Sunday, August 30, 2015

ያሬድ አደመና የማያባራ ሸፍጡ

ለእውነት የቆሙ ወንድሞች ከሓዋሳ

ቤተክርሰቲያን በብዙ ነገርየተሞላች ነች። ከበጎ ህሊና ተነስተው በጎውንአምላክ በእውነት የሚያመልኩናየሚገዙለት ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ከአእምሮዋቸው ጥልቅ ዋሻ ውስጥ ተዘርቶ የበቀለውን ክፋት እያንቆለጳጰሱ ለጠላት ዲያቢሎስ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተው ነገሮቻቸውን ሁሉ በተንኮል የመሰረቱ ብዙዎች አሉ። የእግዚአብሔር ወንጌል ሳይገባቸው ገባን እያሉ ኪዳኑን ሳይቀበሉ “ባለኪዳን” ሆነው በወንጌል ስም የሚያጭበርብሩ እንዲሁ አሉ።
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለታመነው ወንጌል የቆሙና ጌታን የሚያገለግሉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በየዋሁ ህዝብና በሚያድነው ቃል እየዘበቱ ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡም አሉ።  እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ አድርገው ለምድራዊ ጥቅም የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ የተጠሩበትን እውነት ትተው ያልተጠሩበትን ገንዘብ የሚያገለግሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግስት ሥራ እያስነቀፉ ይገኛሉ።

እውነተኛና የዋሃን የሆኑ አገልጋዮች ቢሳሳቱ ልባቸው ለመመለስ ቅርብ የሆነ ማንንም ለመጉዳት የማይሞክሩና ተስፋቸውን በጌታቸው ላይ የጣሉ ናቸው።ክፉዎቹ ደግሞ ሰላም የማይስማማቸው፣ እውነት የሚጎረብጣቸው፣ ተንኮል ካልሰሩበት ቀኑ የማይመሽላቸውናጌታን ከማገልገል ይልቅ ወሬ በማማታት ጊዜ የሚያጠፉ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለምን እንደተፈጠሩ፣ በማን እንደተለዩና ማንን እንደሚያገለግሉ ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ይልቁንም በዙሪያቸው ያለውን ሰው ሁሉ ካልነኩና ካላነካኩ ሠላም የማይሰማቸው ናቸው። ይህን መሰል ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳን ሲያገኙ ያለምንም ማቅማማት ማቅ የሚሆኑ ጴንጤ ሲያገኙ ዋና ባለጉዳይ ሆነው የሚገኙ ከተራማጅ ኃይሎች ጋር ራሳቸውን ለማመሳሰል ስንፍና የማይገኝባቸው ናቸው። ይህ የእስስት ባህሪያቸው የማንም ወዳጅ እንዳይሆኑ ማንንም ከልብ እንዳይቀርቡ አድርጓቸዋል። የሚያምኑበት እምነት እና የተመሰረቱበት እውቀት የላቸውም፡፡ ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ መሰረት አድርገው የሚነሱት ጥቅምን ነው። ጥቅም እስካገኙበጠዋት ተነስተው ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሌላ አልሰብክም ይላሉ። ከሰአት ደግሞ ከማርያም ውጭ ለማንም አልዘምርም ለማለት አይሰንፉም።
በሁሉም ነገር መሰረታቸው ጥቅም ነው። ለማያውቃቸው ሰው ስለ እነርሱ ብዙ ለማለት ድፍረት አይሰጡም። ከሁሉም ጋር ይመሳሰላሉ። በዚህ መመሳሰል ውስጥ ግን ልባቸው ከሚያገኙት ጥቅም ጋር እንጂ ከማንም ጋር የለም። ያምናሉ እንዳንል የእምነት ሕይወትና የአማኝ ልብ የላቸውም። አያምኑም እንዳንል አማኞች ካሉበት ሥፍራ እና መድረክ አይጠፉም።
በዚህ ባህሪ ከተያዙ ሰዎች መካከል የአንዱን ማንነት፣ ባህሪና ካደረጋቸው ክፋቶች አንዳንዶቹን ጠቅሰን ለመጻፍ ተገደናል።ይህን የምናደርገው ስም ለማጥፋት ብለን ሳይሆን የወንጌሉን አገልግሎት ከጥፋት መልእክተኞች ለመጠበቅ ባለብን ሃላፊነት ነው፡፡ አባ ሰላማ ብሎግም ይህን ከግምት አስገብታ ጽሁፉን እንደምታወጣልን እናምናለን።ይህ ግለሰብ ለቤተክርስቲያኒቱ በጎ ለውጥ ከሚታገሉ ወንድሞች መካከል ተወሽቆ ብዙ ነገሮችን እየፈጠረና እያበላሸ ይገኛል። ለምክር የማይመችና የሚፈልገውን ጥቅም እስኪያገኝ ድረስ ወደ ኋላ የማይል ሰው ነው። ስለ ሰውየው ማንነት አንባቢ የራሱ ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ ይህን ጽሁፍ ጽፈናል። ይህ ሰው ያሬድ አደመ ይባላል።

