Tuesday, July 7, 2015

ይድረስ ለመምህር ዘመድኩን በቀለ፡- ሰባኪዎቻችንና መምህራኖቻችን ወዴየት እያመሩ ይኾን?!ከዲ/ን ኒቆዲሞስ
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ እንድጽፍ ያስገደደኝ ከሰሞኑን መምህር ዘመድኩን የተባለ የኢትዮጵያ ቤ/ን አገልጋይ በፌስ ቡክ ገጹ ያስነበበን ነገር እረፍት ቢነሣኝ ነው፡፡ መምህር ዘመድኩን በሊቢያ በአይ ኤስ አክራሪ ቡድን ሰማዕት የኾኑትን ወንድሞቻችን፣ ቤተሰዎቻቸውን በማጽናናት፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያውያንን አስተባብሮ ሲያደርገው በነበረው ቀና የኾነ አገልግሎት ስንቶቻችን አስደስቶን ከልባችን መርቀነው እንደነበር የትናንትና ገና ያልበረደ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡
ከሰሞኑን ግን መምህር ዘመድኩን በደቡብ አፍሪካ ባለው መንፈሳዊ አገልግሎት አስታኮ እንዲያ ልባችንን ከነካው አገልግሎቱ፣ ልፋቱና፣ ለወገን ያለው ፍቅርና መቆርቆር በተቃራኒ በሆነ መልኩ አንዳንች ፍቅርና ትሕትና በጎደለው መንፈስ ይሄንንም ያንንም ሲያዋርድ፣ ሲዘልፍና ሲሳደብ ባይ መምህርን ምን ነካው በማለት ይህችን አጭር ጦማር አደርሰው ዘንድ ብዕሬን ለማንሣት ወደድኹ፡፡
አስቀድሜ መምህር ለቤተ ክርስቲያንህ ያለህን ቅናት በግል አደንቃለኹ፡፡ የአባቶቻችን፣ የቅዱሳን አምላክ አገልግሎትህን የቀና እንዲያደርግልህም ጸሎቴ ነው፡፡ ግና በደቡብ አፍሪካ ስላለህ አገልግሎትህ በፌስ ቡክ ገጽህ ባስነበብኸን ጽሑፍ ቅሬታ አድሮብኛል፡፡ እስቲ በጽሑፍህ ቅር ካሰኘኝ መካከል አንዳንዶቹን ላንሣ፡፡ ‹‹… እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር አውሮጳም አፍሪካም ለአገልግሎት ስለዞርኩኝ ዩሮና ዶላር አበል ተቀብሎ ነው እንዲህ ደፋር የሚኾነው ብላችሁ የምታስቡ ካላችሁ እርማችሁን አውጡ፡፡ እኔ ዘመድኩን የጋሽ በቀለ ልጅ ሰባራ ሳንቲም ከቤ/ን አበል አልቀበልም፡፡››

