Tuesday, November 3, 2015

በስካር አውደ ምሕረት ላይ በወጣ የክፍለ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ጉባኤ ታጠፈ

Read in PDF

ባለፈው አርብ በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ይሰጥ የነበረውን መደበኛ ትምህርት ለማስተጓጎል በዓላማ መጥቶ በስካር መንፈስ ወደ አውደ ምሕረቱ የወጣው ቄስ ሙሴ ዘነበ የተባለው የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ጊዜውን በሞቅታ በሚነዳው አንደበቱና ምንም ፍሬ ነገር በሌለው እዚህና እዚያ በሚረግጠው “ስብከቱ” ብዙ ምእመናንን ማሳዘኑንና ብዙዎች ትምህርቱን አቋርጠው መሄዳቸወን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ተርበውና ተጠምተው የመጡት ምእመናን የፈለጉትን ሳያገኙ የግለሰቡን እንቶ ፈንቶ ወሬ በግድ ሰምተው ለመሄድ የተገደዱ ሲሆን፣ ይህንንስ አንሰማም ያሉ በርካታ ምእመናንም የሰውዬውን ሁኔታ በማየት ጉባኤውን አቋርጠው ሄደዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ሥራ አስኪያጁ መድረኩ ላይ የወጣው በደብሩ ውስጥ ያለውን ጤናማ የወንጌል አገልግሎት ለማፍረስ ተልእኮ ተሰጥቶት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቄስ ሙሴ ዘነበ  የተወለደው ሳሪስ አቦ አካባቢ ሲሆን ይህ ነው የሚባል የቤተክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖረው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ሆኗል፡፡ ከሳሪስ አቦ ከደጀሰላም ጀምሮ በሰካራምነቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ባህርዩ እስካሁን አብሮት እንደቀጠለ ነው፡፡ እሱ በሚመራው ወረዳ ቤተክህነት ውስጥ ብዙዎች ወንዶችንና ሴቶችን በጉቦ ቀጥሯል፡፡ ከተራ ዲያቆን ጀምሮ “ልትቀየሩ ነው ልትታገዱ ነው” እያለ በማስፈራራት ጉቦ የሚቀበል ሙሰኛ ነው፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በሊቀማእምራን የማነ ስም በርካታ ወንጀሎችን እየፈጸመ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራ አስኪያጁ እንደ ሙሴ ባሉ ሙሰኞች አስተዳደራቸው ላይ ጥላ እንዳያጠላ የብዙዎች ሥጋት ነው፡፡ 

