Monday, October 26, 2015

ሊቁን በረኃብ የምትቀጣ መናፍቁን በጥጋብ የምታቀናጣ ቤተ ክርስቲያንቤተክርስቲያናችን ብዙ ጉድ የሚታይባት፣ ፍትሕ የጎደለባት፣ ዘረኛነት የተንሰራፋባት፣ የዘመድ አዝማድ ሥራ ሥር የሰደደባት፣ ሊቃውንቷ አፋቸው የተሸበበባት፣ መናፍቃን እንደልባቸው የሚፋንኑባትና ደረታቸውን ነፍተው ኑፋቄያቸውን የሚያራግፉባት፣ እውነተኞች የሚወገዙባትና የሚሰደዱባት፣ ሐሰተኞች የሚነግሡባትና የከበሬታ ስፍራ የሚያገኙባት ቤተ ክርስቲያን ከሆነች ውላ አድራለች፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ችግሮቿ ነጻ እንድትወጣ የሚተጉላት ልጆቿን “ተሐድሶ መናፍቅ” እያለች በአንጻሩ ችግሮቿን የሚያባብሱትንና ነዳጅ የሚጨምሩበትን ትምህርታቸውም ቀና ያልሆነውን “የእፉኝት ልጆች”ን ኦርቶዶክሳዊ እያለች የቁልቁለት ጉዞዋን ቀጥላለች፡፡ እዚህ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሲባል በልማድ እንደሚጠራው ሕንጻውን ግንቡን ሳይሆን በተለይ መሪዎቿንና አስተዳዳሪዎቿን የሚመለከት ነው፡፡ “እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት” (ማቴ. 18፥17) ሲል ለመሪዎቿ መሆኑን ያሳያልና፡፡   
ይህን ከላይ በንጽጽር የቀረበውንና ቤተክርስቲያን ውስጥ በገሃድ እየታየ ያለውን እውነታ ተጨባጭነት በምሳሌ ማስገንዘብ ቢያስፈልግ፣ ከወራት በፊት በሊቁ በመምህር አሥራት ላይ የደረሰውን በደልና ለመናፍቁ ለኀይለጊዮርጊስ የተደረገለትን እንክብካቤ በንጽጽር ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ መምህር አሥራት የቅኔና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅና በርካታ ደቀመዛሙርት ያፈሩ መምህር ሲሆኑ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው፡፡ በእኚህ ሊቅ አገልግሎት ያልተደሰተውና መናፍቅ ናቸው ሲል በፈረጃቸው ማኅበረ ቅዱሳን የንስሐ ልጃቸው ሆና በቀረበች ሴት ተሰልለው በመቅረጸ ድምፅ እንዲቀረጹ ይደረጋል፡፡ እኚህ ሊቅ ዓይነ ስውር መሆናቸውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከቀረጸቻቸው በኋላ ተልእኮውን በሰጣትና በደብሩ ውስጥ ባለው የማኅበረ ቅዱሳን ክንፍ አማካይነት ወደሊቃውንት ጉባኤ ቀርቦ ሊቁ ተከሰሱ፡፡ ከሥራቸውና ከደመወዝ ታገዱ፡፡ 
 የማኅበረ ቅዱሳን አንዱ ችግር እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሃይማኖቱን በስለላ ሥራ ለመጠበቅ መሞከሩ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እውነትን የያዘችና በአደባባይ የምትሰብክ ስለሆነች በሌሎች ትሰለላለች እንጂ እርስዋ በማንም አትሰልልም፡፡ በሐዋርያት ሕይወት የታየውም ይኸው ነው፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ በሌሎች መሰለላቸውን ነው የተናገሩት እንጂ እነርሱ ቤተክርስቲያንን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ወንጌልን በይፋ ከመስበክ በቀር የስለላ ድርጅት አላቋቋሙም (ገላትያ 2፥4 ይመልከቱ)፡፡ ማቅ ግን ክርስቲያናዊ ማኅበር ስላልሆነ ስለላን ሃይማኖቱን የመጠበቂያ ዋና ስልቱ ነው፡፡ በዚህ መንገድ በርካቶችን አባቶችና ወንድሞች ሰልሎ ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ አድርጓል፡፡ በዚህ አድራጎቱ ድል እንዳገኘ ቢቆጥርም ቤተክርስቲያንን ግን በእጅጉ ጎድቷታል፡፡ የሰለላቸውና ከቤተክርስቲያን ያሳደዳቸው ሁሉ የተሰደዱበትን እውነት በነጻነት እንዲገልጡና ብዙዎችን እንዲያፈሩ ነው ምክንያት የሆነው፡፡ አያሌዎችም ከቤተክርስቲያን እየፈለሱ ወደሌሎች ሃይማኖቶች እንዲገቡ ነው ያደረገው፡፡ ይህም የቤተክርስቲያኒቱ ምእመናን ቁጥር እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይታመናል፡፡ ከዚህም የምንረዳው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን የጠቀመ መሆኑ ባይካድም ቤተክርስቲያንን ግን ከጠቀመው ይልቅ የጎዳው የሚበልጥ መሆኑን ነው፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ ከስሕተቱ የማይማረው ማቅ ዛሬም ከዚያው የስለላና የማሳደድ ስራው ያልወጣ መሆኑ ነው፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያት በእርሱ ተጽዕኖ ሥር የወደቁና ፈቃዱን ለመፈጸም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ አንዳንድ ጳጳሳትም የዚሁ አካሄድ ሰለባ ሆነዋል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ መንገድ ወንጌልን ማገድ የሚቻል መስሎት ከሆነ ይቀጥል፤ ወንጌል እንደሁ መሮጡና መፍጠኑ ብዙዎችንም ወደክርስቶስ መመለሱ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት መካከልም መሆኑ እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡

ወደ መምህር አስራት ጉዳይ ስንመለስ ከንስሐ አባቷ ይልቅ “ቤተክርስቲያኗ” ለሆነው ለማኅበረ ቅዱሳን የታመነችው ያች ሴት መምህሩ የሚከሰሱበትን ነጥብ ለመፈለግ ጥረት ያደረገች ሲሆን፣ በኤርምያስ 17፥5 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።” በሚለው ክፍል ላይ መምህር አስራት በሰጧት ማብራሪያ ክርስቲያን መታመን ያለበት በእግዚአብሔር ብቻ እንጂ በፍጡራን አለመሆኑን አስረድተዋታል፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ መታመን ያለብን እርሱ ብቻ አምላክ በሆነው በአንድነትና በሦስትነት ሲመለክና ሲወደስ በሚኖረው በእግዘአብሔር ብቻ ነው፡፡ በሌላ ማለትም በቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ጭምር እንዳንታመን ግን ታዘናል “ኢትተአመኑ በመላእክት ወኢ በእጓለ እመሕያው እለ ኢይክሉ አድኅኖ” እንዲል (መዝ. 146፥3)፡፡ በእውነት የሚፈርድ ስለጠፋ ግን በፍጡር የሚታመኑ አሳጋጅና አጋጅ ሲሆኑ፣ የታገዱት ደግሞ የቀናውን ትምህርት ያስተማሩትና መታመን ያለብን በእግዚአብሔር ብቻ ነው ያሉት መ/ር አስራት ሆኑ፡፡
መጋቤ ጥበባት አስራት ሌላው የተከሰሱበት አንድ መወድስ ቅኔ ነው፡፡ መወድሱ ይህንኑ ሐሳብ የሚያጠናክርና ሲሆን እንዲህ ይላል፡፡
መወድስ
ማርያም ኢክህለት ለአድኅኖ ኵሉ ዓለም
ውሉደ አዳም ወሔዋን ዘተወልዱ እም አዳም
ፍትሐ ኵነኔ ወሞት ወፍትሐ ቀዳሚ መርገም
ደሞ ከመ ይክዓው
ወልደ አብ እም ኢተሠገወ በሥጋ ድኩም
ጳውሎስ ከመ ይቤ
አምጣነ አልቦ ስርየት ዘእንበለ ይትከዓው ደም
ወዝ ኵሉ ለእመ ኮነ ከመ ቃለ መጽሐፍ ኅቱም
እፎኑመ ይትከሃል ለአድኅኖ ኵሉ ዓለም
ወእፎ ይብልዋ ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም
ዲበ ዕፀ መስቀል ዘቀራንዮ እስመ ኢተሰቅለት ማርያም፡፡
ትርጉም፦
ከአዳም እና ከሔዋን የተወለዱ የአዳም ልጆችን ሁሉ
ከምትና ከኵነኔ ፍርድ እንዲሁም ከመጀመሪያው መርገም ፍርድ ማርያም ማዳን ብትችል ኖሮ
ደሙን ያፈስስ ዘንድ ወልደ አብ በደካማ ሥጋ ሰው ባልሆነም ነበር፡፡
ጳውሎስ እንዳለው ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና
ይህ ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቃል የተዘጋ ቢሆን ኖሮ፣
ዓለምን ከገሃነም ማዳን እንዴት ይቻላል?
እንዴትስ ማርያምን የዓለም ሁሉ ቤዛ ይሏታል?
በቀራንዮ የዕንጨት መስቀል ላይ ማርያም አልተሰቀለችምና

ቅኔው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ እየተቀነቀነ ያለውን “ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” እና “ማርያም የዓለም ሁሉ ቤዛ ናት” የሚለውን ኑፋቄ የሚያርምና የወንጌልን እውነት የሚያብራራ መወድስ ነው፡፡ በዚህ ቅኔያቸውም በኋላ ላይ በጥምቀቱ መጽሔት ላይ በማርያም ስም ኑፋቄ ጽፎ እስካሁን ድረስ በማቅ ተጽዕኖ ምክንያት አስፈጻሚ ጠፍቶ ተግባራዊ ያልሆነ ውሳኔ የተወሰነበትን የኃይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄ ቀደም ብለው ያረሙ በመሆናቸው መመስገንና መሸለም ሲገባቸው በተቃራኒው እግዳ ተጣለባቸው፡፡ ኃይለ ጊዮርጊስ ላይ የተወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆንና ለኑፋቄው ተመጣጣኝ ምላሽ እንዳይሰጥ በማድረግ ውሳኔውን መሳቢያ ውስጥ አስቀምጦ መጋቤ ጥበባት አስራትን ማገድ በአባ ማቴዎስ ለሚመራው ጠቅላይ ቤተክህነት እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ 
እነዚህን ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የተመለከተው የሊቃውንት ጉባኤም ሊቁን አቅርቦ የጠየቃቸውና እርሳቸውም ስለተከሰሱበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሶ ማብራሪያቸውን ማስተባበል ያልቻለው “የሊቃውንት ጉባኤም” የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል ለማስተባበል የጠቀሰው በተአምረ ማርያም ላይ የበላኤሰብን ታሪክ መሠረት ካደረገው ከማሕሌተ ጽጌ ድርሰት ላይ መሆኑ ቤተክርስቲያኗ ከምን ላይ ነው የቆመችው ያሰኛል፡፡ ይገርማል! በቦሩ ሜዳው የሃይማኖት ክርክር ላይ “ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ስለ ሃይማኖት ተአምረ ማርያምን ትጠቅሳለህን?” ተብሎ የተአምረ ማርያም ቦታ የት መሆኑ የተነገረበት የሊቃውንት ጉባኤ ዛሬ ለተአምረ ማርያም የማይገባውን ቦታ ሰጥቶ መጽሐፍ ቅዱስን በተአምረ ማርያም ለማረም ሲጠቀምበት ከማየት የበለጠ “የክሕደት ቁልቁለት” እና ውድቀት ከወዴት ይመጣ ይሆን?
መጋቤ ጥበባት አስራትም የተጠቀሰላቸውን የማህሌተ ጽጌ ጥቅስ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንጂ እንደ ሃይማኖት እንደማይወስዱት ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የሊቃውንት ጉባኤው መ/ር አስራት በማኅሌት አገልግሎት ተመድበው እንዲሠሩና ደመወዛቸውም እንዲከፈላቸው ወሰነላቸው፡፡ ይሁን እንጂ ለማህበረ ቅዱሳን የቀኝ እጅ የሆኑትና በአሁኑ ጊዜ በሥራ አስኪያጅነታቸው ጠቅላይ ቤተክህነትን እያሽከረከሩ ያሉት የአባ ማቴዎስ ቡድን መጋቤ ጥበባት አስራት ከቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲታገዱ ደብዳቤ ጽፎ በሀገረ ስብከቱ በኩል ለየአድባራቱ እንዲበተን አድርጓል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው የማጣራት ሥራና የሚሰጠው አስተያየት ከግምት ገብቶ ውሳኔዎች በዚያ ላይ ካልተመሠረቱ የሊቃውንት ጉባኤው ተግባር ምንድነው? እነርሱ ያጣሩትን ከግምት እንኳ ባለማስገባት ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ከሳሽ የሆነበትን ጉዳይ በነአባ ማቴዎስ ማቴዎስ በኩል ደግሞ ዳኛ ሆኖ የሚፈርድ ከሆነ ፍትሕ የለም፡፡
ውሳኔው እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ እውነተኛ ዳኛ ጠፍቶ ነው እንጂ መጋቤ ጥበባት አስራት በቅኔያቸውም ቢሆን እውነትን በመመስከር የመናፍቁን የኀይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄ ነው አረሙት እንጂ የተለየ ነገር አላመጡም፡፡ የኃይለ ጊዮርጊስን ጽሑፍ ኑፋቄ ነው ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔውን ተከታትሎ ለኑፋቄው ተመጣጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ባያደርግም መጋቤ ጥበባት አስራት ቀደም ብለው በቅኔያቸው የእርሱን ኑፋቄ አርመውት ነበር፡፡ ግን በመመስገን ፈንታ ከቤተክርስቲያናቸው ለመታገድ ሰበብ ሆነ፡፡ ይህ የፍትህ እጦት የሚያመለክተው ማቅ የከሰሰው ሰው ነጻ ቢወጣና ቢፈረድለትም እንኳን ወደቦታው ተመልሶ እንዲሰራ ማድረግ በማቅ ዘንድ የማይሞከር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ እኚህ ሊቅ ውሳኔያቸውን የሚፈጽም አካል ጠፍቶ በፍትሕ እጦት እየተራቡና እየተጠሙ ነው፡፡ ታዲያ ይህች ቤተክርስቲያን (ፍትሕ የከለከሉት መሪዎቿ) ሊቃውንቷን በረኃብ የምትቀጣ መባል ይነሳት?
በአንጻሩ ለመናፍቁ ኃይለ ጊዮርጊስ የተደረገውን እንመልከት፡፡ ከዚህ ቀደም እንደተዘገበው ይህ ሰው በማርያም ዙሪያ ቤተክርስቲያን የማታምነውንና የማታስተምረውን፣ ማቅ ግን የሚያምንበትንና የሚቀበለውን የስሕተት ትምህርት በጽሑፍ ቤተ ክህነቱ ለጥምቀት ባዘጋጀው መጽሔት ላይ ታትሞ እንዲወጣ አደረገ፡፡ በኋላ ትምህርቱ ኑፋቄ ሆኖ በመገኘቱ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ቋሚ ሲኖዶስ ወደዚያ መራው፡፡ የሊቃውንት ጉባኤውም ኃይለ ጊዮርጊስ በዚያ ጽሑፍ ላይ ከ12 በላይ ኑፋቄዎች ማስፈሩን አረጋግጦ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና ኑፋቄን በተሞላው ጽሑፉ ላይ በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጥና ታትሞም እንዲወጣ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ ኃይለ ጊዮርጊስም ብዙ ካቅማማ በኋላ አማራጭ ስላልነበረው ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ከደመወዝ አልታገደም፤ ነገር ግን ከስብከተ ወንጌል ወደሌላ ክፍል ተዛውሯል፡፡ ከውሳኔው ውስጥ የሚጠበቀው ዋናው ነገር ለኑፋቄው የሚሰጠውና የሚታተመው ጽሑፍ ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ይህን ያደረጉት ደግሞ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስና ድርጅታቸው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ከማንም ስውር አይደለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ለእውነተኞቹ ሊቃውንት ሳይሆን ተአምረ ማርያምን ስለ ሃይማኖት ለሚጠቅሱ “ሊቃውንት” ነው ትልቅ ቦታ የሚሰጡት፡፡
እነርሱ ፍትሕ መስጠት ባይፈልጉም፣ እግዚአብሔር ግን ፍትሕ ሰጥቷል ማለት እንችላለን፡፡ አባ ማቴዎስ ሊቁን አባረው መናፍቁንና በሃይማኖት ካባ የተደበቀውን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ሃይለ ጊዮርጊስን ለማቀናጣት ቢሞክሩም ባለፈው ጊዜ በሊብያ በአይኤስ ለታረዱት ወገኖቻችን የሐዘን ሥነሥርዐት በተደረገ ጊዜ በአባ ማቴዎስ እንክብካቤ ሲደረግለት የኖረው ኃይለ ጊዮርጊስ መስቀል አደባባይ ድንጋይ ሲወረውር ተይዞ ለእስር ተዳረገ፡፡ ቤተ ክህነቱም ከሥራ ገበታው ላይ ያለፈቃድ በመጥፋቱ ማስታወቂያ አወጣበት ከሥራውም ተሰናበተ፡፡
ስለዚህ ቤተክርስቲያን የመ/ር አስራትን ነገር በቸልታ ማየት የለባትም፡፡ እኚህን ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ ሰው በማባረር ማቅን ማስደስት ካልሆነ በቀር የምታገኘው ጥቅም የለም፤ በብዙ ግን ትጎዳለች፡፡ በመሆኑም ሌላው ቢቀር የሊቃውንት ጉባኤ ባጣራው ላይ የተመሠረተ ፍትሕ ማግኘት ያለባቸው መሆኑ የሚጠበቅ ነው፡፡ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ ጉዳያቸው ታይቶ  ከእርሳቸው እገዳ በስተጀርባ ያለውን የማቅ ፖለቲካ ማክሸፍ ይገባል፡፡ አሊያ ቤተክርስቲያን ወደባሰ ችግር መሄዷ አይቀርም፡፡

17 comments:

 1. "ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማእ" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

  ReplyDelete
 2. ምነው ፈራችሁ? መናፍቅን ተሸከሙ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም ተኩላው ከበጉ ካልተለየ እንዴት የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሊሆን ይችላልን? ደግሞ በኋላኛው ዘመን ሐይማኖታቸውን ይክዳሉ እንጂ የተባለው ሐይማኖታቸውን ይጠብቃሉ አልተባለም፡፡እግዚአብሔር እንግዲህ የተሳዳቢዎችን አፍ ሊዘጋልን ነው መሰለኝ ስራውን እየሰራ ነው፡፡ እኛም እንጸልያለን እናንተም ስድባችሁን ቀጥሉበት፡፡ የእኛ ስራ ጸሎት ነው፡፡ የእናንተ ስራ ደግሞ ስድብ ነው፡፡ እስኪ እግዚአብሔር ጸሎት ነው የሚሰማው ወይስ ስድብ የምናመልከውን ጌታ የምናይበት ጊዜ ነው፡፡ በእርግጥ አውሬው ሁልጊዜ ጌታን የቀደመ እየመሰለ ፊት ፊት እየሄደ ስራውን እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ ይሁንና የተዋህዶ አምላክ መድሀኒያለም ኢየሱስ ክርስቶስን ግን ማንም ሊቀድመው አይችልም፡፡ ስራውን የሚሰራው በጊዜው ነው፡፡ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን የናንተ ካንሰር ናቸው አይደል፡፡ እኔስ ይህ ማህበር እንዳሳዘነኝ፡፡ ደግሞ ደስ እንዳለኝ እንደዚህ ለእውነትና ለዓላማ ዋጋ መክፈል፡፡ በዚህም ዘመን የሚከፈለው ሰማእትነት በጣም ነው የሚያስደስተው፡፡ እኔማ እስከአሁን አባል አልነበርኩም፡፡ አሁን ግን አባል መሆን አስፈለገኝ ከእነርሱ ጋር አብሮ የሰማእትነትን በረከት መውሰድ፡፡ የናንተን ብሎግ መከታተል ስጀምር እነርሱን የበለጠ እንደወዳቸውና የእነርሱ አባል እንድሆን ስላደረጋችሁኝ አመሰግናቸኋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 3. አእመረ አትድከም ቀንህ አልቋል መናፍቃን ሁላ እርር በሉ ስለ አሥራት ብዙ መረጃ አለን ከማርቆስ ጀምሮ እናወጣዋለን ምናልባትም አንተም ልትኖርበት ትችላለህ፡፡

  ReplyDelete
 4. አሥራት በድንቁርና የወለደህና የወለድከት ነው

  ReplyDelete
 5. "ደሙን ያፈስስ ዘንድ ወልደ አብ በደካማ ሥጋ ሰው ባልሆነም ነበር"፡፡እንዴ የነሣው የመላእክትን ሥጋ ነበር እንዴ? ማርያም ቤዛዊት ዓለም መጀሪያ ሊቅያላችሁት ራሱ ቅኔን ይጠንቅቅ፡፡ ጌታ የድንግል ማርያምን ሥጋ ለብሶ ነው ዓለምን ያዳነው፡ቅኔውም ይህንን ነው የሚያመሰጥረው፡፡ ባይዋጥላችሁም፡፡

  ReplyDelete
 6. የናንተ ሊቃውንት ደግሞ የትኞቹ ይሁኑ? አንድጊዜ ሊቃውንት ትሳደባላችሁ አንድ ጊዜ ደግሞ ተቆርቋሪዎች ትሆናላችሁ፡፡ እናንተ የት ሄዳችሁባቸው ነው ደግሞ የናንተ ሊቃውንት የሚራቡት? አይ ኘሮቴስታንቶች አሁን የሰው ቤት ገብታችሁ እንደዚህ ማዳከራችሁ ያስቀኛል፡፡ በእርግጥ ልክ ናችሁ ለአላማችሁ የምትዳርጉትና የምትከፍሉት ዋጋ እንደዓለማ ሲታይ አስተማሪ ነው፤ የዋህ ቤት አገኛችሁና ተጫወታችሁበት፡፡ ለዚህ ነው ተኩላው ከበጉ መሀል ካልወጣ ቤተክርስቲያን ሰላም አይኖራትም፤ የተኩላው ባህሪ ደግሞ ሙስና፣ዝሙት፣ማስመሰል፣ዘረኝነት ስለሆነ ለዚህ ነው ውግዘት የሚያስፈልገው፡፡ ስለዚህ እውነተኞቹ ሊቃውንት ቢራቡም ረሀቡ አይበግራቸውም፡፡ ይህ ሁሉ እኮ የተፈጠረው እናንተው የፈጠራችሁት የተኩላው ባህሪ ነው፡፡ የሉተር ኢየሱስ ካልተሰበከ ብላችሁ፡፡ ወንጌል አላችሁ እስኪ እንያችሁ ተብሎ ሲታይ እንደዚህ አይነት ተኩላ ሆናችሁ ታያችሁ፡፡ የእናንተው ውጤት ነው፡፡ ምን ይደረግ፡፡

  ReplyDelete
 7. የሰይጣን ማጉረምረም ዛሬ አልተጀመረም።ተሳዳቢዎች!

  ReplyDelete
 8. ዉሾች ሆይ! በሰውየው አይነሥውርነት አዝናለሁ። ክህደትን የሚፈፅመውና የሚሰራው ግን በልቦናው ነውና መናፍቅ ሆኖ ከተገኘ ቦታ የለውም። ሊቅ ለምትሉት የናንተው ክህደት ምንፍቅና ሊቅ ሆኖላችሁ ይሆናልና ተሸከሙት።
  ቤተ ክርስቲያን እናንተን አታውቃችሁም። እናንተም የሷ አይደላችሁም። ወንጌል አሉባልታ፣ ውሸት፣ የፈጠራ ወሬ፣ ስም ማጥፋት፣ ሳያምኑ ማሥመሰልና ሥጋዊ አሥተሳሰብ አይደለም። እናንተ ወንጌል የምትሉት ሐዋርያት ያልሰበኩትንና ከመፅሐፍ ቅዱስ የወጣ ባዶ የቃላት ጨዋታ ነውና በቤተክርስቲያን ቦታ የለውም የላችሁም።
  መናፍቆች ህይወት በማይሆናችሁ ከንቱ ሥድብ ከመመላለሥ ምናልባት ምህረት ቢሆናችሁ እራሳችሁን ሆናችሁ አዳራሽም ቀለሳችሁ ዳስ ያመናችሁበትን ብታራምዱ ይበጃችኋል። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የክርስቶስን አምላክነት ለሚያምኑ፣ የቅዱሳኑን ክብርና አማላጅነት ለሚያምኑ ናት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Damot......................................trash as usual

   Delete
  2. Be Egziabher Amsal yetefexeren sewe wesha ? Be ewnet edmea lekachenen yeselexenbet Sedebn Keman endetemarnew enja. Tehadeso .... Ayasfelegenem? Lenegeru krstosenes keneberubet emnet tenestew egziabher weldnetun mech tekebelut? Zaream beteret ena beafetarik betetebetebe ewnetu krstos yemayesebekebet emenet zemenen liwaj yichelal? Ewnet temeralech gen mewax alebat. Kekerstos qedusan ena semaetat beyebelx mesebek alebachew? Zare arseama adanechegn , anegagerechegn, teamer .....tederege yemil mahbereseb moltonal yehenen bewengel adagnu mane endehone lenastemerew ayigebam? E/r yihunen enji bezi huneta addisun tewled lenewajew endet yichalenal?

   Delete
 9. yemote bilog , yemiyadamitachihu binor yesintun sem atefachuh:: wushet endehon yegiber abatachihu newu:: ahuns enquwan sewu diyabilosem yemayawuqewun haset eyetenagerachihu newu

  ReplyDelete
 10. እኔ እውነተኛ መሆናችሁን የማደንቀው ማንም በጨለማ ያለ ሁሉ የስድብ አስተያየት ሲሰጥ ታወጡታላችሁ ሌሎቹ የማህበረ ቅዱሳን ድህረ ገጾች ግን እነሱን የሚደግፈውን አስተያየት ብቻ ነው የሚያወጡት እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ የማይጠፋ እሳት ነዷል እግዚአብሔር አምላክ ስሙ ይባረክ።

  ReplyDelete
 11. Alemayhu. Tadiya ante ezih blog lay min teseralh.ene yemitekmegn wesdalhu n
  Yemaytekmegne tewalhu.tesadabi yediabilos lij bicha new

  ReplyDelete
 12. ኢይሱስ ጌታ ነው ተንጫጩ የተረት ልጆች

  ReplyDelete
 13. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk,,,,,,,,,let me tell u one thing,, change the name of ur blog,, unless abune selama will let u down soon. Dont disseminate ur setanic ideas in the name of our beloved father,,abune selama. Now is the time that u guys wil be washed out from the church by jesus. u have made the church cave of thieves,, dont u think that the lord of the church willnt act upon u?? God will REALLY ACT UPON U unless u stop seeding ur yeast of "nufake". MAY ABUNE SELAMA STOP U FROM ..............................

