Monday, October 19, 2015

የእነ ደረጀ ወይንዬ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በክሽፈት ተደመደመ


ቤተክርስቲያን ተልእኮ ሳትሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ተልከው “ተሐድሶዎች” የሚሏቸውን በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ እናስወግዛለን በሚል ርእስ ገንዘብ ለመሰብሰብና ኪሳቸውን ለመሙላት አልመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትና ለገቢ ማሰባሰቢያው ብዙ ወጪ ያወጡት እነደረጀ ወይንዬ በቅጽል ስሙ “ወርቃለማሁ” (ወርቃለማሁ የተባለው በወይንዬ ተክለሃይማኖት ማህበር የመጀመሪያ ዙር ገቢው ትልቅ የአንገት ወርቅ ስለገዛበት ነው) ያለሙት ሳይሳካ እቅዳቸው መክሸፉና ኪሳራ ላይ መውደቃቸው ታወቀ፡፡ ያዘጋጁትን ምግብም ለመቄዶንያ አረጋውያን ለመስጠት ተገደዋል፡፡
ከግሸን ክብረ በዓል ጀምሮ ቲፎዞዎችን በማሰባሰብ ሲንቀሳቀስ የቆየው ቡድን አንዳንድ በቤተክርስቲያን የሌሉ በዓለም መድረክ ውስጥ ግን የሚታወቁ ሰዎችን ለምሳሌ የጊዮርጊስ ክለብ አስጨፋሪ እንደሆነው ይድነቃቸው (አቸኖ) ያሉ ሰዎችን ወደቡድኑ አስገብተው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሲሆን አቸኖ በደረጀ ወይንዬ አማካኝነት ተጋብዞ እንደመጣና ለምን እንደተሰበሰበ ግን በሚገባ እንደማያውቅ ሲናገር ተሰምቷል፡፡ የደረጀ ዓላማ ግን በአቸኖ ጀርባ ታዝሎ ደጋፊውን ለዚህ እኩይ ዓላማ ማሰለፍ እንደነበር ከአካሄዱ ታውቋል፡፡ ደረጀ እያለ ያለው አቸኖን ይዤ ብዙ ሰው አመጣለሁ ነበር፡፡ 
ፍኖት ዘተዋሕዶ የሚል ስያሜ የሠጡትና በቤተክርስቲያንም ሆነ በመንግስት ዕውቅና የሌለው ይህ የማቅ ተላላኪ ስብስብ ጥቅምት 7/2007 ዓ.ም. የገቢ ማሰባሰቢያውን ለማካሄድ በመጀመሪያ አስቦ የነበረው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ ሲሆን፣ አለቃው ተስፋ ሰጥተዋቸው የነበረ ቢሆንም ከዚህ ቀደም ለቴዎድሮስ ፈቅደው አስሩን መዘምራን በመከልከላቸው ሳቢያ በገጠማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ዕውቅና ለሌለው ማህበር መፍቀዱ እንደማያዋጣቸው ስለተረዱ በበላይ አካላት ትእዛዝም ከልክለዋቸዋል ነው የተባለው፡፡ እነደረጀም ዕለቱ የሥላሴ ወርሃዊ በዓል በመሆኑና ብዙ ምእመናንን ለማግኘት በማለማቸው ከዚያው ሳይርቁ ፊታቸውን ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አቅንተው ጸዳለ ዳና የተባለች አፍቃሬ ማቅ በሆነች የኮሌጁ ሰራተኛ በኩል ገንዘብ ከፍለው የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ በኮሌጁ ዲን በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ እዚያም የገቢ ማሰባሰቢያውን ማካሄድ እንደማይችሉ ተነግሯቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራማቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ስፍራ አጥቷል፡፡ በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ለማቅ የሚሰሩት ጸዳለ እና ፍኖት ዘተዋሕዶ የተሰኘው የማቅ አዲስ ክንፍ ኮሚቴ አባል የሆነው አንድነት አሸናፊ ባይሳካላቸውም ይህ ቡድን ኮሌጁ ውስጥ ስብሰባውን እንዲያደርግ ማመቻቸታቸው የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ ኮሌጁ እንደእነዚህ ያሉትን ከቤተክርስቲያን እየጎረሱ ወደማቅ የሚውጡትን ቅጥረኞች አንድ ሊላቸው ይገባል፡፡
