Saturday, October 24, 2015

የወንጌል እንቅስቃሴ መቼም ሊጠፋ የማይችል እንቅስቃሴ ነውRead in PDF
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለውን የወንጌል እንቅስቃሴ ለማዳፈንና ብዙው ምእመን ወደሌሎች አብያተ ክርስቲያን እንዲፈልስ በፀረ ወንጌል ኀይላት በኩል ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ እነርሱ ይህን የሚያደርጉት ሃይማኖታቸውን ኑፋቄ ብለው ከሚጠሩት ከወንጌል እውነት ለመጠበቅ ወይም ለመከላከል ነው፡፡ ለወንጌል እንቅስቃሴ የተለያየ ስያሜ በመስጠት ወንጌልን መቃወም የዘወትር ተግባራቸው ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ወንጌል ጥንትም በነጻነት ሳይሆን በብዙ ተቃውሞና አድማ በመከራና ስደት ውስጥ እየተሰበከ ብዙዎች ኃጥኣንን በምሥራችነቱ ከሞት ወደሕይወት አሸጋግሯል፤ ዛሬም እያሸጋገረ ይገኛል፡፡

ዛሬ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ትልቁ ግብግብ ባህላዊውን (አገር በቀሉን) ክርስትና ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና እናምጣ በሚሉና አይሆንም ባህላዊ ክርስትናችንን ጥለን ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና አንመጣም በሚሉ ኀይላት መካከል ያለ ነው፡፡ ባህላዊ ክርስትና ያልነው መጽሐፍ ቅዱስን መነሻ ያደረጉና በባህላዊ መንገድ የተፈጠሩ ትምህርቶችን፣ ታሪኮችን፣ ሥርዓቶችን፣ ወጎችንና ለማዶችን ወዘተ. ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ይልቅ እጅግ አስበልጦና መጽሐፍ ቅዱስን ከዚያ በታች አድርጎ የመመልከቱን ጉዳይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ደግሞ ባህላዊው ክርስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ሊሸፍንና እርሱን ሊተካ አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል እየተመዘነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የማይጣረሰው ብቻ ሊቀጥል ይገባዋል፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጣረሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር ትምህርትና ፈቃድ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ፣ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ማድላት ይገባል የሚል ዐቋም ያለው ነው፡፡ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” እንዳሉ ቅዱሳን ሐዋርያት (የሐዋርያት ሥራ 5፥29) ከሁለቱ ለእግዚአብሔር ማድላቱና እርሱን ብቻ መታዘዙ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡

ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ በየጊዜው ሌሎች ሽፋኖች እየተሰጡት አንዱ ሌላውን መናፍቅ ሲል ይኖራል፡፡ ቤተክርስቲያንም ለውዝግቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ለሰው ሥርዓት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቃል የወገነ መፍትሔ መስጠት ሲገባት ይህን ሳታደርግ በመቅረቷ ውዝግቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መጥቷል፡፡ ከዚህ ቀደም መፍትሔ ይሆናሉ ተብለው የተወሰዱ እርምጃዎች መፍትሔ ሲያመጡ አልታዩም፡፡ እንዲያውም ነገሩ በብዙ እጥፍ እንዲስፋፋ ነው ያደረጉት፡፡ ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. ውግዘት ቢተላለፍ መናፍቃን ጸጥ ይላሉ፣ እንቅስቃሴያቸውም ይከሽፋል ተብሎ ውግዘት ተላለፈ፡፡ ውግዘቱ ግን ችግሩን ሲያባብስ እንጂ ሲያሻሽል አልታየም፡፡ ዛሬም አንዳንዶች ተመሳሳይ እርምጃ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲወስድ እየጎተጎቱት ይገኛሉ፡፡ አሁንም ተረኞች ቢወገዙ ችግሩ ይወገዳል ባይ ናቸው በባህላዊው ክርስትና ውስጥ ያሉት ክፍሎች፡፡ ከስሕተት አለመማር ማለት ይህ ነው፡፡ እውን ውግዘት የወንጌልን እንቅስቃሴ ለመግታት ይችላለን? በፍጹም አይችልም፡፡ እንዲያውም የባሰ ያቀጣጥለዋል፡፡ ኢየሱስን በመግደል የወንጌል እንቅስቃሴ ይቆም የመሰላቸው አይሁድ ያን ሙከራ አደረጉ፤ ኢየሱስን ገደሉት፡፡ ወንጌልን ከመስፋፋት አላገዱትም፤ ብዙ ሰዎች በወንጌል እንዳያምኑ ማድረግም አልቻሉም፡፡ ዛሬ ከአይሁድ ተከታይ የኢየሱስ ተከታይ ይበልጣል፡፡ በሐዋርያትም ላይ ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የወንጌልን እንቅስቃሴ ለመግታት የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ፡፡ ገማልያል የተባለው ምሁረ ኦሪት ተነሥቶ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። … ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።” (የሐዋርያት ሥራ 5፥35-39) ሲላቸው ለጊዜው የሰሙት ቢሆንም በቀጣይ ግን ወንጌልን ማሳደዳቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ የወንጌልን ጉዞ መግታት ግን አልቻሉም፡፡ ዛሬም የወንጌልን እንቅስቃሴ ሌላ ስም እየሰጡ ከማውገዝና ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣሉ ከመገኘት ራስን ማቀብ ትልቅ አስተዋይነት ነው፡፡ አሊያ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ደግሞ ይደቅቃሉና፡፡

