልደታ የሚታተመው ጋዜጣ “ዜና ማኅደረ ስብሐት” ሰኔ 27/2007 ዓ.ም እትሙ በወጣው ዘገባ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ስለሆነም ሊቀጠበብት ኤልያስ ለተገኘው መልካም ድል ባለውለታ ነውና እግዚአብሔር ያቆየው እንደርሱ ያሉ እውነተኞች ሰዎችን ያብዛልን ማለት እንወዳለን፡፡ 


በአንፃሩ ጋዜጣው በጉቦና በጥቅም የታወሩትንና ለሆዳቸው ብለው እውነትን በውሸት የቀየሩትንና የሃይማኖት ካባ እየለበሱ የሚዋሹትን ደግሞ በእግዚአብሔርና በታሪክ እንደሚወቀሱ አስነብቧል፡፡ እውነታው ይሄ ሆኖ እያለ በነማቅ ወገን “ሐራ” የተባለው ድረ ገጽ ጽድቅ የሰራውን ኃጢአተኛ ማድረግ ልማዱ ነውና እውነቱን ወደ ውሸት በመቀየር ሊቀጠበብት ኢልያስ የሠራውን መልካም ሥራ ለማንቋሸሽ ሲሯሯጥ ነው የሰነበተው፡፡ እውነት የሚተናነቀውና ሐሰትን እንደ ውሃ የሚጨልጠው ሐራ፣ ወተቱን አጥቁሮ ማሩን አምርሮ ለማቅረብ ቢሯሯጥም የደብሩ ጋዜጣ ግን እውነቱን ማውጣቱ ከዚህ ቀደም የጻፍነውን እውነት ያረጋገጠልን ብቻ ሳይሆን የሐራን ቆሞ የሚሄድ ውሸት ያጋለጠን ሆኗል፡፡
እነሐራ “ጉቦ በልቶ ሊያበላሸው ነበር” እያሉ ዓይን ያወጣ ውሸት ሲዋሹ አንብበናል፡፡ “ሐራ” የአቡሃ ለሐሰት የግብር ልጅ ስለሆነ ውሸት መናገርና በቁም መቀደድ እንጂ እውነት በአጠገቡም አላለፈምና ቢዋሽ ሥራው ነው ከማለት በቀር ምንም ማለት አንችልም፡፡ “ሐራ” እውነትን መመስከር ቢያቅተው ከመዋሸት ይልቅ ዝም ቢል ምን ነበረበት? ሲጀመር እውነታውን ያወጣው ሊቀጠበብት ሆኖ እያለና ይህ ሐቅ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም እስከ ሆነ ድረስ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ቤተክርስቲያን ማንም የላትም ባዩ ሰማእተ ሐሰት ሐራ መመስከርና ከሐቀኞች ጎን መሰለፍ ሲገባው፣ “ህየንተ ሰናይት ፈደዩኒ እኪተ” እንደተባለው በሽልማት ፈንታ ስም ወደ ማጥፋት ነው የዞረው፡፡ ከዚህ ማን ነው ተጠቃሚው? መቆርቆርስ ለማን ነው? ለእግዚአብሔር ነው ወይስ ለሰይጣን? ኧረ ማቆች አስተውሉ ንስሃም ግቡ እውነተኛውን መኮነን አቁሙ፣ እውነተኞችን ሰዎች መግፋት ይቁም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሐሰት “ርእሰ አመፃ” ተብሏልና፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት  

2 comments:

 1. የጠፋ እንግዳ ነን!የአባ ሰላማ ጽሑፎች ጭብጥመደጋገም፣ችኮ መቻንካነት--ክሊሺነት አሰልችቶን ትተናቸው ነበር!ሆኖም ዛሬ በስመ-ካሕን የሚቀስጡ ቁንጽሎችን ስላየን በእለተ-ሐሙስ ቁርሳችንን ዳቦ በወተት እየበላን የሚከተለውን እንላለን!ጀመርን…