ያሬድ አደመ እንደ አየሩ ሁኔታ የሚገላበጡና እየተገላበጡ ያሉ ሰባኪ ወንጌል ሳይሆኑ እንቅፋተ ወንጌል ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ያሬድ አደመ እንደ ንጉሱ አጎንብሱ የሚለውን ተረት እንጂ  ለእውነት ቃል ራሳችሁን ለዩ የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል ያልተረዳ ሰው ነው። ለገንዘብ ያለው ፍቅር የተለየ ነው። ገንዘብ የሚያስገኝ ከመሰለው የተፈለገውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። በዚህም ምክንያት ጥቅም እንጂ ፍቅርና ወዳጅነት አያውቅም ይላሉ የሚያውቁት።
“ላዕከ ወንጌል” ያሬድ (ልቡንና የልቡን የሚያውቁ ሰዎች ላዕከ ወንጀል ይሉታል።) የአካባቢውን ሁኔታ አይቶ የሚሰብክወንጌል እንሰብካለን ብሎ በወንጌል ስም ቢዝነሱን የሚያጧጡፍ እና ወንጌልን በወንጀል በመቀየርሰብዕናውን የገነባ ክፉ ነው፡፡ ላእከ ወንጀል ያሬድ አደመ ከአዋሳ እስከ አዲስ አበባ በወንጌል እሰብካለሁ ስም ከትናንት እስከ ዛሬ የወንጌል አገልግሎትን ሲያበላሽ የኖረና በማበላሸትም ላይ የሚገኝ ሰው ነው፡፡
ላዕከ ወንጀል ያሬድ፣ ገልጦ የሚያነብለት ጠፍቶ ነው እንጂ ሕይወቱ የነውር መጽሔት ነው። የያሬድ ነውር በትንሹ ሀያ አመት ያስቆጠረ ሲሆን ግለሰቡ ጭር ሲል የማይወድ፣ ሁከት ካልተፈጠረ ሰላም የማይሰማውና በተንኮልም የተካነ ነው።
ያሬድ ዲላ ከመግባቱ በፊት ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ በዲላ ከተማ ላይ ያሉት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና የሚካኤል ደብሮች አለመግባባት ላይ ነበሩ ። በመካከላቸው የተከሰተው አለመግባባት ምንጩ ሁለቱም ደብሮች በአንድ ደብር ይተዳደሩ አይተዳደሩ የሚል ሲሆን አቡዬዎች በአንድ ሰባካ ጉባኤ እንተዳደር ሲሉ ሚካኤሎች ደግሞ የለም አንተዳደርም ባይ ነበሩ። አለመግባባቱ ረግቦ እያለ በ1989 ዓ.ም. ያሬድ በነርስነት ተቀጥሮ ዲላ ሰላም ክሊኒክ መስራት ጀመረ። ያኔ በቤተክርስቲያን አካባቢ እየቀዘቀዘ ባለው አለመግባባት ውስጥ ለእሱ አመጸኛ ህሊና የሚጠቅም ነገር ታየው። ስለዚህ ያሬድ ጸቡን አነሳሳው። ሁኔታዎችን አጥንቶ የሚንቀሳቀስ ሰው ስለሆነ ጠንካራው ክፍል ሚካኤል መሆኑን ተረድቶ ለሚካኤሎች በመወገን አቦዬዎችን ማጥቃት ጀመረ። ነገረኛው ያሬድ አውደ ምህረት ላይ ቆሞ “በአቦ ቤተክርስቲያን የሚቀርበው የክርስቶስ ስጋና ደም አይደለም።” በማለት ባደረገው ቅስቀሳ ከፍተኛ ችግር ተከስቶ ነበር፡፡ የተከሰተው አለመግባባት ሥር በመስደዱም ያሬድ ዲላ ከገባበት 1989 ዓ.ም. ጀምሮ ዲላን ለቆ አዋሳ እስከገባበት 1993 ዓ.ም. ድረስ ጠቡን ሲያቀጣጥል ከርሟል። የያሬድ ላእከ ወንጀልነት መገለጥ የጀመረው እዚህ ላይ ነው ይላሉ የሚያውቁት፡፡ችግሩ ብዙ ጊዜ ካስቆጠረ በኋላ ሶስት ጳጳሳት ማለትም አቡነ ይስሐቅ፣ አቡነ ኒቆዲሞስና አቡነ ድሜጥሮስ ተገኝተው ፈትተዉታል፡፡
አዋሳ እንደገባም ሁሌም ጥቅምን በማነፍነፍ የታወቀው ያሬድ ከአንዲት የአሜሪካ ዲቪ ከደረሳት ሴት ጋር ይተዋወቃል። ያኔ ለአሜሪካ ያለውን ህልም ለማሳካት ይህችን ልጅ ለማግባት ይወስናል። ቀጥታም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ሄዶ “አባታችን በዚህ ወር ለማግባት ወስኛለሁ። ይህንን ለማድረግ የፈለኩት ከግንቦት ወር ጋር ተያይዞ ያለውን ጎጂ ልማድ ለማስቀረትና አርአያ ሆኖ ለመታየት ነው።” በማለት ጋብቻውን በቶሎ እንዲፈቅዱለት በማድረግ ከልጅቱ ጋር የውሸት ጋብቻን ፈጸመ።ይህንን ጋብቻ ያሬድ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ተክሊል አድርጎ ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ ላልከዳሽ ላትከጂኝ ብሎ ቃል ገብቶ የፈጸመው ነበር፡፡ በቤተክርስቲያን ሥርዐትም እንኳ ቢሆን የፈጸመው ጋብቻ የውሸት ስለሆነ ብዙ ሰው እንዳያውቅበት የተቻለውን ያህል ጥረት አድርጓል። የጠማማ ሰው ጠማማ ዕድል ወድቆባት የልጅቷ የዲቪ እድል ሳይሳካ በመቅረቱ ከዛን ጊዜ በኋላ እንኳን እንደ ባል ሊያቀርባት ለሰላምታም የሚጸየፋት ሰው ሆናለች። በህመም ይሁን በጤና በሀብት ይሁን በጉስቁልና ላልከዳሽ ብሎ ቃል የገባላትን ልጅ በዲቪው አለመሳካት በጠዋቱ ከድቷታል፡፡ በወቅቱ ጋብቻውን የፈጸሙለት አባት በአሁነ ጊዜ ጳጳስ ሲሆኑ ድርጊቱን የሚያስታውሱት ነው፡፡
ያሬድ በዚህም በዛም ብሎ ብጹዕ አቡነ በርተሎሜዎስንም ወዳጅ አደረገ፡፡ከዛም ሊቀ ጳጳሱን በማግባባት በቀጣዩ ዓመት ማለትም በ1994 ዓ.ም. የአዋሳ ገብርኤልን አስፋልት አሰራለሁ ብሎ እንቅስቃሴ ጀመረ። ያሬድ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴውን በበላይነት በመያዝ የገንዘብ መሰብሰቢያ ፎርም አዘጋጅቶ ያለ ቤተክህነት ሞዴላ ሞዴል በሰበሰበው ገንዘብ የአንበሳ ድርሻውን ለራሱ ወስዶ የድመቲቱን ድርሻ ለአስፋልቱ ማሰሪያ አዋለው። ፎርሙን በመላው የአዋሳ ከተማ ከመበተንም አልፎ የሰበሰበውን በርካታ ገንዘብ ኦዲት ሊደረግበት የሚያስችለውን መንገድ ሁሉ አስቀድሞ ስላጠረ ከወሰደው የአንበሳ ድርሻ(በዘመኑ ቋንቋ ንፋስ አመጣሽ ገንዘብ እንበለው ይሆን?) በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ አምስት የንግድ ተቋማትን ከፈተ። የአዋሳ ገብርኤልን አስፋልት አሰራለሁ ብሎ በዘረፈው ገንዘብ የከፈታቸው ተቋማት
1.     ዳቦ ቤት
2.    የወንዶች ጸጉር ቤት
3.    ኮስትር መኪና(ለቱሪስት ማመላለሻ የሚከራይ)
4.    አትናቴዎስ የሚባል ትምህርት ቤት በአዋሳ ከተማ ሲሆኑ
5.    በዲላ ከተማ ደግሞ ሰማርያ የሚባል መዝሙር ቤት ከፈተ።
ይህ እንግዲህ የያሬድን የሌብነት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ እውነት ነው።
ያሬድ አጨብጭቦ በገባበት አዋሳ ሁለት አመት ሳይሞላው የተጨበጨበለት ሀብታም ሆነ፡፡ ይህም የሕንጻ አሰሪው ኮሚቴንና የሰበካ ጉባኤውን “ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት አመጣው?” የሚል ጥያቄን ፈጠረባቸው፡፡ ጉዳዩም አለመግባባትን ጫረ፡፡ አለመግባባቱም ተካሮ ከአዋሳ ገብርኤል ተባረረ፡፡ ያኔ ቀጥታ ገስግሶ ቃሊቲ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ ቃሊቲ ገብርኤል ለሦስት አመት ያህል የያሬድ ማኩረፊያ ነበር፡፡
ነገር ግን በአዋሳ ከተማ የነበረውን ተቀባይነትና ዝና በፍጥነት በማጣቱ ወደ አዋሳ የሚመለስበትን ሥልት ሲነድፍ የነበረው ያሬድ ከሦስት አመት በኋላ አንድ መላ ተከሰተለት፡፡ ያሬድ በአጋጣሚ አንድ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ፈረንጅ ይተዋወቃል፡፡ ይህም ፈረንጅ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጎ አመለካከት ያለውና በቤተ ክርስቲያኒቱም አገልግሎት ደስተኛ የሆነ ሰው ነበር፡፡ 
ይህም ለያሬድ ትልቅ ዕድል ከፈተለት፡፡ በ1998 ዓ.ም. ጥቅምት 27 ቀን በአዋሳ መነፖል ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን የመድሀኔዓለም ክብረ በዓል ላይ ፈረንጁን ይዞ ብቅ አለ፡፡ ፈረንጁን አስተምሬ አስጠምቄ ኦርቶዶክሳዊ አድርጌዋለሁ በማለትም በቀላሉ መድረክ አገኘ፡፡ ገድሉንም ዘርዝሮ ህዝቡን እልል አሰኘ፡፡ ፈረንጁም ቀርቦ በቅጡ በማያውቀው ቋንቋ ያስጠኑትን መዝሙር መድረክ ላይ አቀረበ፡፡ በዚህም ያሬድ የህዝቡን ልብ እንደገና አገኘ፡፡ በአዋሳው ተክለሓይማኖት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይወሰን በአዋሳ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እየዞረ አዘመረው፡፡ በተለይም ከሥራው የተባረረባትን ደብር ኣዋሳ ገብርኤልን መድረክ ለመርገጥም ፈረንጁ የውሃ መንገድ ሆነለት፡፡ ፈረንጁም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ስለሚወድ ብቻ በአብያተ ቤተክርስቲያን መካከል እንደ ተመሰረተ አንድነት ቆጥሮት ያሬድን እየተከተለ በየመድረኩ ይታይ ጀመር፡፡ የተሰራበትን ደባ ግን ፈጽሞ አያውቅም ነበር፡፡ በዚህ ሰው አማካኝነትም ያሬድ በድጋሚ ወደ ሓዋሳ መድረክ ተመለሰ፡፡