ቡድኑ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳይሰበሰብ መደረጉ የሚያሳየው ስብስቡ ሕገወጥና ቤተክርስቲያን የማታውቀው መሆኑን ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ዕውቅና ለሌለው ለዚህ ስብስብ በሯን መዝጋቷ ተገቢ የሆነና ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ በቀጣይም ቤተ ክርስቲያን ያሉባትን ችግሮች ለመፍታት የራሷን ሊቃውንትና መዋቅር ተጠቅማ ልትሰራ ይገባል እንጂ ከዚህ ቀደም ማቅ እንደሚያደርገው አሁን ደግሞ እንደረጀ እንዳደረጉት የሌሎችን አጀንዳ እንድታራምድ መመቻቸት የለባትም፡፡ በተጨማሪም የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ በሃይማኖት ካባ ሸፍነው በቤተክርስቲያን ስም እናራምድ የሚሉትን አይመለከታችሁም ልትላቸው ይገባል፡፡
በቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩን ማካሄድ እንደማይችል የተነገረው ይኸው ሕገወጥ ቡድን በመጨረሻ ራሱን ወደመሠረቱበት 4 ኪሎ ወደሚገኘው ሜታ የጡረተኞች አዳራሽ በመውሰድ ተገዷል፡፡ ይሁን እንጂ እዚያም ተመሳሳይ የሕገወጥነት ጥያቄ ነው የተነሣበት፡፡ በሜታ የጡረተኞች አዳራሽ የጋበዛቸው ሰዎች ገብተው ምንዳዬ ሁለት ዝማሬዎችን እንዳቀረበ ህገወጥና ከየትኛውም አካል ያልተፈቀደ ስብሰባ መሆኑ ተገልጾላቸው እንዲበተን መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በወቅቱም ደረጀ ዘወይንዬ ጠላት ከኮሌጁ እንዳሳደደን እዚህም ተከትሎን መጥቷልና ጉባኤውን ማካሄድ አንችልም በማለት የተሰበሰበውን ሰው በትኗል፡፡
የገቢ ማሰባሰቢያው እንዲበተን መደረጉን ተከትሎ ደረጀ ወይንዬ በላይ ወርቁና ፌቨን በንዴት ጦፈው ታይተዋል፡፡ ተልእኮ የሰጣቸው ማኅበረ ቅዱሳን የሌሎችን አገልግሎት ለማስተጓጎል በተለይም በቅርቡ የአስሩን መዘምራን የመዝሙር ምረቃ እንዳይካሄድ ከሥላሴ አለቃ ጋር በመሞዳሞድ እንዲስተጓጎል እንዳደረገ ሁሉ በእነርሱም ላይ ያንኑ ደርሶ ለማየት ተገዷል፡፡
ይህ ማቅ ፊት ለፊት ላለመጋፈጥ ተልእኮውን እንዲፈጽምለት አደራጅቶ የላከው ቡድን ለቤተክርስቲያን እንደቆመ ቢናገርም አካሄዱ ሁሉ ግን ተሐድሶን በማጥፋት ስም ገንዘብ መሰብሰብ ነው፡፡ ገና ምኑንም ሳይሠሩና ዓላማውን እንኳ በሚገባ ሳያስተዋውቁ፣ ወዳጃቸው ዳንኤል ክብረት እንኳ በሰዎቹ ላይ ሳይሆን በተሐድሶ ኢሹ ላይ ነው መነጋገር ያለብን እያላቸው፣ ያን ወደጎን ብለው ልባቸው ወዳረፈበት ገንዘብ ስብሰባ ላይ በማተኮር ደረሰኝና ማሕተም ለማሳተም መሮጣቸውና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መንደፋቸው ትኩረታቸው ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ገንዘብ ላይ መሆኑን በተግባር አሳይቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም ማህበረ ቅዱሳን በተሐድሶ እንቅስቀሴ ላይ ዘመቻ ከፈትሁ ብሎ እጅግ በርካታ ገንዘብ የሰበሰበ ሲሆን ገንዘቡ ለተባለው ዓላማ ሳይውል የግለሰቦች መጠቀሚያ በመሆኑ ሳቢያ ብዙዎች እስከዛሬ ድረስ ቅሬታ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ አሁንም ማቅ በአርአያውና በአምሳሉ የተፈጠፈው ይህ ስብስብ የአካሄድ ለውጥ ሳያደርግ በዚያው በማቅ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ ያለመ እንቅስቃሴ ነው እያደረገ ያለው፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ስብስቦች ቤተክርስቲያን ያልወከለቻቸውና በሃይማኖት ሽፋን ድብቅ ዓላማቸውን ቤተክርስቲያን ላይ ለማራመድ ነው የሚሞክሩት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ የሆነ ሥርዓትና መዋቅር ያላት ቤተክርስቲያን ሆና እያለ እነርሱ ግን ባለቤት እንደሌለው ቤት በመቁጠርና ለቤተክርስቲያን የምናውቅላት እኛ ብቻ ያለናትም እኛ ብቻ ነን በሚል የትምክህት መንፈስ ተሞልተው ቤተክርስቲያንን ለማወክ፣ በተለይም በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በራሳቸው መንገድ ለመንዳት የተለመደ የሁከት አጀንዳቸውን ይዘው ተነስተዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ የመጨረሻ ዓመታት በተደጋጋሚ የታየ ሲሆን በአሁኑ ፓትርያርክም ላይ ተመሳሳይ ነገር ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛልና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይገባል፡፡ ያን ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ተው ቢባል ኖሮ ነገሩ እዚህ ባልደረሰም ነበር፡፡ አሁንም ስላልረፈደ ቤተክርስቲያንን እንደፖለቲካ መድረክ በሰልፍና በሁከት የራስን ዓላማ ማስፈጸሚያ አድርጎ ለመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ህገወጥ ቡድኖች ሴራ ማክሸፍ ይገባል፡፡ 
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዚሁ አፍቃሬ ንዋይ ቡድን አባል የሆነውና በግሸን ለሌላ ዓላማ መድረክ ጠይቆ የቡድኑን ዓላማ ለመስበክ የተጠቀመብት ጳውሎስ መልክአ ስላሴ ቀደም ብሎ የዚህን ቡድን ዓላማ ለማስረጽ ምክንያት በመፈለግ በየመድረኩ በስርዋጽ ሲያስተዋውቀው እንደነበረ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡ ለምሳሌ በ2007 መጨረሻ ላይ እርሱ ባልተገኘበት ጉባኤ ላይ በጆሮው ሳይሰማ በስማ በለው በድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል “የተሰጠው ስብከት የመናፍቃን ነው” በሚል ሰኔ 12/2007 ዓ.ም የነበረውን ጉባኤ ነቅፎ ሐምሌ 22/2007 ዑራኤል ቤተክርስቲያን ላይ ጉባኤውን በመተቸቱ የካቴድራሉ አስተዳደር ሀገረ ስብከቱ ጉዳዩን አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ በጽሑፍ የጠየቀ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን የካቴድራሉን ስም ያጎደፈውን ጳውሎስንና ሌላውን ግብር አበሩን ቄስ አዲስ ኪዳነ ማርያምን በህግ እንደሚጠይቅ ገልጿል፡፡ ጳውሎስ መልከአ ስላሴ 12ኛ ሳይጨርስ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ኮሌጅ ገብቶ እንደወጣ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጳውሎስን በሕግ መጠየቅ ያለበት የድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ብቻ ሳይሆን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም ጭምር መሆን አለበት፡፡ ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በታዴዎስ ላይ ያደረገው ማጣራትና የወሰደው እርምጃ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ሥላሴ ገብተው የወጡትንና የኮሌጁን ዲፕሎማና ዲግሪ አለአግባብ የያዙትን እንደ መልክአ ስላሴ እና ዘመድኩን ያሉትን ህጹጻነ አእምሮ ጉድ ሊያጣራና “መምህር” እየተባሉ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ አለአግባብ የሚጠሩበትን ስምና የወሰዱትን ዲፕሎማ እና ዲግሪ ሊነጥቃቸው ይገባል፡፡