  1. ርእሱ ጥሩ ነው!ሌላው ዘበዘባ ነው!ዘርዓያዕቆብ ለቅድስት ቤተክርስቲያንና ለሀገር የዋለውን ውለታ አንድ ጥራዝ ነጠቅ ለአጀንዳው እንዲመች አድርጎ ስለጠመዘዘው ዝቅ አናደርገውም፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስ በመነሻቸው አካባቢ ያራመዱት አቋም ከነባሩ ትውፊት ጋር ስለማይጣጣም ክርክር ተደርጎና የነ ቅዱስ ያሬድ ዜማ፣የአበው ትውፊት፣የአኃት አብያተክርስቲያናት አስተምህሮ ታይቶ ተወግዘዋል፡፡እርምጃው በውግዘቱ መቆም ሲገባው ዘርዓያዕቆብ የአካል ቅጣት መጨመሩ ተገቢ አልነበረም፡፡ግን ሆነ፡፡እንዲህ አይነት ቅጣት እንኳንስ በዘርዓያዕቆብ ዘመን በቅርቡ በአጼ ዮሐንስ ዘመን በቦሩ ሜዳ ከዚህ የተመሳሰለ ቅጣት ተፈጽሟል፡፡ያ ማለት ግን አጼ ዮሐንስ ለቤ/ክ እና ለሀገር የዋሉትን ውለታ ይሰርዘዋል ማለት አይደለም፡፡የዘርዓያዕቆብም እንደዛው፡፡ደግ ደጉን በአደባባይ እንናገርለታለን፡፡ደካማ ጎኑን በመዝገብ ቤት እናኖረዋለን፡፡አለቀ፡፡እንኳንስ የኛ ሀገሮቹ በስንት ባዕድ አምልኮ መካከል ያሉ አማንያን ነገሥታት በስንት የበቁ ነቢያት የሚታገዙት እነ ዳዊትና ሰሎሞንም ታሪካቸው ምሉዕ አይደለም፡፡የኔ ጥራዝ ነጠቅ፣ራስ-አገዝ፣ስመ-ካሕን፣ተልሚድ--እግረ-ተማሪ አትቀስጥማ፡፡ይልቅስ አትሮንሱ ስር ቁጭ ብለህ አንብብ፡፡ኦ አዛል!ንበር ታሕተ-እግረ-ሊቃውንት!
  2. ዘርዓያዕቆብ ባዕድ አምልኮን በማጥፋት፣ሥነ-ጽሑፍን በማነቃቃት፣የአዳል ሙስሊም ወራሪዎችን በብቃት መክቶ ተዋሕዶን ከነክብሯ ለትውልድ በማስተላለፍ የሰራው ውለታ ሺህ ጊዜ ተሰብስበህ ብትንጫጫ ልትፍቀው አትችልም፡፡ቅድስና ለዘርዓያዕቆብ ተሰጠው ምናምን እያልክ የምትደርተው አንተ ነህ፡፡እንጅ ዘርዓያዕቆብ ቅዱስ ተብሎ ጽላት ተቀረጸለት የሚል ታሪክም እውነታም የለም፡፡አለቀ፡፡ለግብዝነትህ እንዲመች የሌለ ታሪክ አትፍጠር!ያለውን ሳታነብ፤በሌለው አትንደፋደፍ!ተገኃሥ እቡይ!
  3. ‹‹ዘርዓያዕቆብ መኖሪያው በሲኦል ነው›› የሚለው ምውት አባባል ምናልባት ሰሞኑን ‹‹አቡነ ጳውሎስ ተኮነኑ፤ጠ/ሚ/መለስ ገነት ገባ›› እያለ የሚለፍፈው ከሞት ተነሳሁ ባይ ጴንጤ አጋብቶብህ እንዳይሆን!መጀመሪያ ነገር አንድ ሰው በፈጣሪው ፊት ይዳን ወይም ይፈረድበት ምድራዊ ሥጋ ለባሽ ሊያውቅ የሚችልበት መንገድ የለም፡፡ፍርዱን ለአንድዬ ተውለት፡፡ድኜያለሁ፣ጸድቄያለሁ ብሎ ፉክራ፤እናቴ ሳትድን፣አክስቴ ጌታን ሳታውቅ ብሎ መታበይ በየመንገዱ የሰለቼን የሞኝ ስብከት ነው፡፡ልድገምልህና የዘርዓያዕቆብ መጽደቅና መኮነን በአንዱ ስለኃጢኣታችን በሞተልን የድንግል ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነው፡፡ላዚምልህ…ንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሐ ዘተሰቅለ በእንተ ኃጥኣን…
  4. ‹‹ጌታ--እግዚእ›› ስለው ደግሞ እንዳንተ የአንገት በላይ መመጻደቂያ ሳይሆን ትርጉሙ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ማለት መሆኑን አውቄ ነው--ጌታ!! ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው›› ስንል ‹‹የኢየሱስ የባሕርይ ኣባቱ እ/ሄር አብ ነው››፤ስለዚህ ድንግል የወለደችው አምላክ ወልደ-አምላክን ነው፤እናም ወላዲተአምላክ መባሉ ትልቅ የምስጢተ-ሥጋዌ መግለጫ የሆነ ቃል ነው ማለታችን ነው!አለቀ!ዘርዓያዕቆብ የምንወዳትን እናት ስላከበረልን እናከብረዋለን፡፡አንዳንድ በድርሰቱ መካከል የገቡና ለቅን አማንያን በቀላሉ የሚገቡ፤ለፀጉር ሰንጣቂዎች ደግሞ በር የሚከፍቱ ቃላት ካሉ ዐረፍተ-ነገሩ ወይም ሐረጉ ብቻ ተለይቶ ልክ በቦሩ ሜዳ እንደሆነው በጉባኤ-ሊቃውንት እንዲቃና ይደረጋል፡፡እንጅ ማንም ዘመን አመጣሽ በነፈሰበት የሚነፍስ የሉተር ውላጅ የሸዋ ዳቦ በቀደደው አፉ እየተነሳ ቤ/ክ ንስሀ ትግባ፣አርጅታለች ትታደስ፣መጻሕፍቷ ተሰብስበው ይቃጠሉ፣ጌታን እናስተዋውቃት፣ማቅ ፈነጨባት፣ካሕናቷ እንዲህ ናቸው፣ምዕመናኗ እንዲህ ያደርጋሉ፣ላላላ…ቢል ከቶም ልብ እና አቅል አንሰጠውም!እንደ አሮጌ እባብ ዘመን በመጣ ቁጥር ቆዳውን የሚገፍና ከዘመናዊነት ጋር አሸሼ ገዳሜ የሚል ኁልቆመሳፍርት የሌለው የሉተር ውላጅ ሁሉ አጥንትና ደም ተከፍሎበት በምስራቅ አፍሪካ ማማ ብቻውን በጀግንነት ቆሞ የኖረ ንጥር ኦርቶዶክሳዊ ዶግማ እንዳሻው እንዲቆነጽለው የማንፈቅድ ብዙዎች ነን!ይሄን ያዙልኝ!ለብው አብዳን ሕዝብ!
  ይቀጥላል….

  ReplyDelete
 2. ……..የቀጠለ
  5. ወደ ተነሳው ርእስ ስመጣ፡-አዎ!እውነት ነው!በቤ/ክ ዘረፋ አለ!እሱ የምግባር ችግር ነው!የምግባር ነገር እያደር ይሆናል!ችግሩ በዋናነት የሃይማኖት አይደለም!ደግሞም ዘረፋው ከበፊቱ ሲነጻጸር ጨመረ ተባለ እንጅ ከፕሮቴስታንት ይነጻጸር ቢባል ኖሮ በእርግጠኝነት ከቤተ-ፕሮቴስታንት ፓስተሮች 90 በመቶ በላይ መገኛቸው ቃሊቲ ይሆን ነበር!ሰማህ፡-የኛ ቄሶች እኮ እንደነ እንትና ቸርች በፈረንጅ ምጽዋት ሳይሆን ከመበለታት መቀነት የተገኘች ሽራፊ ሳንቲም አጠራቅመው ለ150 ከምናምን የሚሆን ሰራተኛ ደሞዝ ከፍለው፣ለሀ/ስብከት 20 በመቶ ፐርሰንታቸውን ከፍለው፣ለአባይ ቦንድና ለአክሱም ሙዚየም በሚሊዮናት አዋጥተው፣የተወሰኑ ልማቶችን በአጥቢያቸው አልምተው፣…ከዚያ የተረፈውን ነው የሚቀነጣጥቡት!ባንድ ጎጥ 6 እና 7 ቸርች እየሸነሸኑ ድቤ እየመቱ፣የለበሱትን ሱፍና ሸሚዝ ፕስስስ እያስባሉ፣ባሕልን አስንቀው በታይት እያስዘለሉ፣በጊታርና ኪቦርድ ኮርኒስ እስኪፈርስ እየጨፈሩ፣ባጓጉል ጥንቆላ መሰል ትንቢታዊ ኮንፈረንስ ተብዬ እያወናበዱ፣ልሳን በሚል ፈሊጥ እየተንተባተቡ፣በስመ-ፈውስና ጸሎት በየባለትዳሩ ቤት እየተንጎዳጎዱ፣…በሰበሰቡት ረብጣ የሚደላንቀቁ የማያምኑ ሰባኪዎች ጋር ሲነጻጸር የኛ ካሕናት ኑሮና ምግባር እጅጉን የተሻለ ነው!ኢየኃፍር አንሰ ህየንቴሆሙ!
