Monday, November 23, 2015

አክራሪውና ጽንፈኛው ማኅበረ ቅዱሳን በጎንደር የአብነት ትምህርት ተማሪዎች ከበጎ አድራጊዎች እርዳታ እንዳያገኙ አደረገበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከእኔ በቀር ማንም መኖር የለበትም የሚል አካሄድን በመከተሉና ሌሎች የአክራሪነት መገለጫዎችን በተደጋጋሚ ማሳየቱን መሠረት በማድረግ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አክራሪና ጽንፈኛ ተብሎ የተፈረጀው ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነቱ ከአዲስ አበባ የሄዱ ኦርቶዶክሳውያን በጎ አድራጊዎች የነገ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ለሆኑት የአብነት ተማሪዎች እርዳታ እንዳይሰጡ ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ለአመፅ ባደራጃቸው ወሮበሎች በኩል መከልከሉ ተሰምቷል፡፡ ማቅ በአመፅ መንገድ ይህን የበጎ አድራጎት ሥራ የከለከለውና የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ እንዳያገኙ ያደረገው በሕገወጥ መንገድ ሲሆን ሊቀጳጳሱና ሥራ አስኪያጁ የፈቀዱትን በጎን አመፅ በመቀስቀስ ማስተጓጎል እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጎ አድራጊዎቹ በጎንደር ግምጃ ቤት ማርያም ላሉ 50 ተማሪዎች በነፍስ ወከፍ 1 ኩንታል ጤፍና አንድ ኩንታል ስንዴ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ ሊያደርጉ ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም በግብሩ እኩይ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን “የተሐድሶ እርዳታ ነው” በሚል እርዳታው እንዳይሠጥ ተማሪዎቹም እንዳይቀበሉ አስከልክሏል፡፡
በጎ አድራጊዎቹ ቀደም ብለው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና ሥራ አስኪያጁ ሐሳቡን ሲሰሙ እጅግ ደስ ተሰኝተው በጎ ዓላማ ነውና ልትረዱ ትችላላችሁ በማለት ግዢው ሊፈጸም በዝግጅት ላይ እንዳሉ ከየት መጡ የማይባሉ የከተማው የማህበረ ቅዱሳን አባላት ተቃውሞ በማድረግ በተማሪዎቹ ላይ ጨክነውባቸዋል፡፡ ተማሪዎቹና አስተባባሪዎቹ ይሰጠን ቢሉም እርዳታውን ብትቀበሉ ከዚህ የአብነት ት/ቤት ትባረራላችሁ ብለው አስፈራርተው እንዳይቀበሉ አድርገዋል፡፡ በጎ አድራጊዎቹም ላይ ጥቃት ለማድረስ ያረፉበትን ሆቴል ከበውና እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግና ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ሲሉም ጥቃት ለማድረስ ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሎች በኩል ጥበቃ ስለተደረገላቸው ምንም ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ 
እንደሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነው በአብነት ት/ቤቶችና በገዳማት ስም ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ የሚሰበስበው ገንዘብ ነው፡፡ ማኅበሩ በእነርሱ ስም በአካፋ እያስገባ ለሪፖርት እንዲያመቸው በማንኪያ ብቻ በማውጣት አንዳንድ ነገሮችን ሠራሁ እያለ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር እንደሚያገኝ ይታወቃል፡፡ ማኅበሩ የበጎ አድራጊዎቹ ኦርቶዶክሳውያንን ድጋፍ የተቃወመው ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሲሆን ከዚህ በስተጀርባ ግን የአብነት ት/ቤቶችንም ሆነ ገዳማትን ከእኔ በቀር ማንም እረዳለሁ ብሎ መምጣት የለበትም በሚል “በጥቅሜ መጣችሁ” በሚል ነው ተብሏል፡፡
ወገንን ለመርዳትና ድጋፍ ለማድረግ ሰብአዊነት እንጂ ሌላ ምንም መስፈርት የሌለው መሆኑ ቢታወቅም ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህን ትልቅ እሴት በሃይማኖት ሽፋን በአደባባይ ሲንደው ማየት እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያቋቋመችው የልማትና የተራድኦ ኮሚሽን የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ለመሥራት በዋናነት ድጋፍ የሚያገኘው ከምዕራባውያን አገሮች ሲሆን ይህም የሃይማኖት ጉዳይን ሳይሆን ሰብኣዊነትንና በጎ አድራጎትን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ አክራሪው ማቅ ግን ኤቢሲዲ የቆጠሩ በርካታ አባላት ያሉት ቢሆንም ብዙዎቹ አእምሯቸው በተረት ስለደነዘዘና በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት ስላልረሰረሰ በሰብአዊነት ወገኖቻቸውን ለመደገፍ ሊቀጳጳሱን አስፈቅደው የመጡትን ኦርቶዶክሳውያንን በጥቅሜ መጡ በሚል ርካሽ ምክንያት ሃይማኖታዊ ሽፋን ሰጥቶ ለክፉ ቀን ለአመፅና ለአድማ ያስቀመጣቸውን “ቅምጥ ሃይሎቹን” በመጠቀም ኦርቶዶክሳውያኑ ድጋፍ እንዳያደርጉ የአብነት ተማሪዎቹም ድጋፍ እንዳያገኙ አድርጓል፡፡
ወሬ “ጠርሮባት” ከሳምንት በላይ ተኝታ የሰነበተችው የማቅ ልሳን ሐራም ለዚህ ጉዳይ ሌላ መልክ ሰጥታና ነገሩን ገልብጣ ያወራች ሲሆን የማኅበሩ ቅምጥ የአመፅ ሃይል በአመፅ ያስከለከለውን እርዳታ ሊቀጳጳሱ እንዳገዱ አስመስላ ጽፋለች፡፡26 comments:

 1. ይህ የወሬ ፋብሪካችሁ መቼ ነው የሚያተርፈው? ነው ወይስ ሁልጊዜ እንደተለመደው በኪሣራ የማምረት ሥራችሁን ቀጠላችሁበት?

  ReplyDelete
 2. engidoch kemalet semachewn metikes simachew setekes degmo maninetachew letawekina alamaw erdata endalhone letawek new beyans asegid sahilu ale atilum wedeh yeabinet temarewoch ewket yegodelachew nachew tamir gedil aquaquam kidase eyalu zemenun yalwaju nachew kirstos endaysebek mesenakil nachew eyalachihu bezih degmo terabu tilalachihu yefelegachihut lenrsu medresin sayhon yemikeretsew kaset habt honoachihu yihew endez eyeredan menafik eyalu simachinen yatefalu lemalet enante bilte lelaw mogn. mesakya nachihu degimo lela menged yizachihu nu.

  ReplyDelete
 3. deg aregu yeprotestant genzeb selmaytekim new!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. ለመሆኑ “ጠርሮባት” የሚለው አባባላችሁ ከየት የተገኘ ይሆን ? ይህ ሁሉ የሚያሳየው ግን ውሎአችሁ ከወዴት እንደሆነ ነው፡፡ ይኽንን በተመለከተ፡- ቅዱስ ዳዊት፡- «ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ፥ ወምስለ ብእሲ ንጹሕ ንጹሐ ትከውን፥ ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን። ከጻድቅ ሰው ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፥ ከቅን ሰው ጋርም ቅን ትሆናለህ፥ ከንጹሕም ሰው ጋር ንጹሕ ትሆናለህ፤» ብሏልና። መዝ ፲፯፥፳፭። አካሄዳቸሁን ብታርሙ ዛሬም የንስሃ ጊዜ ስለሆነ ጊዜያችሁን በከንቱ አታጥፉ ወደ እናት ቤተክርስትያን ተመለሱ እንጂ መልሳችሁ ጡት ነካሽ አትሁኑባት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ለመሆኑ “ጠርሮባት” የሚለው አባባላችሁ ከየት የተገኘ ይሆን ? ይህ ሁሉ የሚያሳየው ግን ውሎአችሁ ከወዴት እንደሆነ ነው፡፡ ..." ያልከው ሆይ አንተስ የት ውለህ ይህን ቃል አወቅከው? ቢገባህ ቋንቋ መግባቢያ ነው፡፡ ይህን ማወቅ ችሎታ እንጂ ኃጢአት አይደለም፡፡ ደግሞስ አለቦታው የጠቀስከው አንተና መሰሎችህ እየቆነጸላችሁ የምትጠቅሱት የመዝሙረ ዳዊት ቃልም ለሰው የተነገረ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የተነገረ ነው፡፡ ክፍሉን ደግመህ አንበበውና ለመረዳት ሞክር፡፡ አንተ እንዳልከው የተለያየ ጠባይ ካለው ሰው ጋር በመኖር ጠባይ ይለወጣል የሚል ፍቺ ፈጽሞ የለውም፡፡ የእግዚአብሔርን ትክክለኛነት የሚያስረዳ ነው፡፡ እባክህ በመጀመሪያ አስተውል አፍህ እንዳመጣልህ አትናገር

   Delete
  2. ለanonymous November 24 2015 at 11:08am
   እቆፃፀላችሁ ነዉ ያልከው። ለምን ሙሉ አድርገህ አታሳየንም ነበር? ደግሞ አዋቂ ነኝ ለማለት ያላዋቂ ተርጓሚነትህን ያለማፈር ፃፍኸው። ለመሆኑ እግዚአብሔር
   ምን ጉድለት አለበትና ነው ከፃድቅና ከመልካም ሰው ጋር
   መዋልና ከሱ መማር ያስፈለገው ?

   Delete
  3. ውድ AnonymousNovember 24, 2015 at 11:08 AMሆይ የፃፍኩትን መጀመሪያ በትክክል አንብብ፡፡ የቤተክርስቲያን ልጆችና የናንተ ልዩነት እኮ እዚጋ ነው፡፡ አሁን

   ም ቢሆን ከአግዚአብሔር የሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል በትክክለኛ መንገድ ይሰብካሉ ያስተምተራሉ ፡፡ ያውም ትሁት በሆነ አንደበትና በሚያራራ ቃል ነው እንጂ ጋጠ ወጥ አነጋገሩማ የነማን እንደሆነ አንተም ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ፡፡ ለመሆኑ ከየትኛው ሐዋርያ ይሆን ቋንቋ መግባቢያ ስለሆነ እንደፈለጉ መዘርጠጥን የተማርከው? ለነገሩ መች ሐዋርያት ታውቃቸውና

   Delete
  4. ዳሞት መቼም እስካሁን የምትሰጣቸውን አስተያየቶች ስከታተል ከአንተ ጋር መከራከር ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ድንጋይ ላይ የሚፈስ ውሃ ድንጋዩን ባይጠቅመውም ለሌላው መጥቀሙ አይቀርምና ጥቂት ነገር ልበል፡፡ "ለምን ሙሉ አድርገህ አታሳየንም" ላልከው የመዝሙሩን ክፍል ከፍ ብለን ቢያንስ ከቁጥር 24 ጀምሮ ብንመለከትና ዝቅ ብለን እስከ ቁጥር 27 ብናይ እንዲህ ይላል፡፡
   "እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።
   የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።
   ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።
   በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።
   እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።
   ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ
   ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።
   አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።"
   እንግዲህ በእነዚህ የመዝሙረ ዳዊት ስንኞች ውስጥ የተላለፈው መልእክት እግዚአብሔር በትክክልና በጽድቅ ለእያንዳንዱ የሚመለስ መሆኑን ነው፡፡ "ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።" ተብሎ የተገለጸውም ይህንኑ የሚያስረዳ ነው፡፡ እግዚአብሔር ንጹሐንን እንደሚታደግና ለክፉዎች ደግሞ እንደ ክፋታቸው መጠን የሚመልስላቸው ጻድቅ አምላክ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ቀጥሎ አስረጂ አድርጎ ያቀረበው "አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።" ተብሎ የተጻፈውም ይህንኑ የሚያጸና ነው፡፡ ስለማን እንደተጻፈም ይገልጻል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የጥቅሱ የተወሰደበት ዐውድ ሳይታይ ጥቅሱ ከመሃል ይወሰድና ሰው አዋዋሉን የሚመስል መሆኑን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ግን ስሕተት ነው፡፡ ይህን ሐሳብ ለመግለጽ ካስፈለገ "ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋዋል" የሚለው ቃል አለ፡፡ ማስተዋል ከቻልክና ከገባህ የላይኛው የተነገረው ግን ስለእግዚአብሔር ትክክለኛነት ነው፡፡ በአንተ በኩል "ለመሆኑ እግዚአብሔር ምን ጉድለት አለበትና ነው ከፃድቅና ከመልካም ሰው ጋር
   መዋልና ከሱ መማር ያስፈለገው ?" ያልከው ግን ቃሉ በሚለው መሠረት ሳይሆን በተለመደው መንገድ ለመተርጎም ስለፈለግክ ራስህ የፈጠርከው ችግር ነው፡፡

