Sunday, August 9, 2015

ሙስና የተፈጸመበት “የመሬትና የሕንጻ ኪራይ ጥናታዊ ሪፖርት” ጥያቄዎች እየተነሱበት ነውከማንኛውም ተቋም ይልቅ ሙስና የተንሰራፋው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኙ አብዛኞቹ አድባራትና ገዳማት ውስጥ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ ወዲህ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እንቅስቃሴ ሲደረግ ነበር፡፡ በተለይም በሊቀ አእላፍ በላይ አስተዳደር ጊዜ እጅግ የነቀዘውንና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረውን ሙስናዊ አስተዳደር ለመለወጥ የተደረገውን ጥረት በዘረኛነት ፍላጻ ክፉኛ የተነደፉት እነአባ ማቴዎስ እንዳልሰሙና ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጥረው በቸልታ አልፈውት ነበር፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ሐራም በጉዳዩ ላይ አንድም ትንፍሽ ሳትል ነው የቆየችው፡፡ የኋላ ኋላ እውነተኛ ጩኸት ሲበዛ ግን ፈቃዳቻው ባይሆንም እነሊቀ አእላፍ በላይ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባለፉት ስምንት ወራት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር ባሉ አድባራትና ገዳማት ያለውን ሙስናዊ ተግባር የሚያጣራ ኮሚቴ ተሰይሞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ የማጣራት ሥራው ተሰርቷል ከተባለ በኋላ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ረጅም እጁን በየቦታው የሚዶለው ማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎቹ ያልሆኑትን ሙሰኞች ብቻ በመጥቀስ ትልልቅ የሙስና ወንጀል እየተፈጸመባቸው ያሉትንና የሚታወቁትን አድባራት በዝምታ እንዲታለፉ ማድረጉ ሪፖርቱ ላይ አመኔታን የሚያሳጣ ጥላ አጥልቷል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ወገን የቆሙትም ሆኑ ከማኅበረ ቅዱሳን በተቃራኒ የቆሙት ሙሰኞች በሙሉ ተጠያቂ ሊሆኑና ቤተክርስቲያን ከሙስናዊ አሠራር ነጻ ልትሆን የሚገባ በመሆኑ ላይ የጸና አቋም ያለን በመሆኑ በየስፍራው የሚታየውን የሙስና ወንጀል እየተከታተልን ጥቆማ ስንሰጥ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የተቋቋመው ኮሚቴ ከማኅበረ ቅዱሳን ረጅም እጅና ተጽዕኖ ነጻ ያልነበረ በመሆኑ ግን ስራውን የሰራው የተፈጸመውን ሙስና ሁሉ በሐቅ ማጣራት ሳይሆን ለማኅበረ ቅዱሳን አስተሳሰብ አልንበረከክ ያሉትን አድባራት ብቻ በሙስና እንዲፈረጁ የማድረግና ሌሎቹን ቀንደኞች አማሳኞች አነስተኛ ሙስና ያለባቸው አስመስሎ ነው ያቀረበው፡፡ ሙስናን በተመለከተ ወንጀሉን በወንጀልነቱ ማቅረብ ሲገባ ወገንተኝነትን መሰረት በማድረግ ማጥቃት የፈለጉትን አካል ለማጥቃት ብቻ “ጠላትን” ፈርጆ “ወዳጅን” ነጻ ማድረግ በማጣራቱ ሂደት የተፈጸመ ሙስና ነው፡፡ የተሰራው የማጣራት ስራ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም ለማስጠበቅ የተደረገ ነው የሆነው፡፡ ማንም ይፈጽመው ማን ሙስና በሙስናነነቱ ሊወገዝና ወንጀለኛውም ማንም ይሁን ማን በወንጀሉ ሊጠየቅ ነው የሚገባው እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ወይም አባል ስለሆነ በዝምታ መታለፍ ወይም “ዝቅተኛ ደረጃ” ሊሰጠው የማህበረ ቅዱሳን አባል ስላልሆነና ማህበሩን ስለሚቃወም ብቻ “ከፍተኛ ደረጃ” ሙስና ላይ ሊቀመጥ አይገባም፡፡ ደረጃው በሙስናው መጠን ሊሰጥ ነው የሚገባው እንጂ በወገንተኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም፡፡

