Wednesday, October 28, 2015

ሐራ ዘተዋሕዶ ለአባ ሳሙኤል የገጽታ ግንባታና ኑፋቄን የመሸፈን ሥራ እየሠራች ነውአባ ሳሙአል ግብረ መንፈስ ቅዱስ በተባለ መጽሐፋቸው ላይ ኑፋቄና የድርሰት ስርቆት ፈጽመዋል ተብሎ በብሎጋችን በቅርቡ ቀሲስ ፈታሒ በተባሉ ጸሐፊ ይፋ የተደረገው ጽሑፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት ጥቅምት 16 ቀን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን “አዋልድ” የሚል ስም የሰጧት የማቅ ብሎግ ሐራ ዘተዋህዶ ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም. በልማትና ክርስቲያናዊ ኮምሽን የተሰጠውን ሥልጠና ይዛ በመውጣት ለአባ ሳሙኤል ያላትን አጋርነት አሳይታለች፡፡ ሥልጠናው የተሰጠው ከአራት ቀናት በፊት ቢሆንም ለወሬ ማንም አይቀድመኝም የምትለውና ወሬ ቢበዛባት እንኳ በሰዓታት ልዩነት እያከታተለች ወሬውን እየገለበጠችና እያጋነነች ማውጣት ልማዷ የነበረው ሐራ ከአራት ቀናት በኋላ የተከናወነውንና በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት መቅረቡና አስፈላጊነቱ ያን ያህል የሆነውን የልማት ኮምሽኑን የሥልጣና ወሬ ይዛ መውጣቷ በኑፋቄና በድርሰት ስርቆት ጥያቄ እየቀረበባቸው ያሉትን የአባ ሳሙኤልን ገጽታ ለመገንባት መሆኑን ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች ይናገራሉ፡፡

ለተዋሕዶ ሃይማኖት ከእኔ በላይ ለአሳር የምትለውና ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ የቆመውን ማንኛውንም ሰው በሃይማኖት ችግር በመክሰስ አለስሙና አለግብሩ ስም ለመስጠትና ግብሩን ለማክፋት ተወዳዳሪ የሌላት ሐራ በተዋሕዶ እምነት ላይ ኑፋቄ ያመጡትንና ከአንድ ሊቀጳጳስ በማይጠበቅ መልኩ የሌሎችን ድርሰት እየቆነጻጸሉ በስማቸው በማሳተም ቤተክርስቲያንን አንገት ያስደፉትን አባ ሳሙኤል እንዲጠየቁ በማድረግ ፈንታ ምንም እንዳልተፈጠረና ሃይማኖት እንዳልፈረሰ በማስመሰል ገጽታቸውን መገንባት ይዛለች፡፡ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳን ለሃይማኖት ያልቆመ የፖለቲካ ድርጅት ነው የምንለው እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ከሚሠራውና ከሚያደርገው በመነሣት ነው፡፡ ለሃይማኖት ቢቆም ኖሮማ አባ ሳሙኤል የተዋሕዶን እምነት ሲንዱት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን ሲያዋርዱና ሌሎችንም ሃይማኖታዊና ሥነምግባራዊ ኑፋቄዎችንና ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ዝም ባላለም ነበር፡፡ ለዓላማው ሲሆን ግን በሕይወት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ጌታን አገልግለው በክብር ያረፉትንና ስማቸውና ግብራቸው ከመቃብር በላይ ውሎ ለብዙዎች አርኣያና ምሳሌ የሆኑትን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ጭምር ለማስወገዝ እንቅልፍ አልነበረውም፡፡ ለአባ ሳሙኤል ሲሆን ግን ዝም ማለት እንኳን ሲገባው በሐራ ብሎጉ ላይ ገጽታቸውን ለመገንባት ሲል የሰነበተና የጠነዛ በዚህ ወቅት ማንም ሊያነበው የማይፈልገውን የሥልጠና ወሬ ዜና አድርጎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱም በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ አባ ሳሙኤል ለማኅበሩ የዋሉለትን ውለታ በማሰብና አሁንም በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ነገሮች ማቅ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄዱ ለማድረግ የአባ ሳሙኤልን አጋርነት ስለሚፈልግ ነው እንዲህ ያደረገው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ሳሙኤል የደረሰባቸውን መጋለጥ ለመሸፈንና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የእርሳቸው ጉዳይ እንዳይነሣ ለማድረግ ከቤተክርስቲያን የዘረፉትን ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ የሐራ የገጽታ ግንባታም የዚህ እንቅስቃሴ አካል መሆኑ ነው፡፡ ሲኖዶሱ ማቅ የቤተክርስቲያን ልጆች ሕዝቡን በትምህርተ ወንጌል ጠብቁ ብሎ በቅንዓት በመነሳሳት ካላስወገዝኩ እያለ ላይ ታች በሚልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ተጨባጭ የሃይማኖት ሕጸጽና የሥነምግባር ጉድለት በቸልታ ማለፍ እንደሌለበት ብዙዎች ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ለአንድ ማኅበር ሳይሆን ለተዋሕዶ ሃይማኖት የቆመ ሲኖዶስ መኖሩን ማረጋገጥም የሚቻልበት ትልቅ አጋጣሚ እንደሚሆን ብዙዎች ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በኑፋቄ የተከሰሱና አንመለስም ሲሉ የተወገዙ ጳጳሳት መኖራቸው የሚታወስ ሲሆን ቀደምት መናፍቃን እነአርዮስ፣ ንስጥሮስ፣ መቅዶንዮስና ሌሎችም በዚህ ጎራ የሚመደቡ ናቸው፡፡ በአገራችንም ዐቋም የለሹ አባ ገብርኤል ሁለት ባሕርይ ብለው ተወግዘውና ስመ ጵጵስናቸው ተገፎ አቶ ኢያሱ ተብለው ተጠርተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በኋላ ግን ኑፋቄያቸውን ስላመኑና ማስተካከያ ስላደረጉ ስመ ጵጵስናቸው እንደተመለሰላቸው አሁንም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ታዲያ አባ ሳሙኤልስ ተጠርተው የማይጠየቁበት ምክንያት ምን ይሆን? ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በአባ ሳሙኤል ኑፋቄና የድርሰት ስርቆት ላይ ቤተክርስቲያኒቱን ስላስነቀፉ ሊጠይቃቸውና ተገቢውን ውሳኔ ሊወስን ይገባል እንላለን፡፡     

6 comments:

 1. I don't think you guys are knowing Lord Jesus. Why don't you share us the word of God instead of some individuals or group of people. Who cares about the website opposing you, please use your site to share the word of life that is Jesus. Girma went to prison now his followers need help at this time, you website can play a significant role on spreading the word of God. I just checking your website wheater you post about Girma , but you aren't. Geta leholachenme lebona yestene! Amen!

  ReplyDelete
 2. የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ።

  የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መኾኑን ተናግረዋል።

  አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ፣ በማጥመቅ እፈውሳለኹ በሚል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሕገ ወጥ ሀብት ሲያካብት እና በርካታ ምእመናንን ለተለያዩ ችግሮች ሲዳርግ ቆይቷል፡፡

  ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነገጋረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ዕውቅና እና ፈቃድ በይፋ የተነፈገው ሕገ ወጥ እንደኾነ አረጋግጧል።

  የፋና ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ በፈውስ አገልግሎት ስም የማጭበርበር ወንጀል ሳይጠረጠር እንዳልቀረ ነው የተናገሩት።

  ReplyDelete
 3. ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ.ም.
  “አባ ሰላማዎች” መቼም የውሸት ፋብሪካ መሆናችሁ ጸሐይ የሞቀው አገር ያወቀው ጉዳይ ቢሆንም ለግብራችሁ የሚስማማ ስም ባለመያዛችሁ ግን አዝናለሁ፡፡ ለምን በታሪክ አባቶቻችሁ በነ ንስጥሮስ፣መቅዶንዮስና ሉተር ስም አትጠሩም? የነርሱ የግብር ልጆች ናችሁና-ወዲያውም ልጆች በአባቶቻቸው ሲጠሩ ይመቻልና፡፡ ምክንያቱም እናንተ የእውነተኛው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን እውነተኛ አባትና የመጀመሪያው ጳጳስ አባ ሰላማ ልጆች አይደላችሁምና፡፡ የቅዱሳን ጠላቶች ሆናችሁ እንዴት አድርጋችሁ ቅዱስ ሰላማን ትወዳላችሁ? እስኪ በእውነት ልጠይቃችሁና በአባ ሰላማ ቃልኪዳንና ምልጃ ታምናላችሁ? ይሄ ወንጌል አይደለም ትሉ ይሆናል፤ አታፍሩምና፡፡
  ክብር ምስጋና ይግባውና ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ እንዳሰፈረው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከኔ የበለጠም የደርጋል” ብሎ ለቅዱሳኑ በሰጠው ቃል ክዳን መሰረት በአጸደ ሥጋና ነፍስ ያማልዳሉ፤ ሙት ያስነሳሉ፤ ከልዩ ልዩ በሽታዎች ይፈውሳሉ፡፡ ምን ታደርጉ-ይሄ እንግዲህ ወንጌል ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ይግረማችሁና ለቅዱሳኑ እንኳን የማማለድ የመፍረድም ሥልጣን ተሰጥቶአቸዋል- የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ልትሸሽጉ አትችሉም፡፡ ይህ የተባለው በአዋልድ መጽሐፍት ላይ እንኳን ቢሆን ምክንያት ይኖራችሁ ነበር፡፡ እኛስ አዋልድ መጽሐፍትም ቢሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመስርተው ስለተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ናቸው ብለን እናምናቸዋለን፡፡
  ሐሰተኞች መምህራን የበግ ለምድ ለብሰው ይመጣሉ ተብሎ እንደተነገረው እውነተኞቹን በጎች ለመምሰል በኣባ ሰላማ ስም መጣችሁ፡፡ እውነተኛ ግብራችሁንና የዲያብሎስ ልጅነታችሁን ግን ለመሸሸግ ስላልቻላችሁ በተሰጣችሁ የስድብ መንፈስ ጳጳሳቱን፣ ሊቃውንቱን፣ ክርስቲያኖችን በጠቅላላው ቤ/ክንን ትሳደባላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 4. ሀራ ከምትባል ሀራ ጥቃ ይስማማታል።ሀራጥቃ።።

  ReplyDelete
 5. ለመስረቅማ ሙሉጋኔን ወልደሰይጣን ከፅጌ መፅሃፍ ከግማሽ መፅሃፍ በላይ ሰርቆ አይደል እንዴ ያሳተመው? ታዲያ ምነው እሱን ፀጥ አላችሁት። የናንተ ጋኔን ስለሆነ? :)

  ReplyDelete
 6. ጌታ ሆይ አውሬው አፉን ሲከፍት እንዴት ያስጠላል? ና እባክህ በመስቀልህ አፉን ዝጋልን አውሬው ለምን ይቆጣል?????????????????

  ReplyDelete