Monday, October 12, 2015

በወንጌል እንቅስቃሴ ላይ ያረጀ ግን አዲስ የተባለ ዘመቻ ለምን ተከፈተ? የከፈተውስ ማነው? Read in PDF
የወንጌል እንቅስቃሴን ለማዳፈን ከተቻለም ለማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳን ያላደረገው ጥረት የለም፡፡ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም፡፡ ያላደራጀው ቡድን የለም፡፡ ያልከፈተው ጸረ ወንጌል ዘመቻ የለም፡፡ ያላሰማራው ሰላይ የለም፡፡ ያልመደበው በጀት የለም፡፡ ያላስጨበጠው ግንዛቤ የለም፡፡ ያላሰባሰበው ገንዘብ የለም፡፡ የወንጌሉን እንቅስቃሴ ጭራቅ አስመስሎ በመሳል ከተራ ምእመን እስከ ጳጳስ ያላወናበደው የኅብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ ብቻ ምን ቅጡ… ነገር ግን የወንጌል እንቅስቃሴ እየተስፋፋና ብዙዎችን እየነካ መቀጣጠሉን ቀጥሏል፡፡ ወንጌል የእግዚአብሔር ክቡር ሐሣብ በመሆኑ ማንም ሊያጠፋው አይችልም፤ እንዲያውም ሲነኩት ይብሳል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ከዚህ ቀደም ራሱን “ጸረ ተሃድሶ ህብረት” ብሎ ሲንቀሳቀስ የነበረው “የቱሪስት ቡድን” እየተባለ ከሚጠራው ስብስብ መካከል አንዳንዶቹን በማካተት እንቅስቃሴዎችን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ይህ ቡድን በማቅ የተደራጀ ቡድን እንደ ሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም ማቅ ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ ሃይማኖቱን በኃይል እንጂ በስብከት የማያስፋፋ በመሆኑ፣ ሃይማኖቱን ለማስፋፋት ሰባክያንን ሳይሆን ሁከት ፈጣሪዎችን፣ በየቤተ ክርስቲያኑ ጠብ አጫሪዎችን፣ ዐውደ ምሕረት ላይ ወጥተው ድምፅ ማጉያ ነጣቂዎችን፣ ከስብከት በኋላ ጠብቀው ሰባክያነ ወንጌልን ለመደብደብ የሚቃጡትን ቅጥረኞችን ነው ያደራጀው፡፡ ከመድረክ በስተጀርባ እንዲህ ዓይነት ቡድኖችን አደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ሃይማኖታዊ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ ከሃማኖተኛነቱ ይልቅ ሌላ አጀንዳ ያለው ወይም ፖለቲከኛ ነው ቢባል ምንም ስሕተት የለበትም እውነት ነው፡፡
 ከላይ የተጠቀሰው የቱሪስቱ ቡድን ከዚህ ቀደም ፋንቱ ወልዴ አምጥታ ካስረከበችው 2ሺህ ዶላር በነፍስ ወከፍ ቢያንስ እስከ 5 መቶ ብር ይደርሳቸው ነበር፡፡ ከጠዋት እስከ ማታ ቱሪስት ሆቴል ተሰብስበው ማታ ለስብከት ሲወጡ በሚመቻችላቸው አውደ ምህረት በተለይ እንደ ዲያቆን መኮንን ደስታ (ጋሽ ጀንበሬ) በአዲሱ ሚካኤል፣ ዲያቆን ብሩክ በማርቆስ ቤተክርስቲያን፣ ተባራሪዎቹ ጰውሎስና ዳንኤል ባለፉት 3 ዓመታት በህዝቡ ሲቀልዱበት በወንጌል እንዳያርፍ ሲያባክኑት ኖረዋል፡፡ ከዚህ ቡድን የቅድስት ማርያም ሰንበት ተማሪ ዲያቆን ሱራፌል ይህን የሻይ ቤት ቡድን ሲመራ፣ ሲነዳ፣ ሲያሰማራ፣ የስብከት ርዕስ  (የስድብ ርእስ) ሲሰጥ ሠንብቶ ይልቁንም ዘማሪት ፋንቱ የምትልከውን ብር ሲያከፋፍል ከርሞ አሜሪካ ገብቷል፡፡ በመድረክ ስድብ የተካነው ዳንኤል ግርማም ከህልም እስከ እውን ሲያቃዠው የኖረው የተሃድሶ ነገር በተገባለት ተስፋ መሠረት ሚስት ከአሜሪካ መጥቶለት ከቦዘኔ ጉደኞቹ ከፀረ-ተሃድሶ ህብረት ተደብቆ ጋብቻ ፈፅሞ ወደ አሜሪካ ሄዷል፡፡
ቡድኑ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው የቱሪስት ሆቴል መዘጋትን ተከትሎ በሠራነው ዘገባ ቡድኑ ተደናግጦ እስከ አሁን በአንድነት ልብ ለልብ ተግባብቶ ሲኖር አላየነውም፡፡ በዚህ መካከል ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ወደ ልብዋ በመመለስ የሠራችው ስህተት እንደሆነ ገብቶአት በተለይ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሣለኝ በሄደበት ጉባኤ ይዞአት በመሄድ ያልተቋረጠ ወይም ፋታ ያጣ አገልግሎት አገልግላ ተመልሣለች፡፡ የቱሪስቱ ቡድን የምታመጣውን ብር እንጂ አንድም ቀን አገልግዪ ባለማለታቸው ማንነታቸውን በደንብ ተገንዝባለች፡፡ ቡድኑም የእስዋን ስም እስከ አሁን ተግተው እያጠፉ አሉ፡፡
ይህን ቡድን የበለጠ እስከ አሁን ተስፋ ያስቆረጠው ዳንኤል ክብረት በማህበረ ቅዱሳን ላይ በጻፈው ጽሑፍ ማህበሩ እነ አባ ሠረቀን፣ እነመ/ሀዲስ በጋሻውን ተሃድሶ የሚላቸው ማህበሩን ስለነኩ ብቻ ነው ብሎ የመሰከረው ቤተክርስቲያን ውስጥ ማህበሩን ሳይነኩ የፈለጉትን መሆን እንደሚቻልና ማህበሩን ከነኩ ግን የተለያየ ስም እንደሚሰጥ ጠቁሟል፡፡ እንግዲህ ተሃድሶ የእግዚአብሔር ሐሳብ እንጂ የሰው እንዳልሆነ ያልተገነዘበው ማቅም ሆነ ይህ ቡድን ማቅ በውስጡ ያለውን ልዩነት አምቆ ይዞ ይህ የሚያሳዝን ቡድን ልዩነቱን በየሜዳው ሲካሰስ እስከአሁን አለ፡፡ ዘመድኩን በቀለ ይህን ቡድን “የ13 ሺህ ብር መጠጥ ጠጥቶ የሚሰክር የአራት ኪሎ የቱሪስት ቡድን በእንዲህ ሁኔታ ነወይ ተሃድሶን የሚዋጋው?” ብሎ በመናገር ቋንቋቸው መደበላለቁን ገሃድ አወጣው፡፡
እንግዲህ ከዘበነ እስከ ምህረተ አብ ከጳውሎስ እስከ ዳንኤል ግርማ ያለው ተረት ተረት አሁን ቦታውን ለወንጌል እየለቀቀ ባለበት በዚህ ወቅት የቱሪስቱ ቡድን ርዝራዥ ከበስተጀርባ ለጥቅምቱ ሲኖዶስ ሌላ የሁከት አጀንዳ ተቀርጾለት ሁለተኛው ዙር ፀረ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ለማድረግ 4 ኪሎ የሚገኘው በኪራይ ቤቶች አዳራሽ ፀረ ተሃድሶ ሰባክንያና ዘማሪያን በደረጀ ነጋሽ በወይንዬ መሪነት በቅርቡ ተሰብስበው ነበር፡፡ በእለቱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዚህ በፊት ለማህበሩ የሰጠውን ማሳሰቢያ እዚህም ደግሞታል፡፡ ተሃድሶ እያልን ሰዎችን አናንሳ ተሃድሶ ባመጣው ኢሹ ብቻ እንወያይ ብሎአል፡፡ የዲያቆን ዳንኤልን ሀሳብ ሁሉም ቢጋራው ጥሩ ነው፡፡
