Monday, August 3, 2015

የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ በስሙ የሚነግደውን መ/ር ሮዳስ ታደሰን አስጠነቀቀከማኅበረ ቅዱሳን “ሊቃውንት” አንዱ የሆነውና ራሱን መጋቤ ሐዲስ በማለት የሚጠራውን መ/ር ሮዳስ ታደሰን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስጠነቀቀ፡፡ ኮሌጁ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የጻፈው ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተማሪ ባልሆነበት ሁኔታ በየመገናኛ ብዙሃኑ፣ በዓውደ ምሕረትና በሚጽፋቸው መጻሕፍት ላይ ራሱን “የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር” ብሎ በመሰየም በኮሌጁ ስም እየነገደ መሆኑን ስለደረሰበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ኮሌጁ አክሎ እንደገለጸው ግለሰቡ ከድርጊቱ ካልተቆጠበ ጉዳዩን ወደ ሕግ እንደሚወስደው አስጠንቅቋል፡፡

መ/ር ሮዳስ የኮሌጁ መምህር ሆኖ ከዚህ ቀደም ለ2 ወራት የቆየ ሲሆን ሊባረር የቻለው በሚያስተምረው ትምህርት ምንጭ አድርጎ የሚጠቅሰው ሐመርና የማቅ ህትመቶችን መሆኑ ያበሳጫቸው የቀን ተማሪዎች አይመጥነንም ብለው ወደ ክፍል አናስገባም በማለት ስለተቃወሙት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መ/ር ሮዳስ  ኮሌጁን “የግቢ ጉባኤ” በማስመሰል የማኅበረ ቅዱሳን የኅትመት ውጤቶችን እንደ ማስተማሪያ መጠቀሙ የማኅበሩን “ርእዮተ ዓለም” በኮሌጁ ለማስረጽ ካለው ጉጉትና ከተሰጠው ተልእኮም አንጻር ያደረገው እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ ምርቱን ከግርዱ ያልለየ መጽሐፍ ቅዱስንና አዋልድን፣ ዶግማና ቀኖናን እኩል የሚያደርግ መሆኑ ስለሚታወቅ፣ እንደውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ትውፊትን፣ ከወንጌል ይልቅ ታሪክን ስለሚዘበዝብ ለብዙዎች ሕይወት የማይገኝበት ትምህርት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምርቱ ከግርዱ የሚለይበት አንዱ ቦታ ደግሞ ኮሌጅ ሆኖ ሳለ እርሱ ኮሌጁን የማቅ የኑፋቄ ትምህርቶች መድፊያ ለማድረግ መሞከሩ ከተማሪዎች ጋር እንዲጋጭ አድርጎታል፡፡ ከዚህ በፊት ከቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅም በተመሳሳይ ሁኔታ መባረሩ ታውቋል፡፡
ሌሎቹ የማቅ ሰዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ ግለሰቡ የማቅ ሰዎች ባሉባቸው ሚዲያዎች ዕድሉ እየተመቻቸለት ብዙ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሳትወክለው ራሱን ወኪሏ አድርጎ በማቅረብ በየበዓላቱ እየቀረበ ሃይማኖታዊ ማብራሪያዎችን ሲሰጥ እንደ ቆየ የሚታወቅ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ውስጥ የማይታወቁና በአብነት ትምህርት የትርጓሜ ዘይቤ ውስጥ የሌሉ መጻህፍትን ለምሳሌ የመጽሐፈ ሰዓታትንና የመልክአ ማርያምን አንድምታዎች አሳትሟል፡፡ ለመሆኑ በየትኛው የመጻሕፍት ወንበር ይሆን መልክእ ትምህርት ሆኖ የሚሰጠው?
መልክእ እንኳን እንድምታ ሊዘጋጅለት ይቅርና ወደ አማርኛ መተርጎም የሌለበት መሆኑ በሊቃውንቱ ዘንድ ይታወቃል፡፡ ሮዳስ ግን ይህን ትውፊት አያውቅ ይሆን ወይም በማን አለብኝነት ለመልክአ ማርያም አንድምታ አዘጋጀሁ ብሏል፡፡ በዚህም ከማፈር ይልቅ መልክአ ማርያም ከተደረሰ ከ600 ዓመታት በኋላ ራሱን የመጀመሪያ ተርጓሚ አድርጎ በማቅረብ ሲመጻደቅበት ከርሟል፡፡ “መልክአ ማርያም ከተደረሰች ጀምሮ አኹን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ስድስት መቶ ዓመታት ቢያልፋትም በንባብ ደረጃ እንጂ ትርጓሜ (አንድምታ) ሳይዘጋጅላት ቈይታለች፡፡” ካለ በኋላ በእርሱ አካማይነት ግን “ትርጓሜው፣ አንድምታው፣ ትንታኔው፣ ምስጢሩ፣ ሐተታው፣ ታሪኩ በጥልቀት ተተንትኖ” እንደቀረበ ለመጽሐፉ ምርቃት የሠራው ማስታወቂያ ላይ ገልጿል፡፡
ይህ መጋቤ ሐዲስነት የማይገባው ሮዳስ ለ600 ዓመታት ሊቃውንቱ መልክአ ማርያምን ጨምሮ ሌሎች መልኮችን በዚህ ደረጃ ያላዘጋጁት መልክ እንኳን አንድምታ በነጠላውም አይተረጎምም የሚል ባህል ስላላቸው ነው፡፡ ይህን ባህል ጥሶ የሌለውንና ዕውቅና የማይሰጠውን አንድምታ ማዘጋጀት ከሌላ ተልእኮ ጋር የሚያያዝ እንጂ መጋቤ ሐዲስ የሚያሰኝ አይደለም፡፡ ሮዳስ በአብዛኛው አንድምታ እያለ የጻፋቸው መጻሕፍት በአብነት ትምህርት ቤት ወንበር የሌላቸውና የማይታወቁ የእርሱው ፈጠራዎች ናቸውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ለነገሩ በዚህ መጽሐፍ ዙሪያ የማቅ “ግልጽ” አመራሮች ዘንድ መጽሐፉ የእርሱ ነው አይደለም በሚል ውዝግብ እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡
በአጠቃላይ ግን “አንድምታ” እያለ የሌለውን በመጻፍ በማደናገር ላይ ያለውን ሮዳስን ኮሌጁ እንዳደረገው ሁሉ ቤተ ክህነቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየተሠራ ያለውን ይህን ሕገ ወጥ ድርጊት ሊያስቆመው፣ በ“አንድምታ” ስም እየጻፈ ያለውን መጽሐፍ ወይ ስያሜውን እንዲቀይር (“አንድምታ” እንዳይለው) መመሪያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ የሞተልንንና በክቡር ደሙ የዋጀን ክርስቶስ ሳይሆን ማርያም እንድትሰበክ እየሠራ ያለው ቡድን ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
       