ሪፖርቱ አባ ማቴዎስ ከሚመሩት የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ውሳኔ ጋር መቅረቡን ተከትሎ ወዲያው በፋንታሁን ሙጩ በኩል ለሐራ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ያልተጠራበት ሪፖርት ቢሆንም ሪፖርቱ ሪፖርተር (ዘጋቢ) የሌለው “ዜና” ሆኖ የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ በሆነው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን በአዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር እያጣ ያለውን ቁልፍ ቦታና ከፍተኛ ጥቅም መልሶ ከእጁ ለማስገባት የሚያደርገውን ጥረት ለማጠናከር መሆኑን አካሄዱን የተመለከተ ሁሉ ብዙ ምርመር ሳያደርግ የሚደርስበት ሐቅ ነው፡፡ ሐራ ብሎግ ሪፖርቱን ጠቅሶ በከፍተኛ ችግር ውስጥ አሉ ብሎ የዘረዘራቸው አድባራት 15 ሲሆኑ አድባራቱ ሙስና የሚፈጸምባቸው መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን አድባራቱ የሚታወቁት የማኅበረ ቅዱሳንን አመለካከትና አካሄድ የሚቃወሙ በመሆንም ነው፡፡ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ያሰኛቸውም በዋናነት ቀጥሎ ከምንገልጻቸው አድባራት ይልቅ ሙስና ስለሚፈጸምባቸው ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳንን ባለመደገፋቸው ነው፡፡ ከእነዚህ የከፋ ሙስና እየተፈጸመባቸው ያሉ አድባራት ግን የማኅበረ ቅዱሳን “ወዳጆች” ስለሆኑ ብቻ አልተጠቀሱም በሙስና ላለመከሰስ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ መገኘት እንደመፍትሄ እየተወሰደ ነውና፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ስላሉ አድባራትና ገዳማት ከሙስና ጋር በተያያዘ ከተነሳ ሳይጠቀሱ የማይታለፉ አድባራት ነበሩ ነገር ግን የማቅ ወዳጆች ስለሆኑ ብቻ የሙስናቸው መጠን ዝቅተኛ ሆኖ ወይም በደህና ሁኔታ ላይ ያሉ ተደርገው እንዲታዩ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ ያህል፦
1.   ሰሎሞን በቀለ ጸሐፊ የሆነበት የቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን
2.   ቄስ ሥዩም ወ/ገብርኤል የሚያስተዳድሩት የቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
3.   ዑራኤልን ሲበጠብጥ የነበረውና በዚሁ ምክንያት የተዛወረው ክብሩ አሁን አለቃ የሆነበት ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን
4.   ለማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ውለታ እየዋሉ ያሉት አባ ገብረ ሥላሴ የሚያስተዳድሩት ጎፋ ገብርኤል
5.   አባ ገብረ ሚካኤል የሚያስተዳድሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የሰንበት ት/ቤትና የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የተጨማለቁበት ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን
6.   የዋናዋ አማሳኚት የወ/ሮ መና ወንድም ቄስ ሩፋኤል ከፍተኛ ሙስናና ዝርፊያ የሚፈጽምበት ሰአሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን
7.   ቄስ በቀለ ተሰማ የሚያስተዳድሩት የመካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው አድባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ነገር ግን የተጠቀሱት ኃላፊዎች ባሉባቸው በእነዚህ አድባራት ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳንም የጥቅሙ ተጋሪ በመሆኑና በውስጣቸው ባሉ የልማትና የንግድ ተቋማት ውስጥ ተከራይና ተጠቃሚ የሆኑት ነጋዴዎች አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በመሆናቸው ብቻ በሙስና ብዙ ችግር የሌለባቸው ሆነው ቀርበዋል፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን ለዋሉት ውለታ የተሰጣቸው “የምስክር ወረቀት” መሆኑ ነው፡፡ ሆኖም ሪፖርቱን በተመለከተ አንድ የአስተዳደር ጉባኤ አባል ማጣራቱ ያነጣጠረው በአንድ ብሔር አባላት ላይ ነው የሚል አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን፣ አንድ የኮሚቴው አባልም አልፈርምም ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ችግሩን በማጣራት ሂደት የማኅበረ ቅዱሳን ጣልቃ ገብነት በሰፊው እንደነበረና ሌላ ድብቅ አጀንዳ የማራመድ ፍላጎት እንዳለ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሙስና የተፈጸመበት የማጣራት ሂደት ነው የተባለው፡፡