ይህ አዲስ ለመቋቋም በእቅድ ላይ ያለው በደረጀ ነጋሽ የተጠራው ስብስብ አንድ የዘነጋው ነገር አለ፡፡ እርሱም ቤተክርስቲያን ያለተሀድሶ ያልኖረች መሆኗ ነው፡፡ በቅርቡ ለሦስት ተከታታይ ቅዳሜዎች ስለ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ በማህበረ ቅዱሳን ህንፃ ላይ ዶክተር ውዱ ጣፈጠ ባቀረቡት ጥናት፣ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተሃድሶ እዚህ ደረጃ ላይ አልደረሰችም፡፡ በየጊዜው ተሃድሶ አድርጋለች፡፡ የፈለገችውን ተቀብላለች ያልፈለገችውን ትታለች” ብለዋል፡፡ አክለውም አፄ ዘርያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን በግፍ ገድሎአል ወዘተ… ብለዋል፡፡ እነ ደረጀም ሆኖ ያሰማራቸው ማቅ ይህን አልሰሙ ይሆን?
ደረጄ ነጋሽ የቅርስ ጠባቂ ነኝ ብሎ ከሰሎሞን ቶልቻ ጋር በጋዜጣ ተሰዳድቦ በዚያውም በሰሜን ሸዋ ሲያጭበረብር አቡነ ኤፍሬም እውቅና ነፍገውታል፣ ማህበሩም በጠቅላይ ቤተክህነት ተዘግቶአል፡፡ ስለዚህ አሁን ያዋጣል ገቢም ያስገኛል ብሎ በፀረ ተሀድሶ እንቅስቃሴ ብቅ ማለቱ ለምን ዓላማ እንደሆነ ተነቅቶአል፤ ቢሆንም ደረጄ ነጋሽ ከዚህ ይልቅ በያዘው የፀረ ግብረ ሰዶም አቋሙ ቢቀጥል ይሻላል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንዱ አሳሳቢው ጉዳይ የግብረ ሰዶማውያን መበራከት ነው፡፡ ተሃድሶማ የምድራችን ሁለንተናዊ ፈውስ ነው፡፡
ሳሚ (የዘበነ ለማ ሞንታርቦና ካሴት አዟሪ) ፌስቡኩ ላይ “በተሃድሶ ላይ እንዝመት” ብሏል፡፡ ዳንኤል ክብረት ግን በምስረታ ዝግጅቱ ላይ እንደተናገረው “ራስህን ማነፅ እንጂ ለውጊያ መሰብሰብ የለብንም፣ የሆኑ ሰዎችን ደግፈን ወይም ተቃውመን አይደለም መሰብሰብ ያለብን” ነው ያለው፡፡ ከዚህ ቀደም ራሱን ፀረ ተሀድሶ ኅብረት ብሎ ሲጠራ ይህ ስብስብ ሁለት ጊዜ በተለያየ ቦታ ተሰብስቦ አሁን በሶስተኛው የምሥረታ ጉባኤውን አድርጓል፡፡ አዲስ ነገር ያመጣ ይመስል ስያሜውን በመለወጥ “ፍኖተ ዘተዋህዶ” ያለው ሲሆን የማህበሩ ምሥረታ አንዷ አንቀሳቃሽ ከዚህ ቀደም የጥምቀት ተመላሽ ማህበርን መሥርታ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲዘጋ የተደረገባት ፌበን ናት፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ፕሮግራም መሪው ዲ/ን ተስፋ እንዳለ ሲሆን እርሱ በየካ ሚካኤል ዙሪያ ካሉ እህቶች ገንዘብ አታሎ ወስዶ ተከሶ ታስሮ የነበረና ከመድረክ ከጠፋ የሰነበተ ቢሆንም ለዚህ ማህበር ምሥረታ ፕሮግራም መሪነቱን ተረክቦአል፡፡ ደረጀ ዘወይንዬ ለአገልጋዮች የሥልክ ጥሪ ያስተላልፍ የነበረ ሲሆን እንደሚታወቀው በሰሜን ሸዋ ወይንዬ ዘተክለሃይማኖት ለተባለው ገዳም ሲነግድ፣ በስሙም ማህበር መስርቶ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ታግዶበት የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ አሁን ባቋራጭ “ፍኖተ ዘተዋህዶ” ለመመሥረት ወደ ቤተ ክህነቱ የተጠጋው ያለ ምከንያት አይደለም፡፡
በዚህ የምሥረታ ጉባኤ ላይ በምዳንዬ ብርሃኑ የድንግል ማርያም መዝሙር ያለቀሱ አርቲስቶች ነበሩ፡፡ ለፀረ ተሃድሶ የሁለተኛው ዙር ቅስቀሳ ግብአት የሆኑ አርቲስቶች መናጆ ሆነው ቀርበዋል፤ በቤቶች ድራማ ላይ የአቶ ዘሩን ቤት የሚጠብቀው እከ በእውነተኛ ስሙ ንብረት ገላው አንዱ ነው፡፡ ንብረት ለመሆኑ ሃይማኖት እንደግለሰብ ቤት በደሞዝ በእንጀራ የሚጠበቅ ነወይ? የጠሩህ እነማን ናቸው? እውነት ቤተክርስቲያን ተሃድሶ አያፈልጋትም ወይ? አንተ እንዳልከውስ ቅዳሴ ኪነ ጥበብ ነው? ከእንደዚህ ያለው ያላዋቂ ንግግር እንድትቆጠብና መመሪያህ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሆን ነው ተሃድሶ ተብለው የተፈረጁት የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚነግሩህ፡፡
ሌላው የጉባኤው ታዳሚ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ደጋፊ አስጨፋሪ የሆነው ይድነቃቸው በቅፅል ስሙ አቸኖ ነው፡፡ እውነት እንደ እግር ኳስ በቲፎዞ የምትቆም አቅም የሌላት አይደለችም፡፡ ከስሜት በፀዳ መልኩ አላማውን ከአንድ ወገን ብቻ ብንመለከት የእነ ደረጀ ወይንዬ አላማ ማህበሩን ወደ እስቴድየም ጐትቶ በመውሰድ ደጋፊ ለመያዝ ያደረጉት እቅድ መሆኑ የተሠወረ አይደለም፡፡ ዳንኤል ክብረት በቀጥታ እርሱን ለመንካት ይሁን በሌላ ምክንያት እንደተናገረው ግን “በደጋፊ ብዛት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ዋንጫ ትበላ ነበር፡፡”
በመጨረሻ ቤተክርስቲያን በማህበረ ቅዱሳን እየተንገላታች ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት በድራፍት ቤት አዳራሽ “ፍኖተ ዘተዋህዶ” ይመስረት ብለው ለሚፎክሩት ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚሰጠውን ምላሽ የምናይ ይሆናል፡፡ እስኪዚያው ግን ዳንኤል ክብረት እንዳለው ተሐድሶ እየተባሉ በተፈረጁት ላይ ሳይሆን ተሃድሶ ባናሣው “ኢሹ” ላይ ብቻ መወየያቱ ይበጃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፀረ ተሐድሶ የሆነ ፍኖተ ዘተዋህዶ የተሰኘ ማህበር አቋቁመን ተሐድሶዎችን ከቤተ ክርሰቲያን ጠርገን እናስወጣለን በሚል እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ማንነት ብቻ ሳይሆን ከሰዎቹ በስተጀርባ ያለው ማን መሆኑን እና ለምን ይህን ጉዳይ አሁን ማንሳት እንደፈለገ ማየቱ የተሻለ ነው፡፡ ይህን አጀንዳ እያንቀሳቀሰ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ አንድና ሁለት የለውም፡፡ ከፊት ያሰለፋቸውና የቤት ሥራውን እንዲያጠናቅቁለት ተልእኮውን የተቀበሉት እነደረጀ ወይንዬ እና እነፌቨን ሌሎቹም ጀሌዎች ማን እንደላካቸው በአንድም በሌላም መንገድ እየመሰከሩ ይገኛል፡፡ እነዚሁ የማቅ ቅጥረኞች ከግሸን ማርያም ጀምሮ ተሀድሶን እናስወግዛለን የሚል ፊርማ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በግሸን ውሎአቸው እንደ ቀድሞው በየአቅጣጫው ሞንታርቦ ተክለው የፈለጉትን መናገር አልቻሉም፡፡ ከእንግሊዝ ያመጣውን ፓውንድ ለማስረከብ ጥቂት የምናገረው አለ በሚል መድረክ የጠየቀው ጳውሎስ መልክአ ስላሴም ከወጣበት ዓላማ ውጪ “ከማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራም በስተቀር በኢቢኤስ የሚተላለፉትን የቃለ ዐዋዲንና የታኦሎጎስን ፕሮግራሞች እንዳትመለከቱ” ብሎ ወርዷል፡፡ የአድማ ፊርማቸውንም በየሚያድሩበት ድንኳን ውስጥ ሲያካሂዱ በፖሊሶች ተይዟል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተያዙም የፈረሙም ነበሩ ለምሳሌ የኤሴቅ ምዝሙር ቤት ባለቤት ሲያስፈርም ተይዞ ፈርሞ ተለቋል፡፡ ይህ ግለሰብ ከዚህ በፊት በረብሻ የተያዘ ግለሰብ ነው፡፡
ደረጀ ወይንዬም በግልጽ ቋንቋ በኢቢኤስ ከሚተላለፉት ፕሮግራሞች የማህበረ ቅዱሳንን ፕሮግራም ብቻ ስሙ ሲል ተደምጧል፡፡ ለካስ አዲስ ማኅበር ማቋቋም ያስፈለገው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለማኅበረ ቅዱሳን ህልውና መከበር ነው፡፡ ከእንቅስቃሴያቸው በስተጀርባ ያለው ማቅ ለመሆኑም ትልቅ ምስክር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በደረጀ ወይንዬና በፌቨን እየተነዳ ያለው ቡድን በየደብሩ ችግር እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በብሄረ ጽጌ ማርያም መስከረም 21 ቀን መጋቤ ሐዲስ በጋሻው እንዳይሰብክ ለማድረግና ከሰበከ በኋላ ለመደብደብ የተደረገው ሙከራ የሚጠቀስ ነው፡፡ ሆኖም በጊዜው ረብሻውን ተከትሎ የፖሊስ ኃይል ወደስፍራው ደርሶ አመፁን ሲያስተባብሩ የነበሩትን በተለይ 4 ወጣቶችን ፖሊስ ይዟል፡፡ ከእነዚህ መካከል ለሌላ አመፅ ሲንቀሳቀሱ ጣቢያው በደረሰው ስም ዝርዝር ውስጥ የሦስቱን ሊያገኝ ችሏል፡፡ የሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ ኤርምያስ ከማል የተባለው ሰውም የተያዘ ሲሆን ሌሎች 8 ሰዎችም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወጥቶባቸው እየተፈለጉ ነው፡፡ በብሄረ ጽጌ ካደረጉት አንጻር በሌሎች ቦታዎች ምን ሊያደርጉ እንዳቀዱ መገመት ቀላል ነው፡፡ ይህ በማቅ የተደራጀ ቡድን ለጥቅምት 7 በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ ስብሰባ ለማድረግ ያቀደና የጠራ ሲሆን የደብሩ አለቃ ለቤተክርስቲያን ልጆች አዳራሹን እየከለከሉ እንደእነዚህ ላሉት አማፅያን የሚፈቅዱ ከሆነ ከማን ወገን እንደቆሙ የሚያሳዩበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የብሄረ ጽጌ አካባቢ ፖሊስ ህግን ለማስከበር እያደረገው ያለው ጥረት ሊመሰገን የሚገባው ነው፡፡    
እነዚህን ለአመፅ ሥራ ያደራጃቸውን ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳን አሁን እያንቀሳቀሰ ያለው ከቤተክርስቲያን ሰዎች ጋር በብዙ ስፍራ እየተጋጨ በመምጣቱና በየአቅጣጫው የተከፈተበትን ተቃውሞ አቅጣጫ ለማስለወጥ መሆኑን ማንም አይስተውም፡፡ ከዚህ ቀደም በሲኖዶስ በእርሱ ላይ የተላለፉት ውሳኔዎችን ተግባራዊ ሳያደርግና ለህገ ቤተ ክርስቲያን መገዛቱን በተግባር ሳያስመሰክር ሲኖዶስ በተሐድሶ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ይስጥልን ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም በማህበረ ቅዱሳን ከሳሽነትና የእጅ አዙር ዳኝነት ውግዘት በማስተላለፉ ምንድነው የተገኘው የሚለውም መፈተሽ አለበት፡፡ የተሐድሶን እንቅስቀሴ ይበልጥ አጠናከረው እንጂ አላበረደውም፡፡ አሁን ይወገዙ እየተባሉ ያሉት ብዙ ደጋፊና ተከታይ ያላቸውን ሰባክያንንና ዘማርያንን ነው፡፡ የምእመናኗ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለባት ላለችው ቤተክርስቲያን ይህ ጉዳይ በስሜትና በባዶ ቅናት እንዲሁም በጥላቻ ሳይሆን በማስተዋል ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ ሰዎችን በማውገዝና በማባረር የወንጌሉን እንቅስቃሴ ማስቆም ስለማይቻል ቤተክርስቲያን ትጎዳለች እንጂ አትጠቀምም፡፡ ከዚህ ይልቅ የተሐድሶን ሐሳብ ልትሰማና ራሷን ልትመረምር ማሻሻል ያለባትን ነገር ልታሻሽል ይገባል፡፡ ሰዎችን በማውገዝና በማባረር የባሰ ችግር እንጂ መፍትሔ አይመጣምና፡፡ 

በእርግጥ የሚሳዝነው “ተሐድሶ” የሚለው የከበረ ስም ሳይገባቸውና ሳይሆኑ የተለጠፈባቸው ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡  ለአንዳንዶች የውርደት የሚመስላቸው ነገር ግን ለክርስቶስ ወንጌል በመቆምና ቤተክርስቲያን ጠቃሚ እሴቶቿንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊቶቿን ጠብቃ ከባህላዊ ክርስትና ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና እንድትመለስና በቃሉ እንድትታደስ ለሚተጉት የቤተክርስቲያን ልጆች ፀረ ወንጌል ኃይላት የሚለጥፉት የክብር ስም አጉል ቦታ ሲወድቅ ያሳዝናል፡፡ ምክንያቱም ፀረ ወንጌል ኃይል የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ስም የለጠፈው ከነጋድራስ ገብረ ህይወት እስከ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ባሉ ብሔራውያን ሊቃውንት ላይ ነው፡፡ እንደ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ያሉ ታላላቅ አባቶችንም ውስጥ ውስጡን ተሐድሶ ሲል እንደነበረና ለሞትም እንደዳረገ በብዙዎች አይዘነጋም፡፡ እነዚህ ተሐድሶ የተባሉ አባቶች ግን ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቀው ያወቁ በባህላዊ ትምህርት የበለፀጉ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የተራቀቁ ለኢትዮጵያ ሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት የደከሙና እንቅልፍ ያጡ የቤተክርስቲያናቸው ችግር ምን እንደሆነ የለዩና መፍትሔውን ለመፈለግ የደከሙ ምን መምሰል እንዳለባትም አቅጣጫ ያሳዩ ሊቃውንት የተጠሩበት የክብር ስም ነው እንጂ ተረትም የሰበኩ ወንጌልን ከሚሰብኩት ጋር ስለዋሉ ብቻ የተለጠፈባቸው ሰዎች ሊጠሩበት የሚገባ ስም አይደለም ተሃድሶ፡፡

31 comments:

 1. Replies
  1. ምንድን ነዉ የምታድሱት?በቃ ማርያምን ጠላችሁ ቅዱሳንን ጠላችሁ።በናንተ ቋንቋ አልጠላናንም።እኛ አማላጅ አይደሉምና ይህ ማለት አይደል ፍራሽ አዳሽ ተሃድሶ?በጣም ታሳዝናላችሁ።ኦርቶዶክስ እኮ ባታምኑበትም ኢትዮጵያውያን ቅርስ እኮ ነዉ።የነጭን ለዛዉም የነጭ ሀይማኖት የቆሮንጦሱን እየሱስን ልትሰብኩን?666 በኛ ላይ ልትሰብኩን።ነዉር ነዉ አረ እግዚአብሔር ፍሩ።ህግ የለም እንዴ በዛች ሀገር።

   Delete
 2. ወንጌል በምድሪቱ ላይ ይሰበካል!!!

  ReplyDelete
 3. አባ ስለማዎች ፀረ- ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ስለመሆናችሁ ከራሳችሁ አንደበት በራሳችሁ ፍቃድ እየሰማን ፤ እያየን ነዉ፡፡ ለዚህም ተሐዲሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ብላችሁ ፀረ ቤ/ክንን ቡድን መመስረታችሁን እናዉቃለን፡፡ይህ የነበረ የጥንተ ጠላት የዲያብሎስ ድምፅ ነዉ፡፡ ዲያብሎስ በዚህ ስሙ እና ግብሩ ፍፁም በሚቃረነዉ አባ ሰላማ ብሎግ አዉሬዉ ከአፉ የሞት ዉሃ እየተፋ ነዉ፡፡ መጽሐፍ እንደሚለዉ ሁለት አይነት ምልክቶች በንጽጽር ቀርበዋል አንዱ የታወቁዉ ከእግዚአብሔር የሆነዉ የመዳን ምልክት ነወ፡፡ ይህ ታላቅና አስደናቂ ምልክት ቅድስት ድንግል ማርያምንና ቅዱስ መስቀሉን ይመለከታል ቅዱስ የሐንስ በራዕዩ ምዕ 12 ሴቲቱንና ዘንዶዉን በገለጸበት አንቀጽ እንዲህ ነዉ ያለዉ "ታላቅ እና አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታዩ ፀሐይን (ክርስቶስ) የለበሰች፤ ጨረቃ (ቅዱሳን) ከእግሮ በታች የሆኑላት በራ ላይ ዐሥራ ሁለት ከዋከብት ያሉት አክሊል የደፋች አንዲት ሴት ታየች " ምዕ 12 ቁ 1 ካለ በኋላ ሁለተኛዉንና ሌላ የተባለዉን ክፉዉን ምልክት ሲገልጽ ደግሞ ምዕ 12 ቁ2 "ከዚያም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ………….ልጁዋን ለመዋጥ ፈልጎ ዘንዶዉ ልትወልድ በተቃረበችዉ ሴት ፊት ቆመ" ቁ5 እርም ህዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛዉን ወንድ ልጅ መለደዉ ይላል፡፡ ስለዚህ እናንተ የቅዱሳን እና የመስቀል ጠላቶች እና ሌላ የተባለዉ ምልክት ጉዳይ ፈጻሚዎች በመሆናችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶች ናችሁ በመሆኑም የቅድስት ቤ/ክ ጠላቶች ናችሁ፡፡ ሃይማኖት እንደ ቁሳቁስ ወይም እንደዚህ ዓለም ህግ በየጊዜዉ አይታደስም፤ እናንተ ግን በመጨረሻዉ ዘመን የትንቢት መፈጸሚያ በመሆናች እናዝናለን ፡፡ እንደ መዥገር ተጣብቀችሁ የቤ/ክንን ደም የምትመጥጡ እናንተ ተሐዲሶዎች ከቤ/ክንን ሆዲ የምትወጡበት ቀን ቅርብ ነወ፡፡ የስድብ አፋችሁን በንጽህ መሬት ላይ አስከመቼ ትረጫላችሁ " ዘንዶዉ ጥቂት ዘመን እንደቀረዉ አዉቆ ወደ እንተ ወርዶአል" ተብለናልና ምዕ 12 ቁ13-17 ተመልከቱ "ዘንዶዉ ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችን ሴት አሳደዳት፡፡ ሴቲቱም በበረሃ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንዲትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክፎች (ንጽሀ ስጋ እና ንጽሀ ነፍስ) ተሰጣት……ይህም ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘምን ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ እነድትኖር ነዉ…... እባቡም ሴቲቱ በጎርፍ ተጠራርጋ እነድትወሰድ እንደ ወንዝ ያለ ዉሃ ከአፉ ተፋ" እንደ ተባለ እናንተ ተሀዲሶ መናፍቃን ሁሉ ቅድስት ቤ/ክንን ማስደድ ክርስቶስን ማሳደድ መሆኑን ስለምታወቁ በንስሃ ተመለሱ ቤ/ክንን ግን ሌላ ምልክት፤ ሌላ ትምህርት፤ ተሀዲሶ አያስፈልጋትም፤ በታወቀዉ ምልክት፤ በታወቀዉ ዶግማ፤ ቀኖናና ስርኣቷ ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች "ምድር ግን ሴቲቱን እረዳቻት፤ አፉዋንም ከፍታ ዘንዶዉ ከአፉ ያፈሰሰዉን ወንዝ ዋጠች" ይላል፡፡ ስለዚህ የመዳን ተስፋችሁን አታጨልሙ ተመለሱ፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ራሳችሁን ቻሉ ከቤ/ክንን ትከሻ ላይ ወረዱ፤ የበግ ለምዳችሁን አዉልቁና ወደ አባታችሁ ዲያብሎስ በግልጽ ተቀላቀሉ እላለሁ፡፡ እኛ ቅድስት ቤ/ክንን ልጆች እናንተን ጸረ ቤ/ክንን ቡደኖችንና ግለሰቦች እንዲሁም አስተምሮአችሁን በሙሉ አንቀበልም፡፡ ስለዚህ ባለፈ የተሀዲሶ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዲዮስ የተወገዘዉ አባ ሰላማ ብሎግ እና ግብረአበሮቹ መጀመሪያ በሁሉም የተወገዙ ይሁኑ፡፡ በተመሳሳይ ከቤ/ክንን እዉቅናና ፍቃድ ዉጭ በቤ/ክን ስም በወንጌል ሳይሆኑ በወንጀል የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ከነ ሀሳባቸዉ ይዘጉልን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰለ ክርስቶስ ወንጌል መናገር አዉሪው የሠኛል?

   Delete
 4. .....ተሃድሶ.... ተረት የሰበኩ ወንጌልን ከሚሰብኩ ጋር ስለዋሉ ብቻ ሊጠሩበት የሚገባ ስም አይደለም!................ ልክ ብላችኋል..... ጌታ ያብዛችሁ

  ReplyDelete
 5. mahbere kidusan yebetekrstyan yekurt lij mehnun seytanim yawuqewal

  ReplyDelete
 6. ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.
  እናንተ ወራዶች፡- አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት ተብሎ የተጻፈውን አታስተውሉም? እስኪ የቱ ነው የሚታደሰው? በኒቂያ፣ በኤፌሶንና በቁስጥንጥንያ የተወገዙትን የክህደት ትምህርቶች ከመቃብር እያወጣችሁና ስታችሁ ለማሳት ደፋ ቀና እያላችሁ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የተለየ ትምህርት የሚያመጣ ሁሉ አስቀድሞ በተጠቀሱት ታላላቅ ጉባኤያት የተወገዘ ነው፡፡ ስለሆነም ኦርቶዶሳውያን በሙሉ ሃይማኖታቸው፣ ሥርዓታቸው፣ ትውፊታቸውና ታሪካቸው እንዲበረዝና እንዲከለስ ከቶ አይፈቅዱም ፡፡ በሌላ አነጋገር ሁላችንም የጸረተሐድሶ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነን፡፡ የጸረተሐድሶ እንቅስቃሴ የማኅበረቅዱሳን ድርሻ ብቻ ሳይሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ቤ/ክ የሁሉም ሕዝበክርስቲያን ተልዕኮ ነው፡፡
  ዲያብሎስና ልጆቹ ክህደትና ጥፋትን ከማስፋፋት የተቆጠቡበት ቀን የለም፡፡ ይሄም የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የፈተነ ሰይጣን በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን እኛን ከመፈተን ወደ ኋላ አይልም፡፡ ዳሩ ግን አስቀድሞ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተሸነፈ አንፈራም-የአሸናፊው የእግዚአብሔር ልጆች ነንና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማስተዋልን ይስጥህ!

   Delete
 7. የምን ወዲያና ወዲህ መቅበዝበዝ ነው ወንጌልማ ሁሉም በአለም ላይ ይሰበካል ሚሊዬን አይነት ክርስትያን ባይ ሰባኪዎች አሉ አታወናብዱ አትሳደቡ እግዚያብሄር በየጊዜው የንስሃ ጊዜ እየስጠን ነው እራሳችሁን በንስሃ እጠቡና ተመለሱ ወደ ጥንተ የቀደመች ሃይማኖታችን።አሁን ወንጌል ስይሁን እናንተ እያስፋፋችሁ ያላችሁት 1/ገንዘብ ማከማቻ
  2/ሃይማኖታችን መቀየር
  3/ሰውን መከፋፈል
  ነው የያዛችሁት ይህ ደግሞ ሃይማኖታዊ ምግባር አይደለም ይህ ይሁዳዊነት፥አሪዬሳዊነት፥ሰይጣናውነት ነው እና እግዚያብሂር ክሁላችን ጋር ይሁን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማስተዋልን ይስጥህ!

   Delete
 8. Dear Brothers and Sister in Wrong Path

  If you say Iyesus, Iyesus it does not mean you are true followers The true followers call Him daily in thier prayer daily., which the summary of new testament,


  I believe in one Lord, Jesus Christ, the only begotten Son of God, begotten of the Father before all ages.Light of Light, true God of true God, begotten, not made, of one essence were made.Who for us all and for our Salvation came down from heaven, and was incarnate of the Holy Spirit and of the Virgin Mary, and became man.Crucified for our salvation under Pontius Pilate, He suffered and was buried.And on the third day He rose according to the Scriptures. And ascended into heaven, and is seated at the right hand of the Father.And He shall come again in glory to judge the living and the dead; Whose Kingdom shall have no end.

  The question is about reducing the True GOD and Judger to the level of intercessor ( which was accomplished b him on the cross as the sacrificial lamb, archpriest (intercessor) and One God the forgiver of eternal sin with His Father and Holy Spirit). This forgery to reduce the Our Lord to level of intercessor was master minded by Satan. The first liar also master minded to reduced the reward of sainthood to the true follower of Our Lord and angles of light received.

  The spiritual warfare between Orthodox Christians and Tehdisos and thier Foreign Masters is written in revelation 12. Those who do not respect the woman the Holy Virgin Mariam stand with the dragon and those who accept Her as thier Mother are Her offsprings.

  Then the dragon was enraged at the woman and went off to wage war against the rest of her offspring—those who keep God’s commands and hold fast their testimony about Jesus.

  You have to now we do not hate you personally but because you stand on the side of the dagon. Listen to the preaching of Kesis Dr Zeben Lemma whom you called Tret Tret .

  Your Masters created too many denomination and anarchic form of believing and made people confused and became non-believers. Stan then lead them to hard rock and gayhood. Finally the made gay marriage legal excelling Sodom and Gomora. How can these people call us we do not know Gospel the acts in thier countries ( thier fruits) are greed, individualism, satanism and gay marriage. Wake-up and repent!

  Our youth and some website who march before God , you have to know the warfare is spiritual, if you are provoked and act violently or focus in blaming individuals you are helping Satan!

  Amen

  ReplyDelete
  Replies
  1. You start your comment with good words as a followers of Christian, then you revealed yourself as a religious person. Brother, Ethiopian Orthodox Church must renew, the church doesn't consider as a Church weather you like it or not. Almost all the Protestant followers in Ethiopia once they used to visited Orthodox Church. The Orthodox Church should excelling Lord Jesus and preaching the word of God instead of the word of gedele (gadele). Please, walk in light on instead of dark. I am the renewed Orthodox Christan. Jesus is Lord!!!

   Delete
  2. First, check your grammar. If you can't understand find someone to read and explain you. I used very simple English words to reach to many participates.

   Delete
 9. እውን ተሐድሶነት ኢየሱስ ብሎ መጥራት ነውን?
  ኢየሱስ ኢየሱስ ማለትማ አይደለም ተሐድሶው መልማዮቹም ፕሮቴስታንቶቹ ሲጮኹት የሚውሉት ነው፡፡ ምናልባትም በዘወርዋራ ለእነርሱ ጥብቅና ሊቆምላቸው ፈልጎ ካልኾነ በስተቀር፡፡ እንዲህ ብሎ የጌታን ስም መጥራት የንጹሕ ክርስቲያንነት መገለጫ ሊኾን እንደማይችል ገና በማለዳ ራሱ የስሙ ባለቤት ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲኽ ብሎ ነገሮናል፡፡

  "በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።የዚያን ጊዜም ከቶ አላውቃችችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።" ማቴ ፯፥፳፪።
  እነዚህስ ቢያንስ በስሙ ያደረጉት የሚመስል ምትሐታዊ ተአምር አድርገዋል፣ እርሱ ግን ከምኑም የለበት፡፡ የሚድኑ አሉ፣ ከኤች አይቪ ቫይረስ በጸሎቴ አድኛለሁ እያለ ከማምታት በስተቀር ምንም የሌለበት ባዶ ክህደት፡፡ እምነት አይሉት ክህደት ወንገርጋራ ሕይወት፡፡ በጸሎቴ ድነውልኛል ያላቸውም ቢኾኑ በራሱ መዝገብ ብቻ ያሉ እንጂ ምስክርነት ሲሰጡ አልታዩም፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ በአንዳንድ የቴሌቪዥን ጣብያዎች እንደምናያቸው በአየር ላይ እንፈውሳለን እንጸልይላችሁ ከሚሉት በምንም በማያንስ ሁኔታ እየተውረገረገ ቤተ ክርስቲያንን ማተራመስ ብቻ፡፡ ችሎታው ካለ በራሱም በቤቱም ያለውን ቃልቻዊ ጠባይ ምነው አላጠፋው?

  በመጮኽ ደረጃ ከኾነ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኢየሱስ የሚለውን ስም ደጋግሞ በመጥራት ይጮኻል፡፡ እኛም ጠባችን ኢየሱስን በሚገባ ልክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደምትጠራው አድርጋችሁ እስካልጠራችሁ ድረስ የቤተ ክርስቲያን አይደላችሁም ብለን ነው፡፡
  እኛ፡-
  ኢየሱስ ስንል አምላከ አማልእክት - የአማልክት አምላክ
  ኢየሱስ ስንል እግዚእ ወአጋእዝት - የጌቶች ጌታ
  ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ነገሥት - የነገሥታት ንጉሥ
  ኢየሱስ ስንል አልፋ ወ ኦ - መጀመሪያው እና መጨረሻው፣ ፊተኛውና ኋለኛው
  ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ሰማይ ወምድር - የሰማይና የምድር ንጉሥ
  ኢየሱስ ስንል ኤልሻዳይ - ኹሉን ቻይ
  ኢየሱስ ስንል አዶናይ - መድኃኔዓለም
  ኢየሱስ ስንል ወልደ አብ ወልደ ማርያም - የአብ ልጅ የማርያም ልጅ በተዋሕዶ ልደት የከበረ
  ኢየሱስ ስንል ፈጣሬ ኩሉ - ኹሉን የፈጠረ
  ኢየሱስ ስንል እግዚአብሔር ማለታችን ነው፡፡

  ስሙን ስንጠራ ይኽ ሁሉ በልባችን ሰሌዳ ታስቦ ነው፡፡ በድፍረት አንጠራውም፣ በፍርሃት በረዐድ በመንቀጥቀጥም እንጂ፡፡ እነዚያን አላውቃችሁም ያላቸው በድፍረት የሚጠሩቱን ነው፡፡ ሳያምኑ፣ ሳያውቁት በስሙ ብቻ ቁማር የሚጫወቱትን ነው፡፡ እነጾም ፋሲካውም ሳያምኑ ሲጠሩት እንቃወማቸዋለን፡፡ ክርስቶስ እነዚያን አላውቃችሁም እንዳላቸው ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም አላውቃችሁም ትላቸዋለች፡፡

  ከነቢያት አንዱ ብለው የሚያምኑት እና የሚከተሉት እኮ ሞልተዋል፡፡ ስሙንም በነጋ በጠባ ይጠሩታል፡፡ እነርሱ ግን ስሑታን ናቸው፡፡ ምእመናንም አይደሉም፡፡ የእነ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘገባ እኮ ያመለከተው ይኽንን እውነት ነበረ፡፡ ከነቢያት አንዱ አይደለም ጌታችን፡፡ እርሱ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት ብቻ ዋስትና አይደለም ማለት ነው፡፡ እንዲች እንዲች እያሉ የውብድና ሥራ ለመሥራት በር መክፈት ለስርቆት ማመቻቸት ከተነቃባችሁ ቆይቷል፡፡ ይልቁንስ በቶሎ ንስሐ ግቡ!

  ቤተ ክርስቲያን ቅድስቲቱ ዐውደ ምሕረት የዘፈን የዳንኪራ ቤት እስክትኾን መሥራት ስለኾነ ተልእኮው ይኸው ዘፈናችሁባት፡፡ እንደ ሲኒማ ቤት ዘለላችሁባት፡፡ ዳንኪራ ረገጣችሁ፡፡ እናንተማ ሥራችሁ ነውና አደረጋችሁ፡፡ ግን ሌሎቻችንስ ምነው ዝምታችን! አባቶችስ እዚያው በመድረኩ የነበራችሁ እንዴት አስቻላችሁ? ልጆቻችን በሰው ሀገር በአረመኔዎች ፊት ሃይማኖታቸውን መሰከሩ እኛ ግን በቤታችን ዝም አልን፡፡ እንዴት ነው ነገሩ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Let me ask you does salvation is calling his with different words or living by word of God? Please read a bible ask Lord Jesus to reveal you the truth that his him.

   Delete
 10. METSHAF KIDUS ATWASH /YEHASET MISKIR /ATHUN YILAL GEDLS WASHU YIL YIHON ENDE? YE MAK MILAS YEHONEW HARATEWAHIDO LEMIN YIWASHAL BEWSHET YADEGE HAGER/HAYMANOTE ALE ENDE? SELAM AWO FROM BIBLE MAK FROM MIRAKLES Replay now your answer Thanks for all

  ReplyDelete
 11. የወንጀል እንቅስቃሴን ለማዳፈን ከተቻለም ለማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳን ያላደረገው ጥረት የለም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማስተዋልን ይስጥህ!

   Delete

 12. I like it. No one can stop gospel. We are tired of hearing' teret teret'. Now we are aware of the mission of MK. They are terrorist groups. They have no religious agenda. Let us stand together and confront this mafia group.

  ReplyDelete
 13. ስለ እውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ልናደርግ አንችልም ይላል ቃሉ፤፤
  ይህችን የእውነት መስኮት አባ ሰላማ ብሎግ ምን አባቴ ላርጋት........!!!!
  በእውነት ቃል እንደ ምታሳርፉን የዘለዓለም አምላክ ጌታ እግዚአብሔር እርሱ በእረፍቱ ውሃ ዘንድ ይምራችሁ።

  ReplyDelete
 14. Keep letting us know what's going on over there please Aba Selama's please thank you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you waiting news about Mehabere Kidusan? Bother the time is up read your bible and live by the word of God, pray for the Orthodox Church, to be real Church. Tebarke!

   Delete
 15. ተሐድሶና አራማጆቱን በሐሜት የሚያብጠለጥሉ ሁሉ ደካሞችና ዐቅመ ቢሶች ናቸው። ሐሜትና አድማ የተሰጠ ለዐቅመ ቢሶች ነውና ሮሜ ፲፩/ ፰ ወሀቦሙ መንፈሰ ድንዙዘ እስከ ዮም፤ እስካሁን ድረስ የፈጣሪን ሥራ
  እንዳያዩ እንዳይሰሙና እዳያስተውሉ የደነዘዘ(ደካማ) መንፈስን ዐደላቸው ይላል እናም ሰዎች ይህን መንፈስ ተሸክመው እናምናለን ተቀድሰናል እውነተኞች እኛ ነን እያሉ ገሮችን ማደናገር ስህተት ነው።
  ፈጣሪንም እደመቃወም ይቆጠራል። ሐመይዎ ለእግዚአብሔር፤ ፍጡርን መንቀፍና ባለንጀራን ማማት
  ከእግዜር መጣላት

  ReplyDelete
 16. ባህሩ ተፈራ ደግሞ የዚህ ጉባኤ አባል መሆኑ የመጠጥ ቤት ጒደኞቹን ለማስደሰት ወይስ እርሱ ከወንጌል እውነት ውጭ ሆኖ ለመታየት ነው? መታደስ ይገባታል እያልክ ስትቀሰቅስ አልኖርክምና ነው?።ምናልባት አሁን የሚያገባት ልጅ ቀደም ሲል የእነርሱ ወዳጅ ስለነበረች ይሆን?

  ReplyDelete
 17. sew hatyatun bemenazez endemedin awkalehu sew yesew dikamin eyefelege bewendimu hatyat medesetin benante ayehu yihin wishetachihun ke 20 amet befit bitnageru minalbat tisemu yihonal hizbu kedmuachihual betimhirtim niseha bemegibatim atilfu yilik hiwetachihun addisu chewa anbabi awsea yemilewin awseb bilo silgeta seyaneb liku tew tew bezih ayhudim alamut alut yibalal mahibere kidusanin enkuan enante seytanim ayamaw

  ReplyDelete
 18. libachihun kidmya addisu yihen wishet ke haya amet befit awirtachihu behon sew bagegnachihu zare refed sew beletachihu betimihertim be neseham silzi kehizbu huala lenesiha teselefu.mizan lay yemewetu temesasay yehonu sehonu lemeleyet seyaschegir new lemizan atibekum kemahibere kidusan gar lememezen atichiluma beg kebeg gar yimezenal orthodox ke protestantgar memezen mizaum yigelebital

  ReplyDelete
 19. ባህሩ ደግሞ ሴቱን ያሳድ እንጅ

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሄር በኢትዮጵያ ምድር ያልፋል

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሄር በኢትዮጵያ ምድር ያልፋል

  ReplyDelete