Saturday, November 7, 2015

የሰማዕቱ የአባ እስጢፋኖስ ስም ሲነሣ የዘርዓ ያዕቆብ መንፈስ ይጮሃል፤ ይታወካል Read in PDF
ሰሞኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ መቼም ቅዱስ ፓትርያርኩ የአትዮጵያ ፓትርያርክ እስከ ሆኑ ድረስ ከአሜሪካ አስከ አውሮፓ፣ ከአረብ እስከ ሱዳን በአገር ውስጥ ከአፋር እስከ ጋምቤላ እየሄዱ ነው፡፡ ወደእነዚሁ አገራት ሲሄዱ ማለትም ከሙስሊም እስከ ፕሮቴስታንት አገራት ሲሄዱ ማቅ የተባለው ጨለምተኛ ቡድን ምንም ብሎ አያውቅም፡፡ ከሰሞኑ ግን መንፈሱን የሚረብሸው አእምሮውንም የሚያውክ ነገር እየተሰማው ነው፡፡ ይኸውም የረበሸው የፓትርያርኩ የአዲግራት ጉዞ ነው፡፡
አዲግራት ትግራይ ውስጥ የሚገኝ የሰማዕቱ የአባ እስጢፋኖስ አገር ነው፡፡ አባ እስጢፋኖስ ደግሞ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ለማንም አልሰግድም በሥላሴ ላይ አራተኛ አልጨምርም ብሎ ከአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋር በመጣላቱ ከነተከታዮቹ ከ15 ሺህ በላይ መነኮሳት ካህናትና ምእመናን ሰማዕት ሆነዋል፡፡ የዘርዓ ያዕቆብ የመንፈስ ልጅ የሆነው ማቅ ቅዱስ ፓትርያርኩ እስከ አሁን በዓለም ላይ ካደረጉት ጉዞ መታገስ ያልቻለውና መንፈሱን በጣም የረበሸው የአዲግራቱ ጉዞአቸው ነው፡፡ አዲግራት ከዓለም የተለየች አገር ይመስል በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ ጉዞ ላይ አብዝቶ ሲጮኸ እና ሲያወግዝ ሰንብቷል፡፡ እርግጥ ማቅ የፓትርያርኩና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የአዲግራት ጉዞ ካላስጮኸውና ካላንፈራፈረው ነበር የሚገርመውና የሚደንቀው፡፡ የግብር አባቱ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ያፈሰሰው የቅዱሳኑ የደቂቀ እስጢፋኖስ ደም በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ያውከዋል፡፡ ለዚህም ነው የሰሞኑ የአዲግራት የፓትርያርኩ ጉብኝት ለማቅ የሆድ ቁርጠት የሆነበት፡፡ 

ማቅ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስን ተጠቅሞ የፓትርያርኩን ጉዞ ሊያደናቅፍ ላይ ታች ሲል ነው የከረመው፡፡ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ማናቸው? ቢባል ከማቅ ጋር የጠበቀና ከ10 ዓመት በላይ የቆየ የቃል ኪዳን ጋብቻ ያላቸው ግብዝ መነኩሴ ናቸው፡፡ ከአሁን በፊት ማቅ እርሳቸውን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ሲያጣላቸው እና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ግዳጅና ተልእኮ ሰጥቶአቸው ሳይወጡት በመቅረታቸው ከማቅ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሰማኒያቸውን ቀደው ሲያበቁ ማቅም ለግዳጅና ለተልእኮ አትበቃም ዓይንህ ለአፈር ብሎ ካላቸው በኋላ ተጣልተው ማስፈራሪያ አድርጎ የያዘባቸውን ነውር በማውጣት መነኩሴ ነኝ እያሉ ነገር ግን በኅቡእ ባለትዳርና የልጅ አባት እንዲሁም የጨለማው ቡድን አባል እንደሆኑ ሃራ በተባለው ብሎጉ ሲያብጠለጥላቸውና ገበናቸውን ሲያወጣ የነበረው ማቅ አሁን በፍቅር ሲከንፉለት ደግሞ ከነትዳራቸውና ከነወለዱት ልጅ ለጵጵስና ሲያጫቸው እያየን ነው፡፡
ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ከማቅ ጋር የነበራቸውን ፍቅር አድሰው አዲስ ውል ተፈራርመዋል፡፡ እሳቸው ማቅ በዓዲግራት እንደልቡ እንዲሰብክ በደብዳቤ ፈቅደዋል፡፡ ማቅም በትናንትና ዘገባው የደብረ ቤቴል ሚካኤል ቤተክርቲያን ሂሳብ ሹም የሆኑት እማሆይ አፀደማርያም ባለቤታቸው እንደሆኑ ሲያወራ ነበር፡፡ ነገሩ እውነት ነው፡፡ ማቅ ይህን ሁሉ ገበና ሸፍኖ ለማያገኙት ጵጵስና ሊያጫቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ በበኩላቸው የማቅን ተልእኮ ለማስፈፀም ላይ ታች እያሉ ነው፡፡ የቅዱስ ፓትርያርኩ የዓዲግራት ጉዞን በተመለከተ ሲያጉረመርም የሰነበተ ሲሆን፣ በተለይ መጋቤ አእላፍ አባ ገብረ መድኅን የሚያስተዳደሩትን አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም ገዳምን እንዳይጎበኙ በሚል ቅዱስነታቸው ወደዚያ ሊሄዱ አይገባም፤ ማቅ ይከፋዋል አባ ማቴዎስ ቁርጠት ይይዛቸዋል በሚል መልኩ አባ ሰላማ የተባለው ማህበር የመናፍቃን ነው እያለ ፓትርያርኩ እንዳይሄዱ ወሬ ሲነዛና በቀራቢዎቻቸው በኩል ሲጠመዝዝ ከርሟል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ላመኑበት ነገር ወደኋላ የማይሉ ጥቡዕ አባት ስለሆኑ ግን ሄደዋል፡፡ አባ ሰላማ ማኅበርና አባላቱ በ2004 የግንቦቱ ሲኖዶስ የተወገዘው በግርግርና መደማመጥ ጠፍቶ ነው እንጂ ሳይወገዙ በክብር እንዳሉት መናፍቃን “የክርስቶስ ንጹሐ ባሕርይነት ከእናቱ ንጽሕና የተነሣ ነው” ብለው ወይም “ሥጋ እምቅድመ ዓለም በቃል ከአብ ተወለደ” የሚሉ የክህደት ትምህርቶችን አስተምረው እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ይልቁንም የሰማዕታቱን የደቂቀ እስጢፋኖስን ደም በከንቱ ያፈሰሱ ንስሓ ሊገቡ ይገባል፡፡ የአባ እስጢፋኖስ ጻድቅነትም ሊረጋገጥ ይገባል ስላሉ ነው፡፡ የእነአባ ማቴዎስ ቡድን ደግሞ ነፍሰ ገዳዩ ዘርዓ ያዕቆብ ጻድቅ ነው ለእምነቱ ሲል የሞተው አባ እስጢፋኖስ ደግሞ መናፍቅና ፀረ ማርያም ነው ብላችሁ ካላመናችሁ አባ ሰላማ የተባለው ማኅበር መናፍቅ ነው ሊወገዝ ይገባል ብለው አንድ ነገር እንኳ ሳይጠይቁ የእምነት አቋሟችሁን አሰሙን ሳይባሉ ለማቅ ስላልተላላካችሁ መናፍቅ ተብላችሁ መወገዝ አለባችሁ ተብለው ነው አለአግባብ በግርግር የተወገዙት፡፡
የሚገርመውና የሚደንቀው ማቅ ለተልእኮው የሚጠቀማቸው ሰዎች በነውርና በምግባር የዘቀጡትን ነው፡፡ እነርሱን ተላላኪዎቹ በማድረግ እየተጠቀመ እርሱን ስለተቀናቀኑት ብቻ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ሥራ የሚሰሩትን በምንፍቅና ስም እያስወገዘ ይህችን ቤተክርስቲያን የት ሊያደርሳት ይሆን? ከሰሞኑ አባ ሰላማ ማኅበር የተወገዙ ናቸውና ፓትርያርኩ ወደአሲራ መቲራ መሄድ የለባቸውም፡፡ የአባ ሰላማ ማኅበር አባላት አባላቱም በዕውቀታቸውና ጉልበታቸውና በገንዘባቸው የሰሩትንና ለ60 ካህናት ማሠልጠኛ የሚሆነውን ማሠልጠኛ ተቋም ለመመረቅ መሄድ የለባቸውም ብሎ አቧራ ለማስነሳት መሞከሩ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምነው በልማት ኮምሽን ስም የሚሠሩ ፕሮጀክቶች ማቅ ዘወትር ከሚያብጠለጥላቸው በውጭ ከሚገኙ መሠረታቸው ፕሮቴስታንት ከሆኑ ድርጅቶች በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ አይደለም እንዴ? ማቅስ ቢሆን ከዚህ የጸዳ ነወይ? ታዲያ ፓትርያርኩ እነዚያን ሊመርቁ ሲሄዱ ምነው አልተናገረ? አሁን በግል ጥላቻ አለአግባብና በግርግር ያስወገዛቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ዕውቀታቸውን ገንዘባቸውን ጉልበታቸውን አስተባብረው ለ60 ካህናት የሚሆን ማሰልጠኛ ሰርተው በማስረከባቸው ያን ሊመርቁ አይገባም ማለት ከየት የመጣ ነው?
የገዳሙ አበምኔት መጋቤ አእላፍ አባ ገብረመድኅን ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ፣ ለገዳሙ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲያደርጉ ለተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አባ ሰላማ መኅበር ተወግዟል ከተባለ በኋላ እንኳ እየተጻፈላቸው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አስተዳዳሪው ገዳሙን በማልማት የሚታወቁ እንጂ ለገዳሙ በሚሰበሰበው ገንዘብ እንደ ማቅ አክስዮን አልገዙበት ወይም አራት ኪሎ ላይ መኖሪያ ቤት አልገነቡበት፡፡ ለማቅ ስላልተላላኩና ማቅን ወጥረው ስለያዙና በገዳማቶቻችን መነገድ የለብህም ገዳማቶቻችን ራሳቸውን መቻል አለባቸው ስላሉት ብቻ መናፍቅ መባላቸው ማቅን ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥለው ነው፡፡
በማቅና በአሲራ መቲራ ገዳም አስተዳዳሪና በአባ ሰላማ ማኅበር መካከል ያለው ትልቁ አለመግባባት የሃይማኖት ሳይሆን ከላይ የተጠቀሰው የጥቅም ነው፡፡ ማቅ በገዳማት ስም የሚሰበስበው የትየለሌ ገንዘብ ስላለና አዲግራት ላይ ሲደርስ ግን በአባ እስጢፋኖስ ገዳማት ስም ምንም አታደርግም ብለው ወጥረው ስለያዙት ለምን ጥቅሜ ተነካ ነው ነገሩ፡፡ ከዚህ ቀደም በአባ እስጢፋኖስ ገዳማት ስም የአጋሜን ሰዎች አሜሪካ ላይ ድጋፍ ጠይቆ ብዙ አልተሳካለትም፡፡ ይህን የሚያደርገው በገዳማቱ ውስጥ የሚገኘውን 170 ያህል በቅርስነት የተመዘገቡ መጻሕፍት ስላሉ የእነርሱን ደብዛ ለማጥፋትና በደቂቀ እስጢፋኖስ ዙሪያ የተጀመረውን ጥናትና ሥራዎቻቸውን ወደብርሃን የማውጣት የተቀደሰ ተግባር ለማደናቀፍ እንደሆነ ብዙዎች ይጠረጥራሉ፡፡ ነገር ግን አዲግራት ላይ ለጉንዳጉንዲ ገዳም መደጎሚያ የሚሆን በገዳሙ መሬት ላይ ባለአንድ ፎቅ ቤት በመሥራት ወዳጅ መስሎ ለመቅረብ እየጣረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እውን ለጊንዳጉንዲ ገዳም ባለአንድ ፎቅ ያሠራው አባ እስጢፋኖስን ተቀብሎ ነው ወይስ ለፖለቲካው ይሆን?
44 comments:

 1. ገድለ እስጢፋኖስ ያልከው ላይ እንዲህ አንደሚልስ ታውቃለህ? "በዛ ላይ አንደ ሌሎቹ ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማርያም እና የቅዱስ ያሬድን አንቀጸ ብርሃን ይደግሙ ነበረ:: እነዚህ ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን የሚያደንቁና የሚያመሰግኑ:በየአንቀጹ 'ሰአሊነ ቅድስት' (ቅድስት ሆይ: ኃጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን)የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው::ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስህተት አይሆንባቹም ብለዋቸው አብረው መስገዳቸውን መስክረዋል::" ገጽ 30 

  ReplyDelete
 2. ማቅ የዘርዐ ያዕቆብ የግብር ልጅ ነዉ

  ReplyDelete
 3. Ye aba natnael titer mechawecha yehonew endet new? All are forged document. Doesn't look real.