ከሁሉም የሚገርመው ሐራ በ10ኛ ተራ ቁጥር ላይ  ያስቀመጠው “ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን” ነው፡፡ የዚህ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የዋና ሥራ አስኪያጁ አባት መምህር ዘመንፈስ ቅዱስ በገንዘብ ጉዳይ የማይታሙና እንዲያውም የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ አላስበላ በማለት የሚታወቁ ከዚህ ቀደምም ዜና ቤተ ክርስቲያን ጭምር በጎላ ሚካኤል ካዝና ውስጥ 700 ብር ተረክበው እስከ 4 ሚሊየን ብር በማሳደጋቸው የተመሰከረላቸው አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ አሁን በሚያስተዳድሩት ብሥራተ ገብርኤልም በተመሳሳይ አቋም ላይ የሚገኙ ናቸው ይኸውም የደብሩን ወርኃዊ ገቢ በአማካይ 1.2 ሚሊዮን ብር እያደረሱት ይገኛል፡፡ ነገር ግን የማኅበረ ቅዱሳንን አፍራሽ ዓላማ የማይደግፉ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዓላማው ሙስናን በሐቅ ማጋለጥ ሳይሆን በሙስና ሰበብ ተቃዋሚዎቹን ስማቸውን በማጥፋት ማሸማቀቅ ስለሆነም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሊመሰገን የሚገባው ደብሩ በከፍተኛ ደረጃ ሙስና የሚፈጸምበት ሆኖ እንዲጠቀስ ተደርጓል፡፡

በአንጻሩ ጉልበተኛዋና አማሳኟ፣ የአድባራትን ካዝና በማራቆት የምትታወቀዋ ወ/ሮ መና (ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት በነበረች ጊዜ ለሠራተኛ የሚከፈል ደመወዝ እንኳን እስኪጠፋ ካዝናውን ባዶ አድርጋ ነበር፡፡ ከሙዳየ ምጽዋት ላይ ስትዘግን አይተው “ኧረ ብራችሁን አይጥ በላው” ብለው በፈሊጥ የተናገሩትን አለቃም በጥፊ በመማታት ጉልበተኛነቷን ያሳየች ሴት ናት) በሙሰኛነቷ የተዛወረችውን አማሳኚት ለአጥኚው መረጃ በመስጠቷ ተዛወረች ተብሎ እንዲዘገብ ተደርጓል፡፡ እያልን ያለነው እነዚህ ተጠቅሰው እነዚያ ለምን ሳይጠቀሱ ቀሩ አይደለም፡፡ ሙሰኞች በሙሉ በሙሰኛነታቸው ብቻ መጠቀስ ሲገባቸው ከሙሰኞች ተመርጦ ማኅበረ ቅዱሳንን የማይደግፈው ብቻ ሙሰኛ ተብሎ ለምን ይጠቀሳል? በዚህ መንገድስ ሙስናን መዋጋት ይቻላል ወይ? ይህን አጀንዳ ማኅበረ ቅዱሳን ለዓላማው ማስፈጸሚያነት እየተጠቀመበት ነውና የማኅበረ ቅዱሳን ወዳጅም ሆነ ጠላት ሙሰኛ እስከ ሆነ ድረስ በሐቅ ይለይና ቤተ ክርስቲያን ከሙስና ትጽዳ ነው፡፡
      