ይህ ምን ማለት ነው መምህር ዘመድኩን?! እንደው የኾነው ኹሉ ቢሆንስ የእግዚአብሔር ሰው ለራሱ ጥብቅና ቆሞ እንዲህ እያለ አዋጅ ሊያስነግርስ ይገባዋል ብለህ ታስባለህ?! ደግሞስ መጽሐፍ እንደሚል ‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፡፡›› ተብሎ ተጽፎ የለ እንዴ?! ታዲያ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደ ዘንድሮ ሰባኪዎች ባልተጋነነ መልኩ ሣይሆን ከቤ/ን አበል ቢቀበሉ ነውር አለው እንዴ?! ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እኛ በመንፈሳዊ ነገር ያገልገልናችሁ ከእናንተ በሥጋዊ ነገር ብንጠቀም ትልቅ ነገር ነውን?›› ሲል አልተናገረም እንዴ?! ታዲያ ይህን ቃል ዘንግተኸው ነው?! በአደባባይስ እኔ የጋሽ በቀለ ልጅ ሰባራ ሳንቲም አልፈልግም በማለት በአደባባይ መፎከርስ ከአንድ ወንጌል አገልጋይ ይጠበቃል?!
በእንዲህ ያለ የአደባባይ ፉከራና ዘለፋ ለአንድ መንፈሳዊ ሰውና አገልጋይ የሚገባ ነው ብለህ ታስባለህ… ምንም ብትቀና… ምንም በቤተ ክርስቲያናችን ዙርያ እየሆነ ያለው ነገር ልብ ድረስ ዘልቆ ቢሰማህና ቢያብሰከስክህ እንዲህ ይባላል፡፡ አሁንም ከጽሑፍህ እጠቅሳለኹ፡፡
‹‹… የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን እንድትዋረድና እንድትጠፋ የማድረግ ሥራውን ከቀጠለ ከእነርሱ ጋር (ዘመድኩን ተሐድሶ ናቸው፣ በኦርቶዶክስ ማሊያ ለፕሮቴስታንት የሚጫወቱ ናቸው ብሎ የሚከሳቸውን ሰዎች እንደኾነ ልብ ይሏል) በቅንጅት እየሠራ ነው ማለት ነው፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ባለቤቶችን የዜግነት ጉዳይ አጠያያቂ ወደመሆን ይሸጋገራል፡፡ ይህ እንኳን ባይሆን፣ ሲኖዶሱም ዝም ቢል እንኳን ጣቢያውን በግሌ ቤቴንም ሽጬ ቢሆን ወደ ፍርድ ቤት ይዤው እሔዳለኹ፡፡ ቱ ምናለ በሉኝ ደግሞ አደርገዋለኹ …!!››
እንዴት፣ እንዴት ነው መምህር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢ.ቢ.ኤስ በሚያስተላልፈው ዝግጅት ዘመቻ ሆነ እንዴ ደግሞ የምትጠፋው፤ ቅዱስ ወንጌሉ፡- ‹‹ቤተ ክርሰቲያንን የገኻነም ደጆች እንኳን አይችሏትም፡፡›› ሲል ነው የተናገረው፡፡ ዘመድኩን በዚህ ማስጠንቀቂያው እኖርባታለኹ፣ አገሬ ናት የሚላትን የአገራችንን፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪን ሕገ መንግሥትን እየተጻረረ መኾኑ አውቆት ይኾን?! ‹‹መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፣ በአገሪቱ ኹሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው፣ የመንግሥት የሚባል ሃይማኖት የለም፡፡›› ተብሎ በግልጽ በሕገ መንግሥቱ ተቀመጠበት ለመኾኑ የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በጣቢያው በሚያስተላልፈው ዝግጅት በምን ሂሳብ ነው የቴሌቪዥን ጣቢያውን ሰዎች/ባለቤቶች የዜግነት ጉዳይ አጠያያቂ የሚያደርገው፡፡ እረ አገልጋዮቻችን ከማስተር መማር ይቅደም እንጂ!!
እሺ የምድራዊውን ሕግ መቼም ለጊዜው እንተወው እንደው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚፈታው በዓለም ፍርድ ቤትና ዳኛ ሆነ እንዴ?! የቀደሙት የወንጌል ገበሬዎችና እውነተኛ አባቶቻችን እንዲህ አላደረጉም፡፡ በተቃራኒው ይህን ክፉ ዓለም እየኮነኑ፣ እንደ ጻድቁ ሎጥ ጻድቅ ነፍሳቸውን እያስጨነቁ ተገፉ፣ ተዋረዱ እንጂ የተገላቢጦሽ ፍትሕን ለማግኘት አቤቱታቸውን ይዘው ወደ ዓለም ሸንጎ ፊት እንደቀረቡ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አንድም ቦታ አልተጻፈልንም፡፡ ታዲያ መምህር ይህን የአባቶቻችን ያልሆነውን ሥርዓት፣ ወግ ከወዴየት አገኘኸው እባክህ ጃል?!
እንዲህ ዓይነቱን አካኼድ ከአባቶቻችን፣ ከቅዱስ ወንጌል የተማርነው አለመሰለኝም፤ እንደው ምንም ቁጭት ውስጥህን ቢያንገበግበውና ቤትህን እንኳን ሽጠህም ቢሆን ሙግት ለመግጠም ብታስብስ ምነው ዘመድኩን አበው ‹‹ሙያ በልብ ነው!›› ይሉ የለ እንዴ እናሳ የአንተ በአደባባይ እንዲህና እንዲያ ባላደርግ ቱ በሉኝ፣ የበቀለ ልጅ አይደለኹም… ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ከልጅነትም በላይ ጅልነትና ቂልነት ይመስለኛል፡፡ ይህ ያሳፍራል፤ በምንም ሂሳብ መንፈሳዊነት ነው ብዬ ለማለት አልደፍርም፡፡ እውነቱን ልንገርህ የወንጌል አገልጋይ ሣይሆን ልክ እንደ አንድ ጀብደኛ ዓይነት ሰው መስለህ ነው የታየኸኝ፡፡
እንዲህ ያለ ቅጥ ስሜታዊ ስትሆን እጅጉን ያስገምትኻል፤ ደግሞስ እየኖርክባት ባለው ኢትዮጵያ የእምነት እኩልነትና ነጻነት በሕገ መንግሥቱ በግልጽ በተቀመጠበትና በከፊልም ቢሆን እየተተገበረበት ባለበት ኹኔታ የሌሎችን እምነት ድርጅቶችንና የግለሰቦችን ስም በመጥራት እንዲህ በአደባባይ ማዋረድና መዘርጠጥ ተገቢ አልመሰለኝም፡፡ በሕግም ሊያስጠይቅኽ እንደሚችል አስበውኻል መምህር፡፡
ከአንድ መንፈሳዊ ሰው ነኝ፣ የወንጌል አገልጋይ ነኝ ከሚል ሰው ‹‹ፕሮቴስታንታዊ ቅርሻታቸውን››፣ ‹‹ፓስተር ፓስተር የሚሸት ስብከታቸውን›› በማለት በእንዲህ ዓይነት የወረደ፣ እጅግ የዘቀጠ አባባል አንድን ሕጋዊ የኾነ የእምነት ተቋምና አገልጋዮቹን ማዋረድ ከተማረ ሰው አይጠበቅም፤ በሕግም ተጠያቂ እንደሚያደርግ አላሰብከውም ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ንግግር ከአንድ የወንጌል አገልጋይ ነኝ ከሚል ኦርቶዶክሳዊ ሰው ሲነገር ደግሞ እጅግ የሳቅቃል፣ ያሳፍራልም፡፡
መምህሩ በዚህ አላበቃም በሌላኛው ማስጠንቀቂያው ደግሞ የፌስ ቡክ ገጽ አንባቢዎችን ከፍ ዝቅ እያደረገ ‹‹አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ጽሑፌን ሳታነቡ፣ በእንግሊዝኛ የተጻፈውን አስተያየት በማንበብ ብቻ አስተያየት መጻፍ አይቻልም፤ መጀመሪያ ለስልካችሁና ለኮምፒተራችሁ አማርኛ ሶፍት ዌር አስገጥሙለት፣ እኔ የማንንም ጥብቅና አልፈልግም፣ ኹልህም ራስህን ችለህ አስተያየት መስጠት ነው የሚቻለው… ወዘተ፡፡››  የሚል ትእቢትን የተሞላ፣ ጸያፍ፣ ነውረኛ፣ ማንንም የማያንጽ ከንቱ ንግግር፣ ዘለፋና ፉከራ ሲያስነብበን የመምህር የጽሑፉ መንፈስ አንድ ግዳይ የጣለ ጀግና ነው ያስመሰለው፡፡
እንደው ‹‹ፕሮቴስታንታዊ ቅርሻታቸውን›› ‹‹ፓስተር ፓስተር የሚሸት ስብከታቸውን›› ይሔ ምን ይሉት ቋንቋ ነው፣ እንደው ቃላት መጡልኝ፣ ደጋፊ አገኘኹ ተብሎ እንዲህ ትርጉም ማይሰጥ ነገር በአደባባይ ይጻፋል እንዴ?! እንዲህ ዓይነትስ ፍቅርና ትሕትና ጎደለው ንግግር ከአንድ አገልጋይ ነኝ ከሚል ኦርቶዶክሳዊ ሰው ይጠበቃል ወገን?! ከሁሉም በላይ ፍቅር ይበልጣል፡፡ ደግሞስ መጽሐፍ፣ ‹‹ተጋድሎአችን ከክፉ መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ ከሰዎች ጋር ነው አለን እንዴ?! እንዲህ ጥርስን ነክሶ ብምራቸው አይማረኝ ዓይነት ንግግር፣ ፉከራና ዘለፋ የመንፈሳዊነት መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡
መምህር ዘመድኩን በዚህ በፌስ ቡክ ገጹ ባስነበበን ጽሑፉ ሲዝትና ሲገዝት ከኢቢ.ኤስ የቴሌቪዝን ጣቢያ እስከ ተሐድሶቹና የአራት ኪሎው ቡድን፣ የውጩ አገር ሲኖዶስና ገለልተኛው አልቀረውም፡፡ በውጭ ያለው ሲኖዶስ የፖለቲከኞች፣ የግንቦት ሰባት፣ የተሐድሶ መሸሸጊያ፣ ገልለተኛው ሕግ የማይገዛው … ወዘተ ብሎ በማለት አንዱን በጠላትነት ፈርጆ ሌላውን ጻድቅ ሲያደርግ፣ እንዴ እረ ዘንድሮ ይኽን ሰው ማነው አይዞህ ያለው ስል ለመጠየቅ ተገድጃለኹ፡፡
ለመሆኑ በአገር ቤት ያለው ሲኖዶስ ፖለቲከኞቹ ያሻቸውን የሚሾሙበትና የሚሽሩበት ሲኖዶስ መሆኑን አያውቅም ማለት ነው ወይስ ጨፍኑና ላሙኛችሁ ለማለት ነው፡፡ በዚሁ በአገራችን አይደል እንዴ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ን በታቦተ ሕጉ ፊት የአንድ ባህታዊ አባት ደም እንደ አቤል ደም በግፍ የፈሰሰው፡፡ ከልደታ እስከ ዑራኤል የእግዚአብሔርን ቤት በጥይት እሩምታ እንዲደባለቅ ያደረገው፣ ደወል መትተው እናት ቤ/ን የሙጥኝ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመንግሥት ታጣቂዎች አሳልፎ የሰጠው የትኛው ሲኖዶስ ይኾን እባክህ መምህር ዘመድኩን?! ዘረኝነት፣ ዝርፊያ፣ ሙሰኝነት እየናጠው፣ እያንገዳገደው ያለው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ አይደል እንዴ፡፡ እና እባክህ መምህር አስተውልህ ተናገር፡፡ ተጠንቅቀህም ጻፍ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ‹‹ማስተዋል ይጠብቅኻል፣ ጥንቃቄም ጋርድኻል፡፡›› እንዲል፡፡
ኢ.ቢ.ኤስን፣ የተሐድሶንና የአራት ኪሎውን ቡድን የምትላቸውን ቤትህንም ሽጠህ ቢሆን እንኳን ፍርድ ቤት ለመገተር ቆርጠህ የተነሣኸው ዘመድኩን ከዛ በፊት ግን መጀመሪያ እየኖርክባት ያለኸውን የአገሪቱን ሕግ መንግሥት ለማንበብ ሞክር፡፡ የተጠራኸው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ከኾነ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ማስተማር እንጂ ስለ ሌሎች ማውራት ምን ይበጃል፣ ለምንስ በውስጡ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ነጻነትን፣ እውነትን፣ ፍትሕን የያዘውን ወንጌልን በምንሰብከበት ከፈጣሪ በተሰጠን ወርቃማ ጊዜያችን ሌላ የማይረባና ሌሎችንም የማያንጽ ነገር በማውራት እናባክናለን፡፡
አሁን ያለኸባትና ወንጌል እያገለገልኩ ነው የምትላት አገር ደቡብ አፍሪካ እኮ እርስ በርስ በመረጋገምና በመዘላለፍ፣ በመለያየትና በመከፋፈል አይደለም ለዚህ የበቃችው፡፡ ኹሉም ሃይማኖቶችና ሕዝቦች ተከባብረውና ተፈቃቅረውና እንደ ማንዴላ ያሉ ፍቅርን፣ ይቅርታን ያስቀደሙ ጀግኖች ለመውለድ በመቻላቸው ነው ሕዝቡን ከእርስ በርስ ዕልቂትና ፍጅት ታድገው የትናንትናውን አስቀያሚና ዘግናኝ ታሪክ በይቅርታ ዘግተው ያችን አገር ‹‹ሬን ቦው ኔሽን›› የሚል ቅጽል ሰም እንዲሰጣት የሆነችው፡፡
መቼም ዘመድኩን የማንዴላ፣ የታታ ማዲባ አድናቂ እንደሆንክ አውቃለኹ፡፡ ታዲያ እንዲያ የምታደንቃቸው ታላቅ ሰው እኮ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው፤ ግን ደግሞ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያላቸው ክብርና ፍቅር በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነው፡፡ መቶ ዓመታትን ያስቆጠረው አንጋፋው ፓርቲያቸው ኤ.ኤን.ሲ (አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ) እንኳን የተመሠረተው በደቡብ አፍሪካ በምትገኘው የኢትዮጵያ ቤ/ን ነው፡፡ ዘመድኩን በደርባን ያገኘኻቸው ደቡብ አፍሪካዊው የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋይ ቀሲስ ክንፈ ገብርኤል ታሪኩን በሰፊው ይነግሩኻል፡፡
ምናልባት ደግሞ ወደ ፕሪቶሪያ ኪዳነ ምሕረት፣ ወደ ጆሐንስበርግ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል፣ በተለይ በመድኃኔ ዓለም ካቴድራል የሚያገለግሉትን መልአከ ሰላም ቀሲስ ዴሊዛ ኔልሰን ቫሊዛን አግኛቸው፣ የታሪክ አዋቂ የዕድሜ ባለጠጋ ናቸውና በደንብ ይነግሩሃል፡፡ በተረፈ ወደ ኬፕታውን ቅዱስ ገብርኤል፣ ወደ ብሉም ፎንቴን ቅድስት ሥላሴና ቅዱስ ያሬድ ገዳም፣ ኢስት ለንደንና ፖርት ኤልዛቤት ከኼድክ በሺህ የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን የኢትዮጵያ ቤ/ን አባላቶች ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ቤ/ን ያላቸውን ፍቅር በሚገባ ትረዳለዋለህ፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ደቡብ አፍሪካውያኑ ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት ክብርን፣ ወንድማማችነትንና ፍቅርን የተሞላ ነው፡፡  
መቼም ዘመድኩን ዞር ዞር ብለህ አገሪቱን እየጎበኘኽ ነው አይደል፡፡ እና እንደው ምን ታዘብክ፡፡ እስቲ በዛች በማንዴላና በትግል አጋሮቹ የዕርቅና የፍቅር መንፈስ መሠረት ላይ በቆመች አገር የታዘብከውን ጻፍልን፡፡ በአገሪቱ ያሉትን ታሪካዊ ቦታዎችና ቤተ መዘክሮች ለመጎብኘት ሞክር፡፡ ከቂም በቀል፣ ከጥፋትና ከመፍረስ ታሪክ ለመውጣት የከፈሉትን የፍቅር፣ ይቅርታ መሥዋዕትነት ለማሣየት በአገሪቱ ቆሙትንና ታሪካዊ ቅርሶችና ሕያው የይቅርታ መዘክሮች ልታሣየን ሞክር፡፡
መምህር ዘመድኩን እስቲ ይህን ለማንኛችንም የማይጠቅመውን ነገር ትተህ የጀመርከውን የዕርቅ የምስራች ዜናዎችህን ትቀጥልልን ዘንድ በዛች አገር የሆነ አንድ አስደናቂ ታሪክ ልንገርህ፡፡ ማንዴላ ከእስር በተፈቱ ማግሥት ነጭ አክራሪዎች ክሪሳኒ የሚባለውን የፀረ-አፓርታይድና የጥቁሮች መብት ታጋይ ጀግና በአደባባይ በመኪናው ሲጓዝ በጥይት ደብድበው ገድለው ሬሳውን መሬት ለመሬት ጎተቱት፡፡ ገና ነጻነታቸው በታወጀ ማግሥት፣ የቀድሞው ቁስላቸው ገና ባልጠገገበትና እያመረቀዘ ባለበት ይህን ጭካኔና ድፍረት ያዩና የሰሙ ደቡብ አፍሪካውያን ‹‹ብጥለው ገለበጠኝ›› እንዲሉ፣ አሁንስ በዛ በማለት ጦር መሳሪያቸውን ወልውለውና ገጀራቸውን አዘጋጅተው ነጮችን ለመበቀል ሆ ብሎ ተነሡ፡፡
ይህን ጊዜ የይቅርታ አባት የሆኑት ማንዴላ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው እግዚኦ ሲሉ ሕዝባቸውን ተማጸኑ፡፡ ሁሉም ሃይማኖት መሪዎች ከአይሁዳውያን እስከ ሂንዱ፣ ከእስልምና እስከ ክርስትና ኹሉም ጾም ጸሎት ይይዙ ዘንድ አዋጅ አሰሙ፡፡ ቂም በቀል ሌላ በቀል እንጂ ጥቅም እንደሌለው ለሕዝባቸው በፍቅርና በትሕትና አስረዱ፡፡ የትግል አጋራቸው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱም ይህን ተከትለው በአገሪቱ ያለ ምንም ልዩነት ሁሉም እንደ እየምነቱ ብሔራዊ ጾምና ጸሎት በአገሪቱ እንዲታወጅ አደረጉ፡፡
በወቅቱ ይህን የሦስት ቀን ጾምና ጸሎት አዋጅ በተመለከተ አንድ ደቡብ አፍካዊ ወዳጄ እንዲህ ሲል ነበር በአገሪቱ ያሳደረውን ድባብ በአጭር ቃል የገለጸልኝ፡- ‹‹South Africa stood still!!›› ከተማይቱ ትንፋሽ ላይሰማባት ፀጥና ረጭ አለች፡፡ ለይቅርታና ለምሕረት የተጉ ደቡብ አፍሪካውያን፣ ጥቁር፣ ነጭ፣ ሕንድና የውጭ አገር ሰዎች ሣይሉ ኹሉም በዛች አገር ያንዣበበው የሞት ጥላ፣ የእልቂት ደመና ይገፈፍ ዘንድ በእንባና በጩኸት ፈጣሪያቸውን በየጓዳቸውና በየቤተ እምነት ተቋማቸው ሲማጸኑ ነበር፡፡
እናም መምህር ዘመድኩን ያ የተፈራው እልቂትና ደም መፋሰስ ሣይሆን በዛች አገር ጥቁርና ነጭ በወንድማማችነት መንፈስ ለመተያየት የበቁበትን አስደናቂ የታሪክ ምዕራፍን በፍቅርና በይቅርታ ከፈቱ፡፡ ለመሆኑ ማንዴላ እስከ ሞታቸው ቀን ድረስ የግል ጠባቂያቸው ነጭ እንደሆነ ታውቅ ኖሯል፡፡ ጥቁር ከሰው በማይመደብባት አገር ያን ዘግናኝ ታሪክ በይቅርታ ዘግተው፣ ሰው በሰውነቱ፣ የሚከበርበት፣ ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል የሚሆንባት፣ ፍትህ ሰፈነባት አገር ለመመስርት በቅተዋል፡፡
ከሰሞኑ በዓለም አቀፉ ጦር ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን የሱዳኑ መሪ ጄ/ል አልበሽርን ከአገር እንዲወጡ አድርጋችኋል በማለት የደቡብ አፍሪካ ጠቅላይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥትን መክሰሱን መቼም ከአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ሳትሰማ አትቀርም፡፡ ይኸውልህ እንግዲህ ደቡብ አፍሪካ ማለት በሕግ ፊት መንግሥትም ሣይቀር የሚጠየቅባት፣ የሚከሰስባት አገር ናት፡፡ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ሳይለያያቸው ለእውነት፣ ለፍትሕ ኹሉም ድምፁን በአንድነት የሚያሰማባት አገር፡፡
ለመሆኑ እኛ እንዲህ ዓይነቱ ኅብረት፣ እንዲህ ዓይነቱ መቀባበል፣ ፍቅርና አንድነት አለን እንዴ፣ በአብዮቱ ማግሥት ወጣቱ እንዲያ በጥይት እየተረፈረፈ ሬሳ እንደ ጉድፍ ሲከመር፣ አገሪቱ በሞት አበጋዞች አኬል ዳማ፣ የደም ምድር ስትሆን፣ እናቶች እርማቸውን እንዳያወጡ፣ ለቅሶ በተከለከለባት፣ ልጆቻቸው ለተገደሉበት ጥይት ብር እንዲከፍሉ በተደረገበት፣ በ1997 ምርጫ ማግሥት ሮጠው ያልጠገቡ ልጆች እንኳን ሣይቀሩ በአጋዚ የጥይት አረር ደማቸው እንደ ውሻ ደም በየአስፋልቱ ላይ ሲፈስ ለመሆኑ የትኛው የሃይማኖት አባት፣ የትኛው ፖለቲከኛ ነው ሕዝቡን አስተባብሮ ለጸሎት፣ ለምሕላ የጠራው፡፡
እናም መምህር ሌሎችን በእምነታቸው፣ በግል አቋማቸው መዝለፍ፣ ማዋረድና ብማራቸው አይማረኝ የሚለው ፉከራው ይቅርብህና ባለፈው ሰሞን እንደ ጀመርከው በኢትዮጵያውያን መካከል እየሆነ ስላላው ፍቅር፣ ዕርቅ፣ ሰላም እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን በወንጌል እውነት አንድ ሆነው እያደረጉ ያሉትን አግልግሎት ብትጽፍልን ይሻለናል፣ ይጠቅመናልም፡፡
መቼም ወገኖቻችን ከወንበዴና ከቀማኛ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው የሚያገኟትን ሳንቲም አጠራቅመው፣ ወንጌል ርቧቸው በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር ብራቸውን ከፍለው ከአገር ቤት የወንጌል መምህር የሚጋብዙት፣ ብር ተርፏቸው ሣይሆን ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ እውነትን፣ ዕርቅን፣ አንድነትን የሚያስተምራቸው ፈልገው ነው፡፡ እንጂ ለመከፈፋፈልና ለመለያየትም እዛ ያለው እኮ ከበቂ በላይ ነው፡፡ እናም ሌላውን ሁሉ ተወውና ወንድማችን የጀመርከውን የዕርቅና የፍቅር አገልግሎት በሌሎችም የደቡብ አፍሪካ ከተሞች እንዲቀጥል ለማድረግ እንድትችል አምላከ ቅዱሳን ይርዳህ!!
በመደምደሚያዬም በደቡብ አፍሪካ የትምህርት ጊዜዬና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎቴ ወቅት ያስተዋልኩት አንድ ችግር በዛች ምድር ለአገልግሎት የሚመጡ መምህራንና ሰባኪያን ከፍተኛ የሆነ ቋንቋ ችግር አለባቸው፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከመጡት ሰባክያን አንዳቸውም ደቡብ አፍሪካውያኑን የቤተ ክርስቲያናችንን ተከታዮች በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር ሳይችሉ ቀርተው እንዲሁ ኢትዮጵያኑን ምእመናን ብቻ ነው አገልግለው የሚመለሡት፡፡ የማስታውሰው በቲኦሎጂ የማስተርስ ድግሪ አለው ተብሎ የመጣው መምህርም እንኳን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሊያስተምር ቀርቶ ራሱ እንኳን በሚገባ ለመግለጽ የማይችል መሆኑ ብዙዎቻችን ነበር ያሳቀቀው፡፡
ለመሆኑ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ በትምህርት ጥራት ላይና በሚያስመርቃቸው ደቀ መዛሙርት ችሎታና የቋንቋ ክህሎት ላይ መሥራት አይገባውምን፡፡ እኛ እኮ ከዓለም አስቀድመን ወንጌልን የተቀበልን ሕዝቦች ነን፡፡ ታዲያ ቢያንስ እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱን ግዙፍ ታሪክ፣ የአባቶቻችንን ተጋድሎን በሚገባ መተርክና ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ማዳረስ ቢያቅተን ለዚሁ በአኅጉራችን ለሚገኙ ቤተ ክርስቲያናችንን ብለው ለመጡ ወገኖቻችን ለማስተማር እንዴት እንሰንፋለን ጎበዝ?!
እነዚህ በየዓውደ ምሕረቱ እዩን እዩን የሚሉ ሰባኪያን በኮሌጁ ቆይታቸው በድግፍግፍ ከዓመት ወደ ዓመት የተሻገሩና የመመረቂያ ጽሑፋቸውን በገንዘብ ያሠሩና የወንጌል አገልግሎትን የትርፍ ጊዜ ሥራቸው አድርገው ያዙ፣ በአገልግሎታቸው ዳተኛ የኾኑ፣ ወንጌልን በአውሮጳ ኳስና ፕሪሚየር ሊግ የለወጡ ከእነዛ ከምናውቃቸው ስም አይጠሬ መምህራን መቼም በጎ ፍሬ መጠበቅ ከእባብ ዕንቁላ የርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ያለ ነው የሚኾነው፡፡   
ግና የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች በዓለም ዙሪያ እየዞሩ የሚያገልግሉ መምህራን በቂ የሆነ ችሎታ ያላቸው፣ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዓለማዊውም በመንፈሳዊውም እውቀታቸው የበረቱ፣ በሁለት ጫፍ እንደተሳለ ሰይፍ የሆኑ፣ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የተመሰከረላቸው፣ ጥሩ የቋንቋ ክህሎት ያላቸው፣ ለገንዘብና ለጥቅም የማይደለሉ ሰባኪያንን በማፍራት በኩል ጠንክረው መሥራት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ በዚህ ረገድም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በሁለተኛ ድግሪ የጀመረው ትምህርትም በስፋትና በጥራት ይቀጥልና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክና ክብር የሚመጥኑ የወንጌል አገልጋዮች ይወጡበት ዘንድ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የኮሌጁ አስተዳደርና መምህራን የበኩላቸውን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል እላለኹ፡፡ አበቃሁ!!