  ReplyDelete
 4. ደስ ሲል፤መንፈስቅዱስ ፊታችሁን ጸፍቶ፣አፋችሁን ከፍቶ አናገራችሁ!
  በተዘዋዋሪ ስላረፉ ቅዱሳን አማላጅነትና ሰይጣን አስጨናቂነት መሰከራችሁ፡፡አቡነ እስጢፋኖስ ከዚህ ዓለም አልፈዋል፡፡በእናንተ አስተምህሮ መሰረት ደግሞ ያረፉ ቅዱሳን ምድር ላይ ስላለው ሕይወት አያውቁም፡፡ስለዚህ ስማቸው ሲጠራ ‹‹አቤት›› የሚለው እነሱ ሳይሆኑ ሰይጣን ነው፡፡
  ሆኖም ለአቡነ እስጢፋኖስ እና ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ሲሆን ግን ይሕ መርሓችሁ አይሠራም፡፡የእስጢፋኖስ ስሙ ሲጠራ በመንፈስ ሕያው ሆኖ ማስደንገጥ መቻሉን ካመናችሁ፣የዘርዐያዕቆብ መንፈስ እንዲሁ ሕያው ሆኖ መደንገጡን ካመናችሁ ታዲያ የእመቤታችንና የሌሎች ቅዱሳን/ቅዱሳት አበው ስም ሲነሳ ሰይጣን እንደሚደነግጥ ለማመን ለምን ከበዳችሁ?
  እስከመቼ ይሆን ከግርግር ለማትረፍ የምትኳትኑት?!አይ!የእናንተ ነገር፡- ግማሽ ልጩ፤ግማሽ ጎፈሬ!ለፌ፤ወለፌ!ተልሚድ--እግረ ተማሪ ሁላ ከመካነ ኢየሱስ እስከ ቃለሕይወት ስትሯሯጥ የኔ የምትለው የእምነት ነመርህ ሳይኖርህ ኅሊናህ እንደተናወጸ ትኖራለህ!በአፍህ መጽሐፉን እንደበላኸው ታወጋለህ፤ውስጥህ ግን ቅንጣት ተአምኖ የለችም!ብዙ የሚያስጮኃችሁ እሱ ነው!ባዶነት ስለሚሰማችሁ እሱን ለመሸፈን ትክለፈለፋላችሁ!መዝሙረኛው ‹‹…አብቀው አፉሁ›› እንዳለው መደዴ አንደበታችሁን በቅዱሳን አበው ላይ ታላቅቃላችሁ!አምላከ ቅዱሳን ልብ ይስጣችሁ!ይመልሳችሁ!
  ተመየጢ፤ተመየጢ፣
  ሐራጥቃ፣ቀሳጢ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስድብ ያቁሙና ንስሐ ግቡ ስድብ ይቁም የምታስረዱትን በጽሞና አስረዱ የስድብ አፍ የተሰጠው ለዲያቢሎስ ብቻ ነው።ቅዱሳን ሁሉ አይሳደቡም ይሰደቡ ነበር እንጂ!!
   ኒቆዲሞስ

   Delete
 5. እናንተ የሥጋ ወንድሞቻችን ማቆች እውነትን መግደልና መቅበር ትችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን መቃብሩ ውስጥ ዘግታችሁበት ማስቀረት እንደማትችሉ አልበራላችሁም። ስለዚህ በብርሃኑ የእውነትን ብርሃን ማንነት አስተካክላችሁ ማየት እንድትችሉ ከሰማይ የመጣውን ብርሃን ብትጠይቁት ተርፋችሁ ታስተርፋላችሁና ምክሬን ተቀብላችሁ እንድትጠቀሙት በሰማይ ፍቅር ስም እጠይቃችኋለሁ???

  ከእናንተ በባሰ ጨለማ ውስጥ የነበርን እኛ የትናንት ግብረ አበሮቻችሁም ከማንም ተቪለን ተገኝተን ሳይሆን በመንፈሱ የፈቃዱን እውቀት ብቻ ተከትለን በእናንተና በመሰሎቻችሁ የሚደርስብን መከራ ሳይበግረን ደስ ብሎን ለተሃድሶው ሥራ እንድናገለግለው እጣ ደርሶብን ወይም ወድቆብን ነው።

  ስለዚህ ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚለው ድምጽ በራሳችሁ መንገድ ላይ ተገልጦ ከመሬት ላይ ፈጥርቆ ከመታወራችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ለራሳችሁ ህይወት ብታስቡለት! ሳይገባው በቅርስ፥ በሃይማኖትና በበሬ ወለደ ወሬያችሁ ለምታታለሉት የዋህ ህዝባችን የምህረት አምላክ በራሱ መለኮታዊ አሠራሩ እንደሚታደገው አትጠራጠሩ።

  እስቲ ለዛሬ ዘመን የማይቪረውን የመለኮትን ቃል አብረን እንድናየው የሃዋርያት ሥራ 5፡33 እስከ 42 ያለውን በተለየ መልኩ ቁጥር 38 እና 39 ላይ ትኩረት በመስጠት ማንበብ ብቻ ሳይሆን ከህይወታችን ጋር በማዛመድ እናሰላስለው??? ከዚህ በተረፈ እኛም ከሰማይ ለመጣው ቃል እምቢ ለማለት አቅሙ ስለሌለን ተወልደን ያደግንበትን ቤት በቃሉ የህይወት ውሀ አጥበን ለማጽዳት ጨካኙ ስላስጨከነን እንደ ውቫ ወደ ትፋት እንደማንመለስ ቁርጣችሁን እወቁ!
  ማስተዋል ለሁላችንም ይስጠን

  እውነቱ ይነገር ይሰማ ነኝ

  ReplyDelete
 6. እውነቱ ይነገር ይሰማNovember 9, 2015 at 7:15 AM

  እናንተ የሥጋ ወንድሞቻችን ማቆች እውነትን መግደልና መቅበር ትችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን መቃብሩ ውስጥ ዘግታችሁበት ማስቀረት እንደማትችሉ አልበራላችሁም። ስለዚህ በብርሃኑ የእውነትን ብርሃን ማንነት አስተካክላችሁ ማየት እንድትችሉ ከሰማይ የመጣውን ብርሃን ብትጠይቁት ተርፋችሁ ታስተርፋላችሁና ምክሬን ተቀብላችሁ እንድትጠቀሙት በሰማይ ፍቅር ስም እጠይቃችኋለሁ???

