Sunday, October 4, 2015

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዝማሬዎችና መዘምራን ላይ የተከፈተ ዘመቻ Read in PDF
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል እንቅስቃሴዋ ጥሩ ደረጃ ያለ መሆኑን ለመረዳት በወንጌል አገልግሎት ላይ የሚታየውን የተቃውሞ ሂደት መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መዝሙሮቻችን ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ተረትን መሠረት አድርገው የሚዘምሩ ዘማሪዎችና መዝሙሮቻቸው ሥፍራቸውን እየለቀቁ እያየን ነው፡፡
አዳነች፣ አዜብ፣ ሲስተር ሕይወት፣ እንግዳወርቅ ምንዳዬ እና ከጋብቻ ውጪ በወለደው ልጅ፣ በጭፍራ ቤት ውሎው በተቀረፀበት ከባድ የሥነ ምግባር ችግር ለማኅበረ ቅዱሳን ተንበርካኪ ሆኖ አንዴ “ፊደል ናት”፣ አንዴ “መሠላል ናት” ወዘተ እያለ (ከዚህ በፊት በተአምረ ማርያም ምን ብሎ እንደቀለደ ማስነበባችን ይታወሳል) ለኑሮው ብቻ የሚዘምረው ቴዎድሮስ ዮሴፍ በተረት ላይ ተመሥርቶ ለፍጡራን ከሚዘምረው ቡድን መካከል የሚጠቀሱ ዘማሪዎች ናቸው፡፡
 እነዚህ “ኦንሊ ማርያም” (ማርያም ብቻ) የተባሉ ዘማሪዎች ወንጌልን እውነትን መሠረት ባደረጉ መዝሙሮች ተሸንፈዋል፡፡ ወንጌል ከሚያመጣው አንዱ ነገር ልዩነትን መፍጠር ነውና ሕዝቡ ለወንጌል ተማረከና ተረት ተረት ሰለቸኝ አለ፡፡ ነፍሱ አዳኟንና እውነተኛ ዕረፍቷን ኢየሱስን ፈለገች፡፡ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን በማሳደድ የወንጌልን ሩጫ አስቆማለሁ ከሚለው ስሕተቱ ሁልጊዜ የማይማረው ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ የግብር ልጆቹን በማንቀሳቀስ በእውነተኛ ዝማሬዎች ላይ የከፈተውን ዘመቻ ቀጥሎበታል፡፡
በዚህ ሳምንት መጨረሻ ማለትም እሁድ መስከረም 23/2008 በአስር ዘማርያን የተዘጋጀና “መልእክተ ዮሐንስ” የተባለ በዓይነቱ የተለየ የህብረት ዝማሬዎችን የያዘ የመዝሙር አልበም ፀረ ወንጌልና ፀረ ቤተክርስቲያን የሆነው የዲያብሎስ የግብር ልጅ ማቅና ተላላኪዎቹ የአራት ኪሎ የቱሪስቱ ፀረ ወንጌል ቡድን አባላት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ እንዳይመረቅ አድርገዋል፡፡ አስሩ ዘማርያን ዝግጅታቸውን አጠናቀውና እንደማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ በአዳራሹ ለመገልገል ክፍያ ፈጽመው፣ የማስታወቂያ ሥራዎችን ሠርተው ሰዎችን ጋብዘው ለምረቃው አንድ ቀን ሲቀረው ከደብሩ አስተዳዳሪ አባ ገ/ሥላሴ “ተሃድሶ ናችሁ” የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው እዚህ ማስመረቅ አትችሉም በሚል የከፈሉትን ገንዘብ በመመለስ ምረቃው ለጊዜውም ቢሆን እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ይህ የሆነውም የአራት ኪሎ ፀረ ወንጌል ቡድን እና ማኅበረ ቅዱሳን ቢሮአቸው ሄደው በመናገራቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲያውም የአራት ኪሎው የቱሪስቱ የድራፍት ቡድን አባላት አባ ገ/ሥላሴን አንድ ኪሎ ሥጋ ጋብዘው እንዳሳመኗቸውና ምረቃውን እንደሰረዙላቸው በኩራት ሲያወሩና ሲያሟቸው ተሰምተዋል፡፡
እኚህ ለሆዳቸው ያደሩ ተራ ሰው የቤተ ክርስቲያን ልጆችን በእኩልነት ማስተናገድ ሲገባቸውና ከዚህ ቀደም ሲኖዶስ ያላወገዘውን ሰው ተሐድሶ ማለት ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑን የቀድሞው ፓትርያርክ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲደርስ በጻፉት ደብዳቤ መመሪያ የሰጡ ቢሆንም ይህን መመሪያና ህሊናቸውንም ለሆዳቸው በመሸጥና ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስደሰት አድልዎ ፈጽመዋል፡፡ ለመሆኑ ቤተክርስቲያኗ የማን ናት? የማኅበረ ቅዱሳን ወይስ የሁሉም ኦርቶዶክሳዊ? ሰው የማኅበረ ቅዱሳን አባል ካልሆነ መብቱ የማይከበርበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነውና እንደዚህ ያለውን አድሎኣዊ ሥራ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቸልታ ሊመለከተው አይገባም