Tuesday, August 18, 2015

በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ማቅ የጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ሊያደርገው ያሰበው ት/ቤት ታገደበትየደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ችግሮችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በመረጃዎች የተደገፉ ዘገባዎችን ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ችግሩ ስለሌለ ሳይሆን የማቅ ጥቅም ስላልተነካ ሐራ በጉዳዩ ላይ ዝምታን መርጣ ነው የከረመችው፡፡ አለቃው አባ ገብረ ሚካኤል በሙስናና በስነምግባር ብልሹነት ውስጥ የተዘፈቁ ቢሆንም አሁንም በደብሩ ውስጥ ሰልጥነናል ያሉ ዕድሜያቸው ከሰንበት ት/ቤት የዕድሜ ጣራ የዘለለ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ተስማምተው የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱና ለማቅም ምቹ ሁኔታዎችን ስላመቻቹ ሐራ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝምታን መርጣ ቆይታለች፡፡ ሲያልቅ አያምርምና አለቃውና የማቅ ቡድን የሆኑ በሰበካ ጉባኤ፣ በሰንበት ት/ቤትና በህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ውስጥ የነበሩ አባላት ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ጉዳቸውን መዘካዘክ ያዙ፡፡ አለቃውም መታገድ አለባቸው ያሉትን አገዱ፡፡ ለሀገረ ስብከቱም አሳወቁ፡፡ ይህን ተከትሎ አማሳኙ የማቅ ቡድን ከአለቃው ጋር እርቅ ቢጤ በማውረድ ከእርቅ መልስ ጮማ ወደሚቆርጡበት መጠጥ ወደሚጠጡበት ቦታ ተያይዘው ሄዱ፡፡ አለቃውም ለታገደው በተለይ ለሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር እግዱን አነሳልሃለሁ ብለው ተስፋ የሰጡ ቢሆንም ጉዳዩ በሀገረ ስብከቱ የተያዘ ከመሆኑ አንጻር በቀላሉ የሚነሳ አልሆነም፡፡
በዚህ መካከል ያረጀ ቢሆንም አባቷ ደጀሰላም ድረገጽ የሚጠቀምበትን ስልት እርሷም መጠቀሙን ተያይዛዋለች፡፡ ከዚህ ቀደም ማቅ ከካዝናው እየዛቀ በሚያፈሰው ገንዘብ የተቆጣጠራቸውን የግል ፕሬሶች ውጤቶችን በመጠቀም ዘገባዎች እነርሱ ላይ እንዲወጡ ካደረገ በኋላ ደጀሰላም እነርሱን ምንጭ አድርጎ ይጠቀም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜም የፕሬስ ውጤቶቹ ከደጀሰላም ዘገባዎችን በመውሰድ እየተናበቡ የማኅበረ ቅዱሳንን ትግል ሲታገሉ ቆይተዋል፡፡ ሐራም ይህን “የተበላ” ስልት መጠቀሟን ቀጥላለች፡፡ አዲስ አድማስን፣ ኢትዮ ምኅዳርንና ሰንደቅን በዚህ በኩል እየተጠቀመችባቸው ነው፡፡ በቅርቡ ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ከፍለው ዘገባ ያሰሩትና የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን በየቤተሰብ ተደራጅተው እየቦጠቦጡ ያሉት የማቅ ቡድን አባላትና ደጋፊዎች እውነቱን ለማድበስበስ ሲጥሩ ታይቷል፡፡ እጅግ በሚዘገንን የእምነትና የሥነምግባር ችግሮች ውስጥ የሚገኙትንና አንዳንድ በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ት/ቤትና በሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ውስጥ ያሉትን አባላት ጻድቃን አድርጎ ሲያቀርባቸው በበላበት መጮኹን