Saturday, November 28, 2015

እነማን ጳጳስ ይሆኑ ይሆን?ጵጵስና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የተሰጠ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ነው። ልብ እንበል! የግለ ሰብእ ሥልጣን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ነው። ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን ዓላማ ውጭ ለሌላ ነገር ሊሠራ አይችልም። ለተቀደሰ ነገር ብቻ እንዲሆን የተሰጠው የህ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ንብረት ለሌላ ጉዳይ ሆኖ ሌላ ነገር ሲሠራበት ቢገኝ ከባድ ወንጀል ነው። ለምሳሌ የግል ጥቅም፣ የዘረኝነት አገልግሎት፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ወይም የዝሙትና የዚህ ዓለም ርኩሰት በጵጵስና ደረጃ ቢገኙ በጌታ መንግሥት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን መታወቅ አለበት። ዛሬ ግን ጵጵስና ቆብና ቀሚስ ብቻ ከሆነ ብዙ ዘመናት አልፈዋል።
በዛሬው ጊዜ የጵጵስና ሹመት እየተፈለገ ያለው ለእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎት አይደለም ማለት ይቻላል።  በዚህ ዘመን በቤተ ክህነትም ሆነ በቤተ መንግሥት የሚሾሙ ሰዎች ሦስት ሰዎች ብቻ ናቸው። እነርሱንም እንደሚከተለው ላስተዋውቃችሁ።

