Friday, November 20, 2015

የኅዳር ሚካኤል በዓል የማን በዓል ነበር?


 Read in PDF
የኅዳር ሚካኤል በዓል የሚከበረው ምንን በማስመልከት ነው? ብለው ቢጠይቁ ወይም በዕለቱ ወደ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ሲሰጥ ቢሰሙ ሚካኤል ህዝበ እስራኤልን ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣበት ቀን ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ይሆናል፡፡ ድርሳነ ሚካኤልን ቢያነቡም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥምዎት፡፡ ነገር ግን እውነቱ ያ ነወይ? እስራኤልን የመራው ማነው? የኅዳር ሚካኤል በዓልስ በምን ምክንያት ነው መከበር የጀመረው? ስለዚህ ጉዳይ በዕለቱ ከሚተረከው ውጪ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ምን ይላሉ? ጉዳዩ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲፈተሽስ እውነቱ የቱ ነው? እስኪ ለሁሉም ቀጥሎ የቀረበውን ጽሑፍ ይመልከቱ፡፡   
“ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ በዓልየ ወሑሩ በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ሚካኤል” (የመስከረም ሚካኤል ዚቅ)።
ትርጓሜ “ሚካኤል አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፣ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችሁ።”
“ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ ሰንበትየ ወሑር በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ቅዱሰ እስራኤል” (መጽሐፈ ድጓ 1959፣ ገጽ 58)።
ትርጓሜ፣ “የእስራኤል ቅዱስ (እግዚአብሔር) አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? ሰንበቴን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፣ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችሁ።”