  ከእናንተ በባሰ ጨለማ ውስጥ የነበርን እኛ የትናንት ግብረ አበሮቻችሁም ከማንም ተቪለን ተገኝተን ሳይሆን በመንፈሱ የፈቃዱን እውቀት ብቻ ተከትለን በእናንተና በመሰሎቻችሁ የሚደርስብን መከራ ሳይበግረን ደስ ብሎን ለተሃድሶው ሥራ እንድናገለግለው እጣ ደርሶብን ወይም ወድቆብን ነው።

  ስለዚህ ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚለው ድምጽ በራሳችሁ መንገድ ላይ ተገልጦ ከመሬት ላይ ፈጥርቆ ከመታወራችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ለራሳችሁ ህይወት ብታስቡለት! ሳይገባው በቅርስ፥ በሃይማኖትና በበሬ ወለደ ወሬያችሁ ለምታታለሉት የዋህ ህዝባችን የምህረት አምላክ በራሱ መለኮታዊ አሠራሩ እንደሚታደገው አትጠራጠሩ።

  እስቲ ለዛሬ ዘመን የማይቪረውን የመለኮትን ቃል አብረን እንድናየው የሃዋርያት ሥራ 5፡33 እስከ 42 ያለውን በተለየ መልኩ ቁጥር 38 እና 39 ላይ ትኩረት በመስጠት ማንበብ ብቻ ሳይሆን ከህይወታችን ጋር በማዛመድ እናሰላስለው??? ከዚህ በተረፈ እኛም ከሰማይ ለመጣው ቃል እምቢ ለማለት አቅሙ ስለሌለን ተወልደን ያደግንበትን ቤት በቃሉ የህይወት ውሀ አጥበን ለማጽዳት ጨካኙ ስላስጨከነን እንደ ውቫ ወደ ትፋት እንደማንመለስ ቁርጣችሁን እወቁ!
  ማስተዋል ለሁላችንም ይስጠን

  እውነቱ ይነገር ይሰማ ነኝ

  ReplyDelete
 7. wishetu yineger mehon new yalebet simeh chekagnu seytan tsenawtohalina yegziabher menfes yalebet yastawikal andebetu yetegetalet egziabher yakeberachiwn yemyakebir. enante ende yihuda genzeb tekebilachihu haymanotin yeregetachihu silehone enante zend ewnet yelem yewnet amlak gin yiferdibachihual.

  ReplyDelete
 8. wishetu yineger degmo zare min eyalk new mechem enante betekiristyan yaladegchihu digis sitasadidu timehirt yameletachihu nachihuna ezaw zanigabachihu gibuna betekirstyanchinen likekulin masrejachihu haymanotawi migbarachiu endehon tselyu enji yedebdabe gagata ayihun mak mak eyalachihu zelalem afachihun kemitkeftu endenersu beserachihu taweku alezam and ken mak lebsachihu neseha gibu.

  ReplyDelete
 9. wishetu yineger weys....................menga luther

  ReplyDelete
 10. የሀሰት ስብከታችሁ መቼ ነው የሚያልቀው????????????????? የመጽሐፍ ቅዱሱን ሲያሳዝነን ደግሞ ወደ ቅዱሳን ገድል ገብታችሁ አንዱን፣ ከአንዱ ማጋጨትና መሳደብ፡፡ እነርሱ እኮ እንደእናንተ ተነቃቅፈውና ተሰዳድበው፣ አይደለም ወንጌልን የሰበኩት ተማምረው ተመካክረው፣ ተደማምጠው የኖሩ አባቶች ናቸው፡፡ ወንጌልን ኖረውበትና ብርሀን ሆነውበት ነው ያለፉት፡፡ እንደእናንተ ገድል መስራት ገደል ሆኖባቸው ያለፉ አይደሉም፡፡ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም፡፡ እኔ የገረመኝ የራሳችሁን የስጋ ስሜትና ምኞት መጽሐፍቅዱሱ መለዋወጥና ማጣመም ሳያንሳችሁ ቅዱሳን አባቶችን ደግሞ እርስ በእርስ ለማጋጨት ጎንበስ ቀና ማለታችሁ ደግሞ የበለጠ አውሬነታችሁን ይገልፃል፡፡ አውሬው ምነው የሚናገረውን አሳጣው????የቃላት አጠቃቀሙ ነው ደግሞ የሚገርመኝ ማቅ ለብሶ ምናምን የሀገራችንን የፖለቲካ ቃላቶችን ይመስል አውሬው የራሱ የሆኑ ቃላቶች እያወጣ የእግዚአብሔርን ስም ይሳደባል፣ ቅዱሳኖቹን ያጋጫል፡፡ ክርስቲያንን ይከፋፍላል የበግ ለምድ ለብሶ ያወናብዳል፡፡ ጌታ ሆይ አለማመናችንን እረድተኸው ይህን ትውልድ ልብ ሰጠውና ወደቤቱ ተመልሶ ከአባቶቹ ትህትናን እንዲማር መንፈስ ቅዱስን ላክላቸው፡፡

  ReplyDelete

 11. ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ አቋም… ባለቺን መነጽር፣እናነጻጽር፤4ቱን አንጻር!

  ክፍል-1

  ዘወትር የሕሊናዬን ሚዛን ዥዋዥዌ ከተትው ከሚያንገላቱት አርእስተ-ጉዳዮች አንዱ ነው--የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ፡፡ታሪካቸው ለሁሉ የተመቸ ሆነ፡፡እናም ሁሉም እንደመስኖ ውሃ እየጠለፈ ወደራሱ ሁዳድ ሊያስተኛው ይጥራል፡፡እየቦጨቀ በቁንጸላ ይወስድለታል፡፡ማን ያለ ያልወሰደለት?!የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥልጣኔ ተንታኞች፣የኢ/ያ ታሪክ ጸሐፊዎች፣የቤተ-እስራኤል ጉዳይ አይሑዳውያን ጸሐፍት፣ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ ያሉ ፕሮቴስታንታውያን፣ወዘተ…እንደየራሳቸው አስተሳሰብ እየቆነጸሉ ታሪኩን ለዓለም ናኝተውታል፡፡ከሞኝ ጓሮ ሞፈር ተቆርጡዋል!ህም!
  እንዲያ ሳይ ከፋኝ!ተከፋሁ!ታሪኩ በልዩ ልዩ ጸሐፍት ግላዊ ትርጓሜ አገልግሎት ላይ ሲውል ማየት አታከተኝ፡፡በማኅበራዊ ሚዲያው እድል ባገኘሁ ቁጥር ለሕሊናዬ የሚሰማኝን ብናገርም አልወጣልኝም፡፡የመተርጕማኑ ጽንፍ እና ጽንፍ ረግጦ እንደተመቸ ታሪኩን መቆልመም ደጋግሞ አእምሮዬን አማታው፡፡ስለዚህ የራሴን አቋም በግልጽ ማጸባረቄን ሳልዘነጋ ከትረካቸውና ከተራኪዎቹ አቋም በመነሳት የደቂቀ እስጢፋኖስን ታሪክ አረዳድ በ4 አርእስት ከፍዬ ገፋ አድርጌ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ዐርባዕቱ (4ቱ) አንጻር የምላቸው፡-

  (1) መፍቀሬ-ዘርዐያዕቆብ የኾነው ዕይታ (በተግባር ኦፊሴላዊው የኢኦተቤክ አቋም!)
  (2) መፍቀሬ-ደቂቀ እስጢፋኖስ የኾነው አቋም/መላምት!
  (3) ጉዳዩን ከሃይማኖት ይልቅ ከንጉሣዊ ሥርዓት ፖለቲካ ጋር የሚያዛምደው አቋም/መላምት!
  (4) አይሑዳዊው እና ፕሮቴስታንታዊው አቋም ናቸው--4ቱ ዐንጻሮቼ፡፡አንዲት (ስርዋጽ) ወሽመጥና መደምዲያምም ይኖረኛል፡፡

