Thursday, August 20, 2015

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር ቸሬ አበበን ከሥራ አሰናበተ


ከመምህር ቸሬ አድራጎት የምንረዳው አብዛኞቹ የዋሃን አባላቱ ሳይሆኑ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ትክክለኛ ዓላማ የገባቸውና ዓላማውን ለማስፈጸም የሚሰሩ አባላቱ ተሰግስገው ባሉበት መንግስታዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ተቋም ውስጥ ተመሳሳይ ድርጊቶችን እንደሚፈጽሙ ነው፡፡ በቸሬ የስንብት ደብዳቤ ላይ የተዘረዘሩት ጥፋቶች እነዚሁ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ዕለት ተዕለት የሚፈጽሟቸው ጥፋቶች መሆናቸው ከማንም ስውር አይደለም፡፡ የመጀመሪያው አሉባልታ ነው፡፡ ቸሬ በፓትርያርኩና በአቡነ ጢሞቴዎስ መካከል ጠብን ለመዝራት የሄደበት መንገድ ከዚህ ቀደም የማኅበሩን ዕድሜ ለማራዘም ማኅበሩ ከተጠቀመባቸው ስልቶች መካከል እውነታዎችን ገልብጦ ማውራት በኃላፊዎች መካከል ልዩነትን መፍጠርና ከተቻለ ማጣላት አንዱ ስልት ነው፡፡ ይህን በዌብ ሳይት ጭምር የሚጠቀሙበት ስልት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሐራ የተባለው የማኅበሩ  እንደሆነ የሚታመነው ብሎግ አንድን ክስተት ገልብጦና የተደረገውን አዛብቶ በማቅረብ ይታወቃል፡፡ በቅርቡ እንኳን ስለ ሊቀ ሥዩማን የማነ የጻፈው ሥራ አስኪያጁን ከፓትርያርኩና ከመንግሥት ለማጋጨት ያለመ ቢሆንም “ልቦለዱን” ያቀረበበት መንገድ ግን ማንንም የማያሳምን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡

ከዚህ ሌላ ቸሬ የኮሌጁ ሬጂስትራር ሆኖ ሲሰራ ለማቅ ሰዎች ዲግሪና ዲፕሎማ መቸብቸቡና ማደሉ ሳያንስ ማቅ በአንድም  በሌላም መንገድ በጥላቻ የሚያያቸውን የኮሌጁን ተማሪዎች የሚበቀልለት እርሱ ነበር፡፡ ቸሬ በመ/ር ባህሩ ተፈራ ላይ የፈጸመው ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በሌላ መንገድ ምንም ማድረግ ባይችል ጋዋን በመከልከል መ/ር ባሕሩ በምረቃው መርሀ ግብር ላይ እንዳይታደም በማድረግ የስነ ልቦናና የሞራል ጉዳት ለመፍጠር ሞክሯል፡፡በዚህ መንገድ ማቅ ተሐድሶ ብሎ የፈረጃቸውን ተማሪዎች የሚያሳድድ ሲሆን ሞራላቸው እንዲነካ በማድረግ ብዙዎች ላይ ግፍ ፈጽሟል፡፡ በዚህ ረገድ ከመምህር ግርማ በቀለና መ/ር ጽጌ ስጦታው እስከ ዲ/ን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል ድረስና ከዚያም በኋላ በብዙዎች ላይ የፈጸመውን ግፍ መጥቀሱ በቂ ነው፡፡ ይህ ለማቅ እግዚአብሔርን እንደማገለገል የሚቆጠር “የጽድቅ ሥራ” ሲሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ግን አብንና ወልድን ካለማወቅ የተነሳ የሚፈጸም እንደ ሆነ በወንጌል ተጽፏል “እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።” (ዮሐ. 16፡1-3)፡፡
ቸሬን ከስራ ለማባረር ያበቃው ሌላው ጥፋት የኮሌጁን ዌብ ሳይት ያለ ኮሌጁ ዕውቅና ለሌሎች 3ኛ አካላት እንዲጠቀሙበት አሳልፎ በመስጠትና ኮሌጁን ለኪሳራ በመዳረጉ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጥፋት በአንዳንድ የማቅ አባላት ላይም ይታያል፡፡ በየተቀመጡበት የሥራ ኃላፊነት ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ መወጣት ሲገባቸው ኃላፊነታቸውን ለማቅ የሚጠቅሙ ስራዎችን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ይፈጽማሉ፡፡ ከምንም በላይ ማቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለራሱ ግላዊ ጥቅምና ድብቅ ዓላማ ማስፈጸሚያነት እንደሚጠቀምባት የቸሬ ተግባር ያመለክታል፡፡ ቸሬ ለቤተክርስቲያን ጥቅምነው የቆምኩት የሚለው የማቅ ሰው ሆኖ ሳለ በቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት እየተጠቀመ ለራሱ ጥቅም የቆመ መሆኑን አስመስክሯል፡፡ ማቅም ከዚህ የተለየ ተግባር የለውም፡፡ ስለ ቤተክርስቲያን ከእርሱ በላይ ያለ እስከ ማይመስለው ድረስ ራሱን የቤተክርስቲያን ብቸኛ ተቆርቋሪ አድርጎ ያቀርባል፡፡ በተግባር ሲታይ ግን ቤተ ክርስቲያኗን መጠቀሚያው እንጂ በእውነት የሚቆረቆርላት እንዳልሆነ ከስራዎቹ መረዳት ይቻላል፡፡

