Thursday, July 16, 2015

በሲልጤ ዞን በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት አሁንም እንደቀጠለ ነው።በሲልጤ ዞን ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን በአካባቢው የእስልምና አክራሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን ግፍና ውርደት አስመልክተው የድረሱልን ጥሪ ማቅረባቸው እና የእኛን ብሎግ ጨምሮ የተለያዩ ብሎጎች ዜናውን እንደሰሩት ይታወቃል። ይህን የድረሱልን ጥሪ ማቅረባቸው እንደ ትልቅ ስህተት ተቆጥሮ ወገኖቻችን በዞኑ አክራሪ ባለሥልጣናት ተጨማሪ እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል። እንዲያው የደረሰባቸውን ግፍ እንዲያስተባብሉም ጫና ተደርጎባቸዋል። የማስተባበያ ደብባቤው አጽፈዋቸዋል። ከዛም አልፎ በፍርድ ቤት ተከሰዋል። 


እንዲህ ያለው አካሄድ ተጨማሪ ጫናን የመፍጠር እንጂ መፍትሔ የማፈላለግ ዘመቻ እንዳልሆነ የአካበባቢው ባለሥልጣነት እንዴት እንዳልገባቸው አላወቅንም። መንግስትም በሐይማኖት ጉዳይ የሚፈጠር ቀውስ፤ ቀውሱ የተፈጠረበትን አካባቢ አልፎ ሊሄድ እንደሚችል መገንዘብ ያቅተዋል ተብሎ አይጠበቅም። ቀጣይ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች መፍትሔም አይሆኑም። ወገኖቻችን ያነሱዋቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ አለባቸው።
በሀገሪቱ ውስጥ እያቆጠቆጠ ያለ አክራሪነት መኖሩ የሚካድ አይደለም። የሲልጤ ዞን ደግሞ ዋናው የሰለፊዎች መፈልፈሊያ ነው።
ይህ ሁኔታ እርግጥ ሆኖ እያለ ጭራሽ ተበደልን ያሉ ወገኖችን ሰብስቦ ፍርድ ቤት ማቅረብ አክራሪው ሀይል የደረሰበትን የእብሪት ደረጃ ያሳያል። መንግስትም ገብቶትም ይሁን ሳይገባው የአክራሪዎቹን ሀሳብ ደግፎ ቆሞ ይታያል። ቤተክህነት እንደተለመደው አንጥፋ ተኝታለች። ለልጆችዎ የድረሱልኝ ጥሪ ምላሹ እስር ሲሆን ምንም ለማለት አልቻለችም። ወይም አልፈለገችም። ወገኖችችን ወደ ፍርድ ቤት የተወሰዱት ቤተክህነት ነገሩን በግዴለሽነት በማየትዋ ነው። አስፈላጊውን ክትትል ብታደርግና ድምጽዋን በተገቢው ሁኔታ ብታሰማ ምላሽ መገኘቱ አይቀርም ነበር።

አክራሪ ሀይል በባሕሪው እሹሩሩ አይወድም። አክራሪነት ሊጠፋ የሚችለው ሲቋቋሙት ብቻ ነው። በአገር ደረጃ ኢትዮጵያ በአክራሪው ሀይል ላይ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ጥሩ ነው። ነገር ግን መንግስትን ተደግፈው አመጽን የሚያስፋፉ አክራሪዎችን በቸልታ ማየት አያስፈልግም። በመንግስት መዋቅር ውስጥ የአክራሪው ኃይል ደጋፊዎች ለመኖራቸው እነ ጁነዲን ሳዶ ምስክር ናቸው።
አሁንም መንግስትንም ቤተክህነትንም የምንጠይቀው በሲልጤ ዞን በአክራሪዎች አየደረሰ ያለው እንግልትና ሽብር በማስተዋል ይያዝ። ተገቢው መፍትሔ ይሰጠው የሚል ነው።
ሰሞኑን የአረፋ በዓል ለማክበር ወደ ሳዑዲ የሄዱ አክራሪዎች ያደረጉት ነገር በተለያየ ሚዲያ ተለቆ እየታየ ይገኛል። ደጀ ብርሃን ብሎግ ቪዲዮውን ተመልካቾቹ እንዲያዩት ይህን ቪዲዮ በብሎጉ ላይ ሼር አድርጎታል። እንድትመለከቱት እንጋብዛለን።

 (በጉዳዩ ላይ ደጀ ብርሃን ብሎግ የጻፈውን ጽሁፍ ከዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ አቅርበነዋል።)
አንደዚህ ያለውን ነገር ቸል ማለት የሚያስከፍለው ዋጋ ይኖረዋል።
እናስብ ይታሰብበት
አሁንም አሁንም በሲልጤ ዞን በአክራሪዎች እየተንገላቱ ያሉ ወገኖቻችን ላይ ማንገላታትና ወከባው ይቁም። ችግሩ ተገቢው መፍትሔ ይሰጠው እንላለን።

  ምንጭ ደጀ ብርሃን

    በኦሮሚያ ክልል የተነሱ የአብዱል ወሀብ ጥራዝ ነጠቅ  ተከታይ ወሀቢስቶች በጅማ፤ በኢሉባቦር፤ በአርሲና በባሌ የተለያዩ ቦታዎች በኦፊሴል የተነገረና ያልተነገረ የሽብር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በአማራ ክልል ደግሞ የወሎ አክራሪ ወሀቢስቶች ቤተ ክርስቲያን ከማቃጠል አንስቶ ሰው እስከመግደል መድረሳቸውን በማስረጃ የተረጋገጠ እውነት ነው። በስልጤና ወራቤ የከተሙ አሸባሪ ፋናቲኮች ተመሳሳይ ድርጊት ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውም ፀሐይ የሞቀው፤ ሀገር ያወቀው ጉዳይ ነው። እነዚህ ሱሪያቸውን የሚያሳጥሩ፤ ካልሲያቸውን የሚያሳዩ፤ የአፍንጫቸውን ስር ጸጉር ሙልጭ አድርገው በመላጨት ጢማቸውን የሚያሳድጉ፤ ግንባራቸው ላይ የተነቀሱ እስኪመስል ድረስ ከመሬት ሲጋጩ የጠቆረ ሰውነት ከማንነት ጋር የተሸከሙ አክራሪዎች የሌላውን መብት እስካልነኩ ድረስ ተቃውሞ የማይቀርብበት ቢሆንም የድርጊታቸው ዋነኛ ምስክር ግን ለማሸበር ልዩ ምልክታቸው ሆኖ መገኘቱ ነው። ወሀቢስቶች ከሱኒና ከሱና ውጪ ያለው ሁሉ ካፊርና ከሀዲ ነው።         
ለዚህም ዓላማ ግብ መንታት መታገል፤ መዋጋትና መግደል ብሎም መሞት ጂሀድ ነው። በዚህ ዓላማ ላይ መሞት በጀና/ ገነት/ ልዩ ዓለም የሚያስገኝ ሲሆን 72 ደናግላን ሴቶች ድንግላቸውን በጂሀድ ለሞተው አሸባሪ ለማስረከብ በጥቋቁር ቀሚስ ተሸፋፍነው እንደሚጠብቋቸው ያምናሉ።

ከዚህ በታች የሚታየው ቪዲዮ በሳዑዲ የአረፋ በዓል ለማክበር የሄዱ አክራሪዎች የወቅቱ የኢትዮጵያ ባንዲራ የሆነውን ዓርማ ከተሰቀለበት አውርደው የኦነግን ባንዲራ ሲሰቅሉ ያሳያል። «ሱባንአላህ» የሚለው የኦሮሞ ኢስላሚስት አክራሪ የአማራ ባንዲራ ወርዶ የኦሮሞ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያ ይቋቋማል ይላል። በዚህ ዓይነት ኦነግ አሸባሪ አይደለምን?
እንግዲህ እነዚህ የመሳሰሉ አሸባሪዎች ናቸው፤ ኢትዮጵያ ተመልሰው ሕዝብን ከሕዝብ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ሲያጋጩ የሚስተዋለው።

ደግመን ደጋግመን የምንለው እውነታ ቢኖር ኢትዮጵያ ውስጥ ምቹ ሁኔታ ጠፍቶ እንጂ ለቁጥር የሚያታክቱ አሸባሪዎች አሉ። «አስቀድሞ ነበር፤ መጥኖ መደቆስ፤
አሁን ምን ያደርጋል፤ድስት ጥዶ ማልቀስ»
እንዳይሆን ሰላምን፤ ፍቅርን፤አንድነት፤ ኅብረትንና በጋራ አብሮ መኖርን በሚፈልጉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በኩል አካባቢንና ውስጥን የማጥራት ሥራ ከታችኛው እርከን አንስቶ እንዲደረግ ከዚህ በፊት ስንለው እንደቆየነው ሁሉ አሁንም ደግመን ለማስታወስ እንወዳለን።


4 comments:

 1. እናንተስ ማን ናችሁ? ከነሱስ በምን ትለያላችሁ? የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች አይደላችሁምን? እናንተስ ሌት ተቀን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተክርስቲያን አይሆንላችሁም እንጂ ለማጥፋት ጉርጓድ የምትምሱላት አይደላችሁምን? የት የምታውቁትን ቤተክነት ነው ደግሞ የምታሳስቡት? ለማያውቁሽ ታጠቢ ነው አይደል የተባለው። ላላወቋችሁ ልታስመሥሉና ልታታልሉ ትችሉ ይሆናል። ነገር ግን የናንተ ተግዳሮትም ከአክራሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተለየ አይደለም። እነሱም እውነትን ያሳድዱ ይቃወማሉ እናንተም እውነትን እየተቃወማችሁ ታሳድዳላችሁ።አክራሪ እስላሞችም ተደብቀውና ተመሳስለው ሰይፍን ለመምዘዝ ያደባሉ እናንተም ተደብቃችሁና ተመሳስላችሁ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በጎቿንም ለመብላት በተኩላነታችሁ ታደባላችሁ። አሁን የምትቀባጥሩት በቤተክርስቲን መከራ በመደሰት ቁማር እየተጫወታችሁ ለመሆኑ እሙን ነው። ክርስቶስን የሰቀሉት አባቶቻችሁ አምላክን ከሰቀሉት በኋላ ቁማር አይደል የቆሞሩት። ታዲያ እናንተስ ያን ብትተገብሩ ምን ያስደንቃል። ከዝብ ማር አይገኝ ቆሻሻ በሽታ አምጭ እንጂ።
  ተኩላዎች ተንቅቶባችኋልና ስለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አይመለከታችሁም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ ዳሞት አንተ በትክክል ሰይጣን ነህ። ጨለማ የጭለማ ልጅ

   Delete
 2. weYe damot min yisalehal gin?

  ReplyDelete
 3. Damot yesemiu trgwame.eda mot berasu lay teshekmo yemihed.yemisefewo neger hulu negative. Melkam neger libonawo yemayaweta fitur.memker wey megesese yemayawok besedb ejjig yeselet ene malet new.

  ReplyDelete