የሙስናው ዋና ተዋናይ የሆነውና በረቀቀ መንገድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት ለፖለቲካዊ ዓላማው በማዋል በገንዘብና በሀብት ክንዱን እያፈረጠመ ያለው ማኅበረ ቅዱሳንም አንዱ አማሳኝ ቡድን እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት አልገዛ ያለውና ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ውሳኔዎችን ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን የገቢ ምንጩን እንዲያሳውቅ በቤተክርስቲያን ሞዴላ ሞዴሎች እንዲጠቀም የተወሰኑትን ውሳኔዎች እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ያላደረገው ማኅበረ ቅዱሳን ተጠያቂ የማይሆነው እስከ መቼ ነው? ማኅበሩ የራሱ ሙስና እንዳለ ሆኖ የወዳጆቹንም ሙስና የሚሸፍንና በሙስናቸው እንዲገፉ “ጥላ ከለላ” የሆነ የማፍያ ቡድን ስለሆነ እርሱን ያልተመለከተ የፀረ ሙስና ትግል ግቡን አይመታም፡፡ ለዚህ ደግሞ በሙስና በነውር ሥራና በመሳሰለው ከማኅበሩ ተጽዕኖ ሥር የወደቁ  ጳጳሳትና ሌሎች የቤተክህነት ሃላፊዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ውሳኔዎች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ እያደረጉ ነው፡፡

የዚህ ኮሚቴ መቋቋም የተቀደሰ ሐሣብ ቢሆንም የማኅበረ ቅዱሳን እጅ ስለገባበት ዓላማው ሙሉ በሙሉ የተሳካ ነው ብሎ መናገር ግን አይቻልም፡፡ ኮሚቴው የተሳካና ኹሉንም ያካተተ ሥራ እንዳይሰራ ማቅ ያደረገ ከመሆኑም በላይ ተዛብቶ የቀረበውን ሪፖርት ለሌሎች ፍጆታዎቹ ለማዋል ተጠቅሞበታል፡፡ አንዱ ቦታ እያሳጣው ያለውን አዲሱን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አመራር ሥራ አልሠራም ብሎ መክሰስ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ የተለመደ ሁከት መፍጠሪያ አጀንዳን ማዳበር ነው፡፡ ሐራ እንደ ጻፈችው በአድባራትና በገዳማት በመሬት፣ በሱቆች፣ በሕንጻዎችና በመካነ መቃብር ተያይዞም በሌሎች የገቢ ማስገኛ ተቋማት -ሕጋዊ አሠራር ሲሠራ፣ ቃለ ዐዋዲው በአደባባይ እየተጣሰ የምዝበራ ኔትወርክ ሲዘረጋ ሀገረ ስብከቱ ምን ይሠራ ይኾን? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ መልሱም በተቋም ደረጃ የማይገለጽ ቢኾንም የጥቅም ትስስር ኔትወርክ እና በማጣራት እና በምርመራ ጊዜ በሚፈጸም እጅ መንሻ የሚድበሰበስ መኾኑን ያለፉ ተሞክሮዎችና በጥናቱ ሒደት ወቅት ከሀገረ ስብከቱ አካባቢ ይፈጸሙ የነበሩ ተግዳሮቶች  ማሳያ ሊኾኑ ይችላሉ፡፡” ብሏል አክሎም “ይህ ኹሉ የሕግ ጥሰት በአድባራት ደረጃ የተፈጸመ ቢኾንም የሕግ ጥሰት መካሔዱን በመከታተል ሕግ ማስከበር የሚገባው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም ከድንጋጌው ውጭ ለተሠሩ ሥራዎች ዕውቅና በመስጠት የሕግ ጥሰቱ አካል እንጂ የሕግ አስፈጻሚ መኾን አለመቻሉ የችግሩ ባለቤት ያደርገዋል፡፡” ሲል ከሷል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ሰዶ የቆየውን ሙስናን ለመታገልና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ተንቀሳቅሷል፡፡ በርካታ ለውጦችንም አስመዝግቧል፡፡ ስለዚህ ሀገረ ስብከቱ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን የሚለካው ግን ከራሱ ጥቅም አንጻር ስለሆነ በሙስናው የተዘፈቁና የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ሚና የነበራቸውን የወንዙን ሰዎች በሌላ ሳይሆን በአማሳኝነታቸው ብቻ የለውጡ ጎርፍ ስለጠረጋቸው ማቅ ቂም በቀል ይዟል፡፡ ስለዚህ የሀገረ ስብከቱን ስራ አስኪያጅ ስም ማጥፋትና የፈጠራ ወሬ እየፈበረከ ማውራት በቀድሞው አመራር የተፈጸመውን ሙስና በአሁኖቹ ስራ አስኪያጆች እንደ ተፈጸመ አድርጎ በማቅረብ ለማሳሳት እየሞከረ ነው፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሙስና ላይ የያዙት አቋም የሚደነቅና ሊደገፍ የሚገባው ነው፡፡ ከዚህ በበለጠም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ ሆኖም አባ ማቴዎስ የጸረ ሙስና ትግሉን ለማኅበረ ቅዱሳን እንዲመች አድርገው እያስኬዱት ስለሆነና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ስለሚመስል በጥንቃቄ ይታይ የሚል አስተያየት እንሰጣለን፡፡ በአባ ማቴዎስና በማቅ በኩል እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየታየ ያለውን ለውጥ ወደኋላ ለመመለስ የታቀደውን ዕቅድ ለመቀልበስ ሥራ አስኪያጆቹ በጀመሩት የለውጥ መንገድ መጓዝ አለባቸው፡፡ ለለውጥ የተነሱ ባለራእዮች እንደመሆናቸው መጠን በመንገዳቸው የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ተግዳሮት በመቋቋም ቤተክርስቲያንን ከሙስና ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ አሁንም ድረስ በሙስና ስማቸውን እያስነሱ ያሉ አንዳንድ ሙሰኞችን ማጋለጥና ተገቢውን አስተዳደራዊም ሕጋዊም ርምጃ መውሰድ፣ ለሙስና ከተመቻቸ የስራ መደብ ወደሌላው ማዛወር፣ አሠራርን ከዚህ የበለጠ ግልጽ ማድረግ፣ ባለጉዳዮች በተመደበላቸው ጊዜ ጉዳያቸው እንዲታይ ማድረግና አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት፣ ዝውውርና እድገት የሚደረግባቸውን ምክንያቶች በግልጽ ማስቀመጥ በዚያ መሰረት ዝውውር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወይም በሰራተኞች ጥያቄ ሕግን ተከትሎና የሰራተኛውን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መፈጸም ወዘተርፈ ይጠበቃል፡፡ 