24 comments:

 1. እናንተ ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ለማፍረስ የተነሳችሁ ግን የማይሳካላችሁ ተኩላዎች ለብር ብላችሁ ነፍሳችሁን የሻጣችሁ ስለ መምህር ሮዳስ አይደለም ሁሉም ስለሚያውቀው ስለ ማንም ኦርቶዶክስ ቢትጽፉ ማንም አይሰማችሁም ።

  ብር ምድር ላይ ብቻ ይሰራል በሰማይ ምን ታደርጉ ይሆን?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እናንተ ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ለማፍረስ የተነሳችሁ ግን የማይሳካላችሁ ተኩላዎች ለብር ብላችሁ ነፍሳችሁን የሻጣችሁ ስለ መምህር ሮዳስ አይደለም ሁሉም ስለሚያውቀው ስለ ማንም ኦርቶዶክስ ቢትጽፉ ማንም አይሰማችሁም ።

   ብር ምድር ላይ ብቻ ይሰራል በሰማይ ምን ታደርጉ ይሆን?

   Delete
 2. ይድረስ ለአባ ሰላማዎች (ሳማዎች)
  ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም
  ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
  ለአባ ሳማዎች ስድብ የተሰጠ ምላሽ
  “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ ርሱ ሌባ ወንበዴም ነው” (ዮሐ 11፡1)
  ይኽነን ቃል የተናገረው የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እናንተ ተሐድሶዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረስ አጀንዳችሁ ጋር ከብፁአን አባቶች ጀምሮ በየጊዜው በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ላይ የከፈታችሁት የስድብ ጦርነትን ሳስብ በዮሐ ራእይ 13፡6-7 ላይ “እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ፤ ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው” የሚለው የአውሬው መንፈስ ምርኮኝነታችሁን ያሳስበኛል፡፡
  ድብቁ ዓላማችሁም የቤተ ክርስቲያኒቱን የአብነት ትምህርት በሚገባ ተምረው ተመርቀው በነገረ መለኮት ትምህርት ተራቅቀው ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚጽፉ ምሁራን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ወጥተው ዘላማጆች እና ቀላማጆች ተሐድሷዊ የልምድ አዋላጆች በቦታው ተተክተው እናንተን የሚያማችሁ የኦየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነትና ጌትነት የቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳይነገርባት ለማድረግ ነበር፤ ነገር ግን ባለቤቱ ልዑል እግዚብሔር “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” ብሎ ቃል ስለገባ የክሕደት ዝናራችሁ ያልቃል እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ምንም ልታደርጓት አትችሉም፤ እውነቱን እላችኋለሁ ቤተ ክርስቲያኗን ለማፍረስ የምትቀበሉትም ከንቱ የክሕደት የይሁዳ ብርን ሳትበሉት እንደ ይሁዳ ታልፋላችሁ፡፡
  መቼም አእምሯችሁ በድንቁርና ፈርሶ እያለ የሊቃውንት መካን የኾነችውን ቤተ ክርስቲያኒቱን በድፍረት እናድስ ስትሉ አለማፈራችሁ በእጅጉ ይገርማል፤ ዳግመኛም በሊቃውንት ላይ የስድብ አፋችሁን ብትከፍቱም ለሊቃውንቱ በረከት ነው፤ ምክንያቱም እንኳን እኛን ቀርቶ ፈጣሪያችሁ ክርስቶስን ዳግመኛም የአምላክን እናት፤ ቅዱሳንን ለመስማት የሚዘገንን ስድብን ለመሳደብ አፋችሁ በትልቁ የተከፈተ፤ ኅሊናችሁም የደፈረ ስለሆነ አይደንቀንም፤ ይልቁኑ እንጸልይላችኋለን እንጂ!!!፡፡
  ሰውን ለማሳመን ስትሉ የጻፋችሁትንም ሳነበው በጣሙን አስገርሞኝ ነበር፤ ምናልባት ስለ ራስ መናገር ተገቢ ባይሆንም ባያንጽም ግድ የለም ምናልባት ልታሳስቱት የሞከራችሁትን ምእመን ለመታደግ ሲባል ብቻ መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ሕይወታችን እድገታችን በአብነት ትምህርት ቤት እና በታወቁት ሊቃውንት አትሮንስ ሥር ስለሆነ ታሪካችን ግልጽ ነው፤ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እንዳሉ አበው ምንም እናንተ ስለ አብነት ትምህርት ቤት ብዙም ባታውቁም ቅሉ እኔ መጋቤ ሐዲስነትን የሰጠኝ ትምህርቴ እንጂ ጉልበት መሳሜ አይደለም!!! ይኸውም ከታላቁ ሊቅ ከመልአከ ፀሓይ ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ የመጻሕፍተ ሊቃውንትን፤ የአቡሻኽርን፤ የውዳሴ ማርያምንና የቅዳሴ ማርያም፤ የኪዳንና የትምህርተ ኅቡአት ትርጓሜን በሚገባ አጠናቅቄ፤ በተጨማሪም ለስድስት ዓመታት ከታላቋ ስምንት ጉባኤ በብቸኝነት ከሚሰጥባት ከታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ለስድስት ዓመታት በጉባኤ ቤቱ ከመጋቤ ሐዲስ ደምፀ አንበርብር የሐዲሳት ጉባኤ ቆይቼ ያውም በከፍተኛ ማዕረግ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ተሸልሜ እንጂ፤ እንደናንተ ዝም ብሎ የተለጠፈልኝ የክብር ዶክትሬት አይደለም፡፡ ደስ ካላችሁ የመምህርነቱን ዲፕሎሙን እልክላችኋላሁ፤ ምናልባት ትምህርት ቤት ያልዋለ ዐይናችሁ ካልደከመው፡፡
  ኹለተኛም በታላቁ ኮሌጅ እንደናንተ ትምህርቱ ከብዶኝ አቋርጬ የወጣሁ ሳይሆን፤ በቀን በአዳሪ ተማሪነት ከዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወዳድሬ አልፌ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቼ የመጀመሪያ ዲግሪዬን በከፍተኛ ማዕርገ 3.7 በማምጣት፤ እንደገና በድኅረ ምረቃ ዲፕሎም ከተሰጡት ስምንት ኮርሶች አራቱን ትምህርቶች A፤ አራቱን ትምህርቶች A ፕላስ በአጠቃላይ 4 ነጥብ አምጥቼ እጅግ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቄ እንጂ እንደናንተ ብሎግ ሥር ተሸጉጬ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት በመሳደብ አይደለም፡፡
  https://www.facebook.com/rodastadese.abebe/posts/958707964191300

  ReplyDelete
  Replies
  1. Edmewo yirzem wondimachin abatachin Megabe Haddis Rodas. Abaselama asafariwoch.

