Friday, July 3, 2015

ይቺ ናት ተአምረ ሥዕለ ማርያም¡ከላእከ ወንጌል ሃይማኖት ታደሰ
«አስደናቂ ዜና»
“አርብ መርካቶ ሸራ ተራ 8 ሰአት የተነሳው ከፍተኛ ውድመት ያደረሰው የእሳት አደጋ ረዘም ያለ ግዜ ውስዶ ቢያንስ ከፍተኛ ንብረት ማውደሙንና እስከ ለሌቱ, 5 ሰአት ድረስ አለመብረዱን በአቅራቢያ የነበሩ ሰዋች ጠቁመዋል በዚህ አጋጣሚ በጣም ብዙ ንብረት መትረፍ አለመቻሉና ውድመቱ ከፍተኛ መሆኑን ተመልክተናል ከዚህ ውድመት ጋር በተያያዘ ትላንትና ቦታውን ፍርስራሽ ለማንሳት በመፈተሽ ላይ የነበሩ ባለንብረቶች ይቺን የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ የድንግል ማሪያም ስዕል አድኖ እሳት ሳያቃጥለው በሚገርም ታዕምር [ተአምር] ተገኝታለች የድንግል በረከት አይለየን ልመናዋ ምልጃዋ ከሁላችንም ይሁን ከዘላለም እሳት ትሰውረን፡፡
አሜን ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ይሄን ታምር ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ! 

እንዲህ ሲል ያስነበበው yehabesha.com ነው፡፡ ወሬው የሰነበተ “ቋንጣ” ቢሆንም ቋንጣም ይበላልና እንደሚሆን አድርጌ በጉዳዩ ላይ ሐሳቤን ለማካፈል ወደድኩ፡፡ ይህን “አስደናቂ ዜና” ብሎ ድረ ገጹ ያቀረበውንና በምን መስፈርት እንደሆነ ሳይታወቅ “ተአምር” ያለውን ክስተት በዝምታ ማለፍ ተገቢ መስሎ አልተሰማኝም፡፡ ወሬው ወር የሆነው በመሆኑ “የጠነዛ” ነው ሊባል ቢችልም በጉዳዩ ላይ የሚነሣው የክርክር ሐሳብ እንደ አዲስ እንድወያይበት ሊያደርግ ይችላልና በሚል እምነት አንዳንድ ሐሣቦችን መሰንዘር ያስፈልጋል፡፡

በክርስትና ትምህርት መሠረት ተአምር ከተለመደውና ዘወትር ከሚከናወነው ድርጊት ለየት ያለ በሕያው አምላክ በእግዚአብሔር የሚከናወን ሰውን የሚያስገርምና የሚያስደንቅ ፈጣሪውንም እንዲከተለው የሚያደርግ ልዩ ሥራ ነው፡፡ ተአምር የሚደረገው የእግዚአብሔር የሁሉን ቻይነት ክብሩ እንዲገለጥና ሰዎች ያን አይተው ታላቅ ኃይሉን እንዲያውቁት፣ እንዲያምኑበትና እንዲድኑ ለማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ተአምርን በልዩ ልዩ መንገድ በተለያዩ ቅዱሳን አማካይነት ይሠራል፡፡ በልማድ እገሌ ተአምር ሠራ እየተባለ ወይም “ተአምረ እገሌ” እየተባለ ይነገራል ይጻፋል እንጂ ተአምሩን የሠራውና የተአምሩ ባለቤት ግን እግዚአብሔር እንጂ ቅዱሳኑ አይደሉም፡፡ በመዝሙረ ዳዊት እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል እግዚአብሔርም ይመስገን። (መዝ. (68)፥35)፡፡ “ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።” (መዝ. (72)፥18)፡፡ “እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና” (መዝ. (136)፥4)፡፡

