Thursday, July 9, 2015

የምናመሰግናችሁ ብቻ ሳይሆን የምንነቅፍባችሁም ነገር አለ“ንብላዕ ወንስተይ ጌሠመ ንመውት ኢያስሕቱክሙ አኀዊነ እስመ ነገር አኩይ ግዕዘ ሠናየ ያማስን”
“ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። አትሳት ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋልና” 1ቆሮ. 15፡33

ይድረስ ለሊቀ ማዕምራን የማነና ለመጋቤ ብሉይ አእመረ በቅድሚያ ለእናንተ ያለንን አክብሮትና አድናቆት መግለጽ እንወዳለን፡፡ በአንድ ወቅት አዞ እና ጦጣ ጓደኝነት ገጠሙ፡፡ ሁለቱም መኖሪያቸውና ምግባቸው ለየቅል ሲሆን አዞ በውሃ የሚኖርና ሥጋ በል የሆነ እንስሳ ነው፡፡ ጦጣ ደግሞ በዛፍ ላይ ነግሣ የምትኖር ፍራፍሬዎችን ሸምጥጣ የምትበላ ወጥታ ወርዳ ዘላና ቦርቃ ከአንዱ ዛፍ ጫፍ ወደ አንደኛው ዛፍ እየተወረወረች የምትመገብ እንስሳ ነች፡፡ አዞ ውሃ ውስጥ የገባውን ሁሉ ከሰው እስከ አንበሳ አድፍጦ በማጥቃት ምህረት የለሽ በሆነ ባህርዩ ይታወቃል፡፡ አዞ የክፉ ሰዎች ምሳሌ በመሆንም ይታወቃል፡፡ እሱ በሚኖርበት አካባቢ ያለ ምህረት በጭካኔ ስለሚያጠቃ እሱም የብስ ላይ ወጥቶ ለመቀመጥ ለመዝናናት ከ1-2 ደቂቃ በላይ መቀመጥ አይሆንለትም፡፡ ኮሽታ በሰማ ቁጥር ይደነግጣል ዘሎ ውሃ ውስጥ ይገባል፡፡ ባጠቃላይ ሰላም የለውም፡፡ ክፉ ሰዎች ነፍሰ ገዳዮችም ተረጋግተው አይኖሩም፣ ይጨነቃሉ ሰላም የላቸውም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ለክፉዎች ሰላም የላቸውም እንደ ተባሉ (ኢሳ. 57፥21) ማለት ነው፡፡ 