   Delete
  2. በመጀመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ራስህን የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የሐዲሳት መምህር ማለትህን ስለተውክ ልትመሰገን ይገባል፡፡ ሮዳስ በቅድሚያ ስለራስህ የሰጠኸው ምስክርነት አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ራስህን ለመከላከል የደረደርካቸው ምክንያቶችም ውሃ አያነሱም፡፡ እንዲያውም ማን መሆንህን በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ አሁን “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ ርሱ ሌባ ወንበዴም ነው” (ዮሐ 11፡1) የተጻፈውን የጠቀስከው ለምንድነው? ራስህን ለመከላከል ከተነሳህበት ጋር ምን አገናኘው? አሁን ማን ይሙት እንዳንተ በበሩ በኢየሱስ ያልገባና በሌላ መንገድ በማርያም ወዘተ የሚወጣ እንዳንተ ማንአለና ነው አፍህ እንዳመጣልህ ይህ ክቡር ቃል በባዶ ሜዳ የጠቀስከው? አሁን አንተ መጋቤ ሐዲስ መባል ይገባሃል? አይመስልኝም፡፡ በተጨማሪስ በዮሐ ራእይ 13፡6-7 ላይ “እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ፤ ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው” የሚለው የአውሬው መንፈስ ምርኮኝነታችሁን ያሳስበኛል፡፡” ያልከው ያው ጥራዝ ነጠቅነትህን እንጂ ሐዲስ ኪዳንን መጠንቀቅህን አያሳይም፡፡ ይህን ጥቅስ ለሚጠይቃችሁ መልስ ስታጡና በድቡሽት ላይ የተመሰረተው ትምህርታችሁ ሲናድ አሁንም እንዳመጣላችሁ የምትጠቅሱት የተለመደ ጥቅሳችሁ ነው እንጂ ትርጉሙን በትክክል ተረድታችሁት አይደለም፡፡ አሁን እግዚአብሔርን የተሳደበ እናንተ "ተሐድሶ" ብላችሁ የምትጠሩት ወገን አለ? ማደሪያው የተባለውን ሰማይንስ ለመሳደብ ምን ምክንያት ይኖራል? ቅዱሳንንስ ከቶ የሚሳደብ አለ ወይ? በፍጹም የለም፡፡ እየተባለ ያለውና እናንተ “ስድብ” የምትሉት እኮ እንደ ቃሉ እናስተምር እንደ ቃሉ እንናገር የሚለው እውነት ነው፡፡ እናንተ ግን አንድ እግራችሁን ገድል ላይ እንድ እግራችሁን ወንጌል ላይ አቁማችሁ ተቸገራችሁ፡፡ ለቅዱሰን ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሰጣችኋቸው ቦታ በወንጌል ሲፈተሽ ስህተት ሆኖ በመገኘቱ ልክ አይደለም ሲባል ይህን ሁኔታ ቅዱሳንን መሳደብ ትላላችሁ፡፡ በዚህ ነገር የተነቀፋችሁት በተሳሳተ ትምህርታችሁ ምክንያት እናንተ እንጂ ቅዱሳን አይደሉም፡፡ ቅዱሳን እኮ አሁን እናንተ የምትሉትን አያውቁም፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አይቀበሏችሁም ነበር እንዲያውም ነገሩ አይቻልም እንጂ ቢቻልና ተገልጠው ማየት ቢችሉ “ይህ ልክ አይደለም አንቀበልም” ቢሏችሁ እነርሱኑ መልሳችሁ ተሐድሶ መናፍቅ ሳትሏቸው ትቀራላችሁ? ደግሞስ ስህተትህ ሲነገርህ እንዳልተሳሳትክ ማሳየትና ማሳመን እንጂ “አውሬው” ማለትን ምን አመጣው?