33 comments:

 1. እኔ ምለው ዘመድኩን የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትን አለው እንዴ ? ካሴት ሻጭ ነው እኮ መምህር እንዴት ተባለ ? ምን ተምሮ መቸም ዲያቆናዋን አልሞከራትም ?
  የሚገረመኝ ደግሞ ወንጌል ሰባኪ ነኝ ይለናል ለምሆኑ ወንጌል ማለት ትርጉሙን ያውቀው ይሁን ? የትኛው ወንጌላዊ /ሐዋርያ ይሳደብ የነበረው ? ዘመድኩን በየእያንዳንዱ አረፈተ ነገር ስለ ገንዘብ ነው የምታወራው እር ግጠኛ ነኝ የጠላሀቸው የጥቅም ጉዳይ ነው ።
  ዘመደኩን ሰባኪ ከመሆን በፊት ክርስቲያን ሁን ፡ በብዙ ክፋት ተይዛሀል እግዚአብሄር ይማርህ መቸም እንደለመድህው እንደምትሰድበኝ አማናለሁ

  ReplyDelete
 2. ዘመድኩን እውድህ ነበር በዚህ ሰሙን አፈርሁብህ
  ይህን ያህል በስድብ የተካንህ ነህ ለካ ? በስድብ መንፈስ ከአውሬው ጋር የተዛመድህ መስለኝ

