Thursday, November 12, 2015

የማኅበረ ቅዱሳን /ማቅ/ የዘረኝነትና የፖለቲካ ሥራ አፍ አውጥቶ ሲናገርባለፉት ዓመታት በነመልአከ መንክራት ኃይሌ ላይ በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሰሩት የልማት ሥራ፣ የአካባቢው ሕዝብ ይሁን የሰበካ ጉባኤ መኪና ሸልሟቸዋል (ሰጥቷቸዋል)፡፡ ምንም እንኳን ሽልማቱ ለሠሩት ሥራ ተመጣጣኝ ነው? ወይስ ከመጠን በላይ ነው? ወይስ ያንሳል? የሚለው ግን በቂ ጥናት የሚፈልግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
አንድ ነገር ማለት ግን ይቻላል መልአከ መንክራት ለቤተክርስቲያን ያደረጉት (የሰሩት) ሥራ በዓይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ መሆኑን መመስከር ይቻላል፡፡ በተለይ በብስራተ ገብርኤል የተሰራው ሥራ ቦታው ለልማት ምቹና አውላላ ሜዳ ላይ ያለ በመሆኑ ለብዙ ዘመናት ያለ ልማትና ያለጥቅም የከብቶች መዋያ ሆኖ ይኖር ነበር፡፡ መንግሥት ለልማት ሊወስደው ሲል መልአከ መንክራት ኃይሌ ወጥተው ወርደው ከመንግሥት ጋር በመግባባትና የቤተ ክርስቲያንዋን ልዕልና በማስጠበቅ አጥርዋ እንዳይደፈር በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን አስከብረዋል፡፡ ሲቀጥልም በተመለሰው ቦታ ላይ በብዙ ሚሊዮን የሚገኝ ልማት ተሰርቷል፡፡ 

መቼም ለውጥ አምጪ ሰዎች ለጊዜው ተቀባይነት አያገኙም፡፡ በመሠረቱ ለውጥ አይቀርም፡፡ በራስ ላይም ማየት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ፀጉራም የነበረ ሰው ፀጉሩ ይመለጣል፤ ጥቁር የነበረው ፀጉር ይሸብታል፡፡ ፊት ይጨማደዳል ወዘተ፡፡ ይህ ሁሉ የለውጥ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ተፈልጎ ሳይሆን በራሱ ጊዜ የሚመጣ ነው፡፡ እኛ ለውጥን ማቆም አንችልም፡፡ ለውጥን የሚያመጡ ሰዎች ናቸው ለውጥን የሚያቆሙትም ሰዎች ናቸው፡፡ የመጀመሪያ የለውጥ ሰዎች እንደ እብድ ይቆጠራሉ ለሞትም ይዳረጋሉ፡፡ ከ30-40 ዓመታት በኋላ ሕዝብ በነሱ ለውጥ ተጠቃሚ ከሆነና የለውጡ ነገር ከገባው በኋላ እነርሱም ከሞቱ በኋላ ትናንትና እብድና ሞት ይገባቸዋል ለተባሉት ሰዎች ለሥራቸው ምስክር የሚሆን ሐውልት ይሰራላቸዋል፡፡ አሁን በቤተ ክርስቲያናችን እየታየ ያለውን ለውጥ አንዳንድ ቡድኖች ከራሳቸው እይታና ጥቅም አንጻር ብቻ በማየት የለውጥ እንቅፋት ሆነዋል፡፡
ለምሳሌ ያህል በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ የተደረገው ልማት ማቆች ብዙ ትርጉም በመስጠት ሲፈለጉ የቅርስ ቦታ ስለሆነ ቤቱን የፈረሰ በማስመሰል ቅርስ ወደመ ገንዘብ ተዘረፈ በማለት የተሰራውን ልማት ዋጋ በማሳጣት ያለ እረፍት ይሰራሉ፡፡ በመሠረቱ ልማት ስለ ተሰራ በልማት ስም ያገንዘብ ይዘረፍ ሥራም ያለ ተጠያቂነት ይሰራ እያልን አይደለም ለሁሉም ህግ አለውና፡፡ እያልን ያለነው
1.     የተሰራው ሥራ ለቤተክርስቲያንና ለሕብረተሰቡ ይጠቅማል አይጠቅምም የሚል ቢሆን
2.    በተጠያቂነትና በግልፅነት የተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ማቅ እንደሚያወራውና በጥቁር መነፀር እንደሚያየው በተለይ በመልአኩ መንክራት ኃይሌ የተሰሩትን መልካም ሥራዎች ከማየት ይልቅ የመልአከ መንክራትን ማንነትና የትውልድ ቦታ በክፉ ማንሳት እንዲሁም ጉድለቶችን ብቻ ማጉላት ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የቆመ ቢሆን ኖሮ ሌሎች ስንቶቹን አስተዳዳሪዎች እና ሥራ አስኬያጆች የቤተ ክርስቲያንን ሃብትና መሬት ፅላት ለእስላም ሳይቀር ሸጠው ማህበሩን እንደ ትልቅ ጫካ በመጠቀም እርሱ ውስጥ በመሸሸግና ማቅም የእነሱን ገበና ሊሸፍን እነሱም ሊላላኩት የአመፅ ጋብቻ ተጋብተዋል፡፡ ይህ ማህበር የቤተክርስቲያኒቱን እምነትም ሆነ አስተምህሮ፣ እንዲሁም የካህናቱን ፍቅርና አንድ የቆሎ ተማሪ የሚያምነውን ማለትም በአገሩ በወንዙ ሳይሆን  “የየኔታ እገሌ ተማሪ ነኝ” ብሎ በመምህሩ እንደሚገልጽ ማቅ እንዲህ የሚያደርግ ማንነት የለውም፡፡

በአስተምህሮአቸው አባቶቻችን በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት አንገታቸውን ሰጥተው (ሰማዕትነት) ከፍለው ያቆዩአትን ቤተ ክርስቲያን፣ ማለትም በሥላሴ ላይ ኢንረብዕ (አራተኛ አምላክ) አንጨምርም ከሦስትነትም አንቀንስም አናጎድልም ብለው የሚያምኑትን “መናፍቅ ተሃድሶ” እያለ ስም ይለጥፋል፡፡ እስኪ እውነት እንነጋገር በነበረው ላይ አንጨምርም፣ አዳዲስ ባዕድ ነገሮችን እናስውጣ በጥንትዋ ቤተክርስቲያን ትምህርት እንመራ አዲስ ነገር አንጨምር የተበላሸውን እናስተካከል ማለት ተሃድሶ ነው፡፡ መናፍቅ ባእድ ነገር ይዞ የመጣ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን አትታደሰም እያሉ አቅጣጫ ማሳት ምን ይባላል?

እስቲ እውነት እናውራ ይሄ ማህበረ ከተቋቋመ ጀምሮ ስንት አዳዲስ ትምህርቶች ገቡ? የገቡት አዳዲስ ትምህርቶችና ስርዓቶች ስንቱን የአበው አስተምህሮ ነው የበረዙት? በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንኳን ስንት መናፍቃን ናቸው ከማህበሩ እየተፈለፈሉ ያሉት? ከጳጳሳት ጀምሮ እስከማህበሩ ኃላፊዎች ድረስ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ ቤተ ክርስቲያንዋ ዋጋ የከፈለችበት የምስጠረ ሥጋዌ ትምህርትን ከአርዮስ በባሰ ከአውጣኪ በበለጠ እያስተማሩና እየጻፉ በአፍም እያሠራጩ ሃይ የሚላቸው ጠፍቶ የቤተክርስቲያንዋን ህልውና እያናጉት ነው፡፡ የማህበሩ “ፖርላማ” የሚሰጣቸውን ያለመከሰሰ መብት በመጠቀምም ስህተት የፈፀሙና ኑፋቄና ክሕደት የጻፉ ሰዎች በሕግም በንስሐም ይጠየቁ ሲባል ምን አገባችሁ? እያለ እርሱ ግን እነርሱን እንደ ቁም እስረኛ በማድረግ ነገ ከማህበሩ አፈንግጠው ቢወጡ ያሉትንም ያላሉትንም አቀነባብሮ የክስ ሰነድ ለማቅረብ ማንም አይቀድመውም፡፡