   “ድብቁ ዓላማችሁም የቤተ ክርስቲያኒቱን የአብነት ትምህርት በሚገባ ተምረው ተመርቀው በነገረ መለኮት ትምህርት ተራቅቀው ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚጽፉ ምሁራን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ወጥተው ዘላማጆች እና ቀላማጆች ተሐድሷዊ የልምድ አዋላጆች በቦታው ተተክተው …” ብለሃል፡፡ በቅድሚያ ቅዱሳት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? እንደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የያዛቸው መጻሕፍት ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎቹ አዋልድ ተብለው የሚጠሩና በውስጣቸው የሊቃወንት፣ የመነኮሳት፣ እንዲሁም ገድላትና ድርሳናት ወዘተርፈ ያሉባቸው ምድቦች ናቸው፡፡ አንተ ይህን ሳትለይ ነው መጋቤ ሐዲስ ነኝ የምትለው፡፡ እንደውም ይባስ ብለህ አንተ የምትጽፋቸውን የእግዚአብሔር ያልሆኑ ሐሣቦች ሁሉ “ቅዱሳት መጻህፍት” ናቸው ለማለት ነውኮ የዳዳህ፡፡ ለመሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት በሐዲሳትና በብሉያት ተፈጽመውና በቀኖና ተዘግተው የለም ወይ? በዚህም ዘመን ለዚያውም እንዳንተ ያሉ ወንጌልና ገድልን የሚያዳቅሉ ፍናፍንቶች ሊጽፏቸው ከቶ ይችላሉን? ጕስዓተ ልብህን ሁሉ “ቅዱሳት መጸህፍት” ብለህ ስትጽፍ እንዲያው እጅህን እንዴት አልያዘህም?
   ደግሞስ “እናንተን የሚያማችሁ የኦየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነትና ጌትነት የቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳይነገርባት ለማድረግ ነበር፤” ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ብቻ ናት እንዲህም ሲባል ድንግል ማርያምን ጨምሮ ያንቀላፉ ቅዱሳንና በሕይወት ያሉ ሁሉ አባላት የሆኑባት ጉባኤ ናት፡፡ ድንግል ማርያም የቤተክርስቲያን አባል እንጂ ከክርስቶስ ቀጥሎ ሁለተኛዋ “ጌታ” አይደለችም፡፡ አንተና መሰሎችህ ግን ደረጃ አውጥታችሁ ቅዱሳንን ከኢየሱስ በታች ተወራጅ አማልክት አደረጋችኋቸው፡፡ ኢየሱስ በቤዛነቱ በኩል ዛሬም አስታራቂ ነው፡፡ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ደግሞ ዳግም የሚመጣ ፈራጅም ነው፡፡ አስታራቂነቱን ገፈህ ፈራጅ ብቻ የምትለው ለምን ይሆን? ያንቀላፉትን ቅዱሳን በአስታራቂነቱ ቦታ ለማስገባት አይደለምን? አሁን “እናንተን የሚያማችሁ የኦየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነትና ጌትነት የቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳይነገርባት ለማድረግ ነበር፤” ብለህ የጻፍክ አንተ እውን መጋቤ ሐዲስ ነህ?
   በመጨረሻው ስለራስህ ስለተማርክበት ቦታ እና ስለአስተማሪዎችህ ስላገኘኸው ውጤት የተናገርከው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ቁም ነገሩ እርሱ አይደለም፡፡ የተጫኑት ማራገፍ ምን ቁም ነገር ነው! የአንድምታ ጋጋታ ወደ እውነት ካላደረሰ ምን ዋጋ አለው? በመጨረሻ ግን አንድ ነገር ልጠይቅህ ከቅድስት ሥላሴም ሆነ ከጳውሎስ ኮሌጅ መባረርህን ከአባ ሰላማ አንብቤያለሁና በምን ምክንያት ይሆን የተባረርከው? እርሱ ላይ ያልከው ነገር የለምና አንድ ነገር ብትል ጥሩ ነው፡፡