በዘንድሮው 34ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ አባታዊ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተክርስቲያን ለህልውናዋ አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንዳለች ጠቁመዋል፡፡ ሁለቱ አስጊ ሁኔታዎች የምእመናን ፍልሰት መናርና የብልሹ አስተዳደር መኖር ናቸው፡፡ ንግግራቸው በጠንካራ ቃላት የተሞሉ መሆናቸውን ለተመለከተ ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ከንግግራቸው ለመጥቀስ ያህል፦
“ቤተ ክርስቲያናችንን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስናነጻጽር በቊጥር እጅግ የላቀ የውሉደ ክህነት ብዝኀነት ያላት ስትሆንታላቁን የቅዱስ ወንጌል ተልእኮንለውሉደ ሰብእ በማዳረስ ረገድ ያለን ውጤት ግን አናሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ባህርን አቋርጦ፣ ድንበርን ተሻግሮ፣ እስከ ጽንፈ ምድር ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በሀገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምእመናንን ማብዛት ብዙ ያልተሄደበት እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያስቆጨው ደግሞ ትናንት ቤተ ክርስቲያንሀብተ ወልድና ስመ ክርስትናሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆችዋ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደሌላው ጎራ የመቀላቀሉ ጉዳይ እጅግ በጣም እየናረ መምጣቱን ነው፡፡

“የምእመናን ፍልሰት በየጊዜው እየጨመረ የመሄዱ መነሻ ምሥጢር ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ልታጤነው ይገባል፤  በዚህ ዙሪያ የሚታየው ክፍተት ፈጣን ምላሽ በመስጠት መግቻ ካላበጀንለት ነገ ከባድ የሃይማኖትና የታሪክ ወቀሳ ማስከተሉ እንደማይቀር ልብ እንበል፡፡ ለመሆኑ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምብ ለመግባት ለምን መረጡ?
- የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው ነው?
- የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት ነው?
- የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር የማያረካ ሆኖ ነው?
- የካህን እጥረት ስላለ ነው?
- ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው? 
- የዚህ ሁሉ መልስ በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ ቁልጭ ብሎ ስለሚታወቅ የጥያቄውን መልስ ለእናንተው ሰጥተናል፡፡ 
ይሁን እንጂ ይህ ዓቢይ ጉባኤ በሁለት ዓበይት የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲነጋገርባቸው ሳንጠቁም አናልፍም ይኸውም፡-
- ምእመናንን የመጠበቅ ተልእኮ በሚገባ እየተወጣን አይደለምና ባዶአችንን ከመቅረታችን በፊት ለተደራጀና ለድንበር የለሽ ትምህርተ ወንጌል ብንነሣ፤
- የአስተዳደር ሥራችን ለምእመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ ነውና የሃይማኖቱን መርሕ ጠብቀን አስተዳደራችን የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጽ፣ ተአማኒና ተጠያቂነትን ያሰፈነ የምእመናንን ልብ የሚያረካ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያናቸው ኵራት እንዲሰማቸው የሚያስችል አሠራር ብናረጋግጥ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን፡፡