ቄስ ሙሴ ጥቅምት 3 እና 4 ብሔረ ጽጌ ተገኝቶ ተሐድሶ የሚባል ነገር እኔ ባሁበት ክፍለ ከተማ የለም ብሎ በአደባባይ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ ዕለት ግን በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክ ተገኝቶ ሕዝቡ መደበኛ ትምህርቱን ለመማር ተሰብስቦ እያለ መደበኛው መርሐግብር እንዳይቀጥል በማድረግ ምእመናኑን ክፉኛ አሳዝኗል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ከአዲስ ሰፈር ኪዳነ ምሕረት አካባቢ ካሉ ወጣቶች ጋር ቀኑን ሙሉ ሲጠጣና ሲሰክር የዋለ ሲሆን የተሰጠውን ተልእኮ ለመፈጸም ወደደብረ ናዝሬት ዮሴፍ ቤተክርስቲያን በመምጣት ከዕለቱ አስተማሪ በፊት እሱ ያለችውን ኃላፊነት ተጠቅሞ መድረኩን በግድ በመያዝ የቀጣዩን አስተማሪ ሰዓት ገድሎ ከመድረኩ ወርዷል፡፡ ቄስ ሙሴን በዕለቱ ላየው ሰው እጅግ ያሳዝን ነበር፡፡ በስካር መንፈስ ነበርና ወደአውደምሕረቱ የወጣው፡፡ “መጽሐፍ መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ” የሚለውን ትእዛዝ እርሱ ገልብጦ በመጠጥ ሰክሮ ነበርና የመጣው የሚናገረውን አያውቀውም ነበር፡፡ ቅል እንኳ ፍሬ አለው ይህ ግለሰብ በዕለቱ ይናገር የነበረው ግን እጅግ አሳፋሪ መያዣና መጨበጫ የሌለው ነበር፡፡ “መልኬን እንደምታዩት ቆንጆ ነኝ” እስከማለት ደርሶ ወንጌል የሚሰበክበትን ዓውደ ምሕረት የቁንጅና ውድድር የሚካሄድበት መድረክ አስመስሎት ነው ያመሸው፡፡ በዚህ የተበሳጩ ብዙ እናቶችም ጉባኤውን ትተው ለመውጣት ተገደዋል፡፡
ይህ ግለሰብ ከዚህ ቀደም ለገጣፎ የአርሴማን አዲስ ጽላት አስገብቶ ሕዝቡን ሲያወናብድ በአባ ቀውስ ጦስ ታግዶ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ቄስ ሙሴ በመጠጥ ተሞልቶ የተሰጠውን የፀረ ወንጌል ኃይላትን ተልእኮ ከፈጸመ በኋላ ጠንካራው የስብከተ ወንጌሉ ክፍል ሃላፊ ጉዳዩን ለሀገረ ስብከቱ ማሳወቁን ምንጮቻችን ይገልጻሉ፡፡ የዕለቱን ትምህርት ያስተጓጎለውም በሊቀ ማእምራን ስም እንደሆነ ተነግሯል፡፡ “ይህን አድርግ ያለኝ ሊቀማእምራን የማነ ነው” ማለቱም ተሰምቷል፡፡ አሁን ጉቦ እየተቀበለ የሚቀጥራቸውን ሰዎች የሚቀጥረው በሊቀ ማእምራን የማነ ስም ላለመሆኑስ ምን ማስተማመኛ አለ? ይህ አልበቃ ብሎት በሌለው ሥልጣን የደብሩን ስብከተ ወንጌል ኃላፊ አግደዋለሁ እያለ ያወራል፡፡ ጉዳዩ ግን ወደሀገረ ስብከቱ በመድረሱ ወደደብሩ ምልጃ እየላከ እንደሆነ ታውቋል፡፡   
ይህ ግለሰብ ምእመናን ወንጌልን እንዳይማሩ ግብረሰዶምን የሚደግፉ ሰዎች ገንዘብ ሰጥተውት ነው ትምህርቱን ያስተጓጎለው፡፡  ከደጀ ሰላም የጀመረው የስካር ጉዞው እስከ ዓውደ ምሕረት ደርሶ ጤናማ የሆነውን የደብረ ናዝሬት አውደ ምሕረትን ለማወክ የተነሣው፡፡ በእርግጥ የአንድ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አርብ ዕለት ያደረገውን ተራ ወሮበላ እንኳን አያደርገውም ቢያንስ ሰክሮ የሚመጣ የለምና፡፡ ብዙዎች ያዘኑት አደገኛ የተባሉ ማቅ የላካቸው ወሮበሎች ያልደፈሩትን አውደ ምሕረት በሰካራም መደፈሩ የቤተክርስቲያንን ስም የሚያጎድፍ ነውና እንደእነዚህ ያሉትን ምንደኞች ሀገረ ስብከቱ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል፡፡


(በዚህ ጽሑፍ ቀደም ሲል ቄስ ሙሴን ሥራ አስኪያጅ የተባለው በስህተት ስለሆነ የሠው ሃይል አስተዳደር ተብሎ እንዲነበብ የተደረገና ማስተካከያ የተሰጠ መሆኑን ለአንባብያን በትህትና እንገልጻለን)

10 comments:

