Tuesday, July 21, 2015

ምናለ ቤተ ክርስቲያንን መሳቂያና መሳለቂያ ባናደርጋት?

የተአምረ ማርያም አንካሳ ሀሳብ

Read in PDF 
በዲያቆን ያለው
ባለፈው ሐምሌ 5/2007 ዓ.ም. በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ ተአምረ ማርያም በድምፅ ማጉሊያ ሲነበብ እጅግ ነው ያፈርኩት፡፡ ያሳፈረኝም የተነበበው ክፍል በመጽሐፍ ቅዱስ የሚታወቅን ታሪክ ተአምረ ማርያም ወደራሱ ወስዶ የኢየሱስን ለማርያም ሰጥቶ በማቅረቡ ነው፡፡ ያን “ተአምር” መርጠው ያነበቡ ቀሳውስት ምናልባት ለበዓሉ ተስማሚ ንባብ መረጥን ብለው ልባቸው ወልቋል፡፡ ለካስ ተአምረ ማርያም ልቦለድ ነው የሚባለውን ብቻ ሳይሆን የወንጌልን እውነት ለመለወጥና የኢየሱስን አዳኝነት በማርያም ለመተካት ታልሞ የተጻፈ ነው ብዬ እንድደመድም አድርጎኛል፡፡ ምናለ ቤተ ክርስቲያንን መሳቂያ መሳለቂያ ባናደርጋት? የሚል ሐሣብም መጣብኝ፡፡  
እንደሚታወቀው ሳውል ክርስቲያኖችን እያሳደደ ወደ ደማስቆ ሲወርድ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን ካንጸባረቀበትና ምድር ላይ ከወደቀ በኋላ “ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን ድምፅ ነው የሰማው፡፡ ከዚያ ሳውል ጌታ ሆይ አንተ ማነህ? ብሎ ጠየቀ፡፡ የሰማው ድምፅም “እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው።” (የሐዋ. 9፥1-5)፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ማርያም ፈጽሞ የለችም፡፡ ተአምረ ማርያም ግን ሌላውን የ2ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ምዕራፍ 12 ክፍል ከዚህ ጋር በማገናኘት ጳውሎስ ስለማርያም እንደተናገረ አድርጎ ጽፏል፡፡
በሐዋርያት ሥራ ላይ የተጻፈው ታሪክ በ2ኛ ቆሮንቶስ ምእራፍ 12 ላይ ከተጻፈው ታሪክ ጋር የሚገናኝ አንዳች ነገር የለውም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጻፈው ሳውል ከሰማይ ብርሃን ካንጸባረቀበትና የጌታን ድምፅ ከሰማ በኋላ፣ የተናገረውንም ድምፅ ማንነት ከለየ በኋላ ተናጋሪው የሚለውን ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ “ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።” በተነሳና አይኖቹን በከፈተ ጊዜ ግን ማየት አልቻለም፡፡ ሰዎችም እየመሩት ወደ ደማስቆ ወሰዱት፡፡ ለሶስት ቀን ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ቆየ፡፡
በዚህ መካከል ግን ወደ ሶስተኛው ሰማይ ተነጠቀ የሚል ታሪክም አልተጻፈም፡፡ ያ ከዚያ በኋላ የተፈጸመ ታሪክ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ሁለቱን አያይዘው ነው የሚተረጉሙት፡፡ ለምሳሌ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ “ነቅዕ ንጹሕ” በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ እንደ ገለጡት “ቅዱስ ጳውሎስ ይህን [2ኛ ቆሮንቶስ] መልእክት የጻፈው በ፶ (፶፯) ዓ.ም. ነው፡፡ ከ፶ው ዓመት ፲፬ ሲነሣለት ፴፮ ዓመት ይቀራል፡፡ እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ በመንገድ ላይ ብርሃን በርቶበት ጌታም ተገልጦለት ነበርና በአካለ ሥጋ ወይም በአካለ ነፍስ አላወቀውም እንጂ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ወጣሁ በዚያም ሰው ሊናገረው የማይቻል ነገር ሰማሁ ያለበት ዘመኑ ጌታችን በተወለደ በ፴፮ ዓመት መሆኑን ያስረዳናል፡፡” ብለዋል (ገጽ 164)፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ንባቡ ከእነ ትርጓሜው ግን ጊዜውን ከዚህ ውጪ ነው የሚያደርገው፡፡ 

ተአምረ ማርያም የተሰኘው ድርሰት ይህን የትርጓሜ ጫፍ ይዞ ታሪኩን ለማርያም በመስጠት ያልተጻፈውን ለማንበብ ይደፍራል፡፡ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፈውን ድርሰት ስናነብ ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ ያጋጠመውንና በሐዋርያት ሥራ የተጻፈውን ይተርካል፡፡ እስከ ሶስተኛው ሰማይ ከወጣ በኋላ “የደም ግባቷ እንደ ፀሓይ የሚያበራ ድንግል ከሩቅ ስትመጣ ተመለከትኩ ከሷም ጋር ሁለት መቶ መላእክት በፊትና በኋላዋ ሆነው እየዘመሩ መጡ” እያለ ያልተጻፈ ማንበቡን ይቀጥላል፡፡ ከዚያ ስለእርስዋ ማንነት ሲጠይቅ መልአኩ “ይህች አንተ የምታሳድደው የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያም ናት” ይለዋል፡፡ ለጥቆም ማርያም ወደ እርሱ መጥታ “ሳውል ሳውል ልጄን የናዝሬቱን ኢየሱስን ለምን ታሳድደዋለህ የሾለውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል” በማለት የጌታን ንግግር ደግማ ትለዋለች፡፡ ይህ እንግዲህ በቀጥታ ጌታ ለሳውል የተናገረውን ቃል ደራሲው ማርያም “ኮፒ ፔስት” አድርጋ እንድትናገረው ያደረገበት ነው፡፡
ከዚያም ሳውል እየፈራና እየተንቀጠቀጠ “እመቤቴ ሆይ ስለ ኃጢአቴ ምን አደርግ ዘንድ ይገባኛል? የሠው ደም እያስፈሰስኩ ወንጀለኛ ሆኛለሁና አሁንም እመቤቴ ሆይ ኃጢአቴን ይቅር በይልኝ እነሆ አንቺ እናቱ እንደ ሆንሽ ተገልጾልኛልና” ይላል፡፡ እርሷም “እነሆ ኃጢአትህ ይሰረይልህ ዘንድ ስለ ለመንኩልህ  እነሆ ኃጢአትህን ይቅር ብሎሃል፣ አሁንም በሕይወተ ሥጋ ሳለህ ወደዚህ ትመጣ ዘንድ ልጄን ኢየሱስ ክርስቶስን ማለድኩት” ትላለች፡፡ ጌታም “እሺ ጥቂት ጊዜ ታገሺ አመጣዋለሁ” ይላታል፡፡
አሁን ግብረ ሐዋርያትን ያነበበ ሰው ይህን ኮፒ ተደርጎ የቀረበውን ድርሰት ለመቀበል እንዴት ይችላል? ለመቀበል ከሚቸገርባቸው ነጥቦች መካከል አንዱ በቤተክርስቲያናችን ትውፊታዊ ትረካ መሠረት ማርያም ያረፈችው በ64 ዓመቷ ነው፡፡ ጌታን የፀነሰችው በ15 ዓመቷ ነው ተብሎ ስለሚነገር ያረፈችው በ49 ዓ.ም. ይሆናል፡፡ ጳውሎስ በጌታ ያመነበትን ጊዜ በተመለከተ፣ ጌታችን የማዳን ተልእኮውን ፈጽሞ ወደሰማይ ካረገ በኋላ ብዙም ሳይቆይ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ብላቴን ጌታ ኅሩይ በ”ጥሩ ምንጭ” መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹትም “እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ የሞተው በ፴፭ ዓ.ም. ነው፡፡ ሁለት ዓመት ከቆየ በኋላ በ፴፯ ዓመ. ምሕ. ቅዱስ ጳውሎስ በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ፡፡” (ገጽ 331፡332)፡፡ ታዲያ በምን ሒሳብ ነው በዚህ ወቅት ማርያም በሰማይ እንደነበረች ተደርጎ የተገለጸው? በዚያ ወቅት እርሷ በዚህ ምድር ላይ አልነበረችምን? ይህን እውነተኛውን ታሪክ በመመርኮዝ በስማቸው የተደረሰውን የተሳሳተ ታሪክ እመቤታችን ማርያምም ሆነች ሐዋርያው ጳውሎስ ቢሰሙ እጅግ እንደሚያዝኑ አያጠራጥርም፡፡
እውን ጳውሎስ፥ ያ ምሁረ ኦሪት በኋላም ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለየውና ወንጌልን ብቻ ማለትም ስለ ክርስቶስ አዳኝነት በመስበክ የሚታወቀውና ከዚያ ወንጌል የተለየውን የሚሰብክ ቢኖር የተረገመ ይሁን ሲል በጽኑ ቃል ያወገዘው ሐዋርያ፥ “እመቤቴ ሆይ ስለ ኃጢአቴ ምን አደርግ ዘንድ ይገባኛል? የሠው ደም እያስፈሰስኩ ወንጀለኛ ሆኛለሁና አሁንም እመቤቴ ሆይ ኃጢአቴን ይቅር በይልኝ እነሆ አንቺ እናቱ እንደ ሆንሽ ተገልጾልኛልና” ይላል ብሎ ማን ያምናል? ጳውሎስ እኮ ኃጢአቱን ለማን መናገር እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅና ለሁላችን ግልጽ አድርጎ ያስተማረን ሐዋርያ ነው፡፡ ምን አደርግ ዘንድ ይገባኛል? ብሎ የጠየቀውም ጌታን እንጂ ማርያምን አይደለም፡፡ ማርያምን እንዲህ ብሎ የሚጠይቅበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ በእውነት ሁሉም ልቦለድ ነው፡፡ ታዲያ ምናለበት እንዲህ ያለው ተረት ከቤተ ክርስቲያን ወደሙዚየም ቢዛወርና የቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረቶች ወንጌል ቢሰበክባቸው?
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ” በሚል ርእስ ያዘጋጁትና በርእሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 5 ቀን 1999 ዓ.ም. በተከበረው የቅዱስ ያሬድ በዓል ላይ ያደረጉትና በጽሑፍ የሰፈረውን ንግግር በመጥቀስ ሐሣቤን ልቋጭ፡፡ ንግግራቸው እንደ ተአምረ ማርያም ያሉት ልቦለድና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ለሚቃረኑ መጻህፍት ተገቢያቸው ካልሆነው ስፍራ ላይ ተነስተው ወደ ተገቢው ስፍራ እንዲዛወሩ የሚጠቁም ነው፡፡  
“የሌሎች እንደኛ ያሉ ሐዋርያዊ አብያተ ክርስቲያን የሚኖሩባቸው ሀገሮች የተራመዷቸውን ታሪካዊ እርምጃዎች ሀገራችንም ባለመራመዷ የእኛ ትውልድ በገድል መልክ የቆየልንን የአባቶቻችንን ታሪክ ለማድነቅ ችግር እንደሚገጥመው እገምታለሁ፡፡ ገድል ጻድቁ መምህር ሲያርፍ እንደ አባቱ አድርጎ የሚያየውና የሚያደንቀው መንፈስ ቅዱስ ለስራው የጠራው ደቀ መዝሙር የሚጽፍለት የሕይወት ታሪክ ነው፡፡ ደቀ መዝሙሩን መንፈስ ቅዱስ ይጥራው እንጂ መምህሩን ከሌሎች ጻድቃን ለማስበለጥ የራሱ መንፈስ ጣልቃ እየገባ ከጥሪው በላይ እንዲጽፍ ይገፋፋውና እውነቱን ሳይቀር ከጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነገር ይጽፋል፡፡
ይህ ዓይነቱ አጻጻፍ በሐዋርያዊ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ዘንድ የተለመደ ነበር፡፡ ግን እነዚያን አብያተ ክርስቲያን ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ የተደረገው ምርምርና ጥርጣሬ ያጋጠሟቸው በየጊዜው በመንጠባጠብ ስለሆነ ምርምሮቹንና ጥርጣሬዎቹን እንደመጡ ተቋቁመዋቸዋል ተላምደዋቸዋልም፡፡ በምርምሮቹና በጥርጣሬዎቹ አሳሳቢነት ከክርስቶስ ትምህርት ራቅ ብለው የተገኙትን ትረካዎች ከቤተ ክርስቲያናቸው አካል ቆርጠው ሲጥሉ ሕመሙ ቤተ ክርስቲያናቸውን ብዙ አይሰማትም ነበረ፡፡ እኛ ግን በአስተሳሰብ ረገድ ከመካከለኛው ዘመን (ከዘመነ ጠጅ) እንዳለን ከምዕራቡ ዓለም ስለ ተገናኘን የሃያኛው ክፍለ ዘመን መጋረጃ ከበራችን ወለል ብሎ ተከፈተብን፡፡ አንዱ አካላችን ዘመኑን ከድቶ ዘው ሲል ሌላው ከቆመበት ለመነቃነቅ እድል አላገኘም። ዛሬ የእነዚያ አብያተ ክርስቲያናት መምህራን አንዳንድ ዱሮ የቀሩ ነገሮችን ከቤተ ክርስቲያናቸው ታሪክ እየጠቀሱ ታሪክ ሲያስተምሩ ከቆመበት ለመነቃነቅ እድል ያላገኘው አካላችን ቢሰማ፣ ታዲያ ምን ስሕተት ኖሮበት ቀረ? በእኛም ዘንድ አሁንም እንዲህ ነው መቅረትም መቀየርም የለበትም ይል ይኾናል፡፡ ሌሎቹ ግን ከዚያ የተለየ ስሜት ሲፈጥርባቸው ማለት ንጽሕት ሃይማኖታችንን ከመጠራጠር ላይ ሲወድቁ ይታያል፡፡
“ሌሎቹ ሐዋርያዊ አብያተ ክርስቲያናት ለዘመኑ የተስማሙ በኋላ ትውልድ ግን የማይሆኑ የተጋነኑ ተአምራቶቻቸውን የምእመናኑን እምነት ሳያናጉ በጊዜው ከቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ወደ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አዛውረዋቸዋል፡፡ በእኛ ዘንድ እድሉ ሳይገኝ ቀርቶ ይህን አይነት እርምጃ በጊዜው መውሰድ ባለመቻሉ የሚጠሉን መስሏቸው በደስታ ወይን ሰክረዋል (ገጽ 5-6)።
ተአምረ ማርያምስ ከቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ወደ ታሪክ መዛወር የለበትም ትላላችሁ?

31 comments:

 1. ወይ አንቺ ቤተክርስቲያን ጉድሽ አያልቅ

  ReplyDelete
 2. Jesus is the way!!!July 21, 2015 at 4:35 PM

  Throw this evil book and others to fire not to museum.

  ReplyDelete
 3. አረ ለመሆኑ ግን እንዴት ነው የሰዉ ጭንቅላት የሚያስበው እነደዚህ ያለውን ግልጽ ክህደት እንዴት ተዓምር ነው ተብሎ ይነበባል። በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። አረ ተይ አንቺ ቤተክርስቲያን ተይ

  ReplyDelete
 4. አንተ እኮ መሄድ የነበረብህ የተዋህዶ ቤ/ክ ሳይሆን የለመድክበት ጭፈራ የተመላው አዳራሽ ነበር....
  እንዳነተ እምነት ፍልስፍና ለሆነባቸው ይቺ ቤ/ክ እንደማትመች ማወቅ አለብህ..... ወዳጄ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን እያልክ ነው። የጨለማው አጋፋሪ እንደዚህ አይነቱን ፍጹም ክህደት እንቀበል?

   Delete
  2. ወዳጄ ለመቀበል ማመን ያስፈልጋል...
   ተቀበል ሳይሆን ያልኩህ ባላመንክበት አትጠልል፤ በማያገባህም አትግባ ነው...

   Delete
 5. እነ ዳሞት ይህን ውሸት ነው ወንጌል ምትሉት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous july 21,2015 at 10:42pm

   ለአንተ ውሸት ነው ልትል ትችላለህ። እውነት ነው ብለህ እንድትቀበለው ማንም አላስገደደህም። ወንጌል ነው አልተባለም። ወንድምህ ከሳሽ፣ ተችና አጥላሊው አቶ ያለውም ወንጌል ነው አሉ ብሎ አልፃፈልህም። አንተም ትችትን፣ ውሸትን፣ ሐሰተኛ ክስን፣ ማጥላላትን፣ ሳይሆን አይቀርምና መሰለኝን፣ ስም አጥፊነትንና የፈጠራ ተራ ወሬን(አሉባልታን) በአጠቃላይ የክፋት ተግባራትን እንደወንጌል እና እውነት ስታንቆለጳጵሳቸው የምትታዮት ይህን ነውን መጽሐፋችሁ የሚያስተምራችሁን? አፍህን ከመክፈትህ በፊት እራስህን ተመልከት፤ ለአፍህም ልጓም ለምን።

   Delete
 6. ZERA YAEKOB TEKORTO KEMEKABIR WETITO HAYMANOTU BITEYEK YiH KEHADI YANE YEFETERWE WISHET ENE ABAMATHEWOS ZAREM ALTEWUTIM

  ReplyDelete
 7. ሌላ ሌላውንት ትተህ ተአምረ ማርያም መወገድ አለበት የለበትም? ልብ ካለህ በዚህ ላይ አስተያየት ስጥ፡፡ ከዚህ ውጪ ያለው ትርፍ ቃል እውነታውን አይለውጠውም፡፡ በእኔ በኩል ተአምረ ማርያም ከቤተክርስቲያን መወገድ ካለባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱና ዋናው ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. መወገድ ያለበትስ እንዳንተ አይነቱ የማይጠቅም ተሃድሶ(መናፍቅ) ነው!!!! ደሞ ራስህን ቅድስት ቤተክርስያን ውስጥ ትጨምራለህ???? አሁን መተህ ቤተክርስትያንን ልታድስ.....ከ2000 አመት በላይ ያላትን ቤተክርስትያን ልታሻሽል????.......ጉድ ኮ ነው እነ አሬዎስ ያልቻሏትን አንተ ልትችላት((የማቴዎስ ወንጌል 16፥18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ))

   Delete
  2. መናፍቅ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ((የማቴዎስ ወንጌል16፥18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።))
   ........ከተሳካልህ ሞክር.......የአሬዎስ ልጅ!!!!!!

   Delete
 8. How you can't think that God can show Paul wherever st Mary was.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተስ ይህ ለምን እንዳስፈለገ የሚለውን ማሰብ እንዴት አቃተህ?

   Delete
 9. Meweged yalebachihus inante menafikan.Bemaninyawum yesewu lijoch dihnet wust imebetachin alech.Getachin bemidir simelales besemayawi kibru indale hulu imebetachin kewuldetwa jemiro bemenfes besemay tigenyalech ante yekoterkewu midrawi idmewan bicha newu.lemasredat yahil raiy miraf 12 lay yemitgenyewu man nat mikael satnaeln sayabar befit bale 12 kokeb yetebalech irswa yegeta inat nat.Hulachinim bemenfes yetefeternewu diro newu besiga wedekn benfes innesalen.Lela asrej muse bebereha yayat its,Yaikob yayat meselal.iyaln inamnalen kegeta madan befit hule irswa alech.Yeirsu fekad newuna .Pawulosim yihn silemayneger sitotaw igziabher yimesgen bilwal. kidusan leinya siletesetu.Yemetshaf kidus yeametat akotater min yahil irgitenya newu bileh taminaleh.Ahun metshaf kidus bilen yeyaznewu ikko yegetan,yepawulosin,yimebetachinin idme aynagerm.Yeimebetachin idme keawald metshaf wesedk yepawulosin degmo kemetshaf kidus.Alasmamahachewum.zim bileh teregomk.Zim bilewu yemiteregumu degmo belibachewu hasab yemikoru tibitenyoch nachew antem keinersu wegen neh.Iwuket kefelek teyk.Yaleabatacho kidusan metshift zig nachewuna

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ሰው ምን እያልክ ነው? የተተቸው እኮ ውሸተኛው ተአምረ ማርያም ነው እንጂ እመቤታችን አይደለችም፡፡ እሷና ተአምረ ማርያም ደግሞ ፈጽሞ የማይተዋወቁ መሆናቸውን ማወቅ አለብህ፡፡ ስለዚህ ውሸተኛው ተአምረ ማርያም ውሸቱ ስለተገለጸ ማርያም ተተቸች ብለህ አታቅራራ፡፡ አታደናግርም፡፡

   Delete
 10. ወንድሜ ይህንን መልዕክትዎትን እያስተላለፉ ያሉት ለዳኑ ሰዎች ነው ወይስ ላልዳኑ? ውዳሴ ማርያምን አምኖ የሚኖርበት ሰው የዳነ ነው እንደማይሉ እርግጠኛ ነኝ ::ካልዳነ ደግሞ የሚያስፈልገው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንጂ 'ውዳሴ ማርያምን' ጣል አትጣል የሚል አተካራ አይደለም::

  ReplyDelete
 11. ለአቶ ያለው

  በመጀመሪያ በሐሰት ትችትና ማጥላሌ

  ReplyDelete
 12. ለአቶ ያለው

  በመጀመሪያ በሐሰት ትችትና ማጥላላት ብሎም ውሸትን ማራመድ እምነት(ሀይማኖት) አይደለም። ክርስቶስም የተናገረውና ያስተማረው በእርሱ መንግስት አምነው በእምነት በመጽናት ለመንግስቱ የሚያበቃ የእምነት ሥራ ሰርተን ፍሬ አፍርተን እንድንገኝ
  እንጂ ማጥላላት፣ ማናናቅ፣ በከንቱ መተቸት፣ ሳይሆኑ ሆንኩኝ ማለትና ሥላላመኑበትና ሥለማያውቁት የሌሎች እምነት አማኝ በመምሰል በክፋት መነሳት አይደለም።
  አቶ ያለው እምነት የለሽና ምንም አይነት ሥለ እምነት ግንዛቤ የሌለውሆኖ ነው ለኔ የታየኝ። አሊያም ደግሞ ትንሽ እውቀት ለዛውም የንባብ እውቀት ይዞ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የሚነገረውንና የሚታወቀውን የእግዚአብሔር ቃልና በእሱ ታምኖ የመኖር እምነትን በቃላት እንዲህ ይላል ውጊያ እውነትን ለመቅበር የሚሞክር ነው የሆነብኝ።
  አቶ ያለው ታምረ ማርያም ሲነበብ የሰማበትን ቤተክርስቲያንና የሚተቸውን ታምር የተነበበበትን ዕለት አይጠቅስም። ይህ ደግሞ የእሱን ክፉ ከሳሽነትና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ቤተክርስቲያን ጠላት መሆኑን ያረጋግጣል። አቶ ያው የቤተክርስቲያንን እምነት አለመቀበልና አለማመን መብቱ ነው። ነገር ግን የቤተክርስቲያንን እምነት ማጥላላትና በውሸት መወንጀል ግን ሐጢያትና በህግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ምክንያቱም በህግ የእምነት ነፃነት ታውጇልና።
  አቶ ያለው የሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 9ኝ ላይ ያለውና በ2ኛ ቆሮ• ምዕራፍ 12 ያለው ታሪክ አይገናኝም ይላል። ለምን እንደማይገናኝ ግን መናገር አልቻለም። ብዙ ሳንጠይቅ በአንድ ነገር እንሿን እንደሚገናኙ የታወቀ ነው። ይኸውም በሐዋርያት ሥራ በደማስቆ ከጳውሎስ ጋ የነበሩት ምንም እዳላዮ ይናገራል። በ2ኛ ቆሮንቶስ 12 ላይ ደግሞ እሥከ ሶስተኛ ሰማይ የተነጠቀ እንዳለ ይናገራል። እነዚህ ሁለቱ የሚያመለክቱት የራሱ የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክና በሰማይ በመንፈስ ተነጥቆ እንደነበር ነው። በደማስቆ በሥጋ አብረውት ከነበሩት ጋር ቢሆንም በመንፈስ ግን በሰማይ ከኢየሱስ ጋ ይነጋገር እንደነበረ ነው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9ኝ የሚያስረዳው። ሥለዚህ በሰማይ በመንፈስ በመሆን ይገናኛሉ። አቶ ያለው ትንሽ ቅርንጫፍ ላይ በሥጋ ተንጠልጥሎ በመንፈስ ቅዱስ አሥተማሪነት የሚገለጠውን በቃላት ጦርነት ለማጣመም ይሮጣል።
  አቶ ያለው ታምሩ ሲነበብ አፈርኩ ይላል። አሥቀድሞ መቸ አመንክና ነው? መቸ የቤተክርስቲያኗ እምነት ኖሮህ በእምነት ፀንተህ ቆምህና? መቸ የታምር መፅሐፍትን ተምረህ ያልገባህን ጠየቅህና ነው? በክርስቶስ መንግስትና በእምነት ሥለ ተደረጉ መልካም ሥራዎች ማፈር እኮ የክርስቲያን መገለጫ ሳይሆን የአህዛብና የመናፍቃን መገለጫ ነው። ታዲያ አንተ አፈርክና ምን ያስደንቃል፤ ቤተክርስቲያንስ ምን ይጎልባታል። አንተ መናፍቅ ነህ። ነውሩን ክብር አድርገህ የያዝህ በጎውን ደግሞ ውርደት የምትል ነህ እኮ። ክርስቶስ የሚወደኝ ቢኖር ይከተለኝ ነው ያለው። ሥለሆነም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሚወድ እምነቷን ይከተላል፤ በእሷም አያፍርም። ታምር የሚነበበውና የሚነገረው እኮ ክርስቶስ ስላዘዘና ክርስቶስ ለመረጣቸውና ለአከበራቸው ፀጋና በተሰጣቸው የአማላጅነት ለምነው ሥላሥገኙት ክርስቲያኖች እንዲያውቁና በእምነት እንዲፀኑ ነው።ክርስቲያኖች የቅዱሳኑን ፀጋና አማላጅነት ተረድተው በረከታቸው ይደርሳቸው ዘንድ እንዲቀርቡና እግዚአብሔር ለቅዱሳኖቹ ያደረገላቸውንና የሰጣቸውን ፀጋና ሃይል አውቀው "ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ" እንደተባለው እንዲያከብሯቸው፣ ፀጋ ስግደትን እንዲሰግዱላቸው፣ በአማላጅነታቸው እንዲያማልዷቸውና እንዲራዷቸው እንዲለምኑ ነው።" እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። 2ኛ ቆሮ• 12:11"። መሳቅ መሳለቁ ብሎም ሁካታ አቶ ያለው የእምነትና የምግባራችሁ ዋና መገለጫ ነውና በደንብ አሥካካ አውካካ።

  ReplyDelete
 13. ለአቶ ያለው

  የቤክርስቲያን ጠላት አቶ ያለው ሌላኛ ማጥላላቱ ድንግል ማርያምንና ቅዱስ ጳውሎስን የለካበት አለካክ ያነፃፀረበት አነፃፀር ነው። ግለሰቡ ቅዱስ ጳውሎስ ከድንግል ማርያም ይበልጣል ለማለት ሞክሯል። የቅዱስ ጳውሎስ እምነት ከተጠራ በኋላ የፀና ቢሆንም ከድንግል ማርያም ይበልጣል ማለት ግን የጠላት ክፉ ሴራና ክህደት ነው። ሌላው ይቅርና ድንግል ማርያም ሐጢያት ያልነካት ንፅህት ለቃል ማደሪያነት የተመረጠች በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፀንሳ አምላክን እሱም ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች ናት። ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በሳውልነቱ ዘመን ወንጀልን ይፈፅምና ክርስቲያኖችንም ያሳድድ የነበረ ነው። አቶ ያለው በምን ሚዛን ነው የምትለካው። ስለ ፀሎቱ ልመናው እንደሆነ አይደለም ድንግል ማርያም ህዝበ ክርስቲያኑን ሁሉ ሥለኛም ፀልዩ እያለ እራሱ ቅዱስ ጳውሎስ አሳስቧል ጠይቋል። እሱ ወደ ማን መለመን ጠፍቶበት ነው ወደ ሚልም ሌላ ክፉ አሥተሳሰብና የውቀት ማነስ ያለበት ትችት አቶ ያለው ሰንዝሯል። የእግዚአብሔርን አሰራርና የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ያላወቁና ያልተረዱት መናፍቃን እንዲህ እንደወንድማቸው ነው ባዶ ማጥላላትንና ትችትን የሚያራምዱት። ለመሆኑ በደማስቆ ኢየሱስ ሳውልን ካነጋገረው በኋላ የሚያደርገውን የሚነግሩት በከተማ አሉ ያለውን አቶ ያለው አንብቦታልን? የሰይጣን ጉድ አያልቅምና አቶ ያለው ኢየሱስን ለምን ሳውልን የሚያደርገውን ይነግሩት ዘንድ ላክኸው ብሎ ይከሰው ይሆን? ወይም ደግም ለምን አንተ አትነግረውም ብሎ ይተቸውና ያጣጥለው ይሆን? ክርስቲያን ግን ሁሌም ሥጋ ለባሽና ደካማ ሐጢያት የሚያሸንፈው በሐሳብም ይሁን በተግባር የሚሠራ መሆኑን ማወቅና ከእኔ ወንድሜ ይበልጣል ማለት ተገቢ ነው። ለዚህም ነው አንድስ እንሿን ፍፁም የለም የተባለው።
  ሌላኛው የጠላት የአቶ ያለው ክስ፣ ማጥላላትና ትችት የታምረ ማርያም ታምር በመጽሐፍ ቅዱስ የለም የሚል ነው። አይ መናፍቅነት! አይ ተጠራጣሪነት! አቶ ያለው አሁንም አለማመንና አለመቀበል መብቱ ቢሆንም ሁሉ ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ አልተፃፈም ማለት ግን አለማወቅ፣ ክህደት፣ ውሸትና ተንኮልና መናፍቅነት ነው። አይደለም ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፀጋና ቸርነት ያደረጉት ይቅርና ክርስቶስ ያደረገው ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም። ዋናው ቁም ነገሩ ቅዱሳን በተሰጣቸው ፀጋና ሥልጣን ታምራትን ያደርጋሉ አያደርጉም፣ ድውያንን ይፈውሳሉ አይፈውሱም ፣ ሙት ያስነሳሉ አያስነሱም፣ በፀሎት በምልጃቸው ምህረትን ያሰጣሉ አያሰጡም፣ ይራዳሉ አይራዱም ነው። አዎ በተሰጣቸው ፀጋና ሥልጣን ታምራትን ያደርጋሉ፣ ድውያንን ይፈውሳሉ፣ ሙት ያስነሳሉ፣ ያማልዳሉ፣ በረከት ያሰጣሉ፣ ይራዳሉ …። ድንግል ማርያም ደግሞ ፀጋ የመላብሽ የተባለላት የአምላክ እናት ናትና ብዙ ማድረግ ትችላለች። አቶ ያለው ያልገባው ታምር ከሆነ ከማጥላላት ከመተቸት በፊት ለመረዳት መጠየቅ ተገቢ ነበር።ሆኖም ጠላት አይደለም ድንግል ማርያምንና ቅዱሳኑን ይቅርና ክርስቶስንም ከማጥላላት፣ ከመተቸት፣ ከመወንጀልና ከመግደል አላረፈም። አቶ ያለውም የአባቱን የጠላት ዲያብሎስን መንገድ ቢከተል አይደንቅ። ከማን ተማረና? እንዲያውም እራሱን አልቆ ታምሩን ያነቡትንና አዘጋጁት የሚላቸውን "ልባቸው ወልቋል" በሚል ዘለፋም ዘልፏቸዋል።
  አቶ ያለው ዘባቶሎዎቹ ብዙ ናቸው። ቀን ማስላት አልቻለም እንጂ የቀን ቆጠራንም ለመተቸት ሞክሯል። ለምንፍቅና አካሔዱም ይረዱኛል ያላቸውን የግለሰቦችን ፅሑፉችንም ጠቅሷል። ግን ደግሞ የቤተክርስቲያኗን መፅሐፍት ሥለ ታምሩ ምን ይላሉ የሚለውን ለማየትም ሆነ ለመጥቀስ አልፈለገም። አቶ ያለው ይከሳል፣ ይተቻል፣ ያጥላላል፣ ሐሰት ይጽፍ ይናገራል እውነትን ያጣምማል። የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደግሞ ዛሬም ነገም እምነቷን ትተገብራለች እንጂ በነ አቶ ያለው የሐጢያት መንገድ አትሔድም። ይህም እስከ ክርስቶስ ምፅዓት ይቀጥላል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ ዳሞት አንተን በቀላሉ ለመግለጥ ያለው ቃል ኮተት የሚለው ነው። ታሳዝናለህ

   Delete
  2. To mr.(ms) anonymous july 26,2015 at 2:44 am.
   ምነው አቶ ተበሳጨህ? አይዞህ! መሳደቡንም ፣ መናፍቅነቱንም ፣ ውሸቱንም ፣ የሐሰት ወሬ መደረቱንም ፣ ስድብና ክፉ ስም አጥፊነትንና ከሳሽነቱን ወንጌል ብለህ መቀበሉንም ብቻ ሥጋህን የሚያስፈነድቅልህን የሥጋ ሥራን ሁሉ ልትፈፅም ነፃ ፈቃድህ ነውና ለንስሐ ፍሬ ለማፍራትና በመዳን ትምህርት አምነህ መዳን ካልፈለግህ በደንብ አጠንክረህ በአመፃህ ቀጥል። ኮተት ውሸት እንጂ እውነት አይደለም። አቶ ያለው የዘበዘበው ደግሞ ውሸትና ክህደት መናፍቅነትን ነው። ሥለዚህ ኮተቱ የአቶ ያለውና የአንተው ሐሰተኛ ትችትና ማጥላላት ነው። ከመሳደብ በክርስቶስ አምኖ ለመዳን የሚያበቃ የክርስትና ትምህርትን ተማር። የያዝከውና እየሔድክበት ያለው ክርስትናን አይገልጥም።

   Delete
  3. አቶ ዳሞት አንተ ክርስቲያን ብለህ ታምናለህ ማለት ነው?

   Delete
 14. Debtarawochu bizu amet atalewnal. Wangelachen sila Kirstos adanyinat sinagar enji yeqesochu afatarik-Wudase Mariam, Te'amra Mariam zibazinke yelem. Better to take those anti-Bible fictions and legends to museum. Read John 14:6:Jesus said , “I am the way, and the truth, and the life. No one comes to the Father except through me.

  ReplyDelete
 15. ስለምን በኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ሳታምንና አባል ሳትሆን ራስህን የእምነቱ ተከታይና ተቆርቋሪ አድረገህ አስተምሮዋንና መጻህፍቶቿን ትነቅፋለህ?
  በማይመለከትህ ጉዳይ ገብተህ ህሊናሀን አትሽጥ !!

  ReplyDelete
 16. The only thing God/Jesus Christ has done by himself is create the universe. Everything else God did through his creatures:humans. A huge example is the Virgin Mary, without her Christ would not be born and we would not be saved so yes She is our savior because she is the mother of our savior. If you speak against our queen and holy mother you are speaking against her son; the creator Christ. In regards to Tamire Maryam, there are many stories that may seem contradictory to the bible, but in truth they are not. Tamire maryam is an addition to the bible, it was written by our fathers filled by God the Holy Spirit to add background information that isnt in the bible. The only thing the tamir mentioned above is saying is that the Virgin Mother helped St. Paul receive mercy from her son, as she does with everyone else including you and me. She is the queen of the universe and the Mother of God, we owe her our life and our praise because she has saved us by birthing our savior Christ and she is always begging on our sinning behalf because we are unpure to do so and she is!
  Praise be to our Holy Mother and Queen Maryam! and may she give all of you the eyes to see for yourself her wonderful works!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Only Jesus Christ is our savior

   Delete
  2. Only Jesus Christ is our savior

   Delete
 17. እግዚኣብሄር ልቦናውን ይስጣችሁ እንጅ ምን ይባላል

  ReplyDelete
 18. bizu dedeboch ayichalehu endanet ayinet gin alayehum.kil ras

  ReplyDelete