ወደ አዞና ጦጣ ጉዳይ እንመለስና አዞ ከመኖሪያ ቤቱ እየወጣ ፀሐይ ለመሞቅ ጦጣ ካለችበት ዛፍ ሥር ይተኛል፡፡ መቼም ክፉዎች ለአላማቸው ሲሉ የማይሆኑት ነገር የለምና አዞ ሆዬ ጦጢትን ለመብላት ፈለገ፡፡ ነገር ግን እሷ ያለችው ሰማይ እሱ ያለው መሬት ላይ ሆነና እስዋን የመብላት ህልሙ እውን የማይሆንለት ሆነ፡፡ ከዚያ አንድ ሃሳብ መጣለት ጦጢትን የሚያጠምድበት ዘዴ ዘየደ፡፡
“ጦጢት ሆይ” አለ፡፡
በጥሩ ቃልና ቅላፄ “አቤት” አለች፡፡
“እንደ ምንድነሽ?” አላት ሰላምታ ጀመረና ተግባቡ፡፡ ከዛ “እኔ ምልሽ ለምንድነው እኔ አንቺ ሰፈር እየመጣሁ ስጎበኝ አንቺ ግን የእኔን ሰፈር የማታይልኝ?” አላት፡፡ ይባስ ብሎ የአዞ መኖሪያ ጥሩ እንደሆነ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ኑሮ ጥሩ አይደለም ብሎ የእስዋን ኑሮ አንቋሸሸባትና አናናቀባት፡፡ ከአሁን በፊት ጓደኛው እባብ እናታችን ሄዋንን የያዘችውን አናንቆ ክብርዋን እንዳስጣላት ጦጢትም ከነበራት የኑሮ ከፍታ ክብር የሱ መኖሪያ በጣም ጥሩ እንደሆነ ሲገልፅላት ከላይ ታች ጉድጓድ ውስጥ ይሻላል ብላ በሱ ሃሳብ ተጠልፋ ወረደች ተስማማች፡፡
“ነገር ግን እኔ ወዳንተ መኖሪያ መሄድ አልችልም ምክንያቱም እኔ መዋኘት አልችልም” አለችው፡፡
“ለሱ አታስቢ እኔ አዝልሻለሁ” አላት
“ካዘልከኝማ ጥሩ” ብላ የዋሁዋ ጦጢት በክፉው አዞ ተታልላ ታዘለችና ዋና ተጀመረ፡፡ ሰዋኙ ሲዋኙ በከንቱ ውዳሴ እያሞካሸ ስለ ውበቷና ስለ ፀጉርዋ ልስላሴ ሲነግራት “አመሰግናለሁ” አለች፡፡
አሁን ወደ ጥልቁ መግባት ሲጀምሩ ከእጁ ማምለጥ እንደማይቻል ሲያውቅ “አሁን እኔ ካንቺ የምፈልገው ልብሽን ነው” አላት እና ሊበላት እንደሆነ አሁን ገና ገባት፡፡ ብልሃት መቼም ከሞትም ቢሆን ያስመልጣል እና አንድ ሃሳብ መጣላት፣ ወደ ልብዋ ተመለሰች፣ “እንዴ ለምን አልነገርከኝም?” አለችው፡፡
“ምኑን?” አላት፣
“ልቤን እንደምትፈልግ እንዴት ቅድም አልነገርከኝም? ልቤን እኮ እዚያው እዛፉ ላይ አስቀምጨው ነው የመጣሁት!” አለችው፡፡
“ታዲያ ምን ይሻላል?” አላት
“አንድ አፍታ መልሰኝና ላምጣልህ” አለችው፡፡
“እሺ” ብሎ ተሸክሞ ወደ ዳር አወጣት፣
“እዚህ ስፍራ ላይ ጠብቀኝ” ብላ ዛፍ ላይ ከወጣች በኋላ ልብ ሊበላ የጐመጀው አዞ “ልብሽን ይዘሽ ነይ እንጂ ውረጂ” ሲላት፣
ከስህተትዋ ተምራ ወደ ልብዋ በመመለስዋ “አግኝቸዋለሁና ተወው ተመለስ” አለችው፡፡ ታዲያ የአዞና የጦጢት ጓደኝነት እንዴት ወደሌላ አቅጣጫ እንደሄደ እንይ፣ ምንም እንኳን ጦጢት በብልጠትዋና በብልሃትዋ ከሞት ብታመልጥም ሁልጊዜ ወደ ጥልቁና ወደ አደገኛ ቦታ ከሄድን በኋላ ሁልጊዜ እናመልጣለን ማለት አይደለም መቅረትም አለና፣ መስመጥም አለና፡፡

አንደኛው ቡድን ሲያሸንፍ ሌላው ቡድን ጉድጓድም ሆነ መቀመቅ ከገባ በኋላም ቢሆን እንደ ጦጢት ወደልቡ ተመልሶ በጥበብ ተፍጨርጭሮ መውጣት መልካም ቢሆንም፣ በመጀመሪያ ጓደኝነት ባልጀርነት መፍጠር ያለበት ከማንና እንዴት መፍጠር እንዳለበት መታሰብና መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የአዞና የጦጢት ጓደኝነት ጉዳይ ያነሳነው ልናስተላልፈው የፈለግነው መልእክት ስላለ ነው፡፡ በመጽሐፍም ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋልና እንደተባለው ክፉ ባልንጀርነት የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስታወስ ነው፡፡ ትናንትና ሊቀ ማዕምራን የማነና መጋቤ ብሉይ አእመረን እንደ ዓይን ብሌን ልናያቸው ይገባል፣ የተማሩና መልካም ራዕይና ጥሩ የምሥራች ለቤተ ክርስቲያን ይዘው የመጡ ስለሆነ እጅግ ደስ ብሎን አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ብለናቸዋል፣ አሁንም እንላቸዋልን፡፡ ነገር ግን እድል ይሁን ወይም እርግማን የማይገባን አንድ ነገር አለ፡፡ እሱም ሰዎች ወጡ ወጡ ሲባል ባለ ራዕዮችን የሚያጨናግፍ፣ የባለ ራዕዮች ዓላማ ግቡን ሳይመታም የሚያመክን ጠላት አለ፡፡ ስለሆነም ያ የተለመደው የጠላት አሠራር አሁንም በጎውን ጅምር እንዳይቀማን ስለ ሠጋን ሥጋታችንን ለመግለፅ ነው የተነሣ ነው፡፡ ሰዎች የሚመሰገኑበት ነገር እንዳለ ሁሉ የሚነቀፉበት ነገርም አይጠፋም፣ ያንን ማንሳት የሚያስፈልገው ጥቂቱ ደካማ ነገር ብዙውን መልካም ነገር እነዳያበላሽ በመስጋት ነው፡፡  