የያሬድ መሰሪነት በዚህ አላበቃም። በተፈጥሮው አጋጣሚን ተጠቅሞ ልዩ ልዩ ተንኮልን በመስራት የተደራጀ አዕምሮ ስላለው በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች “የተንኮል ፋብሪካ ያለው ይመስላል። ክፋትን ሲያመርት ወደር አይገኝለትምና” ይሉታል። ያሬድ ከአቡነ በርቶሎሚዎስ ጋር የመሰረተው ፍቅር አብቅቶ ከአዋሳ ከተማ በእርሳቸው ፊርማ በመባረሩ ያቄመውን ቂም አፍታትቶ የሚበቀልበትን ጊዜ መጠበቅ ጀመረ። በወቅቱ በአዋሳ ከተማ በሊቀ ጳጳሱ ላይ የተነሳው ተቃውሞም ምቹ ሁኔታን ስለፈጠረለት ተቃውሞውን በዋናነት የሚያስተባብርና የሚመራ ሰው ሆኖ ብቅ አለ። በዚህም እንዲያግዙት ሁለት መነኮሳትን እና አንድ ዲያቆንን ፊታውራሪ አድርጎ አቆመ። የግለሰቦቹ ስም አባ ምህረት፣ አባ ሀይለ ሩፋኤልና ዲያቆን መዘምር የሚባል ነበረ። እነዚህን ግለሰቦች ተጠቅሞ አቡነ በርቶሎሚዎስ ከአዋሳ እንዲነሱ ካደረገ በኋላ የእነዚህ ሰዎች አሰፈላጊነት አልታይህ አለው። ሰለዚህም አቡነ ፋኑኤል እንደመጡ ከእሳቸው ጋር የጠበቀ ወዳጅነት በመመስረት እነዚህን ሶስት ግለሰቦች “አሳዳሚ ናቸው ለእርስዎም አይመለሱም” በማለት ከስራቸው እንዲፈናቀሉ አደረገ። ሰውን ከስሩ ነቅሎ ካላጠፋ እረፍት የማይሰማው ያሬድ ሰዎቹ የትም ቦታ ተቀጥረው እንዳይሰሩም ለሁሉም ሀገረ ስብከቶች የሀሰት ውንጀላ ዘርዝሮ ደብዳቤ አሰራጨ።
እነዚህ ግለሰሰቦችም ከእንጀራቸው ከመፈናቀል አልፎ የትም ቦታ ተቀጥረው እንዳይሰሩም ስለተደረገ በወቅቱ አቅርበዋቸው እንጀራን ያበሉዋቸውን እስላሞች ሀይማኖት በመቀበል ሰልመዋል። ሲዲም አሰራጭተዋል። የመረጡት መፍትሔ ተገቢም ባይሆን እንኳ ለእነርሱ መጥፋት ግን ደማቸው ከያሬድ እጅ መፈለጉ አጠያያቂ አይሆንም።
ምንም እንኳ ያሬድ መድረኩን እንደገና ቢቆጣጠርም የከፈታቸው የንግድ ተቋማት ግን በግፍ የተገኙ ስለሆኑ ብዙ አልቆዩለትም። በአዋሳ ገብርኤል በተነሳው የእርስ በእርስ አለመግባባትና ግጭት አንድ ሥራ አስኪያጅን በማንሳት ይፈታ የነበረውን ችግር ያሬድ አቡነ ፋኑኤልን በማሳሳት “እኔና መልአከ ሕይወት ጸሓይ መላኩ አብና ወልድ ነን ብለው ለህዝቡ ቁርጡን ንገሩት ምንም አያመጣም…” ሲላቸው እሳቸውም እውነት መስሎዋቸው ያሬድ ያላቸውን በመናገራቸው አለመግባባቱ ሥር እየሰደደ በመሄዱ በተከፈተው ቀዳዳ ማህበረ ቅዱሳን ገባበት።
ያሬድም ቅን የወንጌል አገልጋይ የሆኑ ወንድሞችን በማሳሳት በመድረክ ላይ ህዝቡን እና ሥራ አስኪያጁን የተቃወሙ ሰዎችን በማስተቸቱ ግጭቱ እየተፋፋመ ሔደ ማህበርዋም ነገሩን በማጋጋል ችግሩን ተቀላቀለች።
በዚህ ጊዜ ስልታዊው ያሬድ በግል የእርቅ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞከረ፡፡ በዚህ የእርቅ እንቅስቃሴው አብረውት መከራ የተቀበሉ ወንድሞቹን ሣያካትትና ሳያሳውቃቸው በግሉ በአዋሳ ከተማ በእሱ እንቅስቃሴ እልህ ከተጋቡት ግለሰቦች ጋር ታርቆ እና እሱ ብቻ ተመልሶ ሌሎች ወንድሞችን የሚያስመታ አካሄድ የተከተለ ነበር፡፡
እነዚህ ግለሰቦች ግን የያሬድን ባህሪ ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለሆነና በጥቅም እንጂ በወዳጅነት የሚያምን ሰው አለመሆኑንስለተረዱ በእርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚያደርገውን ንግግርና የሚናገራቸውን ነገሮች በሙሉቀረጹት፡፡በዕለቱ አብረውት የሌሉትን ሰዎች ሁሉ በማማትና በማጣጣል የሚታወቀው ያሬድ ከፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ፣ በአዋሳ ካሉ የክልሉ መንግስት ባለሥልጣናት እስከ አዲስ አበባ ያሉ ሀብታሞች፣ አሁንም ድረስ በአጠገቡ ያሉ እና ለተንኮሉ ስኬት አለሁ አለሁ የሚሉትንና ገንዘብ የሚረጩትን ሀብታሞችና የቅርብ ጓደኞቹን ጨምሮ ስም እያጠፋና እያክፋፋ ስለእነርሱ በልቡ ያስቀመጠውን ክፋት በውስኪና በጥብስ እያወራረደ ተረከ፡፡