 1. Muse malet yesekaramoch aleqa new sibkete wengel wist min dolew?

  ReplyDelete
 2. ሙሴ የወጣላት ጉቦኛ መሆኗ እውነት ነው፡፡በየማነ ስም እንደምትነግድም ይታወቃል፡፡ለቡ ገብርኤል፣ላፍቶ ሚካኤል፣ብስራተ ገብርኤል፣አቦ ማዞሪያ ቤተክርስቲያን፣ፉሪ ሐና፣ራቅ ያሉ የገጠር አጥቢያዎችን ሙጥጥ አድርጋ በልታለች፡፡ስራዋ ግን ስራ አስኪያጅነት አይደለም፡፡የሰው ኃይል አስተዳደር ናት፡፡በዘሯም በየማነም እያስፈራራች ትሰርቃለች፡፡በስልጣኗ ትቀጥራለች፤የቋሚነት ወረቀት ትሰጣለች፡፡
  ታዲያ አንድ ሀቅ አለ፡፡የምግባር እንጂ የሃይማኖት ህጸጽ የለባትም፡፡ተሐድሶና እንደእናንተ ያለ መናፍቅ አትወድም፡፡ስለዚህ ሃይማኖቷን እያደነቅን ምግባሯን ግን እንድታስተካከል የእኛም መልእክት ነው፡፡በተለይ የብሔር ትምክህት፣በየማነ ስም ማስፈራራትና ጉቦኝነት በጣም አጥቅቷታል፡፡ለቡ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤልንና አርሴማን ሙልጭ አድርጋ ነው የበላችው፡፡እነሱ ‹‹ባንከሩ›› ነው የሚሏት፡፡ስትሰርቅ ዐይን የላትም፡፡ስላልተማረችም ደግሞ በጣም ደፋር ናት፡፡የማነ ከቻለ ቢያነሳት፣ካልቻለም ቢገስጻት ጥሩ ነው፡፡ያለበለዚያ በከፋ ምግባሯ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የነ አባ ሰላማ አይነት መናፍቅ ብሎጎች ማላገጫ ታደርግብናለች!!ትታረምልን!
  በነገራችን ላይ ለቡ ገብርኤል በይፋ ሰበካ ጉባኤና አስተዳደር ተደራጅተው የሚዘርፉት ቦታ ነው፡፡የቦታ ኪራዩ በአከራይ ተከራይ መደራረብ እስከ 4ኛ ጊዜ ተገለባብጦ እየተከራዬ ገቢው በአየር ላይ ይቀረጠፋል፡፡ሰ/ተማሪዎቹም ካልተነካን ምን አገባን ብለው ዝም ብለዋል፡፡አገልጋዩም በእርጥባን አበል አፉ ተዘግቷል፡፡የቢሮ ሰራተኞች ፎቅ የመስራት ውድድር ውስጥ ገብተዋል፡፡ቀሲስ በላይም ዘረፋውን ባርከውት አልፈዋል፡፡የማነም እንዳላየ እያለፈው ነው፡፡ሙሴም የድርሻዋን እየቀነጣጠበች ነው፡፡በተለይ ደግሞ የምዕመናኑ በዚህ ደረጃ ወርዶ ሰበካጉባኤነታቸውን በፀጥታ ያለኮሽታ ከአለቃው ጋር እየተመሳጠሩ በማራዘም በዘረፋው ተሳታፊ ሆኖ መገኘት አሳፋሪ ነው፡፡በዚህ ቦታ ኪራይ ላይ እነ ሊቀማዕምራን ፈንታሁን ሙጨ በሰሩት ጥናት መሰረት እርምጃ ካልተወሰደ እጅግ አሳፋሪ ይሆናል፡፡የቦታው ኪራይ የጥቂት ግለሰቦችና የእነ ሙሴ መክበሪያ ሆኗል፡፡መፍትሄ ይሰጠው፡፡
  ግልባጭ፡- ለሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ
  -ለለቡ ገብርኤል አካባቢ ምዕመናን
  -ለጠቅላይ ቤተክሕነት

