Wednesday, September 30, 2015

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጎ ጅምሮችና ቀሪ የቤት ሥራዎችየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስከረም 13/01/08 በቤተ ክህነት ትልቅ ግብዣ አደረገ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል መልኩ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን ምክትል ሊቃነ መናብርትን ጸሐፊዎችን ሂሳብ ሹሞችን በመጥራት ከዱባይ ዘመናዊ መኪናዎች ከቀረጥ ነፃ በማድረግና 12 ሚሊዮን በላይ በማዳን እንዲገቡ ጥረት ያደረጉት ለሊቀ ጠበብት ኤልያስ እና ለሊቀ ትጉሃን ታጋይ ባደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ልዩ የወርቅ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡ ባጠቃላይ መልኩ ዘርፈ ብዙ የሆነ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ፐርሰንት ለከፈሉ አድባራት ሽልማት፣ ሊቀጠበብት ኤልያስ ላሰለጠናቸው የአድባራት የሂሳብ አያያዝ ደብል ኢንትሪ ሥልጠና ወስደው የተመረቁ ሠራተኞች የሰርተፍኬት ሽልማት ፕሮግራም የተካተተበት ዝግጅት ነበር፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የሃገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ለተገዙት ዘመናዊ መኪናዎች የአድባራት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እውቅናና ክብር በመስጠት ባደረጉት ንግግር በእድምተኛው ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና አድናቆትን አግኝተዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የላመና የጣፈጠ ምግብ ቢቀርብም በተሰብሳቢዎች ዘንድ ግን ልዩ ትርጉም ያገኘው ገንዘብ አምጡ ከማለት አልፎ ምንም ብሎ የማያውቀው ሀገረ ስብከት አሁን “የተገኘው ሃብትና ንብረት በእናንተ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ እውቅናውም ክብሩም ለእናንተ ይገባል” ብሎ ባልተለመደ መልኩ የአድባራት ሠራተኞችን፣ ምክትል ሊቃነ መናብርትና ሂሳብ ሹሞችን ጠርቶ ኑ ዕውቅና እንስጣችሁ ተጋበዙ ደስ ይበላችሁ የእናንተ ውጤት ነው ማለቱ የመጀመሪያ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡

ምንም እንኳን የአድባራቱ ቁጥጥሮች ቀርተው የአራት ኪሎ ዱርዬዎች ገብተው አዳራሹን የወረሩት ቢሆንም ለወደፊት ጥሪ ሲደረግ ቁጥጥሮችን ባያገል መልካም ነው፡፡ እንዲሁም አባቶች ቆመው ማንም ወንበዴ በወንበር ተቀምጦ ለአባቶች ክብር የማይሰጥ ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ውጪ የሆነ ነገር አልፎ አልፎ ቢከሰትም ነገሩ ለታለመለትና ለታቀደለት ዓላማ ካልዋለ እንደ አንድ ግድፈት ስለሚታይ ለወደፊቱ ጥንቃቄ ቢደረግ እንላለን፡፡
ሌላው የነ አባ ማቴዎስ ጨለምተኛ ቡድን በነ ሊቀ ማዕምራን የማነ የተሠራው መልካም ነገር የማያስደስተውና የማይጥመው በመሆኑ ለማየት ሳይታደል ቀርቷል፡፡ እነ ሊቀ ማዕምራን የማነን ለመክሰስ ቢሆን ኖሮ ለማሰማትና ለመዘገብ ማንም የማይቀድማቸው አንዳንዶችም በዚህ ዝግጅት ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ የቅዱስ ፓትርያርኩና የብፁእ አቡነ ገብርኤል ንግግር መልካም የሆነ ቃለ ምዕዳን ነበር፡፡ በተለይ የቅዱስ ፓትርያርክ ቃለ ምዕዳን ስለ ሙስና “ይሄይስ ህዳጥ ዘበጽድቅ” “በጽድቅ ያለ ጥቂት ነገር ይሻላል” የሚለው አባታዊ ምክር ሊሰመርበት የሚገባ መልእክት ነው፡፡  ሌላው አበክረው የተናገሩት ነገር ስለ አስራት ጉዳይ ሲሆን ምእመናንን ማስተማርና በአግባቡ አስራት ሊያወጡ ይገባል ካሉ በኋላ “ለነገሩ አስራቱን ሌሎች ወስደውታል” በማለት በቁጭት የማቅ ሥራ እንዳንገበገባቸው ተስተውሏል፡፡ አቡነ ገብርኤልም ነገ ማቅ ካልቀየራቸውና ካላንሸራተታቸው ጥሩ የሆነ ምክርና ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ጽእለታችን የሆነ ሙስና የተባለ መጥፎ ገጽታ ማጥፋት እንደሚገባና በእነ ሊቀ ማዕምራን የማነ አስተዳደር ጥረት እየጠፋና አኩሪ ሥራ እየተሰራ እንደ ሆነ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከላይ የተገለፁት ነገሮች በሙሉ ምን ያህል ከፍ ያለ ብቃትና ንቃት ያላቸው መሆኑ የራቀውን በማቅረብ የአጥቢያ ሠራተኞችን በማግባባትና መንግሥትን ስለ ቤተክርቲያኒቱ ልዕልናና ክብር በማሳመን ጥሩ የሆነ ዲፕሎማሲ በመፍጠር አኩሪ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሁለት የተማሩ ሥራ አስኪያጆች ለሀገረ ስብከቱ የሚመጥኑና የሚገቡ ሰዎች ስለሆኑ የተሻለና የሚበልጥ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ሰሞኑን በሁለቱ መካከል እየተሰማ ያለው ግጭት መፈጠሩም የሚደነቅ ነው እንጂ የሚጠላ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥራ ሲሰራ ግጭት መኖሩ ጤናማ ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት አንደኛውን እየኮነኑ ሌላውን እያፀደቁ የተጀመረውን በጎ ነገር ወደቀደመው የጥፋት መንገድ ለመመለስ የሚሯሯጡ ሰዎች ወግዱ ሊባሉ ይገባል፡፡ ይልቁንም የተፈጠረው የሐሳብ ልዩነት ሊደነቅ ይገባል ምክንያቱም ከአሁን በፊት በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅና ምክትሉ ሲጣሉ በሃሳብ ልዩነት ሳይሆን በዝርፊያ ገንዘብ አከፋፈል ላይ በጥቅም የእኔ ለእኔ በማለት ነበር የሚጣሉት፡፡ አሁን ግን እንደዚህ ሊሆን ይገባል እንደዚህ ሊሆን አይገባም ተባብሎ በሃሳብ መፋጨት ከተማሩ ሰዎች የሚጠበቅ ነው፡፡ በጣም የሚገርመውና ደስ የሚለው ደግሞ በሃሳብ ልዩነት ምክንያት ወደ አድማና ቡድን መከፋፈል ሳይሆን የሄዱት ወደ ሾሟቸው ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት አሠራር ያልተለመደና በሁለቱ ስራ አስኪያጆች የታየ ነው፡፡ ይህም እነርሱ ምን ያህል አርቆ አሳቢዎች መሆናቸውንና ብቃታቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
በነ ማቅ ቡድን ግን ቤተክርስቲያን ስትበጠብጥ የእነማቅ ገበያ ምን ያህል እንደሚደራና ትርፋማ እንደሚሆን በተደጋጋሚ የታየ ነው፡፡ ይህ የሰይጣን ማህበር እንደ አባቱ እንደ ዲያብሎስ ከግጭትና ደም ከማፍሰስ ትርፍ ለማፈስ የሚሯሯጥ ማህበር መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡ መጽሐፍ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ልዩነታቸው የሚታወቀው የተጣሉትን ሲያስታርቁ ነው ይላል፡፡ የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው ነው እንጂ የተባለው የሚያጣሉ ብፁአን ናቸው አልተባለም፡፡ ማቆች ግን ተጣልተዋል እና  እልል በሉ ሲሉ ከርመዋልና እጅግ ያሳስባል፡፡
ስለዚህ የዚህን ጦረኛ ቡድን ፕሮፓጋንዳ ወደጎን ትቶ እየተሰራ ያለውን መልካም ጅምር ማጠናከርና የማቅን ከንቱ ህልም ማጨናገፍ ይገባል፡፡
ሁለቱም ሥራ አስኪያጆች እስካሁን ያደረጉት መልካም ጅምር እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ሊያስተካክሉት የሚገባ ሰው ያላገኘው ነገር አለ፡፡ እንደ እውቀታቸውና ችሎታቸው ያልሠሩባቸው ነገሮች አሉ፡፡ እንደ እውቀታቸው ስንል ለምሳሌ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ምሁር፣ የህግ አዋቂ፣ ዘርፈ ብዙ እውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጋዜጠኛ ነገሥታት /መሪዎች/ በድብቅ የሠሩትን ግፍና በደል ያለ ፍርሃት ነቅሶ የሚያወጣ፣ ስለ እውነት ብሎ መስዋዕትነትን የሚከፍል ነው፡፡ እንዲሁም ፖለቲከኛ ለህዝብ ነፃነት ብሎ ለሕዝብ የሚኖር ሲሆን በይበልጥ ግን የቤተክርስቲያን ልጅ ቤተክርስቲያን ሁሉ ሰው እኩል ነው ብላ የምታስተምር በመሆንዋ ለሰዎች ሁ፡ እክልነት የሚሠራ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጆቹ ይህን ሁሉ እውቀትና ፀጋ ይዘው ግን በአንዳንድ ቤተክርስቲያን የሚሠራው ግፍና በደል ቃላት ሊገልፁት የማይችሉት ሰብአዊና ሞራላዊ ጥሰቶች ይፈፀማሉ፡፡
ለምሳሌ በሰአሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን የሚፈፀመውን ካየን አንድ ሠራተኛ ተሳስቶ ሰው እንኳን ሰላም ለማለት አዲስ ሃገረ ስበከት ቢታይ ያለ ቅድመ ሁኔታ ያለ ማገጃ ደብዳቤ ከ30-40  ካገለገለበት ደብር በግፍ ይባረራል፡፡ ብሄረ ፅጌም እንዲሁ ተሳስቶ በቆጠራ ጊዜ አስኪርብቶ የያዘ ሠራተኛ እዛም እንደዚሁ ያሉ ወረቀት ከርስቱ ይፈነቀላል፡፡ ለአብነት ያህል ይህን አነሣን እንጂ ሌሎችም እንደ ጉራራ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን የመሳሰሉም የሊቃውንት ፀርና የቤተክርስቲያንን ሃብት በማራቆት በምትታወቀው በጋለሞታዋ ወ/ሮ ምሥራቅ ባህሩ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ወጣ ብሎ ማየት ይገባል፡፡ በእነዚህ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አድባራት እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ወደፊት እንገልጻለን፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን የማነ ይህን ሁሉ እውቀት ይዘው እንደ ጭሰኛ ለሚታየው ሠራተኛ ዋስትና ሊያገኙለት አልቻሉምና በአፅንኦት ቢያሰቡበት ይገባል እንላለን፡፡   