1ኛ ሕሊና የሌለው መሆን አለበት። ይህ ሰው የሚፈለገው አድርግ የተባለውን እንዲያደርግ፣ ጥፋትም ቢያይ እንዳይቃወም ስለሚፈለግ ነው፣ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ሆዱን ቢሞሉለት ሕሊናውን ባዶ ማድረግ እንደሚቻል ይታመናል። ገንዘብ እየተሰጠው ራሱን በተደጋጋሚ እየሸጠ የሚኖር ሰው ስለሆነ ለተፈጠረለት አላማ ኖሮ አያውቅም። ይህ ሰው ሳይኖር የሚሞት ራሱን ሳያገኝ ገንዘብ ለማግኘት የሚደክም ሰው ነው። እግዚአብሔር በሕይወቱ ሊፈጽመው ያሰበው ሳይሆን የሰይጣንን ወይም የሰውን ሐሳብ ተሸክሞ የሚንከራተት ምስኪን ሰው ነው። ስለዚህ ክፉዉንም አሜን ደጉንም አሜን እያለ በተመገበው መጠን የሚያስብ ሰው ስለሆነ አስጊ ሊሆን አይችልም። ስማቸውን መጥራት የማልፈልገው የቀደሙት ፓትርያርክ በዚህ ፍልስፍና በሰፊው ሰርተውበታል። አንዳዶች ጳጳስ ለመሆን ጉቦ ከፍለዋል። ሕሊና የሌለው ሰው ማለት እንደዚህ ነው። ይህ ሰው ከፍሎ ያገኘው ጵጵስና ስለሆነ ያለክፍያ ይሠራበታል ተብሎ አይታሰብም። የቅዱሱን አምላክ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነገር በገንዘብ ለመወሰድ ማሰቡ ይቅርና ከመነሻው ይህን ሹመት ማሰቡ ትልቅ ድፍረት ነው። እግዚአብሔር ለጠራው ብቻ የሚሰጠውን ቅዱስ ነገር በአድማና በዘር፣ በገንዘብ፣ በፖለቲካ የበላይነት ለመውሰድ ማሰፍሰፍ ምን ዓይነት አእምሮ ቢሰጠው ይሆን? በመሰረቱ ጥሩ አእምሮ ያለውና መንፈሳዊ የሆነ ሰው ጵጵስና ሊሾም አይችልም። ቢሾምም በጣም ተለምኖ በጾምና በጸሎትም ጌታን ጠይቆ ነው።
2ኛ እውቀት የሌለው መሆን አለበት። ይህ ሰው ምን እየተደረገ እንደሆነ የማይገባው፤ አለቆቹ ብቻ የሚያስቡትን እያሰበ፣ ለሚሰጡት አስተያየት እያጨበጨበ የሚኖር ስለሆነ በጣም ይፈለጋል። በአንድ ወቅት ስማቸውን መጥራት የማልፈልገው አለቃችን "ሐሳባችንን የሚደግፍ ከሆነ ዘበኛም ቢሆን እንሾመዋለን” ማለታቸውን መቼም አልረሳውም። ይህ አባባል ከውስጥ ለውስጥ መመሪያ በድንገት አፍትልኮ የወጣ ቃል መሆኑ ነው። እዚህ ላይ ብዙ የተማሩ ሰዎች ባለሥልጣን ሆነዋልሳ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል? ነገሩ ልክ ነው ግን እነዚህ ሕሊና የሌላቸው መሆን አለባቸው። እውቀታቸውን ለመጠቀም ተብሎ አንዳንዴ እንዲህ ይደረጋል። ካለቃቸው ሐሳብ ውጭ ቢሆኑ ግን ከጭዋታው ሜዳ በቀይ ካርድ እንደሚወጡ የታወቀ ነው። ወይም ከሙያቸው ውጭ ሌላ ሐሳብ መስጠት የማይችሉ ናቸው። እስኪ ባለፉት 20 ዓመታት ከተሾሙት ውስጥ በጣም ተምረዋል ወይም ሕሊና ያላቸው የሚባሉት እነማን ናቸው? ጮሌነት እውቀት ከሆነ ግን ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ቤተ ክህነትም ሆነ ቤተ መንግሥት ሐሳብ እንደ ዘንዶ የሚፈራባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ።