ይህን የቅዱስነታቸውን አንኳር መልእክት ተከትሎ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሪፖርት አቅራቢዎች በየሪፖርቶቻቸው ካካተቱት ጉዳይ መካከል አንዱ ከሌላ እምነት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባልነት የመጨመራቸው ነገር ነው፡፡ የፓትርያርኩን መልእክት ኣዛብታ ያቀረበችውና ይህን ዜና አለቅጥ ያራገበችው ሐራ ዘተዋሕዶ የተሰኘችው የማቅ ብሎግ “2007 .36874 በላይ ወገኖች አምነውና ተጠምቀው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተደምረዋል፤ ከእኒህም ውስጥ 13‚776 ጥሙቃን፣ ከማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ጋር በመተባበር በተፈጸመ የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት የተገኙ ናቸው” ስትል ስለምእመናን መጨመር ተናግራለች፤ ከፓትርያርኩ መልእክት ጋር በተስማማ ሁኔታ ግን ስለምእመናን ቁጥር መቀነስ አልተናገረችም፡፡ ለምእመናን መቀነስ በአንድ በኩል ተጠያቂ እየተደረገ የሚከሰሰው ማኅበረ ቅዱሳን ሆኖ ባለበት ሁኔታ ከ13 ሺሕ በላይ ሰዎችን ወደ ኦርቶዶከስ ሃይማኖት መመለስ የተቻለው በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ነው ትላለች፡፡

ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሪፖርት አቅራቢዎች ይህን ጉዳይ በየሪፖርቶቻቸው ያካተቱት የፓትርያርኩን ንግግር ከሰሙ በኋላ ይሁን ወይም ቀደም ብለው የተዘጋጁበት ይሁን ለጊዜው ምንም ማለት ባይቻልም፣ ወደ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስለተመለሱት ሲያወሱ፣ ቢያንስ ፓትርያርኩ ከፍልሰት መናር ጋር አያይዘው የተናገሩትን የሚያሳይ ነጥብ ማንሳት ነበረባቸው፡፡ እርግጥ ነው በሦስት አህጉረ ስብከት ውስጥ ከቤተ ክርስቲያን ስለተገፉና ስለፈለሱ ጥቂት ሰዎች ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም፦
“በቄለም ወለጋ- … ሦስት ሠራተኞች፤ ሕዝቡን ግራ ያጋቡ ቆይተዋል፡፡ ግለሰቦቹ ከተሳሳተ ትምህርት ተመልሰው ንስሐ እንዲገቡ ጊዜ ተሰጥቷቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመኾናቸውና በክሕደታቸው በመቀጠላቸው ከክህነት አገልግሎት እና ከሥራ እንዲወገዱ ተደርጓል፡፡”
“ምዕራብ ወለጋ- … በተለያየ ምክንያት ደግሞ ሴት 200 ወንድ 137 በድምሩ 337 ወጥተው ሔደዋል፡፡”
“ሰሜን ሸዋ- … 23 ሰዎች ከእኛ ወደ ሌላ እምነት ሔደዋል፡፡”

ይሁን እንጂ በተለይ ቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ከፍተኛ የሆነ የወንጌል እንቅስቃሴ እየተካሄደ ያለባቸው ስፍራዎች ስለሆኑ ያን አሳንሶም ቢሆን አለመጥቀስ አልተቻለም፡፡ የሌላው ግን አልተጠቀሰም፡፡ ይህን ያህል ሰው ወደ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተመለሰ ብቻ ሳይሆን ይህን ያህል ሰውም ወደሌሎች እምነቶች ሄዷል የሚለው ነገሩን ለመመዘን ያስችል ነበር፡፡ የተመለሰው ይበልጣል ወይስ የፈለሰው? የሚለውን ለማወቅም ይረዳ ነበር፡፡ ነገር ግን የሐራ ዜና አቀራረብ የፓትርያርኩን መልእክት ቆራርጣና እርሷ የምትፈልገውን ብቻ ቆርጣ ማውጣቷ በፓትርያርኩ መልእክት ሙሉ በሙሉ ደስተኛ አለመሆኗን ያሳያል፡፡ ጉዳዩ የፖለቲካ ሳይሆን የሕይወት ስለሆነ እንደ ፓትርያርኩ ገልጦ መናገርና መፍትሔውን መፈለግ እንጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ የሚለው ማዘናጊያና አልሸነፍ ባይነት የትም አያደርስም፣ እውነታውንም አያሳይም፡፡ በምርጫ 97 ሕዝቡ ሁሉ ከእኛ ጋር ነው ብለው የቀድሞውን ጠ/ሚ/ር እንዳሳሳቱትና እርሳቸው ስለ ሕዝብ ማእበል በአደባባይ ሲናገሩ ያ ማእበል በጊዜው ወደ ጅረትነት በአንድ ቀን መለወጡን መርሳት የለብንም፡፡ ከሌላው ስሕተት አለመማር ትልቅ ስሕተት ነው፡፡