እግዚአብሔር ተአምር እንደሚሠራ ሁሉ ሰይጣንም ሰዎችን ለማሳትና ከእግዚአብሔር መንገድ ለማስወጣት ምልክት ሊያሳይ ይችላል፡፡ መጽሐፍስ “የተመረጡትን እስኪያስት ድረስ” ምልክት ሊያደርግ እንደሚችል ተናግሮ የለምን? ማቴ. 24፥24፡፡ በሁለቱ መካከል ያለውን ለመለየት ክርስቲያን የእግዚአብሔርን አሠራር የሥራውን ዐላማና በሥራው የሚገኘውን ውጤት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊፈትሽና በዚያ መሠረት ለይቶ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ በኦሪት ዘዳግም የተጻፈው መመሪያ ዛሬም ይሠራል፤ “በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ።” (ዘዳ. 13፥1-3)፡፡ ማንኛውም ተአምራትና ምልክት የእግዚአብሔርን ክብርና ታላቅነት ካልገለጠ፣ ወደ እግዚአብሔርም ካላቀረበ እርሱ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ከአጋንንት ነው፡፡ በየገድላቱና በየድርሳናቱ ተፈጸሙ ተብለው የተጻፉት ተአምራት በአብዛኛው የእግዚአብሔርን ክብርና ታላቅነት ሳይሆን “ተአምር ሰሩ” የተባሉትን ቅዱሳን ክብርና ታላቅነት ነው የሚገልጡት፡፡ ስለዚህ እነርሱ ከእግዚአብሔር ናቸው ማለት አይቻልም፡፡

ከላይ በቀረበው ዜና ውስጥ መርካቶ ሸራ ተራ በደረሰው የእሳት አደጋ ከፍርስራሽ ውስጥ ተገኘች የተባለችው “ሥዕለ አድኅኖ” በሚል ቁልምጫ የተጠራቸው ሥዕለ ማርያም ተአምር ሰራች፤ በቃጠሎው ምንም ጉዳት ሳይደርስባት በተአምር ተረፈች እየተባለ የተወራው ወሬ እጅግ የሚገርምና ይህን ያወራው አካል ስለ ተአምር ምንነት በቅጡ ያልተረዳ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡ ምክንያቱም ተአምረኛ የተባለችውና የሰዎቹን ንብረት ሳይሆን ራሷን አዳነች የተባለችው ሥዕለ ማርያም በተአምር ተረፈች ለማለት የሚያበቃ አንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ ለምን ቢባል ሥዕሊቱ ከፍርስራሽ ሥር መገኘቷ ተአምር ሳይሆን ዘወትር ሊያጋጥም የሚችል ክስተት መሆኑ ለማንም ግልጽ ነውና፡፡ ወረቀት ከእሳት የመትረፍ እድል አለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምንም የማይሰሩና የተጠራቀሙ ወረቀቶችን ለማስወገድ ፈልገን በእሳት ስናቃጥላቸው እንኳን በእንጨት እየቆሰቆስንና እያገለባበጥን ካልሆነ ሳይቃጠሉ የሚቀሩ ወረቀቶች ያጋጥማሉ፡፡ የሥዕሊቱ አለመቃጠልም ከዚህ ጋር እንደ ተያያዘ መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩን ተአምር ማለት አይቻልም፡፡ ምናልባት ቤቶቹ ተቃጥለው ሥዕሊቱ ያለችበት ቤት ግን ባይቃጠል ተአምር ብሎ ለማውራት ይመች ነበር፡፡ አሁን ግን ራሷን አዳነች ብሎ ነገሩን ተአምር ማለት ፈጽሞ አያስኬድም፡፡