ሰዎቹም ከዋስትና አንጻር ብቻ የቀረጹትን ድምጽ ያሬድ በተለመደ ባህሪው ጥቅሙን መዝኖ  እጥፍ ካለና እንደገና ወደ ጸብ ከተመለሰ የተቀረጸውን ሊለቁበት እርቁን ያሰበው ከልቡ ከሆነ ግን ሚሥጢር አድርገው ሊያስቀሩት ቃል ገብተው የተቀረጸውን ድምጽ ያዙት፡፡
ያሬድ ከቀናት በኋላ የማቅን አካሄድ የተቃወመው ህዝብ መብዛቱን ተመልክቶ ያደረገውን የእርቅ ስምምነት በመርሳት እንደገና ጸቡን የማነሳሳትና የታረቃቸውን ሰዎች ወደ ማጣጣል እንቅስቃሴው ተመለሰ፡፡ በዚህ ጊዜ ግለሰቦቹ ከቀረጹት ድምጽ ከፊሉን ማለትም ስለበጋሻውና ስለ አቡነ ጳውሎስ የሚዘላብድበትን ብቻ ለማቅ ሰጡ፡፡ ሌላውን ላለመስጠት የወሰኑት በቀጥታ ለሕይወቱ ስለሚያሰጋው ብቻ ነበር፡፡
ያሬድ የተቀረጸው ድምጽ ከሌሎች ነገሮች ጋር ተደምሮ በሲዲ በመለቀቁና በነጻ በመሰራጨቱ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ሊያየውና ሊሰማው ቻለ፡፡ ይህም ለማኅበረ ቅዱሳን የወንጌል አገልጋዮችን በብቃት እንዲያሳድድ በር ከፈተለት፡፡ በአዋሳም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ በርካታ የወንጌል አገልጋዮች የአገልግሎት በር እንዳያገኙ ለማድረግ ቻለ፡፡ በሶሻል ሚዲያ ላይም የመልካም አገልጋዮችን ስም ለማጥፋት የያሬድ ድምጽ በር ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በያሬድ ቀዥቃዣ ባህሪ እና ጥቅም ተኮር ጉዞ ነው፡፡
ማኅበርዋ በተንኮልም በእስትራቴጂም ከያሬድ የተሻለች ስለሆነች አቡነ ፋኑኤልን፣ ያሬድንና ሌሎች አገልጋዮችን በመቃወም ሳትወሰን የያሬድ የንግድ ተቋማት ላይ ዘመቻ ከፈተች።ዘመቻው ውጤት በማስገኘቱም ትምህርት ቤቱም ዳቦ ቤትም ሆነ መዝሙር ቤቱ ከስሮ ተዘጋ። መኪናና ትምህርት ቤት የነበረው ቤትም በባንክ እዳ ተይዟል። እስካሁንም አልተለቀቀለትም።
አጅሬው ግን አሁንም ተንኮሉን የሚያስፋፋበትንና ገንዘብ የሚያገኝበትን ነገር ከማነፍነፍ ወደ ኋላ አላላም።ከሀዋሳ ገብርኤል ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመጋጨት የወጣውንና ከ5000 በላይ ሆኖ በውጪ ለዓመታት ሲሰበሰብ የነበረውን ሕዝብ በመጠቀም“ኦርቶዶክስን ልንወርሳት ነው።” በሚል የግል ቢዝነሱን ሲሰራበት ቆየ።
ያሬድ ከፕሮቴስታንቱ ጋር ከአዳር ጸሎት እስከ ቀን ምጽዋት ሥር የሰደደ ፍቅር መስርቶ ከፍተኛ ገንዘብ በህዝቡ ስም ሰበሰበ። ውጭ ያለውን ሕዝብ የሚጠቀምበት መንገድ ያልተዋጠላቸውን አንዳንድ ከህዝቡ ጋር የተሰደዱ ለምን ባይ? እውነተኛ ወንድሞችን የማሕበረ ቅዱሳን ሰላዮች በማሰኘት ከጉባኤው በጥርጣሬ እንዲታዩና አልፎም ገለል እንዲደረጉ አደረገ።  በእውነት የኮሚቴው አባላት እጅግ ቅንና መልካም ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ያሬድ እነርሱንም ቢሆን መጠቀሚያው ከማድረግ አልቦዘነም ነበር። ከተቋቋመው የየዋሀን ስብስብ ከሆነው ኮሚቴ ውስጥም የእሱን ሀሳብ የሚቃወሙትን ሁሉ በተለያየ መንገድ እየመታ አበረረ። ይህም በተሰደዱት ሰዎች ዙሪያ ያሬድን ምሁረ ጸብ የሚል ስም አሰጠው። ከአዋሳ ዩንቨርሲቲ በተመረቀ ጊዜ አንዳንድ ወንድሞች “ምሁረ ጸብ” ተመረቀ ብለው በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረው እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የጥቅም ጥሙ የማያባራው ያሬድ እንደገና ደግሞ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሞዳሞድ ህዝቡን ወደ ቤተክርስቲያን የመመለስ እንቅስቃሴ ጀመረ። ህዝቡን ቤተክርስቲያን ለመመለስም የራሱን ወደ አገልግሎት መመለስ እንደ ቅድመ ሁኔታ አቅርቦ እንደነበር የሚታወስ ነው። በወቅቱ የማኅበርዋ ብሎግ ሀራ ያሬድን ባርካ በጋሻውን ነቅፋ ሰፊ ዘገባ መስራትዋ ይታወሳል።መሰሪው ያሬድም ብዙዎች ውድ ዋጋ የከፈሉበትን አገልግሎት ለተሻለ ቢዝነስ በማዘጋጀት ከልብ ያልሆነ እርቅ እንዲፈጸም በማድረግ በአጋጣሚው ለመክበር በወጠነው ውጥን ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ ማኅበርዋም አካሄዱን ስላወቀችበት ህዝቡ ወደ ቤተክርስቲያን ከተመለሰ በኋላ ፊት ነስታዋለች።
ያሬድ ለገንዘብ ያለው ፍቅርና ከተለያየ ሰው በተለያየ ጊዜና መንገድ የሚወስደው ገንዘብ ልክ ማጣት ይህ ሰው ገንዘቡን ምን እያደረገው ነው? ያሰኛል፡፡ የአመጻ ገንዘብ በረከት ስለሌለው ሁሌም ከብድር ወደ ብድር ሲንከባለል ይኖራል፡፡ አንዳንዶች በዚህ የገንዘብ ፍቅሩን እና አጭበርብሮ ገንዘብ የመቀበል ባህሪውን ከቀድሞ ጓደኛው ሳሙኤል ሌንጂሶ(እሱ ራሱን የሚጠራው ዛሙኤል ዘሚካኤል ነኝ እያለ ነው) ጋር ያመሳስሉታል፡፡በቅርቡ እንኳን ዓለምን ማገልገል ይበቃኛል ብላ ከዘፋኝነት ወደ ዘማሪነት የተመለሰችው አቦነሽን ካሴት የሰራችበትን ገንዘብ በደረቅ ቼክ አጭበርብሮ ሲወስድባት ለምና አስለምና እምቢ ብሎ ሲያስቸግራት ጉዳዩን ለጠበቃ ሰጥታው በደረቅ ቼክ ማጭበርበር ተከሶ ለአራት ወራት ከታሰረ በኋላ ገንዘቡን ከፍሎ በሁለት ዓመት ገደብ ተለቋል፡፡ አቦነሽንም የተወቻት ዓለም በያሬድ በኩል ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀብላታለች፡፡
ላዕከ ወንጀል ያሬድ እንደተለቀቀ ራሱን በንስሀ ከማየትና በእግዚአብሔር ፊት ከመሆን ይልቅ ዘሎ ወደ መድረክ በመውጣት የእግዚአብሔርን ጉባኤ እያበላሸ ይገኛል፡፡
ግለሰቡ ከእስር ቤት እንደተለቀቀ የተሰጠውን የገደብ ጊዜ ሳይጨርስና አቦነሽን በማጭበርበር ከደረሰበት ችግር ሳይማር ከአንዲት ሴት የወሰደውን መቶ ሺህ ብር ባለመመለሱና መውሰዱን በመካዱ ልትከሰው ስትዘጋጅ ጓደኞቹ እኛ እንከፍልሻለን ጥቂት ጊዜ ስጪን በማለት ሃሳብዋን ለማስቀየር ቢጥሩም ታግሳ ታግሳ ገንዘብዋን ለማግኘት ባለመቻልዋ መኪናውን አሳግዳበታለች።
ያሬድ በአገልጋይነት ሥም አምነውት የሚቀርቡትንና በየጉባኤው የሚያገኛቸውን ሴቶች አገባሻለሁ በማለት ገንዘባቸውን በእምነት እየተቀበለ በራሱ የገንዘብ ቤርሙዳ ውስጥ ከቀበረ በኋላ  ገንዘባቸውን ሳይመልስ ፊት እየነሳ ብዙ እህቶችን እያስለቀሰ ይገኛል፡፡  በዚህ ታሪኩም ከዲላ እስከ አዋሳ ከዱባይ እስከ አዲስ አበባ የተደራጀና የበለጸገ የነውር ዶሴ አለው፡፡
ያሬድ አደመ በቅርቡ ግብረ ሰዶማዊነቱ በይፋ ከታወቀው አሸናፊ መኮንን ጋርም ጊዜያዊ የጥቅም ፍቅር ይዞዋቸው ይገኛል፡፡በአቦነሽ ጠበቃ በተከሰሰ ጊዜም በመኪናው እያመላለሰ አለሁ አለሁ ይለው የነበረው ይኸው ሰዶማዊ ግለሰብ አሸናፊ መኮንን መሆኑ ጸሀይ የሞቀው እውነት ነው፡፡ ያሬድና አሸናፊ ባለፈው የትንሳኤ በአል ተያይዘው ኢየሩሳሌም መሄዳቸውም የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን ከአሸናፊ መኮንን ጋር አብረውት የሄዱትን አገልጋዮችና እሱን ይዞ የሄደውን የጉዞ ወኪል ለሊቃውንት ጉባኤ መክሰሱ ይታወቃል፡፡
ምናልባትም አሸናፊ መኮንን በይፋ የከፈተውን ሚኒስቲሪ አትናቴዎስ የሚል ስያሜ የሰጠው የያሬድን የከሰረ የትምህርት ቤት ህልም እውን ለማድረግና ለያሬድ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ ይሆናል የሚሉ አልታጡም፡፡
ያሬድ ጥቅም ያግኝ እንጂ ከየዋህ እስከ ክፉ ሰው ከክርስቲያን እስከ ዓለማዊ ሰው በህግ ጋብቻ እስከ ታሰረ እስከ ግብረ ሰዶማዊ ለመወዳጀት የማይቸገር ሰው ነው፡፡
ይህ ግለሰብ በወንጌል አገልጋዮች መሀል ተጠልሎ የሚፈጽመውን ወንጀል ህዝብ ይወቅልን በማለት በአዋሳ አካባቢ የምንገኝ የወንጌል ወዳጆች ይህንን ጽኁፍ ለአባ ሰላማ ልከናል፡፡
ያሬድን የሚያውቁት ሰዎች በየዋህነት ከመታለል እንዲጠበቁ የማያውቁት ደግሞ ራሳቸውን ከእንደዚህ አይነት መሰሪ እንዲጠብቁ ይህንን መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡
ወንጌል ሊነግዱባት ከሚፈልጉ ከአመጸኞች እጅ ነጻ እንድትወጣና አመጸኞችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እውነተኛ አገልጋዮች ብቻ እንዲያገለግሉዋት የምንጊዜም ምኞትና ጸሎታችን ነው፡፡


15 comments:

 1. yaredeye yanchim tarike leka yisafal? asafari sew min yisafeletal senel neber. maferem leka tarike new.

  ReplyDelete
 2. ወንጌል ሊነግዱባት ከሚፈልጉ ከአመጸኞች እጅ ነጻ እንድትወጣና አመጸኞችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እውነተኛ አገልጋዮች ብቻ እንዲያገለግሉዋት የምንጊዜም ምኞትና ጸሎታችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. በእናንተ ዘንድ እውነት ምንድነች? ቤተክርስቲያኒቷን የሚያምሱትን መደገፍና የእናንተን አጀንዳ ለማስፈጸም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ ደግሞ መሳደብ ነው? በሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል አሁን ካብጠለጠላችሁት ሰውና ከሌሎች ጀሌዎቻችሁ ጋር ምን ስትሰሩ ነበር? 2003 ዓ/ም ትዝ አላችሁ? በቤተክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ጸብ እንዲነሳና በመድር ያለች የመንግሥተ ሠማይ ምሳሌ በሆነች ቤተክርስቲያን ቆሻሻ ላስቲክና ጎማ ስታቃጥሉ አልነበር፡፡ በወቅቱ እውነተኛ ተናጋሪን እያሳደዳችሁ በቆንጨራ ሳይቀር ስትደበድቡ አልነበር? ደግሞ እውነተኛች እያላችሁ አሁንም እኛን ለማታለልና ቤተክርስቲያኒቷ ማመስ አማራችሁ፡፡ ሌባ ሲሰርቅ ሳይሆን ሲካፈል እንደሚጣላ እናውቃለን፡፡ አያችሁ በወቅቱ እውነተኞችን ለማሳደድና ከቤተክርስቲያን በማስወጣት ቤተክርስቲያኒቷን ለመውረስ ካልተሳካም ለመክፈል ጥረት አድርጋችኋል፡፡ አሁን ግን ጉዳያችሁ ፀሐይ ሞቀው! ተንጣጣ! ማንነታችሁ በጊዜ ውስጥ ታየ! ግልጥልጥ አለ! የት ትገቡ! የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆችን አበረከታችሁ፡፡ በየጊዜው የሚቀያረውን ዘዴያችሁን አወቅንባችሁ! እውነተኛ የክርስቶስ ወንጌል የሚሰበከው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሆኑን ተረዳን! የተሰራችው በማይንቀሳቀስ አለት ላይ መሆኑን በጊዜ ውስጥ ታየች፡፡ ስለዚህ አሁን ምን አድርጉ ትሉናላችሁ፡፡ ስለጠቀሳችሁት ሰው እኮ እናንተ ይህን መረጃ ከማውጣታችሁ ከዓመታት በፊት ይታወቅ ነበር፡፡ ግን እውነትን ለጊዜ መተው ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ዘገባችሁ ያስተምራል፡፡ አሁን እንግዲህ ተለያያችሁ፡፡ ተሐድሶና መናፍቅ ጓዛችሁን እየጠቀለላችሁ ስትመጡ እቀበላችኋለሁ ወዳላችሁ ወደአባታችሁ የፕሮቴስታንት አዳራሽ አምሩ፡፡ በዚያ እንደድሮ እየጨፈራችሁ ገንዘብ እንደልብ የሚገኝ መስሏችኋል፡፡ የለም! የዓለም ኢኮኖሚ እየነዳው ላለው አዳራሽ ፈንድ የለም! ተቋርጧል፡፡ ወደቤተክርስቲያን ሲመለሱ ደግሞ በንሰሀ ብቻና ብቻ ነው!
  ያሬድ አደመ ባለፈው ሳምንት እለእመቤታችን በኢቢኤስ ሲሰክ ገርሞኝ ነበር! ለምን አትሉኝም ሰውየውን በደንብ ስለማውቀውና ስለሷ መናገር አቅሙን ከየት አገኘ ብዬ ነው፡፡ ይኸው ከናተ ጋር አጣላው፡፡ ስለእመቤታችንና ስለቅዱሳን አማላጅነት እለመላእክት ተራዳኢነት እና ሌሎች እናንተ ስለሚያቅሯችሁ ጉዳዮች ለመስበክና የጠላችሁን ምዕመን ለማሳመን ፕሮግራም ስለተያዘላቸው ተሐድሶዎችና መናፍቃን እንደማውቅ ብነግራችሁስ፡፡ ስለነሱ ደግሞ ይቆየን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ የማኅበረ ቅዱሳን ድምፅ ነው !!

   Delete
 4. ስለ ያሬድ የተጻፈውን አንብቤዋለሁ፡፡ ከተጻፈው ውስጥ የማላውቀው፣ "ከፕሮቴስታንቱ ጋር ከአዳር ጸሎት እስከ ቀን ምጽዋት ሥር የሰደደ ፍቅር መስርቶ ከፍተኛ ገንዘብ በህዝቡ ስም ሰበሰበ" የሚለውን ሃሣብ ነው። ሌላው ሁሉም ትክክል ነው፡፡ ያም ሆኖ ስለግለሰቡ ባህርይ ብዙ ያልተነካኩ ሃሣቦችም አሉ፡፡ አንዱ እና ዋነኛው ደፋር በጣም ሲበዛ ደፋር፣ ሰውን የማያከብር ትህትና የጎደለው ሰው መሆኑ ነው፡፡ ሰውን ለጥቅሙ ሲል ከተጠቀመበት በኋላ (Use and throw) በሚል ፈሊጥ የቅርብ ወዳቾቹን ፈጥፍጦ ከመጣል የማይቦዝን መሆኑ ነው፡፡
  ከቢዝነስ ተቋማት ያልተጠቀሰው ሌላው በሀዋሳ የዜብራ ፕሪንተር ቀለሞች ወኪል አከፋፋይ ሆኖ የጀመረው ቢዝነስ ሲሆን፣ ይህም አልዘለቀለትም፡፡ የዘማርያንን የመዝሙር ግጥሞችን በመድብል መልክ አሳትሞ ከሸጠ በኋላ ለዜማና ግጥም ባለመብቶች አምስት ሣንቲም ሳይከፍል ጥቅም ማግበስበሱን፣ በዚህም ሳቢያ ተከሶ ፍርድ ቤት መቆሙን ያልተጠቀሰው አንዱ ድርጊቱ ነው፡፡ በሀዋሳ ለምዕመናን መብት ጥያቄ መታፈን፣ ለማኅበረ ቅዱሳን መንሰራፋት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀዋሳ የይስሙላ ዕርቅ ከተደረገ በኋላ ሰበካ ጉባዔውን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እና ልዩ ልዩ መዋቅሮችን ማኅበረ ቅዱሳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል፡፡ እነዚያ ምስኪኖች በገዛ ደብራቸው እንደ የኔ ቢጤ ሜዳ ላይ ተኮልኩለው ሰብሳቢ አጥተው ለአገልግሎት ባይተዋር ሆነዋል፡፡
  ያሬድ እነዚህን ወገኖች የይስሙላ ዕርቅ እንዲያደርጉ እንደ በግ ነድቶ ያስገባው በመንበረ ፓትርያርክ በእነ አቡነ ሉቃስ እና አጥብቆ ይዋጋቸው በነበሩት በአቡነ ገብርኤል በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መንፈሳዊ ትምህርት ለመማር እንደሚፈቀድለት እንዲሁም በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዐውደ ምሕረት ላይ ወንጌል እንደሚሰብክ ቃል ስለተገባለት ነው፡፡
  ይሁን እንጂ ጥቂት ምዕመናንን እንደ በግ ነድቶ ለዕርቅ ካስገባ በኋላ የሀዋሳው የዐውደ ምሕረት ላይ የወንጌል ስብከት ተስፋው እንደ ጉም በንኖ የጠፋበት ሲሆን፣ የቅድስት ሥላሴ ትምህርቱን በተገባለት ቃል መሠረት ቢጀምርም በደረቅ ቼክ ማጭበርበር ቃሊቲ እሥር ቤት በመውረዱ ምክንያት ያም አልተሳካለትም፡፡ የይስሙላ ዕርቁ ከተከናወነ በኋላም የሲኖዶስ ፀሐፊ ሆነው በተመረጡት አቡነ ሉቃስ ቢሮ ባለጉዳይ የሚያስገባ እና የሚያስወጣ ራሱን አጋፋሪ አድርጎ ያስቀመጠ እጅግ ነውረኛ ልጅ ነው፡፡ ያሬድን ነውረኛ፣ ሸፍጠኛ፣ ተንኮለኛ፣ ባለጌ፣ ደፋር፣ ከሐዲ፣ ስግብግብ የሚሉ ቃላቶች በፍጹም አይገልጹትም፡፡ እርሱ ከዚያ በላይ ነው፡፡ ከያሬድ ጋር የነገደ፣ ከሥሮ እንጂ አትርፎ አይገባም፡፡

  ውድ አንባብያን!! ምናልባት አባ ሰላማ ብሎግ የምትፈቅድልኝ ከሆነ እኔም የማውቀውን በያሬድ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ጉዳዮችን ልጽፍ እችላለሁ፡፡ ካልጻፍኩም፣ ከላይ የቀረበው ጽሑፍና እኔም የሰጠሁት አስተያየት ትክክል መሆናቸውን ምሥክርነቴን እሰጣለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please send me all information I'll help you by this meail
   ***********************************
   Tokichaborena@yahoo.co.uk

   Delete
 5. ያሬድ ማለት ከዚህም በላይ ሰነፍ ሰው ነው፡፡ እኔ ግን አንድ ነገር ልቤን ያደማል፡፡ እርሱም እጅግ የተወደደ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ መጋቢ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ በቅን ልብ ሆኖ ከዚህ ክርስቲያን መሰል ሰነፍ ሰው ጋር በሕብረት መንፈሳዊ አገልግሎትን እሰራሁ ብሎ መሰማራቱ ነው፡፡ መጋቢ ሐዲስ እኔ እንደሚመስለኝ ከሆነ ከዓመታት በፊት ወደዚህ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን አገልግሎት ሲሰማራ በቅን ልብ ተነሳስቶ የሰነፉን ያሬድ ልብ ሳያስተውል እንጀመር ባውቅም አሁን አሁን የስንፍናውና የትቢቱን ልክ ሳያስተውል የቀረ አይመስለኝም፡፡ እውነቱን ለመናገር በመጋቢ ሐዲስ በጋሻው ስም ይሄ ሰነፍ ሰው እጅግ ብዙ ዓመጻን ሰርቷል፤ እጅግ ብዙ የቅርምት ገንዘብን አካብቷል፤ እጅግም ብዙ የአግልግሎት በሮችን እየዘጋ ወንጌል እንዳይሰብክ አድርጓል፡፡ በመልካሙ የሽቶ ዕቃ የሚከረፋ አንዳች ጠረን ቢገባበት የቀደመ መልካም መዓዛውን ለውጦ ግማት እንደሚያደርገው ሁሉ እንዲሁ የዚህ ተንኮለኛና ገንዘብ አምላኪ ሰው ማንነት የመጋቢ ሐዲስን ጸጋና አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያኮላሸውና እያኮሰሰው ሲነጉድ ብዙዎቻችን ሳናስተውል የቀረን አይመስለኝም፡፡ እጅግ አዝናለሃሉ! ጸሎቴ ይሄ ነው መጋቢ ሐዲስ በጋሻው አገልግሎቱን በእንዳልነበር ከሚያደባየው ሰው ጋር ሕብረቱን አቁሞ፤ ከመልካም የወንጌል አገልጋዮች ጋር ሕብረቱን እንደገና መስርቶ፣ እግዚአብሔር አትረፍርፎ በሰጠው ጸጋ አሁንም አሁንም እንዲገለግለን ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. ስለ እመቤታችን ስለሰበከ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yehe yetera sew asteyayet new

   Delete
 7. God hate such kind of accusation. Please STOP. Let God judge him.Who we are to judge. Shame on you guys.

  ReplyDelete
 8. ato yared ena ato ashenafi hultehu neweregoche guwadegamoche mehonachewe yidenkal. hultetum gebersedomawina set awel selehonu new yetegebabut wey zendero

  ReplyDelete
 9. አሁን አይናንተ ሀሳብ ዲ/ አሸናፊን ጥላቻችሁ ስለበዛ ከእርሱ ጋር የተጠጋውን ሁሉ ስም ማጥፋት ጀመራችሁ፡፡ አረ ሰይጣን እንኳን በአንድ ነገር ከመጣ በኋላ ተነቃብኝ ብሎ መንገዱን ይቀይራል እስቲ መንገድ ቀይሩ ::

  ReplyDelete
 10. who ever never sin let him trough the rock on him

  ReplyDelete
 11. ተቱ.ቹቾ.7ቸ፤8ቸ

  ReplyDelete