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሊቀ ማዕምራን የማነ እና በመጋቤ ብሉይ አእመረ ዙሪያ የሚዞሩ ሁለት አደገኞች ሰዎች አሉ፡፡ እነሱም አባ ወልደ ኢየሱስ (አባ ህፃን) እና ዲያቆን ፍሬው የተባሉ አደገኞች ናቸው፡፡ የእነዚህን ሰዎች ማንነት መግለፅ አስፈላጊ የሆነው የሥራ አስኪያጆቻችንን በጎ ጅምር ከመጠበቅና ራሳቸውን ከክፉዎች እንዲጠብቁ ከመቆርቆር የመነጨ ነው፡፡ በቅርቡ በዋና ሥራ አስኪያጁ ዘንድ ዋና አጋፋሪ ሆኖ ብቅ ያለው አባ ህፃን በአጭበርባሪነቱ በጣም የታወቀ፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኖ ሲሾም የቤተ ክርስቲያንን ሃብትና መሬት በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጥ ሁልጊዜ ሲታሰርና ሲፈታ የኖረ፣ አባ ተብሎ በሴቶች ነውር ሲከሰስ የኖረ፣ ሴቶችን አታሎ መኪናቸውን በመቀማት የተዋረደ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ “ለምንድነው ሁልጊዜ የምትታሰረው?” ተብሎ ሲጠየቅ ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ በመቀየር “ኦሮሞ ስለሆንኩኝ ነው” እያለ ውንብድናውን ወደፖለቲካ በመለወጥ አመፅ ባህርዩ የሆነ ግለሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በብፁዕ ወቅዱስ አባ ጳውሎስና በአባ ሳሙኤል መካከል የነበረውን አለመግባባት ተጥቅሞ የአለመግባባቱ ዋና አቀጣጣይ በመሆንና የሰይጣን ተልእኮ በመያዝ ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል፡፡ እንደ አውሮፓ ክለቦች ኳስ ተጫዋች አንድ ሰሞን ለአቡነ ጳውሎስ አንድ ሰሞን ደግሞ ለአቡነ ሳሙኤል እየተዘዋዋረ ሲጫወት ነበር፡፡ ምን ያህል እንደተከፈለው ባይታወቅም፣ መጫወቱ ግን በነ ሪፖርተር ጋዜጣ ጭምር ይታወቃል፡፡ ይሄን ያህል ከተበላሸ የሕይወት ታሪኩ በጣም ጥቂቱ ካየን ለሊቀ ማዕምራን የማነ የምናስተላልፈው መልእክት ምንም እንኳን እንደ ብልሁዋ ጦጢት በእንደነዚህ ዓይነት አዞዎች ጭልጥ ብለው ይሄዳሉ ባንልም ስጋታችን ግን እንደእነዚህ ዓይነት ሰበድእት የሆኑ ሰዎች አብዝቶ መጠንቀቁ ይበጃል እንላለን፡፡

በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስተት መለስ ዜናዊ አንድ ነገር ተናገሩ፡፡ አንዳንድ ሰዎች መንግሥት ለዜጎች አደገኛ ካላቸው አሸባሪ ሰዎች ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ግንኙነት ይፈጥራሉ፡፡ መንግሥትም ጉዳዩን ይደርስበትና ከእንደነዚህ ዓይነት አሸባሪዎች ጋር አትገናኙ አላለም ወይ? ብሎ ያስራቸዋል፡፡ ከዚያ ጉዳዩ ፓርላማ ላይ ቀረበ፡፡ አንድ ተከራካሪ እንዲህ ማለት መብት መንፈግ ነው፣ እንዴት በስልክ አታውሩ ይባላል? ብለው ጠየቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲመልሱ “ግንኙነቱና ስልኩ ምን ነበረ? ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር የሚነጋገሩት ስለ አየሩ ፀባይ ነው ወይስ ስለ ሃገር ደህንነት?” ብለው ፓርላማውን ፈገግ አድርገዉት ነበር፡፡ አሁንም ከነ አባ ህፃን ጋር መዋልና መታየት ምክንያቱ ምን ይሆን? ስለ ብሉይና ስለ አዲስ ለመጠየቅና ለመነጋገር ነው? ወይስ በነሊቀ ማዕምራን የማነ ራዕይና ዓላማ ለመደገፍ? እንዲህ ለማድረግ ሞራሉም አቅሙም የላቸውም፣ ይልቁንም አብረው በመውጣታቸውና በመዋላቸው አየህ አብረን በላን ጠጣን እያሉ ስንት መነኮሳትና ሠራተኞችን ደጅ እያስጠኑ እንደሆነ ቢያውቁ፣ ከበስተጀርባቸው እየተሠራ ያለውን ሥራ ቢያውቁ ምን ይሉ ነበር? በጣም የሚያሳዝነውና የሚገርመው በሃገረ ስብከቱ ስንት ሊቃውንት ጉዳይ ለማስፈጸም ወረፋ ይዘው በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ምንም እንኳን አባ ህፃንም እንደማንኛውም ዜጋ ተራቸውን ጠብቀው የመግባት መብት ቢኖራቸውም ከጥበቃ ጀምሮ የሥራ አስኪያጅ ያህል ክብር አግኝተው መጡ መጡ እየተባለ የሚሰጣቸውን ክብር ለተመለከተው እጅግ ያሳፍራል፣ ያስቆጫል፡፡ ሌላው ነገር እንደ አባ ህፃን የመሳሰሉ ይህን ያህል ውንብድና ቢሰሩም ከእነማቅ ወገን እስከ አሁን ድረስ ምንም አለመባሉ ምን ያህል አባልነትና ተልእኮ ቢኖራቸው ይሆን? ብሎ መጠርጠሩ መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ከማቅ ባሕሪ አንፃር “የእነ እንትና” ወገን ቢሆን ኑሮ ይሰቀል ይወገዝ ይባል ነበር፡፡ ለማንኛውም እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች ከቀድሞ ባህሪያቸው በመነሳት ሌላ ቡድን ቢገዛቸው ሕይወት ለማጥፋት ወደ ኋላ ስለማይሉ ይታሰብበት እንላለን፡፡

ሌላው ዲ/ን ፍሬው የተበላ በጎፋ ገብርኤል ያደገው ወንበዴውና ሽፍታው በጎፋ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ4ዐ-5ዐ ዓመታት ያገለገሉ አባቶችን ለብዙ ዓመታት ያካበቱትን ሃብትና ንብረት በሜርኩሪ ሽያጭ እና ከአደገኛ ቦዘኔዎች ጋር በመመሳጠር የስንት አባቶችን ገንዘብ የዘረፈና ያታለለ ወመኔ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አንዳንቹም በብስጭትና በድንጋጤ እንዲሞቱ ያደረገ ሰው መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡ ይባስ ብሎም በየአድባራቱ እየዞረ አዲስ ህንፃ ባለበት ቤተክርስቲያን በዚያ የአስተዳዳሪዎችን ፈረጅያ ልብስና መስቀል እየለበሰ የቤተክርስቲያን ሃብትና ንብረት ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ እየተያዘ ከሦስት ጊዜ በላይ እተፈረደበት የታሰረ፣ የስንት ምእመናንን ልብ ያቆሰለ፣ ራዕያቸውን ያጨናገፈ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፈ፣ አሁን አሁንማ አስር ቤቱን እንደ ቤቱ ስለቆጠረው መግቢያ መውጫውን ስላወቀውና ስለ ለመደው ከፊል ኑሮውን በየጊዜው እስር ቤት ስለሚያሳልፍ ሽልማት የሚያሰጥ ቢሆን ኖሮ ማንም አይቀድመውም ነበር ይላሉ ጓደኞቹ፡፡ ስለዚህ መጋቤ ብሉይ አእመረ ከእንዲህ ዓይነት ሕገወጥ ከሆነ ሰው ከዲ/ን ፍሬው ጋር ብዙ ጊዜ ሲያሳልፉ ስለሚታዩ ብዙ ሰዎች እየተሰናከሉና ከባድ የሆነ ስጋት እያደረባቸው ነው፡፡  

በተጨማሪም መጋቤ ብሉይ አእመረ አንድ የሚታሙበት ጉዳይ አለ፡፡ በዕውቀታቸውና በስነ ምግባራቸው ጥሩ የሚባሉ ሰው ናቸው ቢባሉም ነገር ግን ከእሳቸው ሥነምግባር ጋር ዐብሮ የማይሄድ አንድ ጉድለት አለባቸው፡፡ እርሱም ሻይ ለመጠጣት እንኳ ከተለመዱ ሰዎች ጋር ካልሆነ ከሌላ ሰው ጋር አይታዩም፡፡ ይህ ደግሞ እንደእርሳቸው ለተማረና ሁለገብ ለሆነ ሊቅ አይመጥንምና ቢስተካከል ጥሩ ነው፡፡ በእርግጥ ከላይ የጠቀስነውን ዲ/ን ፍሬውንና የመሳሰሉትን ወንጀለኞችን ከማግለል ይልቅ በትምህርትና በአመለካከት የማብቃት ሃሳብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ዲ/ን ፍሬው “ለእመ ይደቁ የሐድስዋ ካዕበ ለንስሐሆሙ፡፡ ወይሰቅልዎ ሎሙ ለወልደ እግዚአብሔር ወይሜንንዎ” (ዕብ.6፥7) ከተባሉት ዓይነት ሰዎች አንዱ ስለሆነ በህሊናም በህግም ሊማርና ሊጸጸት ያልቻለ ሰው ነውና ለራሳቸውም ለሕይወታቸውም አደጋ ስለሆነ ቢጠነቀቁ መልካም ነው እንላለን፡፡

በአጠቃላይ ለሊቀ ማእምራን የማነም ሆነ ለመጋቤ ብሉይ አእመረ የምናስተላለፍው መልእክት በአባ ሕጻንና በዲ/ን ፍሬው ዓይነት ወሮበሎች ተከበው መታየታቸው ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነውና የሚያስቆጨው የያዙትን ፕላንም ሆነ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እናሳካለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ በእጅጉ ተስፋችንን እንዳያጨልሙት ከባድ የሆነ ስጋት አድሮብናል፡፡ እነዚህ ሰዎች እኮ የአህያ አይን ያላቸው በርቀት የማያዩ ትራኮማዎች ናቸው፡፡ “በጥቅምትና በግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ስለምትወርዱ ዛሬ ብቻ ተጠቀሙ፣ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” እንደሚሏቸው ጥርጥር የለውም፡፡ እኛ ደግሞ ምኞታችንና ፍላጎታችን፦
1.      የጀመሩትን ዕቅድና ፕላን ሳያሳኩ ጠላት ዲያብሎስ ክፉዎችን ተጠቅሞ እንዳያበላሽባቸው በጸሎት በምክር ማገዝ
2.     ጥቅምትና ግንቦት በመጡ ቁጥር መስጋት ሳይሆን በየዓመቱ የመጡት ለውጦች እየታዩና እየተመዘኑ መልካም የሠሩና ተጨባጭ ለውጥ ያመጡትን ለሽልማት ማብቃት
3.     ተጠያቂነትና ግልጽነት አስፍነው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩልና ተጠያቂነት ከላይ እስከታች እንዲያሰፍኑ በአመለካከት መርዳት
4.     ቤተ ክርስቲያናችን ሌላ ባዕድ መጥቶ እንደ ፈለገ የሚፈነጭባት ሳትሆን በራስዋና በራስዋ ልጆች ብቻ የምትተዳደርና በዙሪያዋ የሚያነፈንፉ ውሾች እንዳይገቡና እንዳይወርሷት ጥሩ የሆነ ሰንሰለት ወይም ንቁ ጠባቂ የሆነ ሰራተኛ መፍጠር እንዲችሉ ሁል ጊዜ በምክርና በሐሳብ ከጎናቸው መሰለፍ ነው፡፡

