Sunday, September 13, 2015

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች 13ኛ ዓመታዊ አንድነት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ


Read in PDF 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች 13ኛ ዓመታዊ አንድነት ጉባኤ ከነሐሴ 29 - ጳጉሜ 1/2007 በመካነ ሰላም መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል ኦክላንድ ካሊፎርኒያ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ፡፡ “ለእግዚአብሔር መቅናት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 13ኛው ጉባኤ በተለያዩ መምህራን የተዘጋጁ ትምህርቶች የተሰጡበትና ውይይቶችም የተካሄዱበት ነበር፡፡ ትምህርቶቹ መሪ ቃሉን አጉልተው ያወጡና ለአብዛኞቹ ታዳሚዎች ከፍተኛ መንፈሳዊ መነቃቃትንና በባዶ ሳይሆን በዕውቀት ለእግዚአብሔር መቅናት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከፍተኛ ግንዛቤ የተጨበጠበት ነበር፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙትና ጉባኤውን በቡራኬ የከፈተቱት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሲሆኑ ብፁዕነታቸው “በጉባኤው ላይ የተሳተፉት 150 ወጣቶች ቢሆኑም የሰንበት ትምህርት ቤቶቹ ኅብረት ካሳለፈው 13 ዓመት ዕድሜው አንጻር በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በጉባኤው ላይ የታደሙትን የሰንበት ተማሪዎቹንም “እናንተ የቤተ ክርስቲያን ተረካቢዎች ናችሁ” ብለዋል፡፡
ከብፁዕነታቸው በመቀጠል የሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ ኃላፊው አባ ገብረ ሥላሴ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የእርሳቸውን ንግግር ተከትሎም በቀሲስ በኀይሉ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ቀሲስ በኀይሉ በትምህርታቸው ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ከቀና በኋላ እውነትን ማወቅና ለእውነት መኖር እንደሚጀምር የተናገሩ ሲሆን፣ እውነትም ክርስቶስ እንደ ሆነ ከዮሐ. 4፥42 ላይ የሰማርያ ሰዎች ለሰማርዪቱ ሴት የተናገሩትን “አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም፥ እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።” የሚለውን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡ እውነት ማለት ሐሰትና የሐሰት ትምህርት ያልተቀላቀለበት የሐሰት ፍጹም ተቃራኒ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ውሸት ደግሞ የዲያብሎስ ሥራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
“እውነት የምንለው ማነው?” በሚለው ነጥብ ዙሪያም ክብር ምስጋና ይግባውና እውነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከዮሐንስ 14፥6 ላይ በመጥቀስ ያብራሩ ሲሆን፣ “እውነት ማለት ጸጋን የተቀበልንበት፣ የልጅነት ክብር ማዕረግ ያየንበት፣ ወደ እውነት መንገድ የምንጓዝበት፣ ወደ አብ የምንቀርብበት፣ የዘላለም ሕይወት የምናገኝበት እውነት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ብለዋል፡፡
“እውነት የሆነው ጌታ እንዴት ይገለጣል?” ለሚለው ቀጣዩ ነጥብ ቲቶ 1፥2-5 ላይ ካለው የእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ “የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ” የሚለውን ካብራሩ በኋላ ይህ እውንት ቃሉን በመስበክ የሚገለጥ መሆኑን “በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤” በሚለው ሐዋርያዊ ቃል መሠረት ወንጌልን ወይም ቃሉን ብቻ በመስበክ እውነት እንደሚገለጥ አስረድተዋል፡፡