እየመጣ ባለው ለውጥ ተጠቃሚ የሆኑና ለውጡን የሚናፍቁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኙ አድባራትና ገዳማት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞችና አገልጋዮች በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ለውጥ እየታየ በመሆኑ ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስራ አስኪያጆቹ ጎን መቆምና ለውጡን መጠበቅና መንከባከብ አለባቸው፡፡

13 comments:

 1. አቤት የናንተ መከራ!!! ስትተኙም ስትነሱም ፡ ስታስቡም ስትናገሩም ስትጽፉም: ....ጭንቅላታችሁ ዉስጥ የሚያቃጭለዉ ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ነው አይደል ??? ለምን አትታከሙም???

  ReplyDelete
 2. ኮሚቴዉ በሙስና የተዘፈቁ አድባራትን ያጋለጠዉ ከ 1500 ማስረጃዎች ላይ ተመስረቶ ነዉ ፡፡ እናንተ ግን በ ዜሮ ማስረጃ ማህበረ ቅዴሳንን ትወነጅላላችሁ፡፡ የምትገርሙ መናፍቃን ናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 3. We have seen few government official and few big business people who claim to be arch supporter EPRDF were exposed and thrown into jail on case of high level corruption. It is an open secret that to pretend political supporter and use ethnicity ties with people in high places are used as a cover to conduct corruption, altough it became an old fashion. In EOTC , such people claim to be supporters of the Government and Patriarch and label other as opponent of the church administration and government even as terrorist (are they paid by shabaye to make that its hand fabricated organization have sufficient members).
  Our Government knows that it was elected by more than 75 % of the population who support its achievement in economic development, securing lasting peace and want it to bring more results on the anti-corruption struggle and controlling inflation. Hence, it can not be manipulated by few vocal individuals who only supports themselves!