በመጨረሻ ማንሳት የምንፈልገው ሥራ አስኪያጆቹ ሰሞኑን ስለሰጡት ፍትሕ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተዛውረው ከመጡ በኋላ በመሰሪውና በሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸው ብዙ ሰዎችን በበቀል ከሥራ በማፈናቀል አቻ ያልተገኘላቸው ዘረኛው የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስ የዓይንህ ቀለም አላማረኝም ዓይነት ሰበብ በመፈለግ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ወደሀገረ ስብከታቸው ዳውሮ ላዛወሯቸውና ከአንድ ዓመት በላይ ያለስራና ደመወዝ ለተበቀሏቸው መነኩሴ ሥራ በመስጠት ፍትህ ያለበትን ሥራ ስለሠራችሁ ልትመሰገኑ ይገባል እንላለን፡፡ አባ ማቴዎስ እኚህን መነኩሴ ወደ ዳውሮ ካዛወሩ በኋላ ሀገረ ስብከታቸው እንዳይቀበላቸው በማድረግ በሸረቡት ሴራ መነኩሴው የሚበሉት አጥተው በችጋር አለንጋ ሲገረፉ ነው የከረሙት፡፡ ለብዙ ዓመታት ካገለገልኳት ቤተ ክርስቲያን ወጥቼ ልስለም ወይ? ወይስ ወደሌላ የሃይማኖት ድርጅት ልሂድ ወይ እስኪሉ ድረስ በብዙ ተንገላተዋል፡፡ መብታቸውን በህግ ለማስከበር ክስ መስርተው አባ ማቴዎስን የረቱና የተፈረደላቸው ቢሆንም፣ መሰሪው አባ ማቴዎስ ግን ፓትርያርኩን በማሳሳት እስከ ሰበር ችሎት የደረሰውን ጉዳይ በማሳገድ የበቀል ጥማታቸውን ሲወጡ ነበር፡፡ በዚህ ተስፋ ቆርጠው ለነበሩት መነኩሴ ተገቢው ፍትህ መሰጠቱና ወደ ሥራ መመለሳቸው ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ እንዲህ ባለው ለተበደሉት በምትሰጡት ፍትህ ያለንን አድናቆት በድጋሚ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ እንደ አባ ማቴዎስ ያሉ መሰሪዎች ግን ጳጳስ ስለሆኑ ብቻ ዛሬ የፈለጋቸውን ቢያደርጉም አንድ ቀን በሃያሉ በእግዚአብሔር እጅ መውደቃቸው አይቀርም፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የምንገኝ ካህናት

6 comments:

 1. Good Point. but don't forget that Aemere is the Special One.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I DO NOT THINK

   Delete
  2. Yes he is. A very special super genious. Full of knowledge........

   Delete
 2. You say about Aba Hitsan the Menk and Frew who is ilegal person why not About TAGAY TADELE the PRIST who is MK'S servant who serve for two directions why not MK insult him b/c He is MK at night time and Democrat at day time Thank you for all

  ReplyDelete
 3. I proud of the writer for his future perspective.
  By the way the so called "Aba hitsan" is not only the runner after his money but also he is a spy.

  ReplyDelete
 4. In the Name of the Father the Son and Holy Spirit Amen

  Shame! How can you non-heretic clergy make this tehadiso site your blog! Don't you know that this site is working the foundation of EOTC! ! Let our Lord, kings of kings Lord of Lords. alpha and Omega Jesus Christ light your path!
  If AA hagere sebeket is planning to transform the church, first let them stop tier propaganda agantsit Mahibre kidusan and sunday schools, Second let them distance from corrupts , despots and ethnocenterics ( Our Lord was crucified for Gumz, Ormo , Tigre, Amarah., gurage to all people of the planet! Ethnicity is not a criteria to be saved!) and listen to the laity.

  We are tired of accusation against Mahibre Kidusan and Sunday School students as we see thier fruits such as bring millions at the service of EOTC, helping abenet schools and facilitating bapitization of our brothers and sister in border lands, helping preached the unrevised gospel in TV!

  As they are youth they are fast as result they can commit errors. Such error can be corrected once for all by assigning genuine Fathers that can overlook thier plan and activities similar to board.
  Mostly the accuser are corrupts, white magcians hidden in EOTC, ethnocenterics with political mission rather than pastoral and heretics. This is well known by most EOTC believers. We believe in what we see not hear!

  Aregawi ze Bole

  Amen

  ReplyDelete