  ከላይ የተገለጹትን አቋሞች ከራሴ አቋም ጋር እያስተሳሰርኩና ንባቤ የፈቀደልኝን ያህል እጄ ላይ ባለው ማስረጃ እያስደገፍኩ (በፌስቡክ ስሌት) በረጅሙ ገልጫለሁ፡፡ያም ሆኖ ሓሳቤን በኮምፒተር መትቼ ስጨርስ ብዙ ጊዜየንና ጉልበቴን የነ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ አቋም ያልኩትን መፍቀሬ-ደቂቀ እስጢፋኖስ አቀራረብ በመሞገት ሳላሳልፍ እንዳልቀረሁ ተሰምቶኛል፡፡ምናልባት አሁን አሁን ለታሪኩ ትርጓሜ መብዛት የእሳቸው ድርሻ ስላየለብኝ ይሆናል፡፡

  ከዚያ በፊት ግን ስለመሪ ባለታሪኮቹ መጠነኛ መረጃ ልስጥ፡፡አባ እስጢፋኖስ በትግራይ ከአክሱም በስተምስራቅ ስቡሐ በተባለ አካባቢ በግምት በ1372 ዓ.ም ወይም ዘመናዊ የታሪኩ አጥኚዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ1380 ዓ.ም ከአባቱ ብርሃነመስቀል ከእናቱ ሳራ ተወለደ፡፡ዓለማዊ ስሙ ሐድገአንበሳ ተባለ፡፡አባቱ ገና በማኅፀን ሳለ ስለሞተ ጥቂት ጊዜ እናቱን በእረኛነት ሲያገለግል ቆይቶ ት/ቤት ገባ፡፡በ19 ዓመቱ መነኮሰ፡፡የተረፈ ታሪኩ በጽሑፉ ይዳሰሳል፡፡
  ከአባ እስጢፋኖስ ጋር አያይዘን በዚህ ጽሑፍ የምናነሳው ዘርዐያዕቆብ በ1391 ዓ.ም ከአባቱ ንጉሥ ዳዊት ከእናቱ እግዚእክብራ ተወለደ፡፡በአምባ ግሸንና በደብረ አባይ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማረ አደገ፡፡ከአባቱ አጼ ዳዊት ሞት በኋላ ሥልጣነ-መንግስቱ በወራሾች መካከል ሲገለባበጥ ቆይቶ በስተመጨረሻ በ1426 ዓ.ም እሱ ከአምባ ግሸን ወርዶ ነገሠ፡፡ንጉሡ በመካከለኛው ዘመን ከተነሱ ነገሥታ ሁሉ እጅግ ምሑሩ፣ዝነኛውና ኃያሉ ሳይሆን አይቀርም፡፡በአባ እስጢፋኖስና በዘርዐያዕቆብ መካከል የተጀመውና በወራሾቻቸው መካከልም ከ70 ዓመታት በላይ የቀጠለው ግጭት በዋናነት ለመስቀል፣ለእመቤታችንና ለንጉሥ መደረግ ስላለበት ስግደት በተነሳ አለመግባባት ዙሪያ ያተኩራል፡፡አለመግባባቱ በ2ቱም ወገኖች አልተካደም፡፡ያለመግባባቱ ምንጭና አተረጓጎም ግን በ2ቱም የተለያየ ምክንያት ይሰጠዋል፡፡ፈተናችን እሱ ነው--ከ2ቱ ተገዳዳሪ ጽሑፎች መካከል እውነትን አንጥሮ ማውጣት!የአንዱ ወገን ብቻ ደጋፊ ሆኖ ‹‹የታባቱ፤ድሮስ…›› እያለ መቀጠልን ለሚሻ ግን ታሪኩ የተመቸ ነው፡፡መድከም አያስፈልግም፡፡መርጦ መሰለፍ ብቻ!ወይም ለራስ ሃይማኖታዊ ወይም ፖለቲካዊ፤አለፍ ካለም ለብሔረሰባዊ አጀንዳ ጠምዝዞ መተርጎም!እንዲያ ባይሆን ግን ምኞቴ ነው፡፡አነሳሴም ታሪኩን በተረዳሁበት መንገድ አነጻጽሮ ‹‹እውነት›› ብዬ ያመንኩበትን መጻፍ ነው፡፡ቀጠልኩ…

  ReplyDelete
 12. 1--መፍቀሬ-ዘርዐያዕቆብ የኾነው ዕይታ!

  (1.1) በእኔ ጠባብ ንባብ መሰረት ይሕ እይታ በተአምረ ማርያም፣በንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ዜና መዋዕል እና በማኅሌተ-ፅጌ ከሰፈሩ ታሪኮችና አገላለጾች ይነሳል፡፡በተአምረ ማርያም ደቂቀ እስጢፋ[ኖስ] ለእመቤታችንና ለመስቀል መስገድን እምቢ ያሉ አይሑዳውያን በመሆናቸው ለክርክር ንጉሡና ሊቃውንቱ ፊት ቀርበው በጉባኤ እንደተረቱ፣በንጉሡና በተሰበሰበው ምዕመን ሞት ተፈርዶባቸው በሥልጣነ-ክሕነት ተወግዘው ከተለዩ በኋላ በድንጋይ ተወግረው እንደተገደሉ ተጽፏል(ተአምረ ማርያም በፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንደተጠቀሰው ገጽ 53፣በካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ገጽ 47)፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ በማኅሌተ ፅጌ ውስጥም ‹‹ዘሰ ይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር ተአምረኪ ክርስቲናዊ፣ኢ-ክርስቱስን ውእቱ (ዳእሙ) አይሑዳዊ ወሰርፀ-እስጢፋ ሐሳዊ፣….አንቺን እወዳለሁ እያለ ክርስቲያናዊ ተአምርሽን ግን የማይወድ ክርስቲያን አይደለም፤አይሑዳዊና የውሸተኛ እስጢፋ[ኖስ] ተቀጽላ እንጂ…››የሚል ማኅሌታዊ ድርሰት ያለ ሲሆን በዘመነ-ፅጌ (ከመስከረም 26-ኅዳር 6) ባሉ 5 (አንዳንድ ጊዜም 6 ይሆናሉ) እሑዶች ድርሰቱ በዜማ ይደረሳል፡፡

