Tuesday, November 24, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ስድስት

Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
ስለውግዘት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

   ቤተ ክርስቲያን በውግዘት የካደን ከሃዲና ኃጢአተኛውን ለመለየት የመጨረሻውና አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ይህ ተግባር እጅግ ከባድ፤ የተጋ የጸሎት ጉልበትና የወንጌል ልብ የሚጠይቅ ነው፡፡ መናፍቃንንና ከሃዲያንን ብቻ ሳይሆን ነውራቸው ተገልጦ ብዙዎችን ያሳቱ ኃጥአንንም የምናወግዝ ከሆነ የተከፈለላቸውን ሰማያዊ ዋጋ በማሰብና የሟቹን ሞት የማይፈቅደውን የጌታን መንፈስ ባለማሳዘን በሚያስተውል ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡
    በዛሬ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚመክሩና የሚገስጹ የሚያቀኑም ልቦች ጠፍተው “ሆ” ብለው የሚያወግዙና የሚቆጡ፤ የሚንጫጩና መንፈስን የሚያውኩ፤ በአላዋቂነት ድፍረት ከመደብደብ የማይመለሱ ሥጋዊ(ፍጥረታዊ) ሰዎች የበዙበት ነው፡፡ እነዚህን ልቦችና አንደበቶች ጸጥ አሰኝቶ፤ ገትቶ ወደእውነት ለመድረስ የሚከፈለው ዋጋ እንዲህ በቀላል የሚመዘን አይደለም፡፡ ይህንን በመያዝ ስለውግዘት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን በሦስት ከፍለን ብናይ፦

1.     ከውግዘት በፊት
2.    በውግዘት ጊዜ
3.    ከውግዘት በኋላ፡፡

1.    ከውግዘት በፊት ልናደርግ የሚገባው ጥንቃቄ

      መጽሐፍ “ጥንቃቄ ይጠብቃል፤ ማስተዋል ይጋርዳል” (ምሳ.2፥11) እንዲል ከምንም ነገር በፊት ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ከፍ ያለ ዋጋ አለው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታና በግድየለሽነት መሥራት ፍጹም ያስረግማልና፡፡(ኤር.48፥10) ስለዚህ ቤትን በጥበብ ልንሠራ፣ በማተዋልም ልናጸና ይገባናል፡፡ (ምሳ.24፥3) ጥንቃቄዎች ግን ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብና ከቃሉ በራቀ መልኩ መሆን የለባቸውም፡፡ የምንጠነቀቀውም “ሰዎችን ላለማጣት” ሳይሆን ለእግዚአብሔር እውነት በመወገን ፍጹማን ምስክሮች ለመሆን ነው፡፡
     ሰዎች ያለምስክር ንጹህ ሆነው ሳለ በሐሰት እንዳይነቀፉና እንዳይወገዙ አብዝቶ መጠንቀቅ ያሻል፡፡ “ለፍርድ የተዘጋጀ ኤጲስ ቆጶስ በአንዱ ላይ ስንኳ በሐሰት ቢፈርድ በፈረደው ፍርድ በራሱ ላይ ይፈረድበታል” እንዲል፡፡(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.183 ገጽ.65) በተለይ ብዙ ሰዎች ስለኃይማኖት በመቅናትና መቆርቆር ስሜት በመነሳሳት ብቻ ፍጹም ወደሆነ ሥጋዊ ስሜት በመግባት የሌሎችን ስም ሲያጠፉ፣ደብድበው ጉዳት ሲያደርሱ፣አምጸው ሰው ሲያሳድዱ ፈጣሪን የማገልገል ያህል ቢረኩም በፍቅርና በእውነት በሚከብረው አምላክ ፊት ግን ይህ ድርጊታቸው ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ስለዚህ ለማውገዝ ሥጋዊ ኃይልን መጠቀም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ተቃራኒ መሆናችንን ልንዘነጋ አይገባንም፡፡

   ቅድመ ውግዘት፦

1.1. ሰባት ጊዜ ሰባ መምከር(ማቴ.18፥22)