አስመስክሯል፡፡ ሐራ ጋዜጣውን ጠቅሳ በሙዳየ ምጽዋት የሚሰበሰበውን ገንዘብ በአግባቡ በመጠቀም እና የራሳቸውን አስተዋፅኦ በማከል ሥራው አኹን ለሚገኝበት ደረጃ ያበቁት የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው አባላት ትጋት እና ታማኝነት በአጥቢያው ምእመናን የሚጠቀስ ነው፡፡” ብላለች፡፡ (የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ!) ሕዝቡ እያለ ያለው የሕንጻው ሥራ ከሚፈለገው በላይ ዘገየ፡፡ እጅግ በርካታ ሚሊየን ብር ተበልቶበታል ነው፡፡
በዚህ ውስጥ ሐራ ጊዜውን ጠብቃ እውነትን ለመግለጥ ሳይሆን የማቅ ሰዎች በክፉ ሥራቸው ስለተጋለጡ (ስለተነኩ) ብቻ የእነርሱ ገበና የተሸፈነ መስሏት የተናገረችው አንድ እውነት ብቻ ሲሆን እርሱም አለቃው “ባለትዳሩ መነኩሴ” አባ ገ/ሚካኤል በብዙ የሥነምግባርና የሙስና ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ መሆናቸውን ነው፡፡ አለቃው እንዲህ ከሆኑ የቅርብ ጓደኞቻቸው የነበሩትና አብረው ሲዘርፉ ሲበሉ ሲጠጡ የነበሩት ከዚህ ነጻ ናቸው ማለት አይታሰብም፡፡ ለማንኛውም ሀገረ ስብከቱ አንድ መፍትሄ በመስጠት የደብሩን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንዳለበት የሁሉም ተስፋ ነው፡፡ 
ሰንደቅ ጋዜጣና ሐራ በመጠቃቀስ በጅምላ ያሞገሷቸው አንዳንድ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ አባላት እንደተሞገሱት ታማኝና ታታሪ አይደሉም፡፡ ይልቁንም እነዚህ የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ የዘረፉ ሰዎች በአምልኮተ ጣኦት ውስጥ የሚገኙና በአጋንንታዊ አሠራር የተጠላለፉ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም እስጢፋኖስ ኃይሉና የትናየት ኃይሉ በመርቆርዮስ ጽላት ቦታው ላይ ማሟረታቸው እንደሚታወቅ ጠቅሰናል፡፡ ደብሩን እንደልባቸው የሚያሾሩት  የሀይሉ መላኩ ቤተሰቦች እቤታቸው ውስጥ ያውም ምድር ቤት ውስጥ ማንም ሰው የማይገባበት ቡና ብቻ የሚፈላበት፣ ለጣኦት የሚሰዋበት ክፍል እንዳላቸው በአካባቢውና በደብሩ ሰዎች የሚታወቅ ነው፡፡ እናታቸውም አሁን አልጋ ላይ ውለው ባለባቸው ውቃቢና ዛር ልጆቻቸውን በዚሁ ምድር ቤት እየሰበሰቡ እሮብ እሮብ ይካድማሉ፡፡ ቀለበት መንገዱ መጥቶ የቆመው በራቸው ላይ ሲሆን እሱን እንዳይነካባቸው ያላወጡት ገንዘብ አልነበረም፣ ይህን ያደረጉትም አካባቢውን ላለመልቀቅ ሳይሆን አምልኮአቸው እንዳይነካባቸው ነው፡፡ ማቅ ድጋፋቸው እንጂ ሃይማኖታቸው ስለማያሳስበው እንደእነዚህ ያሉትን ወደቀናው መንገድ ለመመለስ ያደረገው ጥረት የለም፡፡ ነገር ግን በሥነ ምግባር የታወቁ ናቸው ሲል ምስክርነት ሰጠላቸው፡፡
በነአቶ እስጢፋኖስ እየተሰራ ያለው ቤተልሔም እውነት ጌታ ሊከብርበት ነው? ከዚህ ይልቅ በመርቆሬዎስ ጽላት እና አቤታቸው ምድር ቤት ውስጥ ያለውን በሳምንት እሮብ እሮብ የሚካሄደውን አምልኮ መተው አለባቸው፡፡ ለንስሐ ሲዘጋጁ ብቻ ቦታው ላይ ሰላም እንደሚወርድ አያጠራጥርም፡፡