  ReplyDelete
 14. ‹‹ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል››!
  መሪጌታ አስራት ከተወገዙ 8 ወራት ተቆጥረዋል፡፡ሲወገዙም ዝም ብሎ አይደለም፡፡የለጠፋችሁት ቅኔ አንድ ማስረጃ እንጂ ብቸኛ አይደለም፡፡ነገሩ እንዲህ ነው!ሰውየው የመጻሕፍትና የቅኔ ሊቅ፣ሁለገብ ባለሙያ መሆናቸው እውነት ነው፡፡ይሰብካሉ፣ይቀኛሉ፣ያስተምራሉ፣ያመራሉ፣ማኅሌት ይቆማሉ፡፡ሙሉ መሪጌታ ናቸው፡፡ይህ ምልዐት የተናገሩትን ሁሉ ትክክል ያደርገዋል ማለት አይደለም፡፡4 ዐይና ጎሹ ቅባት ነበሩ፡፡አለቃ ተክለጽንን ያህል ሊቅ ጸጋ ነበሩ፡፡ስለዚህ ሊቅ መሆን ከኑፋቄ አያድንም፡፡
  መሪጌታ አስራት በምስጢረ ስጋዊ በኩል ወይም በምስጢረ ሥላሴ ኑፋቄ ቢገኝባቸው ከቀደሙት ምሁራን መናፍቃን ጋር ክብር እንሰጣቸው ነበር፡፡እሳቸው ግን ገና ከጎጃም ጀምሮ ችክ ያለ የተራ ወያላ ‹‹ታማልዳለች›› ‹‹አታማልድም›› ክርክር ሲናገሩ ኖረው የኋላ ኋላ በድፍረት በዓደባባይ መናገር ጀመሩ፡፡ተው ሲባሉም የትምክኅትና የስላቅ ቃል ሆነ የሚናገሩት፡፡የእናንተ አጨብጫቢነትም ልብ ሰጣቸው፡፡ስለ እመቤታችን አማላጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚነገር አስመስለው ነው የሚያወሩት፡፡እሳቸው ማየት የተሳናቸው ናቸው፡፡ኢንተርኔት አያዩምና ካቶሊኮች፣የምስራቅ ኦርቶዶክሶች እና የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት ስለእመቤታችን ያላቸውን አስተምህሮ እንዲያውቁት ለማድረግ ተሞክሮ ነበር፡፡እሳቸው ግን አልሰሙም፡፡የአማላጅነት አስተምህሮ እዚሁ የተፈጠረ የባልቴት ተረት እንደሆነ ጥንት ጎጃም ሳሉ ከፕሮቴስታንታውያንን የሰሟትን ይዘው ታበዩ፡፡ቅኔ ተቀኙ፡፡
  ቅኔው ተመዝግቦ ለሚመለከተው አካል ደረሰ፡፡እሳቸው ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አስመስለው አቡነ ቀሌምንጦስን ደጅ መጥናት ጀመሩ፡፡አቡነ ቀሌምንጦስ የሊቃውንት ጉባኤን ውሳኔ እንዲጠብቁ ነገሯቸው፡፡ጉባኤው ክሱን አጣርቶ መሪጌታ አስራትን የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ ጠራቸው፡፡መጀመሪያ ላይ እመቤታችን በአፀደ ሥጋ እንጅ በአፀደ ነፍስ አታማልድም ብለው በድፍረት ተናገሩ፡፡ቆይተው ደግሞ ሳላውቅ ነው፤ተፀፀትኩ ብለው ይቅርታ ጠየቁ፡፡ጉባኤው ግን በፀፀታቸው ስላላመነበት ቃላቸውን መዝግቦ ደሞዛቸው ሳይነካ ለ2 ዓመታት ቀኖና ተሰጥቱዋቸው እንዲታገዱ ወሰነ፡፡ውሳኔውን ለቋሚ ሲኖዶስ አቀረበ፡፡ቋሚ ሲኖዶስ በበኩሉ በእሳቸው ደረጃ ያለ ሊቅ እንዲህ የጎላና የተረዳ ኑፋቄ ሳያውቅ ይፈጽማል ተብሎ ስለማይገመት 2 ዓመት ከማንኛውም ስራና ደሞዝ እንዲታገዱ ብሎ የሊቃወንት ጉባኤን ውሳኔ አሻሽሎ በውግዘት አፀናው፡፡
  ከዚህ ውጭ አቡነ ማቴዎስ፣ማኅበረውዱሳን ገለመሌ አትበሉ፡፡ከጎጃም ጀምሮ ዳኅጸ ልሳን እንደሚያበዙ እና የጀብደኝነት መንፈስ እንዳለባቸው በደንብ እናውቃለን፡፡አሁንም ችግራቸውን ዘርዝረውና ያሉበትን ሁኔታ አስረድተው ለእለታዊ ፍጆታ የሚሆን ተቆራጭ ቢጠይቁ አባቶች የሚጨክኑ አይመስለኝም፡፡እናንተ እሳቸውን የምትፈልጓቸው ለመርዳትና ለመንከባከብ በማሰብ ሳይሆን ቤ/ክ ላይ ለምታካሂዱት አመጻ መናጆ ለማድረግ ነው፡፡ለእሳቸው ካላችሁ ኀዘኔታ ይልቅ ለቅድስት ቤ/ክ ያላችሁ ጥላቻ የጠለቀ እንደሆነ እናውቃለን፡፡
  ከፕሮቴስታንት በላይ ፕሮቴስታንት ሆናችሁ በወለጋ ያለውን የኦርቶዶክሳውያን ፕሮቴስታንታውያን መሳደድ እንደ ወንጌል ገድል ሰሞኑን ስትዘግቡ አይተናል፡፡ሰው የሚያነባችሁ ለትዝብት ነው፡፡ለመማር አይደለም፡፡ዝንጥ ያላችሁ ፕሮቴስታንት መሆናችሁ ይታወቃል፡፡ከፕሮቴስታንት በጥቂቱ የምትለዩት የኛ ሀገር ፕሮቴስታንቶች በአንጻራዊነት አንደበታቸው ለስላሳ ሲሆን የእናንተ ግን ለስድብ እና ለስም ማጥፋት የተፋጠነ እንዲሁም የቤ//ክ ስም ያከፋልናል ያላችሁትን ነገር ሁሉ አዥጎድጉዳችሁ በማቅረባችሁ ነው፡፡ፕሮቴስታንቶች ቢያንስ ለተወሰኑ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊና ሀገራዊ አስተዋጽኦዎች እውቅና ሲሰጡ እናንተ ግን ሁሌም ከፕሮቴስታንት በላይ ፕሮቴስታንት መሆናችሁን ለማሳየት እንቅልፍ የላቸውሁም፡፡ደግነቱ ሁሉም ያውቃችኋል፡፡
  ለማንኛውም የኔታ አስራት የባሰ ችግር ከገጠማቸው ማመልከቻ ያስገቡ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ ጨካኝ አይደለችም፡፡ተፀፀችለሁ ወዳሉበት እምነት ተመልሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቅ መሰኘትን ከፈለጉ ግን የሚያዋጣው አዲስ ቤት መፈለግ ነው፡፡ቤቱ የእመቤታችንን አማላጅነት ሳይቀበል በዓለማዊነት በተገራው ፕሮቴስታንት ዘይቤ ለሚታበይ ሰው ቦታ የለውም፡፡ከዓለም ክርስትና 30 በመቶ እንኳ ሳይሸፍን ‹‹የዓለም ሕዝብ የሚያምነው›› እያለ በሚመጻደቀው ፕሮቴስታንቲዝም አስተምህሮ ከተቃኙ ወዲያ የኦርቶዶክስ ሊቅ መሰኘት የለም፡፡ዋነኛ ዓላማው መቃወም የሆነው ፕሮቴስታንቲዝን ዓለምን ወዴት እንደመራት ለማወቅ አሜሪካን ማየት በቂ ነው፡፡ካስፈለገም የእስካንዲቪኒያን ሀገሮችና ጀርመንን፡፡ሁሉም ዓለማዊነትና ግብረ ሰዶም የገነነባቸው ናቸው፡፡ይብዛም ይነስም ዛሬ ለዓለም ሞራል መጠበቅ ተሸለው የተገኙት ካቶሊካውያንና ኦርቶዶክሳውያን ናቸው፡፡መሪጌታ አስራት ስለነዚህ ዕምነቶች የአማላጅነት አስተምህሮ ለመረዳት ከሀገራዊ ሊቃውንት ጽሑፎች በተጨማሪ ኢንተርኔቱንም በማሰስ የሚረዳቸው ሰው ቢኖር ጥሩ ነው፡፡81ዱ መጻሕፍትን የበላሁ ነኝ ብሎ ሲመኩ ከቆዩ በኋላ በሊቃውንት ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ፊት ሐሳብ እየቀያየሩ መቸገር አያሥፈልግም፡፡እናንተ ግን ሰውየውን መጠቀሚያ ለማድረግ አታሽቃብጡ፡፡የከረመ ወሬ ሰምታችሁ እብደት ውስጥ አትግቡ!‹‹ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል›› እንዲሉ አበው!

  ReplyDelete
 15. እሰይ።።።።።
  እኔ እኮ አባቶቻችን መስራት አቁመዋል እያልኩ ነበር። ለካ ይወስናሉና። እሰይ። እኒህን አስመሳይ ሃራጥቃ መናፍቃን ከቤተክርስቲያኗ ንቀሉልን።

  ReplyDelete