      ማውገዝን መምከር ይቀድማል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ሥራ ማውገዝ ሳይሆን የተሳሳተውን መክሮ መመለስ ነው፡፡ በአንዳች ሰው ጥፋት ልትደሰት፤ በመውደቁም ልትፈነድቅ ፈጽሞ አይገባትም፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩ አማኞች ቢኖሩን አንዱን በግ መፈለግ መንፈሳዊ ግዴታችን፤ ኃላፊነታችንም ነው፡፡  በደል የፈጸመ ሰው በአግባቡ በመጀመርያው በግል ሊመከር፤ ሊዘከር ይገባል፡፡ ይህ የሚሆነው ኃጢአተኛውን “ከእሳት ነጥቆ ለማዳን” ነው፡፡(ይሁዳ.22) በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን ከዚያ ሰው ደም ንጹህ ለመሆንና ለእግዚአብሔር ተገቢውን ክብር ለመስጠት ይቻላት ዘንድ ነው፡፡(ህዝ.3፥18 ፤ ሮሜ.2፥23-24)
     የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ትጋት ክርስቶስን ይመስል ዘንድ ነው፡፡ ክርስቶስ ኃጠአተኞችን መተኪ በሌለው ሞቱ እንዳዳነ ቤተ ክርስቲያንም የትኛውም አማኟ “ከእውነት በሳተ ጊዜ ብትመልሰው ከተሳሳተበት በመመለሷ ነፍሱን ከሞት ታድናለች፤ የኃጢአቱንም ብዛት ትሸፍናለች”(ያዕ.5፥19-20) ስለዚህ  ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ፈቃድ አጥብቃ በመከተል “ሰባት ጊዜ ሰባ” ማለትም በበዛ ይቅርታና በተትረፈረፈ የምህረት ልብ፤ በትህትናም ልትመክረው ይገባል፡፡ “ሰባት ጊዜ ሰባ” የቁጥርና የቀመር ጉዳይ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ኃጢአተኛን ለመምከር የተዘጋጀና ልብና መንፈስ እንዲኖራት የሚያስገነዝብ ነው፡፡
      ለዚህ የማሳያ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ነቢዩ ዮናስ በመርከብ ይጓዝ በነበረ ጊዜ በዙርያው የነበሩት አህዛብ ያደረጉለትን ቸርነት ማንሳት የተገባ ነው፡፡ ታላቁን ነቢይ ዮናስን አብረውት የሚጓዙት አህዛባውያን የተርሴስ መንገደኞች ለንብረታቸው መጥፋት (ዮና.1፥5) እና ለመርከባቸው እስከመሰበር መድረስ ጥፋተኛው ነቢዩ ዮናስ መሆኑን ደርሰውበታል፡፡ ትልቁ የእግዚአብሔር ነቢይ በአህዛብ መንገደኞች ፊት ተዳኝቶ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱ ባይደንቅም ይህ ነቢይ ግን ለእነዚህ ሰዎች ጥፋቱን አምኖ በራሱ መፍረዱ ይደንቃል፡፡ የገዛ ወገናቸውን መክሰስና በወገናቸው መፍረድ እንጂ ዝቅ ብሎ ራስን ማየትና የራሳቸውን ጥፋት በማመን ንስሐ ለማይገቡና ይቅርታ ለማይጠይቁ አገልጋዮች ዮናስ የሚደነቅ መልዕክት አለው፡፡
      ጥፋተኛ እንደሆነ ቢረዱም፤ እርሱም ጥፋቱን ቢያምንም(1፥12) እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ፈጽመው ሊፈርዱበት አልወደዱም፡፡ “ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉም።ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው። አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልና እንለምንሃለን አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን አሉ።” (1፥13-14) እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ህግ ከሌላቸው አህዛብ መስማት በእጅጉ ይደንቃል፡፡ ትዕዛዝ አልቀበል ብሎ ከእግዚአብሔር ፊት ላመጸ ነቢይ ይህን ያህል ትዕግስትና የምክር ቃል ከአህዛብ ከተገኘ በብዙ የእግዚአብሔርን መንጋ  ለመጠበቅ የተሾምን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ከአህዛብ ብልጫ ያለው ትዕግስትና የምክር ቃል ከልባችን መዝገብ ሊወጣ ይገባል፡፡ አልያ ግን “የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?” የሚለው ተግሳጽ ያገኘናል፡፡ በእውነትም ብዙ ትዕግስትና ምክር ለማይገባቸውና ሊወገዙ ይገባቸዋል ለምንላቸው ሰዎች ይገባል፡፡