እንላለን፡፡ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተዘጋጀው ሥልጠናና የውይይት መድረክ ላይ ከተነሱት ሐሣቦች አንዱና ዋናው የአክራሪነት መገለጫ ከእኔ ውጪ ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ማንንም አልይ ማለት ነው፡፡ የአሁኑ ድርጊት ደግሞ የአክራሪነቱ ነገር ምን ያህል እንደጦዘና የቤተክርስቲያንን አስራት ወደራሱ ኪስ እያስገባ ባለው ማቅ ለቤተክርስቲያን የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ ያሉ የቤተክርስቲያን ልጆች ተገቢውን አገልግሎት እንኳን ከቤተክርስቲያን እንዳያገኙ አክራሪው ማቅ በጥቅም የገዛቸውን የደብር አለዎች እየተጠቀመ ያሻውን እያደረገ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡    
አባ ገብረ ስላሴ ለመዘምራኑ አስቀድመው ማሳወቅና ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ማድረግ የነበረባቸው ቢሆንም ዓላማቸው አዳራሹን መከልከል ብቻ ሳይሆን የምረቃውን መርሐግብር ማስተጓጎልና የልጆቹን ሞራል ለመንካት ስለነበረ ዘማርያኑ አዳራሽ ፈልገው ለማግኘትና ጥሪውን በተገቢው ሁኔታ ለማስተላለፍ በማይችሉበት ጊዜ ውስጥ ነው የከለከሉት፡፡ የሚገርመው ግን የዛሬ 15 ቀን በዚሁ አዳራሽ ከላይ የጠቀስነው ቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙሩን አስመርቆበታል፡፡ የእሱ የኦርቶዶክስ የእነዚህ ደግሞ የተሃድሶ መሆኑን አባ ገብረ ሥላሴ የለኩት በምን ይሆን? ሲኖዶስ በተገቢው መንገድ ያላወገዘውን ሰው በዚህ መንገድ መፈረጅና አገልግሎት እንዳይሰጥና እንዳያገኝ መከልከል የአክራሪነት መገለጫ ነው፡፡
ደስ የሚለው ግን ዘማሪዎቹ ማቅ በተቆጣጠራቸው አስተዳዳሪዎች በኩል መዝሙራቸውን በተባለው ቀን በቤተክርስቲያናቸው ቅጥር ውስጥ ማስመረቅ ባይችሉም ወደፊት በተሻለ ሁኔታ እንደሚያስመርቁ አሁን የደረሰባቸው ተቃውሞ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑ ነው፡፡ ስለደረሰባቸው ተቃውሞም ደስ ሊላቸው ይገባል እንጂ ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ቤተክርስቲያናቸውንም ከማገልገል ወደኋላ ማለት የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም የደረሰባቸው ተቃውሞ የሚያሳየው እውነተኞች መሆናቸውንና በትክክለኛው የወንጌል መንገድ ላይ መቆማቸውን ነው፡፡ የዘመሩት መልእክተ ዮሐንስን መሠረት ያደረገ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሲሆን ተቃውሞ የገጠማቸውም ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬም ለማርያም መዘመር የሚያስከብርበት ለኢየሱስ መዘመር ደግሞ ዋጋ የሚያስከፍልበት ዘመን ላይ መሆናችን በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ ክርስቲያን በትክክለኛው መንገድ ላይ ከቆመ እንዲህ ያለው ነገር እንደሚያጋጥመው የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ የተናገረለት እውነት እንዲህ ሲል፡-
“ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።” (ማቴዎስ 5፡10-12)
 “በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤” (ፊልጵስዩስ 1፡28-29)፡፡
ይህን እውነት መለወጥ አይቻልም፡፡ ዛሬ እንደ ማቅ ባሉ አመፀኛ ቡድኖች ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን መዘመር ዋጋ ሲያስከፍል አዋልድን መዘመር ግን ያስከብራል፡፡ ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ግን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዝማሬዎች ሥራው እየፈረሰበት ያለው ጠላት ዲያብሎስ ደስተኛ ስላልሆነ ለእርሱ መሳሪያ ሆነው የቀረቡትን ሰዎች በመጠቀም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሚዘምሩትን ዘማርያን ማሳደዱን ቀጥሏል፡፡ እነዚህ አሥሩ ዘማርያንም ይኸው ዕጣ ፈንታ ነው የደረሳቸው፤ ምክንያቱም በዝማሬያቸው ውስጥ፡-
“ዓለም ባያውቀን እንዳይገርመን
በሰማያት ነው ሀገራችን
የዲያብሎስ ሥራው ፈርሷል በአዋጅ
ተገልጦአልና የእግዚአብሔር ልጅ” ብለዋል፡፡