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት

6 comments:

 1. የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ሰይጣንን ያስደስታል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ሰይጣን ሁሌም ጨለማን ተገን አድርጎ በስንዴ አዝመራ ውስጥ እንክርዳድ ከመዝራት ተቆጥቦ አያውቅም፡፡ ሕዝብ የተባሉት አማጽያን አይሁድ አሕዛብ ከተባሉት ሮማውያን ጋር ተባብረው ምንም በደል ያልተገኘበትን ንጹሐ ባሕርይ ክርስቶስን የሰቀሉት ለሃይማኖትና ለሥርዓት በመቆርቆር ሽፋን የጨለማ ሥራዎቻቸውን ለማጧጧፍ ነበር፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የጨለማ ሥራዎቻቸውን ስለገለጠባቸው እርቃናቸውን ቀሩ፡፡ በመሆኑም በክርስቶስ ላይ በቅናት ተነሳሱ፡፡ የአባ ሰላማዎችና የሌባው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ስራአስኪያጅ ተብየ የማነ ቡድን የጨለማ ቡድን መሆኑ የተገለጠ ነው፡፡ ይሄንን ቡድን የማኅበረቅዱሳንና የሌሎች መልካም አገልጋዮች ውጤታማ ሥራ ኣያስደስታቸውም፡፡

