Friday, October 30, 2015

አባ ሳሙኤል በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በርካታ ችግሮችን እየፈጠሩ ነውበጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ዋዜማ ላይ በድርሰት ስርቆት እስከተጋለጡበት “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ድረስ በሰው መጽሐፍ ራሳቸውን ጸሀፊ ለማሰኘትና የሌላቸውን ማንነት ለመገንባት ያልተሳካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩት አባ ሳሙኤል በግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ግን የፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት መጋለጡን ተከትሎ ሌሎች መሰሪና አሳፋሪ ሥራዎቻቸው መጋለጥ ቀጥለዋል፡፡ ከግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ጋር ጋር በተያያዘ ለማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ከማኅበሩ ግልጽ አመራሮች መካከል አንዱ ቀርቦ የተጠየቀ ሲሆን ስለ መጽሐፉ በአባ ሰላማ ድረገጽ የቀረበው ትክክል መሆኑን አምኗል፡፡ መጽሐፉን እነርሱም ሽጡ ተብለው እንደተረከቡና መጽሐፉ ችግሮች ስላሉበት ሳንሸጥ መጋዘን በማስገባት ክፍያውን ግን ፈጽመንላቸዋል ብሏል፡፡
ይህም የሚያሳየው ማቅ ለሃይማኖት ሳይሆን ለግል ጥቅሙ የቆመ ድርጅት መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ለሃይማኖቱ ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ አባ ሰላማ እስኪያጋልጥ ድረስ የአባ ሳሙኤልን ሃይማኖታዊ ሕጸጽና ቅስጣ ድርሰት በቸልታ ማየት እንዳልነበረበትና ጉዳዩን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያን አካል አቤት ማለት እንደነበረበት ማንም የሚናገረው እውነት ነው፡፡ ማቅ ግን ለፖለቲካው ሲል እንዲህ አላደረገም፡፡ ለዚህም እንዲህ ባደርግ በአባ ሳሙኤል በኩል የሚፈጸምልኝ ጉዳይ ሊበላሽ ይችላል ብሎ ቅድሚያ ለዚያ ሰጥቶም እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ሌላውን አለስሙ ስም ለመስጠት አለቅጥ የሚጣደፈውና ማንም የማይቀድመው ማቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሳየው ዳተኛነትና ቸልተኛነት ሰዎች እንዲወገዙ ጥያቄ የሚያቀርበው በሃይማኖታቸው ላይ ሕጸጽ ስለተገኘ ሳይሆን ለእርሱ አልመች ስላሉትና ስለተቀናቀኑት ነው ለሚለው የብዙዎች እምነት ትልቅ ማጠናከሪያ ሆኗል፡፡ 

ውሸት ቢሮጥ እውነትን አይቀድምም “አሪፍ ለወሬ አይቸኩልም” ይላሉ የአራዳ ልጆች፡፡ መጽሐፍም “ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” ይላል፡፡ (ያዕቆብ 1፥19)፡፡ በዚህ የማይመራው የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሐራ እውነትን ለማድበስበስና ብዙዎችን በወሬ ለመፍታት ያልተደረገውን ተደረገ የተደረገውን ደግሞ አልተደረገም በማለት ሐሰቱንና የልቡን ተምኔት ሁሉ “ሰበር ዜና” እያለ ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡ ሰበር ዜናፈቃድ የሌላቸው የኢ..ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ 24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል” በሚል ርእስ ሰሞኑን ያናፈሰው ወሬ የተዛባና ሐሰት የተቀላቀለበት መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ በሐራ ዘገባ ሐሰትነት ያዘኑት ምንጮች ሐራ እንዲህ የምታደርገው ሰውን በወሬ ለመፍታት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሲኖዶሱ በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ በተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተመስርቶና በሌሎች የራሱ ጉዳዮችም ላይ አጀንዳውን እንደሚያረቅ እየታወቀ በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያልተነሣውንና በመግለጫው ላይ ያልተነሣውን የተሐድሶን ጉዳይ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በስርዋጽ አስገብቶ እንዲያነበው በማስደረግ ሸፍጥ ተፈጽሟል፡፡

(ዳንኤል በት/ቤት እያለ የማቅ ደጋፊ በኋላ ደግሞ ተቃዋሚ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በፈረንሣይ ኤምባሲ እርዳታ አባ ጳውሎስ የተወለዱበት መደራ አባ ገሪማ ገዳም ሙዚየምን ለማሠራት በገዳሙ ስም ገንዘብ ተቀብሎ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲው ገዳሙን ሲጠይቅ ገንዘቡ እንዳልደረሰው በመግለጹ ዳንኤል ከሥራ ታግዶና ወደ ውጪም እንዳይወጣ ጭምር ተፅፎበት ነበር፡፡ እሱም ከላይ የተገለጸውን ችግር የሠሩብኝ ማቆች ናቸው ይል ነበር፡፡ ጉዳዩ በምን እንደተዘጋ ሳይታወቅ አሁን የአቡነ ገሪማ ምክትል ሆኖ እየሠራ ይገኛል፡፡ በ34ኛው የሠበካ ጉባኤ የመዝጊያው የአቋም መግለጫ ላይ ከስብሰባው መንፈስ ውጪ በሥርዋፅ የገባ “ተሃድሶ” የሚል ቃልና ሐሳብ መነበቡ ዳንኤል እነ አቡነ ማቴዎስን ለማስደሰት ያደረገው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ምክንያቱም ከፈጸመው የሌብነት እገዳ በኋላ መልሰው ያስገቡት እሳቸው በመሆናቸው ለውለታቸውና በቀጣይም ለማቅ አጋር ሆኖ መቀጠል እንደሚፈልግ ለማሳየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡)

Thursday, October 29, 2015

ይድረስ ለዲ/ያረጋል የፀረ ተሃድሶ እንቅስቃሴ አባልና አስተባባሪ


Read in PDF
የሰሜን አሜሪካ ኮንፈረንስ ላይ ስለተሐድሶዎች ያቀረብከው መግለጫ ውሸት የተሞላበት ነው ።
የተሃድሶ እንቅሥቃሴ በአስገራሚ ፍጥነት እያደገ መምጣቱ ከተጠበቀው የጊዜ ግምት እጅግ የፈጠነ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ሐሳቡ ከቀሳውስትና ከቤተ ክህነት ሰዎች እጅ አፈትልኮ ወደ ሕዝቡ በመድረሱ ነው። የተሃድሶ እንቅስቃሴ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በባነኑ ካህናት በስውር እና በዝግታ ለረጅም ጊዜ ይካሄድ የነበረ እንቅሥቃሴ ነው። ማህበረ ቅዱሳን ግን ካህናቱን ያገላጥሁ መስሎት ሐሳቡን ለሕዝብ በመግለጡ ሕዝቡ በተቃራኒው ተሐድሶዎችን ፍለጋ ያዘ። እውነት ለመናገር ከሁለት ሺህ አራት ዓ.ም ሕረቱ ውግዘት ወዲህ ለተሀድሶዎች ሥራ በዝቶባቸዋል። ማህበረ ቅዱሳን ለግንዛቤ በማለት በየአዳራሹ እየሰበሰበ ተሃድሶን ለሕዝብ በማስተዋወቁ በርካታ ወጣት ባስፈሪ ሁኔታ ተሀድሶውን ተያይዞታል። ይህ ጉዳይ እንኳን ለማህበረ ቅዱሳን ለተሃድሶ መሪዎችም አሳሳቢ ሆኗል። ከእንቅሥቃሴነት ወደ ማዕበልነት ሊቀየር ይችላል የሚል ሥጋት አለ። ሥጋቱ የተፈጠረው ይህን ማዕበል ባግባቡ መምራት የሚችል ጠንካራ ተቋም ባለመኖሩ ነው። ይህን የተሃድሶ እንቅሥቃሴ ራሱ ቤተ ክህነቱ ቢመራውና አቅጣጫ ቢያስይዘው ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ እድል ነበር። ነገር ግን በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል? እንደተባለው ተሃድሶን እንከላከላለን በሚሉ ሞኝ ወንድሞች ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እንደተቋም የእንቅሥቃሴው ተጠቃሚ እንዳትሆን እያረጉ ነው።
ይህን ካልኩ በኋላ ወደ አንተ ልመለስ ዲያቆን ያረጋል ለኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ያቀረብከው ሪፖርት ተሃድሶዎች ያላሉትን እንዳሉ አድርገህ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ውሸት ሲገለጥ ሰዎችን እንዲሸሹ ያደርጋል እንጂ አንዳች ፋይዳ አይኖረውም። አሁን የዚህ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ተሃድሶዎችን ቢያገኙና ቢጠይቁ ያረጋል ስለተሃድሶዎች ከተናገርከው ስለሚለይ እንዲህ ዓይነቱን ውሸታም ሰው በቀላሉ ለመሸሽ ምክንያት ይሆን ነበር። እስኪ በራስ መተማመኑ ካለ ከተሃድሶዎች አንዱ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ተጋብዞ ይጠየቅ! አንተ እንደምትከሰው ሆኖ ይገኝ ይሆንን?  ዲያቆን ያረጋል ስለተሃድሶዎች ስትናገር ከሰማሁት ውስጥ ጥቂቶቹ፦

Wednesday, October 28, 2015

ሐራ ዘተዋሕዶ ለአባ ሳሙኤል የገጽታ ግንባታና ኑፋቄን የመሸፈን ሥራ እየሠራች ነውአባ ሳሙአል ግብረ መንፈስ ቅዱስ በተባለ መጽሐፋቸው ላይ ኑፋቄና የድርሰት ስርቆት ፈጽመዋል ተብሎ በብሎጋችን በቅርቡ ቀሲስ ፈታሒ በተባሉ ጸሐፊ ይፋ የተደረገው ጽሑፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት ጥቅምት 16 ቀን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን “አዋልድ” የሚል ስም የሰጧት የማቅ ብሎግ ሐራ ዘተዋህዶ ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም. በልማትና ክርስቲያናዊ ኮምሽን የተሰጠውን ሥልጠና ይዛ በመውጣት ለአባ ሳሙኤል ያላትን አጋርነት አሳይታለች፡፡ ሥልጠናው የተሰጠው ከአራት ቀናት በፊት ቢሆንም ለወሬ ማንም አይቀድመኝም የምትለውና ወሬ ቢበዛባት እንኳ በሰዓታት ልዩነት እያከታተለች ወሬውን እየገለበጠችና እያጋነነች ማውጣት ልማዷ የነበረው ሐራ ከአራት ቀናት በኋላ የተከናወነውንና በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት መቅረቡና አስፈላጊነቱ ያን ያህል የሆነውን የልማት ኮምሽኑን የሥልጣና ወሬ ይዛ መውጣቷ በኑፋቄና በድርሰት ስርቆት ጥያቄ እየቀረበባቸው ያሉትን የአባ ሳሙኤልን ገጽታ ለመገንባት መሆኑን ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች ይናገራሉ፡፡

ለተዋሕዶ ሃይማኖት ከእኔ በላይ ለአሳር የምትለውና ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ የቆመውን ማንኛውንም ሰው በሃይማኖት ችግር በመክሰስ አለስሙና አለግብሩ ስም ለመስጠትና ግብሩን ለማክፋት ተወዳዳሪ የሌላት ሐራ በተዋሕዶ እምነት ላይ ኑፋቄ ያመጡትንና ከአንድ ሊቀጳጳስ በማይጠበቅ መልኩ የሌሎችን ድርሰት እየቆነጻጸሉ በስማቸው በማሳተም ቤተክርስቲያንን አንገት ያስደፉትን አባ ሳሙኤል እንዲጠየቁ በማድረግ ፈንታ ምንም እንዳልተፈጠረና ሃይማኖት እንዳልፈረሰ በማስመሰል ገጽታቸውን መገንባት ይዛለች፡፡ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳን ለሃይማኖት ያልቆመ የፖለቲካ ድርጅት ነው የምንለው እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ከሚሠራውና ከሚያደርገው በመነሣት ነው፡፡ ለሃይማኖት ቢቆም ኖሮማ አባ ሳሙኤል የተዋሕዶን እምነት ሲንዱት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን ሲያዋርዱና ሌሎችንም ሃይማኖታዊና ሥነምግባራዊ ኑፋቄዎችንና ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ዝም ባላለም ነበር፡፡ ለዓላማው ሲሆን ግን በሕይወት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ጌታን አገልግለው በክብር ያረፉትንና ስማቸውና ግብራቸው ከመቃብር በላይ ውሎ ለብዙዎች አርኣያና ምሳሌ የሆኑትን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ጭምር ለማስወገዝ እንቅልፍ አልነበረውም፡፡ ለአባ ሳሙኤል ሲሆን ግን ዝም ማለት እንኳን ሲገባው በሐራ ብሎጉ ላይ ገጽታቸውን ለመገንባት ሲል የሰነበተና የጠነዛ በዚህ ወቅት ማንም ሊያነበው የማይፈልገውን የሥልጠና ወሬ ዜና አድርጎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱም በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ አባ ሳሙኤል ለማኅበሩ የዋሉለትን ውለታ በማሰብና አሁንም በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ነገሮች ማቅ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄዱ ለማድረግ የአባ ሳሙኤልን አጋርነት ስለሚፈልግ ነው እንዲህ ያደረገው፡፡

Monday, October 26, 2015

ሊቁን በረኃብ የምትቀጣ መናፍቁን በጥጋብ የምታቀናጣ ቤተ ክርስቲያንቤተክርስቲያናችን ብዙ ጉድ የሚታይባት፣ ፍትሕ የጎደለባት፣ ዘረኛነት የተንሰራፋባት፣ የዘመድ አዝማድ ሥራ ሥር የሰደደባት፣ ሊቃውንቷ አፋቸው የተሸበበባት፣ መናፍቃን እንደልባቸው የሚፋንኑባትና ደረታቸውን ነፍተው ኑፋቄያቸውን የሚያራግፉባት፣ እውነተኞች የሚወገዙባትና የሚሰደዱባት፣ ሐሰተኞች የሚነግሡባትና የከበሬታ ስፍራ የሚያገኙባት ቤተ ክርስቲያን ከሆነች ውላ አድራለች፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ችግሮቿ ነጻ እንድትወጣ የሚተጉላት ልጆቿን “ተሐድሶ መናፍቅ” እያለች በአንጻሩ ችግሮቿን የሚያባብሱትንና ነዳጅ የሚጨምሩበትን ትምህርታቸውም ቀና ያልሆነውን “የእፉኝት ልጆች”ን ኦርቶዶክሳዊ እያለች የቁልቁለት ጉዞዋን ቀጥላለች፡፡ እዚህ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሲባል በልማድ እንደሚጠራው ሕንጻውን ግንቡን ሳይሆን በተለይ መሪዎቿንና አስተዳዳሪዎቿን የሚመለከት ነው፡፡ “እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት” (ማቴ. 18፥17) ሲል ለመሪዎቿ መሆኑን ያሳያልና፡፡   
ይህን ከላይ በንጽጽር የቀረበውንና ቤተክርስቲያን ውስጥ በገሃድ እየታየ ያለውን እውነታ ተጨባጭነት በምሳሌ ማስገንዘብ ቢያስፈልግ፣ ከወራት በፊት በሊቁ በመምህር አሥራት ላይ የደረሰውን በደልና ለመናፍቁ ለኀይለጊዮርጊስ የተደረገለትን እንክብካቤ በንጽጽር ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ መምህር አሥራት የቅኔና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅና በርካታ ደቀመዛሙርት ያፈሩ መምህር ሲሆኑ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው፡፡ በእኚህ ሊቅ አገልግሎት ያልተደሰተውና መናፍቅ ናቸው ሲል በፈረጃቸው ማኅበረ ቅዱሳን የንስሐ ልጃቸው ሆና በቀረበች ሴት ተሰልለው በመቅረጸ ድምፅ እንዲቀረጹ ይደረጋል፡፡ እኚህ ሊቅ ዓይነ ስውር መሆናቸውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከቀረጸቻቸው በኋላ ተልእኮውን በሰጣትና በደብሩ ውስጥ ባለው የማኅበረ ቅዱሳን ክንፍ አማካይነት ወደሊቃውንት ጉባኤ ቀርቦ ሊቁ ተከሰሱ፡፡ ከሥራቸውና ከደመወዝ ታገዱ፡፡ 

Saturday, October 24, 2015

የወንጌል እንቅስቃሴ መቼም ሊጠፋ የማይችል እንቅስቃሴ ነውRead in PDF
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለውን የወንጌል እንቅስቃሴ ለማዳፈንና ብዙው ምእመን ወደሌሎች አብያተ ክርስቲያን እንዲፈልስ በፀረ ወንጌል ኀይላት በኩል ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ እነርሱ ይህን የሚያደርጉት ሃይማኖታቸውን ኑፋቄ ብለው ከሚጠሩት ከወንጌል እውነት ለመጠበቅ ወይም ለመከላከል ነው፡፡ ለወንጌል እንቅስቃሴ የተለያየ ስያሜ በመስጠት ወንጌልን መቃወም የዘወትር ተግባራቸው ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ወንጌል ጥንትም በነጻነት ሳይሆን በብዙ ተቃውሞና አድማ በመከራና ስደት ውስጥ እየተሰበከ ብዙዎች ኃጥኣንን በምሥራችነቱ ከሞት ወደሕይወት አሸጋግሯል፤ ዛሬም እያሸጋገረ ይገኛል፡፡

ዛሬ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ትልቁ ግብግብ ባህላዊውን (አገር በቀሉን) ክርስትና ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና እናምጣ በሚሉና አይሆንም ባህላዊ ክርስትናችንን ጥለን ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና አንመጣም በሚሉ ኀይላት መካከል ያለ ነው፡፡ ባህላዊ ክርስትና ያልነው መጽሐፍ ቅዱስን መነሻ ያደረጉና በባህላዊ መንገድ የተፈጠሩ ትምህርቶችን፣ ታሪኮችን፣ ሥርዓቶችን፣ ወጎችንና ለማዶችን ወዘተ. ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ይልቅ እጅግ አስበልጦና መጽሐፍ ቅዱስን ከዚያ በታች አድርጎ የመመልከቱን ጉዳይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ደግሞ ባህላዊው ክርስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ሊሸፍንና እርሱን ሊተካ አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል እየተመዘነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የማይጣረሰው ብቻ ሊቀጥል ይገባዋል፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጣረሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር ትምህርትና ፈቃድ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ፣ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ማድላት ይገባል የሚል ዐቋም ያለው ነው፡፡ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” እንዳሉ ቅዱሳን ሐዋርያት (የሐዋርያት ሥራ 5፥29) ከሁለቱ ለእግዚአብሔር ማድላቱና እርሱን ብቻ መታዘዙ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡

Tuesday, October 20, 2015

የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ይመርመር!!!ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በኑፋቄ እና በቅስጣ ድርሰት (በድርሰት ስርቆት) (Plagiarism) የተሞላው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ እንዲመረመር ስለ መጠየቅ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሰኔ 2007 ዓ.ም. ላይ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” የሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በአባ ሳሙኤል ስም የታተመ ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ራሳቸው የደረሱት ሳይሆን ከሰዎች ድርሰቶች ላይ የሰረቁትና በስማቸው ያሳተሙት ነው፡፡ በመጽሐፉ ገጽ 133 ላይ “ብዙ የዘመናችን ጸሐፊያን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ላይ የሠሩት ሥራ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ጸንታ የምትኖርበት ተከታዮች ምእመናንዋን የምትመራበት በነገረ ድኅነትም ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ የሚገኘው ግብረ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ስለግብረ መንፈስ ቅዱስ ጠንክረን ማስተማር አለብን፡፡” ብለው ፈር ቀዳጅ ለመምሰል ጥረት ቢያደርጉም የእርሳቸው ሥራ ባለመሆኑ ስለመንፈስ ቅዱስ የተጻፈ ፈር ቀዳጅ መጽሐፍ ሊባል አይችልም፡፡ እንዲያውም ወደ መጽሐፉ ውስጥ ሲገባ የሚያስደነግጥ ኑፋቄና የሚያሳፍር ስርቆት የተፈጸመበት ሆኖ ስለሚገኝ አንገት ያስደፋል፡፡ 

ይህን ጉድ ሸፍኖ ማለፍ ለቤተ ክርስቲያን ውርደት እንጂ ክብር አይሆንም፡፡ ለአቡነ ሳሙኤልም ቢሆን ይበልጥ የሚያዋርዳቸው ነውና ስለ ፈጸሙት ስሕተት ትምህርት በመውሰድ ይጸጸቱና ንስሓ ይገቡ ዘንድ፣ ሌሎች እንዲህ የሚያስቡና የሚያደርጉ ካሉም እንዲማሩበት በሚል፣ ከምንም በላይ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጉዳዩን እንዲመለከትና ውሳኔ እንዲሰጥበት በሚል ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ተነሣሁኝ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ስነሣ ማተኮር የምፈልገው ኑፋቄዎችን በመግለጥ፣ ቅሰጣ ድርሰትን በማጋለጥና ይህ ከሕግና ከሃይማኖት ትምህርትና ሥነ ምግባር አንጻር እንዴት ይታያል? የሚለውን በመጠቆም ይሆናል፡፡ የአንዱን ድርሰት ሌላው ሰርቆ የመጠቀም ባህል በቤተክርስቲያን ፈጽሞ የተወገዘ ተግባር ለመሆኑ በቅኔ ቤት የሚታየውን የሌላ ሰው ቅኔን መቀኘት ከሚያስከትለው ውርደት ጋር ማነጻጸሩ ብቻ እንኳ በቂ ነው፡፡ 

Monday, October 19, 2015

የእነ ደረጀ ወይንዬ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በክሽፈት ተደመደመ


ቤተክርስቲያን ተልእኮ ሳትሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ተልከው “ተሐድሶዎች” የሚሏቸውን በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ እናስወግዛለን በሚል ርእስ ገንዘብ ለመሰብሰብና ኪሳቸውን ለመሙላት አልመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትና ለገቢ ማሰባሰቢያው ብዙ ወጪ ያወጡት እነደረጀ ወይንዬ በቅጽል ስሙ “ወርቃለማሁ” (ወርቃለማሁ የተባለው በወይንዬ ተክለሃይማኖት ማህበር የመጀመሪያ ዙር ገቢው ትልቅ የአንገት ወርቅ ስለገዛበት ነው) ያለሙት ሳይሳካ እቅዳቸው መክሸፉና ኪሳራ ላይ መውደቃቸው ታወቀ፡፡ ያዘጋጁትን ምግብም ለመቄዶንያ አረጋውያን ለመስጠት ተገደዋል፡፡
ከግሸን ክብረ በዓል ጀምሮ ቲፎዞዎችን በማሰባሰብ ሲንቀሳቀስ የቆየው ቡድን አንዳንድ በቤተክርስቲያን የሌሉ በዓለም መድረክ ውስጥ ግን የሚታወቁ ሰዎችን ለምሳሌ የጊዮርጊስ ክለብ አስጨፋሪ እንደሆነው ይድነቃቸው (አቸኖ) ያሉ ሰዎችን ወደቡድኑ አስገብተው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሲሆን አቸኖ በደረጀ ወይንዬ አማካኝነት ተጋብዞ እንደመጣና ለምን እንደተሰበሰበ ግን በሚገባ እንደማያውቅ ሲናገር ተሰምቷል፡፡ የደረጀ ዓላማ ግን በአቸኖ ጀርባ ታዝሎ ደጋፊውን ለዚህ እኩይ ዓላማ ማሰለፍ እንደነበር ከአካሄዱ ታውቋል፡፡ ደረጀ እያለ ያለው አቸኖን ይዤ ብዙ ሰው አመጣለሁ ነበር፡፡ 

Friday, October 16, 2015

ሰበር ዜና፡- በወንድሙ ስምና የትምህርት ማስረጃ ሲነግድ የቆየው የማቅ ልጅ “ታዴዎስ” ሽፈራው ታሰረእውነተኛና ሚዛናዊ በሆነ ዘገባውና ተጨባጭ የሆነ መረጃ በማቅረብ የሚታወቀው አባ ሰላማ ድረ ገጽ ባለፈው ዘገባው በአዲስ አበባ /ስብከት /ቤት የህግ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረውታዴዎስ ሽፈራው” ተብሎ የሚጠራውና የራሱ ስም ግን አበባው ሽፈራው የሆነው ግለሰብ የህግ ትምህርት ሳይኖረው በማጭበርበርና የወንድሙን ስም በመጠቀም ታዴዎስ ተብሎ የህግ ትምህርት ሳይኖረው ተምሬአለሁ በማለት ሀ/ስብከቱን እንደ ልቡ ሲፈነጭበት አባ ሰላማዎች ይህ ግለሰብ በማጭበርበር እንጂ የሕግ ትምህርት እንዳልተማረ አረጋግጣችሁ ዘግባችሁ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ስለሆነም ዘገባችሁ እውነት ምስክርነታችሁም ሐሰት የሌለበት በመሆኑ ጊዜ ገቢር ነውና ይሄው ጊዜው ደርሶ አቶ ታዴዎስ ጥቅምት 1/2008 .. በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
 የጨለምተኛው የማቅ ቡድን አባላት ግን ይህንን ከባድ ወንጀል የተሸከመ ግለሰብ ለማስፈታት በየፖሊስ ጣቢያው ወጣ ገባ ሲሉና ቅጥረኞች ለሆኑት አንዳንድ የፖሊስ አባላት ገንዘብ ሲመነዝሩና ወንጀሉ 10 -15 ዓመት የሚያሳስር ወንጀል ሆኖ እያለ በእውነተኛው ስሙ አበባው በህግ እንዳይጠየቅ በገንዘባቸው ብዛት ህግን ለመጨፍለቅ ሲዋትቱ ታይተዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው የማቅ አባላት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ሳይማሩ የቀሰሱ ስለሆኑ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲፕሎማ ዲግሪ ሳይማሩ በገንዘብ በመግዛት መ/ር የተባሉ ልጆች ስላሉት ነው ጉዳዩን በአመፅ መንገድ በአጭሩ ለመቅጨት የሚሯሯጡት፡፡ 

Monday, October 12, 2015

በወንጌል እንቅስቃሴ ላይ ያረጀ ግን አዲስ የተባለ ዘመቻ ለምን ተከፈተ? የከፈተውስ ማነው? Read in PDF
የወንጌል እንቅስቃሴን ለማዳፈን ከተቻለም ለማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳን ያላደረገው ጥረት የለም፡፡ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም፡፡ ያላደራጀው ቡድን የለም፡፡ ያልከፈተው ጸረ ወንጌል ዘመቻ የለም፡፡ ያላሰማራው ሰላይ የለም፡፡ ያልመደበው በጀት የለም፡፡ ያላስጨበጠው ግንዛቤ የለም፡፡ ያላሰባሰበው ገንዘብ የለም፡፡ የወንጌሉን እንቅስቃሴ ጭራቅ አስመስሎ በመሳል ከተራ ምእመን እስከ ጳጳስ ያላወናበደው የኅብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ ብቻ ምን ቅጡ… ነገር ግን የወንጌል እንቅስቃሴ እየተስፋፋና ብዙዎችን እየነካ መቀጣጠሉን ቀጥሏል፡፡ ወንጌል የእግዚአብሔር ክቡር ሐሣብ በመሆኑ ማንም ሊያጠፋው አይችልም፤ እንዲያውም ሲነኩት ይብሳል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ከዚህ ቀደም ራሱን “ጸረ ተሃድሶ ህብረት” ብሎ ሲንቀሳቀስ የነበረው “የቱሪስት ቡድን” እየተባለ ከሚጠራው ስብስብ መካከል አንዳንዶቹን በማካተት እንቅስቃሴዎችን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ይህ ቡድን በማቅ የተደራጀ ቡድን እንደ ሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም ማቅ ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ ሃይማኖቱን በኃይል እንጂ በስብከት የማያስፋፋ በመሆኑ፣ ሃይማኖቱን ለማስፋፋት ሰባክያንን ሳይሆን ሁከት ፈጣሪዎችን፣ በየቤተ ክርስቲያኑ ጠብ አጫሪዎችን፣ ዐውደ ምሕረት ላይ ወጥተው ድምፅ ማጉያ ነጣቂዎችን፣ ከስብከት በኋላ ጠብቀው ሰባክያነ ወንጌልን ለመደብደብ የሚቃጡትን ቅጥረኞችን ነው ያደራጀው፡፡ ከመድረክ በስተጀርባ እንዲህ ዓይነት ቡድኖችን አደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ሃይማኖታዊ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ ከሃማኖተኛነቱ ይልቅ ሌላ አጀንዳ ያለው ወይም ፖለቲከኛ ነው ቢባል ምንም ስሕተት የለበትም እውነት ነው፡፡

Wednesday, October 7, 2015

ግብረ ሰዶማዊነትን ለመቃወም ሙጋቤያዊ አቋምም ከመሪዎቻችን ያስፈልጋል!


 Read in PDF

ምንጭ፡-የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
               እኛ ግብረ ሰዶማውያን አይደለንም!!!” (ሮበርት ሙጋቤ)


    በዘመናችን መንፈሳዊ ማንነታችን ስለተጐሳቆለብን ኃጢአትን በአለም መድረክ የሚቃወሙት አለማውያን መሪዎች፥ ከእኛ ይልቅ በብዙዎች ዘንድ የመደመጥን ዕድል ያገኙ ይመስላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ፍጹም ስትዋብ በአለማውያን መሪዎች ላይ ተጽዕኖ ስለማሳደሯ ምንም ጥርጣሬ የለውም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን መለያ ባሕርያት መካከል አንዱ ክርስቶስ በገዛ ደሙ መሥርቷታልና ቅድስት መሆኗ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቅድስናን ጠባይ ገንዘብ ያደረገችው፥ ከመሠረታትና ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ ከሚሆን ከክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡
     ቤተ ክርስቲያን ከአለማውያን መሪዎች ጋር ያላት ግንኙነት እጅግ ጤናማ መሆን አለበት፡፡ ግንኙነቱ ጤናማ መሆን አለበት ስንል፥ መርሑ ቅድስናና ንጽሕናን ብቻ በተከተለ መንገድ መሆን መቻል አለበት ማለታችን ነው፡፡ ቅድስና በኃጢአተኛው ላይ እጅግ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን በስደት ዘመን የሰማዕታትን አንገት ይቀሉ የነበሩት ወታደሮች፥ በሚያስደንቅ መንገድ የጌታ ባለሟሎች የሆኑትና ከመግደል ለጌታ እስከመሞት የደረሱት የሰማዕታቱን የቅድስና ጉልበት አንገት በመቁረጥ ፤ በማቃጠልና በብዙ መከራ ማሸነፍ ስላልቻሉ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የክርስቶስ ኢየሱስን ሕይወትና ቃሉን እጅግ በመውደድና በማንበብ ለአገራቸው ሕዝቦች እጅግ ቅን የነበሩትን እንደመሃተመ ጋንዲ ያሉ መሪዎችንም ማንሳትም ይቻላል፡፡

   ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር በመንገዷ ፍጹም በሆነችበት ዘመኗ፥ አለማውያን ቅን መሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ጨካኝና እጅግ ደንዳና መሪዎችም ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖን ማሳደር ችላለች፡፡ በዚህም ተጽዕኖ መሠረት እንደኮሞዶስ(Comodous)(180-192 ዓ.ም) ሮማዊ ያሉ መሪዎች ከፍጹም ጭካኔያቸው ሲታገሱ ፤ ጌታን አሳልፎ እንደሰጠው ጴንጤናዊ ጲላጦስ አይነቶች ደግሞ ፍጹም ወደጌታ ኢየሱስ ፊታቸውን መልሰው ሰማዕት ሆነዋል፡፡ ለቁጥር የሚታክቱ አመጸኞችና ጨካኞች ፤ ዘፋኞችና አመንዝሮች … ወንጌልን በማንበብ ፣ በመስማት ፣ ከቤተ ክርስቲያን ሕይወት በማየት ፊታቸውን ዘወር ሲያደርጉ በዘመናችንም በጥቂቱ እያየን ነው፡፡
    የኢትዮጲያን መሪዎች ስናነሳ ደግሞ፥ ለአገሪቱ ባስቀመጡት ፍሬያማ የእድገት ቀመር ወይም መሠረት “እጅግ የተተቹ” ቢሆንም፥ ከቤተ ክርስቲያን ጋር “የቅርብ ሽርክና” እንዳላቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ያላቸው የቅርብ ግንኙነት ያን ያህል የእነርሱን መንፈሳዊ ሕይወት የነካና ተጽዕኖ ያሳደረ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ እንደአፄ ዓምደ ጽዮን ያሉ የአባታቸውን ሚስት ዕቅብት አድርገው ይዘው ፣ እንደአፄ ፋሲል(ፋሲለደስ)ና ሌሎችም በአመንዝራነት እጅግ የታወቁ ሆነው ቤተ ክርስቲያን በማሠራታቸውና ለገዳማት ብዙ አስራት በኩራት በመላካቸው ብቻ ተፈርተው ተቀመጡ እንጂ በተጠጓት ቤተ ክርስቲያን ሕይወታቸው አንዳች አልተለወጠም ማለት ያስደፍራል፡፡ እንዲያውም የተቃወሟቸውን ሰዎች በግልጥ በአደባባይ ያስገርፉ ፤ ያግዙ (ያስሩ) እንደነበር ታሪክ ከነትዝብቱ ይነግረናል፡፡

Sunday, October 4, 2015

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዝማሬዎችና መዘምራን ላይ የተከፈተ ዘመቻ Read in PDF
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል እንቅስቃሴዋ ጥሩ ደረጃ ያለ መሆኑን ለመረዳት በወንጌል አገልግሎት ላይ የሚታየውን የተቃውሞ ሂደት መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መዝሙሮቻችን ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ተረትን መሠረት አድርገው የሚዘምሩ ዘማሪዎችና መዝሙሮቻቸው ሥፍራቸውን እየለቀቁ እያየን ነው፡፡
አዳነች፣ አዜብ፣ ሲስተር ሕይወት፣ እንግዳወርቅ ምንዳዬ እና ከጋብቻ ውጪ በወለደው ልጅ፣ በጭፍራ ቤት ውሎው በተቀረፀበት ከባድ የሥነ ምግባር ችግር ለማኅበረ ቅዱሳን ተንበርካኪ ሆኖ አንዴ “ፊደል ናት”፣ አንዴ “መሠላል ናት” ወዘተ እያለ (ከዚህ በፊት በተአምረ ማርያም ምን ብሎ እንደቀለደ ማስነበባችን ይታወሳል) ለኑሮው ብቻ የሚዘምረው ቴዎድሮስ ዮሴፍ በተረት ላይ ተመሥርቶ ለፍጡራን ከሚዘምረው ቡድን መካከል የሚጠቀሱ ዘማሪዎች ናቸው፡፡

Friday, October 2, 2015

ለወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፡- እንደእነ አቶ ግርማ ያሉት የሐሰት መምህራንና አጥማቂ ነኝ ባዮች ሊጋለጡና ወደ እውነት መንገድ ሊመለሡ ይገባቸዋል!!

 Read in PDF


በዲ/ን ኒቆዲሞስ
‹‹… በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክህነቱ ተቋም ዝም ቢልም መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን የማኅበረሰቡን አብሮነትና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚንድ የእነ አቶ ግርማ ዓይነት ያለ አጥማቂ ነን ባዮችን፣ የኢትዮጵያ ቤ/ን የማይወክሉና የማታውቃቸውን ግለሰቦችን እኩይ ሥራን እያየና እየሰማ መታገሥ አለበት ብዬ አላስብም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ እኚህን ሰውና መሰል ግለሰቦችን ሊያስቆም፣ በሕግም ሊጠይቃቸው ይገባዋል ባይ ነኝ …፡፡››
ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል በቤተ ክርስቲያናችን ስላሉ አጥማቂ ነን ባዮች፣ ሐሣይ መሢሕዎች ላይ የጻፈው ጽሑፍ ብዙዎችን እያነጋገረ እንደሆነ ሳንታዘብ እንዳልቀረን እገምታለኹ፡፡ በዚህ ጽሑፍህ ላይም በመጦመሪያ መድረኩና በተለይም ደግሞ በሶሻል ሚዲያው የስድብ፣ የውግዘት፣ የርግማን መዓት እንዳስተናገደ ታዝበናል፡፡ አንድ ጸሐፊም ይህ የዲ/ን ዳንኤል ጽሑፍህ አጥማቂውን አቶ ግርማን የተመለከተ መሆኑንም ከግንዛቤ በማስገባት የሰጠውን ምላሽ የ‹‹ዘሐበሻ ገጸ-ድር›› አስነብቦናል፡፡
ከኢትዮጵያ እስከ ሰሜንና ደቡብ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካና ካናዳ ድረስ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለጋሽ ግርማ ፍጹምነት፣ ታላቅነት፣ ጻድቅነት፣ የፈውስ ስጦታና  ገቢረ ተኣምራት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ ጥብቅናም ቆመዋል፤ ይሄን ያህል ደጋፊና ተከታይ አላቸው ማለት ነው፤ በእውነት አስገራሚ ነው!!