በሪፖርቱ ውስጥ ስለ ወለጋ ቄለም እንዲሁም ምዕራብ ወለጋ የቀረቡት ሪፖርቶች እጅግ የሚገርሙ ናቸው፡፡ በዚያ አካባቢ ከፍተኛ የወንጌል እንቅስቃሴ እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን ሕዝቡም ወደሌላ ለመሄድ ሳይሆን በሃይማኖቱ ጸንቶ ወንጌል እንዲሰበክና በባህላዊ ክርስትና ውስጥ ያለው ሕዝብ ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና እንዲመጣና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ ቆርጦ ተነሥቷል፡፡ እንቅስቃሴው እንደ ሰደድ እሳት እየገፋ ባለበት ሁኔታ 8000 ያህል ሰዎች ከፕሮቴስታንት ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ተመልሰዋል የሚለው ሪፖርት እውነት ሊሆን አይችልም፤ ነጭ ውሸት ነው፡፡    

ከአካባቢው በደረሰን መረጃ መሠረት 1200 የሚደርሱ ወገኖች ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በወንጌል እንቅስቃሴ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በደንቢ ዶሎ፣ ጅማ ሆሮ፣ የማሎጊ ወለል በሚባሉ ወረዳዎች ውስጥ እንቅስቃሴው እየተቀጣጠለ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጅማ ሆሮ ውስጥ 2 ቄሶችና ከ30 በላይ የሚሆኑ ዲያቆናት ተጆ ላይ 1 ቄስ 6 ዲያቆናት፣ ደንቢ ዶሎ ላይ 2 ቄሶች 28 ዲያቆናት፣ ሱዲ ሥላሴ 96 ሰዎች፣ ከዓለም ተፈሪ ዳሌ ሰዲ ወረዳ 8 ዲያቆናት ከቤተክርስቲያን ታግደዋል፡፡ ጊዳሜ ውስጥ የተዘጋ ቤተ ክርስቲያን አለ፡፡ የኮሌ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ታቦት ሀገረ ስብከቱ መልሱልኝ ቢል ደብሩም በገንዘባችን የገዛነው ነውና ብራችንን መልሱ ብሎ ሀገረ ስብከቱ ለደብሩ የሸጠበትን ብር 3ሺህ (?) እንዲመልስ ከተደረገ በኋላ ታቦቱን ወስዶታል፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በእነዚህ ቦታዎች የወንጌልን እንቅስቃሴ በመቃወምና ሰዎቹ ተሐድሶ ሆነዋል የሚል ስም በመስጠት ነው፡፡ ጥያቄው ግን በዚህ መንገድ የወንጌልን እንቅስቃሴ ማስቆም ወይም መግታት ይቻላል ወይ? ነው፡፡

ከምንም በላይ ፓትርያርኩ ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ ያነሧቸው ጥያቄዎች መጤንና ምላሽ ማግኘት አለባቸው፡፡ ለሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች ደግመን እንመልከታቸው፦
- ለመሆኑ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምብ ለመግባት ለምን መረጡ?
- የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው ነው?
- የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት ነው?
- የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር የማያረካ ሆኖ ነው?
- የካህን እጥረት ስላለ ነው?
- ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው?  
እነዚህ ጥያቄዎቹ ተገቢ ምላሽ ይፈልጋሉ፡፡ መፍትሔ የሚገኘው ችግሩን በማለባበስ ሳይሆን በችግሩ ላይ በተገቢው መንገድ በመወያየት ነው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበትን ችግር ከመሸፋፈን ይልቅ ገሃድ አውጥተዉት መፍትሔ እንፈልግ ብለዋል፡፡ ጥያቄዎቹ የቀረበላቸው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተወካዮች ምን ምላሽ ሰጥተው ይሆን? በአብዛኛው ከዚህ ቀደም ሲሰጡ የነበሩትንና መፍትሔ ያላመጡትን ምላሾች እንደሚሰጡ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ችግሩን እየጠቀሱ መፍትሔ አለን የሚሉት ግን አስቀድመው ችግሩን የፈጠሩት ክፍሎች ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት የጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አባ ሄኖክ በሀገረ ስብከታቸው የነበረውን የወንጌል እንቅስቃሴ በመቃወም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተሐድሶን የሚያጠና ኮሚቴ እስከ ማሰየም ደረሱ፡፡ ውጤቱ ግን ከላይ እንዳየነው እንቅስቃሴውን ይበልጥ የሚያቀጣጥል ነው የሆነው፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከቤተክርስቲያን በማባረር “ወደሌላ ሄዱ” ብሎ ሪፖርት ማድረግም አሳፋሪ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ለችግሩ ተገቢው መፍትሔ እስካልተሰጠው ድረስ ችግሩ ይቀጥላል እንጂ የሚቆም አይሆንም፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷን ሥርዓቷን በመጽሐፍ ቅዱስ መፈተሽና ተሐድሶ ማድረግ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡

ችግሩ ሌላ ሳይሆን በባህላዊው ክርስትና እና በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና መካከል የተፈጠረ ነው፡፡ ባህላዊው ክርስትና ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ትምህርት መምጣት አለበት በሚለውና ባህላዊው ክርስትና ያለ ምንም ለውጥ መቀጠል አለበት በሚለው አስተሳሰብ መካከል ያለ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ባህላዊው ክርስትና የሰው ሐሳብ፣ ምድራዊና ሃገራዊ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ግን መንፈሳዊ ሰማያዊና አምላካዊ ነው፡፡ ስለዚህ ከሰው ሐሳብ ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ ዘወር ማለት አማራጭ አይገኝለትም፡፡ ይህ ከመሠረቱ እስካልተፈታና ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ ተሐድሶ እስካላደረገች ድረስ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ተጽዕኖው እየበረታ መሄዱ፣ ባህላዊው ክርስትናም በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና እየተለወጠና እየተዋጠ መሄዱ ላይቀር መፍጨርጨሩ ዋጋ የለውም፡፡ ሆኖም ድሉ የማታ ማታ የመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ነው፡፡ ምክንያቱም ባህላዊው ክርስትና የሰውን አእምሮ በአገራዊ ዕውቀት ከማወፈር ባለፈ የሰውን ሕይወት የመለወጥ፣ የሰውን የሕይወት ጥያቄ የመመለስና የማሳረፍ፣ ለእግዚአብሔርም የማስገዛት ዐቅም የለውም፡፡ እነዚህን ያላገኘ ሰው ደግሞ እውነትን መፈለጉ እስኪያገኝም ድረስ አለማረፉ የታወቀ ነው፡፡
በአጠቃላይ ይህን የወንጌል እንቅስቃሴ ማስቆም አይቻልም፡፡ ስለዚህ የሚሻለው ሰዎችን ማወገዝ ሳይሆን ሐሳባቸውን ሰምቶ ከባህላዊው ክርስትና ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ፊትን መመለስ ነው፡፡ ለዚህም ቤተክርስቲያን ቆም ብላ ራሷን ልትመረምርና በየጊዜው የተሐድሶ ጥያቄን የሚያነሡ ልጆቿን ጥያቄ በማገድና በማውገዝ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ጥያቄያቸውን መቀበልና እንደመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሊስተካከል የሚገባው ነገር ካለ ማስተካከል ምላሽ የሚገባው ነገር ካለም ምላሽ መስጠት ይጠበቅባታል፡፡ አሊያ ጥያቄው ደጋግሞ መነሣቱ የሰዎች ፍልሰትም ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም፡፡

14 comments:

 1. ጥቅምት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.
  “ባህላዊው ክርስትና” ያልከው ያልተነቃብህ መስሎህ ነው? “ከትንባሆ ልምልሜ ከመናፍቅ …” እንደተባለው መልክና ዘዴውን በመቀያየር የኑፋቄ ትምህርታችሁን ለመዝራት ከመባዘን አትቆጠቡም፡፡ዲያብሎስ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀረው እየጠቀሰ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንኳን እንደፈተነው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ከቁጥር 1-10 ከተጻፈው ብቻ በመነሳት የአባ ሰላማን ብሎገሮች (አብዛኛዎቹን) ማንነት መረዳት ይቻላል፡፡ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መሆናችሁን እናስተውላለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ልክ እንደ ዲያብሎስ ባልተፈለገበት ቦታ ትጠቀማላችሁ፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ወንጌል ላይ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያብሎስን “ሂድ አንተ ሰይጣን” እንዳለው እኛም እናንተን ሂዱልን ውሉደ ሰይጣን እንላችኋለን፡፡

  እናንተ የታሪክ አተላዎች፡- የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ብሉያትንና ሐዲሳትን አስተባብራ የያዘች፣ የተሟላ የቅዱሳት መጽሐፍት መገኛ ሀገር፣ እነሆ በፍርድ ቀን ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን በዚህ ትውልድ ላይ ተነስታ ትፈርድበታለች ተብሎ በጌታችን የተመሰከረላት፣ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ ሳይሆን በቅዱሳን ሕይወታቸውና በሚታይና በሚዳሰስ መልኩ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዲገለጥ ያደረገች ስንዱ እመቤት፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን ከፍልስፍና መጽሐፍት ለይታ ሰፍራና ቆጥራ ለዓለም ያበረከተች፣ ወዘተ. ናት፡፡
  እናንተ ፍሬ አልባ መናፍቃን፡- ወንጌል ምን እንደሆነ እንኳ በቅጡ ሳትረዱ በጨለማ ውስጥ ሆናችሁ ብርሃን ለመምሰል የምትሞክሩ፣ የሉተርን የሞት ፍልስፍና አንግባችሁ ለጥፋት የምትፋጠኑ፣ ሳይረፍድባችሁ ንሰሐ ግቡ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziar Yistwot! Anjet yemiyareka mels setulign.

   Delete
  2. Egziar Yistwot! Anjet yemiyareka mels setulign.

   Delete
  3. አካሄዳችሁ አደገኛ እና ስውር ደባ ያለበት መኾኑን ከዕለት ወደ ዕለት ተረዳነው፡፡
   እባካችሁ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ችግር ስለሌለብን ይልቁንስ በወገበ ነጮች
   በሊቃውንቱ ላይ የሚደርሰውን በደል እና ችግር ብቻ (ምን አልባት በእናንተም
   ላይ) ለይተን እንዋጋ፡፡

   Delete
 2. መጽሐፍ ቅዱስ የስድብ አፍ ተሰጠው የሚለውን ታስታውሰዋለህን?ለማነው የስድብ የተሰጠው???መሳደብ ጥቅም የለውም ለቀረበው ሃሳብ ተግዳሮታዊ መልስ መስጠት እንጂ እንደእድል ሆኖ መሳደብ ለእኛ ለማህይሞቹ የተሰጠ መሆኑ ነው የሚያሳዝነው መድረክ ሲከፈት በጥሞና ተናግሮ ማሳመን ሃሳብን ማንሸራሸር መናገር መጻፍ በትህትና እንጂበማለት ደህናውን ጠላ ማክፋፋት አይቻልም ትውልዱ አንባቢ ቀማሽ ተመራማሪ ነው የሚሳደብ ሰው መሸነፉን ነው የሚያሳየውና ቤ/ክርስቲያናችንን በስድበኞች መሙላት ራሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አይደለም ስለመድሃኒታችን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የሚለው እኮ<ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ ነው የሚለው ውድ ወገኔ ስለዚህ ለስድቡ ንስሐ ቢገቡ ለወደፊቱ ቁምነገር ቢጽፉ ይመረጣል።አመሰግናለሁ ስላነበቡት !

  ReplyDelete
 3. ኢየሱስ በኢትዮጵያ ምድር ይከበራል አዲስ ትውልድ ተነሷታል
  በየቤቱ የወንጌል እሳት ተለኩሶል
  ውግዘት አያቆመውም

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼም ቢሆን ሉተር የፈጠረው ኢየሱስ በኢትየጰያ ምድር አይሰበከም፡፡ የተሰበከ ስለመሰላችሁ ነው እንጂ እናንተ ተሰበከ የምትሉትና ተከታየቻችሁን ዞር ብላችሁ ተመልከቷቸው፡፡ የት እንዳሉና ምን እየሰሩ እንደሆነ አጥኗቸው፡፡ አውሮፓውያኑ የሉተር ኢየሱስ የፈጠረው እግዚአብሔር የለሽ ትውልድ ነው ያፈራው፡፡ ስለዚህ መሰረቱ አሸዋ የሆነው ጎርፉ ሲመጣ ተጠራርጎ የሚወድቅ ስለሆነ ነው፡፡ ኋለኛው ዘመን ደግሞ ይህ እንደሚፈጠር ቀድሞ ተነግሮናል፡፡ አውሬው አሸዋ ላይ ቆሟል ራእ 12 ፡፡ ስለዚህ አሸዋ ላይ የቆመ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ የት እንደሚጣል ግልጽ ነው፡፡ አሸዋ ስለበዛ ምርት አይገኝበትም፡፡ ምክንያቱም ምን ውሃ ቢጨመርበት መምጠጥ ስለማይችል፡፡ ስለዚህ በትንሹ አትርኩ፡፡ ሰነፎች አትሆኑ፡፡

   Delete
  2. ሉተር የፈጠረውና የሰበከው ኢየሱስ እኮ እየሰበከ ያለው ግብረሰዶምን ነው፡፡ አሜሪካንን መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለዚህ የሉተር ኢየሱስ ካልተሰበከ ብላችሁ ለምትደክሙ ሰነፎች እባካችው ምንጩን ተመልከቱት፡፡ ምንጩ ደርቋል፡፡ ምንጩ እያፈለቀ ያለው የሕይወትን ውሃ ሳይሆን የሕይወትን ሞት ነው፡፡ ለምን መነሻውን አንመለከትም፡፡ አውሮፓውያኑና አሜሪካኑ እየሆኑ ያሉትን መመልከት ነው፡፡ የሉተር ውጤት እኮ ነው ይህ የምንመለከተው፡፡ ምንም እንኳን ለስጋና ለደም ጥሩ ቢሆንም ግን የሕይወት ውሃ ግን አልቆባቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያናቸውን እየሸጡት ነው፡፡ ዳንስና ዳንኪራ ቤት ሆኗል፡፡ ካዲያ ሀገራችሁ እንደዚህ አይነት እንድትሆን ነው እየሰራችሁ ያላችሁት፡፡ አዲስ ጌታ የለም፡፡ ጌታ አንድ ነው፡፡ ሐይማኖትም አንድ ነው፡፡ ለአረም ብዙ መድከም አያስፈልገውም በራሱ ይበቅላል፡፡ በተዋህዶ የከበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተዋሉን ይስጣችሁ፡፡

   Delete
 4. Thank you aba selama. Aynachenen eyegelexachehut newe. Yegna sewech xenquway ena metetegnoch yetagorubet esunm ended xebeb eyeqoteru yemishelelubet wengelen eyasayu Zemen yemayeshager teret (gedel) yemisebku zore belew sewechen lemasaded be tsewa seem yemisebasebu ye admegnoch sebeseb yebezabet honal. Ebakachehu meche yihon krstosen yemenemeslew?

  ReplyDelete
 5. Enat lelijua mit astemarech. ....

  ReplyDelete
 6. Mawgez maberaer mefeth aydelam baselten akhed mwret zemnwenaet new bahola betam ascger new

