Thursday, August 13, 2015

እስመ ናሁ ኃጥኣን ወሰቁ ቀስቶሙ ...“እስመ ናሁ ኃጥኣን ወሰቁ ቀስቶሙ ወአስተዳለዉ አሕፃቲሆሙ ውስተ ምጕንጳቲሆሙ ከመ ይንድፍዎሙ ለርቱዓነ ልብ” “ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋል፣ ፍላፃቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ፡፡” (መዝ. 10፥2)
ባለፈው ጊዜ አባ ሰላማዎች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተደረገው ለውጥና እየተገኘ ባለው አዎንታዊ ውጤት ዙሪያ በሰፊው ዘግባችሁ ሊበረታቱ ስለሚገቡ ነገሮች በስፋት አስነብባችሁን ነበር፡፡ እውነትም የማይካዱ ተጨባጭ ለውጦች ጠላትም ሆነ ወዳጅ ሊክዳቸው የማይችሉ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ ለምሳሌ ከዘር ከሙስና ከአድልዎ በጸዳ መልኩ የተሰሩ በርካታ ሥራዎች አሉ፡፡ አባ ሰላማ ድረገጽ ጥሩና ሚዛናዊ ሚዲያ እንደመሆኑ መጠን ወደፊት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችንም ስለነሊቀ ማእምራን የማነ አንዳንድ ስጋቶችን ተንብዮ ነበር፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደስ የማያሰኝ ለቅዱስ ፓትርያርኩም ትልቅ ሐዘን የሚሆን ወሬ እየተወራ ነው፡፡ ወሬውን የሚያስወራውም ቅኖችን በስውር እንደ እባብ የሚናደፈው ባለሦስት ባህርይ የሆነው የብሔረ ጽጌው አለቃ አባ ነአኩቶ ነው፡፡ ሦስት ባህርይ የተባለው ውሸታም አመንዝራና ሌባ በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ተኩላ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ በመልአከ መንክራት እና በሊቀ ትጉሃን መካከል ለነበረው አለመግባባት የተጫወተው አፍራሽ ሚና ቀላል አልነበረም፡፡ በዚህ እንደ ፈለኩ ለመሆን “የሕይወት ኢንሹራንስ” 80 ሺህ ብር ለጅማ ከፍያለሁ እያለ ሲያላግጥ ነበር፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ወደብሄረ ጽጌ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካዘወሩኝ አንድ ውለታ እውልሎታለሁ ይኸውም መልአከ መንክራት ሃሌ እና ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ በሚወጡበትና በሚገቡበት ቦታ እንዲከታተሉሎት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን በየቀኑ ለላዳ ታክሲ እንዲከፍሉ ይሁን ብዬ የከፈልኳቸውን ብር በተዘዋዋሪ ተቀብያቸዋለሁ፡፡ በብልጠትም ብሄረ ጽጌ ገባሁ ብሎ በየመሸታ ቤቱ ይፎክርበታል፡፡ ነአኩቶ ማለት አቡሃ ለኃጢአት ማለት ነው፡፡ 

አባ ሰላማዎችም ባለፈው የእርሱን ወደ ስራ አስኪያጁ መቅረብ እንደ ስጋት አይታችሁት ነበር፤ ከሰሞኑ በቦሌ መድኃኔ ዓለም  ቤተክርስቲያን ጀርባ ባለው ምግብ ቤት ከሁለት ሌሎች አለቆች አራት ጸሐፊዎች አንድ ሒሳብ ሰራተኛ በድምሩ 7 ሰዎች ባሉበት “እስካሁን የተፈራውን የሙስና መንገድ አስከፍቼዋለሁ ደስ ይበላችሁ” ዓይነት የምስራች ሲናገርና “ለዘመንፈስ ልጅና ለወልደ ሰንበት 350 ሺህ ብር ከፍዬ ነው ጸሀፊና ሒሳብ ሹም የቀየሩልኝ እንጂ ዝም ብለው አይደለም የቀየሩልኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ጥርሱን ያልሸረፈውን እንቶኔን ደግሞ ጥርሱን እንዲሸርፍ እናደርገዋለን” ብሎ ከፎከረ በኋላ “ይልቁን ቶሎ ቶሎ እንቀራረብና ሥራ እንስራ” ሲል ተደምጧል፡፡ ጥርሱን ያልሸረፈ የተባሉት መጋቤ ብሉይ አእመረ መሆናቸው ነው፡፡ ጥርሱን አልሸረፈም የተባለውም ጉቦ አለመብላታቸውን ለማሳየት መሆኑ ነው፡፡             
በእውነት መጋቤ ብሉይ አእመረ ለእግዚአብሔር መታመናቸው “ያልገባው” “ኋላ-ቀር” ያስብላልና “ተሊወ እግዚአብሔርን” መርጠዋልና ብድራቱን የማይረሳ አምላክ ዘመንዎን ያርዝም ዘርዎም ይባረክ እንላለን፡፡ ምክንያቱም ያሉበት ቦታ ብዙዎች ከዚህ ቀደም በዐመጽ መንገድ አለአግባብ የበለጸጉበት እንደ መሆኑ በኑሮዎ ምክንያት ማለትም የግል ቤት የሌለዎ መሆኑንና መኪና አለመንዳትዎን መሰረት አድርጎ ሰይጣን ሹክ ሲልዎ “ወግድ” ማለትዎ ልክ እንደ ዳዊት “እም ብዙኅ ብዕለ ኃጥአን ይኄይስ ኅዳጥ ዘበጽድቅ” በማለትዎ ቤተ ክርስቲያን ታማኝነትዎን አትረሳውም፡፡ መጽሐፍ እንደሚል “ወአብደረ ይሕምም ምስለ ሕዝበ እግዚአብሔር እም ይደለው ለሰዓት ወይከውኖ ኃጢአተ እስመ አእመረ ከመ የዓቢ ትዕይርቶ ለክርስቶስ እምኵሉ መዛግብቲሆሙ ለግብጽ፡፡ በተአምኖ ኀደረ ብሔረ ግብጽ ኢፈሪሆ መዓተ ንጉሥ እስመ አብደረ ይፍርሆሙ ለዘኢያስተርኢ እምዘ ይሬኢ ጸኒሖ ዕሴቶ” ማለትም ሙሴ “ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።” ይላል (ዕብ. 11፥24-27)፡፡ ርቱዓነ ልብን ከሚነድፉ እንደአባ ነአኩቶ ለአብ ባሉ ሃይማኖት አልባዎች የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መስረቅ ጽድቅ እየመሰላቸው በየአደባባዩ የሚፎክሩ ህሊና ቢሶች ወጥመድ ውስጥ ባለመውደቅዎም ሊመሰገኑ ይገባል እንላለን፡፡ ስለመልካም ነገርዎ ይህን ያህል ካልን እንደ ድክመት እየታሙበት ያለ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ምንም እንኳን እንደ ሊቀ ማእምራን የማነ ገና ለገና በዘረኛነት ላለመታማት ከአካባቢዎ ሰዎች ጋር ሻይ እንኳን ላለመጠጣት መራቅ አለብዎ ብለን ባናምንም እንዲህ ሊሆን ባይገባውም የአካባቢዎ ካልሆነ ሰው ጋር እንዳይታዩ ማዕቀብ የተጣለብዎ እስኪመስል መራቅ የለብዎም እንላለን፡፡ ምክንያቱም እርስዎ የተሾሙት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለመላው አገልጋይና ሰራተኛ ፍትህና ዳኝነት እንዲሰጡ ስለሆነ ያንን መቼም ቢሆን ሊዘነጉት አይገባም እንላለን፡፡ መጽሐፍም “ወዘሰ ይገብር ለኵሉ ሕግ ወይስሕት በአሐቲ ኮነ መአብሰ በኵሉ” (ያዕ. 2፥10) ነውና የሚለው፡፡
ሌላው ሰው ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት በአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና አስተዳደር ሲሆኑ ከዚህ በፊት የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ በጣም ጠንቃቃና ለሙስና ያልተበገሩ ሰው ሆነው በመገኘታቸው ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በእድገት ሲዛወሩ ብዙ ሰው ይደልዎ (ይገባዋል) ብሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የነበራቸውን መልካም ስምና “እውነትን አይስታትም” ይባልላቸው የነበረውን መክሊት በመተው በነአባ ነአኩቶ ለአብ ክፉ ሥራ ተጠላልፈው በዘረኝነትም በጉቦም አብዝተው እየታሙም እየሠሩም ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ነገር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምን ይሆን የተቀበረበት? ሙስና ካልሠሩ አይጸደቅም የተባለ ይመስል ወይም ካልሰረቁ ልጅ አያድግም የተባለ ይመስል መልካም ሰብእና የነበራቸው ሰዎች በዕድሜ እየበሰሉ ሲሄዱ እንደ ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት ያሉ ሰዎች ኃጢአት ነውርን በመጥላት ፈንታ አስቀድመው በጠሉት ነውርና ሙስና ተጠላልፈው ሲወድቁ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም ከአባ ነአኩቶና በክፍለ ከተማው ካሉ ደላሎች ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን አንዱን ጉቦ ተቀብለው ከሚገባው በላይ በማሳደግ ወገንና ገንዘብ የሌለውን ደግሞ ርስቱን ማስነጠቅን ተያይዘውታል፡፡ ፍርዱ ከእግዚአብሔር ይጠበቃል፡፡ “ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።” (አሞጽ 5፥12-13)፡፡
የካህናት አስተዳደር የሆኑት አባ ህሩይም “እገሌ ሊቀየር ነው ያንን ቦታ ከፈለግህ ይህን ያህል ክፈልና ቦታውን ታገኛለህ” እያሉ በአንድ በኩል ከእዚህ በሌላ በኩል ደግሞ እንዳትቀየር እናደርጋለን ግን ይህን ያህል ክፈል እያሉ ከሁለት ወገን ጉቦ እየተቀበሉ በቀደመ ስራቸው እየገፉበትና የሀገረ ስብከቱን መልካም ጅምር እያበላሹት ይገኛሉ፡፡እኚህ ሙሰኛ ለውጥ ከመጣ ወዲህ የሙስናው በር ስለተዘጋባቸው “ምንም ስራ የለም ወደ አለቅነት መልሱኝ” በማለት ያለጉቦ መኖር እንደማይችሉ አፍ አውጥተው እስከ መናገር መድረሳቸው ከእኛ ስውር አይደለም፡፡ በተለይም በቅርቡ ከጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት የአለቆች ዝውውር ይደረጋል የሚል ወሬ በመንዛት ወደተሻለውና በደንብ ወደሚበላበት ደብር ለመዛወር የቋመጡ እንደዚሁም “እንቀየር ይሆን ወይ” የሚለው ስጋት ያደረባቸው አለቆች አባ ህሩይን ደጅ እየጠኑ ነው፡፡ ይህ ሁሉ እየታየ ያለውን መልካም አስተዳደር በወሬ ለመፍታትና የወሬው ሰለባ ከሆኑት ላይ ጉቦ ለመቀበል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ተነቅቶ ከሰሞኑ ከአለቆች ጋር በተደረገ ስብሰባ ሥራ አስኪያጁ እንዲህ ያለ ነገር እንደሌለ ገልጸው እንቀየራለን ብላችሁ አሳስተዋችሁ ቀብድ የከፈላችሁም ካላችሁ ተቀበሉ ሲሉ በመናገር አለቆቹን በሳቅ ጨርሰዋቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ የሀገረ ስብከቱ አዲስ አሠራር በመልካም የተጀመረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ያለው ነገር ግን ዘላቂነቱ አጠራጥሯል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ተስፋ ሰጪ የነበሩ ነገሮችም ድምፃቸው (ደብዛቸው) ጠፍቷል፡፡ ለምሳሌ በስልጠና ላይ ይነገሩ የነበሩ ነገሮች በሙሉ በህግ የተከለከሉ ይመስል “እናሰለጥናለን፣ ፍትህን በእኩልነት እናሰፍናለን፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ሀብት እናስጠብቃለን፣ የሠራተኞችን መብት እናስከብራለን፣ ለተማሩ ሰዎች በቂና የሚመጥናቸውን ቦታ እንሰጣለን” የሚሉት የተስፋ ቃሎች አሁን አይወሩም፡፡ የስራ ዝውውርን ብናይ በምክንያት ማለትም በሰፈር ርቀት፣ በጥፋትና የሕዝቡን