4 comments:

 1. እነማቆች(ማ.ቅ) ልቅ በሆነ ዲሞ መንገድና ከልክ ባለፈ የሥጋ ንግድ
  ቤ/ክርስቲያኗን መጠቀሚያ አደረጓት ነው እንጂ፤ ለሌላውም ቢሆን የሥጋዊ ጎጆ መቀለሻው ናት።
  ጳውሎስ ወደ ፩ ጢሞ ፮. ፭----፮ ይሬስይዎ ለጽድቀ እግዚአብሔር ተግባረ ቃሉንም እውነትንም
  እየለወጡ መናገጃ ያደርጉታል እንዳለ በዘመናችን ሁሉም ለሥጋው ተኝቶ አያድርም ዳሩ ግን አባ ሰላማና
  ተሐድሶ ከውነት ፈቀቅ ያላሉ አመለካክቶችን ለአንባብያን በማቅረባችሁ ትሞገሳላችሁ የጥበባት ፈጣሪም
  ጥበቡን ይፍጠርላችሁ አለን አለን ከሚሉት ፊቱን እንደሠወረ ፊቱን አይሠውርባችሁ።

  ReplyDelete
 2. አሁን ቸሬ መምህር ሊባል ይገባዋል! በእርግጥ በኮሌጁ ካሉት ኮታሞች መካከል አንዱ ተወገደ የሚለው ዜና አስደሳች ነው፡፡ እነ ፍስሐ፣መብራቱ፣አምሳሉ፣አባተ… እና መሳሰሉትን አፍርታ የአባ ጢሞቲዎስን አሸርጋጆችን ብቻ የሰበሰበችና የወለደቻቸውን ያሳደደች ኮሌጅ!!! ምን ምሁራን አለባት!! ጥቂቶች ቢኖሩም ለመኖር እንጂ ለለውጥ አልሰሩም ፣ አባ ቲሞቲ ያሳድዷቸዋልና ፡፡ ሰው የሌለበት መሆኑን ለማወቅ ብዙ አትድከሙ ለቸሬ የተጻፈውን ድብዳቤ አይታችሁ ትረዱታላችሁ፡፡ ዘበኛው መስፍን ያረቀቀው ይመስላል፡፡