  ReplyDelete
 7. እንዴት ሆኖ ? ምጽአት ሳይደርስ? የአብ ቃል ሳይፈጸም? አውሬው በምድር ሳይነግስ? ይሄማ አይሆንም? የተኩላው ወንጌል መቼም ቢሆን ሊዳፈን አይችልም፡፡ ግን መቀነስ ከተቻለ እንጂ ቃሉም አይልም፡፡ ቃሌ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይሻላል እኮ ነው የሚለው፡፡ ወንጌል ይሰበካል የተባለው እኮ እውነተኛው ወንጌል ማለት አይደለም፡፡ ማስተዋል ይፈልጋል፡፡ እንደእናንተ አይነቱ ተኩላውንም ጭምር ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. አባ ስለማዎች ፀረ- ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ስለመሆናችሁ ከራሳችሁ አንደበት በራሳችሁ ፍቃድ እየሰማን ፤ እያየን ነዉ፡፡ ለዚህም ተሐዲሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ብላችሁ ፀረ ቤ/ክንን ቡድን መመስረታችሁን እናዉቃለን፡፡ይህ የነበረ የጥንተ ጠላት የዲያብሎስ ድምፅ ነዉ፡፡ ዲያብሎስ በዚህ ስሙ እና ግብሩ ፍፁም በሚቃረነዉ አባ ሰላማ ብሎግ አዉሬዉ ከአፉ የሞት ዉሃ እየተፋ ነዉ፡፡ መጽሐፍ እንደሚለዉ ሁለት አይነት ምልክቶች በንጽጽር ቀርበዋል አንዱ የታወቁዉ ከእግዚአብሔር የሆነዉ የመዳን ምልክት ነወ፡፡ ይህ ታላቅና አስደናቂ ምልክት ቅድስት ድንግል ማርያምንና ቅዱስ መስቀሉን ይመለከታል ቅዱስ የሐንስ በራዕዩ ምዕ 12 ሴቲቱንና ዘንዶዉን በገለጸበት አንቀጽ እንዲህ ነዉ ያለዉ "ታላቅ እና አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታዩ ፀሐይን (ክርስቶስ) የለበሰች፤ ጨረቃ (ቅዱሳን) ከእግሮ በታች የሆኑላት በራ ላይ ዐሥራ ሁለት ከዋከብት ያሉት አክሊል የደፋች አንዲት ሴት ታየች " ምዕ 12 ቁ 1 ካለ በኋላ ሁለተኛዉንና ሌላ የተባለዉን ክፉዉን ምልክት ሲገልጽ ደግሞ ምዕ 12 ቁ2 "ከዚያም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ………….ልጁዋን ለመዋጥ ፈልጎ ዘንዶዉ ልትወልድ በተቃረበችዉ ሴት ፊት ቆመ" ቁ5 እርም ህዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛዉን ወንድ ልጅ መለደዉ ይላል፡፡ ስለዚህ እናንተ የቅዱሳን እና የመስቀል ጠላቶች እና ሌላ የተባለዉ ምልክት ጉዳይ ፈጻሚዎች በመሆናችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶች ናችሁ በመሆኑም የቅድስት ቤ/ክ ጠላቶች ናችሁ፡፡ ሃይማኖት እንደ ቁሳቁስ ወይም እንደዚህ ዓለም ህግ በየጊዜዉ አይታደስም፤ እናንተ ግን በመጨረሻዉ ዘመን የትንቢት መፈጸሚያ በመሆናች እናዝናለን ፡፡ እንደ መዥገር ተጣብቀችሁ የቤ/ክንን ደም የምትመጥጡ እናንተ ተሐዲሶዎች ከቤ/ክንን ሆዲ የምትወጡበት ቀን ቅርብ ነወ፡፡ የስድብ አፋችሁን በንጽህ መሬት ላይ አስከመቼ ትረጫላችሁ " ዘንዶዉ ጥቂት ዘመን እንደቀረዉ አዉቆ ወደ እንተ ወርዶአል" ተብለናልና ምዕ 12 ቁ13-17 ተመልከቱ "ዘንዶዉ ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችን ሴት አሳደዳት፡፡ ሴቲቱም በበረሃ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንዲትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክፎች (ንጽሀ ስጋ እና ንጽሀ ነፍስ) ተሰጣት……ይህም ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘምን ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ እነድትኖር ነዉ…... እባቡም ሴቲቱ በጎርፍ ተጠራርጋ እነድትወሰድ እንደ ወንዝ ያለ ዉሃ ከአፉ ተፋ" እንደ ተባለ እናንተ ተሀዲሶ መናፍቃን ሁሉ ቅድስት ቤ/ክንን ማስደድ ክርስቶስን ማሳደድ መሆኑን ስለምታወቁ በንስሃ ተመለሱ ቤ/ክንን ግን ሌላ ምልክት፤ ሌላ ትምህርት፤ ተሀዲሶ አያስፈልጋትም፤ በታወቀዉ ምልክት፤ በታወቀዉ ዶግማ፤ ቀኖናና ስርኣቷ ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች "ምድር ግን ሴቲቱን እረዳቻት፤ አፉዋንም ከፍታ ዘንዶዉ ከአፉ ያፈሰሰዉን ወንዝ ዋጠች" ይላል፡፡ ስለዚህ የመዳን ተስፋችሁን አታጨልሙ ተመለሱ፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ራሳችሁን ቻሉ ከቤ/ክንን ትከሻ ላይ ወረዱ፤ የበግ ለምዳችሁን አዉልቁና ወደ አባታችሁ ዲያብሎስ በግልጽ ተቀላቀሉ እላለሁ፡፡ እኛ ቅድስት ቤ/ክንን ልጆች እናንተን ጸረ ቤ/ክንን ቡደኖችንና ግለሰቦች እንዲሁም አስተምሮአችሁን በሙሉ አንቀበልም፡፡ ስለዚህ ባለፈ የተሀዲሶ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዲዮስ የተወገዘዉ አባ ሰላማ ብሎግ እና ግብረአበሮቹ መጀመሪያ በሁሉም የተወገዙ ይሁኑ፡፡ በተመሳሳይ ከቤ/ክንን እዉቅናና ፍቃድ ዉጭ በቤ/ክን ስም በወንጌል ሳይሆኑ በወንጀል የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ከነ ሀሳባቸዉ እና ብሎጎቻቸዉ ይዘጉልን እስከ ጊዜአቸዉ ግን እኛ ከእነርሱ እርሾ እንጠንቀቅ እላሉ፡፡

  ReplyDelete