Add caption


23 comments:

 1. ጳውሎስ መልከአ ስላሴ 12ኛ ሳይጨርስ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ኮሌጅ ገብቶ እንደወጣ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጳውሎስን በሕግ መጠየቅ ያለበት የድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ብቻ ሳይሆን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም ጭምር መሆን አለበት፡፡ ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በታዴዎስ ላይ ያደረገው ማጣራትና የወሰደው እርምጃ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ሥላሴ ገብተው የወጡትንና የኮሌጁን ዲፕሎማና ዲግሪ አለአግባብ የያዙትን እንደ መልክአ ስላሴ እና ዘመድኩን ያሉትን ህጹጻነ አእምሮ ጉድ ሊያጣራና “መምህር” እየተባሉ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ አለአግባብ የሚጠሩበትን ስምና የወሰዱትን ዲፕሎማ እና ዲግሪ ሊነጥቃቸው ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 2. ተሃድሶ ናችሁ እናነተ

  ReplyDelete
 3. የኤርትራዊዉ ፕሬዚዳነት ኢሳይያስ አፈወርቅ እና ሜዲያዉን ትመስላላችሁ፤ ምን እዉነት የሌለዉ ባዶ ዉሸት በአባ ሰላማ ስም ይጮሃል…. እስከ….

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳን በበጀት ዓመቱ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም፣ በምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ለጉንዳጉንዶ ገዳም፣ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለሐረር ቅዱስ ፊልጶስ ገዳም፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ለሐይቅ እስጢፋኖስ እና ኢየሱስ ሞአ ገዳም፣ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት አርባምንጭ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ለጎንደር በዓታ አቋቋም ት/ቤት፣ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ለሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ት/ቤት፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ለቆማ ፋሲለደስ የቆሜ ድጓ ምስክር ት/ቤት፣ በከሚሴ ሀገረ ስብከት ለከሚሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ት/ቤቶች ግንባታ 19,014,016.80 /ዐሥራ ዘጠኝ ሚሊየን ዐሥራ አራት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም/ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በቤተክርስቲያን ስም ከምእመናን የተሰበሰበ ሐብት ነው የተኛው ፋብሪካ ያገኘው ትርፍ ነው

   Delete
 5. በተጨማሪም በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ 163 የአብነት ት/ቤቶች ለ184 መምህራንና 1111 ተማሪዎች 1,800,000.00 /አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺሕ ብር/ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ማኅበሩ በሙያ አገልግሎት ደረጃ በበጀት ዓመቱ ከየአህጉረ ስብከት ለጠየቁ 38 አብያተ ክርስቲያናት የሕንፃ ዲዛይን እና የልማት ሥራዎች ፕሮጀክት ጥናት በነፃ አጥንቶ በመስጠት ለባለሙያ ሊወጣ የሚችለውን 1,800,000.00 /አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺሕ ብር/ ገንዘብ ድጐማ አድርጓል፡፡ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በተመለከተ በሀገር ውስጥ 440 በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ 15 የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ከማድረጉም በላይ ሐዊረ ሕይወት የሚል የጉዞ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ከ20,000 በላይ ምእመናን በመገኘት ለተልእኮው ማስፋፊያ ገቢ በማግኘቱ ስብከተ ወንጌል ያልተስፋፉባቸው ጠረፋማ የሆኑትን አህጉረ ስብከትን በመለየትና ከአህጉረ ስብከት ጋር በመመካከር ትምህርተ ወንጌል በመስጠቱ 13,776 ምእመናን ተጠምቀው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆች እንዲሆኑና ለጥሙቃኑ 6 አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁላቸው ተደርጓል፡፡ በመንግሥትና በግል ከሚገኙት የትምህርት ተቋማት እየተመሩ ላሉ 200,000 ተማሪዎች ትምህርተ ወንጌል የተሰጣቸው ሲሆን ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 40,000 ተማሪዎች በብፁዓን አባቶች አስመርቋል፡፡ 1,700 ተማሪዎች ደግሞ ወደ አብነት ት/ቤት ገብተው እንዲማሩ አድርጓል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለካስ እነደረጀዘወይንዬን ተልእኮ ሰጥቶ ያሰማራው ማቅ ነው የሚለው እውነት ነው፡፡ ስለእነርሱ በቀረበው ጽሑፍ ላይ ይህን ሪፖርት ማቅረብ ያስፈለገው በዚህ ፍኖተ ዘተዋህዶ ብሎ በሰየመው ቡድን ውስጥ የማቅ እጅ ስላለበት ነው፡፡ ማቅ በአካፋ እያስገባ በማንኪያ መስጠቱ ግን ብርቅ አይደለም፡፡ እያልን ያለነው ማቅ በቤተክርስቲያን ስም መነገዱን ያቁም ነው፡፡

   Delete
  2. ይህ ሪፖርት ከፍኖት ዘተዋህዶ ጋር ምን አገናኘው?

   Delete
 6. Good job !!!! አስደሳች ዜና ነው እየተከታተላችሁ ትኩስ ትኩሱን እና ትክክለኛውን አቅርቡልን እናመሰግናለን

  ReplyDelete
 7. Dukele new melka selase aydelem.fitu ende libu tikur.ye femesenet Tim alebet mikegna kifu
  Sew new.
  ReplyDelete
 8. Abba selama = protestant
  Fenote Tewahe do =orthodox
  Mk= orthodox

  ReplyDelete
 9. የማን ቀሚስ ዕጣን ዕጣን ይሸታል?፡፡
  በዚህ ጽሑፍ የማወዳደርና የማነፃፀር ጉዳይ ሳይሆን እውነትን ለማሳየትና ፍርዱን ለአንባቢያን ማስቀመጥ ነው ፡፡ ማስተማር የሐዋርያት ተግባር ነበር ከዚያም የእነርሱ ደቀመዛሙርት ለሆኑት ጳጳሳት ዲያቆናት ተግባር ነው እንጂ ምዕመናን አይደልም፡፡
  ሐዋርያት ቃሉን ሊሰብኩ ሊያስተምሩ ሊያገለግሉ ተመርጠዋል ትምህርታቸውም እውነትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ተነሳሁበት መሰረታዊ ሀሳብ ላምራና የቤተክርስትያን አገልግሎት ሰፊ ነው ስብከቷም ትምህርቷም ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ነው፡፡በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ናት። የሐዋ ፳፥፳፰፣ ዕብ ፫፥፲፬። በመሆኑም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታስተምረው ትምህርት ሁሉ እውነት ነው። ምክንያቱም እውነት የባሕርይ ገንዘቡ ከሆነ ከእውነተኛው ምንጭ የተቀዳ ነውና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤» ሲለ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያንም ለእኛ ያስተላለፈችው ከጌታ የተቀበለችውን ንጹሕ ትምህርት ነው። ፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፳፫። ይኸውም በዓይኖቿ ያየችውን፥ በጆሮዎቿ የሰማችውን ፥በእጆቿም የዳሰሰችውን ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ፦ «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን፥ በዓይኖቻችን ያየነውን፥ የተመለከትነውንም፥ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል፥ እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም (ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በቅድምና የነበረውን፥ ፈጥሮም የሚገዛውን) ለእኛም የተገለጠውን

