Tuesday, October 20, 2015

የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ይመርመር!!!ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በኑፋቄ እና በቅስጣ ድርሰት (በድርሰት ስርቆት) (Plagiarism) የተሞላው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ እንዲመረመር ስለ መጠየቅ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሰኔ 2007 ዓ.ም. ላይ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” የሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በአባ ሳሙኤል ስም የታተመ ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ራሳቸው የደረሱት ሳይሆን ከሰዎች ድርሰቶች ላይ የሰረቁትና በስማቸው ያሳተሙት ነው፡፡ በመጽሐፉ ገጽ 133 ላይ “ብዙ የዘመናችን ጸሐፊያን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ላይ የሠሩት ሥራ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ጸንታ የምትኖርበት ተከታዮች ምእመናንዋን የምትመራበት በነገረ ድኅነትም ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ የሚገኘው ግብረ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ስለግብረ መንፈስ ቅዱስ ጠንክረን ማስተማር አለብን፡፡” ብለው ፈር ቀዳጅ ለመምሰል ጥረት ቢያደርጉም የእርሳቸው ሥራ ባለመሆኑ ስለመንፈስ ቅዱስ የተጻፈ ፈር ቀዳጅ መጽሐፍ ሊባል አይችልም፡፡ እንዲያውም ወደ መጽሐፉ ውስጥ ሲገባ የሚያስደነግጥ ኑፋቄና የሚያሳፍር ስርቆት የተፈጸመበት ሆኖ ስለሚገኝ አንገት ያስደፋል፡፡ 

ይህን ጉድ ሸፍኖ ማለፍ ለቤተ ክርስቲያን ውርደት እንጂ ክብር አይሆንም፡፡ ለአቡነ ሳሙኤልም ቢሆን ይበልጥ የሚያዋርዳቸው ነውና ስለ ፈጸሙት ስሕተት ትምህርት በመውሰድ ይጸጸቱና ንስሓ ይገቡ ዘንድ፣ ሌሎች እንዲህ የሚያስቡና የሚያደርጉ ካሉም እንዲማሩበት በሚል፣ ከምንም በላይ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጉዳዩን እንዲመለከትና ውሳኔ እንዲሰጥበት በሚል ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ተነሣሁኝ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ስነሣ ማተኮር የምፈልገው ኑፋቄዎችን በመግለጥ፣ ቅሰጣ ድርሰትን በማጋለጥና ይህ ከሕግና ከሃይማኖት ትምህርትና ሥነ ምግባር አንጻር እንዴት ይታያል? የሚለውን በመጠቆም ይሆናል፡፡ የአንዱን ድርሰት ሌላው ሰርቆ የመጠቀም ባህል በቤተክርስቲያን ፈጽሞ የተወገዘ ተግባር ለመሆኑ በቅኔ ቤት የሚታየውን የሌላ ሰው ቅኔን መቀኘት ከሚያስከትለው ውርደት ጋር ማነጻጸሩ ብቻ እንኳ በቂ ነው፡፡ 
        የስርቆት ሆነ እንጂ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ መጻፉ ተገቢና አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ዋናው ሆኖ እያለ ቤተክርስቲያን ግን መንፈስ ቅዱስን ቸል ያለችባቸው ብዙ ሁኔታዎች ስላሉ ይህን ክፍተት ሊሞላ ይችላልና፡፡ በስርቆትና በክሕደት የተሞላው የአባ ሳሙኤል መጽሐፍም ስለመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የሚገባውን ሁሉ ገልጧል፣ ስለ ጸጋ ስጦታዎቹ በቂ ማብራሪያ ሰጥቷል ማለት ግን አይደለም፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፉ ገጽ 101-103 የተጻፈውን ስናነብ ስለ መንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች ተገቢውን ትምህርት ከመስጠት ይልቅ ርእሰ ጉዳዩን አንሥቶ ጴንጤቆስጤያውያንን ወደ መስደብ ነው የገቡት፡፡ እነርሱ በጸጋ ስጦታዎች አጠቃቀም ላይ የሚፈጽሙት ስሕተትና የሚያሳዩት ሥርዐተ አልበኝነት እንዳለ እኔም እስማማለሁ፡፡ ይህ ግን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ወደ መካድ የሚያመጣ አይደለም፡፡ ጴንጤቆስጤዎችንና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎችን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት ነው የሚሰጠው የሚለው ትውፊታዊ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ሊፈተሽና መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲመራትና በጸጋ ስጦታዎቹ እንዲያንጻት በምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሰበብ የተዘጋበት በር ሊከፈትለት ይገባል እላለሁ፡፡
የአባ ሳሙኤል መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ ያነጻው ክርስቶስ የተዋሐደውን ሥጋ መሆኑን ገልጿል፡፡ ይህም የስርቆት ባይሆን ጥሩ ነው፡፡ መጽሐፉ በገጽ 34 ተራ ቁጥር 2 ላይ መንፈስ ቅዱስ በድኅነት ውስጥ ከሠራቸው ሥራዎች አንዱ “ክርስቶስ የተወሐደውን ሥጋ አንጽቶ በመጠበቁ (ሉቃ. 1፥35፣ ዕብ. 10፥5-7)” ነው ይላል፡፡ ይሁን እንጂ አለፍ ብሎ “አነጻ” የሚለውን ሐሳብና ቃል ሲሸሽና ሲገድፍ ይታያል፡፡ “ ‘ከዚህ በመነሣት ነው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አካላዊ ቃል እንበለ ዘርዓ ብእሲ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተፀንሶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ሆነ’ በማለት የሚያትቱት፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ከመክፈሉ ከማዋሐዱ እመቤታችንም ‘ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ’ ከማለቷ የተነሣ አምላክ ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሆነ ማለት ነው፡፡” ይላል (ገጽ 66)፡፡
የሊቃውንቱ ሐተታ ግን “መክፈል፣ ማንጻት እና ማዋሐድ” ነው የሚለው (መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 274)፡፡ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” የተባለው መጽሐፍ ግን “ማንጻት” የሚለውን ለምን ገደፈው? ወይም ተወው? ምናልባት ከላይ “ክርስቶስ የተወሐደውን ሥጋ አንጽቶ በመጠበቁ” ስላለ “አነጻ” የሚለው ቃል እንዳይበዛ ለማድረግና ሊነሣ የሚችለውን ተቃውሞ ለመቀነስ ታስቦ ይሆናል፡፡
በቅድሚያ ሁሉ በግልጽ ሊያውቀው ሲገባ ያላወቀውና በተሳሳተ መንገድ የሚረዳው ሐሳብ አለ፡፡ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ያነጻው ማርያምን ነው ወይስ ከማርያም የነሣውንና ቃል የተዋሐደውን ሥጋ ነው? በሚለው ጥያቄ ውስጥ የተሰወረ ነው፡፡ ወደ መልሱ ለመድረስ በ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” የተጠቀሰውን ሐሳብ መሠረት በማድረግ ወደ ማብራሪያው እንሂድ፤ መጽሐፉ (ግብረ መንፈስ ቅዱስ) “ክርስቶስ የተዋሐደውን ሥጋ አንጽቶ በመጠበቁ” የሚለው ሐሳብ የሚደግፈው መንፈስ ቅዱስ ያነጻው ማርያምን ሳይሆን ቃል ይዋሐደው ዘንድ ከማርያም የከፈለውን ሥጋ ነው የሚለውን አመለካከት ነው፡፡ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚለውን አመለካከት የያዙ ብዙዎች ግን ጌታን ስትፀንስ መንፈስ ቅዱስ ማርያምን አነጻ ብለው ያስባሉ፡፡ መተርጉማኑ ግን ማርያምን ሳይሆን ቃል የተዋሐደውን ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እንዳነጻ ነው የሚያትቱት፡፡ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በመድሎተ አሚን ገጽ 20 ላይ “መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ማለትም ትስብእትን [ማርያምን እንዳላሉ ልብ ይሏል] ከአዳም መርገም አንጽቶ ቀድሶ ለተዋሕዶተ መለኮት (መለኮትን ለመዋሐድ) የበቃ አደረገው” ብለዋል።
ኑፋቄዎችና የተሳሳቱ አገላለጾች
በመጽሐፉ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተወገዙ የቀደምት መናፍቃን ኑፋቄዎችና ክሕደቶች አሉ፡፡ ከኑፋቄዎቹ ዋናውንና ምስጢረ ሥጋዌን የሚያፋልሰውን ኑፋቄ እንመልከት፡፡ ስለ ምስጢረ ተዋሕዶ በተብራራበት ክፍል እንዲህ የሚል እናገኛለን “ቃልና ሥጋ ወይም መለኮትና ትስብእት ስለተዋሐዱ ቅድመ ዓለም ከአብ የተወለደው የቃል ልደት ለሥጋ ተነገረለት፡፡ ድኅረ ዓለም (ኑሮ ኑሮ) ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው (የተገኘ) የሥጋም ልደት ለቃል ተነገረለት፡፡ እንዲህ በማለት ቃል በሥጋ ድኅረ ዓለም ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ሥጋም በቃል ቅድመ ዓለም ከአብ ተወለደ፡፡ ቅድመ ዓለም ከቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘ ሥጋና ነፍስን ስለሆነ (ስለተዋሐደ) አብ በአካላዊ ቃል ትስብእትን ወለደው፣ የኢየሱስ አባት ተባለ፤ “አንተ ልጄ ነህ” እንዳለው ራሱ (ሉቃ. 3፥22)፡፡”
በቅድሚያ ይህን በተዋሕዶ እምነት ዐውድ ለጆሮ እንግዳ የሆነና የሚያስደነግጥ ኑፋቄ ከየት እንዳመጡት አይናገሩም፡፡ በተዋሕዶ የቃል የሆነው ሁሉ ለሥጋ የሥጋም የሆነው ሁሉ ለቃል ገንዘቡ ሆኗል (እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ እንዲል) ቢባልም ሥጋን ወደ እም ቅድመ ወስዶ ከአብ ተወለደ ግን ፈጽሞ አያሰኝም፡፡ ይህ ትልቅ ኑፋቄ ነው፡፡ ደግሞም “አብ በአካላዊ ቃል ትስብእትን ወለደው” የሚለው አነጋግርም እንዲሁ እንግዳ አነጋገር ሲሆን አካላዊ ቃልን መውለጃ አድርጎ የሚያቀርብ ሌላው ኑፋቄ ነው፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቃልና የሥጋ ተዋሕዶ አንጻር ኑፋቄነት ያላቸው የተሳሳቱ አገላለጾች በመጽሐፉ ውስጥ አሉ፡፡ ለምሳሌ፦ በገጽ 72 ላይ “ቃል ሥጋ ሲሆን ከሰውነቱ አልተለወጠም” ይላል፡፡ በዚህ አነጋገር መሠረት መለወጥ አላገኘውም ተብሎ ሊነገርለት የሚገባው ቃል እንጂ ሥጋ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋ ሆነ የተባለው ቃል ነው፡፡ መለወጥ አላገኘውም ሊባል የሚገባውም ቃል እንጂ ሥጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ “ቃል ሥጋ ሲሆን አምላክነቱ አልተለወጠም” ተብሎ ነው መነገር የነበረበት፡፡
በገጽ 73 ላይ ደግሞ “ሥግው ቃል (ሥጋ የሆነ ቃል) ቅድመ ዓለም ከአብ ድኅረ ዓለም ከማርያም ስለተወለደ ሁለት ልደቶች አሉት፡፡” በሚለው ውስጥ “ሥግው ቃል (ሥጋ የሆነ ቃል) ቅድመ ዓለም ከአብ” ተወለደ የሚለው ስሕተት ነው፡፡ “ቃል” ነው እንጂ “ሥግው ቃል” ቅድመ ዓለም ከአብ ተወለደ አይባልም፣ ሥጋ ድኅረ ዓለም ነውና የተገኘው፡፡
ሌላው ክሕደት መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት ቅዱስ መጽሐፍ መሆኑ ቢታወቅም፣ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” የተሰኘው መጽሐፍ ግን ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 45 ቁጥር 7 ላይ “ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።” የሚለውን ኀይለ ቃል ነቢዩ የተናገረው “በእግዚአብሔር መንፈስ ተምርቶ ሳይሆን እንደ መምህርነቱ ሕዝቡን የመጠበቅ አደራ ሰላለበት እስራኤላውያን ክፉን የፈጠረ ሌላ አምላክ አለ ብለው እንዳያምኑ በአንድ በእግዚአብሔር ህልውና አምነው እንዲኖሩ ለማጽናት ሲል ነው፡፡” (ገጽ 38)፡፡ እውን በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ዐይነት አሠራር አለ ወይ? እግዚአብሔር ማንነቱን ፈቃዱንና አሠራሩን በቃሉ ውስጥ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ከእግዚአብሔር ተልኮ ትንቢት የተናገረውን ነቢዩን ኢሳይያስን በእግዚአብሔር መንፈስ በመመራት ሳይሆን ከራሱ ነው የተናገረው ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው፡፡ ይህን የመሰለ ሐሳብ የያዙ ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይም በሐዲስም እናገኛለን፡፡
“በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው” (2ሳሙ. 18፥10)
“ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው።” (2ሳሙ. 19፥9)
“ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።” (2ተሰ. 2፥11-12)
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነው (1ጢሞ. 4፥4)፡፡ ነገር ግን በእርሱ ያመኑትን ሰዎች ከክፉው እንደሚጠብቃቸው ሁሉ በእርሱ ያላመኑትን ባለማመናቸውና ለእርሱ ባለመታዘዛቸው ምክንያት ክፉውን ነገር ያመጣባቸዋል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ከጠቅላላው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር በማገናዘብ ለመተርጎም መሞከር እንጂ በራስ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን ታላቅነት የቆመበትን መሠረት መናድ ተገቢ አይደለም፡፡ ኢሳይያስ ይህን ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ አልጻፈም ከራሱ ነው የተናገረው ማለት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን ትልቅ እምነት የሚንድ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ኑፋቄዎችና የተሳሳቱ አገላለጾች ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመረምራቸውና የተዋሕዶ እምነትን ሊያስጠብቅና የመጽሐፍ ቅዱስን ስፍራ በሚገባ ሊገልጥ ይገባል፡፡
ሌላው የስሕተት ትምህርት “ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስ አካላዊ መለኮትነት በደብረ ታቦር ቢገልጽላቸውም ገና መንፈስ ቅዱስ አልወረደላቸውምና መረዳታቸው እምብዛም አይደለም” የሚለው ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ አባ ሳሙኤል የመጽሐፍ ቅዱስን ሀሁ ገና ያልቆጠሩ መሆናቸውን ከማሳየታቸውም በላይ እርሳቸውን ጳጳስ ብሎ የሾመ ሲኖዶስም ተጠያቂ ነው፡፡ ለመሆኑ በደብረ ታቦር ስለመንፈስ ቅዱስ አካልነትም ሆነ ሌላ ጉዳይ ተወስቷል ወይ? አባ ሳሙኤል ታዲያ ይህን ከየት አመጡት?     
በ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ላይ የተፈጸመ የድርሰት ስርቆት
“ግብረ መንፈስ ቅዱስ” ን ያነበበ ሰው ወጥ የሆነ ሥነጽሑፋዊ ይዘት ስለማያጋጥመው አንድ ጥያቄ ማንሣቱ አይቀርም፡፡ እውን ይህ ጽሑፍ የአንድ ሰው ወጥ ሥራ ነው? ወይስ ሌሎች ሰዎችም የተሳተፉበት ነው? ሊል ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንደ ልመና እንጀራ ውጥንቅጥ ነውና፡፡ ለዚህ ጥያቄው መጽሐፉ በድፍኑ የሚሰጠው ምላሽ ግን ጸሐፊው አባ  ሳሙኤል ናቸው የሚል ነው፡፡ ሆኖም ምላሹ የመጽሐፉን ይዘት ወደመመርመር ይወስደዋል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በዚህ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ ከተጻፉ ጽሑፎች ጋር መጽሐፉን ወደማመሳከር ይገባል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚገኘው ውጤት ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ ያስገኛል፡፡ እኔም መጽሐፉን ሳነብ በዚሁ መንገድ ነው የተጓዝኩት፡፡ ከዚያ መጽሐፉ ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ “ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት” ከተሰኘው መጽሐፍ እና ከቄስ ኮሊን ማንስል “ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ ብዙ ገጾችን እንዳለ በመገልበጥ የራሱ አስመስሎ እንዳቀረበ ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ሌሎቹም ክፍሎች ቢሆኑ ከሌሎች መጻሕፍት እንዳለ የተገለበጡ መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ለዚያውም ታሪክን በማገናዘብ ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳንን ጩኸት በመጮህ እነርሱ ከሚከሷቸው ሰዎች መጽሐፍ ላይ ገልብጠው በማሳተማቸው እጅግ ደንግጫለሁ፤ አፍሬያለሁም፡፡
መቼም መጽሐፍ ሲጻፍ ከሌላ ምንጭ የተወሰደ ሐሳብም ሆነ ጽሑፍ ካለ በመጀመሪያ በአግባቡ መወሰድ አለበት፤ ምንጩም መጠቀስ አለበት፡፡ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” በድርሰት ስርቆት ሊጠቀስ የቻለውም በሚከተሉት ምክንያቶች ነው እላለሁ፦
1ኛ. መጽሐፉ ከ “ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት” እና ከ“ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ” ላይ ሲጠቅስ የራሱን ሐሳብ ለማዳበርና በመረጃ ለማስደግፍ በሚል አለመሆኑና መጻሕፍቱ ላይ እንዳለ በመገልበጡ፣
2ኛ. መጻሕፍቱን ሲገለብጡ ደራሲውን አለማስፈቀዳቸው (በመጽሐፉ ላይ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የተባለ ነገር የለምና)፣
3ኛ. ከሌላ ምንጭ የተወሰደ ጥቅስ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ መቀመጥና ምንጩም መጠቀስ ያለበት ቢሆንም እንዲህ አለመደረጉና የራስ አስመስሎ ማቅረቡ፣
4ኛ. ይህን ያደረገው ደግሞ ሌላ ሰው ሳይሆን አንድ ሊቀጳጳስ መሆኑ ይጠቀሳሉ፡፡
“ግብረ መንፈስ ቅዱስ” ገጽ 20-27 ላይ የምናገኛቸው ጽሑፎች ሙሉ በሙሉ የተገለበጡት ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ “ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት” ከገጽ 170-173 ላይ ነው፡፡ በዋቢ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ መጽሐፍ የተጠቀሰ ቢሆንም የተወሰደው ጽሑፍ ግን ቢያንስ እንኳ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ አልተቀመጠም፡፡ ይህን ያህል ገጽ መጥቀስም የሰውን ድርሰት መዝረፍ ነው የሚሆነው፡፡

"ከአቡነ ሳሙኤል መጽሐፍ የተወሰደ"
ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ መጽሐፍ የተወሰዱ

“ግብረ መንፈስ ቅዱስ” ላይ ከገጽ 27-35 መጀመሪያ ድረስ ያለው ከትምህርተ መንፈስ ቅዱስ ከገጽ 64-70 ካለው ላይ ያለ ትእምርተ ጥቅስ በቀጥታ የተወሰደ ነው፡፡ እንዲሁም “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” ላይ ከገጽ 107-132 ድረስ ያለው ከትምህርተ መንፈስ ቅዱስ ከገጽ 131-143 ካለው ላይ ያለ ትእምርተ ጥቅስ በቀጥታ የተወሰደና የራስ ተደርጎ የተገለበጠ ነው፡፡ 32 ገጽ ያህል ተቀስጧል ወይም ተዘርፏል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ከትምህርተ መንፈስ ቅዱስ የተቀሰጠው ነው፡፡ አባ ሳሙኤል “ፈለገ አሚን” በሚል ርእስ ከዚህ ቀደም ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ስለተሐድሶ የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል በ2004 ዓ.ም. ካወጣቸው ጽሑፎች ውስጥ እንዳለ የተገለበጠ ጽሑፍ አካተዋል፡፡ በዚያ ጽሑፍ የተሐድሶን እንቅስቃሴ በተመለከተ የማኅበረ ቅዱሳንን ጩኸት በመጮኽ እንዳልተሳደቡ ሁሉ አሁን ደግሞ ከቄስ ማንስል መጽሐፍ ላይ እንዳለ በመገልበጥ ቅሰጣ ውስጥ መግባታቸው “የወደዱትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ” ያሰኛል፡፡

