Friday, September 11, 2015

“ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ - በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ” (መዝ. 65፡11)



         ዓመትን በቸርነቱ የሚያቀዳጅ እግዚአብሔር ነው፡፡ በራሱ ኀይል 2007 ዓ.ም.ን ፈጽሞ ወደ 2008 ዓ.ም. የተሸጋገረ የለም፡፡ ይህን ዓመት ሳያዩ በሞት የተወሰዱ እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ በሕይወት ያለነውም ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሣ እንጂ ስለሚገባን አይደለም፡፡ በክርስቶስ ያመንን እስከሆንን ድረስ ግን ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜ የሚጨምርልን ክርስቶስን በማመን ጸንተን ከእምነት የሚነሣው መታዘዝ በሕይወታችን እንዲገለጥ ነው፡፡  ስለዚህ በአዲሱ ዓመት እንዲህ እንድንሆን ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡ ዓመቱን በቸርነቱ ያቀዳጀን ጌታም ፈቃዱን መፈጸም የሚያስችለውን ጸጋ እንዲያበዛልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን፡፡ 

                 እንኳን ለ2008 ዓ.ም. በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!!

2 comments:

  1. እኔ ግራ ያጋባኝ ነገር አለ ለመሆኑ ቅዱስ አባታችን በህይዎት አሉ እንዴት ነው ቡራኬ እንኳን የለም ።እናንተስ የስድብ ውርጅብኝና አንዱን አንዱን ከመራገም ምን እየተስራነው ያለው ።ነው ወይስ የውጩ ሲኖዶስ እንደ አሜሪካን ስታይል የግል አደረጋችሁትና ገንዘብ ብቻ መቁጠር ሆነ ስራችሁ እረ እባካችሁ አስተውሉ ምንድን ነው ነገሩ።ፓትሪያርክ እያለን መሪ እንደሌለው መንጋ ንው ያለነው በዚህ በአትላንታ ዙርያ ያሉ ሁለት ቤ/ክርስትያናት ከነዚያውም ብሶ የጎንደሬ ብቻ ለማድረግ የምደረገው ዘመቻ ቀጥሎ አሁን ደግሞ የፖለቲካ ድርጅቶች እያደረጉ የለውን ድራማ እያየን ነው ይኽውም የፖለቲካ ድርጅት ዌብ ሳይት ECADEF ወይም ESAT ተብሎ የሚጠራው እዝያም ተደብቀው ጎንደሬነታቸው ጥቃት እንዳይሆንባቸው ቢቸግራቸው ስለሃይማኖታቸው ያልትቆረቆሩ ነገር ግን ለተወሰኑ ግለስቦች ፍላጎት ማሟያ ይህን መላው ኢትዮጵያን እወክላለሁ የሚል ድርጂት አየንው አላማውን በትትክክልም አላምቢሶችና ዘረኞች መሁናቸውን የምያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።ያሳዝናል ፖለቲካ አልበቃችሁ ሲል ሃይማኖታችንን እያበላሻችሁ ነው በማያገባችሁ ገባችሁ እግዝያብሄር እነዚህን ነገሮች ይጸየፋልና እብስካችሁ ቅጽፈት እንዳይሆንባችሁ ጥላቻ ከውስጣችሁ አውጡ የእግዝያብሄርን ለእግዚያብሄር ተውለት እሱ በቤቱ ማን በትክክል ማን እንደሚኧገለግለውያውቃልና አሁን የትወስኑ ተሃድሶወችና መናፍቃንን ሰምታችሁ ያሳዝናል ይህን ኢንፎርሜሺን የሚኣቅብላችሁ ሰዎች በትክክል ሃይማኖታችውን አክብረው ኢትዬጵያኖች መሆናቸውንም ያጠራጥረኛል።ምክንያቱም ኢትዬጵያዊነቴ ሃይማኖቴ ነው እና ጥሩ ኢትዬጵያኖች ከሁናችሁ ሁሉንም ስይድ አነጋግራችሁ እውነቱን ለዩ አለዚያ ግን በትክክል የሚያሳየው ለኢትዬጵያ ሳይሁን ይህ ድርጅታችሁ ለተወሰን ክልል ማለትም ለጎንደሬ ብቻ የቆመ ይመስላል ወያኔን ወያኔ ያሰኘው ይህ መሰለኝ እኔ ግን እናንት ከወያኔ የትሻላችሁ እንጅ በአሁኑ ሰአት ግን ያባሳችሁ እየሆናችሁ ነውና ጥንቃቄ አድርጉ እግዚያብሄር አይነልቦናችሁን ይግለጥላችሁ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እንደተባልን ሁሉ አሁንም በቸርነቱ ይቅር ይበለን

    ReplyDelete