   Delete
  5. አናኒመስ ስማ በቅድሚያ "ጋጠወጥ አነጋገር" ምን ማለት ነው? ወደስድብ የተጠጋ አክብሮት የሌለው ወዘተ ማለት ነው፡፡ "ጠርሮባት" ማለት ግን የአራዳ ቃል እንጂ ጋጠወጥ አይደለም፡፡ አራዶች ምስጢራቸውን ለመደበቅና እርስ በእርስ ለመግባባት የሚፈጥሯቸው ቃላት ናቸው፡፡ ጽሑፉ ለማዋዛት ታስቦ እንጂ ጋጠወጥ ለመሆን ተፈልጎ የቀረበ ስላልመሰለኝ ነው አስተያየትህን የተቃወምኩት፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንጻር ብታየው የተሻለ ይመስለኛል፡፡

   Delete
  6. ለanonymous November 26,2015 at 7:18pm
   መቸም አንድ ጊዜ አውቆ የካደንና ልቡን ያሳወረን ለንሥሃ ማብቃት አሥቸጋሪ ነውና አንተም አዉቀህ የካድህ ልቦናህን ላለማሥተዋል ያሳወርህ ነህና የተረትኸዉ ተረት "በድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ " የሚለው አንተን ይመለከታል። ባትረዳውም መዝሞረኛው ዳዊት የተናገረው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እንደ እምነቱና እን ሥራው የሚገባውን የሚሰጥ መሆኑንና ሰውም አዋሉን አካሔዱን እንደሚመሥል ነው የተናገረው። እግዚአብሔርማ ሥጋዊ ሰው አይደል ከቸር ጋ ሆኖ ቸር የሚሆነው። የእግዚአብሔር ቸርነቱማ ለሁሉም ነው። ለኔና ለአንተ እንሿን በሱ ቸርነት እኩል መሽቶ ይነጋል። እግዚአብሔር ንፁሐ ባሐሪ ሆኖ ሳለ ከቀራጮች ጋር ነበረ።በእርግጥ አንተ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችለውንና የተጣለውን ፍጡር ሐሳዊ መሲህን ሥለምታመልክ ነው የሰውን ለፈጣሪ የሰጠኸው።

   Delete
 5. lebaw endih yiserkal yenetelaw sibsib

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous November 24,2015 at 10:47am
   ወንድሜ በአሉባልታ፣ በማስመሰልና በዉሸት ወንጌል የለም ህይወት የለም እምነትም የለምና በከንቱ አትኮፈስ። ለመሆኑ የናንተዉ የባለሱፎቹ አለመኟች ረጌ ራጋ ዘላዮቹ ምን እየሰሩ ነዉ? መጽሐፍ ቅዱስን ተሸክመዉ በማስሰል ዳንኪራ፣ ጋጠወጥነት፣ ምንፍቅና፣ አመፀኝነት፣ ክርስቶስ የሰጠዉን የእምነት ነፃነትን በመፃረር የሌላውን እምነትና ቤተ እምነት ሰላም ማደፍረስና ለማፍረስ በገንዘብ ሃይል የሚንቀሳቀስ፣ ወንጌልም ሆነ ክርስትና የማያዉቁና ያልገባቸዉ፣ በስም እንሿን ክርስትናን ከማይቀበሉት በባሰ በወንጌል ስም ወንጀልን የሚያራምዱና የሚያሰሩ ኢወንጌል ኢክርስትና ናቸዉ። አንድ ጥያቄ፦ ለመሆኑ መሥጠት አያጸድቅም እያላችሁ እናንተ እርዳታ የምትሰጡት ለምን ይሆን? ወንጌል ሥለሚያዝ ነዉ እንዳትል መሥጠት ከእምነት ጋር አይገናኝም መልካም ማድረግ አያፀድቅም ብላችሁ አይናችሁን ጨፍናችኋል። መቸም ያልገባችሁን ወኔጌልና ክርስትና ለማሥፋፋት እንዳትሉ አታፍሩምና። ወንጌልና ክርስትና በእግዚአብሔር ሐይል፣ጥበብና ጥሪ እንጂ በገንዘብ አይደለም።

   Delete
 6. ጎንደር የማቅ መናኸሪያ ሆኖ ህዝቡ ኢየሱስን እንዲጠላ ፀረ ኢየሱስ አድርጎታል በቅርቡ እንኳን አንድ የደብር አለቃ ተሐድሶ ሆነዋል በሚል ገድለዋል፡፡ ማቅ የዲያብሎስ የግብር ልጅ የኢየሱስ ስም ሲጠራ ዛሩ ይነሳበታል፡፡ እርሱን የተሸከመች ቤተክርስቲያን ውድቀቷ የፈጠነ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ሐሰት ከአባትህ ከዲያብሎስ ነው። ነፍሰ ገዳዩማ ተሐድሶ ፕሮቴስታንት ነው፣ ጭራቅ ደመ ጠጭ

   Delete
  2. የሐሰት ልጅ ንግግር ነው። ማኅበረ ቅዱን የፈረደበት ሁልግዜ በሐሰትና በልጁ እንደተከሰሰ...

   Delete
  3. ለይ፣ለይ፣ለይ፣ የትኛው ኢየሱስን ይሄ ስሙን እንኳን በትክክል የማይጠራው??????? በ16ኛው ክፍለ ዘመን በሉተር የተፈጠረውን???????? በእየአዳራሹ የሚያስጮኸውን፣ የሚያስጓራውን?????????? የሚያስለፈልፈውን??????????? የሚያሳብደውን ?????????????? ይሄ የእግዚአብሔር ማደሪያ እናቱን የሚሳደበው????????????? የእግዚአብሔር ስም የሚሳደበውን???????????? ይሄ የሰማይን ቅዱሳንን የሚሳደበውን?????????? ሀሜትና ወሬ ትእቢት ስድብ በራሱ ከፈጠረው ወንጌል ጋር ቀላቅሎ የሚሰብከውን?????????? ይሄ ክርስቲያኖችን የሚያሳድደውን??????????? በሰላም፣ በፍቅር፣ ተሸፍና የነበረችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስና ለማጥፋ የተነሳውን ያንን የዘንዶውን አፉን በየሱስ ስም የሚያወናብደውን ኧረ ስንቱ ይወራል፣ ምቼም ምን ይባላል፣ በተዋህዶ የከበረው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡ ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈልና ለማጥፋት ሰይጣን ተግቶ ቢሰራም፡፡ እግዚአብሔር ለቤቱ ቀናተኛ ነው፡፡ ኤልዛቤል ብትነሳም፡፡ ኤልያስ ግን ተስፋ አይቆርጥም፤ማህበረ ቅዱሳንን ደግሞ እግዚአብሔር አስነሳ፡፡ እነርሱን ያስነሳ እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ፡፡

   Delete
  4. የእኛ ቤተክርስቲያን ግን መቼም ቢሆን አትጠፋም፡፡ አጥፊዎቹዋ ግን ይጠፋሉ፡፡ የገሀነም ደዶች አይችሏትም፡፡ እናንተ ስታልፉ እኮ አየናች በተመሰረታችሁበት በአውሮፓ ምድር፣ ምን ያህል እንደጢስ ተናችሁ እንደጠፋችሁ ታይታችኋል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያናችን አጥር የሆኑትን ያብዛልን፣ ተኩላውን እንደዚህ አፉን ይዝጉልን፡፡ የመናፍቃን ካንሰር ስለሆኑ እነርሱ በብዙ መከራም ቢሆኑም ከምድር ይልቅ ሰማይ ስለሚቀርባቸው የእናንተ ስድብ ለእነርሱ በረከት እየሆነ ተግተው ይሰራሉ፡፡ እንደናንተ በስድብና በወሬ ሳይሆን በተግባር ነው የሚያሳዩት፡፡ ወንጌል የተግባር እንጂ የወሬና የስድብ የኘሮፓጋንዳ መድረክ አይደለም፡፡

   Delete
  5. ለanonymous November 24,2015 at 11:24am
   ውሸትና ሐሰተኛ ክስህ የአባትህ ነዉና ከአንተ የሚጠበቅ ነዉ። ምክንያቱም የወረሥኸው መገለጫህ ነዉና። ለመሆኑ ይህ ከጥልቁ የሚመጣዉ፣ የዚህ አለም ገዠ የተባለው፣ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚመጣዉ፣ ፍጡር የሆነዉ አማላጃችን የምትሉት፣ በምድር ላይ ልታነግሱት ሌት ተቀን የምትባዙኑለት፣ የእዉነተኛዉን አምላክ የክርስቶስን ሃይማኖት እንድትቃወሙና እንድትዋጉለት የክፋት መሳሪያን ያሥታጠቃችሁ፣ በቅዱሳኑ ደም ያሰከራችሁ ሐሳተኛዉን መሲህ የተባለዉን ኢየሱስ ነኝ ብሎ ሊያጭበረብር የሚመጣውን ነዉ ኢየሱስ የምትለዉ? እሱ አምላክ አይደለም የተጣለዉጠላታችን ከያቢሎስ እንጂ። እናንተም አማላጃችን በማለት ፍጡር መሆኑንና በራሱ ማዳን አለመቻሉን መሥክራችኋል እየመሰከራችሁም ነው።

   Delete
  6. DAMOTE ANTE DENEZ YEMTAWERAW ENA YEMTSERAW SIRA LEYEKIL DARU GN YEMAHIBER LIJ NEH...