  (1.2) ዋናውን የግዕዝ ቅጂ ለማግኘት ባንታደልም በፓንክረስት ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በጎግል በኩል የደረሰን የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ዜና መዋዕል ከተአምረ ማርያም ጋር የተመሳሰለ ታሪክ ያቀርብልናል፡፡ደቂቀ እስጢፋ[ኖስ] ለእመቤታችንና ለልጇ መስቀል አንሰግድም የሚል ክሕደት ማምጣታቸውን፣ንጉሡ አስጠርቶ ከካሕናቱ ጋር በመሆን ተከራክሮ ኀፍረት ቢያከናንባቸውም ከስሕተታቸው አለመመለሳቸውን፣በዚህም የተነሳ ንጉሡ ራሱ እና ሹማምንቱ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ተመላሽ ተሳላሚዎች በተሳተፉበት ጉባኤ ደቂቀ እስጢፋ[ኖስ] እስከ ሞት ድረስ እንዲሰቃዩ ተወስኖ በውሳኔው መሰረት ምላሳቸው ተቆርጦ፣አፍንጫቸው ተፎንኖ (ተሟጥጦ) የካቲት 2 ቀን በድንጋይ ውግራት ከተገደሉ በኋላ በ38ኛ ቀን ለመጋቢት መስቀል (መጋቢት 10 የዓመቱ መስቀል ነው!)በደብረ ብርሃን ብርሃን መውረዱን ይተርካል፡፡በፓንክረስት ቋንቋ ሲቀመጥ፡-
  ….there was an uprising of the children of Estifa, who declared that they did [not] want
  to prostrate themselves before Our Lady Mary not before the cross of
  her son. The King had them summoned before himself, made them repeat
  what they had said and, during a discussion in which his priests took part, he confounded them and covered them with shame; but they did not abandon for all this their errors. The King then had them judged, convoked all his court and the pilgrims who had returned from
  Jerusalem, and it was decided that "they should undergo special tortures till they died. Their noses and tongues were cut off and they were stoned to death on the 2nd of the month of Yaktit. Thirty-eight days after their stoning, the 10th of Magabit, the day of the feast of the Cross, a light appeared in the sky and remained visible in all the land for several days, which caused that our King took fancy to this locality which he named Dabra Berhan.
  የሚል ሆኖ ይገኛል፡፡በሥራ አጋጣሚ ባለፈው መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም ደብረ ብርሃን ሥላሴ ለመሳለም ገብቼ ይሕ ብርሃን ወረደበት ተብሎ በትውፊት የሚታወቅ ቦታ በመቅደሱ እና በቤተልሔሙ መካከል በስተደቡብ-ምስራቅ አቅጣጫ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ለማዘከሪያ የሚሆን ምልክት እንደተደረገለት አስተውያለሁ፡፡ወደ ታሪኩ ልመለስ--ወደ ዘርዐያዕቆብ ጉባኤ…..

  (1.3) ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የእግዚአብሔር ስም ሲነሣ ‹‹ገናና ለሆነው ንግስናህ እሰግዳለሁ›› እያሉ ስሙን (የእ/ሔርን) እንዲጠራ፣የእመቤታችን ስም ሲነሳ ‹‹በጉባኤያችን ለድንግልናዋ ራሳችንን በሰጊድ ዝቅ እናደርጋለን›› እንዲባል፣የንጉሥ ዘርዐያዕቆብን ቃል የሰማ ወይም እሱ ፊት የቀረበ ሁሉ ‹‹ንጉሥ ዘርዐያዕቆብን በሰጠን አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ፊት ፊት እንሰግዳለን›› ማለት እንዳለበት በዐዋጅ መልክ ከሞራላዊ (ቀኖናዊ) ቅጣት የተሻገረ ዓለማዊ ቅጣትን የሚያስከትል ድንጋጌ ማውጣቱን ዜናመዋዕሉ ይገልጻል፡፡እንግሊዝኛው ‹‹Our King made also the following prescriptions: When you invoke the name of God, all you Christians, say at first: "I prostrate myself before the magnificence of his Kingship", then invoke his name.Likewise, when you will want to invoke the name of our Lady Mary,say: "It is meet to prostrate oneself before her virginity," then invoke it. Finally, when you hear our word or when you appear before us, say, always prostrating youselves: "We prostrate ourselves before the Father, the Son and the Holy Ghost, who gave us as King, Zara Yaqob" ይላል፡፡ይሕ ድንጋጌ በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዘንድ የነበረው አሉታዊ አቀባበል በገድለ አበው ወአኃው የሰፈረውን መሪር ንጉሳዊ ቅጣት እንደወለደ ግልጽ ነው፡፡የዐዋጁን መጽሐፋዊነት እናቆየውና ወደ መፍቀሬ-ዘርዐያዕቆብ ጸሐፍት እንመለስ፡፡

  ReplyDelete
 13. (1.4) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ዙሪያ ለሚጻፉ ጽሑፎች ሁሉ ቀዳሚ ተጠቃሽ በሆነው የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ‹‹የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ›› ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ በነገሠበት (እ.ኤ.አ) ከ1434-1468 ዓ.ም ‹‹ደቂቀ እስጢፋ የሚባሉ ለእመቤታችንና ለቅዱስ መስቀል ስግደት አይገባም የሚሉ መናፍቃን እንደተነሱ›› ሰፍሯል (አቡነ ጎርጎርዮስ፡ገ.45)፡፡ሊቀካሕናት ክንፈገብርኤል አልታዬ በበኩላቸው ‹‹ደቂቀ እስጢፋ /የእስጢፋ ተከታዮች/ በአለቃቸውና በመምህራቸው በሠርፀ እስጢፋ መሪነት ይሰጡት በነበረው ትምህርት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ክርክር ተነስቶ መለያየት ተፈጥሮ ነበር›› በማለት በለዘብታ አንስተውታል (የኢኦተቤክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻፡ገ.22)፡፡የቤተክርስቲያን ታሪክ በመጻፍና በማስተማር በኢኦተቤክ በተለይም በቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የክብር ቦታ ያላቸውና በአቡነ ጳውሎስ ሰኔ 21 ቀን 2000 ዓ.ም በኢኦተቤክ የቲዎሎጂ ኮሌጆች ታሪክ የመጀመሪያው ረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ሊቁ ሉሌ መላኩ ‹‹ደቂቀ እስጢፋ (የእስጢፋኖስ ተከታዮች፡ልጆች) የተባሉት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም፣ለቅዱሳንና ለጌታ መስቀል መስገድ አይገባም ብለው የክሕደት ትምሕርት ስላስተማሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ተወግዘዋል፡፡በዐፄ ዘርዐያዕቆብም ትእዛዝ የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል፡፡የነዚህ ሰዎች ትምህርት ዘግየት ብለው በ16ኛው መቶ ዘመን አውሮፓ ውስጥ ከተነሱት ፕሮቴስታንቶች እምነት ይመሳሰላል፡፡ይኸው ትምህርታቸው የአይሑድ እምነትም ጠባይ አለው›› ይላሉ (ሉሌ መላኩ፡ገ.132)፡፡ሉሌ መላኩ ባነሷቸው የመጨረሻዎቹ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ላይ አልሳማማም፤ኋላ ልመለስበት!