  6. እውነት ነው!ሐራ ወገናዊነት አለበት!እሱን ሳትነግረን በደንብ እናውቃለን!ባለን አቅም ይህንኑ በኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት ነግረናቸዋል!ያ ማለት ግን እነ ሊቀጠበብት ኤልያስ ንጹሓን ናቸው ማለት አይደለም!ቢያንስ አዲስ ቅጥረኞችን በፔሮል ለመትከልና ደሞዝ ለማስጨመር ብዙ መማለጃ እንደሚቀበሉ እናውቃለን!አሳምረን እናውቃለን!ይህ ሲባል ኤልያስ ልደታ ላይ የሰራው መልካም ስራ ካለ ይሸፈንበታል ማለት አይደለም!እንደውም ላለፈው ስራው ንስሐ ገብቶ በአዲስ መንፈስ መነሳቱ እሰየው ነው!ድሮም የራስ ወዳድነት እንጅ የአቅም ችግርና የሃይማኖት ህጸጽ እንደሌለበት እናውቃለን!ይሕን ስለምናውቅ ነው ሞላጫ ተሐድሶዎቹ እነ አባ ሰላማ ሳይወከሉ የነ የማነ እና የነ ኤልያስ ቃል-አቀባይ መስለው ሲንጎዳጎዱ ‹‹እፎ-እፎ--እኮ እንዴት?!›› የምንለው!
  7. አንተ ግን፡- በሀ/ስብከቱ ካሕናት ስም አትነግድ!ዝምብሎ ያሉበትን አጥቢያ እንኳ ሳይጠቅሱ ‹‹እኛ የአ/አ/ሀ/ስብከት ካሕናት›› ማለት ነውር ነው!ሳትመረጥ፤ሳትወከል ‹‹እኛ›› አትበል!ነውር ነው!ያላየኸውንና ያላነበብከውን አትጻፍ!ዘርዓያዕቆብ በኢኦተቤክ ቅድስና አልተሰጠውም፤ቅዱስ አይባልም!ገናና እና ታላቅ ንጉሣችን መሆኑን ግን አሁንም ላረጋግጥልህ--እንደ ቴዎድሮስ፣ዮሐንስ፣ምኒልክ፣አምደጽዮን፣…!እንጅ እንደ ካሌብ፣ገ/መስቀል፣አብርሃ ወአጽብሃ፣ላሊበላ፣ሐርቤ…ከቅዱሳኑ ወገን አልተቆጠረም!እባክህ በንባብህ ልክ ተናገር፣ሳትወከል እንደራሴ አትሁን፣ምግባር ከሃይማኖት አትቀላቅል፣ታሪክና ገድል አታማታ፣አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለይ፣ተቋም ለመምከር አትንጋጥ፣ማሊያ ገልብጠህ አትጫወት!ጽናሕ፤ወነስሕ!!!
  ምክንያቱም አያምርብህም!የኛ የሆነውን ካልሆነው መለየት እጅግ ቀላል ከሆነ ሰነበተ!ኦ ቀሳጢት አእመርናኪ!እመ ነሳሕኪ ተመየጢ፤ወለእመ ኢነሳሕኪ ኢትኩኒ ቀሳጢተ ወቀበያውባጢተ በስመ-ልዑካን ካሕናት ዘተጸውኡ ለተልእኮ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት እንተ አልባቲ ርስሐት!ለዚህ የሌለ ዘር ዘሪነትሽ ለምን አንድ ግእዝ ጉባኤ-ቃና ጀባ አንልሽም፤በዚያውም ለቅኔው ፍችና ሙያ ስጭ…እህሳ…ካሕን አይደለሽ?…ነይ አንቺ ቁንጽል…ሳይጠሩሽ አቤት የምትይ…የኛን የካሕናትን ስም ይዘሽ ስማችንን በአነጋገረሽ የምታጎድፊ…ተቀበይ…
  ፀሐፌ-ሐሜት ቁንጽል፡ዘኢይፀዋዕ ጽዋዔ፣
  ዘእንበለ-ዘርእ ኮነ፣ዘኢይዘራዕ ዘራዔ፡፡፡፡፡

  ReplyDelete