ጩኸት በመስማት ሳይሆን በመተዋወቅና በጓደኝነት ለሚታወቁት ብቻ እድገትና ዝውውር የተፈቀደ መስሏል፡፡ ለሌላው ግን የተገደበ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን በፊት ከነበረው አሠራር የሰማይና የምድር ያህል ርቀት ቢኖርም በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ትልልቅ ግድፈቶችም እየታዩ ነው፡፡ እያልን ያለነው እየታዩ ስላሉት ግድፈቶች ነው እንጂ የተጀመሩ መልካም ነገሮች እንደቀጠሉ መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን ዘረኝነት የለም፣ የመንፈሳዊ አገልግሎትና የአብነት መምህራን ያለምንም መማለጃና ጉቦ ተወዳድረው እንደሞያቸው ይቀጠራሉ፣ ይህ በእውነት ደስ የሚያሰኝና በዚሁ እንዲቀጥል የምንመኘው ነው፡፡
በሌላ በኩል ግን “ለውጥ እናመጣለን ማንንም አንፈራም ሁሉም ዜጋ እኩል ነው በእኩል ዓይን እናየዋለን” የሚል መፈክር ነበር፡፡ አሁን እየተሰራ ያለው ሥራ ግን  የተዘበራረቀ ነው፡፡ ችግር ያለባቸው መሆኑ በተነገረባቸው ዘራፊዎች ላይ የተወሰደ ቅያሬም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ የለም፡፡ እንደ ብሄረ ጽጌ ጎፋ ገብርኤል ሰአሊ ምሕረት መካኒሳ ሚካኤል የመሳሰሉትን ቦታዎች ያለሕግ ተጠያቂነትና በአምባገነናዊነት ከዕለት ወደዕለት እየጨመሩ እየሄዱ ነው ያሉት፡፡ ይባስ ብለው በሰአሊተ ምሕረት ጭራሹኑ ሥራ አስኪያጁ ለውንብድናው ዕውቅና በመስጠት ሰኔ 21 ቀን አጋፋሪ ሆነው ውለዋል፡፡ ስለዚህ “አይ ገና ነው ሌቦችን የሚቀጣ ዳኛ ገና አልተወለደም፤” ዝውውሩም ብዙ ዓመት ያስቆጠሩ ቤተክርስቲያንን የግል ካምፓኒያቸው እስኪመስላቸው ድረስ በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት እየተጫወቱበት ያሉትን እየነካ አይደለም፡፡ የፈለገው ሥራ አስኪያጅ ቢሾም ያለመከሰስ መብታቸው የማይገፈፍባቸው አሉ፡፡ ለምሳሌ የቦሌ መድኃኔ ዓለም የቅንጡዎች (የአባቶች) ልጅ ሰለሞን በቀለና ሒሳብ ሹሟ የመሳሰሉትን አሰራሩ አይፈትሻቸውም ወይ? እነሊቀማእምራን የማነም እነሰለሞን በቀለን ላለመንካት ይኸው እንደፈሪ ዱላ ዳር ዳር እያሉ ነው፡፡ በመሠረቱ እያልን ያለነው የአሠራር ሂደቱ ሁሉንም ሊነካ ይገባል ነው እንጂ ከዚህም ከዚያም እየሄዱ ይላተሙ ያለተጨባጭ ማስረጃ እርምጃ ይውሰዱ አይደለም፡፡
ባለራእይ ፈሪ አይደለም፣ የዋህም (ሞኝም) አይደለም፣ የያሚበላሹትንና ወደንስሐ ለማይመጡት እንደሙሴ ጨካኝ ነው፡፡ እንደእርጉዝና ገበያ ላይ እንደማይጣላው እንደ እንቁላል ነጋዴም ጠንቃቃ ነው፡፡ እርጉዝ ከለጊዜው እንዳትጨነግፍ በገበያ አትጣላም፡፡ የእንቁላል ነጋዴም እንደዚሁ እንቁላሉ እንዳይሰበርበት አብዝቶ ይጠነቀቃል፡፡ እነሊቀማእምራን የማነ ከየት ወገን ናችሁ? ጥቅምትንና ግንቦትን በመፍራት ለመሸጋገር ወይስ በሐቅና በእውነት ላይ ተመስርታችሁ ተገቢውን ፍትሕ በቤተ ክርስቲያን ለማስፈን በመጨከንና በመጠንቀቅም በመጓዝ ቤተክርስቲያኒቱ ያሉባትን ችግሮች ለመቅረፍ ሕዝቡንና አገልጋዩን ከጥቂት ግፈኞችና ዘራፊዎች ነጻ ለማውጣት ነው የምትሰሩት? መልሱን ለእናንተ እንተዋለን፡፡