   Delete
 3. በዮሐንስ ወንጌል ፰፡፬፬ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እር ሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ኀሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ኀሰተኛ የኀሰትም አባት ነውና
  ይህ ከላይ ያስቀመጣችሁት ውይም ያቀረባችሁት ማስረጃ ከመሃሉ ደምቆ ሚታየው በእውነትም የተቀነባበረ የኀሰት ማስረጃ መሆኑን ማንም ከስእሉ አይቶ መረዳት ይችላል። ከኮለጁም ፈጽሞ እንዲህ ያለ ደብዳቤ አልተጻፈም።
  ግን ምንም አይደል
  የ አውሬው ዘመን ላይ ደርሰናልና እናንተም የ አውሬው ስራ አስፈጻሚዎች ናችሁና የፍርድ ቀን እስኪመጣ ዘመናችሁን ተጠቀሙበት። ጌታ ልብ ሰጥቶ ለንስሃ ያብቃችሁ።

  ለማንኛውም እውነተኛውን ማስረጃ እዚህ ጋር በመጫን ታገኙታላችሁ

  https://drive.google.com/folderview?id=0By4p6dZplRlYfmpYS3VhUm13X3JCalFlX25fTVYwZGh4LU5YZkFKRGhhU3F6WXZ6djNMTHM&usp=sharing

