Monday, November 16, 2015

ተሃድሶ የእምነት መግለጫዉን ይፋ አደረገ

ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ፈቃዱ ልንመለስና ሕይወታችንንና አገልግሎታችንን እንደ ቃሉ ልንቃኝና ልናርም ይገባል የሚል የለውጥ ጥያቄ በማንሣታቸውና ወንጌልን በማስተማራቸው ምክንያት የማያምኑትን እንደሚያምኑና ማንነታቸው ያልሆነውን መገለጫቸው እንደሆነ ተደርጎ ስማቸውን በማጥፋትና በመክሰስ ከእናት ቤተክርስቲያናቸው በግፍ የተገፉትና አሁንም በየሥፍራው በመከራ የሚገኙትን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ማንነታቸውንና እምነታቸውን የሚገልጥ የእምነት መግለጫ ታትሞ በይፋ ተመረቀ፡፡ ጥቅምት 14/2008 ዓ.ም ከቀትር በኋላ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዐት ላይ ካህናት፣ ሰባክያን፣ ዘማርያንና ምእመናን የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በጉባኤው ታድመዋል፡፡

የምረቃ ስነ ሥርዐቱ በካህናት አባቶች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በጉባኤው ላይ የቀረቡት ዋና ዋናዎቹ መርሐ ግብሮች መነባንብ፣ የእምነት መግለጫን ታሪካዊ አመጣጥና ይዘትን የሚያሳይ ትምህርት፣ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ በሚል ርእስ ስለተዘጋጀው የእምነት መግለጫ ይዘት ዳሰሳና እኛ የምናምነው እንዲህ ነው በማለት ይህን የእምነት መግለጫ ስላዘጋጁቱ የስነ መለኮት ምሁራንና ከልዩ ልዩ ሥፍራ የተውጣጡ ወገኖች ማንነታቸውን የሚገልጥ ሰነድና እምነታቸውን በጽሑፍ አዘጋጅተው ለማሳተም ያነሣሣቸውን ዓላማ የሚገልጥ ጽሑፍ ይገኙበታል፡፡
ባለ 42 ገጹ “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ” ስድስት ዐበይት ክፍላት እና 32 ንኡሳት አርእስት አሉት፡፡
ይህ ሥራ ለተሐድሶ እንቅስቃሴ መልክ ሊሰጥ የሚችል፣ በተሐድሶ እንቅስቃሴና ማንነት ላይ በሌሎች ለሚነሡ የማንነት ጥያቄዎችና የተሳሳቱ ብያኔዎች መልስ የሚሆን፣ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ያለውን ራእይ ግልጽ የሚያደርግና ከዚህ ቀደም በተሐድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ይታይ የነበረውን ክፍተት የሚሞላ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
በልማዳዊና ክርስትናን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መንገድ በሚከተሉና ፀረ ወንጌል በሆኑ ቡድኖች ዘንድ የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚጠራው “ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ” እየተባለ ነው፡፡ ይህ አባቶችን ለማሳሳትና ሕዝብንም ለማደናገር የሚጠቀሙበት አጠራር የሚያመለክተው የተሐድሶን እንቅስቃሴ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ተልእኮ ሰጥተው ያሰማሩት እንቅስቃሴ ተደርጎ እንዲታይ ለማስመሰል የተሰጠው ስያሜ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን ፕሮቴስታንታዊ ያልሆነ “ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ” ሊኖር እንደሚችልም የሚጠቍም ነው፡፡ ወንጌላውያን በሚባሉት በኩልም በተሐድሶ እንቅስቃሴና በወንጌላውያን መካከል “የማንነት ተመሳስሎ” እንዳለ ተደርጎ የሚወሰድበት አጋጣሚ አለ፡፡ በሁለት በኩል ያለውን የተዛባ አረዳድ ለማረም “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ” የተሐድሶን እንቅስቃሴ ትክክለኛ ማንነት ለመግለጽ የሚረዱ አናቅጽን የያዘ በመሆኑ በሁለቱም አቅጣጫ በማንነቱ ላይ ጥያቄን ለሚያነሡ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥና ትክክለኛ ማንነቱ እንደሚታወቅ እሙን ነው፡፡
ይህ የእምነት መግለጫ በመቅድሙ ላይ “የእግዚአብሔር ቃል የኾነው መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የምትገዛበት ሕገ መንግሥት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርታም ልዩ ልዩ ትምህርቶችን ቀርጻለች፤ ሥርዐቶችንም ሠርታለች፡፡ ሕገ መንግሥቷ ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረን ትምህርትም ኾነ ሥርዐት ሊኖራት አይገባም፡፡ ቢኖራት ግን የስሕተት ትምህርት ነው፡፡” በማለት መጽሐፍ ቅዱስ መሠረቱ መሆኑን በማወጅ ነው የሚጀምረው፡፡
የእምነት መግለጫው ዐዲስ መሠረት አልጣለም፡፡ የታመኑትና ከቅዱስ ቃሉ ጋር የሚስማሙ ጥንታውያኑንና ነባሮቹን የእምነት መግለጫዎች፣ በእነርሱ ላይ የተመሠረተውን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐተ አምልኮት እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ጕዳዮች ላይ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ያለውን ዐቋም መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡
ብዙ ጊዜ በፀረ ወንጌል ኀይላት ዘንድ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሲገለጥ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት፣ ሥርዓት፣ ትውፊትና ቅርስ ለማጥፋትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ፕሮቴስታንትነት ለመለወጥ የተደራጀ አፍራሽ ኀይል ተደርጎ ነው፡፡ ይህም አባቶችንና ምእመናንን ለማሳሳትና ለማደናገር የሚደረግ ስም ማጥፋት መሆኑ ግልጽ ቢሆንም ጊዜ እንደሚፈታው ይታመንበት ነበር፡፡ ስለሆነም የእምነት መግለጫው የሚያምኑበትን ማንነትና እምነታቸውን በግልጽ በማሳወቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በአጠቃላይ የእምነት መግለጫው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከሞላ ጐደል “ልብ እየገዛ” የመጣ መሆኑን ያሳየበት፣ ማን መሆኑን የሚያስረዳበት፣ የት እንደሚደርስ ግቡን ያመላከተበት ትልቅ ሰነድ ነው፡፡ ተሐድሶው ግቡን እንዲመታ የእምነት መግለጫው በብዛት ታትሞ ወደሚፈለገው ሕዝብ መድረስ እንዳለበት አያጠራጥርም፤ ይህንንም በማሰብ የእምነት መግለጫው ለተጠቃሚዎች በነፃ እንዲሰራጭ መደረጉን ተመልክተናል፡፡