  ReplyDelete
 3. Saron Yohans ይድረስ ለአቶ ዘመድኩን በቀለ ለምን አቶ አልሽኝ ብለህ እንደማትወቅሰኝ ተስፋ አለኝ መምህር ብዬ እንዳልጠራህ መፅሀፍ ቅዱስ ስለሚከለክለኝ ነው ማንንም መምህር ብላችሁ አትጥሩ መምህራችሁ አንድ ነው ተብሎ ተፅፏልና ታዲያ አቶ የሚለው አጠራር የሚበቃህ አይመስልህም ኧረ ሲበዛብህ ነው የሰው ትዳርን ለምታፋታ የብዙ ሴቶችን ህይወት ባጭር ለቀጨኸው ላንተ አቶ ሲበዛብህ ነው የስንቱን አገልጋይ ስም ለምታጠፋ የጓደኛህን የዘማሪ እንግዳ ወርቅን ንብረቱን ዘርፈህ ስሙን አጉድፈህ ላለኸው ላንተ አቶ ሲበዛብህ ነው ያኔ ጌልጌላ መዝሙር ቤቴ እየደከመብኝ ነው ቤተሰቤን ማስተዳደር እየተሳነኝ ነው ከጉድ አውጣንኝ በአንተ አስተባባሪነት ኮሌክሽን መዝሙር ስራልኛ ድጎማ ስጠኝ ያልከው ጊዜ በጋሻው እሺ ቢልህ ኖሮ ዛሬ ከበጋሻው ጋር ሽር ብትን እንደምትል አልጠራጠርም ነበረ ለነገሩ አንተ የበላህበትን ወጭት ሰባሪ የጎረስክበትን እጅ ነካሽ እንደሆንክ የአደባባይ እውነት ነውበቅርቡ በፃፍካት የውንጀላ ጦማርህ ላይ የቅርብ ወዳጆችህን ሳይቀር ሙልጭ አድርገህ ዘልፈሀቸዋል አንተ ራስህን ንፁህ አድርገህ ብትመለከትም ከሰደብካቸው አካላት ግን በሰኔ ፆም ጥሬ ስጋህን ስትቆርጥ ውስኪህን ስትጨልጥ የሚያሳይ ፎቶ ልከውልሀል ለመሆኑ ምን አነሳሳህ የ4 ኪሎውን ጉሩፕ ለመዝለፍ ? ለአንባቢ ግልፅ እንዲሆን ዘመድኩን 4 ኪሎ ብሎ የገለፀው እነማን እንደሆኑ ለመግለፅ እገደዳለሁ 1 ምህረተ አብ አሰፋ 2 ዘሪሁን ሙላት 3 ጳውሎስ መልክአስላሴ 4 በላይ ወርቁ 5 ተስፋዬ ሙሲሳ 6 ዳዊት ጥበቡ ...ወ..ዘ...ተ.. ለምን ሰደብካቸው እንዴ 13 ሺብር አውጥተው በአንድ ቀን ጭፈራ ቤት እንደጨፈሩ ከሴት ጋር እንደማገጡ መግለፅህ ለምን እንዴ አንተ ንፁህ ሆነህ ነው ? ይህንን ተሳዳቢው ዘመድኩን ያለውን እውነት ለማየት 4 ኪሎ ፅግነሽ ፣ ቱሪስት ፣ ምርፋቅ ..መሄድ በቂ ነው ራስህን ግን ንፁህ ለማድረግ አትሞክር ሰሞኑን በተሰውት ሰማእታት ስም የሚመጣውን ገንዘብ ከመቶ ሀያ ፕርሰንት እየቀነስህ ለሟች ቤተሰቦች እንደምትሰጥ ስሰማ ልቤ አዘነብህ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ሲሰራ ከመቶ ሀያ ፐርሰንት እንደምትቀበል አውቅ ነበር ከነዚህ ምኪኖች ላይ መቀነሱ ግን አሳፋሪ ነው እስኪ ወደ ጉዳዬ ልግባ በሰሞኑ የስድብ ፅሁፍህ ብዙ ዘማሪዎችን አዝማሪ ብለህ ስትዘልፍ ታይተሀል ለመሆኑ አዝማሪ ምን ማለት ነው ዘማሪስ ምን ማለት ነው ? አዝማሪ ማለት የሰዎችን ስም እየጠራ የሚጮህ ግጥም እየተነገረው የሚዘፍን ማለት ነው ይህን በል ተብሎ የሚል ማለት ነው እንዴ ገልብጠህ ነው እንዴ የምታስበው ???? ቤተ ሰቦቼ ዘመድኩን በቀለ ጊዮርጊስ ጋር ጌልጌላ የሚል መዝሙር ቤት አለው አሁን ግን የለም ብንለው ይቀላል በቅርቡ ደግሞ ደግሞ መርካቶ ድር ተራ 4ኛ ህንፃ ላይ ሌላ መዝሙር ቤት ከፍቷል እውነቴን ነው የምነግራችሁ በሁለቱም ሱቆቹ አዝማሪ ናቸው ያላቸው ካሴትም ሆነ ቪሲዲ ይሸጣል እንዴ አንተ በሱቅህ የምትሸጠውን ለምንድነው ህዝቡን የምታከላክለው? እስኪ ተሀድሶ ወይም አዝማሪ ያልካቸውን ሰዎች ልግለፅልህ ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ቀሲስ ትዝታው ቀሲስ እንዳልካቸው ዘማሪ ዳግማዊ ዘማሪ ቸርነት ዘማሪ ታምራት ዘማሪ ሀብታሙ ዲያቆን እዝራ ዲያቆን ፍራኦል ዲያቆን ሀዋዝ ዘማሪ ገብረ አምላክ ዲያቆን ነብዩ ዲያቆን ሰሎሞን ዘማሪ አቤል ዲያቆን አማረ ዘማሪ መስፍን ዘማሪ አበበ ዲያቆን ዳዊት ዲያቄን ሰማኸኝ ዘማሪ አሸናፊ አበበ...ዘማሪት ዘርፌ ዘማሪት የትም ወርቅ ሙላት ዘማሪት ቅድስት ዘማሪት ፋንቱ ዘማሪት ዘማሪት ምርትነሽ ዘማሪት ፅጌረዳ ዘማሪት ዘመናይ ዘማሪት ትርሀስ ዘማሪት መስከረም ዘማሪት ሀና ዘማሪት ፍቅርተ ዘማሪት ዮርዲያኖስ ዘማሪት እንቁስላሴ ክራር የሚደረድሩት አንተነህ ተፈሪ ፍስሀ ሚኪያስ ደሳለኝ በሀይሉ ተስፉ የወሊሶው ተስፉ የየትሜ ...ያልጠራኋቸው በጣም ብዙ አሉ ሁሉም ግን አንድ ናቸው አንተ በእጅጉ የምትኮራበት ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ በቅርቡ ባወጣው ኮሌክሽን ላይ የመውጊያውን ብረት ወልደሻል ማለት የለበትም ማርያም የመውጊያ ብረት አልወለደችም የመውጊያ ብረት የተባለው ዲያብሎስ ነው ብለህ ማለትህ ልጅህንም ሳያሳፍረው አይቀርም ታዲያ ዘማሪው ቴዎድሮስ ታኦሎጎስ ላይ ተገኝቶ መዘመሩን አልሰማህምን ኧረ በደንብ ነው የሰማኸው ግን ለምን ታኦሎጎስ ቀረበ ብለህ መረጃ እያሰባሰብክበት ነው ሰምቻለሁ ሰውን መክሰስ ስራህ ስለሆነ አልፈርድብሀም ዘማሪ ነብዩ ለምን ሊቀ ካህን ኢየስስ ብሎ ዘመረ ብለህ እየዘለፍከው ነው ገብረ ዮሀንስ ለምን ዱባይ ሚካኤል ሄደ ብለህ ስሙን እያብጠለጠልክ ነው አንተ ለመሆኑ ማነህ ? ደግሞ የሚያገለግሉት ጃቴ እና ዮሴፍ ብቻ ነው ትላለህ አሉ የሚያገለግሉት ውስን ቦታ ነው ትላለህ አሉ አዲስ አበባ አለም ገና ሙሉውን ማነው የሚያገለግለው? እስጢፋኖስ ቃሊቲ አካባቢ በሙሉ ቂርቆስ ከርቸሌ ሚካኤል ሳሪስ አቦ ኮተቤ አረ ልደታ እስኪ ንገረኝ የት ነው ያላየሀቸው? ክፍለ ሀገር በሙሉ ማነው እያገለገለ ያለው ?ማፈሪያ አትሁን ባክህ የማያገለግሉት የት ነው ብለህ ጠይቀኝ እኔ እነግርሀለሁ ዛሬ ማንም አዲስ አበባ የለም ሁሉም ክፍለ ሀገር ነው እያገለገሉ ያሉት ምዕመናን ሁላችሁ ላሳስባችሁ አገልጋዩ ሁሉም አንድ ነው ሊለያይ ነውና አቶ ዘመድኩን የሚዳክረው እባክልችሁ ለእውነት ቁሙ እግዚአብሔር ሀይማኖታችንን ይጠብቅ።አሜን

  ReplyDelete
 4. ዘመድኩን እስኪ መፅሐፍ ጠቅሰህ አውራ አንተ ደግሞ አሰግድን አትጥራ አልኩህ እኮ ባህታዊ ገብረ መስቀል መሰለህ እንዴ ? ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ድግሪው ነቀጠችው የምትለው ድግሪ የተነጠቀ ሰው የት ሀገር ነው ማስትሬቱን የሚሰራው በዚያው ትያንስ ካልሆነ የትም የለም ። ዳዊት ጥበቡ መሪጌታ ነው አልከኝ እሱማ ዘሪሁን ሙላቱን አፍ ያስያዘው ፅጌ ስጦታውና ሙሴም መሪጌታ ናቸው ምን ዋጋ አለው ...ምህረተ አብ ማለት ለፓስተር ዳዊት እውቅና የሆነው ቤተ ክርስቲያንን ያሰደበው ፍልፍሉን ነው ከኮተቤ ሰክሮ ስፒከር የተነጠቀውን ነው ወይስ አስረግዞ የካደውን ነው እስኪ ማነው ምረተ አብ ንገረኝ ? ተስፋዬ ሙሲሳ ማነው ይሄ ሷዲቅ ለተባለው ሙስሊም አንላካችን አላህ ነው ብሎ የመሰከረውን ነው ደግሞ እሱ የት ነው ያለው ? የት ደብር ነው ሚያገለግለው? ኧረ የት የትስ ነው የተማረው? በላይ ወርቁ ማለት ሚስቱን በፌስ ቡክ ያጣውን ነው ያልከኝ ወይስ ሌላ አለ ጨርቆስ ቤተ ክርስቲያን በውርደት የተባረረውን ነው ያልከኝ ? ጳውሎስ ትዝታውን መች እንዲህ ይጠላው ነበው እንዴ ሴት እኮ መብት አላት የምፈልገው ትዝታው ነው የማገባውም እርሱን ነው ካለች መብቷ ነው የምን ትዝታውን መርገም ነው ጳውሎስም የፈለገውን መርጦ ማግባት ይችላላ በቃ ያ አምልጦታል እስኪ ሌላ የተመካህበትን ንገረኝ አንተ ?????