የሥዕሊቱ ባለቤቶች ንብረታቸው ተቃጥሎባቸው ሥዕሊቱ በመትረፏ ነገሩን ተአምር ብለውት ይሆን? የሚለውን ማወቅ በእጅጉ ያጓጓል፡፡ እነርሱ እንዲህ ካሉ ሃይማኖታቸውን የመሰረቱበትን ትምህርት ሊፈትሹ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ተአምር ማለት እንደ ሥዕሊቱ ራስን ማዳን ሳይሆን የማይቻል በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ድንቅ ነገርን አድርጎ ሌላውን ማዳን ነው፡፡ ለምሳሌ ሠለስቱ ደቂቅ ናቡከደነጾርን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም በማለታቸው ታስረው ከቀድሞው ይልቅ ሰባት እጥፍ ወደሚነደው እቶን እሳት ውስጥ ተጨመሩ፡፡ በተአምር ካልሆነ በቀር ከዚህ ውስጥ መውጣትም ሆነ መዳን ፈጽሞ የማይቻል ነው፡፡ ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጎ ግን ምንም ሳይሆኑ በተአምር ዳኑ፡፡ ወደ እቶኑ እንዲጣሉ ያደረጋቸው “ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።” (ዳን. 3፥28) ብሎ ክብርን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ተአምር ማለት ይህ ነው፡፡ የሥዕሊቱ ግን ከዚህ ውጪ ነውና ለዚህ ተአምር ኃላፊነቱን የሚወስድ ክርስትናዊ ትምህርት የለም፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ሥዕል ተአምር ሰራ የሚለው ነገር አሁን የተጀመረ ሳይሆን በገድላትና ድርሳናት ውስጥ እንደልብ የተጻፈ ነው፡፡ ለዚህም እንዲመች ሥዕልን ሥዕለ አድኅኖ ብሎ መጥራት ተለምዷል፡፡ ነገር ግን ፈጽሞ ሊሆን የማይገባው ነው፡፡ ይህም ድረገጽ ከፍርስራሽ በአጋጣሚ ሳትቃጠል የተረፈችውን ሥዕል “ሥዕለ አድኅኖ” ብሎ በመጥራት በሚገርም ተአምር ተገኘች ሲል አዳንቆ ነው ያወራው፡፡ ተአምር ተብለው በየድርሳናቱና ገድላቱ የተጻፉት “ተአምራትም” አንድም የደራሲያቸው የፈጠራ ሥራዎች ናቸው፤ አንድም እንዲህ ባለ መንገድ የተቀነባበሩና ተአምር ተብለው የሰፈሩ ናቸው፡፡ ጎበዝ፣ ቶሎ ባንደርስበትና እንዲህ በእግዚአብሔር ቃል ዕርቃኑን አስቀርተን ባናሳጣው ኖሮ እኮ ቀስ ብሎ ተአምር ተብሎ ተአምረ ማርያም ላይ ቦታ ያገኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ነቄ ብለናል፤ እንኳን ይኼ የተአምረ ማርያሙም “ተአምር” በልባችን ስፍራ አላገኘም፡፡

15 comments:

 1. አይ መናፍቅ እንግዲህ አንጀትኸ ቅጥል ይበል እንጅ እኛሰ በድንግል አማላጅነት ያልተደረገልን አንዳች ነገር የለም እናንተም ያምላክን እናት ያቃለልክ መሰሎክ ታምሯን ላልሰማ እያሰማኸ ነው ቅድሰት ሆይ ለምኝልን

  ReplyDelete
 2. Ayineh ayayim ende?yetaqefechiw ayitayihm?lene lek seba segel bebetelhem ke Tewedaj lijua gar endayehuat new yemamnew;te'amer yetederegewum besua bicha new yemil alwetanem,ante etechemamerkbet new enji:"Egziabher ke anchi gar new" yemil selamta yeteqebelech Dengel Lijua hulgize kersua gar new,ke ante gar lemehonu gen menm maregagecha yelem;esti leteyiqeh be yohannes raey 13 :9 endemenanebew,wuduq wudaqi yehonew seyitan meselu esat kesemay endemiawerd;bizu tamerat endemiaderg;meslu endemitenefes ena endeminegager;yalsegeduleten endemigedel tetsefual, quter 7 lay endeminanebew seyitanen yashenefew,yetalew ye Melaekt aleqa ye Qedus Mikael se'el te'amer ayadergem malet hilena matat new,lebb yeleshinet new.hilenahen tetekemebet.

  ReplyDelete
 3. ስእሊቷ ዘመናዊ ናት እያንዳንዳሽ ራስሽን አድኝ በማለት ራሱን አትረፋለች ማን ሞኝ አለ

  ReplyDelete
 4. የሰለጠነች ስእል ናት

  ReplyDelete
 5. በዚህ ዘመን ራስን ማዳን ነው ብላ ክእሳት ራሶን ጠበቀች

  ReplyDelete
 6. Oh, a view from a protestant. Zero analysis.

  ReplyDelete
 7. In the Name of the Father, the Son and Holy Spirit
  I beg you to repent and stop being heretic! Your whole attempt is to say Our God does not give special grace to the Saints. Contrary to your belief, Our Lord and Savior Jesus Christ king of Kings Alpha and Omega said to the Apostles that He will give them the right to Judge over the 12 tribes of Israel when He comes in His Kingdom. The grace of intercession and doing miracle to strength believers sothat they cannot not be led astray by heretic teachings is small compared to the grace to judge Our God reveals several miracles in the Name of Those who followed him leaving the wold or the saints!

  In 1968 and recently the holy Virgin Mary appeared on Coptic churches and several people were healed! This has been witnesses by Muslims and Christians and the recent one was also reported on CNN. You can read the following and also see in tube the images.