የእምነት  መግለጫውን ያዘጋጁት ማኅበራትም ሆኑ በየስፍራው ለውጥ ፈላጊ የሆኑ ወገኖች ሁሉ የእምነት መግለጫውን ሊመሩበት፣ በዚያ መሠረት አገልግሎታቸውን ሊያካሂዱበት ስለሚገባቸው እምነታቸውንና አስተምህሯቸውን በመግለጫው መሠረት እንደሚቃኙ ይጠበቃል፡፡  የእምነት መግለጫውን ሙሉ ጽሑፍ ከዚህ ዘገባ ጋር ለተጠቃሚዎች አቅርበናል፡፡

46 comments:

 1. እግዚአብሔር መልካም ነው።
  ትናትናም ሲስራ የነበረ ዛሬም ሆነ ነገ ለዘላለም ሲስራ ይኖራል።
  እግዚአብሔር ይባርካችሁ እውነት ነው ተሐድሶ ያስፈልገናል። ሌላው ተሐድሶ ለሚለው ቃል እንግዳ የሆናችሁና ትርጉሙ ያልገባችሁ ሰዎች እባካችሁ የቅኔ መምሕራኖችን እየጠየቃችሁ ትርጉሙን በትማሩ መልካም ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን መጀመሪያ እራስህ ተሐድሶ ምን እንደሆነ አትጠቅም? በክርስቶስ የሆነ ሀማኖትና በደሙ የተመሰረተች አለማዊ አደሉምና አይታደሱም። መታደስ ያለበት ያንተው አስመሳይ ህይትወና ፕሮቴስታናዊ ተሐድሶነትህ ነው።

   Delete
 2. የጠፋው በግNovember 16, 2015 at 5:26 PM

  Praise God for this wonderful Information to see/read this unexpected decision of improvement as per the inspired word of God by the real children, who paid and are paying the price to arrive on this golden opportunity!

  No matter the position we have, trust me! most people including myself will come back to our beloved historical church from where we are now.

  Thank you God for showing me this before my walk of life is completed.

  I think the real stretching of Ethiopian hands is coming now through confessing as per the word of God.

  God bless you all!

  የጠፋው በግ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን የሐትሰና የክህደት ከሞትህ በፊት ማየትህን ከመናፈቅ የሚሻልህ የንስሃን እድሜ እንዲሰጥህና ከዚህ ከጥፋት ወጥመድ እንድትወጣ ነበር። ግን እንደይሁዳ ከሞት ወደ ሞት መጓዝህን ወደድከው። እግዚአብሔር ይመልስህ።

   Delete
 3. የጠፋው በግNovember 16, 2015 at 5:26 PM

  Praise God for this wonderful Information to see/read this unexpected decision of improvement as per the inspired word of God by the real children, who paid and are paying the price to arrive on this golden opportunity!

  No matter the position we have, trust me! most people including myself will come back to our beloved historical church from where we are now.

  Thank you God for showing me this before my walk of life is completed.

  I think the real stretching of Ethiopian hands is coming now through confessing as per the word of God.

  God bless you all!

  የጠፋው በግ

  ReplyDelete
 4. ሚናችውን መለየታችው በጣም ጥሩ ነው ምክንያቱም ከእንግዲ የኦርቶዶክሱን ምእመን በምንም መንገድ ማሳሳት አትችሉም.... ድሮስ ከሃራጥቃን መናፍቅ ጥሩ ዜና አይሰማ

  ReplyDelete
 5. le Ashenafi gebremariyam situt. Esunew yemibarikilachihu

  ReplyDelete
 6. ደስ ይላል! ጌታ ስሙ ይክበር! ሁሉም ነገር ከርሱ ዘንድ ነዉ የሆነልን ክብር ልስሙ ይሁንልን! ጌታ ራሱ የሚመራዉ እንቅስቃሴ ስለሆነ ማንም ሊያቆመዉ አይችልም! ጌታ ገና ከዚህም በላይ ይሰራል! ጌታ አገልግሎታችሁን ይባርክ ዎዳጆች! ጸጋ ይብዛላችሁ!

  ReplyDelete
 7. I am Orthodox Christian, but I always looking forward for REFORMATION in the Ethiopian Orthodox church otherwise I was about to goo to were gospel of Jesus the Word of God is freely tolled without any barrier. thank you and you came jus about time before I was about go to other churches.

  ReplyDelete
  Replies
  1. That is your free freedom that Jesus gave you and others. Orthodox tewahido church is not foce anybody to belive her faith. If any one who belive and trust her faith or
   doctrines can go with her.

   Delete
 8. ዋሾዎች ቤተክርስትያናችንን ለቀቅ አድርጉ፡፡ አንፈልጋችሁም

  ReplyDelete
 9. በጣም ደስ ይላል። እውነተኛ የቀደመችው ቤተክርሰቲያን ድምጽ ነው። ማቅም ፕሮቴስታንትም አለመሆናችሁን ያስመሰከረ መግለጫ።
  ተባረኩ

  ReplyDelete
 10. ELLLLLLLLL...........thank you Jesus, Kebete kerstiYan meriwoch mels entebkalen

  ReplyDelete
 11. egnam bezih eminetachihu new haratika tehadiso yalinachihu. go to protestant church. they are best fit for such doctrine.
  the most I hate in this world are those bloody muslims and those homosexual protestants.

  ReplyDelete
 12. አይ ተሐድሶ
  በእዉነት አዝነናል በትእቢት እግዚአብሄርን ማገልገል የርሱም መሆን ይቻላልን?
  ቤተክርስቲያንን ዶግማ እና ቀኖና ከተቃወማችሁ ለምን ሌላ የእምነት ተቋም
  አትመሰርቱም? ጊዜዉ እንዲህ ላለዉ የእምነት ክህደት ትምህርቶችን ለማስፋፋት
  የተመቸ ጊዜ ነዉ፡፡ትንቢቶችም እየተፈፀሙ በመሆኑ በጊዜዉ የተወለዳችሁ
  የአዉሬዉ መንገድ ጠራጊዎች ናችሁ፡፡ቢሳካላችሁ ለአዉሬዉ ስልጣን በመሰጠቱ
  እና ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ግድ በመሆኑ እንጂ የእዉነት አገልጋዮች ስለሆናችሁ አይደለም፡፡
  በትዕቢት በአዉሬዉ ስልጣን በሀሰተኛዉ እና ትንቢት በተነገረለት ሊመጣ ባለዉ አሳች
  መንፈስ መነደፋችሁን ታዉቁት ይሆን? ለመሆኑ ከሌሎች ዘመን ከፈጠራቸዉ
  የሀሰተኛዉ ኢየሱሳዉን ልዩነታችሁ ምንድን ነዉ? ለምንስ ጥርግ ብላችሁ በነሱ አዳራሽ
  ለማገልገል አልገባችሁም? ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ጋ አማላጅ ነዉ
  ይህ ቀኖና ሳይሆን ዶክትሪን ነዉ:: የእምነት ትምህርት ነዉ:: ስለዚህ በዚህ ከእዉነት የመዳን
  መንገድ ወጥታችኋል…እናንተ ስታችሁ ሌሎችን ታስቱ ዘንድ ለዚህም ትተጉ ዘንድ ጠላት
  አሳቹ ያግዛችሐኋል፡፡