  As the Government has called upon the public to participate actively in the anti-corruption struggle, we menemena shall stand with our church to expose corruption till every last cent contributed by the public is accounted and an accountable administration and finance system is established.


  Abba selam, a fifth columnist in EOTC that want to stir protestant like reformation and naturally againstMmahibre Kidusan that also exposes heretic underground activities of tehadiso in EOTC feared that such struggle will make Mahibre Kidusan popular and is opposing it and is trying to forge unholy alliance between tehadiso and corrupt clergy! It is also trying to use an old fashioned divide and rule policy! If the Addis hagere sebekt believes that it belongs for the future, it shall work to establish anti corruption committee that involves members elected by Khanaett, Sunday school students and menmenan and free it selves from ethnic ties and political hangover! Moreover, the institutional approach of making each church corruptionproff that was on table by Abba Estifanos shall be revised and put in place!


  As God with us, EOTC will eventually overcome this challenge forging a strong unity!
  Amen!

  ReplyDelete
 4. The writer of this article must be among the corrupts. You will go to jail very soon man.

  ReplyDelete
 5. If Abaselama blog cries in support of someone, that must be either menafik, or corrupt or accuser of Mahiberekidusan. He must be the one standing far away from the truth

  Shame on you!! Leba!!

  ReplyDelete
 6. የውሸት ፋብሪካዎች የእውነት ጠሮች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አርበኛ ማኅበረ ቅዱሳንን ቢትጠሉ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ የአስተሳሰብ ሕመምተኛና የቤተክርስትያን ጠላት ባትሆኑ ኑሮ እግዚአብሔርና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር መሆናቸውን ትረዱ ነበር፡፡ የስድብ አፋችሁን በከፈታችሁ ቁጥርም ማንን እየተሳደባችሁ እንደሆነ ትረዱና ፈጥኖ እየመጣባችሁ ካለው ጥፋት ትድኑ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተመሰረተውን የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎትማ በአራቱም የዓለም ማዕዘናት የሚታይ የሚዳሰስና በአስደናቂ ውጤት በመንፈሳዊና ማኅበራዊ ለውጦች የታጀበ ነዉና፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች እንደ እናንተ የቤ/ክንን ሃብት የሚዘርፉና ኑፋቄን የሚዘሩ ሳይሆኑ እግዚአብሔር በሰጣቸው በእውቀታቸው ገንዘባቸውና ጉልበታቸው የሚያገለግሉ መሆናቸውን ማንም ጤናማና እውነት ፈላጊ ሰው በሁሉ ቦታ አይቶ የሚረዳ ሐቅ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ቤ/ክንን የሚያገለግሉትን ማኅበራትንም ሆነ ግለሰቦችን የሚጠላ ከሰይጣን በስተቀር ማነዉ? “አባ ሰላማዎች” እናንተ ሰ/ት/ቤቶችን ትጠላላችሁ:: ለቤ/ክን መልካምን የሚያደርጉ ማኅበራትን ትጠላላችሁ:: ደጋግ አባቶችን ትነቅፋላችሁ:: ክፉ አድራጊዎችን ታመሰግናላችሁ:: እናንተ የጨለማ ሠራዊት በብርሃን ስትገለጡ ምን ልትሆኑ ነው?