   Delete
  7. እኔን ታውቀኛለህን የማወራውና የምሰራው እንደማይገናኝ ለመናገገር የደፈርከው? ከጥልቁ ነው መልእክቱን ያገኘኸው። እሱ ሁሌም ከሳሽ ነውና አንተም ከሱ ነህ።

   Delete
 7. ብላችሁ ብላችሁ በከተማው ሳያንሳችሁ በአብነት ትምህርት ቤት ገባችሁ????????????????? ይገርማል፡፡የከተማው አለፈበት፣ የሚቀበላችሁ ስታጡ ፡፡ ደግሞ ወደ ገጠር ገባችሁ፡፡ እኔ እንደውም እንደዚህ እያደረጉ ነው ተብሎ ሲነገር እውነት አልመሰለኝም ነበር፡፡ ይህ የሚያሳያው አሁንም በእርዳታ ስም ያንን የኑፋቄ ትምህርታችሁን ለማስተጋባት እንዲመቻችሁ ነው፡፡ በከተማ ያለነው አውቀንባችኋላ ሊሳካላችሁ መቼም አይችልም፡፡ ተኩላው በፈረሰው በኩል እየቆመ አለሁ ማለቱ ባህሪው ቢሆንም ግን በሀገራችን በስንዴና በዘይት የገባው ሉተር ትምህርት ለሀገራችን ያተረፈው ይህ የምንመለከተው ዘረኝነትን፣ መከፋፈልንና፣ ተሰምቶ የማይታወቅ ረሀብ፣ ግብረ ሰዶምን፣ ሌሎችም የሀጢያት ተግባሮች በግልጽ እንዲሰራ ትልቁን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ በግልጽ እየታየ ያለ እውነት ነው፡፡ የአብነት ተማሪዎች ውበታቸው የእመቤታችንን ስም እየጠሩ መለመን እኛ በመስጠት እየተባረክን እነርሱ በመለመን ስሟን እየጠሩ የሚያገኙት በረከት ደስ የሚል ነበር፡፡ ይሁን ጊዜው ካልፈቀደ ደግሞ ግድ ይለምኑ አይባልም፡፡ ግን በስጋ ድህነት ስም ሐይማኖ ት በእርዳታ ስንዴ ያውም በነቀዘ የሰው ልጅ በማይበላው መለወጥ የለበትም፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን፣ ረሀብ ነው፣ ችግር ነው፣ አይደለም፡፡ ስብከታችሁንና መዝሙራችሁን በእግዚአብሔር ቸርነት እየወረደ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በስንዴ መጣችሁብን፣ ይሄንን የነቀዘ ስንዴ፣ የኑፋቄ ትምህርታውንና መጽሐፋችሁን ከቤተክርስትያን አውደምህረታችን ይውረድልን፣ ይውረድልን፣ ይውረድልን፣ ይውረድልን፣ እኛ ረሀባችን ይሻለናል፡፡ መራባችን በረከታችን ነው፡፡ የክርስቶስ የሆነ የሚራበው ድንገት ስጋው ይሆናል የክርስቶስ ስጋና ደም ደግሞ ጥጋባችን ነው፡፡ ነፍሳችን ከጠገበች የስጋ ረሀብን በክርስቶስ ስም ለኖሩት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ነፍስ እየራባት ስጋ ቢጠግብ ምንድን ነው ትርጉሙ???????????????? ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ጭምር፡፡ ማቴ 4

  ReplyDelete
  Replies
  1. eski zim bel ke ewket netsa yehonkew wendimachin

   Delete
 8. egziabher yihien zemenim fetere. kewotatinet befit b/kirstiyanachin neberech. eski abatochachin enisma. alemetadel.

  ReplyDelete
 9. To josant December 1,2015 at 5:36am
  That might be explain you. You are out of mind.

  ReplyDelete
 10. in the above you say this=> "ኤቢሲዲ የቆጠሩ በርካታ አባላት ያሉት ቢሆንም ብዙዎቹ አእምሯቸው በተረት ስለደነዘዘና " we know you tehadso menafk.////

  ReplyDelete