  ReplyDelete
 4. ታዲያ ይህን ያህል ተምረው ታላቁን መጽሐፍ የሃይማኖቶች መጽሐፍ ሁሉ ንጉሥ የሆነውን ታላላቅ አባቶች በቤተክርስቲያናችን የጻፉትን ሳያነቡ ቀሩ?የዮሐንስን ወንጌል ማለት ነው እኮ እርሱን ቢያነቡ ኖሮ ለዚህ ነገር አይደርሱም ነበር እርሱን ቢያነቡ ኖሮ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ከላይ ያለውን ደብዳቤ አይጽፍብዎትም ነበር እኮ?እርሱን ባለማንበብዎ ተው የተባሉትን መተው አቃተዎት እርሱን ቢያነቡና የክርስቶስ ቤተሰብ ቢሆኑ ኮሌጁም አይደፍርዎትም ነበር እርስዎ ግን ያነበቡትን መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሆን የተስፋ ገ/ሥላሴን የገበያ ምንጭ የሆኑትን መጽሐፍት ብቻ ነውና ወደልብዎ ተመልሰው የቅዱስ ማቴዎስን የቅዱስ ማርቆስን የቅዱስ ሉቃስን ና የቅዱስ ዮሐንስን አንብበው ሲጨርሱ ወደ መልዕክታት ከዚያ እያሉ ሲጥምዎት ይመለሳሉ አሁን ያነበቡት ቃሉን ሳይሆን የሰዎችን ፈጠራ ውጤት ነው ስለዚህ እኮ ነው ይህ ሁሉ መሳደድ የመጣብዎትና እባክዎ መጋቢ ሮዳስ ስለመጽሐፍ ቅዱስ መጻፍና መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይለያያልና ስለመጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ትተው መጽሐፍ ቅዱስን ራሱን አንብበው እንደገና ቢመረቁ ምን ይመስልዎታል?እኛም የዚያን ጊዜ ልባችን ያርፋል! በቅድስት ሥላሴ ኮሌጃችንም መነገድ ያቆማሉ የገቢ ምንጭዎም እግዚአብሔር ይሆናልና መናፍቃንን ተሃድስዎችንም ያሸንፋሉ ይረታሉ አለበለዚያ ታሪክ ይጠይቅዎታል ነፍስዎም አታርፍም!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 5. Megabe Hadis,
  Enesu yekentu kentuwoch silehonu niqew yitwuachew.

  ReplyDelete
 6. Megabe Hadis,
  Chigirachew Irswo zend aydelem.
  Dingil silemin temesgenech ,sileminis tewedesech ,sileminis silersua tetsafe new.Diros kekentuwoch ena yanin semayawi mistir meredat kegodelachew yaltadelu minamintewoch min yitebeqal.

  ReplyDelete
 7. የሚያደርጉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ !!

  ReplyDelete
 8. “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” ብሎ ቃል ስለገባ የክሕደት ዝናራችሁ ያልቃል እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ምንም ልታደርጓት አትችሉም፤ እውነቱን እላችኋለሁ ቤተ ክርስቲያኗን ለማፍረስ የምትቀበሉትም ከንቱ የክሕደት የይሁዳ ብርን ሳትበሉት እንደ ይሁዳ ታልፋላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 9. ብር ምድር ላይ ብቻ ይሰራል በሰማይ ምን ታደርጉ ይሆን?

  ReplyDelete
 10. ምነው አቶ ራዳርስ እንደዚህ አንጨረጨረህ አላዋቂነትህን በሚገባ ነገርከን እኪ የተማረ ሰው ትእግስተኛ እንጂ የወረደ አነጋገር አይናገርም ግን ከአስተያየትህ እንደተረዳሁት ምንም የማታውቅ የሰንበት ተማሪ ሆንህን ተረድቻለሁ በዓታ የሊቃውንት መማሪያ ነው ብለህ መጥቀስህ ማንነትህን ገልፆሃል የበዓታ ትምህርት ቤት እኮ ሙዓለ ሕፃናትና የሰንበት ት/ቤት መሆኑን አላወቅክም እንዴ አሳዛኝ ምስኪን ለማንኛው በማታውቀው ትምህርት አትኮፈስ ሆኖ መገኘትን ተለማመድ ለአሁኑ ግን አልተሳካልህም ሌላ ሞክር እሺ የኛ መሀይም!

  ReplyDelete
 11. በመ/ር መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ላይ የሐሰት ወሬ
  ማቴ 7 :15 "የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?"