  ReplyDelete
 5. ባለጌን ባለጌ ማለት ተገቢ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ይህ ግለሰብ ግን በጣም ተራና አልባሌ ነገሮችን የሚደረክት አፍቃሬ ማህበረ ቅዱሳን ስለሆነ እሱ በዘባረቀ ቁጥር መልስ መስጠት ጊዜን ማባከን ይመስለኛል፡፡ የሚያነሳቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ያልበሰሉና የ21ኛዉን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይመጥኑ ስለሆኑ፣ ዘመድኩን በራሱ አለም እንዲኖር ከመተዉ የተሻለ አማራጭ አይኖርም፡፡
  ግለሰቡ በፌስ ቡክ ገጹ የፈለገዉን ነገር መጻፍ መብቱ ነዉ፡፡ እኛ ያለን አማራጭ እሱ የቀባጠረዉን ነገር አይቶ እንዳላዬ ማለፍ ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት በስም አጥፊነት ተከሶ ቃሊቲ ሶስት ወር ታስሮ የተፈታ ስለሆነ የወንጀል ምንነት ይጠፋዋል አይባልም፡፡ ስለዚህ ድጋሚ እስኪታሰር ድረስ እንዳሻዉ መሆን ካማረዉ ይችላል፡፡

  ReplyDelete
 6. ሁለታችም ጠባብነት አየሁባቹ ይገርማል

  ReplyDelete
 7. ዘመድኩንና ሥድብ፣መለያየት ፣ጥላቻ ፣ክፋት መቼ ተለያይተው ያውቃሉ ? ይሡ ተሣዳቢ መምህርነቱ ሲገርመን ብዙ ተሣዳቢዎች ማፍራቱ ። ያሣዝናል ቀሚሡን ጣል አርጎ ወንጌል ጨብጦ ይቆማል አንድም ጊዜ እንኳ ወንጌሉን ሣይገልጥ ሥለ ከበደ፣ሥለ ማሞ ፣ሥለ አሥቴር ብቻ ሥለ ሥጋ ለባሽ አሉ..አሉ...አሉ ብሎ ይቀመጣል።በቃ ።ከዚያም ...." ቃለ ህይወት ያሠማልን ሲባል ....አሜን !!!! ወይ ቃለ ህይወት ????????? ቃለ ሙታን እየሠበኩ ....ቃለ ህይወትን መጠበቅ ???????
  ልቦና ይሥጠው !!!!

  ReplyDelete
 8. ገለባ ቢከመር ገለባ እንጂ ሌላ አይሆነም
  ይህን ከላይ የጠቀስኩትን ለማለት ያነሳሳኝ ከዚህ ቀደም መንፈስ ቅዱስን ስደተኛ ለማድረግና አንዲቷን የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለመሳደብ ለማዋረድ ብሎም በሐሰት ለመክሰስ ይዳክር የነበረው እራሱን ዲያቆን በሚልና የቤተክርስቲያኗ አካል በሚል ሽፋን የሚያወናብደው አቶ ኒቆዲሞስ ዘመድኩን በቀለ ይህን አለ እያለ ትርኪ ምርኪና ዘባራቂ ጽሑፉ ምክንያት ነው።
  ዘመድኩን ምንም ይበል ምን የአቶ ኒቆዲሞስ ምላስ ከሁለትም አልፎ ሶስት አራት በላይ መሆኑ የግለሰቡን ማንነት የሚያመላክት ነው። ይህ ግለሰብ ዘመዱኩንን ስለ እራሱ ተናገረ ብሎ በአብጠለጠለበት አፉ በሌላ መንገድ እራሱን የእንግሊዘኛ ቋንቋ አዋቂ በማድረግ ሌላውን በቲዮዎሎጅ ማስተርስ አለው ያለውን እራሱን መግለጥ እንሿን የማይችል እያለ የሚያቃልልና የሚሳደብ ነው።
  ይህ ግለሰብ ሁሉም ሐይማኖቶች በህገ መንግስቱ እኩል ናቸው እያለም ይናገራል። እኩል ናቸው ማለት ምን ማለት ነው? አንዱ ከሌላው ቤተ እምነት ገብቶ መበጥበጥ ወይስ የእምነቷ አማኝ ሳይሆን ተመሳስሎ በውስጧ ሆኖ ነቀፋና ተፃራሪ አሥተምሮ በመርጨት ማተራመሥ? ሁሉም እምነቶች በህገ መንግስት እኩል ናቸው ማለት እምነታቸውን በማስመዝገብ በነፃነት በተፈቀደላቸው ቦታ ማራመድ ይችላሉ ማለት ነው። እንዲያውም እንደ USA(በተለምዶ አሜሪካ በትጠራው አገር) ባሉ አገራት ዛሬ ሳይሆኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነን በማለትና እራሳቸውን ፕሮቴስታንት መሆናቸውን በለዩ አካላት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ላይ የሚዐመተው ዘመቻ በህግ የሚያስቀጣ ነበር። አቶ ኒቆዲሞስ ግን የእራሱን መናፍቅነት ለመደበቅና ለማድበስበስ ሁሉም ሀይማኖቶች በህገ መንግስቱ እኩል ናቸው በማለት ህገ መንግስቱን ለተሳሳተ አሥተሳሰቡ መከላከያ ለማድረግና በተሳሳተ መንገድ ለመተርጎም ይባዝናል።
  ሌላው ማንና ምን እየሰራ እንዳለ የሚያጋልጠው ዘመድኩን "ፕሮቴንስታታዊ ቅርሻታቸውንና ስብከታቸው የፕሮቴስታንት ፓስተር ይሸታል" አለ ብሎ ለፕሮቴስታንቲዝም ምን ያህል እደቆመ ያመላከተበት ነው። ዘመድኩን የለበሱት ማሊያ ሌላ ተግባራቸውና ግባቸው ግን ፕሮቴስታኒዝም ነው ስለዚህ ወይ የለበሱትን ማሊያ አውልቀው ለባለማሊያዎቹ ይመልሱና ማንነታቸውን ገልጠው ኢቢኤስ ላይ ይውጡ አለበለዚያ ግን የለበሱትን ማሊያ የሚያንቋሽሽ በማሊያው በደብቀው ማራመድ አይችሉም ማለቱ እጂግ ነው ያሳበደህ። ቅርሻት ማለት የማይስማማ ከውስጥ ወደ ውጭ የተተፋ ማለት ነው። ሥለዚህ ሐሰተኛ ትምህርት፣ ክርስቶስን የሚያቃልል ትምህርት፣ ቅዱሳንን የሚጠላና የሚያሳድድ ትምህርት፣ በአጠቃላይ በእውነተኛው የወንጌል አሥተምሮ የወጣ የክፉ ወንጌል ተብዬ ሁሉ ቅርሻት ነው። ታዲያ አንተ እንዲህ የእንቧይ ክምር የሆነ ጽሑፍ ለመከመር የበነሳኸው ይህ ሐሰተኛ ወንጌልህ ቅርሻትነት ለምን ተጋለጠ ይመሥላል።
  ሌላው መንግስት በሀይማኖት አይገባም ትልና ጊዜ ሳትሰጥ ያልከውን በማፍረስ መንግስት በሀይማኖት እጁን አሥገብቷል ትላለህ። ወንድም መዘባረቁን ተወውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት ለአማኞቿ ተወት አድርገህ የራስህ የሆነ ተቋምህን ቢጠቅምህም ባይጠቅምህም ብትገልጥ የተሻለ ነው።
  የገረመኝ ደቡብ አፍሪካን ተንተርሰህ የተናገርከው ነው። ገነት አይደለችም እንጂ ገነት ልታደርጋት ምንም አልቀረህም። የእምነት ተቋማቷን በሞላ ፍፁምና የፍቅር ተቋማትና ሁሉንም የመንግስተሰማይ በሮች ናቸው ለማለት ያክል ነው ያወራኸው። አገሪቷንም ህዝቦቿንም የፍቅር መገኛ አደረግሃቸው። ግና ፓስተር ተብያቸው ተከታዮቹን ትናንት ሳር ያስጋጠና የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እውነተኛ ወንጌልና ፍቅር የሌላቸው መሆኑን ያሳየ መሆኑን ዘነጋኸው። አዎ ሌላም አለ፦ ትናንት በሥደት የተጠጉትን፤ ሰርቀው ሳይሆን በጉልበታቸው ሰርተው የበሉትን ጎራዴ ቆንጨራቸውን ሰብቀው፣ ጋዝ ክብሪታቸውን እያርከፈከፉ ለኩሰው፤ የመኪና ጎማ በአንገት አስገብተው ያቃጠሉ የክርስቶስ እውነተኛ ወንጌልና ፍቅር ሳይሆን የሐሰተኛው ክርስቶስ ትምህርትና ፍቅር እንደሆነ የተሞሉት ማሥመሥከራቸውን ለምን ደበቅህ። ነው ፕሮቴስታንታዊ እንቅስቃሴህ እንዳይገለጥብህ መደበቅህ ነውን? አይ የፍቅር አገር። ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ከሚሰራባቸው አገሮች አንዷ እኮ ደቡብ አፍሪካ ናት። ታዲያ የፕሮቴስታንቱ የፍቅር ውጤት ይህ ሆኖ ሳለ ወዴት ወዴት ነው የምትሮጠው።
  ማንዴላ ፕሮቴስታንት ነበሩ እያልክም ፕሮቴስታንትን እውነተኛ እምነት ለማድረግ ሞክረሃል። ለኔ ማንዴላ ምንም ይሁን ምን ቀና ያደረገው የፓለቲካ አመለካከቱ እንጂ ፕሮቴስታንት መሆኑ አይደለም። እምነቱንም ቢሆን በቅኝ ገዠዎቻቸውና በእርዳታ ሰጭዎቻቸው የተጫነባቸው ሸክም እንጂ የክርስቶስ ሐዋርያ የተሰበከላቸው አይደለም። አዎ ትናንት ኢራቄንና ሊቢያን መሠረተ ልማቶቿን ሳይቀር አመድ አድርገው አሁን ላለባቸው የሰላም መደፍረስ ምክንያቶቹ በእምነታቸው ፕሮቴስታንት የሆኑ የአደጉት አገሮች መሪዎች ናቸው። እና እራስህን አትሸንግል። ፕሮቴስታንት እርግማንና ስድብ ፤ብሎም በከንቱ መኮፈስና ሁከት እንጂ ፍቅር አይደለም።
  ዘባራቂ ምላሶችህ ብዙ ቢሆኑም በዚህ ላቁም። እኔ የተናገርኩት ከጽሑፍህ ተነስቸ እንጂ ለማንም ግለሰብ በመወገን አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ግን ዳሞት ነህ ጻረ ሞት? ትክክለኛ የጨለማ አገልጋይ ነህ

