Thursday, July 23, 2015

በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማኅበረ ቅዱሳን አለኝታ የነበረው መ/ር ቸሬ አበበ ተባረረበቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሬጂስትራር የነበረው መ/ር ቸሬ አበበ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ለሆኑ ግለሰቦች ሳይማሩና የሚጠበቅባቸውን ሳያሟሉ ዲግሪና ዲፕሎማ እንዲሁ ሲሰጥ በመገኘቱ ከሥራ መባረሩን ምንጮች ገለጹ፡፡ በቀንም በማታም ለሚማሩ የማቅ አባላት እንዳሻው ዲግሪና ዲፕሎማ በማደል የሚታወቀው መ/ር ቸሬ አበበ፣ ወደ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ከመግባቱ በፊት የማቅ የጥናትና ምርምር ክፍል ሆኖ መስራቱ ሲታወቅ ወደ ኮሌጁ በዓላማና የማቅን ተልእኮ ለመፈጸም እንደገባ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ይህን በተመለከተ ብዙዎች ኮሌጁ ከማቅ ተጽእኖ ነጻ እንዲወጣ የቸሬን ጉዳይ ቢጠቁሙም ሰሚ ሳያገኙ እስካሁን ድረስ ብዙ ጥፋት ደርሷል፡፡

መ/ር ቸሬ አበበ በኮሌጁ ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታወቀው ወሬ በማመላለስና ሠራተኛን ከሠራተኛ በማጋጨት ጠብ ዘሪ ጠባይ ሲሆን፣ በእርሱ ዘመን እርሱ ያላጣላውና ያልተጣላ አይገኝም፡፡ በዚህ ጠባዩ የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀራቢ በመምሰል በኮሌጁ የሚያጋጥሙ አንዳንድ ችግሮችን በማባባስና መረጃዎችን ለማቅ የወሬ ፍጆታ እንዲውል በማድረግ በኮሌጁ ውስጥ የማቅ ጆሮ ሆኖ ሲሰራ ነው የኖረው፡፡ የያረጋል አበጋዝ አድናቂ የሆነው መ/ር ቸሬ አበበ ኮሌጁ በሃይማኖት እንዲጠረጠርና በማቆች ግቢው እንዲደፈር ለያረጋል መረጃ በመስጠት ትልቁን ድርሻ መወጣቱን ምንጮቻችን ያስረዳሉ፡፡ በግቢው እንደፈለገች ትፋንን ከነበረችው ከወ/ሮ ዘውዴ ጋር ልክ እንደ መ/ር ደጉ የተለየ ቀረቤታ እንደነበረው የሚነገረው መ/ር ቸሬ አበበ ቀረቤታው በአገር ልጅነት ይሁን በሌላ ያልተመለሰ የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ እስካሁን አለ፡፡

መ/ር ቸሬ ከወሬ አመላላሽነቱ በተጨማሪ የሰው ድርሰት የራሱ አስመስሎ በስሙ በማሳተም የሚታወቅ ሲሆን፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” የተባለው መጽሐፍ የእርሱ እንዳልሆነና ለማስተማር ዓላማ የተዘጋጀን የሌላ ሰው “ሀንድአውት” ወደ መጽሐፍ ለውጦ እንዳሳተመው ይታወቃል፡፡ የማን ሀንድአውት እንደሆነና ከዚህ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ወደፊት እንገልጣለን፡፡
መ/ር ቸሬ በዚህ ዓመት ወደ ሬጂስትራርነት ከተዛወረ በኋላ በተደጋጋሚ ሕገ ወጥ ሥራ እንደሚሰራ ቢጠቆምም እርምጃ ሳይወሰድበት እስካሁን ቆይቷል፡፡ አሁን ለመባረር ያበቃው ምክንያት ለማቅ አባላት ተማሪዎች ዲግሪና ዲፕሎማ ሲሸጥ ተደርሶበት ነው፡፡ አሁን ስለተደረሰበት እንጂ ከዚህ ቀደም ለስንቱ የማቅ አባል ዲግሪና ዲፕሎማ እንዳደለ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ለካስ የማቅ አባላት የሆኑ የኮሌጁ ተማሪዎች ያለ ምክንያት አልበዙም የሚለውን የብዙዎችን ጥርጣሬ የመ/ር ቸሬ መባረር አረጋግጧል፡፡ ክፍል ውስጥ ጭራሽ ሳይገቡና ተምረው ሳይፈተኑ ውጤት የሚሰጣቸው ተማሪዎች ቁጥር ያሻቀበው እርሱ ሬጂስትራር ሆኖ በተመደበበት ዘመን ነው፡፡ የእርሱ ጥፋት ከስራ  በማባረር ብቻ የሚቆም መሆን እንደሌለበትና በሙስና ወንጀል መጠየቅ እንዳለበት ብዙዎች ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ድርጊቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያደረሰው በደል በቀላሉ የሚታይ አይደለምና፡፡

መ/ር ቸሬ በዚህ ወር ኮሌጁ ግቢ እንዳይገባ ጭምር የታገደ ሲሆን በእጁ የሚገኘውንም የኮሌጁን ንብረት ባለፈው አርብ አስረክቧል፡፡
     

3 comments:

  1. Ere yikeral Denbulo yemetebal set aseregezu andetaseteweredewu aderegole

    ReplyDelete
  2. does this blog really has "Spiritual people?" Shame on you pastors.

    ReplyDelete
  3. lilan sewu enate yelsetekonenu yelilebete seme setatefu kemere menefeswi nachi MK woche leteyikachihu

    ReplyDelete