Wednesday, November 4, 2015

የጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እና አንዳንድ ክስተቶች ምን ይመስላሉ?ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የሲኖዶስ ስብሰባ ልዩ ትኩረት የሚስብ ስብሰባ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለሳቢነቱ በማቅና በወንጌል እንቅስቃሴ መካከል ያለው ፍትጊያ ተጠቃሽ ነው፡፡ የዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስም በጉጉት ሲጠበቅ ነበር፡፡ ብዙዎች በጉጉት ይጠብቁት የነበረው ግን ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ማቅ በየቦታው ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣል በሚለው አቋሙ ብዙ ሰዎች ሊወገዙ ነው ብሎ ከ6 ወር ላላነሠ ጊዜ ሲያወራና ሲያስወራ ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴውን የሚያሳልጡለትን ቡድኖች ሲያደራጅ ከርሞአል፡፡ በየፌስ ቡኩ እና በተለይም ሐራ በተባለው ብሎጉ የተቻለውን የማደናገሪያ ጽሑፍ ሲለጥፍ ነበር የከረመው፡፡ ፀረ ወንጌል አቋም ያላቸው በዘንድሮ ጥቅምት ይለያል እስከ ማለት የደረሰበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡
በሠበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ አጠንክረው “ሕዝቡ ወደሌላ እምነት እየፈለሰ ነው፤ ባዶአችንን ከመቅረታችን በፊት ለተደራጀ ድንበር የለሽ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንነሳ” ብለው ቤተ ክርስቲያኗ አሁን ያለችበትን ተጨባጭ እውነት በገሃድ አሳዩ፡፡ ይህም ማቅና ያደራጃቸው ቡድኖች ብዙ ሲለፉለት የነበረው የጥቅምቱ ሲኖዶስ የመክፈቻ ፀሎት ላይም ከዚህ በፊት በመናጆነት ወጥተው ተሃድሶን እናወግዛለን የሚሉ ወጣቶች ወደ ቦታው ዝር ሳይሉ ቀርተዋል፡፡ እነዚህን ወጣቶች ሲያስተባብር የነበረው የግቢ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ ሄኖክ አሥራት በሲቪል ሰርቪሱ ውይይት ላይ የቡድኑን ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት አሁን ብዙ ተምሬአለሁ ስላለ ወጣቶችን በማያውቁት መንገድ ለጥፋት ማሰለፉን የተወ መስሏል፡፡

የተጀመረው የሲኖዶስ ስብሰባ ዋዜማ ላይ አባ ሳሙኤል በስማቸው ባሳተሙት ግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ የየድርሰት ስርቆት እና የክህደት ቃል ይፋ በመሆኑ ብዙዎች ሊቀጳጳሱ ይህን ከሠሩ ታዲያ ተሃድሶ እየተባሉ የሚከሰሱ ምን አደረጉ? ወደማለት መጥተዋልና በማቅ ዘመቻ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የቸለሰበትን የራሱን አጋጣሚ ፈጥሮአል፡፡ ነገሩ በዚህ ብቻ መቆም ስለሌለበት የአባ ሳሙኤል ጉዳይ አጀንዳ ተይዞለት አንድ ውሳኔ ያገኝ ዘንድ ብዙዎች እየጠበቁ ነው፡፡ በዝምታ ከታለፈ ግን ቤተክርስቲያን ላይ የፍትሐዊነት ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡
ከ12 ቀናት ስብሰባ በኋላ የተጠናቀቀው የሲኖዶስ ስብሰባ 20 ነጥቦችን ያካተተ መግለጫ ሲያወጣ ብዙዎቹ ፀረ ወንጌል ሃይላት የናፈቁት ተሐድሶዎች ሊወገዙ ነው የሚለው ወሬያቸው ወሬና ምኞት ከመሆን አላለፈም፡፡ ሲኖዶሱ የስብሰባ ቀኖቹን ለቁም ነገር በማዋል በዚያ ፈንታ በእርጋታ፣ በብስለት ከስሜት በፀዳ መልኩ የቤተክርስቲያን ችግሮችን የሚያጠኑ ኮሚቴዎችን በመሰየም ሥራውን ጨርሶ ተበትኖአል፡፡ ይህም የርዕሰ መንበሩ በሳል አካሄድ ታክሎበት የተከናወነ ነው፡፡ ምክንያቱም ፍልሠት በዝቶአል እየተባለ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉበት ሁኔታ እያለ ይህንን የሚያባብስ ነገር መፍጠር ቤተክርስቲያኒቱን ከዚህ ለበለጠ ችግር እንደሚዳርጋት የታመነበት ይመስላል፡፡ በጨለማ ላይ የገደልና የዛፍ ጥላ ቢጨመርበት ጨለማውን ያባብሰዋልና፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱ እንደ አቡነ ጳውሎስ የመጨረሻ ዓመት በማቅ ስሜት የሚነዳ ከመሆን ይልቅ ሰከን ያለበት ነው፡፡
ከሠሞኑ የሀራ ዘገባ በተለይ በ34ኛው አጠቃላይ ጉባኤ በሠራችው ዘገባ በፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ላይ እርምጃ ይወስዳል ብላ በዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል አንባቢነት በኩል በሥርዋፅ ብታስገባም በቅዱስ ሲኖዶሱ ላይ ይህን በተመለከተ በኮሚቴ ይታይ በማለት ዘሎታል፡፡
ከተቋቋሙት ኮሚቴዎች መካከል በአቡነ ሕዝቅኤል ሊመራ የታቀደው የተሃድሶን ጉዳይ የሚያጠናው ኮሚቴ አንዱ ሲሆን ሐራም ዋና ነጥብ አድርጋ እንደፃፈችው ይህ ኮሚቴ ተሃድሶን በትምህርት ይከላከላል የሚል ነው፡፡ አይቀሬውን ተሐድሶን በትምህርት መከላከል የሚለው ተግባራዊነቱ፣ ተፈጻሚነቱና ውጤት አምጪነቱ አጠያያቂ ቢሆንም ቢያንስ ለትምህርት ቅድሚያ መሰጠቱ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ትምህርት ያስፈልጋል፡፡ ነባሩም ምሳሌ የሚለው ከመጠምጠም መማር ይቅደም ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ቤተክስርቲያን በዋናነት ራስዋን ለአለም ያስተዋወቀችው ዘርፍ በሆኑት በቅዳሴ በዜማ በቅኔ ወዘተ ሳይሆን ዋና በሆነው በትምህርተ ወንጌል ነው፡፡     
አሁን ሁሉም ወደ ብርሃን መውጣቱ አይቀርም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን የሕዝቡ ፍልሰት ሊገታ የሚችለው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ያመጣውን ውጤት በረጋ መንፈስ በትምህርት መቃኘት ሲቻል፣ ከተረታተረት ወደወንጌል ፊትን መመለስ ሲቻል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ወንጌልን ለማጥፋት ተረትን ለማጽናት የሚደረገው ትግል ግን የትም አያደርስም፡፡ ብቻ ይህ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ በአቡነ ሕዝቅኤል መሪነት ሊሰየም የታቀደው ኮሚቴ አባላት “… ጽኑ ሃይማኖት መልካም ሥነምግባር ሊኖራቸው ይገባል” ብሏል ብላ ሐራ የሰራችው ዘገባ ደስ የሚል ነው፡፡ አምና በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተሐድሶን የሚያጠና ኮሚቴ መሰየሙን ተከትሎ አባ ሰላማ ብሎግ ተቃውሞዋን አሰምታ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኮሚቴ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች እነ ሰሎሞን ቶልቻ እነ ኀይለጊዮርጊስ ዳኜና ሌሎቹም የሃይማኖትም የምግባርም ችግርና ጉድለት ያለባቸው መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በወቅቱ በተጻፈው ዘገባ ላይ ይህን ታላቅ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከሃይማኖት ሃይማኖት ከምግባር ምግባር የሌላቸው እንዴት ያጠኑታል? ለማህበረ ቅዱሳን አላማ ለመመቻቸት ካልሆነ በቀር ብለን በጽኑ ተቃውመን ነበር፡፡ እነዚያ ተሰይመው የነበሩ ግለሰቦች በቅርስ ሌብነትና ቤተ ክርስቲያን የማታስተምረውን ኑፋቄ በጽሑፍ ያሰፈሩና ሌላም በርካታ የሥነምግባር ችግሮች ያሉባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ከቤተከርስቲያን ይልቅ ለማህበረ ቅዱሳን ተንበርካኪ ሆነው ስለተገኙና ማቅ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለማስወገዝ መንገዱን አልጋ በአልጋ የሚያደርጉለት በመሆናቸው ከዚህ አንጻር ተመልምለው ነበር፡፡
በአሁኑ ሲኖዶስ ስብሰባ ግን ከሰዎች ይልቅ መስፈርት ላይ ያተኮረ ውሳኔ መሰጠቱ ለችግሩ ትክክለኛውን መፍትሔ ለማግኘት ሲኖዶሱ በትክክለኛው መንገድ ላይ መቆሙን ያመለክታል፡፡ እነዚህ ለቤተ ክርስቲያን ፈውስ የሆነውን የተሃድሶ ጉዳይን ማጥናት የለባቸውም ብለን የጠቆምነው በዘንድሮው ሲኖዶስ ስብሰባ ተቀባይነት አግኝቶ ሐራም ዘግበዋለች፡፡ ሆኖም ሲኖዶስ ያለፉት ውሳኔዎቹ ተፈጻሚ የማይሆኑና በቀጣዩ ስብሰባ ተቀልብሰው በሌላ ውሳኔ የሚተኩ መሆናቸው ክብሩን እንዳይቀነስ ጥንቃቄ ያሻል፡፡ ለዚህ ሁሉ አስቀድሞ በማንም ተጽዕኖ ስር ሳይወድቅና የእርሱ ያልሆነውና እንደ ማቅ ያሉ ቡድኖች የሚሰጡትን አጀንዳ ይዞ ለውሳኔ ከመጣደፍ ነገሩን ከሥሩ አጣርቶ ተገቢ ያለውን ውሳኔ ብስለት በተሞላበት መንገድ መወሰን አለበት፡፡ አሁን ከሞላ ጎደል ያደረገው ያን በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
የተሃድሶ ጉዳይ የቤተክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ትምህርት መነካት የለበትም የሚል ሲሆን ይህን ለማየትና ለማጥናት ፅኑ እምነት ያስፈልጋል፡፡ በቤተክርስቲያኒቱ ባህላዊ ትምህርት የጠገበ፣ በነገረ መለኮት ትምህርት የተራቀቀ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን መጻሕፍት በደንብ ያጠና በእውቀት የበለፀገ ሰው በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ሊካተት ይገባዋል፡፡ ደግሞም ጥያቄዎችን የማይፈራ መሆን አለበት፡፡ ማቅን በመፍራት ሳይሆን እውነትንና ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን በማፈላለግ መሥራት አለበት፡፡ እውነትን ለማወቅ የመጀመሪያው መስፈርት ጥያቄን አለመፍራት ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ አቡነ ሕዝቅኤል ይህን ሊያስቡበት ይገባል እንላለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን የማያውቅ ስለተሃድሶ ለማጥናት ቢገባ የበለጠ ችግር ነው የሚፈጥረው፡፡
 በአንድ ወቅት የቅድስት ሥላሴ አስተዳደር የነበረው ሰው አንድ ተማሪ የጠዋት ፀሎት አልገባህም ተብሎ ተከሶ ሲቀርብለት፣ “ዝንየት ተፃብኦ መቶኝ ነው” አለ፡፡ ባለሥልጣኑም በል ሂድና የመታህን ጥራው አለ እየተባለ ይነገራል፡፡ ይህ መሠረታዊና ተሃድሶ እንዲነሳ በር የከፈተ ያለማወቅ ችግር ነው፡፡ ሌላው በሀራ እንደተዘገበው “ምግባር ያላቸው” ይላል አምና የተዋቀሩትና ዘንድሮ የፈረሱትን ኮሚቴዎች በተመለከተ አንዱ ጥያቄአችን ይህ ነበረ፡፡ ምግባረ ብልሹዎች ነበሩ እኮ ተሃድሶን እንዲያጠኑ የቤት ሥራ የተሰጣቸው! ማህበረ ቅዱሳን በባህሪው ሞራል የሌላቸውን ሰዎች ይፈልጋል ምክንያቱም ይታዘዙለታልና፡፡ አሁን ግን ከእነዚህ የፀዱ ከጀርባቸው ላይ ባለባቸው ነውር የማይሸማቀቁ ሰዎች በዚህ ኮሚቴ እንዲዋቀሩ መታሰቡ እጅግ የሚያስደስት ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ የሲኖዶስ ስብሰባ ዝውውር ከተደረገላቸው ጳጳሳት መካከል አንዱ አባ እንድርያስ ናቸው፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ሣንባ የሆነችው ሀራ ሊቀጳጳሱን “አራት አይና” ብላ አሞካሽታቸዋለች፡፡ “አሁን ሊቃውንት ጉባኤ ጥሩ ሰው አገኘ፤ ቦታው የጡረታ መውጫ መሆኑ ቀረ ይህ መምሪያ የጡረተኞች በሌሎች የሚያምፁ የሚከማቹበት የቅጣት ቦታ ነበር፣ ሙያ የሌላቸው ሰዎች የተሰበሰቡበት ነበር” እስከ ማለት ደረሰች፡፡ ለዚህ እኮ ነው በግፍ ተከሰው የሚቀርቡትን ሊቃውነት መሠረታዊ ነገር ሳይመልስ እያስወገዘ የኖረው፡፡ ሀራም የእረፍት ቦታ እንጂ የሊቃውንት መሰብሰቢያ አይደለም ብላ ስትል የሊቃውንቱን ጉባኤ አሳንሳዋለች፡፡ በሌላ በኩል ግን አቡነ እንድርያስ በሀገረ ስብከታቸው መግባባት ስላልቻሉ ወደዚህ መምሪያ መጡ ትላለች፤ ይህስ ለእሳቸው የእረፍት ቦታ የጡረታ መውጫ ቦታ … መሆኑ አይደለም እንዴ!
ሐራ አባ እንድርያስን በሐሰት “አራት አይና ናቸው” ትበል እንጂ እርሳቸው የሚታወቁት በሐዲሳት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሐዲሳት ተቀጥረው ሲያስተምሩ በአብዛኛው “ስለ ሃያው ዓለማት ምንነት ላውርደው? ልተርከው? አእምሮአችሁ ይሸከማል?” እያሉ የባህታዊ ትምህርት ሲያስተምሩ ነው ያሳለፉት፡፡ አራት አይናዎችማ የታወቁ ናቸው፡፡ እነ ዶ/ር አባ አየለ አለሙ፣ እነ አራት ዐይና ጎሹ፣ እነ መላከ ገነት ገ/ሥላሴ፣ እነ አቡነ መርሐ ወዘተ ነበሩ፡፡ አባ እንድርያስ ግን ለዚህ የሚመጥኑ አይደሉም፡፡ በሐራ በኩል ተገቢ ሹመት ነው ተብሎ የተሞካሸላቸው በስሕተትና የማቅን አይዲዮሎጂ ሊያራምዱ ስለሚችሉ ማቅ እየከሰሰ የሚያቀርባቸውን መናፍቅ ይሉልኛል ብሎ ይሆናል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፡፡ አባ እንድርያስ ከአስማትና ከጥንቆላ ጋር ተያይዞ ስማቸው ይነሳል፡፡ ማንም እንደሚያውቀው የቀድሞውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን በአየር ላይ ጋኔን አጥፉልኝ ብለው በጃናሞራ ላሉ ለእስላም ሼኪዎች ጽላትና ብር ከደብዳቤ ጋር የሰጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ደብዳቤው የእሳቸው ለመሆኑ አባ ዲና አረጋግጦ በወቅቱ በግል አባ ጳውሎስን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱን ግን አልጠየቁም፡፡ የ200 ባለሥልጣናት ፎቶ ከአንድ ነጭ በግ ጋር በጎንደር ሀገረ ስብከት ማስቀበራቸውስ ይረሳል? ይህን ሂደት የሄዱት በተለይ አባ ጳውሎስንና የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጽላት ላይ አሟርተው ለማስገደል ከጥቂት የውጭ ሲኖዶስ አባላት ጋር ደብዳቤ ተላልከውና አውርተው እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ሀራ አራት አይና ያለቻቸው ለሊቃውንት ጉባኤ ትክክለኛ ሰው ያለቻቸው አባ እንድርያስ እንኳን አራት አይና ሊሆኑ በአንዱስ መች በሚገባ አዩበት?
ሌላው የሲኖዶሱ ስብሰባ ገጠመኝ አባ ቀሌምንጦስን የተመለከተ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ ሆነው ሲሰሩ፣ በቀሲስ በላይ ሙስናዊና ብልሹ አሠራረት የተነሣ ጩኸት በመብዛቱ ፓትርያርኩ የሥራ አስኪያጅ ለውጥ ማድረጋቸውንና ሥራ አስኪያጆቹም የሙስናውን ሰንሰለት በተቻለ መጠን ለመበጣጠስ እርምጃዎችን እየወሰዱ በነበረበት ሁኔታ ያን መደገፍና ሥራቸውን መሥራት ሲገባቸው ወደአድማና አልቀበልም ወደሚል አቅጣጫ ሄዱ፡፡ ፓትርያርኩ ግን በአቋማቸው ጸንተው ወደፊት ገፉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሐራ ለአባ ቀሌምንጦስ ጮኻላቸው ነበር፡፡ አሁን ግን ወደ ሀገረ ስብከታቸው እንደማይመለሱ ስታረጋግጥ ደግሞ ያቀረቡትን ደብዳቤ አውጥታ ወደ ሥራዬ ልመለስ በማለታቸው ትዝብት ላይ ወደቁ በማለት ቀልዳባቸዋልች፡፡ በገዛ ፈቃዳቸው የተውትን የረዳት ሊቀ ጳጳስነት ሥራ ሀራ እንደተበደሉ ተናግራ ነበር ለነገሩ ከዚህ ቀደም የብአዴን ሠላይ ብላስ ወርፋቸው አልነበረምን?
በአጠቃላይ ሲታይ የዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ከሞላ ጎደል በቅዱስ ፓትርያርኩ በሳል አመራርና የረጋ አካሄድ ያጠፉ መመከር አለባቸው በሚል መንፈስ እናውግዝ ከሚል ፈረጃ ወጥቶ የ4 ኪሎ የሻይ ቤትና ድራፍት ቤት አድማና ጥያቄ ጸድቶ ተጠናቋል፡፡ ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው ችግሮች ተብለው ለተነሡ ነገሮች ሁሉ የተጣደፈና ማቅንና ጀሌዎቹን ለማስደሰት የግብር ይውጣ ውሳኔ የተላለፈበት ሳይሆን ኮሚቴ የተሠየመበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ አሁን ስጋቱ የተቋቋሙት ኮሚቴዎች ሥራ መሥራት አቅቶቸው ይህን የሚያጠና ሌላ ኮሚቴ ይዋቀር እንዳይባል ብቻ ነው፡፡ ምናልባትም ከዚህ ቀደም እንደታየው ኮሚቴው አጥንቶ ያቀረበውን ሐሳብ ሲኖዶሱ ከመቀበል ይልቅ ያን ሽሮ በራስ መንገድ መጓዝ እንዳይኖር ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ምን እናድርግ? ተብሎ እንዲያጠናና ለቤተክርስቲያን ያለውን ጥቅምና ጉዳት እንዲመረምር የተሰየመው ኮሚቴ በማስረጃዎች ላይ ተመሥርቶ ማኅበረ ቅዱሳን ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ቤተክርስቲያን ያለ ማኅበረ ቅዱሳን ኖራለች ወደፊትም ትኖራለች ተብሎ መፍረስ አለበት ከሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ሲኖዶሱ ውስጥ በተፈጠረው ቡድን ምክንያት ራሱ አምኖ የሰየመውን ኮሚቴ ሐሳብ ጥሎ ከጥናት ውጪ በሆነና በሌላ ሐሣብ ተይዞ ማቅ እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ አሁንም አንዳንድ ጥናቶችና ማጣራቶች እንደዚህ ካለው አድሏዊ አሰራርና ማቅን ለማስደሰት በሚል መካሄድ የለባቸውም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ቅዱስ ፓትርያርኩ አምና “በይሉኝታ የራስ አሊ ቤት ተፈታ” ብለው እንዳሉት ይሉኝታ ካልያዘን በቀር ኮሚቴዎች በሐቅ መስራት አለባቸው፡፡9 comments:

 1. ግራ የገባህ ዘባራቂ ወሬኛ።
  ምድረ ሃራጥቃ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችሁ ተነቅቶበታል፣ ኮተታችሁን ይዛችሁ ከቤተክርስቲያናችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠረጉ ጫፍ ላይ ደርሳችኋልና እንዴት ደስ ይላል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከዛ ሕንጻ በቤ/ኑን ታከራየዋለህ

   Delete
 2. አባ ሰላማዎች ለምትሰጡን መረጃ ምስጋናየ ላቅ ያለ ነው ነገር ግን ስለ አቡነ እንድርያስ የቀረበው ዘገባ ትንሽ ከጥላቻ የመነጨ ይመስላል ምክንያቱም አቡነ እንድርያስ የሐዲሳት ብቻ ሳይሆኑ የአራቱ ጉባዔ መምህር ናቸው ሌላው ከውጭ ካሉ አባቶቸ ጋር የተባለውም ፍጹም ሃሰት ነው

  ReplyDelete
 3. ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም.
  ተሐድሶዎች የማይገለጥና ተከድኖ የሚቀር ያለ እንዳይመስላችሁ፡፡ ማንነታችሁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገለጠ ነው፡፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚታደስ ሃይማኖት፣ ትውፊት፣ ታሪክና ሥርዓት የላትም፡፡ በነቢያት ትንቢት፣ በሐዋርያት ስብከትና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የማዕዘን ራስነት ላይ ተመሥርታለችና፡፡ ስለሆነም ሃይማኖት እንደ አባቶቻችን ሥልጣኔ እንደ ዘመናችን እንደተባለው ዘመኑን እየዋጀን እንኖራለን እንጂ ሃይማኖትን እንደ ሸሚዝ እየቀያየርም፡፡ የቤ/ክናችንም አስተዳደር ሲኖዶሳዊ እንጂ የፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ የአዳራሽ ውስጥ ጩኸት አይደለም፡፡
  የቅዱስ ሲኖዶሱንም ውሳኔ የቤ/ክኒቱ ልጆች ሁሉ በደስታ ይቀበሉታል፤ ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ-ተግባራዊ ከሚደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫዎች አንዱ እኮ አገር አቀፉ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ያስተላለፈውን የአቋም መግለጫ የ2008 ዓ.ም. የሥራ ዕቅድ ማድረግ ነው፡፡ የአቋም መግለጫው አንዱ ነጥብ ደግሞ ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶን መከላከል ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በአፍም በመጽሐፍም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በሕግም ከፍተኛ ዘመቻ የሚናካሂድበት ይሆናል፡፡ በሕግ ያልኩት ማንም ስው የፈለገውን ማመን መብቱ ሆኖ ሳለ ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ ኑፋቄያቸውን የግድ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ውስጥ ካልሆነ ብለው የሚቀጥሉ ከሆነ ነው፡፡

  ReplyDelete
 4. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚታደስ ሃይማኖት፣ ትውፊት፣ ታሪክና ሥርዓት የላትም፡፡ በነቢያት ትንቢት፣ በሐዋርያት ስብከትና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የማዕዘን ራስነት ላይ ተመሥርታለችና፡፡

  ReplyDelete
 5. ሃይማኖት እንደ አባቶቻችን ሥልጣኔ እንደ ዘመናችን እንደተባለው ዘመኑን እየዋጀን እንኖራለን እንጂ ሃይማኖትን እንደ ሸሚዝ አንቀያየርም፡፡ የቤ/ክናችንም አስተዳደር ሲኖዶሳዊ እንጂ የፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ የአዳራሽ ውስጥ ጩኸት አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 6. የቅዱስ ሲኖዶሱንም ውሳኔ የቤ/ክኒቱ ልጆች ሁሉ በደስታ ይቀበሉታል፤ ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ-ተግባራዊ ከሚደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫዎች አንዱ እኮ አገር አቀፉ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ያስተላለፈውን የአቋም መግለጫ የ2008 ዓ.ም. የሥራ ዕቅድ ማድረግ ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. ተሃድሶ ያስፈልጋል።ተሃድሶ ወደ ቀደመው እምነት መመለስ ነው። ከሳትንበት መመለስ ቤ/ክ ከቅዱስ ቃሉ ግር ሚጋጭ የተረት ድርሳናት ተሸክማ ልክ ነን እያሉ መፈከር አያዋጣም። ቀን ሳለ መንገድን ማቅናት ይበጃል።

  ReplyDelete
 8. GIZE GEBIR LEGIZIABIHER

  ReplyDelete