በቅርብ ጊዜ ካስተዋልነው አንጻር አንድ ነገር ማለት እንችላለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሰላቸትና ሥራውን ተወት የማድረግ ነገር ይታያል፡፡ በተለይ ዋና ሥራ አስኪያጁ፡፡ ትናንትና በቁጭት ተነሳስታችሁ የካህናቱን መንገላታት ተመልክታችሁ ወንበር በማዘጋጀት የጀመራችሁት መልካም ጅምርና ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ ግልጽ ታዛቢ የሌለው እስኪመስል ድረስ በየክፍለ ከተማው ተከፋፍሎ ለመግባት ተራውን ጠብቆ ለመስተናገድ ሠራተኛው በሳምንት አንድ ቀን ለሚያገኛት ጠዋት በብርድ እየተጠበሰ፣ በትራንስፖርት ወጪ ዋጋ እየከፈለ ጦሙን እየዋለ አስቀድሞ መናገር ሲቻል የማታ ማታ ስራ አስኪያጁ ሌላ ቦታ ለጉዳይ ሄደዋል አይመጡም ወደየሥራችሁ ሂዱ  እየተባለ ለእንግልት እየተዳረገ ነው ያለው፡፡ በጠዋቱ አይመጡም ተብሎ መናገር ሲቻል ባለጉዳይ እንደ ታቦት ጠባቂ ሲንከራተት እየዋለ ያለፍትህ በሐዘን ወደቤቱ ይመለሳል፡፡
እናንተም ብትሆኑ የምትሰሩትን ሥራ በፐርሰንት ብትለኩት ምን ያህል እንደ ወረደና እንደ ቀነሰ ታስተውሉት ነበር፡፡ በእውነት በቃል አለመገኘት ታማኝ አለመሆንና አድሏዊነት ያሳዝናል፡፡ አንዳንድ አምባገነኖች ጉዳያቸውን በርቀት ሲያስፈጽሙ ምስኪናን ግን ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ከስክሰው እንኳን ያለፍትህ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት ማለት ይህ አይደለምን? ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ በቀን በሥራ ሰዓት ሳይሆን በማታ በጨለማ መሥራትና “የተመረጡ ሰዎችን” በማታ ማስተናገድ ለምን ይሆን? ለጽድቅ? ወይስ …. መጽሐፍ “እስመ ዘእኩይ ምግባሩ ይጸልእ ብርሃነ ከመ ኢይትከሠቶ ምግባሩ” የሚለው እንዳይሆን  ሥጋት አድሮብናል (ዮሐ. 3፥19)፡፡ 
ምንም እንኳን በማታ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብለን ሙሉ በሙሉ ባንደመድምም ሕዝብ በሌለበት አቤቱታ ሳይሰሙ በማታ የተፈቀደላቸውን ሰዎች ብቻ ማስተናገድ ምን ይሉታል? ባለፈው አባ ሰላማ ላይ በተፃፈው ጽሑፍ ለሥራ አስኪያጆቹ ፕሮቶኮሉ አይፈቀድላችሁም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ አብራችሁ  የምትውሏቸው ሰዎች አይጠቅሟችሁም ተብሎ ነበር፡፡
ምክትሉ አዋዋላቸውን ቢያስተካክሉም ዋናው ግን በእልህ ማንን የጎዱ መስሏቸው እንደሆነ አይታወቅም ብሶባቸዋል፤ ይቀጥሉበት ውጤቱ እዚያው ያገኙታል፡፡ አንድ መሪ ከሕዝብ እየተገለለ ከጥቂት ወዳጆቹ ጋር ብቻ የሚውል ከሆነ እንዲህ ዓይነቱ ሰው አገልጋይ መሆኑ ይቀርና፣ በአጠገቡ ያሉ አጥፊ ወዳጆቹ በግብዝነት እያሞካሹ ሲጠልፉት ወደ ተገልጋይነት እንደሚያድግ ጥርጥር የለውም፡፡ ሌላው በሙዳየ ምፅዋት ቆጠራ ላይ በሚታየው ብክነት ሊቀ ምእምራን ምን ያህል ቆራጥ ይሆኑ ይሆን? እርምጃስ ይወስዳሉ ወይስ ሆዳቸው ይላወሳል? ተብሎ ተገልጾ ነበር፡፡ እውነትም እንደተባለው የጻፉትን ደብዳቤ ለመከታተል አቅም አጥተው መጨከን ሲያቅታቸው ተስተውለዋል፡፡ በአንፃሩ ግን ለመንግሥት ያላቸውን ታማኝነት ለማረጋገጥ ሲሉ የሠራተኛው ደሞዝ በባንክ እንዲከፈል ለማድረግና ከዚያም የሥራ ግብር ለማስቆረጥ ሲባል አፈፃፀሙን በሥነ ሥርዓት እየተከታተሉት ነው፡፡ ለዚህ የሰጡትን ትኩረት ለሌሎቹም ውሳኔዎቻቸው ቢሰጡ ከዚህ የበለጠ ለውጥ በቅርብ ጊዜ እናይ እንደነበረ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