  ማኅበረ ቅዱሳን የቤ/ክ አካል እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ስለሆነም የቤ/ክ ጉዳይ ጉዳዩ ችግሯም ችግሩ ነዉ፡፡ እናንተ ደግሞ የቤ/ክንን ውድቀት የምትመኙ ሙሰኞች: ክፉዎችና መናፍቃን ቤ/ክንን ሲያዉኩ ጮቤ የምትረግጡ መሆናችሁ የታወቀ ነው፡፡ በዚህ ብሎጋችሁ የምታስተላልፉት በሐሰት የተሞሉ መልእክቶቻችሁ ሁሉ ለዚህ ምስክር ናቸው፡፡
  በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የተንሰራፋዉን ብልሹ አስተዳደርና ሙስና አጥንቶ እንዲያቀርብ ኃላፊነቱ የተሰጠዉ ለማኅበረቅዱሳን አይደለም (ቢሰጠዉም ኖሮ ችግር ባይኖረውም)፡፡ ይሄንን የማጣራት ሥራ የሠራ የትኛዉም አካል ቢሆን ሊመሰገን ይገባል፡፡ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍለዉ ከናንተ ብሎግ ጋር በመጋገብ የንቅዘት ሥራ በቤ/ክ ዉስጥ ሆነው ሲፈጽሙ የኖሩትን ነቀዞች ስላጋለጡ፡፡ እነዚህ ስለተጋለጡ ተቃጠላችሁን? ገና ትቃጠላላችሁ፡፡ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር ሥራ ስለተገለጠ የማኅበረ ቅዱሳን ደስታ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 7. በማኅበሬ ማኅበረ ቅዱሳን እጅግ እጅግ ኮራሁኝ! ተሀድሶን እንደዚ ዕንቅልፍ እየነሳ የሚያባንን ከሆነ! እውነቴነው የምላችሁ ማኅበሬን ከልቤ ወደድኩት!

  ReplyDelete
 8. ሙስናን፡ ዘረኝነትን እና ምንፍቅናን መደ ቅድስቲቱ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያስገባውን የረከሰ ዘረኛ ስርአት ፈጣሪ በቸርነቱ ከመንገድ እስኪያወጣው ድረስ አሁንማ ሙሰኛዉም ሙስናን በአንደበት የሚኮንነዉም ዳኛዉም ጠበቃዉም ሁሉም የዚያ የረከሰ ስርአት ውጤትና ተጠቃሚ ስለሆነ መሰረታዊ ለዉጥ መጥቶ ቤተክርስቲያን ነጻ ትወጣለች ተብሎ ተስፋ አይጣልበትም።

  ReplyDelete
 9. ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን የገቢ ምንጩን እንዲያሳውቅ በቤተክርስቲያን ሞዴላ ሞዴሎች እንዲጠቀም የተወሰኑትን ውሳኔዎች እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ያላደረገው ማኅበረ ቅዱሳን ተጠያቂ የማይሆነው እስከ መቼ ነው? ማኅበሩ የራሱ ሙስና እንዳለ ሆኖ የወዳጆቹንም ሙስና የሚሸፍንና በሙስናቸው እንዲገፉ “ጥላ ከለላ” የሆነ የማፍያ ቡድን ስለሆነ እርሱን ያልተመለከተ የፀረ ሙስና ትግል ግቡን አይመታም፡፡ ለዚህ ደግሞ በሙስና በነውር ሥራና በመሳሰለው ከማኅበሩ ተጽዕኖ ሥር የወደቁ ጳጳሳትና ሌሎች የቤተክህነት ሃላፊዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ውሳኔዎች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ እያደረጉ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለአቶ abebe August 11, 2015 at 6:44am
   የአቶ አበበ፦ ነገርህ ያረጀ የጠወለገ የመናፍቃኑ ከንቱና በወንጌል ማሳመን ወይም ማመን ሲያቅታቸው ተራ ክስና ሥም አጥፊነት ገብተው የሚያራምዱት ከራሳቸው ውጭ ተመልካች የሌለው ቧልት ነው። አንተም ከነሱ ወገን ነህና ጠዉልገህ የጠወለገ ተራ የውሸት ተሪናፋ ትነፋለህ። ለዚህ አይነት ነውረኛ ሥነምግባርና አይምሮ የተዳረጋችሁት ደግሞ እምነታችሁ በክደትና በማሥመሰል መንፈስ የተሞላና የሚመራ መሆኑ ነው። እናም አቶ አበበ ጠውልገህ የመጥፊያህ ቀን ከመምጣቱ በፊት በወንጌል እውነት አምነህ ነስሀ ግባ። ይህ ዘባራቂነት ህይወት አይሆንህም። ንፁህ ልብና ህሊና ይዘህ የማህበሩን ገቢና ወጭ አሠራር መጠየቅና መረዳት ትችላለህ። በእርግጥ በማህበሩ ላይ ከመሬት ተነሥበህ የምታራምደው ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጠላት ከመሆንህ ተነሥተህ ነውና የቤተክርስቲያኗ እውነተኛ አገልጋይ የሆነን ግለሰብም ሆነ ማህበር በሐሰት መወንጀልህና ሥም ማጥፋትህ የሚጠበቅ ተግባርህ ነው። በመሆኑም የማህበሩን ግልፅና የታመነ አሠራር ለመመልከት የማትፈልግ ልብህን በክፋትና አመፀኝነት የአጠነክርህ ነህ።

   Delete
 10. I am Christian but i was confused to be which member should I belong to : Abba Selam Or Mahibere Kidusan?
  Now I decided to stand beside Mahibere Kidusan cos I didnot see any spiritual matter from abba selama except abusing and insulting ....shame on Abba Selama

  ReplyDelete
 11. የሙስናው ዋና ተዋናይ የሆነውና በረቀቀ
  መንገድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት
  ለፖለቲካዊ ዓላማው በማዋል በገንዘብና
  በሀብት ክንዱን እያፈረጠመ ያለው ማኅበረ
  ቅዱሳንም አንዱ አማሳኝ ቡድን እንደሆነ
  ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን
  ሕግና ሥርዓት አልገዛ ያለውና ከዚህ ቀደም
  የተወሰኑ ውሳኔዎችን ለምሳሌ ማኅበረ
  ቅዱሳን የገቢ ምንጩን እንዲያሳውቅ
  በቤተክርስቲያን ሞዴላ ሞዴሎች
  እንዲጠቀም የተወሰኑትን ውሳኔዎች
  እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ያላደረገው
  ማኅበረ ቅዱሳን ተጠያቂ የማይሆነው እስከ
  መቼ ነው? ማኅበሩ የራሱ ሙስና እንዳለ
  ሆኖ የወዳጆቹንም ሙስና የሚሸፍንና
  በሙስናቸው እንዲገፉ “ጥላ ከለላ” የሆነ
  የማፍያ ቡድን ስለሆነ እርሱን ያልተመለከተ
  የፀረ ሙስና ትግል ግቡን አይመታም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለአቶ አበበ
   በሒሳብ ሙያ single entry and Double entry የ ሚባሉ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርኣቶች አሉ፡፡ ከነዚ ዉስጥ ባሁኑ ጊዤ double entry አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለዉ አሰራር ነዉ፡፡ ይህም አሰራር የ ሙስናን እና የማጭበረበርን በር ይዘጋል፡፡ ምከኒያቱም ማንኛዉም ሂሳብ በሁለት በኩል ስለሚመዘገብ፡፡ ማህበረቅዱሳንም ይህንን የ ሂሳብ አያያዝ ዠዴ ይጠቀማል፡፡ በሌላ በኩል ግን ቤተክርሰቲያን ይህንን ዘዴ አትጠቀምም፡፡ የልቁንም single entry ነዉ የምትጠቀመዉ፡፡ ከተቻለ ቤተክርሰቲን ናት ወደ double entry መቀየር ያለባት፡፡ ኦዲትን በተመለከተ ማህበረ ቅዱሳነ በዉጭ ኦዲተር ሂሳቡን ያስመረምራል፡፡ አባኮወትን ሙሰኞች የራሳቸዉን ሙስና ለመደበቅ የሚለፈልፉትን እርሶዎም እየደገሙ ኣያሰልቹን፡፡ እሰኪ የትኛዉ የ ማህበረቅዱሳን ሃላፊ ይህን ሙስና ሰራ ብለዉ ይነገሩን መረጃ ካለዎት፡፡

   Delete