መቼም ቢሆን ጠላት ዲያብሎስ ከስሕተቱ አይማርም፤ አስቀድሞ ክርስቶስን በመግደል ክርስትናን አጠፋለሁ ብሎ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከእርሱ አንጻር ክርስቶስን እንዲገደል ቢያደርግም ክርስትና ግን በመጥፋት ፋንታ እጅግ ተስፋፋ፡፡ ከዚያ ሐዋርያቱን በተመሳሳይ መንገድ ለማጥፋት ሞከረ፤ ብዙዎቹ በሰማእትነት ሞቱ ክርስትናን ማጥፋት ግን አልተቻለውም፡፡ ኦንዲያውም ክርስትና ባሳደዱት ልክ መስፋፋቱን ቀጥሎ ከዘመናችን ደርሷል፡፡ ዛሬም እንደ ማቅ ያሉ በክርስትና ስም የሚጠሩ ነገር ግን ክርስቲያን ያልሆኑ ቡድኖች የግብር አባታቸውን ከስሕተት አለመማር ወርሰው የወንጌልን እሳት ለማዳፈን ከተቻላቸውም ለማጥፋት ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ሆኖም ዘመቻው በወንጌል አሸናፊነት መደምደሙ አያጠራጥርም፡፡
በቅርቡ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ አንዳንድ ሰካብያንንና ዘማርያንን እናስወግዛለን በሚል ማቅ በመልኩና በምሳሌው በፈጠራቸውና ከኋላ ሆኖ በሚነዳቸው የአመፅ ቡድኖች በኩል የድጋፍ ፊርማ እያሰባሰበ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ ማቅ ይህን መንገድ የተከተለው በእርሱ ላይ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እያሰሙ ያለውን ተቃውሞና ማቅን በተጨባጭ ማስረጃ በአክራሪነት መፈረጃቸውንና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናትን ፀረ ማህበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴን አቅጣጫ ለማስለወጥ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን፡፡

21 comments:

 1. ደጋሚና ሙአርተኛ በነገሰባት ቤተክርስቲያን ኢየሱስን ሰብኮ እና ለእርሱ ዘምሮ መወገዝ መወገዝ መወገዝ 10000….. ጊዜ መወገዝ እንዴት መታደል ነው፡፡እንደቃሉ ሲሮጡ ሁሉ ሜዳ አይደለምና ድል መንሳትን በሚሰጥ ጌታ ታምኖ ሩጫን አብዝቶ መቀጠል ነው፡፡እግዚአብሄር ይባርካቹ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሃድሶዋዉያን አሁን ገና መስመር አለፋችሁ።ይህንን ያክል ተደፋፍረናልንሳ።
   ኦርቶዶክስ እምነት እኮ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት የሚከበሩበት እምነት ነዉ።ወላ የግሪክ ኦርቶዶክስ አልያም የሶርያ ወይ የግብጽ ብቻ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት እኮ ቅዱሳን የሌሉበት ከሆነች የፕሮቴስታንት እምነት ትባላለች።በዛ ላይ ልክ እንደጴንጤዎቹ እራሱን አማላጅ ብላ የምትሰብክ ከሆነ የቆሮንጦሱን እየሱስን ወይንም 666 ታመልካለች ማለት ነዉ።እናም እነ መምሬ ሰረቀ ያለዉ መናፍቅ መወገድ አለባችሁ።

   Delete
 2. Asiru zemariwoch or Asiru Zefagnoch? you need to learn what mezmur is from kinetibeb, Yilma, teddy and others orthordox members. Do not involve in our orthodox church........freak out about your protestant stuff....

  ReplyDelete
  Replies
  1. ባይገርምህ አንተ የዘረዘርካቸዉ ዘማሪያን ሳይሆኑ አዝማሪዎች ናቸዉ............. አዝማሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምታዉቅ ይመስለኛል......... የማታዉቅ ከሆነ እኔ እንደማዉቀው ልንገርህ....... አዝማሪ በምን ይታወቃል ብትለኝ አንዱን ባሞገሰበት በዚያው ግጥም የስም ለዉጥ ብቻ አድርጎ ሌላዉን ያመሰግንበታል........ ለዚህ ደግሞ አንተ የጠቀስካቸዉ ዘማሪዎች በጣ...........ም ሃሪፍ ምሳሌዎች ናቸዉ:: ካላመንከኝ መዝሙራቸዉን አንተዉ እንደገና በደንብ ለማዳመጥ ሞክር.............

   Delete
 3. የአስሩ ‹‹ ዘማርያን ››ስም ያልጠቀሳችሁት በእናንተ ጥሩ ነው የተባለ ሁሉ ሕዝቡ ስለሚጠላ ነው

  ReplyDelete
 4. ayzone wendemoche

  ReplyDelete
 5. እነ በጋሻው ተሐድሶ መሆናቸውን መርምሮ ያረጋገጠው ሲኖዶስ ማህበረ ቅዱሳን ይባላል፡፡ ማህበሩ በኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሲቲየን ጉዳይ ላይ ማንኛውንም ውሳኔ ለመወሰን ሥልጣን ከላይ ከሰማይ የተሰጠው ስለሆነ እሱን የሚቃወም ሁሉ ይቀሰፋልና ጳጳስም ቢሆን ፓትርያርክ ዝም ይበል፡፡ አይቆጣ! አይቅጣ!! ስምንተኛው ሺህ እስኪመጣ ድረስ ያሻውን እንዲናገርና እንዲያዝ፣ የሚበቃውንም ያህል ሀብት ይዞ ቤተ ክርስቲያንን የሚገዛበትና የሚቆጣጠርበት የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዲያመርት ጊዜ ይሰጠው፡፡

  ReplyDelete
 6. Ene yegeremgne tedros yemibalew zemari yebetecrstiyan sereat afrso kegabicha befit kelela set weldo teklil adergo siyageba newor aydelem?degmo yeteklil photo new cassette cover yaderegew.wwy tewahdo ymotelsh komo yegedelesh bela.yekasetum birr ke kernbula kumar ayalfm.beshengela kenfer yetezrmere mezmur.kirstos yaltayebet ......

  ReplyDelete
 7. Iwunetim tehadiso yasfeligenal

  ReplyDelete
 8. Keep informing us what's going on Aba Selama's please. Thank you for all you are doing. They start campaigning against those who sing and preach the gospel so we guys gotta stand with those who preach the sing the truth (the Bible). Thank you again Aba Selama's.

  ReplyDelete
 9. ቴዲ ነጋዴ እንጂ ዘማሪ አይደለም።ይልማም ሚስቱነ ፈቶ ቤቱነ ተቀምቶ በ ዜሮ የቀረ የከሰረ ከስር የማያድጉት ዘማሪየያነ ገበያ ዘጉብነ እያለ በየጉባኤው ሲያወራ የሚዉል ሁለቱም ስነ ምግበረ የጎደላተው በማሪም ስም የሚነግዱ ሌላዉነ የሚከሱ ከኔ ወዲያ ዘማሪ የለም የሚሉ ክብሩ የጎደላተዉ ግለሰቦት ።

  ReplyDelete
 10. አሁን ደግሞ ገንዘብ አዋቱ እነ በጋሻውን የምናስገድልበትገንዘብ አሰባስቡ የሚል ከ 200 በላይ የሚሆኑ ሰዎ ያሉበት የስልክ ግሩኘ ተቁዋቁሞአለ ።ሲጀመር በመዝሙር ስም ነበረ አሁነን መልኩን ቀይሮ ለ ዘመድኩን እነበጋሻውን የሚያስወግድበተ ዶላር መሰብሰቢያ ሆነ።በጋሻው እግዚአብሂር ይሁንህ።for your information.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ENDE EBAB AFER EYEBELA INESALE HIHE ZEMDKUN GETA IHUNEH DINGEL TKETELIH !!!

   Delete
 11. ያሳዝናል ወንጌል ወንጀል የሆነበት ዘመን ወይ ጠላት ዋጋ የከፍላሉ ሁሉም
  እኔ የሚገርመኝ ኦረቶዶክስ ሆኖ እንዴት ወንጌል ይጠላል
  ህዝቡን እኮ በደሉት ጥቅመኛ ብቻ

  ReplyDelete
 12. ORTHODOX BECOMES ENEMEY OF JESUS CHRIST!!!!!

  ReplyDelete
 13. Everybody in Orthodox church SCARES to call Jesus Christ. They have fear of saying Jesus Christ because they have others to believe in. Miskin Hezb. please come to the truth, the only truth.

  ReplyDelete
 14. የሚገርመው እኩ የሚከሱበት እንካን በውሸት ነው አንድ የሚረባ ነገር የለውም ።በሙሉ ህዝቡን ተሳዳቢ ረጋሚ ፈሪሀ እግዚአብሄር የሌለው አደረጉት።ዘመድኩን ዳንኤል ክስረት ቴዲ እንደዚህ የደፈራትሁት በልባትሁ የለም በአፋ የምትሸረድዱት አምላክ ጀራፍ ያነሳ ቀን እናንተን አያድርገኝ።ነጋዴ ሁሉ እግዚአብሄር ሳይዘገይ ይፍረድ።

  ReplyDelete
 15. ለአውሬውም የስድብ አፍ ተሰጠው
  ሥድቡ የአውሬው ልጆች ናችሁና ከእናንተ የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእውነተኛው አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቅዱሳኑ እንዲሁም ለእናቱ ለድንግ ማርያም ናት። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታየ የሆኑት ሁሉ እግዚአብሔርን እሱም ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ብለው እያመለኩ ለቅዱሳኑም የክብር ምስጋናንና ክብርን እየሰጡ እምነታቸውን ይፈፅማሉ። አራሙቻ እንክርዳዶች ሐሰተኛ ክርስቶሳውያን፣ ሐዋርያተ ከሰበኩት የተለየ ወንጌልን ካልሰበክን የሚሉ ሐሰተኛ ወንጌላውያን፣ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት ወንጌል የሚመሥላቸው በከንቱ ኢየሱስ ኢየሱስ እያሉ የሚያላዝኑ ደግሞ እውነተኛው ዳኛ አምላክ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። የቅዱሳኑን ክብር እያቃለሉ በመከበራቸው አይናቸው ደም ይለብሳል። መዳን የሚገኝባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍትንም ያራክሱ ይቃወማሉ። የአምልኮ ሥርዓትን ሁሉ ያፈርሱ ይቃወማሉ።
  እናም እናንት እንክርዳዶች ናችሁና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ የላችሁም። ሐሰተኛ ወንጌል፣ በምንፍቅና የተሞላና ኦርቶዶክሷዊ ትምህርት የሌለበት መዝሙር ቦታ የላቸውም። እናንተም የቁራ ጩኸታቹንና ተሳዳቢ አፋችሁን አምቧርቁ ክፈቱ።

  ReplyDelete
 16. እናንተ የቆማችሁ የመስላችሁ ተሳዳቢዎች እግዚያቤሄር ይህን ይጸየፋል እግዚያብሄር ፍቅር ነው። ለምን እውነቱ ወጣብን እናንተ ልባችሁን አድሱ የስትባላችሁ እንጅ ሃይማኖታችሁን አድሱ ወይም ምጽሃፍ ቅዱሱን አድሱ አልተባላችሁ ብቻ ያሳዝናል ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተገዥ መሁናችሁ እናዝናለን።እውነት ነው በመጨረሻው ዘመን ይህን ልናይ ግድ ነው በስሜ የሚጠሩኝ ብዙዎች ናቸው የተጠሩት ግን ጥቂቶች ናቸው እውነትኛዋንና ቀናዋን መንገድ ወይም ጠባብዋን መንገድ የሚከተሏት እጅግ ጥቂቶች ይሁናሉ። እኔ በበኩሌ የኤትዪጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ/ክርስቲያን ከለላ አድርጋችሁ አታወናብዱ ቤቱን አታቆሽሹ ሂዱና እዚያው አዳራሽችሁ ዝለሉና ጨፍሩ እንደዘመዶቻችሁ ይብቃ ለማንኛውም ትግስተኛው አምላካችን ንጹህ ልቦና ይስጠን የሚያሰርጉትን አያውቅምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ያለን ሩህሩህ አምላክ ወደ ቀደመው ቤቱ ይመልሰን።

  ReplyDelete
 17. ይህ ገጽ የሚገርምና ፍቅር የሌለው ማስተዋል የተሳነው ብዙ ከእውቀት የጸዱ ትውልድን የሚያበላሽ ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ የመናፍቅ መድረክ መሆኑን ለማወቅ የምታስተላልፉት መልእክት እጅጉን ገፍቶ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እናንተ ይህንን ገጽ ለምን የወንጌል ማስተማሪያ አታደርጉትም እውነት ክርስቲያኖች ከሆናችሁ፡፡ ለምን ወንድሞቻችሁን ትከሳላችሁ? ለምን ትሳደባላችሁ? እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? ለሚቃወሟችሁ ምን እያደረጋችሁ ነው እየጸለያችላቸው ነው መልሳችሁ፣ የቃላት ስድብ፣ ለዚህ ገጽ የምታወጡት ገንዘብ ትንሽም አይቆጫችሁም፡፡ ስም እየጠቀሳችሁ መሳደብ ምን ማለት ነው? ምን ያህል ክርስትናን ሲኦል እንዳደረጋችሁት ነው የሚያሳየው!! ደግሞ ዘማሪዎችን ስም እየጠቀሳችሁ የምትሳደቡ እናንት ማንናችሁ? ለገንዘብ የሚሰራ ምናምን እናንተ በነፃ ነው የምትዘምሩት? እስከአሁን በነፃ የሚሸጥ መዝሙር ካለ ጠቁሙኝ እንድወስድ፡፡ ወንድሙን የሚሳደብ እርሱ ፍርድ እንደሚገባው ወንጌሉ ያስተምራል፡፡ እናንተ የያዛችሁት ‘bible’ አይልም እንዴ? እራሳችሁን በትእቢት የምትሞሉ!! ፈሪሳውያንን ሰዱቃውያን ነው የሆናችሁብኝ፡፡ ያቺን ሰት እንዴት አድረገው ለፍርድ እንዳቀረቧት እናንተ እየሰበካችሁን ያለው ወንጌል ሳይሆን ‘ቁራን’ ላይ የተገለጸውን ኢየሱስ ነው እንዴ? ግራ አጋባችሁኝ፡፡ እናንተን እኮ ግልጽ የሆነ የመናፍቃንና የኑፋቄ ትምህርት ነው የምታስተምሩት፡፡ እስኪ የትኛው ሐዋርያ ነው ልክ እንደእናንተ በወቅቱ የነበሩትን ትውልድ እየሰደቡ እየነቀፉ ወንጌል ያስተማሩት? ያውም የእነርሱ ዘመን? እብ 13፣7 ላይ ያለው ቃል በእውነት ለእናንተ ይገባቸዋል ማስተዋሉ ካለ፡፡ ህንድ ሀገር የደረሰው የቤተክርስቲያን መከፈል ኢትየጰያ ውስጥ ለመድገም ተግታችሁ እየሰራችሁ መሆኑ ይህ መረጃ በቂ ነው፡፡ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 18. ሰሳበቢስ የምትበለው ሰው ፀረ በጋሻው የሚል ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ተሳዳቢ እና የወንጌል ተላት እንደሆን ያስመሰከርንበትን ፔጅ ሳታየው አልቀረህም።አባ ሰላማ ቢያንስ እውነትን መሰረት ያደረገ ነዉ።

  ReplyDelete