   Delete
  2. ፕሮቴስታንት ሠይጣን

   Delete
  3. ለanonymous july 9,2015 at 1:27pn
   በመጀመሪያ እኔ ዳሞት ነኝ። አንተ ደግሞ የፈለግኸውን ልትለኝ ትችላለህ። ይህን ካልኩኝ በኋላ ወደ ቀጣዩ ያላዋቂ ሳሚና የእንትናን ወደ እንትና ለሆነው ፍረጃህ ዛዝግም።
   ፍረጃህ ከድክመትህና ከስተትህ ላለመማር ይመስላል። አንድን አካል እንዲህ ነው ከማለትህ በፊት የቃሉ ሙላት በውስጥህ እንዲኖርና እውነትን ከውሸት እንድትለይ የእግዚአብሔር ቃል ተማር፤ ያልገባህንም ጠይቅ። አዎ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራልና የእግዚአብሔርን የማዳን አሰራር ስፋትና ጥልቀቱን እንድትረዳና እንድታስተውል የማንንም በይሁዳዊ አይምሮና በሰይጣን መንፈስ የሚፈበረክ አሉባልታና ከንቱ ትምህርት መራገቡን ትተህ ወንጌልንና ቅዱሳትመጽሐፍትን ተማር። ለትችትና ለፍረጃ ከመሮጥህ በፊት ያልገባህን ጠይቅ።
   የጨለማ አገልጋይ ማለት ያልሆነውን ሆንሁ የሚል፣ እውነትን በውሸት የሚለውጥ፣ ስለሚያምነው እምነቱ ሳይሆን የሚያወራው ስለ ሌሎች ቤተ እምነትና ስለእምነታቸው በውሸት የሚዘባርቅ፣ የእግዚአብሔር ወንጌል ሳይሆን አሉባልታና ክስ የሚያወራ የሚፅፍ፣ በአጠቃላይ ዲያቢሎስ የሚሔድበትን መንገድ የሚከተልና የሚተገብር ነው የጨለማ አገልጋይ።
   አንተ በአላማም፣ በአሥተሳሰብም እንዲሁም በእምነት በአቶ ኒቆዲሞስ ጋር ስለምትመሳሰል ይሆናል ወገንተኛ ሆነህ እኔላይ ሰይጣናዊ የሆነውን ፍረጃህን ያራመድከው። ነገር ግን አቶ ኒቆዲሞስ የፃፈውን መለስ ብለህ በማስተዋል አንብበው። በአንደኛው አንቀጽ የተናገረውን በሌላኛ አንቀጽ ያፈረሰ፣ በህገ መንግስቱ ሁሉ ሀይማኖቶች እኩነል ናቸው ማለትን ያላብራራ ወይም ያልገባው፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈፀመውን ግፍ ዘንግቶና ከአገሪቷ መሪ ጀምሮ በምድሪቱ ውስጥ ያሉ የእምነት ተቋማት ድረስ የተፈፀመውን ዘግናኝ አረመኒያዊ ድርጊት ለማውገዝና ለመቃወም ምን ያክል እንደዘገዩ ጀርባውን ሰጥቶ ደቡብ አፍሪካና ህዝቧ ፍቅር የተሞሉ ናቸው እያለ የዘላበደውን ታገኘዋለህ። እስቲ ልጠይቅ፦ ፍቅር ይቀናልን? ፍቅር ይጨክናልን/ ፍቅር ጥላቻን ያራምዳልን? ፍቅር በወንድሞች ላይ አመፃን ይቀሰቅሳልን? ፍቅር ችግረኛን ይገፋልን? ደቡብ አፍሪካና ህዝቧ እኮ ፍቅርን ሳይሆን ገጀራን፣ ጋዝን ከክብሪት ጋር፣ የመኪና ጎማን በሰው አንገት ለማድረግ ከማቃጣጠያው ጋር ጭካኔን ነው ያሳዩን። ማንዴላን ፕሮቴስታንት ነው በማለት የነበረው ስብዕና ከፕሮቴስታንትነቱ የተነሳ ነው በማለት በማይሆን መንገድ ለፕሮቴስታንት ጥብቅና ነው የቆመው አቶ ኒቆዲሞስ። በእርግጥ እምነቱ መሆኑ ግልፅ ነውና በሌላ መልኩ ለፕሮቴስታንት ቆሞ መሟገቱ የሚጠበቅ ነው። ለእኔ ግን ማንዴላ የነበረው መልካም አመለካከቱ ከነበረው የፓለቲካ አሥተሳሰብ የበነሳ እንጅ እምነቴ እንዲህ ይላል ብሎ በመናገር አይደለም። ደግሞ ትናንት ኢራቅንና ሊቢያን መሠረተ ልማቶቻቸውን ሳይቀር አመድ ያደረጓቸውና አሁን ላለባቸው የሰላም መደፍረስ ምክንያቶቹ በእምነታቸው ፕሮቴስታንት የሆኑት የበለፀጉት አገር መሪዎች መሆናቸው አትዘንጉ።
   ለሁሉም ዘለፋህም ሆነ ፍረጃህ ከንቱ ነውና ዝም ብለህ ለማንም ሐሰተኛ የፈጠራ ታሪክ ቲፎዞ መሆንህን ትተህ ዘወትር ቃሉን ተማር። ቃሉም ወደ መዳንና በእምነት መፅናት ያደርስሃልና ነው። ሰላም ሁን ወዳጄ።

   Delete
  4. ዳሞት
   ይኼን ድሪቶ አስተያትህን ገና ሳየዉ እንቅልፌ መጣ፡፡

   Delete
  5. ለanonymous july 9,2015 at 10:39pm
   እንቅልፍህ መጣ። ድሮም እንቅልፋም ነበርክ ማለት ነው። ለዚህም ነው ድሪቶውን ጋቢ አድርገኸው ተከናንበህ ለእውነት ተኝተህ በእንቅልፍ የምታንቋርረው። ስለዚህ በደንብ አንቀላፋ።

   Delete
 9. kikikikiki, qale mutanini eyesebeku kale hiwot metebeqi
  mirt ye ametu anegager biyewalehu

  ReplyDelete
 10. ይህ ሰውዬ መቸ ነው ሰባኪ የሆነው ? እኔም ከማን አንሳለሁ እንዴ ነው ጨዋታው

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ተኝተህ ነዋ። አንተ ለክርስቶስ ወንጌል ተኝተሃላ። አንተ እውነትን እንዳትሰማ ተኝተሃላ። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማትና ከመማር ተኝተሃላ። አንተ ላሉባልታ፣ ለክስ፣ ለዘለፋ፣ ለሐሰተኛ ወንጌል፣ ለከንቱ ተችነትና ለጥፋት ነዋ የነቃኸውና ለመሥማት ጆሮህን የሰጠኸው። ስለዚህ መቸ ወንጌል ሰባኪ እንደሆነ አላየህም አልሰማህም። ያንተ ነው የገረመኝ። አቶ ኒቆዲሞስሲዘላብድ አንተም ከማን አንሸ ይመሥላል የተኝተህ ያመለጠህን ለመተቸት ተንጠራራህ።
   ለanonymous july 8,2015 at 9:46pm

   Delete
  2. Sema leke ende mender arogit leneger yAlehe fiker yigermal aahun zemedkun sew hono new yemetekerakerelet.

   Delete
 11. በመጀመሪያ ከዘመድኩን ጽሑፍ የተረዳሁት የዘመድኩንን መምህርነት የሚያሰረዳኝ ወይንም እውነተኛ ክርስቲያን መሆኑን የሚያሳምነኝን ነገር ሳይሆን ክርስትና ያልገባው፣ ቅልብልብ፣ ቀውስ እና የደላላነት ባህርይ ያለው መሆኑን ነው፡፡ የማዝነው ግን ቤተ ክርስቲያን በስሟ የተጠለሉ ብልጣ ብልጦች ያልተገባ አውቅና ይዘው ሀብት ሲሰበስቡ እስከ መቼ ተመልካች ሆና ትቀጥላለች??? እኛ እኮ ሰብሳቢ አጣን ፡፡ እኔ ዘመድኩን እንዲህ መሆኑን ባውቅ እንዴት ጆሀንስበርግ ድረስ እመጣለሁ?? ብቻ በጣም ያሳዝናል!! በተለይ ስለአራት ኪሎ ሰባኪዎች እየተባለ የሚጻፈው አሳፋሪ ነው፡፡ እባካችሁ እኔ መ/ር ዳንኤል ግርማን በጣም አውቀዋለሁ አከብረዋለሁ እሱን ደግሞ ስሙን እንዲሁ አጥፉት አሉ፡፡ የዘመድኩን ነገር ግን በቃኝ እዚህም አየሁት አጭበርባሪ ነገር ነው፡፡

  ReplyDelete
 12. ዳሞት ወንጌል ምን ማለት እንደሆነ ከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብትማጣ ጥሩነበር ወንጌል የምትለው የተክለ ሃይማኖት ተቀማጥ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanobymous july 9,2015 at 10:18pm
   ለአውሬውም የስድብ አፍ ተሰጠው። እናም አንተስ የማን ልጅ ነህና ምን መልካም ነገር ካንተ ይጠበቃል። ከኩርንችት ወይን አይገኝ።

   Delete
 13. ዳሞት እውነቱን ተናገር ዘመድኩን የቤተ ከርስቲያን ትምህርት ተምሯል ?
  ገበቶ አይቀድስ መጽሐፍ ቅዱስ አይተረጉም ጅሉን ቀሚስ አለብሰውት እንጅ ዝም ብሎ ካሴቱን ይነግድ እርሱ የሚያውቀው እንደ አንተ ስድብ ነው መጽሐፍ ቅዱስን አንብቡ ምትድነው በኢየሱስ ስለ አመንህ እንጅ የአንድ ሃይማኖት አባል ስለሆንህ አይደለም
  የሐዋ 4:12 ተመለከተው አስብበት በሩ አንድ ነው አምሳ ወይም ብዙ በር የለም

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous july 9,2015 at 10:31pm
   በቃ ወንጌል ይህ በሐዋ•ሥራ 4:12 ብቻ ነው። ጥቅስ መጥቀስ፤ ቁጥር መደርደር እኮ በራሱ ህይወት አይደለም። ሰይጣንም ጥቅስ ሲጠቅስ፣ ቁጥርም ሲደረድርና የክርስቶስን ስም እንደሚጠራ ተጽፏል። ታዲያ ህይወት ፅድቅ አልሆነም። ምነው በእግዚአብሔር ቃል ባትቀልድና አንድና ሁለት ጥቅስ ሳትረዳው እየመዝክ በከንቱ ባታስካካ። ከማንብህ ቀድመህ ተማር። የምታነበውን እንድታስተውለውና የምታነበው ስለምን እንደሚናገር ይገባሀልና።

   Delete
 14. hi damot what is meaning of Gospel ? Read Romans 1:1-4
  zemedekun is not a preacher he is trader. If some body hate his brother, he is not a christian. Zemedekun hates his brothers and sisters. H e blames those who did not share the benefit/money.