በመጨረሻም ከሰሞኑ እየተሰሙ ያሉት ነገሮች አስደሳች አይደሉም፡፡ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ሩጫውን ጨርሻለሁ ዓይነት እያስወሩ ነው፡፡ በመሰረቱ እርቅ ባይጠላም ቤተክርስቲያን ውስጥ በማቅና በቤተክህነት መካከል ያለው አለመግባባት የባልና ሚስት ጥል ይመስል ሊቀ ምዕምራን የማነ በግላቸው ከአንዳንድ ማህበራት እየታረቁ ነው የሚባለው ከምን የመነጨ ነው? አድርገዉት ከሆነ ለመጣላት ሲሆን በሕብረት መቆም፣ ነገር ግን በግል ሹልክ ብሎ መታረቅ ከስህተትም ስህተት ነው፡፡ ከቅዱስ ፓትርያርኩ እስከ በሀገረ ስብከቱ ያሉ የመመሪያ ኃላፊዎች ክብራቸውንና  መልካም ሰብእናቸውን ያዋረዱ ጽሑፎች መጻፋቸው አይዘነጋም፡፡ እርቁ ይሁን ቢባል እንኳን ይቅርታው ከቅዱስ ፓርትርያርኩ ነው መጀመር ያለበት፡፡ እንደ አባትም እንደ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንም መሆን ያለበት በዚህ መንገድ ነው፡፡
እንደ አጠቃላይ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ተልኮአቸው እንደ ስማቸው ለሁለት ወገን አምባሳደር ሆነው እንደ ሐመሩ “ሐ” ፊደል ሦስት ቦታ ተመድበው ይሠራሉ፡፡ ለማቅ፣ ለኢሃዲግ እና ለሊቀ ማዕምራን የማነ፡፡ ለየትኛው ክለብ የበለጠ እንደሚያገለግሉ ግን በቀጣይ ውጤቱን አይተን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻ ከላይ የጠቀስናቸው ግድፈቶች ቢኖሩም የተሰሩትን መልካም ሥራዎች እየካድን አይደለም፡፡ ከሊቀ ማዕምራንና ከመጋቤ ብሉይ አዕመረ የተሻለ ሰው ይምጣ እያልንም አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደ እነ አባ ነአኩቶ ያሉ ወንበዴዎች “በሩን ከፍተነዋል የሙስና መንገዱን ጠርገነዋል” እያሉ በየመሸታ ቤቱ የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ እና ከላይ የተጠቀሱት ግድፈቶች ሁሉ በጥንቃቄ ተጠንተው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ አድባራት የሚፈጸመው አድማ የማቅ ወገን (ቡድን) አባል ያልሆነ ሰባኪ በጩኸትና በአድማ እንዲነሳና እንዲታገድ ይደረጋል፡፡ በሀገረ ስብከቱም የአድመኞች ጩኸት ስለበዛ ሰባኪው እንዲዛወር ይደረጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ወደቦታው ሊመለስ ይችላል፡፡ ሊሆን የሚገባው ነገር ግን በመጀመሪያ ሰብእና የሌላቸው አለቃና ጸሐፊ በማቅና በሰንበት ተማሪዎች ተገፋፍተው ሰባኪን በሚያግዱት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ አለቃና ጸሐፊ ከማቅ ወገን ገንዘብ እየተቀበሉ ለሰባኪዎች ሥቃይና መንገላታት መሳሪያ እየሆኑ ስለሆነ ሀገረ ስብከቱ በአንክሮ ተመልክቶ ሊያስተካክላቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ማቅ መልኩን ቀይሮ በአዲስ እስትራቴጂ ስለመጣና በየጊዜው አካሄዱን እየለዋወጠ ስለሚገለጥ እናንተም አዳዲስ ንቃትና አዳዲስ ብልሃት ይዛችሁ አሰራሩን ልታከሽፉት ይገባል እንላለን፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት

10 comments:

 1. አባ ሰላማዎች እንግዲህ አትንጫጩ! ቤተክርስቲያኒቷ የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን የንጽዕተ ንፁአን ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ላይ ነች! ሰአታቷንና ቅዳሴዋን እያከናወነች ነው! አትረብሻት!!!