  በመ/ር መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ላይ ተሐድሶ ወይም በጉያችን ሆነው ራሳቸውን በቀሚሳቸውና በብሎግ እንዲሁም በፌስ ቡክ ደብቀው በቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን ላይ ምንፍቅናን የሚዘሩ የዘመኑ ተኩላዎች የሀሳት ሴራ በማሴር የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመምህሩ ላይ የማስጠንቀቂያ በደብዳቤ እንደጸፈ አድርገው ተኩላዎቹ አባ ሰላማ ብሎግ ላይ ፖስት አድርገዋል ።
  ለመሆኑ እነዚህ ከዚህ በፍት በቤተክርስቲያናችን አሉ የሚባሉ አባቶች ላይ ፣ መምህራና ወንጌል ላይ፣ ዘማሪያን ላይ እንዲሁም ዲያቆናት ላይ የጣሉት መረብ አላጠምድ ሲላቸው አገልጋዮቻችን በብር እንደእነ ሆዶ አንታለል ሲሉ አባ እገሌ በዝሙት ቅሌት ከዚህ ቦታ ተበረሩ ፣ መምህር እገሌ በቅዱስ ሲኖዶስ ተገደ ፣ ዲያቆን እገሌ ግብረ ሰዶምን ተቀብለ እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳን ተበተነ ተከፈለ...... በማለት ስም ሲያጠፉ የቆዩ ናቸው ።
  አሁን በላ ተረ ሆነና መ/ር ሮዳስን ቅ/ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስጠነቀቀው አሉ።
  1. የኮሌጁ ማህትም የረፈበትን ወርቀት ስካን አድርገው ወደ ኮምፕውተር በማስገባት በወረቀቱ ላይ ድገሚ መፀፋቸውን ማንም አትኩሮ ብመለከት እንደውም የውስጠኛው ወረቀት ''እግዚአብሔር ኢት/ያን ይባርክ'' የምል "ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን እናስታውቃለን" ከሚለው በታች የውስጠኛው ወረቀት ላይ ይነበባል ። ዓይን ያለው ማንም አይቶ ይፈርዳል ጽሁፍ በጽሁፍ መደረቡና ማህተቡ መደብዘዙ የቅንብር ሴራቸውን አጉልቶ ያሳያል።
  2. በብሎጋቸው ላይ በፃፉት መምህሩ ከኮሌጁ በተቀጠረ በ2ኛ ወር መበረሩን ጽፈዋል ። ታዲያ ማን ይሆን ለአንድ ዓመት በዶግማ መምህርነት አገልግሎ ህጋዊ ወረቀት ከኮሌጁ የተቀበለው ? (ከታች የተለጠፈውን ህጋዊ የስራ ልምድ ይመልከቱ)
  3. አንድምታ እያለ የሌለውን በመጻፍ በማደናገር ላይ ነው ። የሌላውን መፅሐፍ መምህሩ አደነግረው ቢሆን የመጽሃፉ በለቤት ወይም የሚመለከተው አካል በዝምታ በላለፈ ነበር ። የአዕምሮ ንብረት በለቤትነት የምባል ህግም ነበር እኮ ረሳችሁት እንዴ ለነገሩ እውነታው ሁሉ ጠፍቶባችሁ ከጨለማው አለቃ ጋር አይደላችሁ።ልቦናችውን ወደ ቀደመ ክብር ይመልሳችሁ።
  4.መልክአ ማርያም በመምህሩ መተርጎሙ የእግር እሳት ሆኖባችው ለ600 ዓመታት ሊቃውንቱ መልክ እንኳን በአንድምታ በነጠላውም አይተረጎምም ብለው ያላዘጋጁትን እንዴት ሊያዘጋጅ ይችላል ? በማለት ለክስ ምን አወጣችሁ እኛ ያኢግዚአብሔር መንፈስ የለባቸውን መጽሓፍት ብንጠቀም እናንተ ምናችሁ ተጎዳ?
  "የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።"
  (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16-17)

  በአጠቃላይ አባ ሳማዎች እባካችሁ በቅድስት የቤተክርስቲያን ላይ እላማችሁ ብያነጣጥርም ምንም ማድረግ አትችሉም ። አትችሉም ያለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ነው።

  ''እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።" ማቴ 16 ፡ 18 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካችንና ፈራጃችን ነው ። ሊቃውንቱን ያቆይልን
  ድንግል ማርያም፣ ቅዱሳን መላዕክት፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት በአመላጅነታቸው አይለዩን አሜን።

  ReplyDelete
 12. tinish fer yelekekachihu alimeselachihum aba selamawech yih neger bihon enkuan kirsitina bemikir engi besidib ataminim silezih alu yalnachewun memihiran eshoh atihunubachewu .

  ReplyDelete
 13. Deacon Rodas bante Mk yafral! bante books lay ante yelehm (b/c of all your writings are copy paste. THINK your self who you are?? pray pray pray!!