  ReplyDelete
  Replies
  1. fot anonymous july 9,2015 at 10:41pm
   Brother, I am not standing for zemedeku. He can stand and defend defe himself. But my question according to the quote quo you mention Romans 1:1 to 14 is, which is a Gospel for you? Do you think Mr.Nikodemos wrote the Gospel. If you belive it, you can have, keep and live in it. But for me it is not. It is just trying to against someone someand to cgange the truth to the false ideology.

   Delete
 15. i am not side for any body but Gospel means is Jesus . Gospel is not st.mary or angels or saints.
  if some body preach about st.mary or angels or saints that is not Gospel that is story.So, Zemedekun never say about Jesus , he is not a preacher for Gospel.

  ReplyDelete
  Replies
  1. For anonymous july 10,2015 at 1:12pm
   I don't think you are telling tell the truth. You said you are not going for any one. But according to your gospel explanation and the justification on the Zemedeku, it is clear and known where you are and which side you are. So you are lying.
   Second,you are saying gospel is Jesus. You also said, if someone is preaching about St.Mary, Angels and Saints, that is story but not gospel. Both ideas you brouht are not right.
   One, Gospel is not just only about Jesus even if you are looking the meaning of gospel from the dictionary. Simply, gospel is the word of God.
   Second, in the word of God, we can learn about St.Mary, Angel, saints, rules and laws, Jesus, and so on.
   Then preaching about saints, St.Mary and angels is the word of God which are found in the Bible.
   You may be foolish a human being in your wrong idea and translation, but you
   can't foolish Jesus(God). Everything wrote in the Bible is his words.
   I do understand why you said gospel means Jesus. you are trying to seems a christian and believe Jesus, but not to be a true and right christian. But you are not believe Jesus is God. But you are not know wthat is the Bible is teaching and what message Jesus is sending to the people through the church and in the true faith.

   Delete
 16. ዳሞቴ መዳን በማንም በሌላ የለም ሐዋ 4፤12 የሚለውን እንዴት ታምነዋለህ ?
  ስድቡን ተወውና በህይውት ጉዳይ እንወያይ
  ዛሬ ጌታ ወደ እርሱ ቢጠራህ ምን ያህል ዋስትና አለህ ? የህይውት መድን (life insurance) አለህ ወይ ? አስብበት በዚህ ብሎግ ላይ የአንተ ና እኔ መሰዳደብ ጥቅም የለውም

  ReplyDelete
 17. ሃይ ባይ ያጣው የዘመድኩን አደገኛ አካሄድ
  October 19, 2011 at 9:09am  ዘመድኩን መምህር ቢባልም ከመመህርነቱ ይልቅ በነጋዴነቱ ይታወቃል፡፡ ትርፍንና ጥቅምን መሰረት አድርጎ የሚሰራ ሰው ነው ማለት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን አንድ ሃይማኖተኛ ነጋዴ በማጭበርበር ሊበለጽግ ሲሻ ትንሽ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡ በዚኅ ጽሁፍ ላይ መዘርዘር የማልፈልገው ነገር ግን አለማዊ ጋዜጦችና መጽሄቶች ሳይቀር የተቀባበሉት ብዙ ሰው የሚያወቀው ብዙ ቅሌቶች ያሉበት ሰው ነው፡፡ የቅርብ ሰዎቹ እንደሚያወቁት በበሽተኛ ዘማሪዎች ስም ሳይቀር መነገድ የሚፈልግ ገንዘብ አምላኪ ፍጥረት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ግለሰቡ ጥቅም የሚያገኝበት ከሆነ የማይፈነቅለው ድንጋይና የማይሰራው ሃጢያት እንደሌለ ነው፡፡ ለዛም ይመስላል ከበጋሻው ጋር ተጠግቶ መጠቀም ስላልቻለ በጋሻውን በክስ መእት የሚያጥለቀልቅ ቪሲዲ በመሸጥ የማይረካ የገንዘብ ጥሙን ለማርካት የሚታትረው፡፡ ስለ በጋሻው ተሃድሶነት ቪሲዲ በመሸጥ የገንዘብ ጥሙን ሲያረካ እሱን ከቤተክርስቲያን በማስባረርና ያለውን ዝና በማሳጣት የበቀል ጥሙን ያረካል፡፡ አሳሳቢውና አደገኛው ነገር ዘመድኩን በጋሻውን ከቤተክርስቲያን በማስባረር ብቻ ያለማቆሙ ነው፡፡

  ዘመድኩን የሚያመልከው ገንዘብን ነውና ልክ በጋሻው ተባሮ ስለሱ ቪሲዲ መስራት ምንም ትርፍ በማያመጣ ሰአት ሌላ ተጠቂ ሌላ የቢዝነስ ምንጭ ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ዘመድኩን እንደፈለገው በጋሻው ላይ ሲፈነጭ ዝም ያለ ሰባኪና ዘማሪ ሁሉ ስሙ ተሸጦ ብር የሚያመጣ ከሆነ ይነጣጠርበታል፡፡ ዘመድኩን ለበጋሻው ያስጎነጨውን ጽዋ እያንገሸገሸውም ቢሆን ይግተዋል፡፡ ከመዝሙርና ስብከት ካሴቱ እየተቆረጠና እየተቀጠለ ስም ይወጣለታል፡፡ እሱም እስኪባረር ለዜድ ገበያው ይደራል፡፡ የሚያሳዝነው ግን ዘመድኩን ሄዶ ሄዶ ዛሬ አብረውት አይዞህ አይዞህ የሚሉት ሰዎችም የሱ ስም ማጥፋት ዘመቻና የቪሲዲ ማሻሻጫ ከመሆን አለመዳናቸው ነው፡፡ ገንዘብን የሚከተል ሰው ወንድሙን ከመሸጥ ወደኋላ አይልምና ልክ ዛሬ በበጋሻው ላይ የከፈተውን አይነት ድንቅ ጦርነት ያካሂድባቸዋል፡፡ መጀመሪያ ስም ያወጣላቸወዋል፤ካሴት ይሰራባቸዋል፡፡ ነግዶ ያተርፍባቸዋል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ዛሬ በጋሻውን ላይ ያደረገውን ሁሉ እነሱም ላይ በተሻሻለና በረቀቀ ሁኔታ ይሰራባቸዋል፡፡

  ለምሳሌ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ካለው ዝና አንጻር ለዜድ ገበያ አመቺ ስለሆነ ግንባር ቀደም የጥቃቱ ሰላባ ሊሆኑ ከሚችሉ ሰዎች ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ዝም ብዬ ሳስበው ዜድ የሚያነሳው የመጀመሪያ ጥያቄ “ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የወንጌል መመህርና ተመራማሪ” የሚለውን ስም ማነው ለዳንኤል የሰጠው የሚል ነው፡፡ እሱ እኮ ስለ አለማዊ ፍቅር፤ እግር ኳስ፤ የቁንጅና ወድድር፤ ስለ ስለላ፤ ስለ ፖለቲካ የሚጽፍ ጋዜጠኛ ነው ይለዋል፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማስተማር የለበትም ይላል፡፡ ከዛም ማህበረ ቅዱሳንን “በቁሙ የሞተ ነው ብሎ ስንቶች መስዋትነት የከፈሉበት ማህበረ ሰደበ” ብሎ ከማሀበሩ ወዳጆቹ ጋር ሊያቆራርጠው ይሞከራል፡፡ ይቀጥልና ዳንኤል በብሎጉ ላይ ከሚጽፋቸው ነገሮች እየቆረጠ እየቀጠለ ፓትሪያርኩን ሰድቧል…መንግሰትን ነቅፏል…እስላሞችን እንዲህ ብሏል ወይም ከነሱ ጋር ተሞዳሙዳል..ብሎ ሊከሰው ከዛም አልፎ ወደ ቤተክርሰቲያን ደጃፍ ድርሽ ማለት የለበትም ድርሽ ካለ በድንጋይ ውገሩት ብሎ ሊያሳድምበት ይችላል፡፡ ከዳንኤል ሰብከቶችም ቆርጦ ቀጥሎ ደስ ያለውን ስም ይሰጠዋል፡፡ ቪሰዲ ይሰራበታል…አርማጌዶን ይለዋል…ከቁጥር 10 እስክ 20…፡፡ ቪሲዲው እንደጉድ ይቸበቸባል…ከዛ ለዜድ ገበያው ይደራል…በገንዘብ ይንበሸበሻል..፡፡

  ከዛ ሁሉም በተራው ይቀጥላል፡፡ ለሁሉም ይደርሰዋል…ጳጳሳቱም፤ መነኮሳቱም፤ ካህናቱም….

