Friday, October 30, 2015

ውሸት ቢሮጥ እውነትን አይቀድምም “አሪፍ ለወሬ አይቸኩልም” ይላሉ የአራዳ ልጆች፡፡ መጽሐፍም “ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” ይላል፡፡ (ያዕቆብ 1፥19)፡፡ በዚህ የማይመራው የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሐራ እውነትን ለማድበስበስና ብዙዎችን በወሬ ለመፍታት ያልተደረገውን ተደረገ የተደረገውን ደግሞ አልተደረገም በማለት ሐሰቱንና የልቡን ተምኔት ሁሉ “ሰበር ዜና” እያለ ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡ ሰበር ዜናፈቃድ የሌላቸው የኢ..ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ 24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል” በሚል ርእስ ሰሞኑን ያናፈሰው ወሬ የተዛባና ሐሰት የተቀላቀለበት መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ በሐራ ዘገባ ሐሰትነት ያዘኑት ምንጮች ሐራ እንዲህ የምታደርገው ሰውን በወሬ ለመፍታት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሲኖዶሱ በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ በተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተመስርቶና በሌሎች የራሱ ጉዳዮችም ላይ አጀንዳውን እንደሚያረቅ እየታወቀ በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያልተነሣውንና በመግለጫው ላይ ያልተነሣውን የተሐድሶን ጉዳይ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በስርዋጽ አስገብቶ እንዲያነበው በማስደረግ ሸፍጥ ተፈጽሟል፡፡

(ዳንኤል በት/ቤት እያለ የማቅ ደጋፊ በኋላ ደግሞ ተቃዋሚ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በፈረንሣይ ኤምባሲ እርዳታ አባ ጳውሎስ የተወለዱበት መደራ አባ ገሪማ ገዳም ሙዚየምን ለማሠራት በገዳሙ ስም ገንዘብ ተቀብሎ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲው ገዳሙን ሲጠይቅ ገንዘቡ እንዳልደረሰው በመግለጹ ዳንኤል ከሥራ ታግዶና ወደ ውጪም እንዳይወጣ ጭምር ተፅፎበት ነበር፡፡ እሱም ከላይ የተገለጸውን ችግር የሠሩብኝ ማቆች ናቸው ይል ነበር፡፡ ጉዳዩ በምን እንደተዘጋ ሳይታወቅ አሁን የአቡነ ገሪማ ምክትል ሆኖ እየሠራ ይገኛል፡፡ በ34ኛው የሠበካ ጉባኤ የመዝጊያው የአቋም መግለጫ ላይ ከስብሰባው መንፈስ ውጪ በሥርዋፅ የገባ “ተሃድሶ” የሚል ቃልና ሐሳብ መነበቡ ዳንኤል እነ አቡነ ማቴዎስን ለማስደሰት ያደረገው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ምክንያቱም ከፈጸመው የሌብነት እገዳ በኋላ መልሰው ያስገቡት እሳቸው በመሆናቸው ለውለታቸውና በቀጣይም ለማቅ አጋር ሆኖ መቀጠል እንደሚፈልግ ለማሳየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡)

ሲኖዶሱ በኢቢኤስ የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ ሁሉም ወደ ሕግ ይግቡ አለ እንጂ በስሟ አይጠቀሙ የሚል ውሳኔ እንዳላሳለፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀደም ሲልም በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህን ጉዳይ አስመልከቶ የተናገሩት ሁሉ ወደሕግ እንዲገቡ እንጂ ሌላ የምናደርገው ነገር አይኖርም የሚል መሆኑን ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ቀደም ብሎ እነደረጀ ዘወይንዬንና መሰል ጀሌዎቹን አደራጅቶ በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንደ አጀንዳ ለማስያዝና የሲኖዶሱን ትኩረት ወደሌላ አቅጣጫ ለመውሰድ ያደረገው ጥረት ብዙም የተሳካ አልነበረም፡፡ ሐራ “ታዖሎጎስና ቃለ ዐዋዲ በስም ተጠቅሰዋል” በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ብትዘለውም የማኅበረ ቅዱሳን ወዳጅ የነበሩትና “ዓለም ጉድ ወለደች” በሚለው መጽሐፋቸው ሽያጭ ላይ በተፈጠረው አለመግባባት ቅሬታ ውስጥ ያሉት አባ ቀውስ ጦስ ለምን ታዖሎጎስ እና ቃለ ዐዋዲ ብቻ የማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራምም አብሮ ነው መታየት ያለበት ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሲኖዶሱ ወደፊት ቤተክርስቲያኗ በምትከፍተው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሦስቱም የአየር ሰዓት ገዝተው ፕሮግራማቸውን በዚያ እንዲያስተላልፉ እንዲደረግ ነው የሚፈልገው ተብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም በወንጌል ላይ ባላቸው ጽኑ ዐቋም የሚታወቁትና ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ ሲቆሙ የምናውቃቸው አባ ማርቆስ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ሆነው ውለዋል፡፡ “ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” በሚለው ኑፋቄው ምክንያት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንዳልተጋጩ፣ በጎጃም ምድር እንዳላሳደዳቸውና ሕዝቡን እንዳልቀሰቀባቸው፣ የኀይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄ በአደባባይ በቅኔ እንዳልተቹ፣ አሁን ግን በጥቅም ተደልለው ለሀገረ ስብከታቸው ማሠሪያ 300 ሺህ ብር ስለሰጣቸው በጊዜያዊ ፍቅር ውስጥ የሚገኙት አባ ማርቆስ በመንበረ ፓትርያርክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኀላፊ ሆነው ስለተመደቡት አባ ቃለጽድቅ “መናፍቅ ናቸው ከአሜሪካ ያመጣሁት ማስረጃ አለ” በማለት ጉባኤውን ወደማወክና ቅዱስ ፓትርያርኩን ወደመዝለፍ መግባታቸው ተገልጿል፡፡ አሜሪካ ከርመው የመጡት አባ ማርቆስ የጥቅም ሰው መሆናቸውን ከድሮ ጀምሮ እንደሚያውቁ የተናገሩት ፓትርያርኩ ሥርዓት የማይዙ ከሆነ በሕግ ሥርዓት እንደሚያሲዟቸው ተናግረዋል፡፡
ሌላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲሱን አመራር ለማውረድና ሙስናውን ወደቀደመው ስፍራ ለመመለስ ውስጥ ውስጡን ሲሰሩ የቆዩት ማኅበረ ቅዱሳንና ሙሰኞች ጀሌዎቹ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳንዶች ቢቃወሙትም የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለ ሊቀጳጳስ እንዲመራ ውሳኔ አግኝቷል፡፡
አባ ሳሙኤል በስማቸው ካሳተሙት መጽሐፍ ጋር በተገናኘ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ፣ አባ ሳሙኤል ለአጥማቂው ግርማ በ200 ሺህ ብር ሥልጣነ ክህነት መሸጣቸውንና በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የማቅን የቤት ሥራ በተለይም ከኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጋር በተያያዘ ለመሥራት ከማቅ ጋር መስማማታቸውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ከማውክ ጋር በተያያዘ የአባ ሳሙኤል እጅ ስለመኖሩ የሚናገሩ ተያያዥ ዜናዎችን ይከታተሉ፡፡

7 comments:

 1. አባ ሰላማዎች በእውነት የምታቀርቦአቸው ወሬዎች ሁልጊዜ ይመቹኛል ምክነያቱም 90% እውነት ሥለሆነ ነገረ ግን ሥለ አባ ማርቆስ ያቀረባችሁት ዜና ከሰውየው ሥነ ባሕሪ አንጻር በደንብ አልተዘገበም ምክነያቱም ሰውየው በስነ ባሕሪው እብድ ሥለሆነ እምነት ስለሌለው አምላኩም ገንዘብ ሥለሆነ

  ReplyDelete
 2. ደግ ብላችሁዋል አባ ሰላማዎች ሁል ግዜ እዉነትን መያዝ በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ ያሰጣል። አቡነ ማርቆስ ከፍተኛ የነዋይ ፍቅርና የዘረኝነት ጥማት ያላቸው አባት ናቸው። አሜሪካ የሚመላለሱትም ለገንዘብ በማለትና ጡረታቸው ለመቀበል በየአመቱ ይመላለሳሉ ከዚያም አለፍ ብለው በየማቅ ቤተ ከርስትያናት በመዘዋወር ዶላር ይሰበስቡ ነበር።አባ ማርቆስ የጎጃም ካህናት መሰብሰብ ይወዳሉ ሌላውን ብሄረ ሰብ አይወዱም።የማቅን ገንዘብ ስለጎረሱ ተገልብጠው በማቅ እግር ሥር ወድቀዋል። የዘመናችን አባቶች እውነተኞች ባለመሆናቸው ሁል ግዜ እንደ ቀለሉ ናቸው። ጉድ ጉድ ነው………………………………ገና ብዙ እናያለን ። በቅደስት ቤተ ከርስቲያናችን የመናፍቃን መብዛት ምክርንያቱ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዥና አርአያ የሚሆኑ አባቶች ስለጠፉ ነው ። የአድስ አበባው ቤተ ክህናት በሙስና የሰከሩ አባቶች የተሰበሰቡበት በመሆናቸው ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ ማቅን እያመለኩ በመሆናቸው አምላከችን ተሐድሶን አስነሳልን። የእርሱ ስራ ድንቅ ነው። ማቅ እነሆ ጉድ ፈልቶበት በፈሱ ቡክ ብቻ እየተፈራገጠ ነው። የዘረፈው ገንዘብም ኮረጆው እጅግ ባዶ እየሆነበት መጥቶዋል። በቅዱሳን ስም የማተለሉም መንገድ ህዝቡ ስለነቃ ከቀኝ ወደ ግራ እየተገላበጠ ነው። እውነተኞች ሊቃነ ጳጳሳት ግን ለሃይማኖታቸውን ለህዝበ ከርስትያኑ አንድነትና ጥበቃ እሌት እለተ እየተጉ ናቸው።

  ReplyDelete
 3. tadia yih wushet new ende. Enante sewech min nekachihu.

  ReplyDelete
 4. BALGEWOCH YIHEW YETELEVISION PROGRAM YIJEMERAL TEBALE TEHADISO HULA WUTA KEBETACHN SILEMAGEBAH ATAWRA

  ReplyDelete
  Replies
  1. Beatu ye krstos endehone enkuan tereda. Ewneten bemasaded yemetegenebaw beat bewenet ye krstos newe ? Be lebeh emnet ena ewnet endinor E/R yirdah.

   Delete
 5. ተኩላው ሲያስመስል የሚችለው የለም፡፡ አውሬው ለምን ይቆጣል???????????????????????????????????????????????????????

  ReplyDelete
 6. እንደው ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ መልሱልኝ ህ የምታወጡትን ወሬና አሉባልታ ጌታ ይወደዋል ዌ ጥያቄዬ የመንፈስ ቅዱስ አሳብ ነው ወይ ነው እንጂ እውነት ነው ወይ አይደለም የሚል አይደለም፡፡ ይህን ሥራ እኮ የሚሠሩለት ሰይጣን ብዙ ሰዎች አሉት እናንተ ወዶ ዘማቾች ሆናችሁለት እኮ!

  ReplyDelete