  ReplyDelete
 3. በመጀመሪያ አባ ሰላማ የሚለውን ብሎግ ከፍቼ ሳነብ ደስ ብሎኝ ነበር የከፈትኩት፡፡ የአበሰላማን ታሪክ ጠንቅቄ ስለማውቅ፡፡ ለነገሩ በመዘንጋቴ ነው እንጂ የፊስ ቡክ ጓደኞቼ ብዙዎቹ ኘሮቴስታንትና ተሀድሶዎች ስለነበሩ የቤተክርስቲያንን ዜና ከየት እንደሚያገኙት በአንዳንድ አነጋገራቸው ላይ ይህንን ብሎግ ይጠቅሱ ስለነበር ምንጩን ተረዳሁት፡፡ ይሁንና ብሎጓ በመግቢያዋ ማስጠንቀቂያ መሰል ይዘት አላት ስድብ፣ነቀፋ፣ እንደማትቀበል በመግቢያው ላይ ይናገራል፡፡ ነገር ግን እናንተ የምትለጥፏቸው መጻጽፎች ምርቃት ናቸው? እኔ የምታስተላልፉት ዜናዎች ብዙ አይደንቀኝም፡፡ እንደውም ተግተን መጸለይ እንዳለብን ያነቃቃል፡፡ አሁን ይህ ዜና ለእኛ ምናችን ነው? የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ እስኪ ዜናዎቻችሁን የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ የሚነገርበት መድረክ ብታደርጉት እንዴት ባማረባችሁ ነበር፡፡ ግን ሊሆን አይችልም፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሔር ድንቅ ስራዎችን መናገር ለእርሱ መከራው ስለሆነ፤ ይህንን ያቀረባችሁትን ዜና ግለሰቡን ከመሳደብ ይልቅ ለምን ይህ ሆነ? እውነቱን መርምሩ የአንዳንድ ሰዎች ደካማ ጎን ለሌላ ሰው ትምህርት በሚሆንበት መንገድ ማስተማርና ለወንድሞች መጸለይ ነበር ወንጌል ያስተማረችን፡፡ ከሀዋርያት ሕይወት የምንማረው ይህንን ነው፡፡ እናንተ ማን የዘራችሁና የማንን ጉዳይ አስፈጻሚ ለመሆናችሁ ምንም አይነት መረጃ አያስፈልገውም ይህንን ብሎግ ብቻ ማንበብ በቂ ነው፡፡ ጌታ ለሐዋርያት ሲያስተምር በአህዛብ መንገድ አትሂዱ ሲላቸው ሰምተናል፡፡ የናንተን አይነት አካሄድ እኮ የሀገራችን የፓለቲካ ፓርቲየችና ማስታወቂዎች እየሄዱበት ያለው መንገድ ነው !! የሚገርመኝ አስተያየት የሚሰጡት ናቸው!! ብዙ ተሳዳቢ ደጋፊዎች አሏችሁ፡፡ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 4. አንድ ሰው ምንም ይሁን ከስራ መባሪሩ ምኑ ደስ ይላል? ይሄ ከሰባዊነት አንፃር ብቻ ቢታይ ትክክል ነውን? ከጤንነት መንፈስ የሚመነጭ ነውን? ይገርማል፡፡ ክርስትናስ ይህንን ነው የሚያስተምረው? ወዳችሁ አይደለም ማንነታችሁን የደበቃችሁት? ምስጢሩ ግልጽ ነው!! የምትሰሩት ስራ በህግ ስለሚያቀጣችሁ ነው! ለነገሩ በየትኛው የበረከት ስፍራ ላይ ተገኝታችሁ ቅንነትንና መልካም ነገር ይጠበቃል፡፡ አባቶቻችሁን እየተሳደባችሁ እና እየናቃችሁ በረከት የለም፡፡ ያልተባረከ ልጅ ደግሞ እንደይሁዳ እናቱን ያገባል፣ አባቱን ይገድላል፣ ጌታውን ይሸጣል፡፡ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete