Thursday, August 6, 2015

ጸልዩ በእንተ ዝናም


 READ IN PDF
ኢትዮጵያ አገራችንን የዝናም እጥረትና ድርቅ ቢያንስ በየዐሥር ዓመቱ የሚጐበኟት አገር ከሆነች ውሎ አድሯል፡፡ በ1967 የወሎ ረኃብን፣ የ1977ቱን ድርቅ እያለ እነሆ ዘንድሮ በ2007 ደግሞ በዘንድሮው የክረምት ወራት በአብዛኛው የአገራችን ክፍል ዝናም እየዘነበ አይደለም፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ገበሬዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ እየገለበጡ እየዘሩ ቢሆንም ዝናብ ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል፡፡ እንዲህ የሚሆነው ለምን ይሆን? ይህን ጥያቄ በትክክል መመለስ የሚችል አንድዬ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የአንድዬን ቃል ያነበበና ያስተዋለ ሰውም መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ተነሥቶና የምንገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ መስተዋትነት ተመልክቶ ያመነበትን ምላሽ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ገንብቶ ከጨረሰ በኋላ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆሞ ካቀረባቸው ልመናዎች አንዱ፥ አንተን ስለ በደሉ ሰማይ በተዘጋ ጊዜ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ ባስጨነቅሃቸውም ጊዜ ከኃጢአታቸው ቢመለሱ፥ አንተ በሰማይ ስማ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብ ስጥ።” (1ነገ. 8፥35) ከዚህ ልመናው የምንገነዘበው ዝናብ ከሚጠፋባቸው ምክንያቶች አንዱ እግዚአብሔርን መበደል እንደኾነ ነው፡፡ እንዲህ ሲባል ዝናም የሚዘንበው ሰው መልካም ስለሆነ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ በቃሉ ውስጥ እንደተጻፈው ጌታ ቸር ስለሆነ በክፉዎችና በበጎዎች መካከል ልዩነት ሳያደርግ ለሁሉ ፀሐይ ያወጣል ዝናብም ያዘንባል (ማቴ. 5፥44-45)፡፡ ሆኖም በበደል ምክንያት ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ሊከለከል ይችላል፡፡ 
እንደኛ ሰው የነበረው ነቢዩ ኤልያስ በአምልኮተ ጣኦት ምክንያት ለለእግዚአብሔር ስለቀና ጸልዮ ዝናብ እንዳይዘንብ አድርጎ ነበር፡፡ በኋላም ጸልዮ ዝናብ ዘንቧል፡፡ ይህም በኃጢአት ምክንያት ዝናብ እንደሚጠፋ ሌላው ማስረጃ ነው፡፡ ሰዎች ተጸጽተው የእግዚአብሔርን ስም ቢያከብሩና ከኃጢአታቸው ቢመለሱ እግዚአብሔር እንዲሰማቸው ሰሎሞን ይማጸናል፡፡ እግዚአብሔርም “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ” (1ነገ. 9፥3) ሲል ምላሽ ሰጥቶታልና በበደል ምክንያት ዝናብ በተከለከለ ጊዜ በንስሐ ወደ ፈጣሪ ብንጮህ ልመናችንን ሰምቶ ዝናብን ሊሰጠን የታመነ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እንደተጻፈው ራሳችንን አዋርደን ብንጸልይ እግዚአብሔር እንደሚሰማንና ዝናመ ምሕረቱን እንደሚያወርድልን እሙን ነው፡፡

ልዑል እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ሲል አዟቸው ነበር፤ “እንዲህም ይሆናል እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ እህልህን ወይንህንም ዘይትህንም ትሰበስብ ዘንድ በየጊዜው የበልጉን ዝናብና የክረምቱን ዝናብ ለምድራችሁ አወርዳለሁ። በሜዳ ለእንስሶችህ ሣርን እሰጣለሁ፥ ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ። ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንዳይነድድባችሁ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ።” (ዘዳ. ፲፩፥፲፫-፲፯)፡፡ ዛሬም በምድራችን የዚህ ትእዛዝ ውጤቱ እየታየ ነው፡፡    
በቅድሚያ እግዚአብሔርን ስለበደልንበት ነገር ንስሐ መግባት አስፈላጊና መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ትልቁ በደላችን እግዚአብሔርን ትተን ሌሎችን አማልክት መከተላችን ነው፡፡ በዚህ ረገድ በተለይ የገጠሩ ሕዝብ የባእድ አምልኮ ሰለባ መሆኑ አይካድም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም በአክብሮት ስም እየፈጸመች ያለውን አምልኮተ ፍጡራን ወኪነ ጥበብ ቆም ብላ መፈተሽ አለባት፡፡ ይልቁንም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ስሟ እየገነነ የመጣው “አርሴማ” የሚለው ስም ብዙዎችን እያሳተ የእግዚአብሔርን ቁጣ እየቀሰቀሰ ነው፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ወር በገባ በ6 የሚታሰበው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ቁስቋም ተብሎ የተራራ ስም ቀኑን ቀምቶት የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ አርሴማ ነግሣበታለች፡፡
ከዚህ ቀደም አርሴማ በሚል ስም የምናውቃትና በ6 የምትከበር “ጻድቅ” ወይም “ሰማዕት” የለችም፡፡  ዛሬ ግን አገር ምድሩ ሁሉ አርሴማ አርሴማ እያለ ነው፡፡ ገቢው ደካማ የሆነበት ደብር ሁሉ ገቢውን ለመጨመር ሲል ደባል ማድረግ የሚፈልገው አርሴማን ነው፡፡ ጳጳሳቱም ይህን አምልኮ ባዕድ መገሠጽና በትምህርት ማስቀረት ሲገባቸው ልባቸው እያወቀ ለመኖር ሲሉ የአርሴማን ታቦት እየባረኩ ይሰጣሉ፡፡
አርሴማ በቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰት ውስጥም ሆነ በዚቅ ውስጥ አትታወቅም፡፡ ስለዚህ ደብተራዎቹ በመጨናነቅ ለእሷ ተስማሚ ያሉትን ድርሰት የሌሎችን ስም እየፋቁና የእርሷን ስም እየተኩ ማሕሌት ይቆሙላታል፤ ወረብ ይወርቡላታል፡፡  
አሁን አሁንማ በአንዳንድ በኩል አርሴማ ከማርያምም በልጣለች፡፡ ወሎ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ አንዲት ሴት መከሰሷን ሰማሁ፡፡ ይኸውም ያቺኛዋ (ማርያም) ምን አደረገችልን? ይችኛዋ (አርሴማ) ከመጣች ጀምሮ ግን ብዙ ተአምር ነው እያየን ያለነው በሚል የጌታችንን እናት ማርያምን ዝቅ አድርጋ አርሴማን ደግሞ ከፍ እያደረገች በመናገሯ ነው፡፡ ሕዝቡ ዛሬ አዳኙን ኢየሱስ ክርስቶስን እየገፋና አዲስ አምላክ ሆና ብቅ ያለችውን አርሴማን ወይም በአርሴማ ስም የሚሠራውን መንፈስ እየተከተለ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ድርጊት እግዚአብሔርን የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ በደል ነው፡፡ በዚህና በሌላውም አምልኮተ ባእድ ምክንያት ዝናብ ሊከለከል ይችላል፡፡ መፍትሔው ደግሞ በደልን አምኖ ንስሐ መግባት ወደ ነፍሳችን ጠባቂ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡
እንደዚህ ባለው የዝናብ እጥረት በሚያጋጥም ወቅት በደህናው ጊዜ የተከማቸ ምርት ቢኖር ሊያገለግል ይችላል፡፡ ፈርኦን ባየው ህልም መሠረት ዮሴፍ በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ምርት እንዲከማች በማድረጉ ቀጥሎ በመጡት ሰባት የረሃብ ዓመታት ምንም ችግር ሳይፈጠር ሕዝቡ በሰላም እንዳሳለፈና ግብጽ ለሌሎች ጎረቤቶቿ ሁሉ እንደተረፈች በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፡፡ ዛሬ ገበሬውን ቁጠባ በማስተማር በኩል የተሰራው ስራ አጥጋቢ ባለመሆኑ አብዛኛው ገበሬ ቆጣቢ አይደለም፡፡ በማኅበራዊ ኑሮው በክርስትና በተዝካር በዝክርና በሌሎችም ምክንያቶች የተንዛዛ ድግስ በማድረግ ምርቱን ያባክናል፡፡ መንግስትም በተለያዩ አጋጣሚዎች በራሱ ሥርዓት ውስጥ በዓልና ድግስ ወዳጅ በመሆኑ ሕዝቡም ያን እያጠናከረ ነው የሚሄደው እንጂ በዚህ በኩል ለውጥ እያሳየ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ ስለዚህ ለወደፊቱ በዝናብ ዓመታት የተገኘውን ምርት መቆጠብና በአግባቡ መጠቀም በረሃብ ጊዜ ዋስትና ሊሆን ስለሚችል ገበሬውን ማስተማር ይገባል፡፡
ለሁሉም ግን አሁን በአብዛኛው የአገራችን ክፍል የሚታየውን የዝናም እጥረት አስመልክቶ ወደፈጣሪያችን በንስሓ እየተመለስን ልንጸልይ ይገባል፡፡ በእውነተኛ ልብ ንስሓ እየገባን፣ በሌሎች አማልክት ያስቆጣነውን አምላካችንን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ በኋላ የአርሴማም ሆነ የሌላው/የሌላዋ አንሆንም ይቅር በለን እያለን በፊቱ እንዋረድ፤ ጌታም ይቅር ብሎ ወደእኛ በምሕረት ይመለሳል፤ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ ስለዝናም ጸልዩ፡፡
ዲያቆን ይልቃል

5 comments:

 1. your message is as clear as pure water, I don't any one will miss it, u are trying to dishoner Kidusan, tsadkan, sema'etat...please don't blind yourself. I would be fool if I think that you haven't read mat 10:40.... Amlak yakeberewn man yawaredewal, yekonenewuns man yatsedekewal...anyways telling you the truth, will not open your eyes since you are trying g to misguided or mislead on purpose to against the church that introduce you to Jesus Christmas other wise you would have been E-amani, ahezab, aremenie.....this is not how you pay back to Mother...me and the rest of us (milions) will continue praying to let GOD almighty open your heart....we don't hate or fight u instead our fight is against the devil that you carried on....peace and love  ReplyDelete
 2. አደባባይ የወጣዉን የክህደት ትምህርታችሁን ስትዘሩ አታፍሩም? መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ክብርና አማላጅነት ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ በምልአት እያስተማረ መሆኑን በማስተዋል የሚያነቡት ሁሉ የሚረዱት ነው፡፡ እናንተው እራሳችሁ በዚሁ ስሑት መልእክታችሁ ላይ ጠቢቡ ሰሎሞን ስለሕዝቡ ፋንታ ያቀረበውን ልመናና ከእግዚአብሔር ያገኘውን መልካም ምላሽ ጽፋችኋል፡፡ ነቢዩ ኤልያስም በጸሎቱ ዝናብ እንዳይዘንብ መከልከሉን እንዲሁም በጸሎቱ ዝናብ ማዘነቡንም ለመግለጽ ሞክራችኋል፡፡ “ፈርኦን ባየው ህልም መሠረት ዮሴፍ በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ምርት እንዲከማች በማድረጉ ቀጥሎ በመጡት ሰባት የረሃብ ዓመታት ምንም ችግር ሳይፈጠር ሕዝቡ በሰላም እንዳሳለፈና ግብጽ ለሌሎች ጎረቤቶቿ ሁሉ እንደተረፈች በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፡፡” በማለትም ተርካችኋል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ- ግብጽ ከሰባት ዓመታት ረሃብ የተረፈችው በቅዱስ ዮሴፍ አማላጅነት በተገለጠው የእግዚአብሔር ቸርነት ነው ወይስ አይደለም? እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ማለትስ ምን ማለት ነው? ቅዱሳት መጻሕፍቱንስ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው የጻፉትስ ቅዱሳኑ መሆናቸውን ዘነጋችሁ እንዴ?

  እንግዲህ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ያከበራቸዉን ቅዱሳኑን የምታከብር እንጂ እንደ “አባ ሰላማዎች” የሐሰትና የክህደት ትምህርት የምትመራ አይደለችም፡፡ የምታመልከውም እግዚአብሔርን ብቻ ነው፡፡ ወልድ ዋሕድ ብላ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርዪ አምላክነት የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነትና አማላጅነት የምትመሰክር የጻድቃንን የቅዱሳንንና የሰማእታትን ክብራቸዉን የምትዘክር በቃል ኪዳናቸውና በአማላጅነታቸው የምታምንና የምትጠቀም ናት፡፡ ይሄውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነዉ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ሀገረ-እግዚአብሔር ተብላ በነቢያት በሐዋርያትና በሊቃውንት የተጠራችው በእነዚህ እውነታዎች ላይ ተመስርታ እንጂ ከመሬት ተነስቶ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚያዋጣችሁ እውነቱን ተረድታችሁ ወደ ተቀደሰችዉ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት መመለስ ወይም የለበሳችሁትን የበግ ለምዳችሁን አዉልቃችሁ ወደየአዳሮሾቻችሁ መሄድ፡፡

  ReplyDelete
 3. ለሰይጣኑ ይልቃል
  በክፋት ልቀያሀል ዲያቆን የሚለው ሥመ መአረግ አይመጥንህም። በመሆኑም ክፋቱ ይልቃል ለማንነትህ ተገቢ መጠሪያ ነው። ክፋት ደግሞ የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት የአባትህ የዲያቢሎስ ነው። አንተም ልጁ ነህና ክፋቱ ይልቃል( ይልቃል ክፋቱ) ለእውነት ተግዳሮትህ ተገቢ መገለጫህ ነውና መጠሪያመሆኑም ተገቢ ነው።
  እውነትን በመካድ በውሸት ማጥላላትና ያልተደረገን ተደረገ ብሎ መንዛት እውነትን ለሚጠሉና ወንጌልን የማያውቁ ዋነኛ ሥራቸው ነው። አንተ በውሸት ማሥመሰል ሰይጣናዊ ውጊያህን በእውነት ላይ ብትነዛ ለአንተ ይብስብሀል እንጂ አውነትን ልታጠፋት አትችልም።
  ለምን ጥላቻና ያንተው ሥላልሆነ ቤተ እምነት ከምትዘባርቅ የምታምነው ካለ ሥለዚያ እምነትህ አታወራም። ወንጌል ማሥተማርና ሲያቅታችሁና ስህተታችሁ በእግዚአብሔር ቃል ሲጋለጥባችሁ ያልሆነ ሆነ በማለትና በተራ ባዶ ማጥላላት ተጠመዳችሁ።
  እኔ ማነኝ ማለትና የራስህን ድክመት ማየት ትተህ የአለምን ሐጢያት ሁሉ አንዲት ቤተክርስቲያን ላይ መፈረጅ ክፉነትና መታመም እንጂ ሌላ አይደለም። ዝናብ አልዘነበም ተብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የምነት ተቋም ያለች በማሥመሠል ችግር በመጣ ቁጥር ካለበደሏ በደለኛ ብሎ መፈረጅ ነገ ያስፈርዳል።
  አቶ ክፋቱ ይልቃል፤ እውነቱ ቢገባህና አንዲት የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ባታሳድድ ኖሮ ይህ የዝናብ መጥፋትም ሆነ ሌላ ችግር ባልመጣ ነበር። አምላክ ያላደረገቻቸውን አምላክ ብላለች እያልክ ባትከስ ኖሮና እግዚአብሔር ቅዱ ሳኑ ሲከብር እንደሚከብር ብታውቅና የቅዱሳኑ መክበር አይንህን ደም ባታለብስ ኖሮ ይህ የምትለው ችግር ባልተከሰተ ነበር።
  አቶ ክፋቱ ይልቃል፦ ታቦትና ጣኦት ያልለየህ፣ ማክበርና ማምለክ የልተገነዘብህ፤ አምላክ በአምላክነቱ ሲመለክና ሲከብር፤ ቅዱሳን በቅድስናቸው እንደሚከብሩና እንደሚከበሩ ያላስተዋልክ ባዶ ሀሜተኛና ትችት ጥላቻ ነዠ ነህ። በዚህም የምትለው መከራ ሊሆን ችሏል።
  ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔር ሥለ እምነቷ በሰጣት ቅድስናዋ ትከበራለች እንጂ አትመለክም። አምላክ ናት ያለም የለም ካንተ በሥተቀር። ቅድስት አርሴማ ሥትከብር እግዚአብሔር ይከብራል በአምላክነቱ ይመለክ ይታወቃል።

  ReplyDelete
 4. ዳሞት ሁሉን ካልነቀፍ ደስ አይለህም ይህ ለአንተ እርግማን ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ባታስተዉሉም ይህን ፃፍኩላችሁ
   ልቦና ይስጣችሁ የእግዚአብህር ቸርነት እና ምህረት ይጎብኛችሁ፡፡ በ ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ የምትሰጡት አሳዛኝ እና ሠይጣናዊ ትምህርታችሁን ሳስብ ከዘመኑ መፍጠን ጋር በአንፃራዊነት አየዋለሁ፡፡አለም በዝሙት በነደደበት ዘመን ይብስ ብሎም በዚህ ዘመን ሠለጠንን በሚሉ አነበብን በሚሉ ሐገሮችና ህዝቦች እና መሪዎች እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ለመጣዉ የስልጣኔ መገለጫ ተደርጎ የተወሰደው ግብረ ሠዶም እንቅስቃሴ እና 666 አቀንቃኞች ጋር የናንተ የድፍረት ትምህርት እና ቅድስት ቤተክርስቲያን ለዘመኑ ክርስቲያኖች ከዚህ ሰደድ ሐጢያት መሸሸጊያ እንዳትሆን እናንተ ለጥፋቱ ሠራዊት መንገድ ጠራጊ በመሆን ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ተነስታችኋል፡፡ መልዕክታችሁ ከጥፋቱ ሠራዊት የመጣ መሆኑንስ ቆም ብላችሁ አስተዉላችሁ ታዉቃላችሁ ማስተዋላችሁን እንዲመልስ በጌታ ፊት ተንበርክካችሁስ ታዉቃላችሁ ይህን ጊዜ ይህን መልእክቴን በፌዝ እና በቀልድ እንደምትመለከቱት ሳስብ ልቤ ስለ እናንተ በጣም ያዝናል ለነገሩ ልቦናችሁ ታዉሯልና ለእኔ ብላችሁ አታነቡም አትመለሱም ይልቁንም በሠያጣናዊ ትዕቢት ለነገዉ የጥፋት መልዕክት ደፋ ቀና ስትሉ ይታየኛል፡፡እለት ተዕለት ቤተክርስቲያንን ከሚፃረር ከማንኛዉም ሠራዊት ጋር ስትሠለፉ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

   Delete