  On April 2, 1968, the Blessed Holy Virgin Saint Mary, Mother of God, appeared in different forms over the domes of the Coptic Orthodox Church named after Her at Zeitoun, Cairo, Egypt.

  Residents of Assiut, Egypt were awakened in the middle of the night on August 17, 2000 by an exceptionally bright light coming from Saint Mark's Coptic Orthodox Church. Those who looked toward the church saw an apparition of Mary between the church's two towers, accompanied by large, glowing white doves (a traditional symbol of peace and the Holy Spirit) flying around her.

  These miracles strengthened the belief of Our Egyptian Bother when the sword was over there neck they were praying when they were being sl beheaded knowing that they will join the saint in the Kingdom of our Lord! There Ethiopian (including our Eritrean brothers) Brothers accepted in Grace beheading and shooting in the name of thier faith! Now the protestant and catholic world is talking about the Martyrdom of Member of the unrevised Apostolic Church and the strength of the belief in the two sisterly churches
  In EOTC , several people have witnessed miracles, miraculous healing and there are Churches and monasteries where miracles is everlasting( Abune Haron, Armania merkorios etc).

  Amen

  ReplyDelete
 8. የማርያም ስም ሲነሳ የምትቃጠሉት ሰይጣን እና እናንተ መናፍቃን ናችሁ።

  ReplyDelete
 9. ዮሐ.ርእይ 13፥15"የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬው ምስል የማይሰግዱትን ሊያስገድላቸው;ለአዉሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።" ወንድሜ ይህንን አታስተውለውምን? እግዚአብሔር ብቻ ነው ሰጭ;እዚህ ላይ ፈጣሪ በሚያውቀውና ትንቢቱም የፈጸሙ ዘንድ ዝአውሬ የተባለ የሰይጣን ምስል እንዲህ የሚተነፍስ የሚገድል ብዙ ተአምራት የማድረግ ሥልጣን ሲሰጠው እንዴት ነው እግዚአብሔር ለእናቱና ለራሱ ሥዕል፣ለቅዱሳን መላእክት ለነቅዱስ ሚካኤል ሥዕል(ሰይጣንን ለአሸነፈ ወደ ምድር እንዲጥለው የሥልጣን የተሰጠው)፣የጻድቃንና የሰማዕታት ሥዕሎች እንዴት ነው ተአምር የማያደርጉት?የሰይጣን ምስል ከገደለ የነሱ ሥዕል የማያድኑት?የዚህን ትክክለኛ መልስ ቢኖርህ ኖሮ ነገ በአውሬው ምስል ከመንበከክ ድነህ በነሱ ሥዕሎች አማካኝነት በዳንክ ነበር።

  ReplyDelete
 10. ወዳጄ ምስል ተአምራት የማድረግ ሥልጣን እንዳለው በየተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አለ ?

  እኔ ግን ይህን ብቻ አምናለሁ
  ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።” (መዝ. (72)፥18)፡

  “እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና” (መዝ. (136)፥4)፡፡

  ReplyDelete
 11. ኤጭ አሁንስ በደንብ ማንነታችሁነ አሳወቃችሁ ልብ በል ልብ ያለው አሁን እነዚ ከመናፍቃን ጐራ ወይስ ከኛ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የማን ልጆች ናቸው ሌቦ አንተ የቤተክርስቲያን ልጅ ነኝብለህ ይህን ድረ-ገፅ ስለከተፈትክ ምንም ብታወራ አትታመንም ከአታላይ እውነት አይገኝም ያቺ ፍርፋሪ ሳንቲም እንዳትቀርብህ ሌላም ብትል አይገርምም በቀጣይ ደሞ ምን ብለህ ደሞዝህን ትቀበል ይሆን

  ReplyDelete
 12. yeamelak enate mekeberua yehene yahele yananedale? abete meshewede......

  ReplyDelete
 13. ቀልደኞቹ አሳቁኝ። አንድ ወቅት ክ/ሀገር የተወለድኩበት አካባቢ የሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ተቃጥሎ ደብሩ በእሳት ሲወድም ሚካኤል ግን በርሮ እንዳመለጠ አጎቴ አጫወቱኝ።የደብተራዎቹ ፈጠራ የተለመደ ነውና ምዕመናን እንጠንቀቅ።

  ReplyDelete
 14. የወላዲተ አምላክ ድንቅ ተአምር

  ReplyDelete