  ReplyDelete
 10. (በመለኰት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ከሰማየ ሰማያት በመውረድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ የነስቶ በመወለድ ሰው ሆኖ የታየውን) የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ » ያለው። ፩ኛ ዮሐ ፩፥፩-፫። ስለሆነም፥ የቅዱሳን ሐዋርያትን ትምህርት በመያዟ፥ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የምትባለው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን በቅዱሳን ሐዋርያት ዓይኖች አይታዋለች፥ በጆሮዎቻቸው ሰምታዋለች፥ በእጆቻቸውም ዳስሰዋለች። ይህም፦ ቤተ ክርስቲያንን ብፅዕት ያሰኛታል። ምክንያቱም ጌታ ደቀመዛሙርቱን፦ «የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ፥ ጆሮዎቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው፤» ብሎአቸዋልና። ማቴ ፲፫፥፲፮።
  በአንድ ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ ላይ ብዙ ግዜ ቤተክርስትያንና በውስጦ ያሉት መንፈሳዊ ልጆቿን በአደባባይ ሲሰደቡ እያየን ዓመታትና እየቆጠርን ነው፡፡ ደግሞም ስድቡና ሀሜቱ በየዓመቱ ጽሑፉቸው እራሱን እየተደጋገመ ነው፡፡ ጦማር ለመሆኑ ስድብ ምን ያስተምራል እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው የሚለው?ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ ስድብን በስድበ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ ›› እንግዲህ ይህ ከሆነ ሚስጥሩ ወንድሞችን በአደባባይ መሳደብ ምን ማለት እንደሆነ መልሱን ለፀሐፍዎች እተዋለሁ ፡፡ ከመነሻ ሀሳቤ እንደገና የማን ቀሚስ እጣን ዕጣን ይሸተል ብይ እራሴን እና ንፁሀ ኦርቶዶክሳዊያን ልጠይቅ ለዛሬው ሁለቱም በአንዲት ቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት በመጥቀስ ጽሑፍኔ ላስቀምጥ
  1 ቤተክርስትያን ያደገና ቤተክርስትያን ያሳደገቸው ፡- ትርጉሙ ግልጥ ነው ቤተክርስትያን የፀጋ ግምጃ ቤት ናት ደግሞም ዝግጁ እመቤት ናት በዚህ ዘመን ፈተና የሆኑባት ሁለቱ አካላት ናቸው ቤተክርስትያን ያደገው ፍላጎቱ አንድ ነው፡፡ እሱም የዕለት እንጀራን ፍለጋና ባገኝው አጋጣሞ ተጠቅም ተረማምዶ ማለፍ ቤተክርስትያ ትሸጥ ብትባል ስንት የሚል ብሎ የዋጋ ተመን የሚያወጣ ደግሞም የሚደራደር ማለት ነው፡፡ ቤተክርስትያን ያሳደገችው ደግሞ ዋጋ ከፍላለታለች ህመሟ ያመዋል ለምን አካሏ ነው ፊደል ከእርሷ ተምሮልና የጥበብ ቤት ናት የእውቀት አድማስ ናት ልዩነቱ ይህ ነው በዚሁ አሳብ በቅርቡ በሊቢያ በረሃ ምስክር የሆኑት ሰማዕታት ቤተክርስትያን ስላደጉ ነው፡፡ መምህር ጳውሎስ መልክዕሥላሴና በበጋሻው መካከል ያለውን የቤተክርስትያን ልጅነት ባስቀመጥኩላችሁ የመለኪያ ሚዛን መዝናችሁ ፍርዱ አሁን ልብሱ የማን ነው ዕጣን ዕጣን የሚለው፡፡

  ReplyDelete
 11. 2 ቅዳሴ ገብቶ የሚቀድሰው ቀድሶም ማነው መምህር ጳውሎስ ወይስ በጋሻውና እርዝራዦቹ ሀራጥቃ ተሃድሶ
  3 በየክፍለ ሀገር ያላችሁ አባቶች ካህናት ወንድሞች ዲያቆናት ላገልግሎት ስትጠሮቸው ሲመጡ አብሮችሁ ማህሌት የሚቆመው ማነው በጋሻው ወይስ ጳውሎስ
  4 የቤተክርስትያኖን የግእዝ ቋንቋ የሚናገረው ማነው መምህር ጳውሎስ ወይስ በጋሻው
  5 ቅኔና ትምህርት የሚጠየቀው ማነው በጋሻው ወይስ ጳውሎስ
  6 ባሏት የቤተክርስትያኒቶ የሙያ ዘርፍ ማን ከሁለቱ ማን ይጠየቃል
  7 ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ማነው ተምሮ የጨረሰ
  8 አሁን ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር አስራ ሁለተኛ ክፍል በቂ እደሆነ ግልፅ ነው ሆኖም ግን በሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ ላይ ያልሆነ ተረት ተረት በሬ ወለደ ወሬ በመምህር ጳውሎስ ላይ የውሸት ፕሮፓንዳ ሲወራ ይታያል ይህ ከእውነት የራቀ ውሸት ነው፡፡ እሺ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማስተር ፕሮግራሙን ጨረሰ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያልጨረሰ ሰው እንዴት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ገብቶ የማስተር ትምህርት ይማራል ስለዚህ ይህ ስም የማጥፋት ሚስጥር ደባ ነው ምክንያቱም መምህር ጳውሎስ የማስተር ዲግሪ እንዳለው ግልጽ ነው አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ PHD ለመስራት በዝግጅት ላይ ነው በጋሻው የአንደኛ አመት ትምህርቱ ከብዶት አምስት F በማምጣት በግቢው የመጀመሪያ የ F ሰቃይ በመባል ይታወቃል ከዚህ የተነሳ ትምህርቱ አቅቶት እንደወጣ ግልጽ ነው ፡፡
  9 መምህር ጳውሎስ ስምንት መንፈሳዊ ስብከት ካሴት እዳለው ግልጽ ነው አንዱም ስብከት ሰውን ግራ ሲያጋባ አልሰማንም …
  10 ማነው ስለቅዱሳን የሰበከ ጳውሎስ ወይስ በጋሻው
  11 ማነው በአውደምህረት ላይ ታናሽ ብላቴና እያለ እራሱን የሚሰብከው ከማጽናናት ይልቅ ሙሾ የሚያሶርድ
  12 ማነው የሐዋሳና ምዕመን ለመናፍቃን አዳራሽ አቀባብሎ ጥይት በመተኮስ የሰጠው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይልቃል ወንድሙ እስከመቼ በጥርጣሬ ታቆየናለህ ጳውሎስ ዶክሌ 12 አለመጨረሱን ለማረጋጥ እባክህን የ12 ክፍል መልቀቂያ ሰርተፊኬቱን ፖስት አድርግልን፡፡