ሌላም ሌላም ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም ከዚህ ቀደም የዘገብነውን በማስተዋስ በዚሁ እንለፈውና ጥቅሙን ብቻ በማሳደድ ላይ ያለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ስራ ከደብሩ ት/ቤት ጋር በተያያዘ እንጥቀስ፡፡ ት/ቤቱን ደብሩ ማስተዳደር ቢሳነው ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለማቅ ያደሉ የሰበካ ጉባኤው አባላት ጎርጎርዮስ ት/ቤት እንዲጠቀልለው አደረጉ፡፡ ሆኖም በሀገረ ስብከቱ ትእዛዝ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጎ ጎርጎርዮስ አሸነፈ ተባለና የጎርጎርዮስ አጸደ ሕጻናት አካል ሆነ፡፡ ስግብግብ ነጋዴው ማቅ የድሃ አደግ ልጆች እንዳይማሩ ወርሃዊ ክፍያውን 1200 ብር በማስገባት ማስታወቂያ ለጠፈ፡፡ በዚህም  በነጻ የሚማሩና መክፈል ያቃታቸው ወላጆች አዝነዋል፡፡ በነጻ ሲማሩ የነበሩ ልጆች እጣቸው ምን ይሆን? የአካባቢወ ሀብታም ነን ባዮች ከህንጻው ሲዘርፉ ተጨማሪ የምስኪኖችንም ጊዜ ጉልበትና የመማር ዕድላቸውን ጭምር ዘርፈዋቸዋል፡፡ እጅግም ጨክነውባቸዋል፡፡ ባስልዮስ “ቤተ ክርስቲያን አሳዳጊ የሌላቸውን ድሆችን ልትረዳቸው ይገባል” ያለውን በወሬ የቅዱሳን ወዳጅ ነኝ ባዩ በተግባር ግን አርኣያቸውን የማይከተለው ማቅ ትክክለኛ ማንነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ደስ የሚያሰኘው ነገር ማቅ እንዲረከበው የተደረገው ት/ቤት ማቅ ባደረገው ከፍተኛ የገንዘብ ጭማሪ ምክንያት ታግዷል፡፡ እግዱ በማቅ ላይ የተጣለው ከአካባቢው ነዋሪዎች አቅም በላይ የሆነ ክፍያ ማስከፈል በመጀመሩ፣ ሳያስፈቅድ ባነር በመለጠፉ እና 18 መክፈል የማይችሉና የነጻ የትምህርተ ዕድል የተሰጣቸውን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ በማስወጣቱ አቅም የሌላቸው ወላጆች ለወረዳው አቤት በማለታቸው የእነዚህ ወላጆች ጥያቄ ሳይመለስ ት/ቤቱ መቀጠል እንደሌለበት በመወሰኑ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በሰሚት መድኃኔ ዓለም የተከሰተውና ማህበረ ቅዱሳን አለልክ ሲያስጮኸው የነበረው ሰለሞን ሙሉጌታ የሀብታም ልጆችን ብቻ ነው የሚያስተምረው በሚል ነበር፡፡ በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ግን ይህንኑ ስህተት ማቅ ሲደግመውና የድሃ ልጆች ተባረው 1250 ብር መክፈል የሚችሉ እንዲማሩ ለማድረግ ዱብ ዱብ ሲል እንደ ችግር አልታየም፡፡ ምክንያቱም ማቅ እስካደረገው ድረስ በማቅ መንደር ማንኛውም ችግርና ክፉ ነገር ሁሉ ትክክል ነውና፡፡ 
የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት በቤተ ክርሰቲያኑ ቅጽር በሃይማኖት ካባ ፖለቲካዊ አላማ ያላቸው ሰዎች በየጊዜው ስብሰባ እያደረጉ ለረብሻ ሰዎችን እያደራጁ መሆናቸውን በመግለጽ በተለይም ከዚህ ቀደም በ97 ዓ.ም ታስሮ በአሁኑ ጊዜ ሃይማኖት ለበስ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ፓርቲ ደጋፊ የሆነው እንደ ሻለቃ ጣሰው ያሉ  ግለሰቦች ችግር እየፈጠሩ በመሆናቸው ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳያደርጉ አስታውቋል፡፡ እንደ ሻለቃ ጣሰው ሁሉ ሌሎቹም የአካባቢው ሃብታሞች በጥንቆላና በሟርት የሠበሰቡትን ብር አመጽን ለማደራጀት እየተጠቀሙበት መሆኑ በገሃድ ታይቷል፡፡

3 comments:

 1. ሣማዎች በሉ ሃሜታችሁን ንዙ
  የሚሰማችሁ ግን የለም

  ReplyDelete
 2. የተሸፈነች እወነት በተገለጠች ጊዜ እንደ ሣማ እንደምታቃጥል መረዳትህን ተረድቼልሃለሁ

  ReplyDelete
 3. እናንተ ምን አገባችሁ እናንተኮ መናፍቅ ናችሁ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ደግሞ የኦርቶዶክሳውያን ጉዳይ ብቻ ነው .......አይ እነ ሰሎሞን ዮሐንስ

  ReplyDelete