እውነት የሚገለጠው ደግሞ ለማንም ሳይሆን ለአማኞች መሆኑን ቀሲስ በኀይሉ አብራርተዋል፡፡ ብዙ ስላነበብንና ዕውቀቱ ስላለን ብቻ እውነት ሊገለጥ እንደማይችልና እውነት እንዲገለጥልን የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወት ሰጪነቱና እውነትን ገላጭ መሆኑን ማመን ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር እውነት በፍልስፍናና በዕውቀት ሊገለጥ አይችልም መጽሐፍን በማንበብ ብቻም ማወቅ አይቻልም፡፡ እንዲያ ቢሆን ኖሮ ስለእርሱ የሚናገሩትን መጻሕፍትን እያነበቡ እርሱን ማወቅ ባልተሳናቸው ነበር በማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን ለዕውቀት ብቻ እንጂ ለሕይወት ያላነበቡትን አይሁድ ተሞክሮ ጠቅሰዋል፡፡ “እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።” (ዮሐ 5፥ 39-40) ስለዚህ እውነት የሚገለጠው እንደ አይሁድ ለዕውቀት ያህል መጻህፍትን በመመርመር ሳይሆን በእምነትና የእግዚአብሔርን እውነት በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት መረዳት ለሚፈልግ ትሑት አማኝ ነው ብለዋል፡፡  
“እውነትን እንዴት መረዳት እንችላለን?” በሚል ባነሡት ቀጣይ ነጥብ ደግሞ በማቴ 11፥25 ላይ “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤” በሚል የተሰፈረውን ቃል መሠረት በማድረግ እውነት በራስ ጥበብና ማስተዋል በመደገፍ ሳይሆን እግዚአብሔር ሲገልጥልን መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ስለዚህ ማንም እውነትን ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር ሊገልጥለት ስለሚያስፈልግ ወደ እግዚአብሔር በእምነት መቅረብ አለበት፡፡ 
እውነትን በደቀ መዝሙርነት ብቻ እና መዝሙር በመዘመር ብቻ ማወቅ እንደማይቻል ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሕይወት በመጥቀስ ያብራሩት ቀሲስ በኀይሉ፣ ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ ከጌታ ጋር እየኖሩ ጌታን ያለማወቅ ጉድለት ነበረባቸው በማለት  ጌታ ለፊልጶስ የሰጠውን ምላሽ ጠቅሰዋል “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?” (ዮሐ. 14፥9)፡፡ በተጨማሪም መዝሙር በመዘመር ብቻ እውነትን ማወቅ እንደማይቻል አሁንም ከደቀ መዛሙርቱ ልምድ ጠቅሰዋል፡፡ ጌታ በተያዘባት ሌሊት ከደቀመዛሙርቱ ጋር መዝሙር እንደ ዘመሩ የተጻፈ ሲሆን መዝሙር የዘመሩት ደቀመዛሙርት ግን በኋላ ላይ ጥለውት ሸሽተዋል (ማቴ 26፥30)፡፡ ይህም የሚያሳየው መዝሙር መዘመር ብቻውን በተግባር የሚገለጥ እውነትን ማወቅ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡ በተለይም ይህ ለሰንበት ተማሪዎች ትልቅ መልእክት ነው፡፡ ስለዚህ የሰንበት ተማሪዎች መዝሙር መዘመር የመጨረሻ ግብ እንዳልሆነና ከዚያ ባለፈ እውነትን ማወቅ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ 
ሌላው እውነትን የማወቂያ መንገድ ጌታ በውስጣችን ሲገለጥ ነው፡፡ ለዚህም በ2ቆሮ 3፥17-18 “ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።” የሚለውን ጠቅሰዋል፡፡ አክለውም በዚህ ጊዜ የሕይወት መንገድ ጌታ ብቻ እንደሆነ እንረዳለን (ዮሐ 6፥68)፡፡ በጌታ እንኖራለን፤ በጌታ ስንኖር ሞት አይነግሥብንም፤ ሞትም የለብንም (1ቆሮ 15፥55 ኢሳ. 35፥10 ራእ 7፥13) ይህም ብቻ አይደለም በጌታ ስንኖር ኩነኔም የለብንም (ሮሜ 8፥1-2)፡፡
በትምህርቱ መጨረሻ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የመወያያ ጥያቄ የነበረውም “እውነት በዘመናችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ቦታ አለው” የሚል ነበር፡፡ ነጥቡ እጅግ አነጋጋሪና ብዙዎች የሐሳብ ፍጭት ያደረጉበት ሲሆን፣ በቤተክርስቲያናችን በእውነት ዙሪያ ያለውን ክፍተት በግልጽ መገንዘብና ማስተዋል የተቻለበት ነበር፡፡ በትምህርቱ አብላጫው ታዳሚ ወይም 95 በመቶ ያህሉ ተደስቶበታል፡፡