  ReplyDelete
 13. ተመስግን ለዚ ህ መብቃታችን አጅግ ደስ ይላል ጌታ ሰሙ ይባረክ ለዚህች ቤተክረሲያን ትልቅ ምስራች ነው .አሁን ሁሉ ነገር መለክ እየያዘ ነው ፡፡
  ጌታ ሆይ ተመስገን !!!!!

  ReplyDelete
 14. What is the new b/n tehadiso and those Menfiakans/tehadiso then. nothing new

  ReplyDelete
 15. Interesting document, this was the belief of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church before Zere Yaeqob messed it up. So this is not reformation rather it is getting back to the Original belief. The doctrine is also analogous with the four Oriental Orthodox Churches. We all expect an answer from the Holly Synod which is the Higher authority off our church after all.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @Anonymous November 18, 2015 at 1:48 AM

   What Oriental church believes in any of these doctrines? Please name one with a sufficient evidence. They all believe in the intercession of the saints even after their departure and the Eucharist being the literal body and blood of Christ not symbolic. I agree the Ethiopian Church needs "restoration", doctrines consistent with the other Oriental Churches. We emphasize way too much on the intersession of the saints but never speak of Jesus Christ being the eternal high priest, the mediator between man and God, who is able to take away sin. We have a different view of the mosaic laws, as if they are still applicable for Christians. We still view the tabot as having relevancy, asides for the consecration of the Eucharist. We have countless unbiblical "gedelat" which we never find anywhere else in the ancient church. In general we have somehow deviated from the true faith of Orthodox Church. For God's sake, we try to take out demons in the name of the saints when the apostles and all the holy church fathers did it in the precious name of Jesus. I don't even want to get into the so called "teamire mariyam". So much fallacy and inconsistency with the bible and the ancient Orthodox Church. This is an undeniable truth, but to proclaim we should accept protestant teachings is a completely different approach. I expect an answer for your claims. God bless!

   Delete
  2. I am sure you agree that I can not list the details off all your claims in a blog but to enlighten a bit:
   1. it states in the document which is exactly the way EOTC accepts it:
   ስለ አንቀጸ ተዋሕዶ በተፈው ገፅ 31
   “ሳይደባለቁ
   ሳይለዋወጡ
   አንዱ ለሌላው ባዕድ ሳይኾን
   ሳይከፋፈሉ
   በተዓቅቦ ተዋሕዶ አንድ ነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ክርስቶስ በአንድ ህላዌ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ኾኖል፡፡”
   2.About the Eucharist the Coptic Orthodox Church which is one of the oriental Orthodox Church also believes in the same staተment please see the link below
   “The Lord Jesus instituted the holy Eucharist on Covenant Thursday, in the Upper Room of Zion, shortly before His arrest and trial. After He celebrated the Rite of Passover of the Jews, He rose and washed the feet of His disciples, as a sign of repentance and preparation, then sat down and instituted the Passover of the New Covenant, which is the Sacrament of Holy Communion. “He took bread, blessed it and broke it, and gave it to the disciples and said, “Take, eat, this is My Body”, then He took the cup and gave thanks, and gave it to His disciples saying, “Drink from it, all of you, for this is My Blood of the New Covenant, which is shed for many for the remission of sins” (Matthew 26:26-28), and our teacher St Paul repeats the same words in 1 Corinthians (11:23-25).
   http://www.copticchurch.net/topics/thecopticchurch/sacraments/4_eucharist.html

   3. this document also agrees with the three councils accepted by oriental orthodox churches which first three ecumenical councils -- the First Council of Nicaea, the First Council of Constantinople and the First Council of Ephesus
   4. on Teamire mariam, the teamere mariyam EOTC accepts before zereyaeqob and the one we have know is completely different. For instance they have even at this age added about Abune Paulos at the end. The old Teamere mariam was justifiable by the Big book(the by bible)
   Not enough answer for your comments but

   Delete
  3. @ Anonymous November 19, 2015 at 10:29 PM

   Thank you for your response but I'm not sure if you get my point. I'll rephrase it. My statement is regarding your previous claim, "the doctrine is also analogous with the four Oriental Orthodox Churches."

   The points you made (1-3), I don't have any problems with nor was my statement regarding that. I agree this document has some truth but is also partially heretical. My points are targeted toward those partially heretical points made in the document. Even Martin Luther believed in many similar things as Catholic Church after his split from the church, but that doesn't negate the fact he made some crucial errors. Islam might teach about Jesus and his virgin birth but that doesn't mean its teachings are similar to Christianity in its entirety. In the same light, this "tehadiso" statement confesses the Eucharist is a symbolic act (look on page 35 of the document). So my question to you is, how is this “analogous with the four Oriental Orthodox Churches”? This is Martin Luther’s doctrine, a protestant.

   Also this document denies the intercession of the saints (look on page 35 of the document). So again explain to me how this document is "analogous with the four Oriental Orthodox Churches"?

   Delete
 16. እገዚአበሔረ ይባረካችሁ ነገር ግን ይህ ሰነድ ገና ብዙ ዝርዝር ይቀረዋል ለምሳሌም ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር እየተመረመረ የሚለዉ አልባት እስካልተሰጠዉ ድረስ ቆይቶ ሊያነጋግርና ሊከፋፍል ይችላል ግልፅ በሆኑ እንደ ለስዕል መስገድ ላይ ያነሳችሁት በጣም የተዳከመና ፍርሃት የተሞላበት ነዉ እኔ እናንተን ብሆን ጥያቄ ሊያስነሱ የሚቸሉትን ሁሉ በግልፅና በማያዳግም መልኩ አስቀምጠዋለሁ ስጋታችሁ ቢገባኝም የበለጠ አስጊ የሚሆነዉ ለበርካታ ጥያቄዎች ዝሆን የሚያስገባ በር መክፈታችሁ ነዉ ለማንኛዉም ተባረኩ

  ReplyDelete
 17. የተሀድሶ ማንነት ቀድሞም ቢሆን የታወቀ ቢሆንም እንዲህ እምነትን በግልጥ ማስቀመጡ ግን የጨዋ ደንብ ነው፡፡ አጥፊም ይሁን አልሚ የራስን ማንነት ገልጦ መራመድ አቋም ያለው ሰው የሚሠራው ሥራ ነው፡፡ ሌላውም ወገን አጥፊ ቢሆን ላለመቀበል፤ አልሚ ቢሆን ከጎኑ ቆሞ ለመደገፍ ይመቻልና፡፡ እንደኔ እንደኔ ግን እናንተ ተሀድሶ ነን የምትሉ አካላት ይህንን አቋማችሁን ይዛችሁ ፍትሕ ሚኒስቴር ሄዳችሁ ፈቃድ በማውጣት የራሳችሁን የእምነት ተቋም መመሥረት እየቻላችሁ፤ሕገ መንግሥታዊ መብታችሁም ሆኖ ሳለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ለመውረስ መነሳታችሁ የክፋታችሁን ብዛት ያሳያል እንጂ ምንም ቁምነገረኛነታችሁን አያመለክትም፡፡ ይህቺ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ለፍታ በቅዱሳኗ ደምና አጥንት ያቆየችልንን የሃይማኖት ቅርስ እናገኛለን ብላችሁ ማሰብ ራሱ የባልንጀራህ ሆነውን አንዳችም አትመኝ ያለውን ትዕዛዝ ማፍረስ፤ ባልደከማችሁበትም ለመበልጸግ መነሳት ነውና ከቅጣት የምታመልቱ እንዳይመስላችሁ፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን የምናመልከውን እናውቃለንና የናንተ የጥፋት ምክር አያሻንም፡፡ ለናንተ የተሳሳትን ቢመስላችሁም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ዋጋችንን እናውቀዋለንና ቀድሞም ከእኛ ያልነበራችሁ እናነተ ተውን ከእኛም ተለዩ፡፡አትበጥብጡን፡፡የራሳችሁን ተቋም መመስረት መብታችሁ ነው፤ ከመብታችሁ ውጪ መንቀሳቀስ ግን መቸረሻው ለሀዘን ይጥላችኋልና ተረጋግታችሁ አስቡ እላችኋለሁ፡፡ ደግሞም እስካሁን ተሸሽጋችሁ እሠራችሁት የነበረው በቤተክርስቲያን ላይ የዘመታችሁት የጥፋት ዘመቻ የማይታወቅ፤ ካሁን በኋላም የሚረሳ እንዳይመስላችሁ፡፡ በጓዳችን የሰገሰጋችኋቸው ብዙ እንዳሉ እናውቀለን፡፡ ፍርደ እግዚአብሔርን እየተበቅን ታግሰናችኋል፤ከዚህ በኋላ ግን እኛም ቤታችንን ለሌባ አሳልፈን አንሰጥም፤ ቅዱሳን አባቶቻችንም ዝም አይሉም፡፡