"ከአቡነ ሳሙኤል መጽሐፍ" የተወሰደከቄስ ኮሊን ማንሰል መጽሐፍ የተወሰደ

አባ ሳሙኤል በዚህ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም መጻሕፍቶቻቸው እንዲሁ ከሌሎች መጻሕፍት የቀሰጧቸው የሌሎች ሰዎች ሐሳቦች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍም ከተጠቀሱት ሁለት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች መጻሕፍት ውስጥ እንዳለ የገለበጡት ጽሑፍ አለ፡፡ እነዚህን በሌላ ጊዜ እመለስባቸዋለሁ፡፡ ጳጳሱ እንዲህ ማድረጋቸውና የሰው ድርሰት እየቀሰጡ የራሳቸው ሥራ በማስመሰል በስማቸው መጽሐፍ ማሳተማቸው “ብዙ መጻሕፍት የጻፉ ሊቀ ጳጳስ” የሚል ስምን ለመጎናጸፍ ይሆንን? ወይስ ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ይኖራቸው ይሆን?
ቅሰጣ ድርሰቱ ከሕግ አንጻር እንዴት ይታያል?
በድምሩ 35 ገጽ ጽሑፎች ከሁለት መጻሕፍት ላይ ያለፈቃድና ተገቢ ባልሆነ የአጠቃቀስ ሥርዐት መውሰድና የራስ አስመስሎ ማተም በየትኛውም መስፈርት ወንጀል ነው፡፡ የአገራችን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ዐዋጅ ፬፻፲/፲፱፻፺፮ ዓ.ም አንቀጽ ፲ ስለ ጥቅስ ይናገራል፡፡ ቁጥር “፩. ጥቅሱ ከተገቢ አሠራርና ዓላማው ከሚጠይቀው በላይ መሆን የለበትም፤
“፪. ጥቅሱ የተወሰደው የሥራው አመንጪውን ስም ከያዘ ሥራ ሲሆን የጥቅሱን ምንጭና የሥራውን አመንጪ ስም መጥቀስ አለበት፡፡” ይላል፡፡ አንቀጽ ፴፮ ተራ ቁጥር ፩ ላይ ይህን ተላልፎ የተገኘ ሰውም በተለይም “ሆነ ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው ከ፭ ዓመት በማያንስ ከ፲ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል” ይላል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” በተሰኘው መጽሐፋቸው በዋናነት ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ “ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት” እና ከቄስ ኮሊን ማንስል “ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ” መጻሕፍት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቅሰጣ ድርሰት ፈጽመዋል፡፡ አፈጻጸሙም በዐዋጁ እንደ ተደነገገው ከተገቢ አሠራርና ዓላማው ከሚጠይቀው ውጪ ከተጠቀሱት መጻሕፍት ላይ የተወሰነውን የመጽሐፉን ክፍል በመገልበጥ የተከናወነ ነው፡፡ ይህ ሲሆንም በተገቢው መንገድ የጥቅሱን ምንጭና የሥራውን አመንጪ ስም አልጠቀሱም፡፡ ለነገሩ የቀሰጡት በጥቅስ ደረጃ ሳይሆን የመጻሕፍን የተወሰኑ ክፍሎች በመሆኑ ጥፋቱን ከፍ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም በዐዋጁ መሠረት የየመጻሕፍቱ ባለቤቶች መብታቸውን በሕግ ቢያስከብሩ መጽሐፉ ወንጀለኛ ከመሆን በስማቸው የእኔ ነው ብለው ያሳተሙት አባ ሳሙኤልም ከቅጣት አያመልጡም፡፡ ብዙ ገጾችን ይቅርና አንዲት አረፍተ ነገርም ብትሆን ምንጭ ካልተጠቀሰና በአግባቡ ካልተቀመጠ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እንኳ የደርሰት ስርቆት ተፈጽሞ ቢገኝ አንድ ተማሪ በዓለምዐቀፍ ደረጃ ጭምር በየትኛውም የትምህርት ተቋም ዳግም እንዳይማር እስከማድረግ የደረሰ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ ይህን የድርሰት ስርቆት ካረጋገጠ ሲኖዶሱ ምን እርምጃ ይወስድ ይሆን የሚለው አጓጊ ነው የሚሆነው፡፡
እንዲህ ያለውን የሰውን ድርሰት እንዳለ ገልብጦ የራሴ መጽሐፍ እነሆ የሚልንና በኑፋቄና በክሕደት ትምህርት የተሞላን ጳጳስ በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ውስጥ ኮሚቴ አድርጎ መሰየሙ እንደእርሱ ያሉትንና በግብር የመሰሉትን ሰዎች እንዲሾምና ቤተክርስቲያንለዘመናት ስትዋጋው የነበረውን ኑፋቄና ክሕደት እንዲያስፋፋ ዕድሉን ማመቻቸት ነውና የአባ ሳሙኤልን አስመራጭነት ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያስብበት ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህን ታይቶም ተሰምቶም የማያውቀው ከባድ ክሕደትና የስርቆት ወንጀል ለዚያውም በአንድ ሊቀጳጳስ መፈጸሙ ለቤተ ክርስቲያን ሞት ነውና አባ ሳሙኤልንና በስርቆት የታተሙ መጻሕፍቶቻቸውንና ኑፋቄዎቻቸውን እንዲመረምርና ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ አመለክታለሁ፡፡
                                                                    ከቀሲስ ፈታሒ

26 comments:

 1. I don't understand it why the churches needed reforms now?i thinks what's this articles and others what's trying to do is to repeated European history.
  Why you needs to renewal all churches dogmas?do you think Ethiopian orthodox churches does needs transformations?lets saying we renewed dogmas.if we do this there's is no rules and regulations?we became
  Luteran or protestants or only Jesus or other denominations!but which denomination orthodox is gonna be?instead of distructed or distroyed what's orthodox have it.why keeping it the original as it is.to be honest i used to thinks orthodox should be distroyed and whatever mythology they been thoughts us was wronged.but after so many year's studying Bibles and quorans and other chronologicals holy book's i 100%orthodox tewhdo no needed renewal.whatever ideas begashawus groups have is either luck of knowledge of holy books or iggnorance or crethics.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The Ethiopian orthodox church must be renewed, because the church hide christ. Let me ask you brother, if your house is damage because of either internal or external factors, are you going to let the damge to be continuing?

   Delete
  2. its not the orthodox church who hide Christ the Lord but you brothers who are intentionally remove the glory of Our Lord in your faith. our symbol is the cross, our holy Communion is all about Jesus Christ, we respect saints and Vrgin Mary(the mother of our Lord) because the bible taught us so. we don't need dogmatic reform but we need administrative. we don't need the garbage of Europians to be laid upon us, because we don't want to end up gnostic or gay/lesbian. we believe the beginning of wisdom is the fear of GOd.

   Delete
  3. @AnonymousOctober 26, 2015 at 10:46 PM

   Not only does the church need administrative changes, as you pointed out, but also some unorthodox, unbiblical teachings it has been carrying for centuries. If indeed our church is Orthodox, it must be in line with the teachings of the holy Apostles, the church fathers, and the universal Orthodox Church. There are countless and numerous errors in some of our Mariology teachings, our view of the mediation of Christ as the high priest, our view of the holy Eucharist, some of our teachings on the saints, and many more in comparison to the Universal Church. We view the arc (tabot) as if it's still relevant, asides for the consecration of the Eucharist, after the sacrificial death and resurrection of Our Lord Jesus. We still want to abide by the mosaic laws and dietary laws, as if we're Jews. If you're an honest Orthodox, you'd know what I'm talking about. Look at the Coptic and the other sister churches, compare their view in contrast to ours. If the church prides its self in being “Orthodox”, then without a shadow of a doubt, the church needs some form of reformation to get it in line with the ancient universal orthodox church.