  በመጨረሻም እንዲህ አንዲህ እያለ ሁሉን ካባረረ በኋላ ዘመድኩን ብቻውን ሲቀር ታቦታቱንና ንዋየቅድሳቱን እያዞረ “ ድሮ በዚህን ያህል ብር የነበረውን አሁን በዚህን ያህል ብር ብቻ” እያለ በየመንገዱ ቸርችሮ ይሸጥና ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን ይሰበሰባል፡፡ ይህ ነው ገንዘብ አምላኪ የሆነ ሰው ህልምና ሩጫ፡፡ ይሁንና ይህ ነገር ቤተክርስቲያንንና ህዝቡን የሚጠብቅ ጌታ እያለ ፈጽሞ አይሆንም፡፡ የግለሰቡ ህልም ግን ከዚህ የሚዘል አይደለም፡፡ በመሆኑም የዘመድኩንን አደገኛ አካሄድ ካሁኑ ሃይ ካልተባለ በኋላ ላይ የሚያደርሰው ችግር ቀላላ አይሆንም፡፡ ከገንዘብ አምላኪነት በንስሃ ወደ እግዚአብሄር አምላኪነት እንዲመለስ በቅርቡ ያሉ ሰዎች ሊረዱት ይገባል፡፡ ግብር አበሮቹም ነግ በኔ ብለው ለክፍ ሰራው ከመተባበር እንዲቆጠቡ እንዲሁም ቤተክርስቲያንም በማይመለከተው ገብቶ ሲፈተፍት እና በአደገኛ አካሄድ ውስጥ ተጠምዶ ሲባዝን ተው ልትለው ይገባል፡፡

  ፍቅር ነኝ ከዮሴፍ

  ReplyDelete
 18. ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው (መጋቤ ሃዲሰ) በጋሻው ደሳለኝ ላይ የተለያዩ ክሶች ተነስተዋል፡፡ ከከሳሾቹ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ደሞ (መምህር) ዘመድኩን በቀለ በፊት አውራሪነት ከሚገኙ አካላት አንዱ ነው፡፡ ለዚህም ምስክሮቹ ያሳተማቸው በበጋሻው ላይ ብቻ ያተኮሩ ቪሲዲዎች፤ በየጋዜጣውና መጽሄቱ የሰጣቸው ግለሰቡ ላይ ያተኮሩ ቃለ መጠይቆች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ግለሰቦችበፊት የነበራቸው ፍቅር ተለውጦ ለምን እንዲህ አይንና ናጫ ሆኑ ለምንስ በነብስ መፈላለግ ውስጥ ገቡ የሚለው ነገር ራሱን የቻለ ታሪክና ሚስጥር ይኖረዋል፡፡ ብዙዎች የዋሃን ግን ዘመድኩንን እንደ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪና ሃይማኖተኛ ሰው በጋሻውን እንደ በደለኛና ቤተክርስቲያን አፍራሽ አድርገው ቆጥረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በንጹህ ልብ ላጤነው ዘመድኩን የሚሰራቸው ቪሲዲዎች፤ የሚሰጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ቃለመጠይቆች የሱን ትክክለኛ ማንነት ለአለም የገለጡ ናቸው፡፡ በበጋሻው ላይ የሚያደርጋቸው ዘመቻዎች የሚያሳዩት ግለሰቡ ምንም አይነት የሃይማኖት ሰው ሳይሆን በሆነ ሃይልና ፍላጎት እየተነዳ ለበቀልና ለጥፋት የተዘጋጀ መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ዘመድኩን እውነተኛ ክርስቲያን ቢሆን በጋሻው በተሳሳተ መንገድ ቢሄድ እንኳን በወንድማዊ ፍቅርና በአባቶች ተግሳጽ እንዲመለስ ጥረት ማድረግ ነበር የሚጠበቅበት፡፡ እሱ ግን ጭራሽ ልጁን ከመንግሰት፤ ከሌላ ሃይማኖት ሰዎችና ከግለሰቦች ጋር ለማጋጨት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ሳያንስ ወደቤተክርስቲያን እንዳይመለስና በዛው ጠፍቶ እንዲቀር የተቀናጀ ጦርነት ነገሩ ባልገባቸው ሰዎች ጋሻ ጃግሬነት አውጆበታል፡፡ በዛ ላይ የቃላትና የአፍ ወለምታ ሰብሰቦና ሰካክቶ ያላሰበውን አለ ለማለት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ ሲጀመር ሰይጣን አይደለም ከሃጢያተኛውና እልፍ ስህተት ሊሰራ ከሚችለው ከበጋሻው አፍ አይደለም ከንጹሃ ባህሪ ከኢየሱስ ክርስቶስም ከሚናገረው ስህተት እየለቀመ ሲከሰው ስለነበረ የዘመድኩን ስራ ከግብር አባቱ ከሰይጣን የተማረው መሆኑን ይመሰክራል፡፡ይህ ደሞ በምንም ሚዛን ቢለካ የዘመድኩን ክርስቲያንነትን አያሳይም፡፡  በጋሻው እየቀረበበት ያለው ክስ ተሀድሶ ነው የሚል ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃዎች በተለያዩ አካላት ለሲኖዶስ መቅረባቸውን ሰምተናል፡፡ በጋሻውም በሃጢያት እንጂ በእምነቱ ምንም አይነት ቁስል ጀርባው ላይ እንደሌለ በተደጋጋሚ ገልጽዋል፡፡በጥቅምቱ ጉባኤ አባቶች ያለውን መረጃ መርምረው የማያወላዳ ውሳኔ ያሳልፋሉ፡፡ የቀረበውን መረጃ መርምረው አይተው ይፈርዳሉ፡፡ በጋሻውን ወይ ንጹህ ይሉታል፤ ወይ ንስሃ ይሰጡታል፤ እምቢ ካለም ያወግዙታል፡፡ አለቀ፡፡ ከዛ በኃላ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ያባቶችን ውሳኔ ተቀብሎ ይቀጥላል፡፡ እኛ የዮሴፍ አካባቢ ልጆች በጋሻውን ቀርበን ስላየነው ንጽህናውን ብናውቅም ያባቶችን ውሳኔ ያለጥርጥር እንቀበላለን፡፡ ምክንያቱም እኛ ካባቶቻችን አንበልጥምና፡፡ ከዛ በኋላ የበጋሻው ታሪክ ይዘጋል ማለት ነው፡፡ የዘመድኩን ታሪክ ግን እንዲሁ በዋዛ የሚያበቃ አይመስልም፡፡

  ከግለሰቡ አደገኛ አካሄድ በመነሳት ዘመድኩን በጋሻው ተወግዞ ካላየ የከፈተውን ጦርነት ያቆማል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው፡፡ አባቶች በጋሻውን ንጹህ ነው ካሉት ሲኖዶሱንም ተሃድሶ ነው ይላል፡፡ ስህተቱን አምኖ ተቀብሎ ንስሃ ቢሰጡትም ለዘመድኩን አይዋጥለትም፡፡ “አይታመንም አድፍጦ ጊዜ ሊጠብቅ ነው” ይላል፡፡ ስለዚህ ዘመድኩንን የሚያስደስተው በጋሻው ተወግዞ ሲለይ ብቻ ነው፡፡ ይህን ፍላጎቱንም በቅርቡ በበጋሻው ላይ ባቀረበው ቪሲዲ “ እኔን ብትጠይቁኝ ልጁ ፈጽሞ አይመለስም” ብሎ ገልጾታል፡፡ ግን አለማፈሩ! የሃይማኖት መምህር ተብሎ ስንት የሚሰበክበት ርዕስ እያለ በገዛ ወንድሙ ላይ የክስ መአት ደርድሮ ነጠላውን አጣፍቶና ካሜራ ላይ ፍጥጥ ብሎ የጥፋት መልክት አባዝቶ ሲቸበችብ ትንሽም የማይሰቀጥጠው ውስጡ ምን አይነት መንፈስ ቢኖር ነው ? እኔን የሚደንቀኝ እስካሁን አንድም የዘመድኩንን ስብከት ሳላዳምጥ በበጋሻው ላይ የሰራውን ካሴት ማየቴ ነው…ግን የስብከት ካሴትስ ሰርቶ ያውቅ ይሆን…እኔ መረጃው የለኝም፡፡ በስብከቱ መታወቅ ቢያቅተው በጋሻውን በመሳደብ ታዋቂ ሆነ፡፡ እረ በጣም ያሳፍራል…ያስነውራል፡፡ ከላይ እንደገለጽኩት በቪሲዲ ካሴቱ ላይ የሚያነሳቸው ነገሮች ሁሉ እንደ አንድ ክርስቲያን ልጁን ለመመለስ ሳይሆን ከቤተክርስቲያን ገፍቶ ለማስወጣትና ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት እንጂ ለማስተማርና ለመመለስ እንዳልሆነ በንጹህ ክርስቲያናዊ ህሊና ለመረመረው ስው በግልጽ የሚታይ ነገር ነው፡፡

  ዘመድኩን የሚናገራቸውና የሚሰራቸውን ነገሮች ቅንጣት ታህል ክርስትና እና መንፈሳዊነት የሌለው መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የሚያሳየው መራርነት፤ እልህ፤ ጥላቻ ሁለቱ በአንድ ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት ውስጥ የነበሩ ሊያውም በቅርብ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ሳይሆኑ በደም የሚፈላለጉ አለማዊ ባላንጣዎች ያስመስላቸዋል፡፡ የዘመድኩን ቅንጣት ታህል የሃይማኖት ምልክት የሌለው ባህሪ የዚህ ሁሉ ጥላቻና ዘመቻ መሰረቱ ሃይማኖት አለመሆኑን ያሳያል፡፡ ታዲያ ሁለቱን ሰዎች እንዲህ ያባላቸው ዘመድኩንንስ እንዲህ መራራ፤ በቀለኛና እልኸኛ ያደረገው ምንድነው ብንል ጥቅም ነው፡፡

  ReplyDelete
 19. https://www.facebook.com/notes/fikir-yibeltal/%E1%88%83%E1%8B%AD-%E1%89%A3%E1%8B%AD-%E1%8B%AB%E1%8C%A3%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%8A%A9%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%8C%88%E1%8A%9B-%E1%8A%A0%E1%8A%AB%E1%88%84%E1%8B%B5/102644879847719

  ReplyDelete
 20. ምድረ መናፍቃን በመጀመሪያ ይሔንን ገጽ አይቼው አላውቅም ለምን የመናፍቃን የከሀዲ ስለሆነ መቼም ከናንተ አፍ ቅርሻት ብቻ ሳይሆን ትውከትም ጭምር ነው የሚወጣው ልክ ነው መቼም ዲን ዘመድኩን መቆሚያ መቀመጫ አሳጣችሁ አይደል ምን ታደርጉ ተንጫጬ እርሱም አይለቃችሁ ገና አዳሚ ጉድሽ ይወጣል የናት ጡት ነካሾች

  ReplyDelete
 21. hulachihum ewuroch nachihu.zemedkun malet ye orthodox tewahido yekirt ken lij nw. bizu bitaworu man yisemachihual.....

  ReplyDelete