መጽሐፈ ዚቅ ይህ ቃል የሚካኤል ቃል ነው ቢልም፣ ድጓው ይህን የሚሠራው ግን ለእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስም ይህ ሥራ የሚካኤል ሳይሆን የሚካኤል አምላክ የሕያው እግዚአብሔር ተግባር መሆኑን ያረጋግጣል (ዘሌ. 25፥18-22፤ ኢሳ. 59፥1)። “በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፣ ከበረከቴም ትበላላችሁ” ለማለት የተገባው ከአንዱ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በቀር ከቶ ማነው? (መዝ. 103/104፥13)።
 “ሚካኤል በዓሌን አክብሩ” አለ ብለው ያልተጻፈ በማንበብ እውነቱን እንድንመሰክር ካነሣሡን፣ የሚካኤል በዓል አከባበር በተለይም የኅዳር ሚካኤል እንዴት መከበር እንደ ጀመረ ታሪካዊ የት መጣውን ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ማስረጃ በማቅረብ ማሳየት እንችላለን።
 “በግብጽ አገር ‘ዙሐል’ ተብሎ የሚጠራ ጣዖት ነበር። የግብጽ ሰዎች ከሌሎች ጣዖታት እጅግ አደርገው ያከብሩታልና ያመልኩት ነበር። ከሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ቀጥለው የተሾሙ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ቅዱሳን አበውም ሁሉ የዙሐልን ተመላኪነትና ተከባሪነት ማስቀረት ሳይቻላቸው እስከ 320 ዓ.ም. ያህል የግብጽ ሰዎች ሲሰግዱለት ሲያመልኩት ኖረዋል።
 ዙሐል ከቀሩት ጣዖታት የበለጠ ተኣምራታዊ ኀይል ወይም የተለየ ምትሀት ኖሮት ሳይሆን፣ የቀሩት ጣዖቶች አንድ በአንድ ሲወድቁና ሲደመሰሱ የግብጽ ሕዝብ አልተጋፋም ነበር። ዙሐልን የደፈርን እንደ ሆነ ግን ሕዝብ ይነሣብናል በማለት ፈርተው ነበር። በተጠቀሰው ዓ.ም. ግን የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባ እለእስክንድሮስ እንደ ምንም ብሎ ሕዝቡን እያግባባና እያስተባበረ፣ እያባበለም ብዙዎችን በማስረዳትና በማሳመን “ዙሐል” ከምኵራበ ጣዖትነቱ ተነሥቶ በምትኩ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት[1] እንዲገባበት አድርጎ[2] የዙሐል በዓል በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን ይከበር ስለ ነበረ፣ ‘ኀዲገ ልማድ ጽኑዕ ውእቱ - (ልማድን መተው አስቸጋሪ)’ ነውና ሕዝቡን ለማስደሰት ሲል በዚያው በተለመደው ኅዳር 12 ቀን ይከበር ብሎ ዐዋጅ አስነግሮ ዐዋጁም ጸደቀ። (መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት 1988፣ ገጽ 152-153)።”
 የእግዚአብሔር እውነተኛና ታማኝ አገልጋይ፣ ምን ጊዜም ቢሆን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ለማስደሰት ሲል አይኖርም። አሊያማ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሊባል አይችልም። “ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም” (ገላ. 1፥10፤ 1ተሰ. 2፥4)።
 የኅዳር ሚካኤል በዓል አከባበር የት መጣው እንዲህ ሆኖ ሳለ፣ ዛሬ ግን በዕለቱ የሚነገረው የዙሐልን በዓል ለማስቀረት ባለመቻሉ በምትክነት የተሠራ በዓል መሆኑ አይደለም፤ ‘ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣበት ቀን’ ተብሎ ነው የሚከበረው (ድርሳነ ሚካኤል ዘኅዳር)።
 መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ማውጣቱን አይናገርም። ርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ሚካኤልን ልኮ ሕዝቡን ከግብጻውያን እጅ ሊያድናቸው ይችላል። እንዲያውም በዘመኑ መጨረሻ በክርስቶስ አዳኝነት አምነው ለሚድኑቱ የእስራኤል ቅሬታዎች (ትሩፋን) ሚካኤል እንደሚቆም የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል (ዳን. 12፥1 ፤ ራእ. 12፥7)።
 ሙሴ ጽላት ተቀብሎ ከተራራው እስኪወርድ ድረስ ታግሠው መጠበቅ አቅቷቸው፣ አሮን ያቆመላቸውን ጣዖት ማምለክ በቀጠሉት፣ ዐንገተ ደንዳኖቹ የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ዐዝኖ፣ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆንህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁሲላቸው በሰሙት ክፉ ወሬ ዐዘኑ (ዘፀ. 331-4) ከዚህም የምንረዳው እስከዚህ ጊዜ ድረስ እስራኤልን የመራው ፍጡር መልአክ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ነው። በዚህ ጊዜ ግን እርሱ ዐብሯቸው እንደማይወጣና ፍጡር መልአክ እንደሚመድብላቸው ነገራቸው። ለእነርሱ ይህ ክፉ ወሬ ነበርና በሰሙት ነገር ዐዘኑ።አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፣ ከዚህ አታውጣን አሉ በመጨረሻም እግዚአብሔር እኔ ከአንተ ጋር እኼዳለሁ፣ አሳርፍህማለሁ አለው (ቍጥር 14-16) ስለዚህ እስራኤልን የመራቸው ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሚካኤል አልነበረም ማለት ነው።
 ሙሴና ሕዝበ እስራኤል ፍጡር መልአክ (ሚካኤል) ሳይሆን፣ ጌታ ራሱ ነጻ እንዳወጣቸውና የሚመራቸውም እርሱ ራሱ መሆኑን ተረድተዋል በጣዖት አምልኮት እስካሳዘኑት ጊዜ ድረስም ዐብሯቸው የተጓዘው እግዚአብሔር እንደ ነበረ፣ ከዚህ በኋላ ግን እርሱ ዐብሯቸው እንደማይወጣና ሌላ ፍጡር የሆነ መልአክ እንደሚልክላቸው መናገሩ ብቻ እንኳ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው ይህን ሁኔታ የሰሙት ሙሴና ወገኖቹ፣ በፍጡር መልአክ በመመራትና በራሱ በእግዚአብሔር በመመራት መካከል ትልቅ ልዩነት አለና በሰሙት ክፉ ወሬ ማዘናቸው፣ እርሱ ዐብሯቸው ካልወጣም ከዚያ ስፍራ እንዳያወጣቸው መማጸናቸው የነገሩን እውነተኛነት ያረጋግጥልናል
 መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝበ እስራኤል ከምድረ ግብጽ ሲወጡ በፊታቸው የወጣው መልአክ ሚካኤል ነው አይልም (ዘፀ. 3፥2-6፤ 23፥20-23፤ ሐ.ሥ. 7፥30-34)። ስሙ በግልጥ ያልተጠቀሰው ይህ የጌታ መልአክ፣ ፍጡር የሆነ መልአክ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር በአርኣያ መልአክ ተገልጾ መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ስፍራ ያስተምረናል (ዘዳ. 32፥12፤ መሳ. 2፥1-5፤ 6፥8-9፤ መዝ. 135/136፥16፤ 104/105፥43፤ ኤር. 32፥21፤ ሆሴ. 12፥14)።
 አባ ስብሐት ለአብ በተባሉ አባት እንደ ተደረሰ በሚነገረውና “ሰይፈ ሥላሴ” በተሰኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ የጸሎት መጽሐፍ በረቡዕ ምንባብ ላይ፣ በምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ የታየውና ሕዝቡን የመራው የእግዚአብሔር መልአክ፣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላል፤ “ስብሐት ለመልአከ እግዚአብሔር ዘአስተርአዮ ለሙሴ በነደ እሳት በኀበ ዕፀ ጳጦስ መልአክኒ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ። - በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መልአክ ክብር ይሁን። መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው” (1991፣ ገጽ 66)።
 እግዚአብሔር ወልድ በተለየ ግብሩ ልጅ ነውና ልጅነቱን ለአባቱ የሚታዘዝ፣ የሚላክ፣ ጻድቅ ባሪያ፣ ቅን አገልጋይ፣ ፈቃድ ፈጻሚ በመሆን አሳይቷል (ኢሳ. 42፥1፤ 52፥13-15፤ 53፥11፤ ዮሐ. 17፥1-5፤ ዕብ. 5፥8)“ቃሉን ላከ፤ ፈወሳቸውም” ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. 106/107፥20) እግዚአብሔር በአርኣያ መልአክ ወደ ሕዝቡ የላከው አካላዊ ቃሉን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው እርሱም በዘመነ ሥጋዌው አይሁድ፣ “አንተ ማነህ?” በማለት ላቀረቡለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ፣ “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ” በማለት እርሱነቱን ገልጦላቸዋል (ዮሐ. 8፥25) በዚህም ሕዝቡን በክርስቶስ ያሉ የክርስቶስ ሕዝብ አሰኝቷል (ኤፌ. 2፥12፤ ዕብ. 11፥25-26)
 ተልኮ መምጣት የልጅነት ግብሩ መሆኑንም በቃሉ አረጋግጧል (ዮሐ. 7፥28-29፤ 8፥26) በሌላም አኳኋን ቅዱስ ጳውሎስ ሕዝበ እስራኤልን በምድረ በዳ እየተከተለ ውሃ ያጠጣቸው ዐለት ክርስቶስ መሆኑን መስክሯል (1ቆሮ. 10፥4)ሙሴ፣ “እባክህን ክብርህን አሳየኝ” ሲል ላቀረበው ጥያቄ፣ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም፤ … እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ። በዐለቱም ላይ ትቆማለህ፤ ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዐለት አኖርኻለሁ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ። እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ። ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴን ግን አታይም” የሚል መልስ ከእግዚአብሔር ተሰጠው (ዘፀ. 33፥18-23)
 እግዚአብሔር መንፈስ በመሆኑ በመለኮታዊ ባሕርዩ መታየት ባይችልም፣ የክርስቶስ አምሳል በነበረው ዐለት ለሙሴ ክብሩን አሳይቶታልዛሬም ቢሆን እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም ለሙሴ በምሳሌው ዐለት ላይ ክብሩን እንዳሳየ ሁሉ፣ በአማናዊው፣ በዕቅፉ ባለውና የመለኮቱ ሙላት በተገለጠበት፣ የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ በሆነው፣ ሥጋን ለብሶ በመጣው በክርስቶስ እግዚአብሔር ተገልጧልና “እኔን ያየ አብን አይቶአል” (ዮሐ. 14፥9) ሲል መሰከረ (ዮሐ. 1፥18፤ ቈላ. 2፥9፤ ዕብ. 1፥3፤ ፤ 1፥14)
 እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን፣ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአርኣያ መልአክ በአርኣያ ኰኵሕ (ዐለት) ተገለጠ ማለት፣ እርሱ ፍጡር መልአክ ነው፤ ወይም ደግሞ የዘመኑ አርዮሳውያን አፋቸውን ሞልተው እንደሚናገሩት፣ ‘ኢየሱስ ሚካኤል ነው’ ማለት አይደለም ነገር ግን በመልአክ አምሳል ተገልጦ ሕዝቡን መራ፤ እኛንም ሰው ሆኖ አዳነን ማለት ነው እንጂ።
“ወበእንተ ዝንቱ ተሰምየ ውስተ መጻሕፍት ወልደ እጓለ እመ ሕያው በእንተ ሥርዐተ ትስብእቱ፣ ወዓዲ ተሰምየ እግዚአብሔር፣ ወልደ እግዚአብሔር፣ ወመልአከ፣ ወመዝራዕተ፣ ወነቢየ፣ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ አምላክ ወዓዲ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ ሰብእ
 ትርጓሜ፣ “ስለዚህም ሰው ስለ ሆነ በመጻሕፍት ውስጥ የሰው ልጅ ተባለ። ዳግመኛም እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአክ፣ ክንድ፣ ነቢይ፣ ተባለ። አምላክ እንደ ሆነ መላልሶ መጽሐፍ ያስረዳል። ሰውም እንደ ሆነ መላልሶ ያስረዳል።” (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 350፤ ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቍጥር 6 እና 7)።

(ምንጭ የተቀበረ መክሊት ገጽ 54-58)


[1] ግብጾች ታቦት ስለሌላቸው “ታቦተ ሚካኤል” የሚለው ትረካውን ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ታስቦ የቀረበ ይሆናል።
[2]  በአገራችንም ተመሳሳይ ልማድ እንደ ነበረ መገንዘብ ይቻላል። በተስዓቱ ቅዱሳን የተገደሙ ገዳማት አስቀድሞ አብያተ ጣዖታት ነበሩ፤ በኋላ ግን ወደ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንነት ተለወጡ (The Church of Ethiopia: a Panorama of History and Spritual Life 1970: p.p. 7:8).

13 comments:

 1. Daniel 10:21 "be ewunet metsehaf yetetsafewun enegrehalehu,ke aleqachihu ke Mikael beker ye miatsenagn manem yelem"
  Ze tse'at 23:20 befiteh mele'alun esedalehu;seme bersu selehone kalun adametu;atasmerurut;hatiat keserachihum yiqer ayilem

  ReplyDelete
 2. KE MAK ENG KEKIDUS MIKAEL BATTALION YISHALAL MELAEKTIN LEMIN FETERACHEW BIBAL LETELEKO TADIYO KEGZIABHER TELKO HIZBE ESRAALN ALAWETAM LEMAT BEKI MASRJE YELACHIHUM BEMEGBIYACHIHU YEZIHUL BEAL LEMASKERT YEKIDUS MIKAEL BEAL TEJEMRE YEMILEW AYATALAM TADIYA LIKEPAPASU EKO KENANTEYILK SILEHAYAMANOT BESGAWBICHA SAYHON BEMENFESUCHIMR YADEGE NEW TEWUT MENAFKNET KETETERATARINET YEMIMENECH DKMET NWE

  ReplyDelete
 3. Bemelaikt bota Igziabiher beIgziabiherm bota melaikt yemitemrubet bizu yemetsha kifloch alu.Mehayim menafikan gin ayredutm.Lefituran yemaynegerewu Meftemr bicha newu.

  ReplyDelete
 4. ዛሬ ደግሞ ተኩላው በደንብ እራሱን ነው የገለጸው ዛሬ ደግሞ ክርስቶስ መልአክ ሆነ!!!!!!!! ‘በምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ የታየውና ሕዝቡን የመራው የእግዚአብሔር መልአክ፣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላል’፤ ምንጩ የአበው መጽሐፍና ጮራ የአበው መጽሐፍ ክርስቶስ መልአክ ነው የሚል አስተምሮ እንደሌለላቸው ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ የሉተር ልጆች ጸሐፊያን ግን ሊሉ ስለሚችሉ ብዙ አይገርመኝም፡፡ ተኩላው የሚናገረውን ነው ያሳጣው፡፡ ክርስቶስ እግዚአብሔርነቱና አምላክነቱ ቀርቶ መልአክ ሆነ?????????????????? ያሳዝናል!!! ይሄ በነሉተር መርከብ ውስጥ የሚሰበከውና የሚመለከው አምላክ/ጣኦት/ መላእክትም የሉትም፤ ሲያዝን ብቻውን ነው የሚደክመው፡፡ አማኞቹ ስላላወቁ ነው እንጂ ማንም አምላክ ነኝ ብሎ የተነሳ ሁሉ ግን የራሱ መልአክት አላቸው፡፡ አላህ የሚባለው በወንድሞቻችን ሙስሊሞች የሚመለከው አምላክ እንኳን አንድ ገጽ ብለው መልአክ እንዳለው ይነግሩናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ መልአክ ነው የሚል አለ???????????????????????????????????? ወይም በመልአክ አምሳል ተገልጾ የታየበት ጊዜ አለ?????????????? እኔ የምፈራው ትንሽ ቀይታችሁ ክርስቶስ በመልአክ አምሳል ከተገለጸ ሰይጣንንም አድኖታል ብላችሁ የራሳችሁን መጽሐፍ እንደምትጽፉ ነው የሚታየኝ፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ በሰው ሀምሳል የተገለጸው ሰውን ለማዳንና ሰው እንድንሆን ነው፡፡ እንግዲህ ክርስቶስ መልአክ ከሆነ ነገ ደግሞ በመልአክ አምሳል የተገለጸው ሰይጣንን ወደ ክብር ቦታው ለመመለስ ነው ብላች መስበክ እንደምትጀምሩ ይህ መልእክታችሁ ያሳያል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአርአያ መላክ ማለት መልአክ ማለት ነው እንዴ? ለምን ስተህ ታሳስታለህ? የቤተክርስቲያን መጻሕፍት "መልአክ" ብለው ጠርተውት እያለ ይህን ለማስተባበል ለምን ትሞክራለህ፡፡ እንዲያ ካልክ ሃይማኖተ አበው ሰይፈ ስላሴ የሰጠው ምስክርነትን ምን ልትለው ነው? በአጠቃላይ የተባለው በብሉይ ኪዳን በአርአያ መልአክ ተገልጧል ነው እንጂ ኢየሱስ መልአክ ነው አልተባለም፡፡ መልአክ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያ ነቢይ ካህን ተብሏል፡፡ እንዲህ ማለት ከነቢያት አንዱ ነው ከሐዋርያትበአንዱ ነው ማለት እንዳልሆነ እንዳንተ ያለው ወገበ ነጭ ሳይሆን በሙያው የዋሉበት ያውቁታል፡፡ ለማንኛውም “ስለዚህም ሰው ስለ ሆነ በመጻሕፍት ውስጥ የሰው ልጅ ተባለ። ዳግመኛም እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአክ፣ ክንድ፣ ነቢይ፣ ተባለ። አምላክ እንደ ሆነ መላልሶ መጽሐፍ ያስረዳል። ሰውም እንደ ሆነ መላልሶ ያስረዳል።” (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 350) ሰይፈ ስላሴ ደግሞ “ስብሐት ለመልአከ እግዚአብሔር ዘአስተርአዮ ለሙሴ በነደ እሳት በኀበ ዕፀ ጳጦስ መልአክኒ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ። - በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መልአክ ክብር ይሁን። መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው” (1991፣ ገጽ 66)። ይላል፡፡

   Delete
  2. እግዚአብሔር ይባርካችሁ ወንድሞቼ አባ ሰላማ ብሎግ ማንበብ ከጀመርኩ ወዲህ አዳኘ ማን አንደሆነ አየበራልኝ ነው ክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝ ነው

   Delete
 5. በግብጾች ብለህ…………………….. በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያሉት ታቦታት የሚካኤል ብቻ ያለ አስመሰልከው፡፡ የታሰበ ይሆናል ላልከው አንተ እልክ ብያለሁኝ፡፡ ዘጠኙ ቅዱሳን ስም የተገደመው ቀድሞ የጣአት አብያት ላልከው ምን ያገናኘዋል???? መቼው አውሬው ስድብና ነቀፋ ስለሚወድ እንጂ የእናንተም ዛሬ የምትጫሁበትና የምታመልኩበት አዳራሽና ሆቴልም እኮ ዝሙትና ስካር የሚከናወንበት የነበረ ነው፡፡ የሙሉወንጌል እኮ በፊት የቀበሌ ካፍቴሪያ ነበረ፣ ዛሬ በእየሆቴሉ አዳራሽ የምትጫሁበት እኮ ዝሙትና ስካርና ሌላም የሚከናወንበት ስፍራ ነው፡፡ ምን ይገርማል ካዲያ፡፡

  ReplyDelete
 6. እናንተ አሳሳቾች ኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 23 ቁጥር 20ን አንብቡ እስኪ፡፡ ኤረ ባካችሁ ሐሰትም እኮ ልክ አለው፡፡ የእኛ ተከታዮች ናቸው የምትሉአቸው ስሑታን እንኳን ልክ በለሌው ውሸታችሁ ይታዘቡአችኋል፡፡ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳንን የሚከሳቸው እንደለሌ ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡

  ReplyDelete
 7. Melekt. Ena sadkane yamaldalu yemtlwan batekrstyane lmafrese ytensacue yezmenacene menafkane nacheu egzabher lebona yestacheu Ethiopia ortodox tewhido batekrestyane eske Eyesuse kerstose dagem meseate senta tenoralche yegehanem dejoche aychelushem tebelo ytesafelate tenbit ale byzemenu leminesubat tewagiwocua balebatu lebonacune yabralachue ezebume nektobacuale yebekale eskeaune yatalelacute leyu leyu behone engda temherte atewsedu teblenale anwesdeme tekulawochene Egzabhere amlake yastagselene Amen!!!

  ReplyDelete
 8. For mulugeta do you know who lead and follow israli people when they out from egypt that is Jesus christ 1cor 10-1-10

  ReplyDelete
 9. ታቦት አገልግሎቱን ፈፅሟል አማናዊው ታቦት ኢየሱስ ክርስቶሰረ ነዉ ሃይማኖት አበዉ መፅሀፍ ን አንብብ

  ReplyDelete
 10. Ye kidus Mikael sim sitera ye tehadiso menfes yichohal

  ReplyDelete