Sunday, September 6, 2015

አክራሪነት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መኖሩን የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ገለጹ


 Read in PDF

አክራሪው ሃይልም ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ማሳያዎቹ ጠቁመዋል
በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ በተደረገው ውይይት ሁሉም ተወካዮች በሚያሰኝ ሁኔታ አክራሪነት መኖሩን ገለጹ፡፡ ከ900 መቶ በላይ ተሳታፊዎች በ10 ቡድን ተከፍለው በአክራሪነት መንስኤዎች መገለጫዎችና በመፍትሔዎቻቸው ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ያለው ተጨባጭ ሁኔታ አክራሪነት መኖሩን እንደሚያሳይ በውይይቶቹ የተደረሰባቸው ድምዳሜዎች አመልክተዋል፡፡ በቡድን አወያዮች የቀረቡት ሪፖርቶች ስም አይጥቀሱ እንጂ አክራሪው ቡድን ማቅና ከእርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ክፍሎች መሆናቸውን እንደሚያሳይ ብዙዎች ተስማምተዋል፡፡
በቡድን 1 በአራዳና ጉለሌ ክ/ከ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     ቃለ አዋዲውን  አንቀበልም ቅዱስ ፓትርያርኩ የሾሟአቸውንም አንቀበልም ብሎ ሁከት መፍጠር
2.    በዐውደ ምህረት ድምፅ ማጉያ እስከመንጠቅ የደረሰ የሀይል እርምጃ መውሰድ
3.    የሥም ማጥፋትና የሀይል እርምጃ ለመውሰድ ማስፈራራት
4.    አሳሳች መልእክቶችን መጠቀም ለምሳሌ የሃይማኖት ጥያቄ አልተመለሰልንም በማለት ሌላ ቅስቀሳና አድማ ማድረግ
5.    ህግን ለማስከበርና የቤተ ክርስቲያንን ሰላም ለማስከበር የሚንቀሳቀሱትን የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ፖለቲከኛ (ወያኔ) በማለት ማስወራት
6.    በቤተ ክርስቲያን ሞዴላ ሞዴል አለመጠቀምና ለህገ ቤተ ክርስቲያን ተገዢ አለመሆን
እንደ መፍትሔ የቀረበው አንዱ ሐሳብ ወጣቶች ለሕግ እንዲገዙ አበክረን ማስተማር አለብን የሚል ነው፡፡

ቡድን 2 የተወያዩ በቂርቆስና በአዲስ ከተማ ክ/ከ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     በሰንበት ት/ቤቶች አካባቢ ድርሻንና ሃላፊነትን አለማወቅ
2.    በነጭ ወረቀት ገንዘብ የሚሰበስቡ እንዳሉና ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚፈጠር ልዩ ልዩ የአመፅ ሥራ እንደሚያውሉት ተጠቁሟል
ስለዚህ በሃይማኖት ካባ ሥር የለበሱትን ፖለቲካ በቁርጠኝነት መታገል ይገባል የሚል የመፍትሔ ሐሣብ ቀርቧል፡፡
ቡድን 3 የተወያዩ በቦሌ ክ/ከ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የጽንፈኞች ኢላማ እየሆኑ መጥተዋል፡፡
2.    ቤተ ክርስቲያንን ተገን አድርጎ ያለው ቡድን (ያው ማኅበረ ቅዱሳን ነው) ሰላምን ፈጽሞ እንደማያውቅ በማመላከት ይህ የጽንፈኛነት መገለጫ መሆኑን ገልጿል፡፡
3.    የእነርሱን አላማ የማይደግፈው ሁሉ ተሐድሶ መናፍቅ አማሳኝ ይባላል የሐራ ብሎጋቸውም ማጣፈጫ ይሆናል፡፡
4.    ቡድኑ መነሻውን ያደረገው ቤተክርስቲያንን ቢሆንም መድረሻው ግን ሌላ (ቤተ መንግሥት) መሆኑን ቡድኑ ተስማምቶበታል፡፡
ቡድን 4 ውስጥ የተወያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     ቃለ አዋዲውን ተከትሎ አለመስራት ይታያል
2.    ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት አካላት የችግሩ ቀጠና ሆነዋል ይኸውም
·        የሰበካ ጉባኤ አባላት የሌላ አካል (የማኅበረ ቅዱሳን) ጉዳይ አስፈጻሚ መሆን
·        መዋቅርን ባለመጠበቅ ሰንበት ት/ቤት ወሳኝ አካል ለመሆን እየተንደረደረ መሆኑ
3.    ቡድኑ የሚደግፈውን አገልጋይና ሰባኪ ኦርቶዶክስ የሚጠላውን ደግሞ ተሐድሶ ማለት በስፋት ይታያል
4.    ሁለት ጠጉር ያወጡ ጎልማሶች በሰንበት ት/ቤት አባልነት መበራከታቸው ሰንበት ት/ቤትን ለተለየ ዓላማ እየተጠቀሙበት እንዳሉ ያሳያል
5.    የሰንበቴ ማኅበራት የመቃብር ፉካ ንግድ ውስጥ መግባታቸውና በአንዳንድ ደብሮች የሌላቸው ሥልጣን ለመጠቀም መሞከራቸው
ቡድን 6 የተወያዩ የየካ ክ/ከ ምድብ 1 የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     እኔ ያልኩት ብቻ ይሰማ ማለት
2.    በስብከተ ወንጌል ሃላፊነት የተመደቡትን ከአውደ ምህረት በማውረድ ሁከት መፍጠር
3.    ሲኖዶስ ያላወገዘውን ተሐድሶ ነው መናፍቅ ነው ብሎ ስም መስጠት አክራሪነት ነው ብለናል ስለዚህ እንዲህ ያሉት በሕግ እንዲጠየቁ መደረግ አለበት፡፡
4.    በለውጥ ጎዳና ላይ ያለውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ እንዳይሠራ በየጊዜው ሰልፍ በመጥራት ስራ ማስፈታት
5.    ሰንበት ት/ቤቶች የሌላ (የማኅበረ ቅዱሳን) መጠቀሚያ መሆናቸው፡፡
እንደ መፍትሔ የቀረበው ሐሣብ እነዚህ አክራሪ ቡድኖች ወጣት ወንዶችንና ሴቶችን ለእኩይ ዓላማቸው ለአክራሪነት እንዳይመለምሉ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
አስራት መውጣት ያለበት ለቤተክርስቲያን ሆኖ ሳለ አስራት እያወጡ ያሉ ማኅበራት (ማኅበረ ቅዱሳን) ከዚህ ህገወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መደረግ አለበት
ቡድን 8 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
1.     የዚህ ቡድን ሰብሳቢ የማርቆስ ቤ/ክ ሰባኪ የሆነው ቡሩክ ማርቆስ ሲሆን ስለማኅበረ ቅዱሳን ሲነሳ ሐሳብን ይገድብ ነበር፡፡ ሪፖርት ሲያቀርብም እያዛባ ነበር ያቀረበው፡፡ ለምሳሌ  ዕውቅና የተሰጣቸው ማኅበራት እውቅናቸው ይጠና ሌሎች ማኅበራትም እየተጠኑ ይሰጣቸው ብሎ ያቀረበው ሪፖርት በውይይቱ ላይ ማኅበራቱ እየፈጠሩ ያለው ችግር ትቶ ይነጠቁ ነበር የተባለው፡፡
ቡድን 9 ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች
1.     አክራሪና ጽንፈኛው ቡድን በብፁዓን አባቶች የማገልገያ ሳይሆን “የክብር ክህነት” እያሰጠ ወደ መንደር ይልካል፡፡
2.    አክራሪውና ጽንፈኛው ቡድን የሰበካ ጉባኤ ምርጫን ይቆጣጠራል፣ ከዚህ የተነሣ የሌላ አጥቢያ የሆኑና የማይታወቁ ግለሰቦችን የሰበካ ጉባኤ አባል ያደርጋል፡፡
3.    በሕንጻ ኪራይ ታች ደብር ላይ ሆነው ሙስናውን የፈጸሙት አሁን ቤተ ክህነት ገብተው አጣሪ መሆናቸው አስገራሚ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ (ከሰሞኑ ሐራ በጥናቱ መሠረት እርምጃ ሊወሰድ ነው ብላለች) ይህ ነጥብ “ራሷ ክርስትና አልተነሣች ልታቋቁም ሄደች” በሚለው ማጎላመሻ የቀረበው ሐሣብ የብዙዎችን ድጋፍና ይሁንታ አግኝቷል፡፡ (ጉዳዩ ሙስናን ማጣራት ሳይሆን በሙስና ማጣራት ስም ለአክራሪው ቡድን ተቃራኒ የሆኑትን ሃላፊዎች መበቀል ነውና ቤተክርስቲያን ቤተክርስታየን ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስወገድ ከዚህ የበለጠ መሥራት ይጠበቅባታል፡፡ ሙስናን በማጣራት ስም እየተፈጸመ ያለውን አደገኛ ሙስናም ትኩረት ልትሰጥ ይገባታል፡፡)
4.    ጽንፈኛው ቡድን የሀገረ ስብከቱን አመራር በጎ ሐሳብ በሌላ መልክ በማቅረብና ሚንስትሩ ያላሉትን ገልብጦ ማውራቱ ጽንፈኛነትን የማስፋፋት አንዱ ስልት መሆኑ በዚህ ቡድን ውስት ተወስቷል፡፡
ቡድን 10 ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 2 ውስጥ የተወያዩ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች
የዚህ ቡድን ሰብሳቢ የአዲሰ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ህብረት ሰብሳቢ ተሐድሶ ሳይል ማውራት እንኳ የማይሆንለት ሄኖክ ሲሆን ከ900 በላይ ተሰብሳቢ ተጽዕኖ ስላረፈበት በሪፖርቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ “ተሐድሶ”ን ሳይጠቅስ ዘሎታል፡፡ “ሲያበጣብጠን የኖረው እርሱ ስለሆነ አያወያየንም” በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ እንዲያውም “ቅስናውን (የክብር ቅስናውን ለማለት ነው) ከየት ነው ያመጣኸው?” ተብሎም ተጠይቋል፡፡ በቡድኑ ከተሰጡት አስተያየጦች መካከል
1.      ዘረኝነት ኪር ሰብሳቢነት አክራሪነትን ፈጥሯል
2.    በሚፈጠሩ ችግሮች ዙሪያ ውይይት የለም አባቶችና ልጆች አይገናኙም
3.    በሕግ አለመመራት የፋይናንስ አሰራር ዘመኑን የዋጀ አለመሆን
ሥራ አስኪያጁ በኩል ከቀረቡት ሐሳቦች መከከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ
1.     አክራሪዎች ቤተ ክርስቲያኗንና ገንዘቧን ይጠቀማሉ
2.    የአክራሪው ኢላማ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ (የቀድሞውም ጭምር)፣ ሰባክያነ ወንጌል እና አስተዳዳሪዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በተለይም ሰባክያነ ወንጌል አውደ ምህረቱን ስለያዙ በእነርሱ ላይ ሰንበት ተማሪዎችን ማኅበራትን ያደራጃሉ፡፡ በዚህ ወር እንኳ ስለ እመቤታችን አላስተማረም፣ እገሌ የተባለ ሰባኪን አላመጣም ተብሎ ተጋላጭ የሆነ አለ ብለዋል፡፡
3.    አንዳንድ የግል ጋዜጦች ማስታወቂያ ሳይሰሩ ወጪያቸው ተሸፍኖላቸው ከጽንፈኛው ቡድን በሚመደብላቸው ብር ይታተማሉ፡፡ ከዚያ ቡድኑ የሚፈልገውን ዘገባ በዜና መልክ ያቀርቡታል፡፡ (በዚህ በኩል በአሁኑ ጊዜ በተለይ ሰንደቅ ጋዜጣ ተጠቃሽ ነው፡፡ ማስታወቂያ ሳይሰራ እስካሁን እየተታመ መዝለቁ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ምክንያቱም ጋዜጦች ያለ ማስታወቂያ ህትመታቸው ዋጋውን እንኳን መሸፈን አይችልም፡፡ ሰንደቅ ግን ከቡድኑ በሚያገኘው ገንዘብ ቡድኑ የሚፈልገውን ዜና እያወጣለት፣ ሐራም ሰንደቅን በምንጭነት እየተጠቀመች መጻፏ ሁለቱ ያላቸውን ትስስር ያመለክታል)፡፡ ይህ ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን በሚዘረፈው ብር የሚሰራ ነው፡፡
4.    በየቦታው የሚረብሹ ሰዎች ተመሳሳይ ናቸው አንድ እሑድ አንዱ ጋ ይረብሻሉ፣ በሌላው እሁድ ደግሞ ሌላው ጋ ይሄዳሉ፡፡ የሚሄዱት በአውቶቡስ ተጭነው ነው፡፡ የትራንስፖርት ወጪያቸውን ማን እንደሚከፍላለቸው አይታወቅም
5.    ጽንፈኝነቱ የትምክህት፣ የጎጥ የዘረኝነት ችግር ሁሉ ይታይበታል ብለዋል፡፡   
ሪፖርቶቹ ተጨምቀው ሲቀርቡ የሚከተለውን ይመስላሉ
የአክራሪነት መገለጫ በየአጥቢያ ምን ይመስላል ለሚለው የተነሡት ነጥቦች
1.     ሰንበት ት/ቤቶች አጥቢያዎች የማያዙበትና የማይቆጣጠሩት ገንዘብ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ከመዝሙር ቤት ከጉዞ ማኅበሮችና ከመሳሰሉት የሚያገኙት
2.    ቤተ ክርስቲያን ደክማ ያስተማረችውንና በአገልግሎት ያሰማራችውን ሰባኬ ወንጌል ተሐድሶ መናፍቅ ጴንጤ በማለት ይፍረጃሉ፡፡ ይህም ሰባኬ ወንጌሉ ለእነርሱ አካሄድ አልመች ሲልና የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበርና ተልእኮዋን በአግባቡ እንድትወጣ ለማድረግ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ምክንያት ነው፡፡
3.    አክራሪነት የተጠናወታቸው ክፍሎች ዋና ዓላማቸው ዐውደ ምህረቱን መያዝ ስለሆነ አውደ ምህረቱን በኃይል ለመቆጣጠር ከሰባኬ ወንጌሉ ማይክ ስጠን የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ጥያቄያቸው አግባብነት የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት ሲያጣ ይደባደባሉ፡፡ ለዚህ በምሳሌነት የተጠቀሰው በገርጂ እግዚአብሔር አብ የተፈጸመው ድብደባ ነው፡፡
4.    እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ግለሰቦች የሰንበት ት/ቤት ሊቀመንበር ሆነው ይመረጣሉ፡፡ ለምሳሌ የአማኑኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት አቶ አንተነህን የዛሬ 20 ዓመት ጀምሮ ሊቀመንበር ነበረ አሁንም ሊቀመንበር ሆኖ ተመርጧል፡፡
5.    አብዛኞቹ የሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢዎች ሥራ የላቸውም ነገር ግን የብዙ ሀብትና ንብረት ባለቤቶች ናቸው፡፡ ይህ ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ የአክራሪነት መገለጫ ነው፡፡
6.    ሁል ጊዜ መዋቅርን ጠብቀው አይሠሩም ደብሩንም ሰባኬ ወንጌሉንም ሳያስፈቅዱ እነርሱ የሚፈልጉትን አስተማሪ ይመድባሉ፡፡ ለዚህም ግጭት ለመፍጠር ፖስተር ይለጥፋሉ፡፡
7.    እንደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች ህብረት አባል የሆነው እንደ ሳሙኤል እሸቴ ያሉ ሆን ብለው በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጥሩ ምሳሌ የሆነውን የደብረ ናዝሬት ዮሴፍን ቤተክርስቲያን ሲዘልፉ ታይተው ተገቢ መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡
8.    አንድ ቅን የሰ/ት/ቤት ተወካይ ደግሞ አንዳንድ ሰ/ት/ቤቶች አለቃ ማባረርና የንግሥ በዓላትን ማስታጎል የመሰለው አሳፋሪ ተግባር መቅረት አለበት ሲል ድርጊቱን ተቃውሟል፡፡
9.    በቦሌ ክፍለ ከተማ ያሉ ተወያዮች በተሻለ መልኩ በሕግ እየሄዱ ያሉበት ክልል መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የካ 2 ላይ የተወያዩ ደግሞ ፍጹም የአክራሪነት መገለጫው መነሻው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አራዳና ጉለሌ ደግሞ እግዚአብሔር አብ ብስራተ ገብርኤል የአክራሪነት ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች እንዳሉበት ተገልጿል፡፡
10.  በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ሁለት ዓይነት የገንዘብ አሰባሰብ ያለ ሲሆን አንዱ በሰበካ ጉባኤው በኩል በደረሰኝ ሌላው በሰንበት ት/ቤቱ በኩል በነጭ ወረቀት ይሰበሰባል፡፡ በነጭ ወረቀት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለምን ተግባር እንደዋለ አይታወቅም፡፡
11.    የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ከእገሌ ማኅበር ጋር (ያው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር መሆኑ ነው) ጉባኤ እናዘጋጅ የሚሉ እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ለምሳሌ በእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን
12.   በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች መጥተው ያስተምራሉ ሌሎች በቤተ ክርስቲያኒቱ የታወቁትን ሰባክያን ግን የእነርሱ አመለካከት ደጋፊ ስላልሆኑ ብቻ ፈቃድ የለውም ብለው ይተቻሉ፡፡
13.  ቂርቆስ አዲስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ የመጣ ሲሳይ የተባለ ወጣት 1.5 ቢሊየን ብር ተዘርፏል ብሎ ያቀረበው ሐሣብ ተቀባይነት አጥቷል ምክንያቱም የሀገረ ስብከቱ ተወካይ የሀገረ ስብከቱ የ10 ዓመት በጀት እንኳን ይህን አያክልም፡፡ ይህ የሐራና የሰንደቅ ወሬ ነው ብለውታል፡፡
14.  የሃይማኖት ክስን በተመለከተ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ የተሰጠው አስተያየት ደግሞ እገሌ ተሐድሶ ነው ብለው የሚከሱ እነርሱ፣ መረጃ ሰጪ እነርሱ፣ አውጋዥ እነርሱ ናቸው፡፡ ይዘው የሔዱት ክስ አያስኬድም ሲሏቸው መልሰው ወደ አጥቢያ መጥተው ይበጠብጣሉ ተብሏል፡፡
በ10ሩም ቡድኖች ውስጥ የበላይነትን የያዘው ሐሳብ፦
1.     አክራሪነትና ጽንፈኛነት ቤተክርስቲያን ውስጥ አለ 
2.    የመዋቅር ጥሰት አለ
3.    ሰንበት ት/ቤቶች በራሳቸው ጉዳይ ላይ ብቻ አያተኩሩም በቀጥታ የሌሎች ማኅበራትን (የማኅበረ ቅዱሳንን ለማለት ነው) ሐሳብ ነው የሚያራምዱት
4.    የፖለቲካ አዝማሚያ ይታይባቸዋል
5.    ምንጩ የማይታወቅ ገንዘብ ያንቀሳቅሳሉ
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ችግር ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳን እጅ ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡


       

16 comments:

 1. Werenyoch! tikus were metalachihu! inkuan dess alachihu. ayzo'achihu abatachihu diablos iskemecheresha sira ayfetam; ye Egzi'abher lijochim sira ayfetum.

  ReplyDelete
 2. chelemawuen geletute Enji Zem atebelu

  ReplyDelete
 3. አሁን ገና ማህበረ ቅዱሳን አንገቱ የታነቀ ይመስላል!! በተለይ በየአጥቢያው ያው የሰንበት ት/ቤት መዋቅር የገንዘብ አያያዙ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መሆኑ የማህበሩን አንገት ያደነደነ ነበር፡፡ የየአጥቢያ ሥርዓት ከያዘ በኋላ የ5 ኪሎውንም ባለሕንጻ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት ማስገባት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ግን ምንም ተባለ ምንም አሁን ያለው ማ/ቅ እንደገና ክርስትና ተነስቶ ዐቃቤ ሥርዓት ተመድቦለት በትክክል ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊነትን ካልተማረ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን ከማመስ አያርፍም፡፡
  ማ/ቅን በማውገዝ እና በመክሰስ ሰበብ ተሸፍናችሁ ቤተክርስቲያንን የምትቦጠቡጡ አስተዳዳሪዎች፣የቢሮ ሰራተኞችና በየቦታው እውቀትና ችሎታ ሳይሆን ቀን ያስቀመጣችሁ!! ቀን ያስቀመጣችሁ!! ጉዶችም ከማ/ቅ የማትተናነሱ የቤተክርስቲያንን ደጃፎች በስግብግብነታችሁ ያከረፋችሁ ጅቦች ናችሁ፡፡
  ቀን/ጊዜ ሰጠን ብላችሁ፣ ሥልጣን ለእኛ ብቻ!! የምትሉ ዘረኞችም ሌላውን በመናቅና ለቤተክርስቲያን ሀላፊነት እንዳይበቃ፣ ያለእናንት ሌላው ሁል ጊዜ ትንሽ የሚመስላችሁ ገፊዎች ጎጃም ጎንደር ሸዋ ኦሮሞ…. ያስጠላችሁ፣እረ ለመሆኑ ቤቱ የክርስቶስ አይመስላችሁም?? ክርስቶስን ምሰሉ እንጂ ስንት ዘመን ለመኖር እሳት ትበላላችሁ????

  ReplyDelete
 4. “የሰንበት ት/ቤቶች ሕብረት“ በማለት ያደረጃው ስውር ሠራዊት የማኅበረ ቅዱሳን የአክራሪነት መገለጫው አንዱ ድርጊት ነው፡፡ ይህ ሕብረት ተብዬ ነገር መንግሥታዊንም ሆነ ቤተክርስቲያናዊ ትዕዛዞችንና መመሪያዎችን በመቃወም እስከ ኃይል ጥቃት የሚደርስ ጥፋት ለመፈጸም የተዘጋጀ ድብቅ ሠራዊት ነው፡፡ መንግሥትም ዝም ብሎ እያየው ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም በመዋቅሯ የማታውቀው ሕገወጥ ቡድን ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. «ከማኅበሩና ከሙሰኞቹ የትኛው በመወገድ ሊቀድም ይገባል? የሚለው ካልሆነ በስተቀር በሁለቱም አላስፈላጊነት ላይ አንዳችም ብዥታ የለንም»

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች በእውነት የምታቀርቡአቸው መረጃዎች
  ተክክለኛ መረጃዎች ናቸው በዚሁ ቀጥሉበት
  የሐራንም ውሸት ተከታትላችሁ አምክኑባት !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሰውን ስጋ ከመብላተ፤ሰው ከማማት ፤ነገር ከማላመጥ የክርስቶስን ወንጌል መብላት፤ማላመጥ ይሻላልና እባካችሁ ስለ እግዚአብሄር ብላችሁጌታችንን እንደከሰሱት እንደ አይሁዶች አትሁኑ፡፡ይፈረድብሃልና አትፍረድ፤ፈራጅ እግዚአብሄር ነው፤የሚኮንንም የሚያፀድቅም እርሱ ብቻ ነው፡፡

   Delete
 7. ሣማ ሀራዘተዋህዶ እና ማህበረቅዱሳንን ታብጠለጥላለች፡፡ ሐራ ዘተዋህዶ ግን ሙሰኞችን ታብጠለጥላለች
  ሣማ የሙሰኞች ደጋፊ እና በእነሱ የምትንቀሳቀስ ናት፡፡ ሐራ ግን በአዉነተኛ የእግዚየብሄር ልጆች ትንቀሳቀሳለች፡፡ ሳማ የከሃዲ እና የ መ ናፍቅ አንደበት ናት፡፡ ሀራ ግን እዉነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች አንደበት ናት

  ReplyDelete
 8. ጳጉሜን 4 ቀን 2007 ዓ.ም.

  ተሐድሶዎችና የፕሮቴስታንት ተላላኪዎች- የናንተና የሚኒስትር ሺፈራው ተ/ማርያም ልዩነት ምንድነው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናችሁን ኦርቶዶክሳውያን ያውቁታል፡፡ ሚኒስትሩ ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ በፖለቲካ ሽፋን ቤ/ክንን እየወጉ ያሉ ፕሮቴስታንት ናቸው፡፡ ከጫካ ጀምሮ ቤ/ክንን ስልታዊ በሆነ መንገድ ማዳከምና ከልዕልናዋ ለማውረድ ስውርና ግልጽ አሠራር የዘረጋችው ወያኔ የሚኒስትር ሺፈራው ተ/ማርያምን እኩይ ተግባር ከኋላው ሆና ትደግፋለች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክንን የገጠመው የመልካም አስተዳደርና ሙስና ተግዳሮት በከፊል ከውስጥ የመነጨ ቢሆንም በዋነኛነት ግን የወያኔና መሰሎቿ ቀጥተኛ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገነዘበው ሐቅ ነው (በግላጭ የሚታዩ ማሳያዎች ስላሉ ነው-የዋልድባን ገዳም ማጥፋት፣ እንደ ዚቋላና አሰቦት የመሳሰሉ ገዳማት ሲቃጠሉ እንዳላዩ ማለፍ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርሰቲያኖች ላይ ግፍ ጭፍጨፋና ስደት ሲደርባቸው አለመከላከል፣ ወዘተ.) ፡፡

  ዛሬ ጎልቶ የወጣው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግር አባ ጳውሎስ ላለፉት ሃያ ዓመታት ካድሬዎችንና ታጣቂዎችን የውሸት ቆብ አልብሰዉ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች አድርገው በመሾማቸው የተከሰተ አይደለም ወይ? ዱሮስ ክርሰቲያን ያልሆኑ ብሉሹዎች እንዴት ቤ/ክንን ያስተዳድራሉ? አሁንስ ቢሆን ሚኒስትር ሺፈራው እነዚህን ሆዳሞች በመጠቀምና በእኩይ ሥራቸው በማስቀጠል ቤ/ክንን የበለጠ ለማዳከም እተፍጨረጨረጨረ አይደለም ወይ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን ዶግማ፣ ሥርዓት፣ ታሪክና ትውፊት ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ ይተላለፍ የሚሉትን “አክራሪ” ብሎ መጥራት ምን ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ዳሩ ግን እንደ ሰው ሰውኛ እንፈራ ወይ እናመነታ ይሆናል እንጂ በክርሰቶስ ደም የተመሰረተችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የገሃነም ደጆች ቢፈትኗትም አይችሉአትም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነት ነው ወንድሜ፡፡ ይህ እኮ ግልጽ የሆነ ነው ምንም ጥርጥር የሌለው፡፡ ካዲያ እንደዚህ ዓይነቱን ፈተና ማለፍ የምንችለው በጾም፣በጸሎት፣ በስግደት እንዲሁም ከጎናቸው ሆኖ ማበረታት ያስፈልጋል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ከበፊቱ የበለጠ የአሁኑ ፈተናቸው ከፍተኛ ነውና እንጸልይ፡፡ የእኛ አቅማችን ፊደራል አይደለም፣የእኛ አቅማችን ሚኒስትሮች አይደሉም፣ የቤተክርስቲያኗ እራስ ክርስቶስ ነው፡፡ እኛ ደግሞ አካሉ መሆን አለብን፡፡ የሚደርስብንን ፈተና ሁሉ ማሸነፍ የምንችለው በጸሎት እና ተግቶ በመስራት ነው፡፡ ተኩላው ምቹ ጊዜ ፈልጎ ነው የሚበላው፡፡ ወገኖቻችን በተኩላው እንዳይበሉ የራሳችንን ስራ እንስራ፡፡እነዚህ በተኩላው ስለተበሉ ምን እያደረጉ እንደሆነ እንኳን አይገባቸውም፡፡ ዜናቸው ሁሉ ስድብ፣ ገንዘብ ነው፡፡ ምስጥራቸው ስለተነቃባቸው ነው፡፡ እህኔ እነዚህ ቢጣሩ እኮ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ የሚበዘብዙ ጎቦኞች ይሆናሉ፡፡ ማን ያውቃል? ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ? እግዚአብሔር ተዋህዶ ሐይማኖታችንን ይጠብቅልን፡፡

   Delete
 9. bertu tikikil nachuh MK is the collection of brokers and dealers in the name of the church. alamachew betekristianin benesu halafinet sir madreg ena genzebuwuan mekoteter yerasawhew madreg new they are also politicians not religious .

  ReplyDelete
 10. I am sorry very much! Is AA hager sebekt making EOTC political platform! Are you going to through the younger generation out of EOTC! If you want to through them fist you have to through us! But you will not do that you want our money! Are blaming them for they have spoken the truth calling a spade spade! Tehadiso tehadiso and the corrupt clergy corrupt! God and truth will save our children!
  But our Holy Father will not give us to the Hyenas!

  ReplyDelete
 11. minstru man nachew mn hasabs alachew? teklayus mn yluachewal? mahberun lemn mewagat asfelegew? yeato meles ekd mn neber? abune mattias lemn teteku? yh hulu zemecha lemn? lezefagn tabotn yawetut abat mot endet ? htsanat bejachew mn mlkt endisayu aderegech? obama etiopian edget weys illuminati abalatn lematenaker metu? yh hulu and lay sihon tewahdo lay yetekefetew zemecha ygebachual:: 666 man yemistr abal endehon atawkun? ethiopia lem temesasay tsota gabchan lemn betewekelechbet medrek zm alech? yerejm gize ekdu mn askemtual? yzih tomera abalat enhn tyake melsoch stawku mahberu gon endemthonu tesfa alegn ene gn.......... tewahdo lezelalem atnawetsm....... amen

  ReplyDelete
 12. Jesus Christ is the LORD of LORD

  ReplyDelete
 13. አዎ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማመናችን አክራሪነት ካስባለን፣ክርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር፡፡ ተዋህዶን ከአክራሪነት በላይ ቃላት ካለም እየፈለጋችሁ በሉንንንንንንንንንንንንንንንንንንን፡፡ አንሰማችሁም አሁንማ አወቅናችሁ ተኩላዎች፡፡ ማህበረ ቅዱሳንንንንንንንንንንንንንንንንን ደግሞ እናንተ ስላላችሁ አይጠፉም ስራቸው ያኖራቸዋል፡፡ አወናባጆች የቤተክርስቲያንን አገልጋይ የተባሉት ደግሞ እነማን ይሁን? ቤተክርስቲያኗን ዙሪያ ለዘፋኝና ለዳኒኪራ አከራይተው እያስደነሱ ያሉት ናቸው? የአይጥ ምስክር ድንቢጥ፡፡ አዎ ቅኔ ዘረፉ ሲባሉ ምዳዋይ ምጽዋት የሚዘርፉት ናቸው፡፡ ሌብነታቸው ስለተጋለጠባቸው ነው፡፡

  ReplyDelete