1.2.                የጠራ ምስክር፤ በቂ ማስረጃ መሰብሰብ

     ፍጹም ዳኝነት የሚበየነው በእውነተኛ ምስክር ላይ ነው፡፡ “ጆሮ እንጂ አይን የለንም” የሚለውን የአለሙን የዳኝነት ችሎት መርህ የምትከተል ቤተ ክርስቲያን ዳኝነቷ ፍጹም ይሆናል ብሎ መጠበቅ ዘበት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች(ቅዱስ ሲኖዶስ)የማውገዝ ሥልጣን ከተሰጠው በመጀመርያ “ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ” (ሐዋ.20፥28) የሚለውን ትእዛዝ በብርቱ ማስታወስ ይገባል፡፡
     ለመንጋው ከመንጠንቀቂያው አንዱ መንገድ በግልጥ ነውር ወይም በኑፋቄ ተገኘ የተባለን ሰው “ምን እንዳደረገ ቀድሞ ከእርሱም፤ ከምስክርም” ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የኦሪቱ የህግ ባለሙያ የነበረው ኒቆዲሞስ ስለጌታ ኢየሱስ በተከራከረበት ንግግሩ ገልጦታል፡፡(ዮሐ.7፥51) የሚቀርቡት ምስክሮችንና ምስክርን የሚያጠራውም አካል ከአድልዎ፣ ከጥላቻ፣ ከቂም፣ ከበቀልም … ንጹህ በመሆን ሊያጣራ ይገባዋል፡፡(ዘሌ.19፥17-19)
       ኤጲስ ቆጶስ “ልከኛና ራሱን የሚገዛ” መሆን ይገባዋል ካልን(1ጢሞ.3፥3)፥ “በዲብሎስ ፍርድ እንዳወድቅ የበሰለ ክርስቲያን፥ ጠንቃቃ … ህይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመሰክር፥ ተቃዋሚዎችንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ … ” የተገባው መሆን አለበት ማለት ነው፡፡ (1ጢሞ.3፥6፤ቲቶ.1፥8-9) ዛሬ ላይ ውግዘትን በበቀልና በአድልዎ፤ በጥላቻና በአድማ ሲሰጡ ስናይ “በአእምሮው ጉድለት ምክንያት በቀልን የሚሻ ኤጲስ ቆጶስ ይባላል እንጂ ሹመቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም ፤ ከሰው የተገኘ ነው እንጂ”(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.150) የሚለው ብርቱ ቃል ከወዴት ተዘነጋ ያሰኛል?
     ስለዚህ እውነተና ዳኝነት ለመስጠት ለእውነትና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ከቆሙ ወገኖች የጠራ ምስክርነትና በቂ ማስረጃን ልንሰማ ገባናል፡፡ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዳኝነት ከመስጠቷ በፊት ግን “ልጆቿን በመክሰስ የሥጋ ዳኝነት” ፍለጋ “ወደ ፍርድ ቤት ልጆቿን በመጎተት”(ያዕ.2፥6) ከአለማውያን የፖሊስና የፍርድ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች አካላት “እግሯን ሰብስባ” ቤቷን ብታስተካክል መንፈሳዊ ዳኝነቷ ይበልጥ ይሰማ ነበር፡፡ ለተራበ ዳቦ ሳይሰጡ፣ ለታረዘ ሳያለብሱ፣ ለበደለ ዕድል ሳይሰጡ፣ በአግባቡ ሳይዳኙ ወንጌል መስበክ ወንጌል የማያውቀው ያልተሰማ በጎነት ነው!!!(ያዕ.2፥15)

1.3.            ከማስፈራራት፤ ከዛቻ መቆጠብ

         አለም እንኳ ታዝባን እኛን ካቀለለበችበት አንዱ “አመጻችን” እርቅ አሻፈረን ብለን በኢትዮጲያና በአሜሪካ ሲኖዶስ ተከፋፍለን አንዱ ሌላውን በውግዘት ሲያስፈራራና ሲዝትበት መታየታችን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን “ሥልጣን” የእረኝነትና ወንጌል አስተምህሮ ሰዎችን ወደእግዚአብሔር ልጅነት እንዲመጡ የማድረግ ሥልጣን እንጂ እንደአለማውያን መሪዎች ለመግዛትና ለመንዳ እንዲያመች ማስፋራራት አይደለም፡፡

“አለቃው ሕዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደለ በመስቀል የሚያሥራቸው ይሁን፡፡ በማይገባ አያውግዝ፡፡ ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለትፈልጎ በማይገባ ቢያሥር ቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታሠረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት፡፡”
(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.184)

    ሁለቱ “ልክ ነን አልተሳሳትንም” ባይ የዛሬዎቹ ሲኖዶሶች ዛሬም ድረስ  ለእርቅ አለመሸነፋቸው፤ እርስ በእርስ በጥላቻና በንቀት፤ በውግዘትና በክስ ተጠላልፈው መያዛቸውን ሳስብ ይህን “ልዩ ወንጌል” ከየት አመጡት ብዬ እደነቃለሁ፡፡ አንዱ ሌላውን “እኔ የበላይህ ነኝ፤ እኔ ነኝ ትክክል፤ ታሪክ አናበላሽም” ለማለት እውነትንና የእግዚአብሔርን ምህረትን ይቅርታ በሚቃወም፤ ትህትናን በሚክድ ሥጋዊ ትምክህት  በዛቻ፤ በከንቱ ቃል ማስፈራራትን ከወዴት አመጡት? እላለሁ፡፡
    የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስናጠና በጉባኤ ኬልቄዶን ላይ ዲዮስቆሮስን “ማዋረዳቸውን” ብቻ ሳይሆን ብዙ ማስፈራሪያ፤ ዛቻም እንደደረሰበትና ኋላም አንደተደበደበ (የሲኖዶሱ አባላት እንዳስደበደቡት) ተዘግቧል፡፡ እኛ ይህን ጉባኤ ላለመቀበል አንዱ ምክንያታችን ይህ ከሆነ ምነው እናስ ለምን እንዲህ ካለ አሠራር አልጸዳ፤ ህወታችንንና ጉባኤያችን ምነው በዚህ የተከበበ ሆነ?
   አዎ!  ህዝብን፤ አገልጋይን በውግዘት ማስፈራራት ያይደለ በመስቀል(በክርስቶስ በመስቀል ላይ የማዳን ሥራ) መሠር ለዘላለም ህይወት ያበቃል፤ እኛንም እውነተና ምስክር ያሰኛል፡፡

1.4.            የሐሰት ክስን፤ ምስክርንና ማስረጃን በግልጥ መቃወም

          “ … ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።” (2ጢሞ.3፥13)

     ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁን ቅዱስ ጢሞቴዎስን ሐሰተኞችን ፤ ኃጢአትን የሚወድዱትን፤ ልዩ ትምህርት ያላቸውን፤ በከንቱ ልፍለፋና በአሮጊት ተረት የተጠመዱትን፤ ለማንም ፊት ሳያደላ ሊገስጽ (1ጢሞ.5፥21) ፥ ከእነርሱም ሊሸሽ(1ጢሞ.6፥11)፥ እንዳተባበራቸው (1ጢሞ.5፥22) ብሎም ሊርቃቸው አንደሚገባ(1ጢሞ.4፥7 ፤ 6፥6 ፤ 20 ፤ 2ጢሞ.2፥26) በግልጥ መክሮታል፡፡ እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚገኙት በመካከላችን ነው፡፡ እንኪያስ በሚገባ ልናጤናቸው፤ ሃሳባቸውን እንደቃሉ ልንመረምረው ይገባናል፡፡
    ብዙ ጊዜ ሀሳባቸው ከእውነት ጋር ተለውሶ ስለሚቀርብ ነገራው ሁሉ በፍትፍት እንደቀረበ ምርቅ ያለ ነው፡፡ በቅርብ የማይዘነጋንን የውግዘት ታሪከረ ብናነሳ “ክሱን አሰናድቶ አቀረበ” የተባለ አንድ አካል በክሱ ካጨቃቸው ሰዎች መካከል “ቤተ ክርስቲያን አንቱ ብላ በሊቅነታቸው የመሰከረችላቸው” አባቶች ጭምር ከውግዘት ሰነዱ ውስጥ ሰፍረው መቅረባቸውን ሰምተናልም፤ አይተናልም፡፡ እኒህ አባቶች አይወገዙ እንጂ የሐሰት ክሱን፤ መስረጃውንና ምስክሮቹን ግን ሥልጣን ካለው አካል ተቃውሞ ሲቀርብበት ፤ በግልጥ ሲተችም አላየንም፡፡
  የሐሰት ነገር በግልጥ አለመቀበልን ማሳወቅ ሌሎች በሐሰት እንዳይከሱ “በር ከመዝጋቱም” ባሻገር ቤተ ክርስቲያን ከእነዚህ ወገኖች ክፋት አለመተባበሯን ያስመሰክርላታል፡፡ የሐሰት ክስን መርምሮ ሐሰት መሆኑ ከተረጋገጠ እንደአለማዊው ህግ ከሳሽ አካል የተከሳሹን ንጽዕና ተጸጽቶ ንስሐ ቢገባ እንኳ በግልጥ መመስከር አለበት፤ በመንፈሳዊው ህግም በግልጥ ሳያመቻምች በበደለበት መንገድ ይቅርታ ሊጠይቅ፤ ማቸውም መሥዋዕቱ በፊትም አስቀድሞ በንስሐ ሊያደርገው ይገባዋል፡፡ (ማቴ.5፥23-26 ፤ የወንጀል ህግ 1996 ዓ.ም የወጣው አን.610(2)፤  617(2))
       ስለዚህም፦
·        ሐሰተኛን ምልስ እግዚአብሔር ስለሚጠየፍ (ምሳ.6፥17) ፤
·        ሐሰተኛነት የኀጥዕ ሰው ሙያው ስለሆነ (ምሳ.11፥18) ፤
·        ሐሰተኛ ምስክር ስለሚጠፋና ከመቀጣትም ስለማያመልጥ (ምሳ.19፥5 ፤ 9 ፤ 21፥28) ፤
·        የሐሰት ምስክር ተንኰልን ስለሚያወራ (ምሳ.12፥17) ፤
·        የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ ስለሆኑ (ኢሳ.30፥9) ፤
 ቤተ ክርስቲያን ከምንም በላይ የሐሰተኛን ሰው ምስክር በሚገባ መጠንቀቅ ፤ መመርመር ይኖርባታል፡፡ በተለይም ቤተ ክርስቲያን ከኃጢአተኞች ጋር አንድ እንዳትሆንና የሐሰቱ ክስ ዋጋ እርሷንም እንዳያገኛት የሐሰትን ምስክር ልትጠላ (ዘጸ.23፥1 ፤ ዘዳግ.19፥16-19) ፤ ከሥር ያሉት ልጆቿም ዓመጸኞች ሆነው ከልክ ባለፈ ኃጢአት እንዳይፋንኑ ከመኰንን በተሻለ እርሷ ተጠንቅቃ ልታደምጥ ፤ ልትመረምር ይገባታል፡፡ (ምሳ.29፥12) 
    ስለዚህ የሐሰትን ነገር በሚገባና በማስተዋል መመርመር ከብዙ ነገር ያድነናል፡፡ በተለይ ዛሬ የሐሰት ክሶች በበዙበት በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከጸሎት ጋር የሐሰተኞችንና እየባሰ የሄደውን የአታላዮችን ክፋት ተግታ ልትዋጋ፤ ድል በመንሳትም የንስሐ ዕድል እየሰጠች፤ ካልተመለሱ ልታጋልጥ፤ ልትቃወምም ይገባታል፡፡

“እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።” (መዝ.144፥7-8)

                                                                                         ...ይቀጥላል

4 comments:

 1. ምነው በጣም የፈራችሁ ትመስላላችሁ፡፡ምን ያህል ቢያስጨንቃችሁ ነው ይህን ጽሑፍ የጻፋችሁት፡፡ደግሞስ ‹‹ ሰባት ጊዜ ሰባ መምከር ›› ያላችሁት ለጥፋታችሁ ጊዜ እንድታገኙ ነው፡፡ሲኖዶስን እንደተለመደው ማታለል ትችላላችሁ መንፈስ ቅዱስን ግን ማታለል አትችሉም፡፡ሐዋ 5

  ReplyDelete
 2. ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም.
  የማታምኑበትን ፍትሐ ነገሥት ዛሬ ከየት አገኛችሁ? በፍትሐ ነገሥት የምታምኑ ከሆነ በናንተ ላይ የሚፈርደው ይሄው የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ ነው፡፡ የኑፋቄ ትምህርት ከእውነተኛው የቤ/ክ አስተምህሮ መለየት አለበት፡፡ የተገለጠውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ እንቅስቃሴን ከቤ/ክን ለመለየት ብዙም ከባድ አይሆንም፡፡ እናንተው ራሳችሁ አለን እያላችሁ ምንስ ማስረጃ ያስፈልጋል? ከእንግዲህ የሚመለሱትን መልሶ እንቢ ያለውን መለየት ብቻ ነው የቀረው፡፡ አሁንማ ሕዝቡስ ራሱ እየለያችሁ አይደለም?

  ReplyDelete

 3. በእርግጥ ውግዘቱ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ሁሉም ሰው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ወንድሜ ጥያቄ ልጠይቅህ፣ ጹሁፍህ ላይ ቅሬታ አለኝ፤ በይቅርታ ላይ የጻፍከው፡፡ ክርስቶስ ይቅር በሉ ያለው እኮ እርስ በርስ ላለው ግንኙነት እንጂ በሐይማኖት ችግር ያለበትን አይደለም???????????? ነገር ግን የሐይማኖት ችግር ያለባቸውንማ እራሱ እግዚአብሔር አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ እንዳስተማረን መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቅር እንደማይባሉ አበክሮ አስተምሮናል፡፡ አሁን እኮ እየታየ ያለው አንተ ከምትለው ግንኙነት ያለው አይመስለኝም፡፡ እንዴት ነው???????????? ዲየስቆሮስን እኛ የተቀበልነውና እነርሱን የነቀፍነው ስለደበደቡት ሳይሆን አስተምሮውና የተከራከረበት ጉዳይ እውነት ስለሆነ ነው፡፡ እንግዲ አርየስም እኮ ብዙ መከራ ደርሶበታል እንግዲህ እሱን መከተል ነበረብን እንዴ?????????????????? የይሁዳንና የቅዱስ ጴጥሮስን ክህደት መመልከት እንችላለን፡፡ ስለዚህ መወገዝ ያለበት በአብዛኛው የቤተክርስቲያናችን አስተምሮ ያልሆነውን አስተምሮ በቤተክርስቲያናችን አውደምህረት ላይ እያሰሙ ያሉት ዳንሰኞችና፣ ዘፋኞች፣ ተሳዳቢዎችና አስመሳየች ተኩላዎች መወገዝ አለባቸው፡፡ እኔ እስከአሁን በዚህ ጉዳይ ላይ እኔም የአንተን አቋም ይዤ በጣም ተከራክሬ ነበር፣ በዚህ ጉዳይ የታሙትን ሰዎች በቅርበት ተመልክቼ አይቻቸዋለሁኝ ግን በራሴ አጣርቼ በትክክል መናፍቃን እንደሆኑ ያረጋገጥኩት ነገር ከራሳቸው አንደበት በተነገረው አስተምሮ ቃል በቃል ተነጋግረን ነው ማንነታቸውን ያወኩት ፡፡ ስለዚህ ሁሉንም አጥርቶና አረጋግጦ መንቀፉን እቀበለዋለሁኝ፡፡ እኔ ግን እስከአሁን በለኝ መረጃ እየተነገረ ያለው የተሀድሶ ኘሮቴስታንት የተባሉትን በአስር ጣቴ የምፈርምባቸው ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች አሉ፣ ከመዝሙራቸውም የምንረዳው አለ፣ ከአስተምሮዋቸው ዘይቤም የምንረዳው አለ፣ አካሄዳቸው ሁሉ ግልጽና የክህደት አስተምሮ ነው፡፡

  ReplyDelete
 4. አንተም እራሱ የእነርሱ ወገን ሳትሆን አትቀርም፡፡ እንዳለ ጹሁፍህ ይህንኑ ነው የሚያሳብቅብህ፡፡ እኛ የሰለቸን የተኩላው የማስማሰል ትምህርት፡፡ ተኩላው ዝም ሲሉት የመርዝ አፉን ይተፋል፣ ጉዱን ሲነግሩት የበግ ለምዱን ለብሶ በማር የተቀባ መርዙን ሸፍኖ ማር ይሆናል፡፡

  ReplyDelete