   Delete
 12. 13 ማነው ስለ ድንግል ማርያም የሰበከ
  14 ማነው ኦርቶዶክሳዊ አንደበት ለዛን ያለው
  15 አባቶችን ማነው በአደባባይ የተሳደብ ጳውሎስ ወይስ በጋሻው
  16 ማነው አደበባይ ሥላሴ አትበሉ ያለ ጳውሎስ ወይስ በጋሻው
  17 ማነው የንፍሮ ቀቃይ ልጅ ያለ
  18 ማነው የእነ መለሰ ወጉን ስብከትና መፀሐፍ ገልብጦ የሰበከ
  19 ማነው የፕሮቴስታንተ ሰባኪያን በአደባባይ የመሰከሩለት
  20 በመንፈስ ቅዱስ ከመጠበቅ በፖሊስ በመጠበቅ ታጅቦ የሚሰብክ ማነው
  21 ማነው በአደባባይ ተሃድሶ የለም ያለ፡፡
  22 ማነው እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ምልእተ ጸጋ
  ወእትጋነይ ለኪ ኦ ምልእተ ውዳሴ
  ተዘከርኩ በሌሊት ንጽሐ ድንግልናኪ ዘኢማሰነ አንቲ ብሎ ክብር የሚሰጣት ማነው
  23 ማነው አባቶች ባወገዙት ቤተክርስትያን በእነ ፓስተር ሰይፉ የሚመራው በቅዱስ ሚካኤል ስም ተሰይሞ አሁን አዳራሽ በሆነው ሄዶ የሚሰብከው ጳውሎስ ወይስ በጋሻው፡፡
  23 ማነው መነኝ የሚለው
  24 ማነው ግብረ ሰዶም እንዲስፋፋ የሚፈልገው ችግር የለውም ብሎ በግልጥ የሚናገረው
  25 ማነው በሃይማኖት ሰበብ ባል የሞተባቸውን ባለፀጋ ሴቶች አጽናኝ መስሎ ገንዘባቸውን የሚዘርፍ
  26 ማነው ከቤተክርሰትያን አስወጥቶ ምዕመናን በየሆቴሉ፤በየመንደሩ ግቢ እየተከራዩ በቤታቸው የሚሰበስብ ማነው?
  27 ህይወታቸው በእናት ቤተክርስትያኒቱ ላይ የቆመ በስሟ የሚነግዱ በአደባባይ የሚሰድቧት የእናት ጡት ነካሽ
  ሁለቱን ማነፃፀር ፈልጌ ሳይሆን ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ ሲያደርግ የቤተክርስትያን ልጆች እውነቱን አውቃችሁ ከክፉ ወሬ እንድትቆጠቡ ነው፡፡ ማቴ 7፡16 ወእም ፍሬሆሙ ተአምሮሙ ከፍሬያቸው ታውቆቸዋላችሁ ይላል፡፡ ስለዚህ በነገሮች ማስተዋል ከመናገር ይልቅ ለማዳመጥ መፍጠን ያድለን ስለዚህ የማን ቀሚስ ነው ዕጣን ዕጣን እንደሚል መልሱ ለቤተክርስትያን ልጆች ይሁን ‹‹ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ››
  እውነት የነፍስ ትክክለኛ ምስጢር ናት የነፍስም ትክክለኛ ያለው በእውነት ውስጥ ነው ስለእውነት መስክሩ፡፡