  ReplyDelete
 2. የካህናት አስተዳደር የሆኑት አባ ህሩይም “እገሌ ሊቀየር ነው ያንን ቦታ ከፈለግህ ይህን ያህል ክፈልና ቦታውን ታገኛለህ” እያሉ በአንድ በኩል ከእዚህ በሌላ በኩል ደግሞ እንዳትቀየር እናደርጋለን ግን ይህን ያህል ክፈል እያሉ ከሁለት ወገን ጉቦ እየተቀበሉ በቀደመ ስራቸው እየገፉበትና የሀገረ ስብከቱን መልካም ጅምር እያበላሹት ይገኛሉ፡፡እኚህ ሙሰኛ ለውጥ ከመጣ ወዲህ የሙስናው በር ስለተዘጋባቸው “ምንም ስራ የለም ወደ አለቅነት መልሱኝ” በማለት ያለጉቦ መኖር እንደማይችሉ አፍ አውጥተው እስከ መናገር መድረሳቸው ከእኛ ስውር አይደለም፡፡ በተለይም በቅርቡ ከጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት የአለቆች ዝውውር ይደረጋል የሚል ወሬ በመንዛት ወደተሻለውና በደንብ ወደሚበላበት ደብር ለመዛወር የቋመጡ እንደዚሁም “እንቀየር ይሆን ወይ” የሚለው ስጋት ያደረባቸው አለቆች አባ ህሩይን ደጅ እየጠኑ ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. ሌላው ሰው ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት በአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና አስተዳደር ሲሆኑ ከዚህ በፊት የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ በጣም ለሙስና የተበገሩ ሰው ሆነው በመገኘታቸው ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በእድገት ሲዛወሩ ብዙ ሰውአዝኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የነበራቸውንመጥፎ ስም በመሸፈንበአሁኑ ጊዜ ከነአኩቶ ለአብ ክፉ ሥራ ተጠላልፈው በዘረኝነትም በጉቦም አብዝተው እየታሙም እየሠሩም ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ነገር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምን ይሆን የተቀበረበት? ሙስና ካልሠሩ አይጸደቅም የተባለ ይመስል ወይም ካልሰረቁ ልጅ አያድግም የተባለ ይመስል መልካም ሰብእና የነበራቸው ሰዎች በዕድሜ እየበሰሉ ሲሄዱ እንደ ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት ያሉ ሰዎች ኃጢአት ነውርን በመጥላት ፈንታ አስቀድመው በጠሉት ነውርና ሙስና ተጠላልፈው ሲወድቁ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም ከአባ ነአኩቶና በክፍለ ከተማው ካሉ ደላሎች ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን አንዱን ጉቦ ተቀብለው ከሚገባው በላይ በማሳደግ ወገንና ገንዘብ የሌለውን ደግሞ ርስቱን ማስነጠቅን ተያይዘውታል፡፡ ፍርዱ ከእግዚአብሔር ይጠበቃል፡፡

  ReplyDelete
 4. “ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።” (አሞጽ 5፥12-13)፡፡

  ReplyDelete
 5. yih tsihuf ye mahiberekidusan woyim ye Eritrea Eji Alebet...........kikikiki .....Ento Fento As usual.

  ReplyDelete
 6. First of all you represent yourself not Addis Ababa betkinhet kahnet! The very fact you appreciated Abba Selama which oppose the dogma of “ the intercession of the st Maraiam and the saints” of EOTC put your belief in question!
  Second you are afraid to blatantly say that business goes as usual in Addis Ababa hagere sebekt with corruption and favoritism, but yo indirectly said it and questioned the capability of Lkememehren Yemane!
  Third you accused MK as if being MK is a sin while you give due to respect to Abba Selama. Mk does not enter in your context. You brought Mk here only to attack Memeher Tagaye and Lekememehren for “making peace with MK" .
  Third you wanted Lekememheran to attack for individuals like Memeher Solomon Bekele.
