Saturday, July 11, 2015

የሰበካው (የአጥቢያው) አባል ያልነበረው የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቀመንበር ከኃላፊነቱ ተነሣየደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሰበካ አባል ሳይሆን በተጭበረበረ መንገድ የሰበካ ጉባኤው ም/ሊቀመንበር ሆኖ የቆየው ዮናስ ሽፈራው ከም/ሊቀመንበርነትና አባልነት ተሰናበተ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን አባልነትና ደጋፊነት የሚታወቀው ይህ ግለሰብ በተጭበረበረና ከቃለ ኣዋዲው ደንብና መመሪያ ውጪ የተመረጠ በመሆኑና በኃላፊነት በቆየባቸው ዓመታትም የቃለ ዐዋዲውን ደንብና መመሪያ አክብሮና ጠብቆ ባመለገኘቱ ሊሰናበት እንደቻለ የተጻፈበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡ በተደረገው ማጣራትም ግለሰቡ ለደብሩ የሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያበቃ በቂ ማስረጃ እንደሌለው ከባሕር መዝገቡ ተረጋግጧል፡፡ 
በእግድ ደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው ግለሰቡ በግንቦቱ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት ላይ ከኃላፊነቱ ውጪ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች በማስተባበር የጉባኤውን መክፈቻ በማደናቀፍ፣ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር የ2007 ዓ.ም. የፋሲካን በዓል ምክንያት በማደረግ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህሙማን ድጋፍ በሚል የሰበሰበውንና የት እንደደረሰ ያልታወቀውን ገንዘብና ሌሎችንም ጥፋቶች መሰረት በማድረግ የአመራር ለውጥ ለማድረግ በተጠራው ስብሰባ ላይ ችግር ሲፈጥር በመገኘቱና በሌሎችም ምክንያቶች ከኃላፊነቱ ሊነሳ ችሏል፡፡ ይህ ግለሰብ እስካሁን የተደረሰበት የሰበካው አባል ሳይሆን የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቀመንበር የሆነ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡  

ዮናስ ሽፈራው ለቦታው ሰላም መደፍረስ ለስብከተ ወንጌል የተመደበውን በጀት አልፈርምም በሚልና በሌሎችም ምክንያቶች ለስብከተ ወንጌል መዳከም ምክንያት ነው፡፡ ግለሰቡ ከኃላፊነቱ መነሳቱ ብቻ ሳይሆን ከህግና ከሥርዓት ውጪ በተሸጠው የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆነ ቤት ጉዳይ እጁ ስላለበት በህግ ሊጠየቅ ይገባል የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ቤቱን ደግሞ ይድነቃቸው ወይም እስጢፋኖስ ናቸው የገዙት የሚል ከፍተኛ ግምት አለ፡፡
ከዮናስ ሌላ ያለ አጥቢያው የዚሁ ሰበካ ጉባኤ አባል የነበረው ዶ/ር ኃይሉ በሰበካው አባልነት የተመዘገበው ከቃለ ኣዋዲው ደንብና መመሪያ ውጪ ከተመረጠ በኋላ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እርሱና ሌሎቹም ያለአጥቢያቸው የሠበካ ጉባኤ አባላት ሆነው የተመረጡትን የጀሞውን የሰንበት ት/ቤት ሊቀመንበር መንክርን፣ የወይራ ሰፈሩን የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ይድነቃቸውን ሕጋዊነት ማጣራትና ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
ሰዎች ያለ አጥቢያቸው የሰበካ ጉባኤ አመራርም እንዲይዙ የሚያደርጋቸው ማነው? ከሚለው ጥያቄ በስተጀርባ ማኅበረ ቅዱሳን እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በየደብሩ ያለውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በቁጥጥሩ ስር ለማዋልና ያሻውን ለማድረግ እንደ ሆነ ከእነዚህ ሰዎች ተሞክሮ መረዳት ይቻላል፡፡ ማቅ እንዲህ ሲያደርግ በየሰበካ ጉባኤው የሰገሰጋቸው ግለሰቦች ቤተ ክርስቲያንን የማያውቁ ብቻ ሳይሆኑ ቤተክርስቲያንም የማታውቃቸው መሆናቸው ይገርማል፡፡ የሰበካ ጉባኤ አባል ለመሆን ደግሞ የአጥቢያው አባል መሆን የግድ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህን እያወቀ ህጉን በመጣስ የእርሱን ዓላማና የሚያስፈጽሙለትንና ጥቅሙን የሚያስጠብቁለትን ግለሰቦች ከማይታወቁበት ቦታ እያመጣ ቤተክርስቲያንን እያመሳት ይገኛል፡፡ በሌሎች አጥቢያዎችም ያሉትንና የምእመናን ተወካዮችም የሆኑትን ግለሰቦች ማንነትና የአጥቢያው ምእመናን መሆናቸውን ማጥናት አስፈላጊ ነው፡፡
የደብሩ አስተዳደር እንዲህ ላለው እርምጃ ቢዘገይም የወሰደው እርምጃ ግን በራሱ የሚደነቅና ለሌሎችም ደብሮች ምሳሌ የሚሆን ነው፡፡ ስለዚህ ሌሎች ደብሮች ይህን አርኣያ ተከትለው ሰበካ ጉባኤዎቻቸውን መፈተሽ አለባቸው፡፡ ሀገረ ስብከቱም እንዲህ ያለውን ውሳኔ በተገቢው መንገድ አጣርቶ ውሳኔውን ሊያጸና እንደሚገባ፣ በተጨማሪም ተንጠልጥሎ ያለውን የሠንበት ት/ቤት አመራር የመለወጥ ውሳኔን ያዘገየው ምን እንደሆነ ማጣራትና የአመራር ለውጡን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ብዙዎች እየጠየቁ ነው፡፡      

2 comments:

 1. የብሔረፅጌ ማርያሙ ነአኵቶ ለአብና የላፍቶ ሚካኤሉ ተክለማርያም በተለየ መልኩ የቤተክርስቲያን ቦታ እየሸነሸኑ የማከራየት መብት የተሰጣቸው ናቸው፡፡ነአኵቶ መመሪያ ከወጣ በኋላ ወደወንዙ(ወደ አቃቂ) ያለውን ይዞታ ቀኑን መመሪያው ከመውጣቱ በፊት(back-date) በማድረግ የቦሌ ቡልቡላን ይዞታ ለጋራዥነት ከያዘው ግለሰብ ጋር የጋራዥ የኪራይ ውል የተዋወለ ሲሆን ተክለማርያም በበኵሉ የቅ/ገብርኤልን ጸበል ይዞታ ቆርጦ እንዲሁ በ19ሺህ ብር አከራይቷል፡፡የመቃብርና የሐውልት ብር የቢሮ ሰራተኞችና የአለቆቹ መክበሪያ ነው፡፡