  ReplyDelete
 13. ማጠቃልያ፡- ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ ቅዱሳን የሚሰደቡበት እነ አቡነ ተክለሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠመው በጦርነት ነው ተብሎ የሰደቡበት ብሎግ ድንግል ድንግል ማርያም ሞታ አልተነሳችም አላረገችም አባቶቻችን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰደቡበት ማህበረ ቅዱሳን የሚሰደብበት ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ እነ በጋሻውን መሰሎቹ ክብራቸው ሰማይ ሰማያት ከፍ ክፍ የሚልበት በዚህ ብሎግ ላይ መፃፋቸውን ያለመቃወማቸው ምንድን ነው ምክንያቱም ድንግል ማርያም አቡነ ተክለሃይማኖት በግልፅ የተሰደቡበት እነሱ የሚመሰገኑበት ታሪኩ እና እውነቱ ልባቸው አንድነት ስላለው ነው በጣም የሚሳዝነው ቤተክርሲቲያኒቷን የሚያገለግሉ ወንድሞች መምህራን እነ መምህር ዳንኤል ግርማ፡ እነ ቀሲስ ሱራፌል እኔ መምህር ተስፋይ ሞሲሳ መምህር አንድነት አሸናፊ ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ ተሰድበዋል በአጠቃላይ ቁጥራቸው ጥቂት የሚባል በገንዘብ ተቀጥረው የሚጠጽፉ ሀራጥቃ ተሃድሶ ብሎግ አገልጋዮች ከሚሰጣችሁ ገንዘብ ከምታገኙት ስጋዊ ጥቅም እውነት የሆነው ቃል ይፈርድባችዋል መልሱን እና ፍርዱን ለአንባቢያን አስቀምጫለሁኝ፡፡

  ReplyDelete
 14. Mk kefafay atfi anti kerstos yebetecrstiyan telat.

  ReplyDelete
 15. አቤት ሰይጣን ስም ማውጣት ሲችልበት ምህረተአብ ፍልፍሉ ደግሞ ስንት ተከፈለህ?የእግዚአብሄር ጅራፍ ይመታችውሀል ይፈርዳል እርሱ ስም የምትለጥፉ ክፉ ስም ይለጠፍባችሁ በሰፈራችሁበት ቁና ተሰፈሩ ለቃሉ ጠላት የሆናችሁ የምታሳድዱ እግዚአብሄር ያሳድዳችሁ በቃሉ የሸቀጣችሁ ያፈራችሁ ዳግም ሲመጣ ይፈርባችሁ።ክርስቶስን የማይወድ ትውልድ የተረገመ ይሁነ።ስድብ የተማርኩት ከዘመድኩነ ነው።

  ReplyDelete
 16. ምህረተ አብ ሚስቱን የፈታ ና ሰካራም መሆኑን ታዉቁ ይሆን

  ReplyDelete
 17. ጳዉሎስም ቢሆን ሴት አይቶ አያልፍም ጠስቃሚ ነዉ

  ReplyDelete
 18. እኔን የሚገርመኝ ዘበነ የሜልኮም ልጅ ዘመድኩን የሰይጣን ረዳት ጳውሎስ ዱከሌ ሴት አውል ምረተአብ ጋለሞታ የቴዲ ተነግሮ አያልቅም ደንኤል ክብረት አስመሳይ እነዚህ ናችው የኦርቶ ዶክስ ምርጦች?? የነዚህነ ሰዎች ሀጢያት የተገለፀ ቀን እግዚአብሄር ትእግስቱ ታግሶ ታግሶ የተነሳ ቀነ ያን ግዜ ነዉ ጉድ የሚፈላ

  ReplyDelete