3ኛ ነውር ያለበት መሆን አለበት። በዚህ ዘመን ነውር ያለበት ሰው በመብራት ተፈልጎ ይሾማል። ከባድ ወንጀል ከፈጸመ ትልቅ የሥልጣን ቦታ እንደሚያገኝ የታወቀ ነው። ይህ ሰው የተማረ ወይም ሕሊና ያለው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን "ምን ያለበት ዝላይ አይችልም” እንደሚባለው አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በሠራው ስሕተት ስለማነኛውም ጥፋት የተቃውሞ አስተያየት መስጠት ስለማይችል በጣም ይፈለጋል። ነውሩን ረስቶ የሐሳብ የበላይነት ቢያሳይ ግን ከመዝገብ ቤት ፋይሉ ወጥቶ ይነበብለትና እጁን ባፉ ላይ እንዲጭን ይደረጋል። ዛሬ በነውር የሚታወቁ ሰዎች ትልቅ ቦታ ላይ ሆነው የሚታዩት ለምን ይሆን ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር መልሱ ከላይ የጠቀስሁላችሁ ነው።
አንድ ገጠመኝ ላጫውታችሁ አንድ ቀን በሐሳብ የተሸነፉ የማህበረ ቅዱሳን አባላት በድንጋይና በዱላ ይደበድቡኝ ጀመር። ጥፋቱ የኔ ነው። ቻይናዎች የኢትዮጵያን ተራራዎች እየናዱ መንገድ ሲሰሩ ያየ ገበሬ "የሚከብዳችሁ ምንድር ነው?” ብሎ ቻይናዊዉን ጠየቀ ቻይናዊዉም "ከባዱ ነገር የማይገባቸውን ሰዎች ማስረዳት ነው” አለ ይባላል። እኔም ያንን የተቀደሰ ትልቅ ሐሳብ ለማይገባቸው ሰዎች በዚያ ወቅት ማቅረቤ ከባድ ነበር። እናም በርካታ ድንጋዮች በራሴ ላይ ወድቀው ተጋግጬ ነበር። በዘመናዊ ህክምና እንዲሁም በወጌሻ ቅቤ ጀርባየን ታሽቼ ይህችን ለመጻፍ እድሜ አገኘሁ ተመስገን ነው! ወዲያው በዚያ ወቅት በአንድ ቤተ ክርስቲያን በማህበረ ቅዱሳን አባላት፣ ባካባቢው በሚገኙ ወጣቶችና ሰንበት ተማሪዎች "ስለ ተሐድሶ አስጊነት” ስብሰባ ተደረገ። ከተሰብሳቢዎች ውስጥ አንድ የማህበረ ቅዱሳን አባልና የኢሕዴግ አባል የሆነ ሰው ይሳተፍ ነበር፤ ሥልጣኑ ደህንነት ነው። ይህ ሰው በቅርብ እንደማውቀው ለማህበሩም ለኢህዴግም ይሠራል። እኔ በዱላው ብዛት ታምሜ ተኝቼ ስብሰባውን የሚካፈሉ ሰዎችን ልኬ እከታተል ነበር። ይህ ሰው ተራ ደረሰውና ስለተሀድሶዎች አስተያየት ሲሰጥ "ጴንጤን መከራከር ይቻላል ተሓድሶን ግን መግደል ነው ሌላ ምንም አማራጭ የለም” ነበር ያለው። እንደዚህ ዓይነት ሰው ባለሥልጣን ሲሆን ለዚያውም የሕዝብ ደህንነት! የመንፈሳዊው ማህበር አባል ሆኖ መገኘቱ ገረመኝ! በነዚህ ሰዎች ፊት የተሻለ ሐሳብ ማቅረብና ማሸነፍ ገደል አፋፍ ላይ ሆኖ ትግል እንደመግጠም ነው። የሁለቱም አብዛኛዎቹ አባላት ከዚህ ውጭ ማሰብ እንደማይጠበቅባቸው የታወቀ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚከበሩት የኢሕዴግ ወይም የማህበሩ አባል ስለሆኑ እንጂ በሌላ አይደለም። ወደ ፊት ለኢትዮጵያ ስለመጥቀም የተቀደሰው ሐሳቤን ለነዚህ ሰዎች ማካፈል አልፈልግም። ዘመነ ጠብመንጃ እስኪያልፍ ድረስ የሚገባቸውን ሰዎች ውስጥ ለውስጥ ማብዛት በሚለው አምኜ በሐሳብ የበላይነት የሚያምኑ ሰዎችን እያበዛሁ እገኛለሁ። በኢትዮጵያ የሐሳብ የበላይነት ገዢ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም የሚል ተስፋ አለኝ።
ንግባዕኬ ኀበ ጥንተ ነገር። ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ነገርን ነገር እየወለደው ብዙ አወራሁ መሰለኝ። ልናገረው የምፈልገው በአሜሪካው ሲኖዶስና በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ጳጳሳት ሊሾሙ መሆኑን ስለሰማሁ እነማን ይሾሙ ይሆን የሚለው ስላሳሰበኝ ነው። ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር መንግሥት እስክትንበረከክ ድረስ ሥራችንን ሳናቆም፤ በቦታው ላይ ሕሊና ያላቸው፣ እውቀት የሸመቱና ወንጀል የሌለባቸው እንዲሆኑ ስለምመኝ ነው። እንደ ሐዋርያት ቀኖና ቢሆን ኖሮ ጳጳስ መሆን ያለበት ባለትዳር ነው። ይህን የምለው መጽሐፍ ቅዱስና የሐዋርያትን ቀኖና ላነበቡ ስለሆነ በሦስት ወር የሰንበት ትምህርት ቤት ኮርስ ለተኮፈሳችሁ ድንጋይ ወርዋሪዎች አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል የማይነቀፍ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ እንደሚገባው የሚሠራ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለማስተማር የሚበቃ፣ የማይሰክር ፣ የማይጨቃጨቅ፣ ነገር ግን ገር የሆነ፣ ገንዘብን የማይወድ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር” 1ጢሞ 3፥1-5። ይህ የሐዋርያት ቃል ነው፡፡ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንም ይኸው ነው የሚታወቀው። እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጳጳሳት የሚሆኑት ባለትዳሮች ነበሩ። ነገር ግን ያልተማረ ሕዝብ እስካለ ድረስ ለድንጋይ ወርዋሪዎች ትልቅ ድል ነው። ይህን ቃል ማስተማር እንዳንችል ትልቅ ጥበቃ ይደረጋል ከዚህም አልፎ ይህን ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ማንሳት በድንጋይ ያስመታል።
 እሺ ዋናውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ተቀባይነት ስለሌለው እንተወውና እንደ ሰው ሥርዓት እነማን ናቸው ጳጳስ የሚሆኑት? እንደሚወራው ከሆነ በአሜሪካም በኢትዮጵያም ጳጳስ ለመሆን እያደቡ ያሉ ማፍያዎች እንዳሉ ታውቋል። አሜሪካ ከሚገኙት ውስጥ እዚህ ጳጳስ ለመሆን ለሹመት ደላላዎች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ያልተሳካላቸው ከገንዘባቸውም ከጵጵስናውም ሳይሆኑ ቀርተው በብስጭት የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ዘርፈው አሜሪካ የገቡና ፀረ ወያኔ ነን እያሉ እያታለሉ ጵጵስናን የሚያደቡ ማፍያዎች አሉ። አንዳንዶች ቆብና ቀሚስ ሁሉ ገዝተው አስቀምጠው እየጠበቁ ነው ተብሏል። መሾማቸው ባይቀርም ማንነታቸው ሳይገለጥ እንደማይታለፍ ግን መታወቅ አለበት። ኢትዮጵያ ውስጥ ጵጵስናን እያደቡ ካሉትም ከአሜሪካ ሙዳዬ ምጽዋት ዘርፈው የተመለሱ የሰው ትዳር አፍርሰውም የመጡ አሉ። የማህበሩን ፖለቲካ ይከላከላሉ ተብለው የታሰቡ ከወዲሁ መንፈሳዊ ለመምሰል በባዶ እግራቸው ያለጫማ መሄድ የጀመሩም አሉ ይባላል። እነዚህም ወደፊት ይገለጣሉ። በመንፈሳዊ ቦታ ላይ መንፈሳዊ ሰዎችን መሾም ተገቢ ነው። የሐዋርያት ቀኖና ባይታሰብም መንፈሳዊ የሆኑ መነኮሳት እንዲሾሙ የተቻለንን ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። ሕሊና ያላቸው፤ በመንፈሳዊ እውቀት የበሰሉ፣ ወንጀል የሌለባቸው መንፈሳዊ መነኮሳት ቢሾሙ ትልቅ ለውጥ ይመጣል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቃል የመመለስ እድልም ቤተ ክርስቲያን ታገኛለች የሚል ሐሳብ አለኝ።  ይህም ያስደበድበኝ ይሆን?
መ/ መልካም ሰው


