Friday, October 2, 2015

ለወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፡- እንደእነ አቶ ግርማ ያሉት የሐሰት መምህራንና አጥማቂ ነኝ ባዮች ሊጋለጡና ወደ እውነት መንገድ ሊመለሡ ይገባቸዋል!!

 Read in PDF


በዲ/ን ኒቆዲሞስ
‹‹… በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክህነቱ ተቋም ዝም ቢልም መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን የማኅበረሰቡን አብሮነትና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚንድ የእነ አቶ ግርማ ዓይነት ያለ አጥማቂ ነን ባዮችን፣ የኢትዮጵያ ቤ/ን የማይወክሉና የማታውቃቸውን ግለሰቦችን እኩይ ሥራን እያየና እየሰማ መታገሥ አለበት ብዬ አላስብም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ እኚህን ሰውና መሰል ግለሰቦችን ሊያስቆም፣ በሕግም ሊጠይቃቸው ይገባዋል ባይ ነኝ …፡፡››
ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል በቤተ ክርስቲያናችን ስላሉ አጥማቂ ነን ባዮች፣ ሐሣይ መሢሕዎች ላይ የጻፈው ጽሑፍ ብዙዎችን እያነጋገረ እንደሆነ ሳንታዘብ እንዳልቀረን እገምታለኹ፡፡ በዚህ ጽሑፍህ ላይም በመጦመሪያ መድረኩና በተለይም ደግሞ በሶሻል ሚዲያው የስድብ፣ የውግዘት፣ የርግማን መዓት እንዳስተናገደ ታዝበናል፡፡ አንድ ጸሐፊም ይህ የዲ/ን ዳንኤል ጽሑፍህ አጥማቂውን አቶ ግርማን የተመለከተ መሆኑንም ከግንዛቤ በማስገባት የሰጠውን ምላሽ የ‹‹ዘሐበሻ ገጸ-ድር›› አስነብቦናል፡፡
ከኢትዮጵያ እስከ ሰሜንና ደቡብ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካና ካናዳ ድረስ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለጋሽ ግርማ ፍጹምነት፣ ታላቅነት፣ ጻድቅነት፣ የፈውስ ስጦታና  ገቢረ ተኣምራት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ ጥብቅናም ቆመዋል፤ ይሄን ያህል ደጋፊና ተከታይ አላቸው ማለት ነው፤ በእውነት አስገራሚ ነው!!

ነገርዬው ከመገርመም አልፎ እጅጉን የሚያሳዝንና ምእመናችን ምን ያህል በክህደትና በስህተት አሠራር ተጠላልፎ የወደቀ፣ ልክ እንደ ነነዌ ሕዝብ ግራና ቀኙ መለየት ያቃተው፣ ምልክትን የሚሻ፣ ተኣምራትን የሚያሳድድ ትውልድ እንደሆነ የሚያሳየን ነው፡፡ በመሠረቱ ዳንኤል በእነዚህ አጥማቂ ነን ባዮች የቅዱስ ወንጌል ጠላቶች፣ ሐሰተኞች፣ ከሃዲዎች፣ አጭበራባሪ ነጋዴዎች ዛሬ የተፈጠሩ አይደሉም፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ የነበሩና አሁንም መልካቸውንና አካሔዳቸውን ቀይረው የተከሰቱ ናቸው፡፡
የእኚህን አጥማቂ ነኝ ባይ የአቶ ግርማን ቪዲዮ በመጀመሪያ ጊዜ ያየኹት ለትምህርት ደቡብ አፍሪካ በነበርኩበት ወቅት ነበር፡፡ በዚህ ቪዲዮ እጅጉን ነበር ያዘንኩት፡፡ እንዲያ ያን ምስኪን ምእመን ሰብስበው ድራማ ሲሰሩበት ሣይ ልቤ ተነክቷል፡፡ እንዴት እንዲህ ዓይነቱ የጥፋት ርኩሰት በቤተ ክርስቲያናችን አውድ ምሕረት ላይ ያለ ምንም ከልካይና ሃይ ባይ ብዙዎችን እያሳተና እያሳሳተ እንደ ይሁዳ የገንዘብ ከረጢታቸውን ሲሞሉ አባቶችና ቅዱስ ሲኖዶስ እንዴት ዝም ይላሉ ብዬም ነበር፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ዘግይቶም ቢሆን እኚህ ሰው እንዳያጠምቁ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም ልባቸውና ዓይናቸው በገንዘብ የታወረ የአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ገቢያችንን ይጨምሩልናል፣ ምእመናኑን ይስቡልናል በሚል እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት እየተዘዋወሩ እያጠመቁ ነው፡፡ የእኚህ አጥማቂ ነኝ ባይ ይህ አገልግሎታቸውም ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ ወደ ባሕር ማዶም ተሻግሮ በርካታ የዋህ ምእመናን እያሳሳተና ወደ ክህደት መንገድ እየመራ ነው፡፡
መቼም በቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ዓይነቱ ርኩሰትና ዓመፃ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ እንደሆነ ትስተዋለህ ብዬ አልገምትም፡፡ የግብጽን ጥበብ- አስማትን፣ ሟርትንና ድግምትን ከአብነት ትምህርቱ ጋራ ጎን ለጎን ተምረው አጋንትን የሚጎትቱና ሙታንን የሚስቡ፣ ከዓውደ ነገሥት እስከ መርበበተ ሰለሞንና መልከአ ሳጥናኤልን የሚደግሙና በዚህ ሥራቸውም እጅግ የሚፈሩና አንቱታንና ከበሬታን ያተረፉ ደባትራን እንደነበሩ  ታሪካችን ይነግረናል፡፡ ድማሙ ብዕረኛ መንግሥቱ ለማ ‹‹ትዝታ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ›› በሚል በተዉልን የአባታቸው ማስታወሻ ላይ አንድ የተከበሩ መምህር ይህን የሰይጣንን ጥበብ የተማሩ ተማሪዎች በላኩባቸው አይጥ መንጋ በቁማቸው ተበልተው መሞታቸውን መጽሐፋቸው ያትታል፡፡
እንደውም አለቃ ለማ እነዚህን ይህን ክፋት የሚማሩ ተማሪዎችና ደባትራንን እንዳይቀርቧቸው በግልጽ ይቃወሟቸው እንደነበር ይህ መጽሐፍ ያትታል፡፡ አስገራሚው ነገር ይህን የአጋንትን ሥራ የሚሠሩ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አግልግሎት የሚሳተፉ፣ ማሕሌቱን የሚያደምቁ፣ የሚከበሩና የሚፈሩ መሆናቸው ነው አሳዛኙ እውነታ፡፡
ዳኒ እንደ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይነትህና ተቆርቋሪነትህ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ ትንሽ አልዘገየኹም ብለህ አታስብም፡፡ ስንቱ ነው እናጠምቃችኋለን፣ ለበሽታችሁና ለችግራችሁ ፍቱን መፍትሔ አለን በሚሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን ጥላ መከታ አድርገው የስንቱን ቤት ያፈረሱትን፣ ትዳር የበተኑትን፣ አእምሮአቸውን ያሳጡትን፣ ብኩንና እብድ አድርገው ያስቀሯቸውን ወገኖቻችንን ቤት ይቁጠራቸው፡፡
አሳዛኙ ነገር ይህን የአጋንንት ሥራ ከመማርና ከመለማመድ አልፈው በሌሎች ላይ የሚሞክሩ፣ ይህን የክፋት ሥራ ሚያስፋፉ በጵጵስና ደረጃ ላይ ሣይቀሩ ያሉ አባቶች መኖራቸው ደግሞ ልብን በኀዘን የሚሰብር ነገር ነው፡፡ ይህ ትውልድ እንዲህ ዓይነቱን አጋንንታዊ አሠራር ሊቃወምው ይገባዋል፡፡ ምንም ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ እውቀት የሌላቸው፣ ቁጭ ብለው ከመማር ይልቅ በዙረት ዕድሜያቸውን የፈጁ፣ ትዳራቸውን ያፈቱ፣ ኑሮ ያልተሳካላቸው፣ ወታደሮችና ጨዋዎች ኹሉ ከመርካቶ ቆብና ቀሚስ እየገዙ በመልበስ የዋህ ምእመናኑን እንዲህ መጫወቻ ሲያደርጉት ዝም ማለት አለብን እንዴ … አይመስለኝም … ?!
እንዴት ሰው በሰለጠነ አውሮፓና አሜሪካ ባሉ ዓለማት ነገሮችን ኹሉ በሎጂክና በምክንያት በሚቀበል ራሽናል በሚባል ማኅበረሰብ መካከል እየኖረ ቢያንስ እምነት እንኳን ቢጎድለው እንዴት እንደ ባለ አእምሮ እንዲህ ዓይነቱን የለየለት ማታለል፣ ድራማና ማጭበርበር መለየት ይሣነዋል፡፡ በቅርቡ ያየኹት የእኚህ ሰው-የአቶ ግርማ ቪዲዮ ላይ አንድ የናሳ ሳይንቲስት ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ወንድማችን በእርሳቸው ጥምቀት ሲናዘዝ አይቼ እጅጉን አዘንኩ፡፡ ይህ ሰው እንኳን የናሳ ሳይንቲስት ሊሆን ቀርቶ በዚህ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋኩልቲ በር ማለፉን እንኳን ያጠራጥራል፡፡
ለዚህ ሰው አጥማቂ ነኝ ባዩ አቶ ግርማ ባደረጉለት ኢንተርቪው ላይ ክፉ መንፈስ ለምን አበሾች ላይ ብቻ ትበረታህ ተብሎ ሲጠየቅ፡- ‹‹አይ አንተ ደግሞ ፈረንጆቹ እኮ ኹሌም የእኛ ናቸው የት ያመልጡናል ብለህ ነው?! ደግሞ ፈርንጆቹ ምንም አያውቁም አልጫ ነገር ናቸው …፡፡›› ይህን ነው የናሳው ሳይንቲስት ነኝ ባይ ተጠማቂ ቃል በቃል የተናገረው… የሚገርመው በቪዲዮው ላይ ተደጋግሞ ይህ ሰው የናሳ ሳይንቲስት መሆኑ ነበር ሲነገር፣ ሲሰበክ የነበረው፡፡ ይህ ደግሞ ለምን እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ምእመናን የእኚህ ሰው ገቢ ተኣምራታቸው ወደተከበረው ተቋም ወደ ናሳ የጠፈር ምርምር ማእከል እንኳን ድረስ ሣይቀር ዘልቆ የገባ ነው የሚል የጭንቅላት ጨዋታ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
ዳኒ ብትችል ቤተ ክርስቲያናችንን ተጠግተው ይህን የዋህ ምእመናን በማታለል ላይ ያሉትን አቶ ግርማንና ሌሎች እርሳቸው መሰሎችን ነጋዴዎችንና አጭበርባሪዎችን በማጋለጥ ተከታታይ ጽሑፎችን ብታስነብበን በእውነት ነው የምልህ ይህን ምእመናን ከሐሰተኞች መምህራንና ሐሣይ መሢሕዎች ትታደጋለህ፡፡ ከማንም ይልቅ አንተ በዚህ ጉዳይ መጻፍህ ብዙዎችን እንደሚያንቀሳቅስና እንዲሚያነቃቃ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይህን ደግሞ በሰሞኑ ጽሑፍህ እንደተገነዘብከው ተስፋ አድርጋለኹ፡፡
መጽሐፍ፡- ‹‹በሰው ልማድ ምንም እንኳን የምንመላለስ ብንሆን እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፣ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፡፡ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ኹሉ እናፈርሳለን፣ ለክርስቶስ ለመታዘዝ አእምሮን ኹሉ እንማርካለን፣ መታዘዛችሁ በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ደግሞ ልንበቀል ተዘጋጅተናል፡፡›› እንዲል፡፡ (፪ቆሮ. ፲፣፫-፮)
እንግዲህ ዳኒ እንደ መጽሐፉ ቃል ይህን የአጋንትንንና የሰው ልጅ ጥልቅ አእምሮ የፈጠረውን አሳብና የክፋት አካሔድ/ክፉ የጨለማ ሥራ ማፍረስና እነዚህን ሰዎችንም ወደ ክርስቶስ መንግሥት መማረክ፣ አለመታዘዝን ደግሞ ለመበቀል የመንፈስ ሰይፍ የኾነው ቃለ እግዚአብሔር በእጃችን እንዳለ የሚያስረዳን ኃይለ ቃል ነው፡፡ እናም ዳኒ በዚህ በጀመርከው የጨለማውን አጋንንታዊውንና የሰው ልጅን አእምሮ የክፋት ሥራ ማፍረስና ማጋለጥ እንድትቀጥልበት ታናሽ ወንድምህ አደራ እልኻለሁ፡፡
ወንድማችን ብትችል የእኚህን ሰው ተከታታይ ቪዲዮቻቸውን እየመረመርህ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋራ በማነጻጸር ትንታኔ በመስጠት ብትተቸው መልካም ይሆናል፡፡ ልክ ባለፈው ጽሑፍህ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልወጣ ያለ አጋንንት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም መውጣቱን ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ አንጻር ይህ መናፍቅነት/ክህደት መሆኑን እንደለጽከው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ከእውቀትና ከእውነት የጎደሉ ሰዎች ናቸው ምእመኑን እያሳቱት ያለው፡፡
ትዝ የሚለኝ ባህታዊ ገ/መስቀል ዝናቸው በገነነበት ዘመን ልጅ ሆነን አንድ ጊዜ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሲያስተምሩ ‹‹ጂሆቫ ማለት ጅብ ማለት ነው፡፡›› እነዚህ የሖዋ ምስክሮች/ጂሆቫዎች የስማቸው ትርጉም ጅብ ነው የሚለውን ትምህርታቸውን በኋላ ነፍስ አውቄ ‹‹ጂሆቫም ሆነ ይሖዋ›› እስራኤላውያን እጅግ ሚያከብሩትና በዘመኑ የነበሩ አይሁዳውያን ጸሐፍትም ይህን የአምላካቸው ስም ሲጽፉ በታላቅ ፍርሃት በመንቀጥቀጥና በመቆም በልዩ ወርቃማ ቀለም እንደሚጽፉት ከእውነተኛ መምህራን በተረዳሁ ጊዜ አለማወቅ፣ ማይምነት ምን ያህል ሕዝባችንና ሳይማሩ እናስተምራለን በማለት የተነሡ ወገኖቻችንን ከእውነት መንገድና ሕይወት እንዳጎደላቸው ሳውቅ ከልቤ ማዘኔን አስታውሳለኹ፡፡
ወንድሜ ዳንኤል እባክህ ይህን ጽሑፍህን ቀጥልበት፣ ከኢትዮጵያ እስከ አፍሪካ፣ አውሮፓና አሜሪካ ድረስ ሣይቀር ዘልቆ ምእመኑን እውነትና ሕይወት ከሆነው ከቤተ ክርስቲያነችን መንገድና አስተምህሮ እያወጣ ያለውን የሐሰት ትምህርትና ሐሳይ መሢሕዎችን አጋልጥልን፡፡ አቶ ግርማ ያለ ምንም ቅድመ ኹናቴ ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እያደረጉት ያለውን የክህደት አስተምህሮአቸውን፣ ልምዳዳቸውንና የለየለት ንግዳቸውንና ዝርፊያቸውን ትተው ወደ እውነተኛይቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ እንዲመለሱ ሊነገራቸውና ሊገሠጹ ይገባቸዋል፡፡
በተጨማሪም እኚህ ሰው አጠምቃችዋለኹ የሚሏቸውን ሰዎች ኹሉ እከሌና እከሊት፣ ዘመድህ፣ ጓደኛህና የትዳር አጋርህ አስደግሞብሻል፣ አስደግሞብኻል፣ አስመትቶብሻል፣ አስመትቶብኻል በሚል በኅብረተሰባችን መካከል ለዘመናት የቆየው ማኅበራዊ መስተጋብር፣ አብሮነት፣ መተማማመንና መተዛዝን በማኅበረሰባችን መካከል እንዲዳከምና እንዲጠፋ እያደረጉ እያሉ መሆናቸው ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባዋል፡፡ እናም የማኅበረሰብ ሳይንስ ምሁራንና ማኅበረሰቡ ይህን እርስ በርሳችን ያለንን ፍቅር፣ መተማመንና መተሳሰብ እየሸረሸረ ያለውንና እርስ በርስ በጠላትነት እንድንተያይ እደረገ ያለውን የአደባባይ ሸፍጥ፣ የማኅበረሰባችንን አንድነት ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውንና እየተናደ ያለውን መልካም እሴታችንን ለመጠበቅ በጋራ መነሣት ያስፈልገናል ብዬ አስባሀለሁ፡፡ 

በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክህነቱ ተቋም ዝም ቢልም መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን የማኅበረሰቡን አብሮነትና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚንድ የእነ አቶ ግርማ ዓይነት ያለ የኢትዮጵያ ቤ/ን የማይወክሉና የማታውቃቸውን ግለሰቦችን እኩይ ሥራን እያየና እየሰማ መታገሥ አለበት ብዬ አላስብም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ እኚህን ሰውና መሰል ግለሰቦችን ሊያስቆም፣ በሕግም ሊጠይቃቸው ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡  


አበቃሁ!! ሰላም!!

21 comments:

 1. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ፡- እስመ በቅንአትሰ ኢይትረከብ ፀጋ እግዚአብሔር
  በቅንአት የአግዚአብሔር ፀጋ አይገኝም
  ቅንአት ማለት ለሌላ ሰው የተደረገውን መልካም ስጦታ እና ፀጋ በመፈለግ መመቅኘትና ስም ማጥፋት የማይገባ ነገር መናገር ቅንአት ይባላል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ በሰዎች ምርጫ የሚሰጥ ሳይሆን እግዚአብሔር በአወቀና በተረዳ ለቤተክርስቲያን ለምዕመናን ይጠቅማል ብሎ ለመረጠው የሚሰጠው ስጦታ ነው፡፡ በዚህ በአለንበት ዘመን በፍፁም ፀጋ እግዚአብሔር ተቋርጧል፡፡ ወይም የፀጋ ስጦታ ያለው ሰው የለም አይባልም ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላካችን ሁሌም ህያው ስለሆነ ነው፡፡ አንዳንድ እንደእነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ ከየት ጎራ እንደሆኑ የማይታወቁ አስማሳይ በቤተክርስቲያኒቱ ስም የሚነግዱ በሚዲያ መቅረብን መንግስተ ሰማያት መግባት አድርገው የሚገምቱ ከእኛ በቀር ለምን ሌላ ሰው አንቱ ይባላል ብለው የትውልድን ተስፋ የሚያጨልሙ አንዳንድ አስማሳይ የወንጌል አገልጋይና ተራ ሁለገብ መልስ ሰጪ የሆኑ የእግዚአብሔርን ሥራ ቀርበው ሳያዩ የእግዚአብሔር ሰዎችን ሥራ ቀርበው ሳይረዱ በቅናት መንፈስ በየፌስቡኩ የለቀቁትን የቅናት ውጤታቸውን ተመልክተን አላውቂ በመሆናቸው አምላክ ሆይ ይቅር በላቸው ብለናል፡፡
  ለመሆኑ ለዘመናት በቤተክርስቲያኑቱ ላይ አንዳንድ ከአምልኮተ አግዚአብሔር ወጥተው ለአንጀራ ብቻ ተጠግተው ሕዝቡን በደብተራዊ መተት ግራ ሲያጋቡትና ሲመትቱበት የኖሩትን ለምን ተው አላላቸውም፡፡ ሰይጣንን በሰው ልጅ ላይ መልክዓ ሳጥናኤል እየደገሙ ሲያሳብዱ ለምን ከክርስቲያናዊ ህይወት ውጭ ነው ብሎ አልፃፈም? ለነገሩ አንተም የእነርሱ ተባባሪ ስለሆንክ ዝም አልክ፡፡ አሁን ግን በአደባባይ ለምን አጋንት ወጣ ትውልዱ ለምን ቆረበ ሰገደ፣ ፀለየ፣ መቆጠሪያ ለፀሎት ተጠቀመ፣ ብሎ ለሰይጣን ዋስ ሆኖ መቆም በጣም ይገርማል፡፡ ይህ አባባልህ ምንም ዲያቆን አያሰኝህም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልክቱ በምዕራፍ 13 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በክርክርና በቅናት አይሁን›› ይላል ይህ ዳንኤል ክብረት እውነት ለትውልዱ ያሰበ ቢሆን ነገሩን ጉባዔው የሚካሄድበት ቦታ ድረስ መጥቶ ለግለሰቡ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ትምህርታቸውንም በማድመጥ አና የጉባዔውን ምዕመናን በመጠየቅ መሆን ነበረበት ግን ለምን በፀጋቸው እግዚአብሔርን አገለገሉ ፣ ለምን የእግዚአብሔር አምልኮ የገባው ሕዝብ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ወደዳቸው፣ ትምህርታቸውንስ ለምን ሰማ በማለት በቅናት የተፃፈ ጽሁፍ ስለሆነ መላከ መንክራት ግርማ ወንድሙን አይመለከትም፡፡
  ለመሆኑ መላከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ማናቸው? እስኪ በጥቂቱ እንመልከት መላከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ከካህን አባታቸው ከመምሬ ወንድሙ መንግስቱ ተወልደው በባሌ ጎባ ባለወልድ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ ዲቁና ተቀብለው ከዚያም በኋላ ብዙ መንፈሳዊ ትምህርት እና የእርኩስ መንፈስ ውጊያን ከግብጽ አባቶች በህይወት አይተውና ተምረው ዛሬ በሥልጣነ ክህነት ሕዝቡን አጋንንት በማውጣትና ድውይ በመፈወስ ፀጋቸው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አገልግሎታቸው ብዙ ፈተና እና ትችት ያለበት ቢሆንም ፕሮግራሙ የሚካሄድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ እስከዛሬ ድረስ በርሱ ቸርነት አልተቋረጠም፡፡ አሁንም ማንም በማንኛውም የሥልጣን ደረጃ ላይ ያለ ሰው ለማውገዝም ለማገዝም በግልጽ የሚካሄደውን ጉባዔ የማካሄድበት ቤ/ክ ድረስ በመምጣት መከታተል እና ችግር ካለ በመረጃ መንቀፍና መተቸት ይችላል፡፡ ይህ ባልሆነበት መልኩ አንድ ቀን እንኳን ጉባዔው ላይ በግልጽም ይሁን በስውር ሳይገኙ መተቸትና መንቀፍ ራስን ከግምት ውስጥ ይጥላል፡፡ ለነገሩ ሰካራም ያለበት ቤትና ባዶ በርሚል መጮኸ ያበዛሉ፡፡ ብዙ ጽሁፎችን ተመልክቼአለሁ፡፡ አንብቤአለሁም ከርዕዬተ ዓለመኞቹ ርዕዬተ ዓለመኞ ነህ ከማርክሲስቶቹ ማርክሲስት ነህ ፣ ከተቃዋሚዎቹም ተቃዋሚ ነህ በጣም ደግሞ የሚገርመው ከመንፈሳዊዎቹ መንፈሳዊ ነህ እንዲህ ስልህ ግን በፀጋ አይቼ አይደለም፡፡ የምትጽፋቸውን ጽሁፎች አንብቤ ነው፡፡ እንደ አኔ አሁን ሳይህ ግን ተራ ጋዜጠኛ ነህ ይህን ያልኩበት ምክንያት 1ኛ ሕዝቡ ውስጥ ያለውን ህይወት ችግርና መከራ አጠቃላይ የሆነውን የክፉ መንፈስ ጉዳት ምን ያህል ወገኖች እንደተሰቃዩ ለመረዳት በጎ ህሊና የለህም በ2ኛ ደረጃ አንተ አስተምረዋለሁ ብለህ በወንጌል የምትሰብከው ሰይጣን ከአንተ እውቀት በላይ አልፎ እንደሄደ መረጃው የለህም ስለዚህ መረጃ በሌለህ ነገር ላይ የፃፍከው ነገር ሁሉ ባዶነትህን ያሳይብሀል፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠው ለመሆኑ ለህዝብ ወይም ለምዕመናን ችግር መፍትሔ በመስጠት ነው ወይስ ለብቻ ተሰውሮ በዋሻ ውስጥ እድሜ በመጨረስ ነው፡፡ክርስቶስ እኮ ያለው ወደ አለም ሂዱ ነው፡፡ ይህን የወንጌል ቃል ወዴት አደረስከው የዮሐንስ ወንጌል 7 ፡- 4 ላይ ለጌታ እንኳን ሐዋርያት ያሉትን ከዚህ ወንጌል ተረዳ፡፡ አሁንም አንተ እውነታውን ለማወቅና ለመረዳት ጉባዔው በሚካሄድበት ቤተክርስቲያን መጥተህ ብትከታተልም ብታስተምርም መላከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በፍፁም ፈቃደኛ እና ደስተኛ መሆናቸውን እያረጋገጥኩልህ ምናልባት አንተ ገና ስለሆንክ መንፈሳዊ ውጊያ ስላልገባ በውስጥህም ያለው ክፉ የሰይጣን መንፈስ ወደ ጉባዔው እና ወደ ወንጌል እውነት እንድትመጣ ካልፈቀደልህ እኔ የምመክርህ በመምህሩ የተፃፉትን በማለዳ መያዝ ቁጥር 1 እና 2 ትን በደንብ አንብብ የመምህሩን የአገልግሎት ሁኔታ እና ትምህርት የሚያሳየውን በቪሲዲ ከቁጥር 1 እስከ 36 ያለውን ካሴት ተመልከት፡፡ ወንድሜ ከተዋህዶ እውነት ከወንጌልና ከዓይናችን በላይ ማንንም አስመሳይ ያለፀጋ እግዚአብሔር የሚጮህ የወንጌል አስተማሪነኝ ባይና ሁለገብ ተራ መልስ ሰጭን አንቀበልም እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይስጥህ ፀጋ እግዚአብሔር ያላቸውን የቤተክርስቲያን አባቶች አያሳጣን አሜን ፡፡
  ከነቃጥበብ ዘወንጌል

  ReplyDelete
 2. አንተ አባሰላማ ደግሞ መንፈስ እስር ቤት በመግባት ይለቃል ብለህ ነው እንዴ ?ደግሞ እስርቤት ገብቶ ከሚበክል በውጭው የእግዚአብሔር ክንድ ተገልጦ እስከሚንደው መጸለይ እንጂ! ምን ይደረግ ነብዩ ኤልያስ ከሰማይ እሳት ወርዶ እንደበላው መሰዊያ የአባ ግርማንም መሰዊያ እስከሚበላው ሁሉ በጸሎት በክርስቶስ ስም እየተቃወሙ መጸለይ ዋናው ነገር ነው? ሌላው እንደ ነቢዩ ኤልያስ አባግርማን <ይህ የምትሰራው ሥራ ከአጋንንት ስለሆነ ከአጋንት መሆኑን እንድታውቅ በዚህ ሕዝብ ፊት አጋንንቱ ከአንተ ውስጥ በዚህ ሰዓት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መሬት ላይ ዘርሮህ እንዲወጣ እጸልያለሁ!በማለት የሚወራረድ ሰው እንዲያስነሳልን እንማልድ ወደጌታችችን!ያነበብነውን በልቦናችን ያሳድርልን!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለመምህር ሴጣንም እኮ መሰከረ አልቻልኩህም የተሰጠህ ከላይ ነው አልላቸው አባክህ ኒቆዲሞስ ጎራ በልና አንድ ቀን በጸሎትህ በእሳት አስበላልን የመምህርን የጸጋ ስጦታ የሄንን የትእቢት ንግግር የጥሩ መንፈስ ስላልሆነ በእግዚያብሄር ስም ተቃጠል ብለው የገላገሉህ ነበር

   Delete
 3. ለወንድማችን በእውነቱ እውነተኛው መንገድ ምን ይመስላል??? አዎ ምን አልባት ሰዎች በራስቸው ጥብብ የሚያወሩትን የጽድቅ ሥራ ብለህ ልትናገር ትችላለህ። ነገር ግን እውነት በስብሰባ በመጽሀፍ በመጻፍ በብዙ በመጻፍ አይደለም። በመጀመሪያ የምናመልከውን አምላካችንን እናውቀዋለን??? ራስን እንድ ጻድቅ የእግዚአብሔርን ቃል አዋቂ አድርጎ ማቅረብ ታላቅ ስህተት ነው። ሁሉም በእግዚአብሔር ሥም የሚነግዱ የራሳቸውን ጥቅም ከጸሐፊው ጀምሮ እስከ ተጠቃሹ ሰው ድረስ ያስታውቃል። እስኪ አንተ የእግዚአብሔር ቃል አውቃልሁ የምትል ዲያቆንም ወይም ቄስ የሆንክ ወይም ጳጳስ አንድ ሰው ካለበት ክፉ መንፈስ በእግዚአብሔር ሥም እንዲፈውስ አድርገሃል???? አይመስለኝም ነገር ግን በቅናት ላይ በዝሙት ላይ በግብዝነት ላይ በሴሰኝነት ላይ በተንኮል የተወሳሰበ ትምህርት ይዘህ እግዚአብሔርን ያውቀን እየመሰላችሁ ነገር ግን ሰዎችን ወደ ክፉ ሞት የምትመሩ የሐሰት እረኞች ናችሁ። እንዲሁም በእግዚአብሔር ሥም የምንነግድ ብዙዎች በቤተ ክርስትያናችን ሞልተዋል። በዚህም ከእነርሱ ላይ ያለው ክፉ የሰይጣን መንፈስ በመቅናቱ ምክንያት ለሰው ጠበቃ ነን ብለው ይቆማሉ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰዎች በዚህ በእርኩስ መንፈስ ሕዝባችን እንዲጠመድ ለገንዘብ ለሰይጣን የሚሰሩ ብዙ ደብተራዎች ከእናንተ ነው የሚወጣው፡፡ ሰዎች ጠላታቸውን ሊከላከሉ የሚችሉበትን የእግዚአብሔር የመንፈስ ሰይፍ የእግዚአብሔርን ቃል ስለማታስተምሩ ሁሉም የጠላት ምርኮ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ ምነው ሰው በመዳኑ በመፈወሱ ተንገበገባችሁ????? ወይስ ለመዳን የሚፈልገው ሰው ወደ እናንተ ወደ ጻድቆች ጋር እንዲመጣ አድራሻችሁን ስጡን። በዚያም እንመጣለን። አለበለዚያ የቅናት መንፈስ የተጫናችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይሆን በቀኖና ታሪክ ያበዳችሁ የእግዚኦአብሔርን ማንነት ያልገባችሁ ዝም ብላችሁ በመጽሀፍ በወሬ እራሳችሁን ታላቅ ያደርጋችሁ እንናተ ለቤተ ክርስትያናችን ጠላቶች ናችሁ። በእናተ ምክንያት ብዙ ሰው ሞቷል። ስለዚህ አሁንም ሰው እንደ ዝንብ እንዲሞትና ከእግዚአብሔር ቃል እንዲወጣ የምታደርጉ ለራሳችሁ ጥቅም የቆማችሁ ሁሉ እባካችሁ ወደ ኋላ ሂዱ የሐስት አባታችሁ ጋር ኑሩ። ሰው ወደ መረጠው ወደ መሰለው ይሂዲበት ተውት!!!!

  ReplyDelete
 4. ማህበረ ቅዱሳን አባላት ሰሞኑን በየፈስ ቡክ ተሀድሶ EBS TV ላይ የእግዚአብሔር ቃል አስተላለፉ በማለት ያጨናንቁ ነበር።እዉነት የማይዋጥለት የሰይጣን ማህበር አልሳካለት ስል። ሌላ መንገድ ጀምረዋል። የማቅ ማህበር እየደከመና ስለመጣና ሁሉም ህዝበ ከርስቲያን ስለነቃ ሰሞኑ በዳንኤል ክብረት ፊት ሯጭነት መምህር ግርማን መዋጋት ጅምሮዋል፡፤ ምከንያቱም ብዙ ተከታይ ስላላቸውና እዉነቱ ስለማይወጥለት። ዳንኤል እራሱ ብመረምር መልካም ነው። በመጀመሪያ ደራጃ ጎጃም በነበረበት ወቅት በቀኝ ትከሻው ላይ ያስቀበረውን መተት ማስወጣት አለበት። ስላልተሳካለት ጦርነት አውጀዋል። በመምህር ግርማ አድሮ ድንቅ ሥራ እየሰራ ያለው ጌታ መንፈስ ቅዱስ ነው። እኛ ሰዎችን በመንፈሳዊ ህይወታቸው ልንመረምራቸውና ወሳኔ መስጠት አንችልም። ሥራው በራሱ በግዜው ይገልጠዋል። በአሁን ሰዓት አኝህ ብዙዎችን ከአጋንንት እስራት በእግዚአብሔር ሃይል እየፈወሱ ናቸው።እግዚአብሔር በዘመናት የራሱ የሆኑትን እውነተኞችን ያስነሳል።አዋቅዉ ልዑል እግዝአብሔር ብቻ ነው። በእኝህ ሰው እጅ እግዝአብሄር መንፈስ ቅዱስ ተአምራቱን እየገለጸ ነው:፡ ይልቁን ማቅ ብዙዎችን ካህናት በጥንቆላ ያሰማራቸው ሞልተዋል። ከእግዚአብሔር ስላልሆኑ ስራቸው በጨለማ አንጅ በአደባባይ አይደለም። ዳንኤል እውቀት ሳይኖርው እወቀት አለኝ እያለ በማያገባው ለመታወቅና ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የምሰራ ሰው ነው። በቀደመው ዘመንም ጌታችን ኢየሱስ በዙዎችን ከአጋንት እስራት ነጻ ስያወጣቸው ካህናቱ ይቃወሙት ነው። ምንም አዲስ ነገር የለም። ካህናቱ ጌታ የሰቀሉት ናቸው። ዛሬም የእረሱን ቤተ መቅደስ እያወኩና የንግድ ቤት ያደረጉተም አነርሱ ናቸው። የፈርሳዊአን እርሾ ዛሬም በምድራችን ላይ አለ።የታመሙት ሰዎች ከአጋንንት እሳራት በመፈታታቸው መቃወም መንፈሳዊነት አያሰኝም። ሁሉንም በሰዓቱ የሰራዊት ጌታ ይገልጠዋል። ማቅ አበላት ብንጫጩም እነሆ የእግዚአብሔርን እውነተኛ መንገድ ልሰዉሩት አይችሉም። ማቆች አርፋችሁ ንግዳችሁን ብትነገዱ ይሻላችዋል። ተሃድሶ ማሸነፍ ስያቅታችሁ አሁን ደግሞ የማይትችሉትን መንገድ ጀምራችዋል። አያወጣም ትርፉ ክሳራ ነው። መላው አለም እውነቱ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስራ እያየ ስለሆነ መደበቅ ከቶ አይቻላችሁም። መምህር ግርማ ለገንዘብ ሳይሆን በጌታ ጸጋ ስጦታ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ የአግዚአብሐርን ማዳን እያሳዩ ናቸው። ለመሆኑ ማቆች በebs Tv ላይ የራሰችሁን መርሃ ግብር እንድታስተላልፉ ማን ፈቀደላችሁ? ድሞክራስ ለሁሉም ይሰራል። እርግጠኛ ነኝ ebs tv በማቅ እንደማይመራነ ነጸ የሆነ ድርጅት ነው።እግዚአብሔር የማንንም እርዳታ እገዛ አይሻም። በሰው አትፍረድ ይፈረድብሓልና ።በሰው የምትፈርድ አንተ ማነህ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጀመሪያ የአማርኛ ፊደላትንና አጻጻፋቸውን አጥርተህ ተማርና ለመጻፍ ሞክር፤ ካለበለዚያ የምትጽፈው ለሰው አይገባም፡፡ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲያ ይሆናል፡፡

   Delete
  2. You never accept the realty, It is not about the amahric misspelled. Memeher Grima is doing through the Holy Spirit.

   Delete
  3. ya mejemeriya elayk ley yalutn menafst asweta zen u will talk abt memhir medre tragi hula

   Delete
 5. We do not need your witness. You are like the devil that fools people by Memhir Girma. How can a protestant defend orthodox church? Your witness is not different from witness by Devil

  ReplyDelete
 6. Memeher grim is doing through Holy Spirit . A lot of people are healing from Satan. MK members are know disappointed on Holy God. Because Holy Spirit giving power to Grima. Wow wow wow thanks Lord for healing your people from evil. We all truth Orthodox Tewahedo Christan standing against of MK. No more spot for MK in our church. Go hell MK

  ReplyDelete
 7. Anonymous said...
  መምህር ግርማ በእዉነት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሰጣቸው ፃጋ በጌታችን በኢየሱስ እና ቅዱሳን ስም አጋንንትንና ሰራዊቱን በመገሰጸ በገሃድ እየፈወሱ ናቸው። እግዚአብሔር ድንቅ ስራውን በእኝህ ሰው አድሮ በአደባባይ እየፈወሰ ነው። ታድ ዳንኤል የብዙዎች ከዲያብሎስ እሰረኞች በእግዚአብሄርና ቅዱሳን ስም መውጣት ቅር አሰኘው? በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ተጠቅሰው እንደምገኘው ሁለቱ አይነ ስውሮችን በኢያርኮ መንገድ ላይ ተቀምጠው የሚለምኑትን እንደት ፈውሳቸው ማቴ 20 ቁ 20 በደንብ ተቀምጠዋል።ጌታችንን የሚከተሉት ሰዎች አትጩሁ ብለው ስከለክሉዋቸው አይነ ስዉራኑ ለመዳን ስሉ እጅግ አብዝተው የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆን ማረን እያሉ ጩሁ በመጨረሻም መዳን አገኙ።ሰዎች አንኳን ብከለክሉዋቸውም እነርሱ ግን አብዝተው ወደ አምላካቸው በመጮህ መዳን አግኝተዋል።ዳንኤልም ዛሬ ክፉ መንፈስ ያደረበት ሰው በመሆን። ሰዎችን በህመማቸው ለማን ዳኑ በማለት መቅናት እጅግ አሳዛኝ ዜና ነው። እግዚአብሔር በውደደው መንገድ ህዝቦቹን ያድናቸዋል። ማንም የልዑል እግዚአብሔር ስራ ለመረምረው አይችልም። ብቃት ያለቸው አባቶችም እንኳን ተመራምረው ልደርሱበት አልቻልም።ነቢየ እግዚአብሔር እንዳለም የእርሱ ሥራ ድንቀ ነው በማለት አልፎታል።ሁሉም ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት ከሁሉ ይበልጣል።You don't have any ability to judge someone. You must stop your mouth and do your personal business, God never never never ! ask anybody to help him for what is doing. ወገኖቼ እንደ በአለ አእምሮ ብናስብ መልከም ነው። በእኔ ዳንኤል መሰሎች የቅድስት ቤተ ክረስትያናችን አባላት እየሸሹ ናቸው። አመጸኞች በዝተዉባታልና። መልአከ መንክራት መምህር ግርማን እግዚአብሔር አምላካችን ይጠብቅል። እውነተኛ አገልጋይ ካልሆኑ እኩ እግዚአብሔር በግዜውና በሰዓቱ መልስ ይሰጣል። በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ያለአቅማችን ባንገባ ትልቅ ጥበብና አዋቅነት ነው።1. በገሃድ በህዝብ ፊት ክፉ መንፈስን በእግዚአብሔርና በቅዱሳን ስም እየገሰጹ በብዙ ሽህዎች የምቆጠሩት ህመምተኞችን እየፈሱ ናቸው።2. ቅድስት ቤተ ከርስቲያን በየስፍራው እንድታነጽ እያገዙ ናቸው።3. ታላቅ የወንጌል ትምህርት በየስፍራው እያስተማሩ ከመጥፎ አምልኮች ሰዎች እንድመለሱ እያደረጉ ናቸው። 4. እለት እለት ሥለ በክፉ መንፈስ ስለ ታሰሩ ሰዎች ከህመማቸው እዚአብሔር እንደያደናቸውና ለመላው ሰዉ ልጅ ይጸልአሉ።

  ReplyDelete
 8. one day the truth it will come out
  Thank you to you and Deyacon Daneal Keberet
  ayzohe berta becouse this a lot of people reyalze and rember bahatwi Gebere meskel :)

  ReplyDelete
  Replies
  1. DEDEB Daneal Kebrete & Mahibere kidesan mrzoh Ywengel Telatoce Rejim edme LEMEMEHR GIRMA WENDMU!!!!!!

   Delete
  2. Memeher Girma Wondimu VCD 36 A

   Delete
 9. መርበበተ ሰለሞን የጥንቁልና መጽሐፍ ኣይደለም አንናንተ መጀመሪ ግእዝ ተማሩ ዳንኤል ደግሞ መጀመሪያ ቅዳሲ ተማር

  ReplyDelete
 10. ዳንኤል በመጀመሪያ ቅዳሴ ተማር አሳዳጅ ያለአንተ አዋቂ የለም ።እንደውም ፀበል ያስፈልግሀል።መ ምህር ግርማ ደግሞ ምን ያድርጉህ

  ReplyDelete
 11. በእውነት እናንተ መምህርን የምታወግዙ ሰዎች ሲጀመር ምንያህል ሰው ከስቃይ እንደሚድን ብታዪ እውነት ይህንን ሁሉ እርግማን ባልፃፋችሁ ነበር።
  ወይ በኛ ስላልደ ረሰ ምን አገባን እያላችሁ ለመራቀቅ (አውቃለሁ)
  ለማለት ነው ። አረባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ እስቲ መ ምህር ጋ ባትሕሄዱ እንኮአን እስቲ ካሴቶቹን እዩ ።ደሞ ካሴት ሽጡ እያላችሁ ትዝብት ውስጥ አትውደቁ ሰንት ዘመን የናንተን ካሴት ስንገዛ ከርመን ምነው አሁን ኡ ኡ ኡታው? አይ ገንዘብብብብ ባካችሁ ሰድቦ ለሰዳቢ አትስጡን ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር።

  ReplyDelete
 12. መ/ር ግርማና ጓደኞቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ።አያልቅበት ተሾመን(ሬዲዮ አቢሲኒያን) ቀኝ እጅ በማድረግ ጋሻው መንግስቱ ካሜራ ማን ፌስ ቡክና አንድሮይድ አፕ ተቆጣጣሪ።ዳንኤል ለታ ዌብ ሳይት ተቆጣጣሪ በማድረግ በፈውስ ስም የሚነግድ። የአጋንንት ምስክርነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ እውነተኛ መረጃ የተወሰደበት ቦታ የለም።ስለ መ/ሩ አጋንንት መሰከሩ እንጂ መንፈስ ቅዱስ መቼ ተናገረ።በዋልድባ በጣና ደሴቶች በመላው ኢትዮጵያ ቅጠል እየበሉ ድንጋይ እየተንተራሱ በጾም በፀሎት ከዘጉ አባቶች መ/ሩ ይበልጣሉ ብላችሁ ለምታስቡ በከንቱ ጊዜአቸውን ፈጁ ትላላችሁ።በተአምር ለምታምኑ ቃልቻው የገብርኤልን የሚካኤልን የማርያምን የአቦ ሌሎችንም የፃድቃን ስም እየጠራ እርኩስ መንፈስ ወጣ ይል የለ መናፍቅስ ጋ በኢየሱስ ስም እርኩስ መንፈስ ወጣ ሽባው ዳነ አይነስውር በራ በሽተኛው ዳነ ይሉ የለ።እርኩስ መንፈስ ስለ ጮኸ ወጥቻለሁ ስላለ የታመመው ስለዳነ ለቀቀው ማለት ነው።ሰይጣን በተአምር የተመረጡትን እንኳን ያስታል ለምን ይላል መጽሐፉ።መ/ሩ ቤታቸው 8 ሲም ካርድ ሲገኝ አገልጋይ ከሆኑ ለምን ለሚፈልጋቸው ሰው አንድ ቁጥር ይሰጣሉ እሱም የማይሰራ።ለመፈወስ መንፈሱ ታስሯል ማስረጃችሁን ስታመጡ ይሸኝላችኋል።እንደዚህ የሚል በቤተክርስቲያናችን አባት አለ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥስ አለ።መ/ሩ ስለ ብሉይ ኪዳን ከካባላ(ዞሀር)የተቀዳ ትምህርት ያስተምራሉ ስለ አዲስ ኪዳን እውቀት ተላቸውም።የአክብሮት ስግደት ይገባኛል ብለው ሲሰገድላቸው እናያለን። ራሳቸውን እንደ አገልጋይ ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን በቦዲ ጋርድ ሰው እንዳይነካቸው ሲሄዱ በፈርስት ክላስ በመጓዛቸው እዲታወቅላቸው ተቀርጾ የሚተላለፍ የሚደረግላቸውን አቀባበል የአበባ ስጦታዎች ይኸውላችሁ ከጳጳሳት ከፓትሪያርኩ በላይ ነኝ ብለው። አሳዪን አባቶችን ግን ሁል ጊዜ ይተቻሉ።አንድ ወቅት በርኩስ መንፈስ ባደረባቸው መናፍቅ የሆኑትን ሲያስደበድቡ አየን።በእውን ጠላትህን ውደድ ይላል እነጂ ደብድብ ይላል።የመናፍቅ መንፈስ እያሉ ሲጠሩ ይሰማ ነበር በኋላ መናፍቆቹ በሃይማኖታችን መጣችሁ ብለው ሲሞግቷቸው መጥራቱን አቆሙ።ታዲያ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት በድርድር ያቆማል።የመ/ሩ ደጋፊ ነን ጻድቅ ናቸው ለምትሉ መልስ ስጡኝ።ትዳራቸውን ፈተው የሌላው ርኩስ መንፈስ ተጫወተብህ ማለት ምን ማለት ነው። ከድቁና እንዴት መስቀል ይዞ ማሳለም እንጀመሩ ክህነት ስልጣን መቼና የት አገኙ። ለምን ታሪካቸውን ደብቀው መቅረብ ፈለጉ።

  ReplyDelete
 13. m/r girma wendimu yezemenachin sileezigiabiheri yemibesekiru hawariya nachewi . Digili mariyam : E/r hoyi le abatachin fitihi siti.

  ReplyDelete
 14. እኔ መናገር ምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም አባታችን ግርማ በእሱ ቃል በድንግል ማርያም ቃል እና በመላክቶቹ ቃል እየተናገሩ ከፈወሱ ለምን አስማተኛ ይባላሉ ለነገሩ አልፈርድብህም እግዛብሄር እንካን ተገልጦ ሲሰብክ ተፍተውበት አሽማጠውበት ነበር ስለዚህ አንተ እንካን ብዙ ብትናገር ተሰሚ የለህም ምክንያት ምትለው ሁሉ ግራ ነው ደግሞ ፈራጅ ሰው አይደለም እግዛብሄር እንጂ ሁሉ የራሱ የሆነ ፀጋ አለው ስለዚህ ምንም አይግረምህ ይሄ ማለት ከተሰጠን ፀጋ ትንሹ ነው እሱ እራሱ በቃሉ ምን እንዳለ ታቃለህ ቅንጣት ያህል እንካን እምነት ቢኖራቹህ ይህን ተራራ ተነስተህ ወዲያ ሂድ ብትሉት ይሄዳል ስለዚህ መምህር ግርማ ደግሞ በተሰጣቸው ፀጋ መሰረት እርኩሳን መናፍስትን እያሳደዱ ወደ ሲኦል እየላኩ ስለዚህ ይሄ የግዛብሄር ፀጋ ነው ማለት ነው ስለዚህ እባካችሁ ያለ ስማቸው ስም አትስጡ እናተን ማን ፈራጅ አረጋቹህ እሱ እግዛብሄር እንጂ ሁሉ ለሰራው ስራ ከእግዛብሄር የእጁን ያገኛል ስለዚህ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከቻልክ ዝም በል ፈራጅ ለመሆን አትሁን ምክንያቱም ካንተ በፊት እግዛብሄር ስለ ሁሉም ነገር ያቃል አለማችን እንካን ኢሉሚናቲን ተቀብላ ልክ እንደ እምነት አድርጋ ወደ እርኩሰት አለም የሆሞ ሴክሻል እንካን ፈቅዳ የለ እንዴ በነፃነት የምትራመደው ስለዚህ መምህር ግርማ ደግሞ ይህን ትውልድ ወደ መጥፎ ነገር እንዳይሄድ እየቀረፁት ያሉት እውነተኛ አባት ናቸው ስለዚህ ለሳቸው እረጅም እድሜ ይስጥልን በጤና ያቆይልን እንደነሱ አባት ነው ያጣነው ሌሎችንማ አየናቸው ወደ መጥፎ ነገር ሲመሩን ስለዚህ አባ ግርማ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል እሩቅ ሳትሄድ በኔ ማየት ትችላለህ ብዙ ነገር ተምሬያለው ከመጥፎ ነገርም ተቆጥቤያለው እንደ ጋደኞቼም አጫሽ አይደለሁም ዱርዬም አይደለሁም በጣም ስነ ስርአት ያለኝ ነኝ ይሄንንም የተገነዘብኩት የሳቸውን ቪዲዮ ካየሁ በሃላ ነው እግዛብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ አሜን ፤፤፤፤፤፤፤

  ReplyDelete
 15. ማቴዎስ 12
  25 ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።

  26 ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?

  27 እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።

  28 እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።

  ከቃሉ እንደምንረዳው፣ አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን፣ አጋንንት በአጋንንት መውጣት እንደማይችሉ ነው። ዛሬ ሃብተ ፈውስ ያላቸው አባቶች የሚከሰሱበት መንገድ ጌታ ኢየሱስ እንደተከሰሰበት አይነት ነው። ከሳሾቹ እንደ ፈሪሳውያን ሲከሱ፣ እኛ ደግሞ እንደ ጌታ ቃል እንምልስላቸዋለን። በቅናት መንፈስ ተሞልተው፣ የሰውን ስሕተት ብቻ ለቅሞ ማውጣት አስተዋይነት የሚመስላቸው ሞኞች ናቸው። ደግሞ መናፍቃኑ የተደበደቡት በራሳቸው ድፍረት እንጂ፣ መምህሩ አዘው አይደለም። በመንፈስ የተሞላን ፓስተሮች ነን፤ በ ኢየሱስ ስም አጋንንትን እናወጣለን ብለው ራሳቸው ናቸው ያለ አቅማቸው አጋንንቱን የተዳፈሩት።

  13 አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
  14 የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
  15 ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
  16 ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
  17 ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
  18 አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።

  በሃዋርያት ስራ 19 ላይ መረዳት እንደምንችለው፣ ያለ አቅማቸው በኢየሱስ ስም ኣጋንንት እናወጣለን ያሉ ሰዎች፣ ኣጋንንት ባደረባቸው ሰዎች መደብደባቸው ተጽፉኣል። ታድያ እነዚህን ሰዎች ሃዋርያት ኣስደበደቡኣቸው ልንል ነው?
  አይደለም፣ እንደዚህም ሁሉ መምህር ግርማ መናፍቃንን አስደበደቡ ብለን ጭፍን ፍርድ መፍረድ የለብንም። እስከ ዛሬ መምህር ግርማ በማስተማራቸው፣ በማጥመቃቸው፣ አጋንንትን በማውጣታቸው እስቲ ማን ተጎዳ? የተጎዱማ አሉ፥ መተተኞች፣ ኣስማተኞች እና መናፍቃን። ስለዚህ መምህር ግርማ ስራ ያቁሙ የሚል ሰው ሁሉ ከተጎዱት ወገን የሆነ ነው። የዳኑትማ የእግዚኣብሄርን ስራ እያደነቁ ይኖራሉ።  ReplyDelete