  ሁለቱም አለቆች ሲበዛ እልኸኞች፣ቂመኞች፣ተገለባባጮች፣በአንድ ብሔር ጥላቻ የተለከፉ፣በግልጽ ጸጥታ ሲነግሥ ይጨንቀናል የሚሉ፣በራሳቸው ስልጣን ባልተገባ መንገድ በሰፊው የሰራተኛ ቅጥር የሚፈጽሙ፣ሰ/ተማሪና ካሕን ሰው የማይመስላቸው፣ከምዕመን አስከ ሊቃውንት ርስበርስ በመከፋፈል የሚያናክሱ፣አንደበታቸውን የማይቆጣጠሩ፣በየፍርድ ቤቱና በየፖሊስ ጣቢያው ከዘበኛ እስከ ጸሐፊ እየተካሰሱ በቤተክርስቲያን ብር መቀለዳቸው ሳያንስ እከሌ የተባለውን ቄስ በፍርድ ቤት ስላሸነፍነው እልል በሉ የሚሉ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያን ለዛ የሌላቸው ግለሰቦች ናቸው፡፡
  ሆኖም ማሙየ የክፍለከተማው ስራ አስኪያጅ እያለ እሱን እየተንከባከቡ፣ሊቀአእላፍ በላይ ሲመጣ እግር ለግር እየተከተሉ አሁን እነ የማነ ሲሾሙ ደግሞ ለሦስት አመታት ከአድማ እና ተራ ካሕናትን ከማስለቀስ በቀር የረባ ስራ ያልሰሩበትን ደብር እነ ተክለማርያም ደርሰው የልማት አርበኛ ለመባል እነ የማነን ጋብዘው ዜናውን በሀገረስብከቱ ዌብሳይት አስወጥተዋል፡፡ብቻ ያሳዝናል፡፡የተገፉ ካሕናትና ሰ/ተማሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቅዱስ ፓትርያርኩ አጣሪ የላኩበት ደብር የአጣሪው ሪፖርት ሳይሰማ ካሕናቱ የአማሳኞች በትር ሰለባ ይሆናሉ፡፡ጥቆማዎችና ማስረጃዎች የሀገረስብከቱ መዝገብ ቤት ውጡዋቸው ይቀራሉ፡፡ከዛ ያ ፍትሕ አገኛለሁ ብሎ የተነሣ ካሕን በላተኛውን አለቃ ይማጸናል፡፡ደሃ ተበድሎም ይቅርታ ይለምናል፡፡መቆርቆር ሞኝነት ይሆናል፡፡ዝምታ ወርቅ ይሏት ብሂል ትነግሣለች፡፡
  አንድ አለቃ የልጆች አባት የሆነና ከቤተክርስቲያን ውጭ ትም ሄዶ ሰርቶ ለመብላት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት የሌለውን ካሕን/መሪጌታ አባሮ ለአንድና ለሁለት አመት ቢያንገለታ ትልቁ ቅጣት ሰራተኛውን ወደ ስራው መልስ የሚል ነው፡፡ላንገላታበትና ለተሳሰተ አስተዳደራዊ ውሳኔው አይጠየቅም፡፡ስለዚህ የካሕናት እጣፈንታ በአንድ አለቃና ፀሐፊ እጅ ነው፡፡በስንት ጉባኤ የዋሉ መምህራንም እንዲሁ በእንደነ ለአኵቶ እና ተክለማርያም ባሉ ወፈፌዎች እየተሸማቀቁ እጣቸው አንድም አንገት ደፍቶ መኖር ያ ካልሆነም ከስራና ደሞዝ ታግዶ በ31 ቁጥር አውቶብስ ከለገሀር 4 ኪሎ እየተመላለሱ አዳዲስ ሹማምንትን ደጅ መጥናት ሆኗል፡፡ይሄ ያሳዝናል፡፡ቤተክርስቲያን በየጉባኤው የደከሙላትን ገፍታ ብልጣብልጦችን አንግሣ ልጆቿ በቤታቸው ባይተዋር ሲሆኑ ማየት ያማል፡፡
  እነ የማነ እና በጉባኤ ቤት ያለፈው ሊቁ መጋቤ ብሉይ አእመረ ወደ መንበሩ ሲመጡ እንዲህ አይነት በካሕናትና በሊቃውንት ላይ የሚደርስ አስተዳደራዊ በደል ይረግባል ብለን ጓጉተን ነበር፡፡የተስፋችንን ፍጻሜ ለማየት አልታደልንም መሰል፡፡ዛሬም እነዚህ ሰዎች አንድ ሰሞን በተፈጠረው በሰንበት ትምህርት ቤቶችና ሀገረስብከቱ ጊዜያዊ አለመግባባት ሽፋን የሀገረስብከቱ ቀራቢ መስለውና በአስተዳደሩ ተመክተው የቀደመ አስጸያፊ እና ብሔር ተኮር የሆነ ዘመቻቸውን እንዲሁም ከገንዘብ ያዥ፣ከሂሳብ ሹም፣ከቁጥጥርና ከጸሐፊ ጋር የተቀናጀ ስልታዊ ዘረፋቸውን ቀጥለዋል፡፡ከስራ ያስቀየሩትም እንደተቀየረ፣ያባረሩትም እንደተባረረ፣ከደረጃ ያወረዱትም እንደወረደ፣ያጎደሉትም ሂሳብ በፓትርያርኩ እንዲጣራ ቢታዘዝም ምርመራው በሀገረስብከቱ እንደተዳፈነ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ሁኖ ይቅር ተብሏል፡፡