  Fourth you want Lekememhren to stop transfer of preachers that are considered incompetent and heretic by sunda yschool students and the believers as a whole. (Is the church only for the clergy? What did St paul said on this topic)
  If you have genuine concern on fighting corruption and you believe in dogma of EOTC, this is not the right place. Second as a Christian you are expected to pray for your enemies and attacking individuals you hate without proof is not acceptable. You have to forward with proving document to the concerned bodies of EOTC believing God will stand with you and truth will prevail. I have seen spiritual braveness from our children in Sunday school who stood all intimidation! Feedback on performance of Addis Ababa Hagere Sebeket can be sent directly to them.
  After corruption, the second issue that has to be addressed are reconciling conflicting parties and individuals. In this direction a peace and reconciliation committee shall be established in EOTC that will reconcile conflicting parities by pinpointing not repeat the major mistakes o the mistakes they have committed. . If the mistake is on religious dogma the committee will make sure they have repented and give them probation period. After that it will put wegzet on all blogging sites that wrote allegation on individuals, association and institutions !
  Had we have done this before the rain would have been normal!
  Amen

  ReplyDelete
 7. ጽሑፋ ከሞላ ጎደል በጣም ጥሩ የሆና በእውነት ላይ የተመሰረተ ዘገባ ስለሆነ ፀሐፊው ሊመሰገን ይገባዋል።ነገር ግን አቶ ወ/ሰንበት የክፍለከተማ ሥ/አስኪያጅ በነበረበት ጊዜ ሙስና የሚፀየፍ ጠንቃቃ ነበር ማለት ምን ማለት ነው? ማ ሆነናነው የሙስናዋ መሃንዲስ ለመሆኑ ይኽ ሰው ታውቁታላችሁ? ከ985ዓ/ም ጀምሮ በተለያየ አጋጣሚ ወደ ሀገረ ስብከቱ እተመላለሰ የሙስና ስልጠና እየሰጠ ያለው ማነው? አሁንስ ቢሆን ከአ/ጉ/ ክፍለ ከ/ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሲዛወር ባለው የጉቦ አቀባባይነት ልምዱ ተመርጦ አይደለም እንዴ በሰው ኃይል አስተዳደር የተመደበው? እንግዲያ በየተኛው እውቀቱ ተመዝኖ ነው? በማኔጅሜንት ትምህርቱ ነው ወይስ በቤተ ክርስቲያን አውቀቱ ነው? "ለእመ ይመርሆ ዕውር ለዕውር ክልኤሆሙ ይወድቁ ውስተ ግብ " እንዳይሆን ነገሩ ልብ ያለው ልብ ይበል።

  ReplyDelete
 8. Great minds discuss Idea,
  Average minds discuss Events and
  Small minds discuss People!

  ReplyDelete
 9. ቤተክርስቲያናችን እጅግ ከምንወዳት ከእናታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ማሪያምም ፍልስታ ጾም በኋላም ሆነ በፊት እጅግ በፀጥታና በእርጋታ ምእመናንን ይዛ ወደ አምላካችን መንግስት የምትጓዝ አገራችን ቤታችን ናት!!!!!! ማንም አይበጠብጣትም። የበጠበጧት መስሏቸው እንዳላችሁት በየመሸታ ቤቱ የሚወሸክቱ እነሱ በጣም በጣም በጣም ሰነፎች፣ ስንፍናቸው መለኪያ የማይገኝለት እግዚአብሔርን የማያውቁ ካለቦታቸው የገቡ ወንበዴዎች እርሱ እራሱ ባለቤቱ በጊዜው እስኪቀጣቸው ድረስ የሚሰሩት ነገር ልክ የሚመስላቸው ቀዥቃዦች ናቸው። ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን ሰዓታቷንና ማህሌቷን በፀጥታ እያከናወነች እናታችንን ታመሰግናለች። እነሱም የፍርድ ጊዜያቸውን ያፋጥናሉ።

  ReplyDelete
 10. አይመረን አድናለሁ ብላችሁ ቀድሞውንም የየማነን ሌብነት መደበቅ ፈለጋችሁ።ለመሆኑ አጥቢያ ላይ ማን ነው ከየማነ በላይ ሲዘርፍ የነበረው። ሰለሞን በቀለ እኮ የማነ እግማምቶ የተጫወበትን ህንጻ በጥንቃቄ ጨርሶ ፍጻሜ ላይ አድርሶታል።እንዲያው የከተማና የመሀል ሀገር ሰዎችን ሆን ብሎ ለመቃወም ይመስላል ።መቼም ሸዋ መጥቶ ነው ሁሉም እድፉን ያራገፈው።

  ReplyDelete