  (1.5) እስከ ቅርብ ጊዜ ባለው የኢኦተቤክ ታሪክ አጻጻፍ ሂደት ዘርዐያዕቆብ ከደቂቀ እስጢፋኖስ ጋር ባለው ግንኙነት እና በወሰደው ቅጣት በወቀሳ የጻፈበት ሰው ብዙም አይገኝ፡፡ከዛ ይልቅ የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ዘመን ሥነ-ጽሑፍ በማነቃቃት፣ሥርዓት በመደንገግ፣‹‹ደስክ›› እና ‹‹ዲኖ›› የተባሉትን የአምልኮ-ባእድ መንገዶች በማጥፋት፣ተስፋፊ ሙስሊሞችን በመግታት፣አብያተ-ክርስቲያናትን በማሳነጽ(ለምሳሌ በጋሞ-ጎፋ ጨንቻ ያለችው ብርብር ማርያም፣ደ/ሊባኖስ፣ደ/ብርሃን ሥላሴ፣የጎጃሟ ደ/ወርቅ ማርያምና የባሕርዳሩ ቅ/ጊዮርጊስ ካቴድራል፣ጻድቃኔ ማርያም፣ግሸን ማርያም፣አክሱም ጽዮን መጠኑ ቢለያየም ከንጉሡ ጋር የተያያዘ ታሪክ አላቸው)፣የኢየሩሳሌም ገዳማትን ይዞታ በማጠናከር፣በ1440-41 በፍሎረንስ ከተማ በተካሄድ ጉባኤ ወኪል ከኢየሩሳሌም ገዳም አባ ኒቆዲሞስ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ስለመላኩ፣የግብጻውያን ክርስቲያኖችና የኢየሩሳሌም ተሳላሚ ኢትዮጵያውያን ደኅንነትን ለማረጋገጥ ስለመድከሙ የኢኦተቤክ ታሪክ ላይ በጻፉ ሰዎች ሁሉ ተጠቅሶለታል፡፡

  (1.6) ያም ሆኖ ንጉሡ በኢኦተቤክ በክብር ከመነሳት በቀር የቅድስና መዐርግ የተሰጠው ስለመሆኑ የጻፈ ሰው የለም፡፡በዚህ ዙሪያ ዲ/ዳንኤል ክብረት አራቱ ኃያላን በተሰኘ የትርጉም ስራው ውስጥ በኅዳግ ማስታወሻ መልኩ ሲጽፍ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ቤተክርስቲያን ዐፄ ዘርዐያዕቆብን ቅዱስ እንዳለችው ይገልጣሉ፡፡እኔ እስካሁን ባለኝ መረጃ ዐፄ ዘርዐያዕቆብ የክብር እንጂ የቅድስና መዐርግ በቤተክርስቲያን አልተሰጣቸውም፡፡አብዝቶ በሚከበሩበት በደብረ ብርሃን ሥላሴ ያረፉበት ጳጕሜን 3 በቅዳሴ ይታሰባል እንጂ የዘርዐያዕቆብ በዓል ተብሎ አይከበርም፡፡ገድል አልተጻፈላቸውም፤ጽላት አልተቀረጸላቸውም፡፡ነገር ግን ባበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ቦታ አላቸው››(ዳንኤል ክብረት፡ገ.55) ይላል፡፡ዲ/ዳንኤል እንደታዘበው በ333 ዓመታት ቆይታ 4 ቅዱሳን ነገሥታትና አንዲት ቅድስት ንግሥት ካበረከተው የዛጕዌ ስርወ-መንግሥት ጋር ሲነጻጸር በ800 ዓመታት ቆይታው ውስጥ 2 ቅዱሳን ነገሥታት (ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ እና ዐፄ ገላውዴዎስን) ብቻ የተገኙበት ሰሎሞናዊ ስርወ-መንግስት በምግባር ረገድ ደካማ የነበረ በመሆኑ እንደ ዐፄ ዘርዐያዕቆብ ያሉ ቀናዒ ሃይማኖተኞች ሳይቀሩ ዕቁባት በማበጀት ለቅድስና ሳይበቁ ቀርተዋል(ዳንኤል ክብረት፡ገ.80 እና 238)፡፡አክሱማውያንም ከ4ኛው እስከ 6ኛው ክ/ዘ ብቻ በ200 ዓመታት ውስጥ 4ት ቅዱሳን ነገሥታትን አስመዝግበዋል--አብርሃ-አጽብሃ-ካሌብ እና ገብረመስቀል፡፡በተለይ ካሌብ በካቶሊኮችም ኦክቶበር 26 በቅድስና እንደሚታሰቡ ይታወቃል፡፡ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና የሰሎሞናዊ ነገሥታትን ነገር እንቋጭ፡፡የዳንኤል አባባል ከክርስትና ስነ-ምግባር አንጻር ግድፈት የለበትም፡፡ነገር ግን የወቅቱ የሰሎሞናዊ ነገሥታት የምግባር ህጸጽ እና ቅጥ ያጣ ኢ-ክርስቲያናዊ ቅጣት እንዳለ ሆኖ ዘመኑ የሐዲያና የቆላው ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኃይል እየተሰማቸው የሄዱበት ከመሆኑ አንጻር ከአንድ በላይ ሚስት የማበጀቱ ሂደት ከተራ ዝሙት ባለፈ ፖለቲካዊ ትርጉም እንደነበረውም ማስተዋል ይገባል፡፡ለምሳሌ:- የዘርዐያዕቆብ እና የገራድ መሐመድ ልጅ የነበረችውና ኋላ ክርስትና ተነስታ እነ መርጡለማርያም የመሳሰሉ ገዳማትን የሰራችው ንግስት እሌኒ ጋብቻ መንስኤ ከዘርአያዕቆብ ሴሰኝነት ይልቅ ጋብቻው ካነገበው ሰላም የመግዛት ተልእኮ አንጻርም ቢታይ አይከፋም፡፡የሐዲያ ሕዝብ ታሪክ ጸሐፊዎች በዚያ መልኩ ተርጉመው ጽፈውታል (አለባቸው ኬዕሚሶ እና ሳሙኤል ሀንዳሞ፡ገ.23-31)፡፡ይሄም ሆኖ የደቂቀ እስጢፋኖስ ሰቆቃ <<ሃይማኖታዊ ልዩነትን የተመረኮዘ በመሆኑ…›› ብለን በአመክንዮ ብናልፈው እንኳ ንጉሡ በሃይማኖት ህጸጽ የማይታሙትን እንደ አባ ተክለሐዋርያት አይነት ቅዱስ በማሳደዱ በሙት ዓመቱ ከመዘከር በቀር ቅድስና ሊያገኝበት የሚችል እድል እንደማይኖር ግልጽ ነው፡፡ስለዘርዐያዕቆብ የአስተዳደር ዘይቤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በያዝኩት ጽሑፍ ወደፊት በተደጋጋሚ ስለማነሳው በዚሁ ይብቃኝና ወደሌላኛው አንጻር ልሂድ!