   Delete
  4. I agree with your idea yet what the Church need is a strong and free Orthodox scholastic involvement of dialogue following the soul of the church before it too late to clam Orthodox.The church's orthodoxy is stuffed between eutachianism and leonism.may God bless you.

   Delete
 2. እኚህን አባት በአካል አላውቃቸውም፤ ስማቸውን ነው የማውቀው የነበረው፡፡ ይህ ብሎግ እስከአሁን ከተመለከትኩት ጽሁፎች የተለየ አቀራረብና እውነትን የያዘ የሚመስል ነገር አለውና እንደዚህ በመረጃ የተደገፈ ሲሆን ጥሩ ነው፡፡ ትምህርት ይሰጣል፡፡እንደዚህ አይነት ጽሁፎችን ልማድ አድርጉ፡፡ ስድብና፣ ሐሜት፣የፈጠራ ወሬ፣ ተረት የሚመሰሉ ልበወለድ፣ የማያሳምኑ፣ የሚያስቆጡ ጹሁፎችን፣ አብዛኛው ማንነታቸውን ደብቀው ግን የሰውን ወይም የተቋምን ስም እየጠቀሱ መሳደብ፤ በእውነት የክርስትናውን ሕይወት ያጎድፈዋልና አህዛብን የምናስተምር እንጂ ከእነርሱ ብሰን የምናሳዝን ከሆንን ምኑን ከአለም ተለየን፡፡ ተለዩ የተባልነው እኮ ከዚህ ከመሰለው ነውር ነገር ነው፡፡ በአህዛብ መንገድ አትሂዱ ነበር ያለን መድሀኒት ዓለም ክርስቶስ፡፡ እኛ ግን አህዛብ እንኳን ላለመሄድ ጥረት እያደረጉ ያሉበትን መንገድ እኛ አስፍተንና አጠናክረን መሄድ መልካም አይደለም፡፡ እነዚህና የመሳሰሉትን ከመለጠፍ ብትቆጠቡ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ጥሩ ምንም እንኳን ሁለቱንም መፃሐፍ ባላነበውም በትክክል እርስዎ የጠቀሱትን ከጻፉ እሳቸው ድንገት የቅባት እምነት ተከታይ እንዳይሆኑ እሰጋለሁኝ፡፡ በተዋህዶ የማያምኑ ስላሉ ማለቴ ነው፡፡ እርሶን ቃለሕይወት ያሰማልን፡፡ ለእርሳቸው ደግሞ ማስተዋሉንና ጥበቡን ይስጥልን፡፡ መልእክቱ ከደረሳቸው መልስ ይሰጣሉ ብዬ አምናለሁኝ፡፡ ይህንን ጹሁፍ እንዲደርሳቸው ተደርጎ መልስ ቢሰጡ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ እጠብቃለሁኝ፡፡

  ReplyDelete
 3. የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ፤ ሰውየው በግርግር ስራ አስኪያጅ ከዚያም ሊቀ ጳጳስ ሆነው ለፓትርያርክነት ሲንደረደሩ በግንባራቸው ተደፍተው ስም አጠራራቸው በብዙ የዝሙት እና ሙስና ቅሌት ተደፍቆ ፤ እንኳን እንደ ጳጳስ እንደ ምእመን እንከዋን ቤተ ክርስቲያን ለመግባትና ለማስቀደስ አፍረው በየእለቱ 24 ሰዓት በመንፈሳዊ ኮሌጁ መኖሪያ ቤታቸው ተወሽቀው ኖሩ፡፡
  አሁን ደግም በቀን ብዛት ሁሉም ይረሳል ብለው ድሮ በሚያውቁት በዝነኝነት ማትረፊያ ስልቶች በልማት ኮሚሽን፣ እና በቤቶች ግንባታ በሚሰሩ ሥራዎች ይህ ተደረገ ይህ ሊገነባ ነው እያሉ በሚዲያ እና በደራሲነት ሥራቸውም ተጻፈ ተደረሰ ቢሉ ምን ይደንቃል ፡፡ በዝነኝነታቸው ቀጥለው አባ ጳውሎስን ለመገልበጥ እንደቃጡት ሁሉ አሁንም የአባ ማትያስን መንበር ለመያዝ የሚችሉ መሆኑን አምነውበት (ትንቢት ስለተነገረላቸው) ቆርጠው ተነስተዋል፡፡
  እባካችሁ አሁን እንከዋን ተውአቸው ዱላው በዛባቸው ሊሮጡ ሲነሱ እንዲህ አይነቱ ወገብ የሚቆርጥ ገበና መግለጥ እድሜያቸውን ያሳጥራል፡፡

  ReplyDelete
 4. ሊቀ ጳጳሱ ከራሳቸውም ሆነ ሰው ጽፎላቸው ቢያዘጁት ከሌሎቹ ተሸለው ተገኝተዋል ማለት እችላለሁ፤ ብዙ ባንወርፋቸው መልካም ነው፤ የሞከረውንም ዝም ያለውንም እንዴት ዘልፈን እንችለዋለን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሽለው የተገኙት በምንድነው ደርሰትን በመስረቅና የራስ አስመስሎ መጽሐፍ በማውጣት?

   Delete
 5. ውይ ውይ ውይ አቤት ቅሌት አቤት ቅሌት አቤት ቅሌት

  ReplyDelete
 6. ነፍሰ ገዳይ ተሐድሶ ፕሮቴስታንት በሰው ቤት ገብተህ ለምን እንደመቃብር የተከፈተ አፍህን ትከፍታለህ? አያገባህም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Who is killer? Better shutup your wide mouth

   Delete
  2. እርስዎ አባታችን እኮ እንደ አንተ ጀሮ ጠገብ አይደለም ምክንያቱ በየጉባኤ ቤቱ የተማሩትን በኮለጅ የተማሩትን ፃፉ ታድያ ይህ ኮፒ ራይት እያልክ ነው ሞኙ እንዷው ቢሆንስ አንድን (መልካም)ሰው አንብበህ መጠቀም ሃጢአት ነውን እንዷው በአንድ ቤት እንደ ዓለማዊነት አይምሰለህ መንፈሳዊ እንጀራ መንፈሳዊ አደራሽ ስለሆኑ አንተ መናፉቁ ምን አገባህ

   Delete
 7. ከሌሎቹ ተሸለው ተገኝተዋል ማለት እችላለሁ ይልከው ወንድማችን አባ ሳሙኤልን በደንብ አታውቃቸውም ማለት ነው፡፡ ይልቅስ አሁን ያሉት ጳጳሳት በሙሉ የመንፈሳዊ ብቃት ምዘና (በመንፈሳዊነት፣ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አጠባበቅ እና በሁለገብ እውቀት) ተደርጎላቸው እንደገና ጵጵስና ይሰጣቸው ቢባል የተሻለ ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. እንዴ ማሩ ከበደ አንተነህዴ ኮርጀህ ጽፈህ የሰጠሃቸው? ለምን ማፈሪያ ትሆናለህ የተባለው ነገር እውነት ነው።

  ReplyDelete
 9. የሚገርም ነው፡፡ ይህ የአባ ሳሙኤል ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያኗ ውድቀት ነው፡፡ ያኔ ሰሚ ባይገኝም አባ ሳሙኤልን ጳጳስ አድርጋ የሾመች ዕለት ነው ቤተክርስቲያኗ መውደቋ የተረጋገጠው፡፡ ይህን ጊዜ ወንጌልን ስለሰበኩ፣ እውነትን ስለዘመሩ ብቻ ይወገዙ የሚል ጩኸት የሚበዛባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ እውነት እዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍትሕ አለ? ፍትሕ መኖሩን የማረጋግጠው የአባ ሳሙኤል ጉዳይ ከታየ ነው፡፡ ካልታየ ግን ሁሉ ነገር “ፌክ” ነው ማለት ነው፡፡ አባ ሳሙኤል በቀረበው ማስረጃ መሠረት የማይጠየቁ ከሆነ ትልቅ አደጋ ነው የሚፈጥረው፡፡ የጳጳስ ያለመከሰስ መብት መኖር አለ፡መኖሩም የሚታየው አሁን ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የሊቃውንት ጉባኤ አባላትና የሚመለከታችሁ የቤተክርስቲያኗ አካላት ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት ስጡ፡፡

  ReplyDelete
 10. ማኅበረ ቅዱሳን ምነው ዝም አልሽ? ለህማኖቱ ቀናኢ ነኝ ባይ አይደለሽም እንዴ? ከሁሉም በላይ አንቺ ማቅ ምን እንደምትዪ መስማት እፈልጋለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. mahiberekidusan lewusha chuhet mels aysetim. kewusha bemin tileyalachihu?

   Delete
  2. to AnonymousOctober 23, 2015 at 6:00 PM
   wesewema yesewene sehuf eyelekakeme yene new belo yemiyasatemna lesu yimikerakker ndante yalew new

   Delete
 11. ቤተክርስቲያኗ አማኝን እንጂ መናፍቅን አውግዛ ስለማታውቅ የአባ ሳሙአል ጉዳይ የትም አይደርስም፡፡

  ReplyDelete
 12. ሲያሸኛችኁ መንፈስቅዱስ ተረሳ ብላችሁ ትጮሀላችሁ፡፡ስለመንፈስቅዱስ ሲጻፍ ደግሞ ደርሳችሁ የቀኖና እና ዶግማ ጠበቃ መስላችሁ ትቀርባላችሁ፡፡መንፈስቅዱስ ከአብ ብቻ ሳይሆን ከወልድም ሰርጹዋል፤እመቤታችን ወላዲተአምላክ አይደለችም በሚል የኑፋቄ አስተሳሰብ በነጠላው ‹‹ማርያም›› እያሉ ከሚሳለቁት ጋር ገጥማችሁ አሸሼ ስትሉ ትከርሙና ደርሳችሁ የምስጢረ-ሥላሴና ምስጢረ-ሥጋዌ መምህራን መስላችሁ ትከሰታላችሁ፡፡ለነገሩ ‹‹ተሐድሶ›› ማለት የራሴ የሚለው ዕምነት ሳይዝ ከየዕምነቱ ህጸጽ ያለ አስመስሎ በማቅረብ ራስን የመቆለያ አውሮፓዊ ፍልስፍና ነው፡፡
  ለማንኛውም አቡነ ሳሙኤል እንኳን ጻፉ፡፡ስለቃላት መውራረስና አጠቃቀስ ያቀረባችሁት ማስረጃ ከአቡነ ሳሙል 7 ገጽ ጋር የሊቀጉባኤ አበራ 4 ገጽ ቃልበቃል ተወሰደ ማለት የማይመስል ነው፡፡7 እና 4 እኩል አይደለም፡፡ቢመሳሰልም የአስተምህሮው ምንጭ መጽሐፍቅዱስና ኦርቶዶክሳውያን አበው የጻፏቸው መጻሕፍት እስከሆኑ ድረስ አይገርምም፡፡ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ኮፒራይት የለውም፡፡ከዚያ አለፍ ካለም 2ቱም አባቶች ኦርቶዶክሳውያን ስለሆኑ ጉዳዩ የውስጣችን ነው፡፡ተሐድሶን አይመለከተውም፡፡ባይሆን ለፈረንጃችሁ ከተቆረቆራችሁ ፋይል ከፍታችሁ መብቱን አስከብሩለት፡፡ፈንድ ከቃለሕይወት ወይም መሰረት ስብሐትለአብን ስትደጉም ከኖረችው መካነ ኢየሱስ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡በውስጥ ጉዳይ ግን አትፈትፍቱ፡፡ያው መጽሐፉን እንደገዛው ስለገፋፋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡እናንተ የምታጥላሉት ነገር ብዙ ጊዜ ጠቃሚ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ያለው ነገር ሲሆን እንደሆነ በተደጋጋሚ ስላረጋገጥኩ በደስታ ገዝቼ ለማንበብ ቸኩያለሁ፡፡አቡነ ሳሙኤል ይጻፉ፤እኛ ልጆቻቸው እናነባለን፡፡ከለባቱ ከበር ቆመው የመጮህ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡በክህደት ያሳደፉትን ዕምት እንደያዙ እንገባለን ካሉ ግን ያው ነው፡፡መጀመሪያ በውግዘት፣ሲቀጥል በመቋሚያ ቋ አድርገን በቦታቸው እናስቀምጣቸዋለን፡፡ያለ ሥፍራ ገብቶ እምቡር እምቡር የለም፡፡
  ተመየጢ፡ተመየጢ፣
  ተሐድሶ፡ቀሳጢ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እናንተ የማቅ ግርፎች መቼ ይሆን እውነትን የምትናገሩትና ስለእውነት ጥብቅና የምትቆሙት? ይህን አስተያየት የሰጠኸው ሰው ሚዛናዊነት ይጎድልሃል፡፡ የቀረበው ጽሑፍ ትክክለኛና ሚዛናዊ መሆኑን ማንም ሊክድ አይችልም፡፡ በማስረጃ ተደግፎ የቀረበ ስለሆነ መረጃውን መመልከትና እውነት ሐሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ስድብህን ልለፈውና ለመተቸት የሞከርካቸውን ነጥቦች ላንሳ፤ 1/ አቡነ ሳሙኤል እንኳን ጻፉ ብለሃል እየተባለ ያለው አቡነ ሳሙኤል አልጻፉም የሰው ድርሰት ገለበጡ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅ ነውረኛ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ሥራ ማበረታታት በራሱ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ 2/ “ስለቃላት መውራረስና አጠቃቀስ ያቀረባችሁት ማስረጃ ከአቡነ ሳሙል 7 ገጽ ጋር የሊቀጉባኤ አበራ 4 ገጽ ቃልበቃል ተወሰደ ማለት የማይመስል ነው፡፡7 እና 4 እኩል አይደለም፡፡” ስላለከው በአባ ሳሙኤልና በሁለቱ መጻሕፍት መካከል የታየው የቃላት መወራረስ ሳይሆን እንዳለ የመገልበጥ ጉድ ነው፡፡ ገጹን በሚመለከት ያነሳኸው ግን ማደናገር ካልሆነ በቀር አንተም ማንም ሊያየው በሚችል መልኩ ሁለቱም መጽሀፎች አባሪ ስለሆኑ ማስተያየት ይቻላል፡፡ ለማየት አንደሚቻለው ግን የአባ ሳሙአል መጽሐፍ ፊደሉ ጎላ ያለ የመጽሐፉ መጠንም A5 የአባ አበራ ግን ጽሑፉ ድቅቅ ያለና መጽሐፉም በመጠኑ ከፍ ያለ ነው፡፡ የገጽ ልዩነቱ የተፈጠረው እዚያ ላይ ነው፡፡ ይህን ትቶ ሊረጋገጥ የሚችል እውነት ለማለባበስ መሞከርህ ግን አሳፋሪ ነው፡፡ 3/ ለመጽሐፍ ቅዱስ ኮፒ ራይት የለውም ላልከው እንዴት የለውም? ማንኛውም ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲጠቅስ ምንጩን መጥቀሱ አይቀርም ምንጩን ሳይጠቅስ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርን ሳያስፈቅድ ልክ እንደ አባ ሳሙኤል እንዳለ ገልብጦ የእኔ መጽሐፍ ቅዱስ ብሎ ቢያሳትም ይጠየቃል፣ ስለዚህ አትሳሳት፡፡ አባ ሳሙኤል የሰረቋቸው ድርሰቶችም በህግ ሊያስጠይቁ መቻላቸው አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ለማንኛውም አነባለሁ ያልከው ጥሩ ነው አባ ሳሙኤል ድርሰቱን ሰርቀው በስማቸው ያወጡትን መጽሐፍ በማስተዋል ካነበብከው ወደወንጌል እውንት መድረስህ አይቀርም፡፡ ስለዚህ አንብብ፡፡ በተረፈ ግን እዚህ ሁሉ ዝባዝንኬ ውስት ከምትገባ አባ ሳሙኤል መሳሳታቸውን ብትናገር የተሻለ ይሆን ነበር፡፡

   Delete
 13. ልክ ብለሃል

  ReplyDelete
 14. የተከበርክ ዘላፊ ሆይ እንዲህ ዓይነቱ ወሬ ስራ እንደሚስፈታ ማን ነገረህ

  ReplyDelete
 15. የተከበርክ ስራ የፈታኸው ወይ እንዲህ ያለው ታላቅ ውድቀት ተሸፋፍኖ መቀረቱ ምን ይሆን ስራ የጨመረልህ

  ReplyDelete
 16. Please continue to stop such kinds of unresponsive psudofathers(false fathers). Be strong. God bless Ethiopia and the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.

  ReplyDelete