2ኛ ትምህርት የአባ ገብረ ሥላሴ ሲሆን፣ እርሳቸውም “ራሴን ለእግዚአብሔር እንዳለስገዛ የሚይዙኝ መሰናክሎች ምንድናቸው” በሚል ርእስ ነው ያስተማሩት፡፡ ዝሙት ርኩሰት ራስ ወዳድነት በቀል ውሸት ነገረ ሰሪነት አጭበርባሪነት ለሌሎች አለመታመን ለእግዚአብሔር ቃልና ለፈቃዱ አለመታዘዝ፣ ምክንያት መደርደርና የመሳሰሉት እንደሆኑ ገልጸው በእነዚህ ምክንያቶች የሰይጣን ኃይል፣ የሥጋ ኃይል፣ የሥልጣን ኃይል፣ የገንዘብ ኃይል የዓለም ኃይል ለእግዚአብሔር እንዳንገዛ ያደርጉናል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ራስን ለእግዚአብሔር አስገዝቶ መኖርና ለእግዚአብሔር መቅናት ሲኖር እነዚህ ነገሮች ኃይል ያጣሉ፡፡ እኛም በድል ሕይወት ውስጥ መመላለስ እንጀምራለን ብለዋል፡፡
3ኛው ትምህርት “ፍቅርና ለአእምሮ የሚመች አገልግሎት” በሚል ርእስ የቀረበ ሲሆን በቀሲስ ተገኑ ወርቅነህ ነው የቀረበው፡፡ በእርሳቸው በኩል ፍቅር በክርስትና ሕይወት ውስጥ ዋናው ነገር መሆኑን ጠቅሰው “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም” የሚለው ቃል ጠቅሰው አብራርተዋል (1ዮሐ. 4፥8)፡፡ የፍቅርን ምንነት፣ ፍቀር በሥራ እንጂ በቃል ብቻ የሚገለጥ አለመሆኑን (1ዮሐ. 3፥18)፣ የእርስ በርስ ፍቅር የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለመሆናችን መታወቂያው መሆኑን (ዮሐ. 13፥33) አብራርተዋል፡፡ ከአገልግሎት ጋር በተያያዘም የአገልግሎትን ምንነት ያስረዱ ሲሆን፣ አገልግሎት ከእግዚአብሔር ዋጋ የሚያስገኝ (ዕብ. 6፥10)፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት መሆኑን (ገላ. 1፥10)፣ ለአእምሮ የሚመች (ሮሜ 12፥1) መሆኑን ያብራሩ ሲሆን፣ አገልግሎት በቸልተኝነት መደረግ እንደሌለበትም ኤር 48፥10ን በመጥቀስ አስተምረዋል፡፡
በመጨረሻም “ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው” በሚል ርእስ በዝማሬ ላይ ያጠነጠነ ትምህርት የሰጡት ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ናቸው፡፡ የትምህርታቸው ዐላማዎች
1.     የመዝሙርን ትክክለኛ ትርጉም መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ያለንን የአምልኮ ቅንዓት በዝማሬ እንዴት እንደምንገልጽ ማሳየት፣
2.    በመጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር  የተሰጡ የጸሎትና የዝማሬ ቃላትን ለሌሎች መስጠት እንደማይገባ ማስገንዘብ፣
3.    እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዓይኖቻችንን በመላእክት፣ በሰዎችና በሌሎች ፍጥረታት ዝማሬ ወደሚቀርብለት ወደ ታረደው የእግዚአብሔር በግ (ራእ. 5፥6-14) ማቅናት እንዳለብን መጠቀሞ ነው ብለዋል፡፡
መዝሙር ምን እንደሆነ? ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎችን በመስጠት ያብራሩ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማኅበረ እስራኤል በጉባኤ (ዘፀአት 15፥1-18 እንዲሁም መሳፍንት 5፥2-3) ከግለሰቦች ደግሞ የሳሙኤል እናት ሐና (1ሳሙኤል 2፥1-10) የሠለስቱ ደቂቅን፣ የዳዊትን (መዝሙር 148፥1-13) የጠቀሱ ሲሆን ከሐዲስ ኪዳን ደግሞ የድንግል ማርያምን መዝሙር (ሉቃስ 1፥47-55) ለታረደው በግ ከመላእክት በምድር፣ ከምድርም በታች ያሉ ሌሎች ፍጥረታት ሁሉ መዝሙር (ቅኔ) (ራእይ 5፥9-13 7፥9-12) የጠቀሱ ሲሆን፣ “ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና” የሚል ንኡስ ርእስ በሰጡትም ክፍል ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መጽሐፈ ሰዓታትን ጭምር በመጥቀስና ከቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢር ጋር በማገናዘብ ዝማሬ ለእርሱ ብቻ ሊቀርብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ “ሰላምታ ዘጉባኤ ጻድቃን” በሚል ሌላ ንኡስ ርእስ ስርም ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በመጥቀስ የቅዱሳን ስፍራ የት እንደሆነ አሳይተዋል፡፡
“እንዴት እንዘምር?” በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ደግሞ አንድ ሰው ከመዘመሩ በፊት ሊያውቃቸው የሚገቡትን መሰረታዊ ነገሮች አስጨብጠዋል፡፡ በዚሁ መሠረት፦
1.     የምናመልከውን ጌታ በማወቅ (ቆላስይስ 3፥24፣ ሉቃስ 17፥10)
2.    ከልብ በሆነ ሐሤትና ደስታ (1ሳሙኤል 1፥13 ቆላ. 3፥16)