8 comments:

 1. እነማን ጰጰስ ይሆኑ ይሁን??????????????? መልሱ አንተ ለራስህ ለእግዚአብሔር መልካም ጰጰስ ስትሆን!!!!! እንግዲህ እግዚአብሔር ለዚህ ትውልድ የሚገባውንና ትውልዱን የሚወክሉትን ሰጥቶናል፡፡ ከሰማይ ሾሞ አይልክልን እንግዲህ??????????????? ለእግዚአብሔር መልካም ናቸው አይደሉም የሚለውን መጀመሪያ እኛ ለእግዚአብሔር መልካም ሳንሆን ከየት አምጥቶ ነው የሚሾምልን?????? ሁላችንም የራሳችንን አምላክ ፈጥረን የምንጓዝ ጎበዝ ትውልድ ብንኖር ይህን ትውልድ የሚያክል የለውም???????? እያመለክን ያለውን እውቀታችንን፣ ጽድቃችንን፣ እስካልቀበርን ድረስ ይቀጥላል…………

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mulugeta, what kind of person you are? The article is supported by biblical verses. So, I ask you to see things widely, instead of narrowly.

   Delete
 2. እራስህን መልካም አድርገህ የጻፍከው፡፡ አንተ የወንድምህን እድፍ እንደዚህ ስትናገር አንተ የሰውን እድፍ እንድትናገር ማን ፈቅዶልህ ይሁን????????????????????????????????? እራስህን መልካም መምህር ሰው ያደረከው የጠፋኸው ወንድሜ እንደአንተ እና እንደእኔ አይነት እራሳችንን አዋቂና ጻድቅ አድርገን የምንኖር በትእቢት የተሞላን የእኛን ስሜት ብቻ የሚቀበሉትን አወድሰን፣ የሚቃረንን እየሰደብንና እየነቀፍን የምንኖር ትውልድ እንዴት ሆኖ ነው አንተ እግዚአብሔር የሚፈልገውን አገልግሎት የሚኖሩትን ጰጰሳትን ማየት የምንችለው???????????? እኛ እራሳችንን አዋቂ አድርገን እንዴት ነው የሌሎችን አዋቂነት ማወቅ የምንችለው???????????? እኛ ማን ነን????????????? ጰጰሳት እኮ ከሰማይ ተሾመው የመጡ ሳይሆን ከእኛው ትውልድ የወጡ ናቸው፡፡መጥፎም ይሁኑ ጥሩ የእኛን ትውልድ ነው የሚወክሉት፡፡ አንተ የገለጽከውን ስህተት በሙሉ እኮ እኛም ጭምር የምናደርገው ነው፡፡ እነርሱ ያድርጉ አያድርጉ አላውቅም፡፡ ይህንን የሚያውቀው የስልጣኑ ባለቤት ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ለአንተ ለጠፋኸው ወንድሜ መልካም ነኝ ብለህ ስም ያወጣኸለት ጽሁፍህ ግን መልካም ሰው መሆንህን አይገልጽም፡፡ ብቻ ሰሞኑን ምንፍቅናቸው ከተጋለጠባቸው ወገን ሳትሆን አትቀርም፣ እራሴን ሾሜ ተሳድቤ የተሰጠኸን የተኩላውን የመስቀል ቃል ለመግለጽ መሰለኝ ይህ ሁሉ ስድብና ነቀፌታ የበዛበት ጹሁፍ የጻፍከው?????በእርግጥ የዚህ ትውልድ አንዱ መገለጫው የሆዱን ነገር ሲነኩበት ያስለቅሰዋል፣ ያስጩኸዋል፣ የሚናገረው ሁሉ ስጋው ያሸከመውን ስለሆነ ምን ይደረግ!!!!!!!!!!እንግዲህ ያችው የስጋ ስራ በዝቶባትና ከብዷት በከተማ ባህር ሰጥማ የቀረችውን የሉተር መርከብ ውስጥ ግባና አጓራ፣ በውስጧ ያሉት አዞና፣አሳነባሪ፣ ቡጭቅጭቅ ሲያደርጉህ ያን ጊዜ መልሱን እንደተሳዳቢው ከአምስቱ መነኮሶት አንዱ አባ ገብረክርስቶስ ነኝ ባይ ገብሬ ታሪክ ተሰርቶብህ ታልፋለህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እየተወራ ያለወ እኮ ስለጰጵጵስና ዉ

   Delete
 3. Excellent article!

  ReplyDelete
 4. ሙሉጌታ ፦ ለምን ጌታ ልቦና እንዲሠጥህ አትፀልይም? ጌታ ይማርህ!

  ReplyDelete
 5. አቤት! አቤት! እንዳው ዲያብሎስ በደንብ ነው ያጠመቀህ ሙሌ። ለመሆኑ ከድርሳን ሌላ መጸሐፍ ቅዱስ አንበህ ታውቃለህ?

  ReplyDelete
 6. የሄ መዘዝኛ ማኅበረቅዱሳን እሱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ማድረግ ይፈልጋል አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል፣
  ለሰው ጉደጓድ ስትቆፍር አታርቀው ማን እነደሚግባበት አይታወቅምና አሉ
  ምድረ ወሬኛ ደስ በላችሁ አስወሰዳችሁት ሁሉንም

  ReplyDelete