  ReplyDelete
 14. “አባ ሰላማዎች” ሐሳባችሁ ያለምንም ጥርጥር ሰይጣናዊ ነው፡፡ እስኪ እናንተኑ ልጠይቃችሁና ከእንደዚህ ዓይነቱ ውሸትና ክፋት ምን ታተርፋላችሁ? እውነት እናንተ በኢትዮጵያ ምድር የበቀላችሁ ፍጥረት ናችሁ!? እባካችሁ በሞት መንገድ እየሄዳችሁ ነዉና ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 15. RODAS WE KNOW YOU. DO NOT DECIEVE THOSE WHO DO NOT KNOW YOU.

  ReplyDelete
 16. በጣም ያዘንኩት በእናንተ ድክመት ነው መምህራችን መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ አስተማሪያችን ነው ቅድስት ስላሴ ካሉ የሐዲስ ኪዳን መምህራን እሱ ታላቅ ነው በእውነት ስለ እሱ መናገር ይከብደኛል ግን የእናንተን ክህደት ዛሬ ቁልጭ ብሎ ወጣ Stars can't shine without darkness. የሚለውን የፈረንጆቹን አባባል አስታወሰኝ የመምህራችን መጻህፍትም ብዙ የሚያንጹ እና የሚያስተምሩ ናቸው ለነገሩ እናንተ ስለ መልክ ስለ መጋቢ ሐዲስነት የት ታውቃላችሁ ሞተልኝ ቅብጥስዬ እያላችሁ የጌታችንን የአምላካችንን የድህነት ምስጢር የምታቃልሉና የማትረዱ መናፍቃን አሁን ትውልዱ አውቁችኃል ብዙ አትድከሙ ብዙ ኃይል አለን ከቅዱሳኑ ጋር ግን ሰውን ለማንኛውም "Great minds discuss ideas; average minds discuss events; small minds discuss people." ይላል ፈረንጅ ትንሽ አእምሮና ስራ ፈት ትውልድ ቤተክርስተያን የላትም ፈረንጅ ለሰው ጥቅም የሰራውን ቴክኖሎጂ እናንተ የሰውን ስም ለማብጠልጠል ተጠቀማችሁ ት ያሳዝናል ፈጣሪ ማስተዋሉን ይስጣችሁ ድንግል አማላጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ጌታ አምላክ ነው አሜን አሜን

  ReplyDelete
 17. LEGES HAIL ANTE BEBELAHIBET YIMITCHOH YALSELETENK WISHA NEH ROADS ASTEMIROH MINAYNET MIHUR LITTON NEW RASU ROADS ALTEMARKIM MAFERIYA NEW BE EWIR BET ANDAYNA BIRKNEW YIBALALA BEBATA LEMARYAM KG TEMIRONEW LIK YEMIKONEW GIN ANTENA DENKOROWOCH NEH AYGEBAH YELIKAWNT MEFLEKYA YEHONEW GONDERNA GOJAME ENKAN ATAWKIM ZEREGNA YENANTE LIKELIKAWNT EKO TSEBATE HAILE MEKELR NEW AFALEGN BILE TINGRALEH MAFERIYA YESENBET TEMARINEH RASIHN AWAKE ADRIGEHAL MUTICHA EMEN TIDNALEH ROADS BE LEBNETU ENJI BETMIHRTU YITAWEKAL ENDE YE MK TEBEKA NEH EHSA DOMA YEHENOK TEMARINEH

  ReplyDelete
 18. አባ ሰላማዎች፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን!
  ከላይ በመልዕክቱ ላይ የለጠፋችሁት ‹‹ስካን አድርጋችሁ ያቀረባችሁት ደብዳቤ›› ውሸት ነው ወይስ እውነት ነው? እውነት ከሆነ እንድታረጋግጡልን እንፈልጋለ፣ ውሸት ከሆነ ግን ከዚህ በኃላ በእናንተ ላይ ያለንን አመኔታ ለማቆም እንገደዳለን፡፡

  ReplyDelete
 19. Why aba selama wants to lie us?

  ReplyDelete
 20. MEGABE HADDIS RODAS Vs "MEGABE HADDIS" Begashaw(kikikikii)
  You accepted Ato Begashaw's Megabe hadis who cannot speak even one word of Geez......Maferiawoch
  Megabe Haddis Rodas is well known across the globe for his True Preach which is not comfortable for pasters like aba selamawoch..

  ReplyDelete
 21. አይ አባ ውሸት። አባ መስጠት። አባ ዲያብሎስ።

  ReplyDelete