በቅርቡ እንኳ የማህበሩ አባላት በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ የፈጸሙት ዓይን የወጣ ክፋት እዚህ ላይ ቢጠቀስ መልካም ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው የቅዱስ ፓትርያርኩን ፎቶ መፅሔት ላይ እንዲታተም ለማድረግ ምን ያህል እንደተናነቃቸውና ስለማያስኬዳቸው ግን በስንት ጭቅጭቅ እንዳወጡት መታዘብ ተችሏል፡፡ በተለይ የህንፃ አሰሪ ኮሚቴው አባላት በአብዛኛው የማህበሩ አባላት ስለሆኑ ከማህበሩ በተማሩት ክፋት ታሪክ የማይረሳው ስህተት እየፈፀሙ ነው፡፡ ነገር ግን፦
1.     አባ ቀሌምንጦስ ጥለውት የሄዱትን ሀ/ስብከት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እርስዎ ነዎት በማለት በሌሉበት በመፅሔት ላይ መልዕክት እንዲያስተላልፉ በማድረግ፣
2.    ሊቀ ማዕምራን የማነ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ የእኛ አባልም ወገንም ስላልሆነ በሚል በመፅሄቱ ላይ ፎቶው እንዳይወጣ መልዕክትም እንዳያስተላልፉ በማድረግ
3.    ለአለቃው (አስተዳደሪው) መኪና ገዝተው በአባ ቀሌምንጦስ አማካኝነት በጉራጌ ሀገረ ለመሸለም መዘጋጀታቸው
4.    የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ እርስ በርስ በቤተ ክርስቲያን ሃብትና ወርቅ ለፅድቅ መስራት ቀርቶ እርስ በርስ መሸላለም ውስጥ መግባታቸው
5.    በሴት የማይታሙ አባት የነበሩት አቡነ ቀሌምንጣስ ከዚህ ማህበር ጋር ከተወዳጁ ወዲህ እሳቸውም እንደሌሎች እየታሙ ነው፡፡ ለብዙ ጊዜ ከሳቸው ቤት እየሰራች ያለች የቤት ሰራተኛቸው አርግዛለች፡፡ ከማን ነው ሲባል ለማመን በሚከብድ ሁኔታ አግብታ መጥታ ተመልሳ ወደሳቸው ቤት ይሻለኛለች ብላ ነው ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ ልናስተላልፍው የፈለግነው መልእክት የሰሩ ሰዎች አግባብ ባለው እውቅናም ሆነ ማበረታቻ አይገባቸውም እያልን አይደለም፡፡ እነ መልአከ መንክራት ሃይሌ የቤተ ክርስቲያንዋን ይዞታ አስከብረው ልማት ሰርተው ሲሸለሙ፣ ጥፋት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ማህበሩም ዓይኑ ደም ይለብሳል፡፡ የማቅ አባላት ግን ምንም ሥራ ሳይሰሩ ሲሸለሙ ጽድቅ ይሆናል፡፡ እስኪ በፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የትኛው ልማት ተሰራ? የመቃብር ቦታ እንኳን ያላስከበረ ደብር ነው፡፡ ከበሩ መዘጋጃ ቤት ነው የሚጠቀምበት፡፡ ህንፃውም ስንት አባቶች የደከሙበት ነው፡፡ እንዲውም አሁን ያለው አለቃ ለመዘግየቱም ለሙስናውም ከህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ጋር በመሆን ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሀብት አባክኗል፡፡ ይኸው ነው የማህበሩ ሚዛን የሰሩትን ከልክሎ ያልሰሩትን ግን መሸለም፡፡ ቦታቸውን የለቀቁት አባ ቀለምጦስ የአዲስ አባ ሊቀ ጳጳስ ከሆኑ በቦታው ላይ ያለው ሊቀ ማእምራን የማን እንደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልእክት የማያስተላልፍበት ምክንያት ምንድነው? ቢባል ያው የተንሻፈፈ ሚዛኑና ዘረኛነቱ ነው፡፡ ፍርዱንም ሕዝብ ይፍረድ፡፡ ምንም እንኳን ሊቀ ማዕምራን የማነ በዚህ እኩይ ማህበር ወዳጅነትም ሆነ መሞገስ ያስፈልገዋል ብለን አናምንም፡፡ ምክንያቱም ወቅብዐ ኃጥአንሰ አይትቀባዕ ርእስየ እንደሚል አንጠራጠርም፡፡ አንድ ነገርም ማለት ይቻላል ሊቀ ማዕምራን የማነና መጋቢ ብሉይ አእምረ በዚህ ጽበተ ኅሊና ባለው ማህበር መጠላታቸውም ሆነ መወገዛቸው በትክክለኛ መስመር ላይ እንዳሉና እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናቸውን በግልፅ ያስያል፡፡

እግዚአብሔር ባስቀመጣችሁ ስፍራ ጸንታችሁ ቤተክርስቲያናችንን በቅንነትና በታማኝነት አገልግሉ እንላቸዋለን፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት

10 comments:

 1. ‹‹በኢየሱስ ስም የሚደረግ ውሸት፣ስለእውነት ይቆጠራል››፡-የተሐድሶ መርህ!
  ሊቀማዕምራን የማነም ሆነ መጋቤ ብሉይ አእመረ የቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው፡፡መልአከ መንክራት ኃይሌም ንፁህ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ልጅ ናቸው፡፡ማኅበረቅዱሳን እና አቡነ ቀሌምንጦስም በተዋሕዶ እምነታቸው ህጸጽ እንደሌለባቸው ሁሉ ሰው ያውቀዋል፡፡ያለው መጠነኛ አለመግባባት እናንተ ሲሻችሁ በእምነት፣ስትፈልጉ በዘርና በሃይማኖት እያስመሰላችሁ እንደምታወሩት ሳይሆን አስተዳደራዊ ልዩነት ነው፡፡
  አሁን የእናንተ ዐላማ እነ የማነን ይዞ ማኅበሩን ለመምታትና የሞራል የበላይነት አለን ለማለት ነው፡፡ይሄን ስልታችሁን ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ካሕናት የተሐድሶ ሞግዚት አያስፈልጋቸውም፡፡ትግራውያን ካሕናትም ቢሆን ከማኅበረቅዱሳን ጋራ እናንተ እንደምትሉት ያለ ተቋማዊ የዘር ቁርሾ የለባቸውም፡፡የአዲግራቶቹ ንቡረዕድ አባ ዮሐንስና አቡነ ዲዮስቆሮስ፣የሐረሩ አቡነ ሰላማ፣የሑመራው አቡነ ሉቃስ፣የደቡብ ሸዋው አቡነ ጎርጎርዮስ፣የተራድኦ ኮሚሽኑ አቡነ ሳሙኤል፣የአርሲው አቡነ ናትናኤል ሁሉም ትግራውያን አባቶች ሲሆኑ ከማኅበረቅደሳን ጋራ በተፋቅሮ ይሠራሉ፡፡
  የማነም ቢሆን ሪፖርቱን ለጠቅላይ ቤተክሕነት ሲያቀርብ ማኅበረቅዱሳንን አልወቀሰም፡፡ዝምብላችሁ ሳትወከሉ ጥላቻ እየዘራችሁ መንጋውን ለመበተን የምታደርጉት ውንብድና ያሳዝናል፡፡አንድ ሳምንት ለስደተኛው ሲኖዶስ ትጫወታላችሁ፣በሌላኛው ለሀገር ውስጡ ትሰለፋላችሁ፣በሌላ ቀን ደግሞ ለፕሮቴስታንቶች ትከራከራላችሁ፡፡አይገርምም!ተሐድሶ ማለት ይኸው ነው፡፡
  ዐላማው ለፌ ወለፌ የሆነና የራሱ አቋም ሳይኖረው ሁሉን የሚቃወም ማለት ነው፡፡በውስጠ ታዋቂ ‹‹በኢየሱስ ስም የሚደረግ ውሸት፣ስለእውነት ይቆጠራል›› የሚል መመሪያ ሳይኖራችሁ አይቀርም፡፡መልአከ ምንክራት በነ ሐራ ስማቸው መጠራት ሲቆም የግርግር አጀንዳችሁ ርእስ አጣ መሰል ከላይ ታች ወሬ ትቃርማላችሁ፡፡በዚህ ከንቱ ወሬ ስንት ሰው በስሙ ወደምትወሸክቱበት ጌታ እንደምትወስዱ እሱ ይወቅ!

  ReplyDelete
 2. ኅዳር 3 ቀን 2008 ዓ.ም.
  ማኅበረ ቅዱሳን ዘረኛ አይደለም፡፡ ለዚህ ማስረጃ ለመፈለግ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ የአባላቱን ስብጥርና በወዳጅም በጠላትም የተመሰከረለትን ውጤታማ የፍቅርና የአንድነት አገልግሎት ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የማኅበሩ አባል ያልሆኑት እነማናቸው? እንኳንስ ኢትዮጵያውያን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑ አያሌ የውጭ ሀገራት ዜጎች አሉ፡፡ የማኅበሩን አባላት ያገናኛቸው ሃይማኖት ብቻ እንጂ ወንዝና ተራራ እንዲሁም ሌሎች ደካማ የሆኑ ሥጋዊ አስተሳሰቦች አለመሆኑም ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የክርስትና መሰረቱም ዘረኝነት አይደለም፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ በተዋሕዶ የከበረው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግማዊ አዳም የተባለው የአዳም ልጆችን ሁሉ አንድ ለማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ዘረኝነት በክርስትና ሃይማኖት ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ሕዝቡን አንድ አድርጋ እንደ ድርና ማግ ያስተሳሰረችው በክርስትና ሃይማኖት ላይ ተመስርታ ነው፡፡ የቤ/ክኒቱ ዓላማ የክርስቶስ ዓላማ ስለሆነ ሕዝብና አሕዛብን አንድ ማድረግ ነው፡፡
  የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ዓላማ ስለሆነ የአዳም ዘር ሁሉ በአንዲቱና እውነተኛይቱ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጥላ ሥር በፍቅርና በአንድነት እንዲሰባሰብ ማድረግ ነው፡፡ መጽሐፉስ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት ብሎ የለም፡፡ ኤፌሶን 4፣5፡፡
  ስለሆነም በዚህ ብሎግ ላይ የቀረበው ዘገባ ሁሉ የአደባባይ ውሸት ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ የአንድነትና የፍቅር ጠላት ሆኖ ሳለ የርሱን ግብር ለሌላ ለመስጠት መሞከሩ ነው፡፡ እስኪ በመጀመሪያ የአባቶቻችሁን የነ ሉተርን፣ አርዮስን፣ መቅዶንዮስንና መሰሎቹን ታሪክ አጥኑ-የዘረኝነት፣ የክህደት፣ የጥላቻ፣ የኑፋቄና ዛሬ በዓለም ላይ እኩይ ተግባራት መሰረቶቹ እነርሱ አልነበሩም ወይ? ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶስ እነዚህን እኩይ ተግባራት ሁሉ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ብዙ ማስረጃ የሚያስፈልገው አይደለም-የአደባባይ ምስጥር ነውና፡፡ በአጠቃላይ የብርሃን ሥራ የሆነው የማኅበረቅዱሳን አገልግሎትና የፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ የጨለማ ሥራ እንዴት ይገናኛል?

  ReplyDelete
 3. Ere tinish eferu kiristyan kehonachihu kedmo bekedmo kirstinachihu dihre getsu yetekefetew lesidib new? kidus dawit leafe tebaki anurlet bilo tselyual esti enantem yaltegera yesidib afachihu yarf zend tselyu mahibere kidusanin enawkachewalen lemehonu beageritu hulu yetenesu gudayoch enersu yalgebubet yelem eyalachihun new ?wishet wishet wishet beza beza yesemonu beagerachin yederesew rehab lay mak eju yinorbet yihon?

  ReplyDelete
 4. እናንተ ጽላት ታውቃላችሁ.... ጉደኞች... ግብረ ሶዶሙን 'ዲን' አሸናፊ መኮንን ረሳችሁት...

  ReplyDelete
 5. እነ እምነት የለሾች የእግዚአብሔር ቤት አፍራሾች ለመሆኑ ሶስት አላክ አለ እንዴ አራተኛ ያላችሁት? አንድ አምላክ እንጂ ሶስትም ሆነ አራት አምላክ የለም። ሚሥጢረ ሥላሴን ሥላልተገነዘችሁ ሥታችሁ ለማሳት ዘላበዳችሁ። ለነገሩ ከመናፍቅና ክርስትናን በተግባር ከማያውቅ ሐሰትና ክፋት እንጂ ሌላ ምን ይገኛል።

  ReplyDelete
 6. Very stupid article. What a devil spirit is covering your eyes all????/

  ReplyDelete
 7. የአብዬን ወደእምዬ፡፡ የራሳችሁን ተግባር ለማህበሩ ለመስጠት ያማትቆፍሩት ድንጋይ የለም፡፡ ግን አንሰማም እኛ የመናፍቃን ተሀድሶ ወሬ በጣም ነው የሰለቸን፡፡ ዘረኝነት፣ፖለቲካ፣ ስድብ፣ ነቀፋ፣የእንግዳ ትምህርት ይዛችሁብን የመጣችሁት እናንተ ናችሁ የእናንተ ድምጽ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ነው፤ ክፉውን ስራችሁን ለማህበሩ ጥሩ የሚባል ባይኖራችሁም ግን የራሳችሁ ለማድረግ የምትጥሩት ነገር ይገርመኛል፡፡ እስኪ ገጻችሁን ተመልከቱት፤ ዜናችሁ የሚያተኩረው ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ የእናንተን ማንነት ለመረዳት እኮ የለጠፋችሁት ገጽ ነው የሚያሳብቅባችሁ፡፡ የምትገርሙኝ በአይን የሚታየውን እውነት ለመሸፈን የምታደርጉት ድርጊት ሁልጊዜ ያስደንቀኛል፡፡ በእርግጥ የተኩላው ባህሪ መሆኑን ብረዳም ግን ይህንን የማያውቁ የዋሀን ሲታለሉ ስለተመለከትኩኝ ነው፡፡ ማስተዋሉን ይስጣችሁ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር አምላክ ያበርታልን፡፡ ማህበሩን ያስፋልን፡፡ ደስ የሚለው እናንተን የማሰማ ጆሮ የላቸውም ለማዘናጋት የምትሰሩት ስራ ደግሞ ታውቆባችኋል፡፡ እድሜ ይስጣቸው የማህበረ ቅዱሳን ወንድሞቻችን ሁሉንም በግልጽ እያሳዩ እያስረዱን ገብቶናል ተረድተናቸዋል፡፡ አምላክ እስከፈቀደልን ጊዜ ድረስ ሁልጊዜ ከእነርሱ ጎን ቆመን እንሰራልን፡፡

  ReplyDelete
 8. Makoch maninetachihu sinegerachu ende Fiyel kibe Tolo yaletsehay Tikeltalachihu Yesidb af yalew mahber Bealem lay Yifeleg ketebale Mahbere kidusan New HARAYETEBALEW MID YACH MECHENEWE TIMHRTE WENJEL YEMISEBEKBET HULE SIDB..SIDB...SIDB EWROCH ZEREGNOCH NACHHU ATSDAKINA KONAGNIS MANADEREGACHIHU YEKEDMO ABATACHIHU SEYTAN WISHETAM NEBR ENANTEN SIMKEYRACJIHU YETEFETERACHIHU SEYTAN AN OCH NACHHU BE HAK YEMIFERD EGZIABHER YIFREDBACHIHU LEBOCH ENANTEN LEBA TILALACHIHU .MENAFKAN ENANTE YETELACHIHUTIN MENAFK TILALACHIHU MUSEGNOCH ENANTEN MUSEGNA TILALACHIHU AMENZRAWOCH ENANTE AMNZRA TILALACHIHU SIMU AYMETINACHIHUM SIM KEYRU ZEREGNA KIDUS YELEM DEGMO BIHERESEBOCHIN MEKUTER JEMERACHIHU HATIATACHU BEGZIABHER YIKOTER ENA

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous November 14,2015 at 8:24Pm
   በአንተ እውቀት ምሳሌ አግኝተህ አሥጨፍረሀል ወይም ነገር አሳምረሐል። ለመሆኑ የፍየል ቅቤ ብቻ ነው በፀሐይ የቀልጠው ብሎ ያሥተማረህ የእግዚአብሔርን ቤትና እውነትን እንድትቃወም ያሰማራህ አባትህ ነውን? ህይወት የሚሆንህ ጽድቅን የምታገኘው ያንተውን የተጠላ አሥመሳይነትንና የተንኮል ምግባር ለሌሎች በመሥጠት ሳይሆን ከሐጢያትህ በመፀፀት ሐያተነትህን በማመንና በመናዘዝ ነው። ተደብቆ ክርስትና፣ ሳይሆኑ በማስመሰል ክርስትና፣ ክርስቶስ የሰጠውን የእምነት ነፃነት በመፃረር ቤተክርስቲያንን በመሳደብና በማጥላላት ክርስትና፣ ውሸት በመንዛት ክርስትና፣ በዘለፋ ክርስትና፣ በአጠቃላይ በዲያቢሎስ አሠራር እየተመላለሱ ክርስትና የለምና አትድከም። በሌሎች ቤትና እምነት እየገባ የሚበጠብጥና በጎችን የሚነጥቅ ከዛም የሚገል ዲያቢሎስና ሰራዊቶቹ ናቸው።

   Delete
 9. እንደማህበረ ቅዱሳን ድካም ቢሆን ተኩላ ተመሳስሎ ባልገባ ነበር I love Mehberkdusan kefrachew tawkuachrwalacue yemilewe bezulgeeeeeeeeeeeeeeeeèeeeeeeeeeeeeeee

  ReplyDelete