  ReplyDelete
 18. Wow that is blessed news for our future church believer and faith. We have to depend on holy bible not in something. Let us come together for truth as orthodox tewahedo church memeher. Pls forget about MK memeber . They are laid for so many years . Enough is enough now. Thanks

  ReplyDelete
 19. የተሐድሶ እና የፕሮቴስታንት ልዩነቱ ታዲያ ምኑ ላይ ነው?እኔ ደግሞ ሰው መስላችሁኝ።በሉ ደህና ሁኑ

  ReplyDelete
 20. ኅዳር 9 ቀን 2008 ዓ.ም.
  አፄ ገላውዴዎስ ያወጡት የእምነት መግለጫ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዘመኑ ቤ/ክኒቱን ይፈታተኑ ከነበሩት ከካቶሊክና የናንተ ብጤዎች የምትለይባቸውን የዶግማና የሥርዓት ልዩነት ለማሳየት ነው፡፡ እናንተ ደግሞ ውሉደ ካቶሊክ ፕርቴስታንታዊ ተሐዲሶ ሆናችሁ የእምነት መግለጫ የሚታወጡት ከማን ለመለየት ነው? በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስም መነገዱን የሚታቆሙበት ጊዜ ግን አሁንና አሁን ነው፡፡

  ReplyDelete
 21. YE KIRSTOS SIGANA DEMU METASEBIYA ENJI AMANAWI AYDELEM EYALACHIHU ORTHODOX TEWAHIDO LITIHONU ATICHILUM CHILIT YALE MENAFIKI ENJI...LIBONA YISTACHIHU

  ReplyDelete
 22. tekula mehonachihu sirachihu yimesekiral lemin ye tsafiwoch simina maninet begilts altesafem. be fitlefit sayhon be guaro yemigeba hulu ewnetegna sayhon leba new

  ReplyDelete
 23. what is the difference between your doctrine and those of protestant? it is all the same. Shame on you. now we all know What Mahiber kidusan was saying is true PROTESTANTAWI TEHADISO

  ReplyDelete
  Replies
  1. from what you are saying, I don't think you know either doctrine. Is your objective to be different from other Christians? This is the cause of all the unti-Biblical teaching we have in the church -to cater to people like you who want to make sure we are different from protestants in every way. You are probably willing to deny Christ just because the protestants believe in him (just to be different)

   Delete
  2. Yes i want to be completely different from protestant who pretends to be believers but totally non believer(be kirstos sim yemetu gin hailun yekadu amlakinetunim ye mayaminu ) don't you read the bible" ....tsidk keametsa gar min tekafayinet alewna ? birhanim kechelema gar min hibret alew? ... "

   Delete
  3. To anonymous November 19,2015 at 1:41pm
   You are so funy and cofused. The protestants and their follower do not kow what christanity means and Jesus. Calling Jesus name is not the the prediction beliving in Jesus.

   Delete
 24. I guess I am tehadso because I can't find anything I disagree with. You guys are basically declaring the orthodox christian faith removing the not so biblical practices/teachings. In my opinion, this shouldn't even be labeled as orthodox tehadeso. This should just say orthodox teaching.

  ReplyDelete
 25. elelelelelelelelelelele

  ReplyDelete
 26. ጥቅምት 14/2008 ዓ.ም ከቀትር በኋላ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዐት ላይ ካህናት፣ ሰባክያን፣ ዘማርያንና ምእመናን የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በጉባኤው ታድመዋል፡፡


  ዜና አይደል? እንዲህ ከምትሸፋፍነው እስኪ ማን ማን ተገኘ። እስኪ ስማቸውን ቁጭ አድርጓቸው። የምን መሸፋፈን ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. QIL NEH. ANTE MANEH? KEWUNET ENJI KESIMACHEW MIN ALEH?

   Delete
  2. eski ante man endehonk bemejemeriya tenager

   Delete
  3. አይ ወንድሜ ተኩላ መቼ ተኩላ ነኝ ይላል፡፡ በግ ነኝ ብሎ አይደል ልባችንን የሚያተክነው፡፡ የሚገዛው የለም እንጂ ቢችል ተኩላው በግ ነኝ ብሎ ገበያ ላይ ወጥቶ መሸጥ ሁሉ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ተኩላ በግ ነኝ አይልም፡፡ተገኙ ያልካቸው ወንድማችን መርካቶ ያለበሰቻቸው ካህናትና ዲያቆናት ዘማሪያን ናቸው የተገኙት?????????????????????????????????????????????????????????????????????

   Delete
 27. ተሀድሶ ለኦርቶዶክስ ይገባል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አትታደስምምምምምምምምምም

   Delete
 28. Ymiasazenew neger ortodox rasane aladesem bemaleta bezuwoch wodelela hayemanot eyefelesu yalebet gudaye new  ReplyDelete
 29. አሳዘነችኝ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! መቼም ያቺ ዘማዊው ልበል ምክንያቱም በመጀመሪያ ለእግዚአብሔር በድንግልና ለማገልገል ቃል ገብቶ በኋላ ግን ያፈቀራትን ሴት መነኩሴ ለማግባት ሲል ነው የራሱን እምነት መስርቶ ከካቶሊክ እምነት የወጣው ይህ ስጋዊ ስሜቱ የሚገዛው ሉተር የመሰረታት የኘሮቴስታንቱ አዳራሽና ጉባኤ አሳዘነችኝ፡፡ እንደው መች ይሁን ወንጌል የሚሰበክባት???????????? መቼ ይሁን እውነተኛው የድንግል ማርያም ልጅ ክርስቶስ ተገኝቶ ማስተዋሉን የሚሰጣቸው ????????????? ሉተር ከመሰረታት ጊዜ ጀምሮ ከስሙ ጀምሮ ስንመለከት ኘሮቴስታንት ክርስቲያን/የክርስቲያን ተቃዋሚ/ ክርስቲያንን በመቃወም፣ በመሳደብ፣ የውሸት ትምህርትና ምስክርነት የሚሰጥባት የአህዛብ መንደር ጌርጌሳዊያን የበዙባት ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ፣ መሰብሰቢያ መሆኗን የምታቆመው መቼ ይሁን?????????????????????????? አሁን አሁንማ የከሰረ ዘፋኝ፣ መተተኛው፣ ጠንቋይ፣የከሰረ ነጋዴ፣ የቢዝነስ ስፍራ ሆና በግልጽ እየገቡባት የለመዱትን ዓላማቸውን ማሳኪያ ሆናለች፡፡ አሳዘነችኝ፣ እግዚአብሔር ሆይ ልብ ሰጥተሀቸው ሰው ከመሰረታት መርከብ ውስጥ ገብተው አንተን ያገኙ እየመሰላቸው ተኩላው ያየውን አምላክ ብቻ የሚያመልኩትን የዋሁን ህዝባችን እውቀት በማጣት እየጠፋና መርከቢቷ ጭራሽ ሰጥማ የአውሬው ማጫወቻ ሆናለችና እባክህ አምላካችን ህዝብህን ፈውሰው፡፡

  ReplyDelete
 30. Tekual temsaslo begebame teterargo degmo mewtatu aykereme yetwhedo lejoche ahuneme Eysuse krestose bedemu ywajatene batekrstiyane ke asawi mesei yetbklene lenesume lbona ysetlene abate masmesele seyawkubete yelaba aynedereke meleso lebyaderke alu abew

  ReplyDelete
 31. ፈጣሪ ልቡና ያድላችሁ!

  ReplyDelete