3.    በቅድስና (ዘፍጥረት 4፥4 ሮሜ 12፥1)
4.    በአንድ ልብ (ያለመከፋፈል) (ቆላ. 3፥12-17)
የሚሉ ነጥቦችን በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሠረት አቅርበዋል፡፡ በማጠቃለያቸውም ለአገልግሎት ከመሰለፍ በፊት የምናገለግለው ጌታ ማን እንደ ሆነና ከእኛ ምን እንደሚፈልግ ማወቅ እንደሚገባ፣ የእርሱን የትሕትና መንገድ መከተል እንደሚገባና “የምስጋናን ንጉሥ” በልባችን መሾም እንዳለብን አስገንዝበዋል፡፡
ከትምህርቱ በኋላ ውይይት የነበረ ሲሆን የመወያያ ነጥቦቹ ሦስት የካሴት ዝማሬዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ በመፈተሽ ላይ የጠመሰረተ ሲሆን የተጠቀሱት ዝማሬዎች፦
“ድጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምሕረትን ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሐዘኔን” የሚለው
“ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።” በሚለው የመዝሙር 39/40፥1 ቃል፣
ገብርኤል/2/ ስለው ሰምቶ መጣ ወደኔ ፈጥኖ ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ” የሚለው የካሴት መዝሙር ደግሞ
“አቤቱ ወደ አንተ በለመንሁ ጊዜ ጸሎቴን ስማኝ (መዝ.63/64፥1)
“ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደአንተ ይመጣል (መዝ. 64/65፥1)፣
“አምላኬ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ” (ዳን. 6፥22) በሚሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተመዝነዋል፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው አንዳንድ መዝሙሮች ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ እንደሚቀርቡና ሕዝቡን ወደተሳሳተ አምልኮ እየመሩት እንደሆነ ነው፡፡
በአጠቃላይ የዘንድሮው 13ኛ ጉባኤ እጅግ በተሳካና ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ነው የተከናወነው፡፡ ልዩ የሚያደርገውም ከሌሎቹ ጉባኤዎች ይልቅ ክርስቶስን ማእከል ያደረገ በመሆኑ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ የተሰጡ ትምህርቶች ጥሩና ወቅታዊ የነበሩ ሲሆን የተወሰኑ ከቶሮንቶ በመጡ ወጣቶች ሰይጣን ክፉ ሥራውን ሊዘራ ፈልጎ የነበረ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ያ ከቁጥር እንዳይጣፍ አድርጎ አክሽፎታል፡፡ ምን ጊዜም እውነተኛ ነገር ባለበት ሁሉ እንዲህ ዓይነቱ የጠላት ሥራ መኖሩ የማይቀር በመሆኑ ከተሰጡት ትምህርቶች አንጻር ለዚያ ትኩረት የሰጠም የለም፡፡ ጉባኤውን በሚረብሹ ሰዎች መደግገጥ አያስፈልግም፡፡ 
ለዚህ ጉባኤ እንዲህ መሳካት የመምሪያ ኀላፊውን ከእርሳቸው ጋር ሆነው በኮሚቴነት ያገለገሉት ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ በተለያዩ ርእሶች ላይ ያስተማሩትን መምህራንም ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ቄስ / መብራቱን እውነተኝነት ምን እንደሆነ አሳይተዋልና ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በውጭ ያለውን የወንጌል እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የሚሰሩ ሰዎች በስውር ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ እነርሱም 1 ከአትላንታ ቅድስት ማርያም አባ /ሚካኤል፣ 2 ከሎስአንጀለስ ቅሰድስት ማርያም አባ ቶማስ፣ 3. ከኦክላንድ ኢየሱስ አባ /ሚካኤል፣ ከዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቄስ አንዷለም፣ 5 ከቶሮንቶ ቅድስት ማርያም መሪጌታ ተስፋ እና ከዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ፍሬስብሐት ናቸው፡፡ ይህን በጣም የረቀቀና በቀላሉ እንዳይደረስበት ተደርጎ እየተሠራ ያለውን የወንጌልን አገልግሎት የማደናቀፍ ሥራ በውጭው ሲኖዶስ ስር ያሉት የወንጌል አገልጋዮች እየተከታተሉ እንደሆነ መረጃው ደርሶናል፡፡ መረጃው ተጠናክሮ እንደደረሰን ይፋ እናደርጋለን፡፡

13 comments:

 1. I have a question. So your telling me the true father under the American Synod are 1) Abune Yacob (Aka Abba Gebremariam) 2) Abune Yosef 3) Abune Samuel (aka Abba Gebremariam) 4) Abune Yohannes (aka Abba Birhanhiwot) 5) Abba GebreSelassie 6) Kesis Melaku 7) Abba Woldetensai 8) Abba Habtemariam 9) Abba Lakiemariam 10) Kesis Merbatu 11) Memhir Leulkal 12) Memhir Tekeste
  if so, I can write an article about each one of them. It's funny how this article is very all one sided. If you are suppose report news then you don't have to express your opinion within your article. This is called being biased. The fake American Synod is split into two groups you are supporting one group and demoting the other side because you are in favoritism. The funny thing is you named everyone that goes to Dallas Kidus Mikael for beal's. This strongly seems like a personal hate towards these individuals. While you were at it why didn't you name the other fathers you have a problem with as well?

  ReplyDelete
 2. Agreed with the first comment. Now I am forced to ask who is responsible for this web site? Is this really NEWS or personal comment? Why not detail of the type of the 'obstacle planned by devil' is clearly mentioned in detail? What is the evidence that the individuals listed at the bottom of the article are being obstacle for the spread of Gospel? Is that the fact they are serving the church from their heart? One can easily observe that the writer of this article and people behind him/her have personal problem? I wish to know who is responsible for this annual North American Sunday School's meeting? Are they checking the content of such article before someone post in their behalf? A lot of questionable contents in it.

  ReplyDelete
 3. Anonymous One: Can you please write an article on each of them as you said? Or at least could you please give as a brief introduction to each of them (to the 12 Abatoch/Memehiran) whose name you mentioned? We really need to know them.