  ReplyDelete
  Replies
  1. በቅድሚያ ትሩዝ የሰጠኸው አስተያየት ጥሩ ነው፡፡ እኔም እስማማበታለሁ፡፡ ከአንተ የምለው ግን ስለሙሴ ሃይማኖት በሰጠኸው ምስክርነት ነው፡፡ "የምግባር እንጂ የሃይማኖት ሕጸጽ የለባትም፡፡ ሐድሶና እንደእናንተ ያለ መናፍቅ አትወድም፡፡ ስለዚህ ህማኖቷን እያደነቅን ምግቧሯን ግን እንድታስተካክል የእኛም መልእክት ነው" ባልከው (ባላችሁት) አልስማማም፡፡ መቼም የምታምኑት በክርስትና ትምህርት ምግባር የሚመነጨው ከሃይማኖት ነው፡፡ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል እንዳለ ጌታ ሕጸጽ የሌለባት ሃይማኖት የምትታወቀው በበጎ ምግባር ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ "... ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ..." በማለት መታዘዝ ወይም መልካም ሥራ ከእምነት እንደሚነሣ መስክሯል፡፡ ሮሜ 1፥5፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብም ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ መሆኑንና እንደማያድን መስክሯል፡፡ እናንተ እምነት የምትሉት ምኑን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ተቋሙን (ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን) ከሆነ እርሱ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ የተቋሙ አባል ወይም ተከታይ ሆኖ ምግባረ ክፉ ይኖራል፡፡ እንዲህ ስል በእውነተኛው እምነት አምኖ ፍጹም የሆነ ሰው ብቻ ነው ያለው እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን በኀጢአት ውስጥ ተዘፍቆ ሊኖር የሚችል የለም፡፡ በኀጢአት ተዘፍቆ የሚኖር ካለ ግን እርሱ አንተ ከጠቀስከው ከሙሴ በምንም አይለይም፡፡ ስለዚህ የሙሴ ሃይማኖት ያስገኘችው ፍሬ ሰካርና ዝርፊያ ከሆነ ሕጸጽ የሌለባት ሃይማኖት ልትባል አትችልም፡፡ እንዲያውም ከምግባር የተለየች ሃይማኖት ስለሆነች የሞተች ናትና አታድንም፡፡
   ሌላው እናንተ ተሐድሶ መናፍቃን በማለት የፈረጃችኋቸው ወገኖች ሃይማኖት በሥላሴ ማመንና በክርስቶስ አዳኝነት ማመን ስለሆነ ሕጸጽ የለበትም፡፡ ስለዚህ ትችታችሁ ጥራዝነጠቅና ተራ ስድብ ከመሆን አይዘልም፡፡ ለነገሩ የቄስ ሙሴ ሃይማኖት እኮ የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅደስ ሳይሆን እንደፈለጋችሁ ሆናችሁ በቅዱሳን ስም ዝክር ብትዘክሩ በቀጥታ ወደ ገነት ትገባላችሁ በሚለው ተረት ላይ ነው፡፡ ለዚያ ነው መጠጥ ላይ ችክሎ ያለው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሕጹጽ ሃይማኖት የት አለ? ፍሬውም ስካርና ዝርፊያ ሌላም ሌላም ሆነ፡፡

   Delete
  2. የአይጥ ምስክር ድንቢጥ፡

   Delete
 3. like mamiran musina eysera adelem lemalet new , LEBOCH SINT SETACHU

  ReplyDelete
 4. አሁን አሁን ማንነታችሁን አሳወቃችሁን፡፡ እነማን እንደሆናችሁ አወቅናችሁ፣ ምስጢራችሁ ወጣ፡፡ አሰግድ በስብከት ላይ እንዳይሰብክ እኚህ አባት ስለከለከሉ ነው ይህንን ሁሉ ያወራችሁት????? አቤት እንዴት ነው የምታስቡት???? የሚደግፏችሁን አወድሳችሁ፣ የሚቃወሟችሁን ሰድባችሁ አዋርዳችሁ ትችሉታላችሁ? ኧረ ክርስትና እንደዚህ አይደለም፣ ክርስቲያን መባል እኮ በራሱ ከባድ ነበር፤ እንደው ሌላው ቢቀር ክርስቲያን የሚለውን ስም ከተሸከመ ሰው ይህ ይጠበቃል????????????????????????? ጽድቃችሁ ከፈሪሳውያን ካልበለጠ ከቶ መንግስተ ሰማያት አትገቡም፡፡ ይህንንማ አህዛብም ያደርጉታል፡፡ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡ አውሬው ለምን ይቆጣል? ??? በእውነት ተኩላው ሲያስመስል እንጂ እራሱን ሲገልጽ ያስጠላል፡፡

  ReplyDelete
 5. ሃራጥቃ ጉድሽ ፈላ።

  ReplyDelete
 6. አዋቂነን ብላችሁ አላወቂነታችሁን በምትለጥፉDቸው ጽሑፎች ታሳብቃላችሁ:: እናንተ አስቀደሞም የተዋህዶ አልነበራችሁምና በፍፁም የጌታችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ የተነችሁ የትንቢት መፈፀሚያ ጠላቶች ሆናችሁ መገኘታችሁንና መለየታችሁን አሳየታችሁናል፡፡ ይህን አስባችሁ ወደ ቀደመች ብርሃን ወደ ሆነች እውነተኛ መድኃኒት ፈራጅ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሚገኝባት ድንግል ማርያም ቅዱሳን ሰዎች ወመላእክት ካሉበት ኅብረት በንስሐ ብትመለሱ ይሻላችኀDል፡፡ ልብ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete