Saturday, November 14, 2015

በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ባልተፈታው ችግር ምክንያት ካህናቱ ደመወዝ የሚከፍላቸው አጡ

Read in PDF

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስንዘግብ እንደነበረው በደብሩ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስናና ብልሹ አሰራር በአንድ ወገን ለመሸፋፈን በሌላው ወገን ደግሞ ይህን ለማጋለጥና ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ተጠቂዎቹ የደብሩ ካህናት ሆነዋል፡፡ የደብሩ ካህናት ሙዳየ ምጽዋት ባለመቆጠሩ ምክንያት ደሞዝ አልተከፈላቸውም፤ ሙዳየ ምጽዋቱ እንዳይቆጠር አለቃውን አናስገባም በሚሉ ሙሰኞችና እነርሱ ባሳደሟቸው ክፍሎች በተደረገው አመፅ ምክንያት መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያና የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው በትናትናው ዕለት ተሰብስበው መጥተው በሀገረ ስብከቱ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አቤት ብለዋል፡፡ ችግሩን ለኩሰው ያሉትና በዝርፊያ የበለፀጉት የተደላደለ ኑሮ ሲኑ ካህኑ በረሃብ ላይ ነው፡፡
ቀደም ሲል በካቻማሊ ተጭነው ወደ ሀገረ ስብከቱ እና ጠቅላይ ቤተክህነት በመሄድ አለቃው ይነሱልን ቢሉም አጣሪ ልከን ችግሩን አውቀን ነው አለቃውን የምናነሳው ተብለዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በዚህ ጥያቄ ላይ ወሳኝ ነገር ያስተላለፈ ሲሆን ይኸውም በህገወጦች አድማ አለቃ አይነሣም በማለት ለደብሩ አለቃ ገብተው እንዲሠሩ መመሪያ ተሰጥቶአል፡፡ አለቃውም ገብተው መሥራት ጀምረዋል፡፡ ይህ ጥሩ እርምጃ ነው፡፡ አለቃው መነሣት ያለባቸው በህገወጥ ድርጊት ሳይሆን በቦታው ላይ በመደባቸው በሀገረ ስብከቱ አሰራር ብቻ መሆኑ መረጋገጡ በህገወጥ መንገድ መጓዝ ለሚፈልጉ ህገወጦች ትልቅ ማስተማሪያ ነው፡፡

ጥቅምት 8/2008 ከሀገረ ስብከት፣ ከደብሩ አስተዳደር፣ ሰንበት ትምህርት ቤት፣ ከሰንበቴ ማኅበራት የተውጣጡ ሰዎች በተገኙበት በእለቱ ከ3-9 ሰዓት በፈጀው ውይይት የማጣራት ሥራ የተሠራ ሲሆን ወሳኝ ነገር ተገኝቶአል፡፡ በመጀመሪያ የፉካ ባለቤቶች እኛ በማናውቀው ነገር ነው መናጆ የሆነው በሠበካ ጉባኤው መውረድ እናምናለን ብለዋል፡፡ አንዳንዶች በጥቅም ሌሎች በየዋህነት አድማውን የተቀላቀሉ ሽማግሌዎች የሰሙት አንድ እውነት ቢኖር የቤቱ ሽያጭ ጉዳይ ነው፡፡ እስከዚያ ቀን ድረስ ለደብሩ የተሰጠውን ቤት ኮሚቴዎቹ መሸጣቸውን አልሰሙም ነበር፡፡ አሁን በመስማታቸው ግን አሰላለፋቸውን እያስተካከሉ ነው፡፡ ቦታው ላይ ለተፈጠረው ለዚህ ሁሉ ውዝግብ መነሻው የቤቱን ሽያጭ ለመደበቅ የተደረገው ከንቱ እንቅስቃሴ ነው፡፡ አሁን ግን ጉዳዩ እስከ ፓትርያርኩ ስለደረሰ በገንዘብም ሆነ በሌላ መንገድ አፍኖ ማስቀረት የሚቻል አይደለም፡፡
ቤቱን ገዝቶታል ተብሎ የሚጠረጠረው ይድነቃቸው መኮንን ወደ ውጭ ሀገር እንደሄደ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ወደ ውጭ የሄደበት ምክንያት ባይታወቅም ጥሩ ሂደት ላይ ያለውን ነገር እንዳያጓትተው ያሰጋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ለመደበው አጣሪ “ቤቱን የገዛው ሰው ጀርመን አገር ነው ያለው” ብሎ የተናገረው እሱ ነውና፡፡ በአጣሪዎች ሪፖርት የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ቤቱን ተዋውለው የሸጠውና ካርታ የተረከበው እስጢፋኖስ ሀይሉ መሆኑን ስለደረሰበት ተጠርተው ይጠየቃሉ የሚል ተስፋ አለ፡፡ መሆንም ያለበት ይህ ነውና፡፡
ከዚህ ቀደም የህንፃ አሰሪ ኮሚቴው እቃ ግ የሆነው በለጠ ደሳለኝ ጉዳ ቤቱ 2ሚሊዮን 6ዐዐ ሺህ ነው የሸጥነው ቢልም አሁን ለመጡ የሀገረ ስብከቱ አጣሪዎች ደግሞ የበለጠ እህት ባል የሆነው አቶ ይድነቃቸው መኮንን ለሀገረ ስብከቱ አጣሪዎች 2 ሚሊዮን 400 ሺ ነው የሸጥነው ብሎአል፡፡ የሀገረ ስብከቱ አጣሪዎች ሰነዳችሁን አቅርቡ ብለው ሲጠይቁ በከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የነበረው ይድነቃቸው የፈራሁት አልቀረም ብሎ ሳያስበው አምልጦት ተናገረና ዝርዝር ሁኔታውን ልትጠይቁን ነው እንዴ?” ሎ በድንጋጤ ሲዋጥ ተስተውሏል፡፡ በመቀጠል ቤቱን የገዛው ከጀርመን የመጣ ሰው ነው፡፡ ቤቱን ከሰጡት ሰጪዎች ካርታውን የተቀበለው ከጀርመን ለመጣው ሰው ውልና ማስረጃ ሄዶ ሽያጩን ያከናወነው እስጢፋኖስ ሀይሉ ነው ብለው ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ከዚያ 200 ሺ ብሩን ለተለያየ ነገር አውለነዋል በማለት ለአጣሪዎች መልሰዋል፡፡
ሀገረ ስብከቱ የተላኩ አጣሪዎችም ከማስጠንቀቂያ ጋር የደብሩ አስተዳደር ሰነዱን እንዳቀረበ ሁሉ እናተም በአጭር ጊዜ አቅርቡ ተብለው ሲጠየቁ የህንፃ አሰሪው ሊቀመንበር ውጭ ሀገር የገዛው ሰው ውጭ አገር ያለ በመሆኑ ማቅረብ አንችልም በማለት ናገም እንደሚያዋጣቸው አይተው ከሁለት ቀን በላ የይድነቃቸው ወንድም ዮናስ መኮንን እና የእስጢፋኖስ ወንድም ወጣት የትናዬት ሰነዱን ለሀገረ ስብከቱ አስረክበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በበቂ መረጃ ላይ ተመስርተን የዘገብነው ይህ ጉዳይ አሁን በህግ የመጠየቅ ደረጃ ላይ የደረ እንደሆነ መመልከት ይቻላል፡፡ የተሰየመው የሀገረ ስብከቱ አጣሪ ከዚያ ስብሰባ በኋላ ጉዳዩን አጥንቶ ትልቅ በየት ደብር ያልተፈፀመ ደብሩ ሀገረ ስብከቱ ሳያውቀው 310 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት በህገወጥ መንገድ በተምታታ ሂሳብ መሸጣቸውን ከአንደበታቸው መስማቱን ሽያጩም ለመደበቅ ጀርመን ላለ ሰው ነው የሸጥነው ብለው መናገራቸው በተጨማሪ ህገወጥ ሰበካ ጉባኤ ስለሆነ መፍረስ አለበት ብሎ ወስኖ ለዋና ስራ አስኪያጁ ሪፖርት ማድረጉን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ሀገረ ስብከቱ ይህን ትልቅ ወንጀል ወደ ህግ እንደሚወስደው እና ቤቱን እነማን እንደገዙት ማቅረብ እንዳለበት ሁሉም ያምናል፡፡ ሽያጩም ታግዶ ጨረታ ወጥቶ መቀጠል አለበት የሚል ተስፋ አለ፡፡ ቦታው ላይ ይህ ሁሉ ሁከት የተፈጠረው ነገሮችን ከሃይማኖት ጋር ለማያያዝ የተሞከረው ይህ ነገር እንዳይወጣ እንደሆነ ማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በቀጣይም ዕሉ ጨረታ፣ የእቃ ግው፣ የመቃብር ሽያጩ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ስርቆት በቀጣይ የሚጣራ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሎአል፡፡  

No comments:

Post a Comment