  ReplyDelete
 4. የእግዚአብሔር ቤተሰቦች !
  እንደሚታወቀው እኛ እንደ ባሕል አድርገን የያዝነው በሰንበት መሰብሰብን ራሳችንን ለሥጋዊ ድግስ መጋበዝ ደስ ይለናል። በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሸቀጥ የሚሸጥበት ዘመን ደርሰናል። የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ነው። መጽሀፍ እንደሚያስተምረን " ልጁ ያለው ሕይወት አለው" ይላል። ነገር ግን እኛ በራስችን ጥበብ ለሥጋችን በማዳላት በዚሁ የተሰበሰቡት አባቶችና ወንድሞች የእግዚአብሔር ቃል በመዝሙር ሆኖ ሲቸረቸር የጥቅሙ ተካፋይ በመሆን አንድም ቀን በቤተ ክርስትያናችን ሲያወግዙ ወይም ይህ ትክክል አይደለም ብለው ሲቃወሙ አይታዩም። በተመሳሳይ መልኩ ሰዎች ሊድኑበት የተሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ባለመመገባችን ምክንያት " ኢየሱስ" ተብሎ ሲነገር የሚደነግጡም ብዙዎች ናቸው። ሌላው ይቅር ሰዎች በጠላት ተይዘው ሲሰቅዩ የሚድኑበትን መንገድ ሲፈልጉ አሁንም በቤተ ክርስትያን ያሉ አባቶች ሰው የሚድንበትን የመንፈስ ስይፍ ለክርስትያኑ ባለማስታጠቃቸው ምክንያት ብዙዎች ሞተዋል። ይህም ብቻ አይደለም ሰዎች ሊድኑበት በሚችሉበት መንገድ እግዚአብሔር አንዳንድ ቅዱሳን የሆኑ ሰዎችን በሚሰድበት ወቅት በቅናት ለምን ከእናንተ ስይጣን ይወጣል አትሂዱ! አትዳኑ ብለው ሰዎችን የሚከለክሉ ሁሉ ዛሬ በአዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላሉ። ነገር ግን ፍቅር የሆነውን በመጽሀፉ የተጻፈውን እውነተኛውን እግዚአብሔርን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም የተረዳው የለም። ቃሉን በመደርደራቸው ሁሉን ያቅሉ ማለት አይደለም። እግዚአብሔርን ለማወቅ ጥበብ ያስፈልገናል። እውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ በተናገረው ቃል መሠረት " 40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" (ማቴ. ም12) ይላል። እስኪ ከዓርብ ቀን ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ይህንን ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት ብሎ የሚያስረዳን ይኖራል???? ስለዚህ መጽሀፉ እንደሚያስተምረን እውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት በምድር ልብ ቆይቶ ሞትን ድል በማድረግ የተነሳ የእግዚአብሔር የበኩር ልጅ ነው። ከእርሱስ ቀድሞ የተነሳ ወይስ በኋላ የተነሳ አለ? ወንጌላውያን ሊያስረዱን ይችላሉ?? ይህንን በመጽሀፉ ከተረዳን እውነተኛውን ኢየሱስ ክርስቶስን እናውቀዋለን ማለት ነው። አመስግናለሁ!

  ReplyDelete
 5. ca article was written is wrong and the fathers you mention on your article they send their senbit mezmrian representing their church and those fathers that you accusing they are true disciples the reason why you single them out 1st you are bias and you are a divider rather than a preacher you might call yourself you are a true disciple you need to ask your conscious. It's ridiculous that you talk about sendos there is none. God people know whats going on we are not foolish any more we are sick and tired of distortion.

  ReplyDelete
 6. Wrong information that's a lie

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመናፍቃን ስውር ደባ በራሱ ሲገለጥ
   እነዚህ ስማቸው የተገለጸው የእውነተኛዋንና ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛውንና ያልተበረዘውን አገልግሎት በመስጠት ሕዝበ ክርስቲያኑን እያገለገሉ ያሉ አባቶች ናቸው።
   ትምህርት የሚያስተምሩና እናንተ መናፍቃን የቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ሀብት የሆነውን ያሬዳዊ ዜማ እናንተ አውጥታችሁ ለመጣል የምታደርጉትን ጥረት ስለአጋለጡና ሀብታችንን ወጣቱ ተተኪው ትውልድ እንዲያውቀው በማድረጋቸው እንደተከፋችሁ እናውቃለን። ወንጌሉንም ሃዲስ ከብሉይ እየጠቀሱ ሳትጨምሩ ሳትቀንሱ አስተምሩ በማለት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠው መሪ ቃል የሚያስተምሩ በመሆናቸው ለወንጌል መስፋፋት የሚጥሩ እንጂ እናንተ መናፍቃን የተሃድሶ አራማጆች እንደምትሉት አደናቃፊዎች አይደሉም ኧረ ወዴት ወዴት የእምዬን ወደ አብዬ ልክክ ይሏችኋል ይሄ ነው። እናንተ እንደምትሉትና እንደምትቃጁት አለመሆኑን ሕዝበ ክርስቲያኑ ካወቀ ውሎ አድሯል።
   እናንተ ለሸቀጥ ስሩ እነርሱ ደግሞ ለእውነተኛይቱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ምዕመናን እውነተኛውን፤ ያልተከለሰ፤ ያልተበረዘ ፫፻፩፰ አባቶች ያጸደቁትን ስርዓት ጠብቀው ያገለግላሉ።
   ልብ ይስጣችሁ፤ አይኔን ግንባር ያድርገው ብሎ ከማለት ያድናችሁ።
   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘለዓለም ትኖራለች!!!!!!!!!!!!!!
   የመናፍቃን ተሃድሶ ሩጫ ይቆማል!!!

   Delete
 7. I'm so eager to see the result of the last sentence...'We will notify you when we receive complete evidence'.

  ReplyDelete
 8. እንደናንተ አይነት ወንጌላውያን አይተንም ሰምተንም አናውቅም።
  ግለሰቦችን ወንድም ከሳሾች እያላችሁ በቀንም በሌሊትም ባልሰላ
  ብዕራችሁና ባልተባ አንደበታችሁ የእርኩም ጬኸት ትጮኻላችሁ። ታዲያ እናንተ ወንድምን በመክሰስና በመውቀስ ፈንታ እያወደሳችሁ ይሆን? እስኪ ለሰአታትና ለደቂቃዎች አልልም
  ለሰከንድ ሥራችሁን ከቅዱሱ ቃል አንፃር ተመልከቱት፡ እናንተ እንደምትሉት ወንጌላውያን ከሆናችሁ በየትኛው መፅሐፍ ነው
  አንድ ወንጌላዊ የግለሰቦችን የግል ቂም ለመወጣት ሲል ግለሰቦችን ሰድቦ የሚአሰድብ ተሰናክሎ የሚአሰናክል???
  ቅዱስ ቃሉ ባየነው እና በሰማነው ብቻ ምስክሮች እንድንሆን ይነግረናል፡ ያ ማለት አይተንም ሰምተንም ማለት ነው። ታዲያ እናንተ እያያችሁና እየሰማችሁ ይሆን የምትመሰክሩት?? አይደለም
  በመስማት ብቻ ነው። ለምሳሌ በማየት ሳይሆን በመስማት ብቻ ከላይ የጠቀሳችኋቸውን ግለሰቦች ማየት ይቻላል።ስለነዚህ ሰዎች
  በህሊና ዐይን በሚአዩቸውና በህሊና ጆሮ በሚሰሙአቸው ሰዎች
  የሚመሰከረው ሌላ እናንተ የምትከሱት ሌላ፡ ይህን ሁሉ የሚፈጥረው ለግል ስሜት መገዛት፣ ነገሮችን በህሊና ዐይን አለማየትና በሰዎች ጭንቅላት መመራት ስለሆነ የህሊናችሁን ዐይን እንዲአበራ የህሊናችሁን ጆሮ እንዲከፍት የድንግል ማርያም
  ልጅ ወደ ሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኑ።

  ReplyDelete
 9. እናነተ የምትሉት አንድነት ጉባኤ እንደው ያንድነት ሳይሆን እናንተ የምትፈልጉትን የተሃድሶ ጉዳያችሁን የምታሰለጥኑበት ጉባኤ ነው እውነት ስለንድነት ታምናላችሁ፡ ትሰብካላችሁ በጣም ያሳዝናል በልባችሁ መለወጥ ታደሱ አዲስ ሰዎች ሁኑ ነው እንጂ የሚለው ቃሉ ሃይማኖታችሁን አድሱ ያላችሁ ማነው እባካችሁ የናንተ መጥፋት አልበቃ ብሎ ልጆቻችንን ይዛችሁ አትጥፉ እውነቱ ይህ ነው ይህን ጉዳያችሁን ለመሽፋፈን በንጹህ መንገድ ይችን የተክበረችና የተቀደሰች ሃይማኖታችን ስረቷን ይጠበቅ ስላሉ አፍራሽ ብላችሁ ስም ታጠፋላችሁ እግዚያብሄር ትግስተኛ አምላክ ነው ብዙ ያወቃችሁ መስሏችሁ ከመውደቃችሁ በፊት ቁሙና አስቡ ጸልዩ በፍቅር አገልግሉ በልህ አይደለም አገልግሎት በከንቱ ውዳሴ እንድይሆንባችሁ።እኔ የምላችሁ እናንትው ናችሁ የክርስቲያኑን ምንም የማያውቀውን የዋህ ህዝብ እያወናበዳችሁ ያላችሁ ብዙ መእመናን አውቆባችኋል ትንሽ ጊዜ ነው የሚፈልገው ከእግዚያብሄር ፈቃድ ጋር ተውን እውነተኛዋን ተዋህዶ እናምልክበት ይህ ከከበዳችሁ ደግም ከረባታችሁን ደንቅሩና ያው ለይቶላችሁ ከዝመዶቻችሁ ጋር ተቀላቀሉ አስመስሎ ማምለክ አይፈቀድምና በፈጠራችሁ እግዝያብሄርን ፍሩት ሃያሉ አምላክ ምህረቱና ትእግስቱ የማልቅበት ለሁላችንም በንህረቱ ይማረን።

  ReplyDelete
 10. በቶሮንቶ ቅድሥት ማርያም ቤተከርስቲያን የተነሳው የሃይማኖት ውዝገብ ና መንስኤው

  የውዝገቡ መንስኤው የሆነው የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት የተሰጠው በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች 13ኛ ዓመታዊ አንድነት ጉባኤ ላይ ሲሆን የትምህርቱ ርእስ “ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው” የሚል ሲሆን በዚህም ትምህርታቸው ላይ “ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና”በሚል ንኡስ ርእስ "ዝማሬ ለአምላክ ብቻ ሊቀርብ እንደሚገባ በመናግራቸው ክቶሮንቶ በቦታው ከተገኙት ምአመናን በቦታው ከፍተ ተቃወሞ አስምተዋል

  የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት እንዳበቃ በጉባኤው በተደረገው ውይይትም ላይ "“ድጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምሕረትን ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሐዘኔን” ብሎ መናገር በራሱ ምመጽሐፍ ቅዱስ የማይደገፍ ነው ተብሎ በድፍረት በጉባኤው በስፋት ተነግሮአል የዚህን ጉባኤ ዝርዝር በበለጠ ለመረዳት ክዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ

  http://www.abaselama.org/2015/09/13.html#more

  እነዚሁ የእመ ቤታችን እና የቅዱሳን ፍቅር የአንገበገባቸው የቶሮንቶ ምአመናን በአንድነት ጉባኤው ላይ በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ የተስጠውን የስህተት ትምህርት እርምት እንዲደርግበት በመጠየቃቸውና ትምሀርቱ ምንም ስህተት የለውም ተብሎ ከካቲድራሉ አስተዳዳሪ ጉዳዩን ለማስተባበል በመሞከሩ ክፍተ አልመግባባት አስነስቶአል ::አስትዳዳሪው l ሊቀ ካህናት ምሳለ እንግዳ ለብዙ ዘመናት የደክሙበት ቤተከርስቲያን የመናፍቃንና የተሃድሶ መ ታጎሪያ እንዲሆን ይፈልጋሉ ብሎ ማመን ቢክብድም " ኪዳነ ምሕረትን ድጅ ጠናሁ" ማለት ስህተት ነው የተባልበትን ትምሀርት ክግርማ ሞገሳቸው ከእመ ቤታችን መንበር ፊት ቆመው ትምሀርቱ ስህተት የለውም ማለታቸው ለምን ይሆን?

  ReplyDelete
 11. Rahel Aserat: ስለማታቂው ነገር ለምን ትዘባርቂያለሽ? በቶሮንቶ ቅድሰት ማርያም ቤተክርስቲያን ምንም አይነት የሃይማኖት ውዝግብ የለም። ባለፈው አሑድ ስብሰባ የነበረው መዘመር ስላቆሙ አባላት ለመነጋገር ብቻ ነው። ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ በትምህርታቸው “ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምሕረትን” ስለሚለው መዝሙር ምንም ነገር አላነሱም። ትምህርታቸውን አዚህ ላይ ተመልከች፡ https://www.youtube.com/watch?v=a8PYj9Z1KYY ። ትምህርታቸው ካበቃ በሃላ ተነሳ ባልሽው ጉዳይ አርሳቸውን መወንጀልሽ በመምህሩ ላይ ችግር አንዳለብሽ ያሳብቅብሻል።

  ReplyDelete