  ReplyDelete
 2. ማኅበረ ቅዱሳንማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንድትመለስ ተግቶ የሚሠራና በዚሁም አገልግሎቱ መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታዮችን ያስተባበረና ያሳተፈ ብሎም የሚታዩና የሚዳሰሱ ውጤቶችን ያመጣ ማኅበር ነው፡፡ በዚህ አገልግሎቱ ሌቦች፣ ሙሰኞች፣ መናፍቃን፣ ተሐድሶዎች፣ የቤ/ክ ታሪካዊ ጠላቶችና የኢትዮጵያን ትንሣኤ የማይወዱ ሁሉ የማኅበረቅዱሳን ጠላት መሆናቸው አይደንቅም፡፡ የአባ ሰላማ ብሎገሮችም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን እና የኢትዮጵያ ጠላት ስለመሆናቸው ማረጋገጫው ከቤ/ክን ጠላቶች ጋር ተሰልፈው እውነተኞቹን የቤ/ክ አገልጋዮችን፣ ማኅበረ ቅዱሳንን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን፣ ሰ/ት/ቤቶችን፣ ማኅበራትንና ሌላው ቀርቶ በሰማይ ያሉ ቅዱሳንን ሳይቀር መሳደባቸው ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ያለምንም ጥርጥር የአውሬው መንፈስ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥባቸዋል፡፡
  የኢሐዴግ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን አስተዳደርን ከሁለት የከፈለ፣ ገዳማቶቿን ያፈረሰ፣ ካድሬዎችንና ሌቦችን አስታጥቆ በቤ/ክ አስተዳደር ውስጥ የሰገሰገ፣ ለቤ/ክን ሕልውና የተሟገቱ ጳጳሳትን በጠቅላይ ቤተክህነት ያስደበደበ፣ የዋልድባ መነኮሳትን ያሳደደ፣ አክራሪ እስላሞችን አነሳስቶ አብያተክርስቲያናትን እንዲያቃጥሉ ያደረገ፣ ክርስቲያኖችን ያሳረደ፣ የቤ/ክ ይዞታዎችን ያስነጠቀና በማስነጠቅ ላይ የሚገኝ፣ በአጠቃላይ ይሄ ቀረሽ የማይባል ግፍ ሲፈጽም የኖረና ያለ አገዛዝ ነው፡፡ ዛሬ ጎልቶ የወጣው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግር አባ ጳውሎስ ላለፉት ሃያ ዓመታት ካድሬዎችንና ታጣቂዎችን የውሸት ቆብ አልብሰዉ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች አድርገው በመሾማቸው የተከሰተ አይደለም ወይ? ዱሮስ ክርሰቲያን ያልሆኑ ብሉሹዎች እንዴት ቤ/ክንን ያስተዳድራሉ? አሁንስ ቢሆን ሚኒስትር ሺፈራው እነዚህን ሆዳሞች በመጠቀምና በእኩይ ሥራቸው በማስቀጠል ቤ/ክንን የበለጠ ለማዳከም እተፍጨረጨረጨረ አይደለም ወይ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን ዶግማ፣ ሥርዓት፣ ታሪክና ትውፊት ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ ይተላለፍ የሚሉትን “አክራሪ” ብሎ መጥራት ምን ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ዳሩ ግን እንደ ሰው ሰውኛ እንፈራ ወይ እናመነታ ይሆናል እንጂ በክርሰቶስ ደም የተመሰረተችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የገሃነም ደጆች ቢፈትኗትም አይችሉአትም፡፡

  ReplyDelete
 3. Bekerstos dem betcrstiyanwa endetemeseretch mahbere kidusan ayamnim.yihn mahber yemeseretew sew egziabher yiker ayelewom .tesadabi wenbede kifu geday aremene kinategna mikegna yehonu zegochen yafera mahber.yewengel telatoch.

  ReplyDelete
 4. Lemin yegehanb dejoch yefetnwatal??wengeln besereat selematgeleglebet lijochwa eyetenteku alekubat.yekerutem endebeal ketema beal kemadmek yalefe ewoket yelachewom.eweye anchi kidest betecrstiyan egziabher yehunsh

  ReplyDelete
 5. እኔ የሄ ማህበረቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ባይቆም ኖሮ የሄኔ ህዝቡ ሁሉ መናፍቅ ሆኖ ነበር ምናምን
  የምትሉት በጣም ይገርመኛል ቤተክርስቲያን ጠባቂዋም መስራችዋም መድህን ኢሱስ ክርስቶስ ነው
  የቀራችሁ እኮ ሞቶ ተነስቶ ያዳናችሁ ማህበረቅዱሳን ነው እያላችሁ ነው ጠርዘችሁን እወቁ ተማሩ ለአድማ ቤተክርስቲያን አትሂዱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔ የሄ ማህበረቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ባይቆም ኖሮ የሄኔ ህዝቡ ሁሉ መናፍቅ ሆኖ ነበር ምናምን
   የምትሉት በጣም ይገርመኛል ቤተክርስቲያን ጠባቂዋም መስራችዋም መድህን ኢሱስ ክርስቶስ ነው
   የቀራችሁ እኮ ሞቶ ተነስቶ ያዳናችሁ ማህበረቅዱሳን ነው እያላችሁ ነው ጠርዘችሁን እወቁ ተማሩ ለአድማ ቤተክርስቲያን አትሂዱ

   Delete