Sunday, November 1, 2015

ዘከመ ርኢነ ሰማዕተ ንከውን

Read in PDF


መጽሐፍ ያየነውን እንመሰክራለን ይላል፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ያየነውን መመስከር የሰማነውን መናገር ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነው፡፡ ስለሆነም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያየነውንና የተመለከትነውን በታሪክ የምናውቀውን ለመመስከር ተነሥተናል፡፡ እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን ያልተለመደ ክስተት አስተናግዷል፤ ያልተለመደ የጸባይና የባሕርይ ለውጥም አምጥቷል፡፡ ቅን ህሊና ላለውና ታሪክን ለማይረሳ ሰው የትናትናዎቹ ጥቅምትና ግንቦት ወሮች በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ሥር ላሉ ሠራተኞች ለሆኑ ካህናት ትልቅ ሕመምና ሰቀቀን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለት ወሮች ጥቅምትና ግንቦት የሲኖዶስ ስብሰባ የሚካሄድባቸው ወሮች በመሆናቸው ሥራ አስኪያጁ ይቀየራል ጳጳሳቱ አይሰሙም አይከታተሉም ተብሎ የአንዱን እንጀራ ቀምቶ ለሌላው በመስጠት ሊቃውንቱን በማፈናቀልና ከሥራ ውጪ በማድረግ፣ የክህነቱና የሥራ ደረጃው ለጨረታ የሚቀርብበት ወቅት ነበር፡፡ ብዙ የአብያተ ክርስቲያናቱ ሠራተኞች በዚህ ወቅት ወይም በጥቅምትና በግንቦት ወሮች የቅርብ ዘመድ እንኳን ቢሞትባቸው የዓመት ፈቃድ (ዕረፍት) ወስደው ክፍለ ሀገር ለመሄድ ፈቃድ የማይጠይቁበት ወቅት ነበር፡፡
በተለይ በመጋቤ ሐዲስ ይልማና በቀሲስ በላይ የተፈጸመውን ግፍና በደል ታሪክ ሊረሳው ከአእምሮም ሊጠፋ የማይችል ነው፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ኃላፊነትና ሥልጣን ተሰጥቷቸው እያለ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በገንዘብ በመቀየር የሰንቶችን ርስትና ሥራ በመቀማት ገንዘብ ላለው በመሸጥ የብዙዎችን ጉሮሮ ዘግተዋል፡፡ የሾሟቸው ጳጳሳት ለሰባት ቀን ስብሰባ ገብተው እስኪመለሱ ድረስ ለአንድ ሳምንት እንኳን መጠበቅ አቅቷቸው ቤቱን ወና በማድረግ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ቤተክርስቲያኗን ጎድተዋታል፡፡ በተለይ መጋቤ ሐዲስ ይልማ የፈጸሙት ግፍና በደል በጣም ስላሳፈራቸው ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛው ዓይኔ ነው ካህናቱን የማያቸው? በማለት የፖለቲካ ጥገኝነት በሚመስል መልኩ ከአገር ተሰደው የቤተክርስቲያንን ሀብት በመዝረፍ ኮብልለዋል፡፡ እርሳቸው የሸጧቸው ሠራተኞች ግን እስካሁን ድረስ ወደ ቀድሞ ስራቸው ለመመለስ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ለማስተካከል አስቸግሯል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ሙስና በመንግስት በኩል ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ዝም አይባልም ነበር፡፡ የዜጎችን ሃብትና ንብረት የዘረፈ የትም አገር ቢኮበልል ጉሮሮአቸውን አንቆ አምጥቶ ፍትህ ሲያሰጣቸው አይተናል፡፡ ቤተክርስቲያናችን ግን አንዲት መሆንዋ ተዘንግቶ ይሁን ወይም የማቅ አባላት የሆነውን ስንቱን ወንጀለኛ መቆጣጠር ይቻላል በሚል እንዲህ ያለ ወንጀለኛ ሆነው እያለ መጋቤ ሐዲስ ይልማ በውጭ አገር በምትገኘው ቤተክርስቲያን ያገለግላል፡፡
ቀሲስ በላይም አምና በዚሁ ወቅት ጥቅምት ላይ ጳጳስ የለም በማለት ስንቱን ጉቦ በልተው በልተው እጅግ ከአቅም በላይ የሆነ የሰው ኃይል በመቅጠር አድባራት ከአቅም በላይ የሆነ ወጪ እንዲሁም ዕውቀትን ማእከል ባላደረገ መልኩ የሰው ኃይል በመጫን ከፍተኛ ስሕተት ሰርተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጸም የአሁኑን አስተዳደር እየተቃወመ ያለው ማቅ የተባለው ጨለምተኛ ቡድን እያየና እየሠማ ድምጹን አላሰማም፡፡ አንድም ቀን ስለዚህ ትልቅ ስህተት ትንፍሽ ሳይል ሊታረም ይገባል የሚል አቅም ሲያጣ ይልቁንም እነ ቀሲስ በላይ መውረድ የለባቸውም በሚል ሲጮኽላቸው ተሰምቷል፡፡ ለዚህም ነው ይህ ማቅ የተባለ ቡድን የፖለቲካ እንጂ የሃይማኖት ሽታ የለውም፣ ለቤተክርስቲያንም ውድቀት እንጂ ጥቅም አይሰጥም የምንለው፡፡
ሲጀመር መሃል አገር ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ የፖለቲካ እንጂ የሃይማኖት ስብስብ ላለመሆኑ ሌላው ማሳያ ነው፡፡ የሃይማኖት ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ  መጀመር ያለበት ጎንደር፣ አክሱም ጎጃም ወዘተ ነበር፡፡ ነገር ግን በፖለቲካና በገንዘብ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረጉ በአንድ አካባቢ ብቻ የታጠረ መሆኑ ዓላማውንና ራእዩን በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ በነሊቀ ማእምራን የማነና በመጋቤ ብሉይ አእመረ ላይ የከፈተው ዘመቻ ነው፡፡ እውን ካህናቱን በድለው ግፍ ሰርተው ማቅ ተቆርቁሮ ነው እንዳንል ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ሃይማኖቱ ይህን ማድረግ አይፈቅድለትም፡፡
ለምሳሌ ከሰሞኑ ሐራ የተባለው የማቅ የውሸት መፈብረኪያ ሚዲያቸው እንዲሁ ሎጂካል ባልሆነ መልኩና ባለማመዛዘን የጸፈውን አንድ ውሸት ላነበበው ሰው ያስቃልም ይገርማልም፡፡ ይህ ማቅ የተባለው ጨለምተኛ ቡድን የዘረኝነት፣ የፖለቲካና የሃይማኖት ችግር ያለበት ብቻ ነበር የሚመስለን፡፡ ለካስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ከተጣላ የሚናገረውንና የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነሥቶ መመስከር አቅቶት ማቅ  ሊቀማእምራን የማነ ጳጳሳቱን ደጅ እየጠና ነው ይላል ሲጀምር፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደ ማንኛውም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳሱ የሚያዝበት ነው፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከታቸው ስለሆነ ሥልጣን አላቸው፡፡ እነሊቀ ማእምራን የማነ በቅዱስ ፓትርያርኩ ትእዛዝና ፈቃድ ነው የተሾሙት፡፡ ሲቀጥል የእነርሱን ሹመት ተከትሎ ማቅ አለቦታው በመግባት ቤተመቅደሱን ስላረከሰው በዘመናዊም ሆነ በቤተክርስቲያን ያልተማሩትን ደጓእሌዎች አስገብቶ ቤቱን ስላስደፈረ እንዲያጠሩና እንዲመነጥሩ ነው የተሾሙት፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ጳጳሳቱን ይለማመጣል ደጅ ይጠናል ማለቱ ራሱን ማቅን ያስገምተዋል፡፡ ይህ ለጳጳሳቱ ያለውንም ንቀት ነው የሚያሳየው፡፡ ምክንያቱም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚሠራው ሥራ እኮ በዕውቀትና በችሎታ እንጂ በልምምጥ አይደለም፡፡ ወይም ማቅ እንደሚያደርገው ያልተማሩትን ጎልማሶች ክህነት ለማሰጠት ጠዋት ማታ የጳጳሳቱን በር ደጅ በመጥናትና ፋታ በማሳጣቱ ከዓይናቸው ዞር እንዲል የሚሰጡት ክህነት መስሎት ይሆን?
በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባም ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሀገረስብከታቸው የፈለጉትን ሥራ አስኪያጅ የመሾም መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን ጽኑና ቆራጥ አቋማቸውን በማሳየት እነዚሁ ሥራ አስኪያጆች እንዲቀጥሉ አድርገዋል፡፡ ለማቅ ወግነው የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ግን በውዴታቸው የለቀቁትንና ክፍት ያደረጉትን የረዳት ሊቀጳጳስነት መንበራቸውን ብኩርናውን ከሸጠ በኋላ ተግቶ ቢፈልገው እንዳላገኘው እንደኤሳው ተግተው ቢሹትም የሚያገኙት አልሆነም፡፡ ምሽጉን እንደለቀቀ  ወታደር ነው የተቆጠሩት፡፡ ሀገረ ስብከቱም ያለሊቀጳጳስ በሥራ አስኪያጅ እንዲመራ ነው የተወሰነው፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ የማቅ ምክንያት ውሃ የሚቋጥር አይደለም፡፡ ምክንያቱም የማቅ ልጆች እነ መጋቤ ሐዲስ ይልማ በአንድ ሳምንት ሙስና ሰርተው አሜሪካ የሚያደርስ ከሰበሰቡ እነ ሊቀማእምራን የማነ አንድ ዓመት ሙሉ ያለአዛዥ ሊቀጳጳስ ሲሰሩ ለገንዘብ ብለው የሚሰሩ ቢሆን ኖሮ ማርስ የሚያደርስ ገንዘብ በሰበሰቡ ነበር፡፡ ይልቁንም የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተልእኮ ጠንቅቀው ስለሚያውቁና ልንቀየር እንችላለን የሚል ሥጋት ሳያድርባቸው በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ እስከሚያልቅ ባልተመለደ ሁኔታ ለሊቃውንቱ ከሥጋትና ሽብር ነጻ እንዲሆኑ ሰው ሳይቀጥሩና ሳያዛውሩ ማለፋቸውን ሳናደንቅና ሳንመሰክር ብናልፍ ህሊናችን ይወቅሰናል፡፡ በእውነት ሊቀ ማእምራን የማነና መጋቤ ብሉይ አእመረን ኮርተንባቸዋል፡፡ የሐድገ አንበሳ (አባ እስጢፋኖስ) ልጆች ብለናችኋል፡፡ ልኡል እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ፡፡ ገና ከዚህ የበለጠ መልካም ነገር ታሳዩናላችሁ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት

4 comments:

 1. lemanew yemitinegrut miemenu kenante slemishal man tiru endehone yawkal ene yemilew enante bewnet bete kiristyan wist adgachehual aymeslegnem beruam lay alneberachihum papasin ende guadegn yemitsedbu rakutachihu endayigelet meshefegna yihon zend lesewoch widase kentu yemitawerdu emnet binorachihu beamilakachihu guya tigegnu neber enante gin sewochin eyamesgenachihu gebena litishefinu sayrefd neseha gibu mahibere kidusan abal balihonim man mehonachewin sew sayihon sirachew negrognal silenante sewim sirachihum aynagerim

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ ጌታው ማኅበረ ቅዱሳን መሆንህን ማን ጠየቀህና ነው የማኅበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ያልከው፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም አሉ?

   Delete
  2. ስማ ጌታው …………….. ተብሎ አይጠራም፡፡ ተኩላው ሲያስመስል እንጂ እራሱን ሲገልጥ ያስጠላል፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን ለመደገፍ ግድ አባል መሆን አይጠበቅም፡፡ ፍሬያቸውን መመልከት በቂ ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የምንወዳቸው የቤተክርስቲያን አጥር ናቸው፡፡ ገና ታሪክ ይሰራሉ እውነት የያዘ መቼም ቢሆን አይወድቅም፡፡

   Delete
 2. Ewunet kehaset yibeltalna yetignaw tikkil new blo lemewesen bizum aykebdim miknyatum ewynetegna sira beglits yitayalna.

  ReplyDelete