  የነ የማነና የነ አእመረ የአጥቢያ ጉብኝት ካሕናትንና ሰንበት ተማሪዎችን እንዲሁም ምዕመናን ሳይሆን አለቆችንና የቢሮ ሰራተኞችን ብቻ እያነጋገሩ ካንድ ወገን የሚመነጭ መረጃን ይዞ ለመሄድ ከሆነ ባይደረግ ይሻላል፡፡ስራ አስኪያጁ በእጄ ስለሆነ ወላ ሰንበት ተማሪ፤ወላ ተራ ሰራተኛ ለጥ ሰጥ ብለሽ ተገዢ ለሚሉ እንደ ተክለማርያም አይነት ግብዝ አለቆች የልብ ልብ ሰጥቶ የካሕናትንና ሰንበት ት/ቤትን ሰቆቃ ማራዘም ተገቢ አይደለም፡፡
  ይባስ ተብሎ ነአኵቶለአብ የፈለገውን የሚያስቀይርበት፣ተክለማርያም ያላግባብ ያባረረውን ሰራተኛ መልስ ተብሎም በግልጽ አልመልስም እያለ በሦስት አመታት ቆይታው የረባ ስራ ሳይሰራ እንደ ልማት አርበኛ የሚታይበትና በሀገረስብከቱ በይፋ እውቅና እንዲያገኝ የሆነበት አካሄድ አሳዛኝ ነው፡፡ሰውን ባልዋለበት ማመስገን ደግ አይደለም፡፡የሁለቱ አለቆች ሪከርድ በክፍለከተማው ሀገረስብከት ሳይቀር ይታወቃል፡፡ይሁንእንጅ አዲሱ የሀገረስብከት አስተዳደርም ሰዎቹን እንኳን ሊያርማቸው ጭራሽ የሞራል ድጋፍ እየሰጣቸው ይመስላል፡፡ያሳዝናል፡፡እድሜያቸውን ባለሙት ልማትና ባሰፈኑት አስተዳደራዊ ሰላም ሳይሆን ባስከፈቱት የወንጀልና የአሰሪና ሰራተኛ የክስ መዝገብ የሚለኩ ሰዎች ያሻቸውን የሚያስቀይሩበት፤ያሻቸውን ከስራ አፈናቅለው በስዕለት ብር በተገዛ ጠበቃ እያንከራተቱ ምስኪን ካሕናትን በረሀብ አለንጋ መቅጣታቸው የልማት አርበኛ ሲየሰኛቸው ማየት ያሳዝናል፡፡

  ReplyDelete
 2. DEG BILE HALL MEAZA GIN ANTENA EWIR MERIW YEMAYKEDISBET KISNA ALEGN BAYU DAWIT YARED LEBOCH LEMEHONACHIHU MISKIR YASFELGAL YENANTE ZERGNINETS MELEKIYAW MINDINEW YEABATACHIHU YEABA MATEWOS ZREGNINETINA KIFAT BAHIR KELEM HONO YEAWSTRALIYA ZAFOCH BIER HONOW BITSAF YALKAL...YETENEKABACHIHU LEBOCH.ZEREGNOCH HAYMANOTE ALBAWOCH NACHHU YIH SIL NEAKUTONA TEKLEMARYAM EWNETEGNOCH NACHEW MALETE AYEDELEM GIN YEMUDAYEMUTSIWAT TEZERFANA ZEREGNINET YETEMARUT KE.ENANTE NEW ERKUSOCH MEHAYMOCH YEKETEMA DENKOROWOCH DAWIT YARED 4KIFL TEMERKO MEMRIYA HALAFI YEHONEW BENANTE ZEREGNINET AYDELEM YEMTIGERUM FITURANIN NACHIHU

  ReplyDelete