  ReplyDelete
 14. 2-- የመፍቀርያነ ደቂቀ እስጢፋኖስ ዕይታ
  !
  በዚህ ጎራ ውስጥ የመደብኳቸው የገድሉን ተርጓሚ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እና በትርጉሙ ገድል ላይ ተንተርሰው ስለ ኢትዮጵያ የምንኵስና ሥርዓት አነስተኛ መጽሐፍ የጻፉትን መምህር ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሄርን ነው፡፡አስቀድሞ 2ቱንም አንጋፋ ጸሐፍት ማመሰገን የተገባ ነው፡፡በተለይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ለተዋጣ ትርጉማቸው፣ምራቅ ለሚያስውጥ ውብ ቋንቋቸው፣ህጸጽ ለሌለበት ጥንቁቅ ኣርትዖታቸው፣የገድሉን በስድ የቀረቡ ጥቅሶች ከየምንጮቻቸው የማቆራኘት ለአረጋዊ ያውም በዊልቼር ለሚረዳ አረጋዊ ቀርቶ በመንፈቀ-ዓመት ላለነው ምሉዐነ-ኃይል ወጣቶች እንኳ የማይሞከር ሥራቸው፣በቁርኝቱም “ገድል” ማለት በቅጡ ያልተረዱት እንደሚሉት “የመበለት ተረት” ሳይሆን በቅዱስ መጽሐፍ ቃል ያሸበረቀ ጥዑም መዓዛ የሞላበት ሕይወት መተረኪያና የምዕመናን ገቢራዊ መማማሪያ መሆኑን በማሳየታቸው፣በመግቢያቸውና በአንዳንድ የኅዳግ ማስተወሻዎቻቸው ላይ ያለኝ መማረር እንዳለ ሆኖ ለጥልቅ ንባባቸውና ለጥንታዊ መዛግብት ስሱነታቸውን ያለኝ ክብር ክንብንብ በማውረድ ብቻ ሳይሆን እንደ ግብረ-ሕማማት አንባቢ አደግድጎ እጅ በመንሳት የሚገለጽ ነው፡፡ክብር አለኝ!ያሰንብታቸው!ይሕን ካልኩ በኋላ ወደ ቅሬታ ያዘነበለውን በዕይታቸው ላይ ያለኝን ሙግት ላንጸባርቅ!

  2.1 ኦ!ፕሮፌሰር! ገለልተኛ ተርጓሚነት የታለች?!

  ፕ/ር ጌታቸው በመግቢያቸው እንዲሁም መምህር ካሕሳይ በመጽሐፋቸው የደቂቀ እስጢፋኖስን እንቅስቃሴ በታላቅ አድናቆት ዘክረውታል፡፡ፕ/ር <> የሚል የፕሮቴስታንት መለያ መርህ ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ገዳማዊ ጽሞና የታከለበት ጥብቅ የምግባር ሥርዓት ጋር ያለው ተቃርኖ፣የሉተር <> የሚል መፈክር 81ዱን ብቻ ሳይሆን ልዩ ልዩ አዋልድ መጻሕፍትንና መንፈሳዊ ትውፊቶችን ሲቀበሉ ከምናያቸው ደቂቀ እስጢፋኖስ ጋር እንደማይስማማ፣<<All believers are priests--አማኝ ሁሉ ካሕን ነው›› በሚል አመጻ ከገዳም አፈንግጦ የወጣው መነኩሴ(ሉተር) ክሕነት ለመቀበል የሲናን በረሃ አቋርጠው እስከ ግብፅና ኢየሩሳሌም ድረስ ሲንከራተቱ ከነበሩት ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያኑ እነ አባ ዕዝራ ጋር ሲነጻጸር ማየት ሕመም አለው፡፡ያሳምመኛል፡፡ይሕ የፕ/ር የተለጠጠ መላምታዊ አቀራረብ ከላይ ካቀረብኳቸው የመፍቀርያነ-ዘርዐያዕቆብ ያላግባብ ደቂቀ እስጢፋኖስን በይሑዲነትና በፕሮቴስታንትነት የመፈረጅ አካሄድ ጋር ተዳምሮ ታሪኩን ላልተገባ ቁንጸላ ዳርጎታል ብዬ አምናለሁ፡፡እሱ ይቆየን!ወደሌላ ርእስ፤ወደሌላ የልዩነት ሐሳብ…

  ReplyDelete
 15. 2.3 እውን ደቂቀ እስጢፋኖስ ተወግዘው አያውቁም?!

  ፕ/ር ጌታቸው በገጽ 25፣መ/ር ካሕሳይ በገጽ 52 ደቂቀ እስጢፋኖስ መንፈሳዊ ሥልጣን ባላቸው ጳጳሳት እንዳልተወገዙና “ተወግዘዋል” የሚለው ዘርዐያዕቆብ ያስጻፈው/ያስተረጎመው ተአምረ ማርያም ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡የውግዘቱ ታሪክ ተአምረ ማርያም ላይ ሲሆን ‹‹በተአምሩ የዘርዐያዕቆብ እጅ ስላለበት ተአማኒነት የለውም፤እነሱ የጻፉት ግን በተአማኒነቱ ጥያቄ ሊነሳበት አይገባም›› ይመስላል አቀራረቡ፡፡እዚህ ላይ መፍቀሬ ደቂቀ እስጢፋኖስ መሆን ዐይን ሳትጋርድ አልቀረችም ብዬ እጠራጠራለሁ፡፡እኔ “ውግዘት ነበረ” ባይ ነኝ!መከራከሪያዬን ላስመዝግብ፡-

  (2.3.1) ገድላቸውን ያነበበ ሁሉ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለእመቤታችን ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም በአማላጅነቷ ማመናቸውን ለማረጋገጥ አይቸግረውም፡፡ለእመቤታችንና ለመስቀል የጸጋ ስግደት ማድረግን በሚመለከት ግን መጀመሪያ አካባቢ በራሳቸው ተነሳሽነት ሲያከናውኑት ማግኘት ከባድ ሲሆን በተለይ በገድለ እስጢፋኖስ ውስጥ አንድም ቦታ ለእመቤታችንና ለመስቀል ሲሰግዱ አናገኛቸውም፡፡ስለመስገዳቸው ማስረጃ ከሌለ ስለመወገዛቸው የሕሊና ግምት ለመውሰድ የሕግ መርህ ይፈቅድልናል፡፡ምክንያቱም የጊዜው ትውፊትና ሕግ ለማርያምና ለመስቀል አለመስገድን ኃጢኣትም ወንጀልም ስለሚያደርግ!

  (2.3.2) በገጽ 146 ለቅ/ማርያም ስገዱ ሲባሉ ‹‹ለልጇ ስንሰግድ እዚያው እናገኛታለን›› የሚል ከቅን ልቦና የራቀ መልስ ሲሰጡ እና በገጽ 155 ስለ እመቤታችን ስዕል ሲጠየቁ ‹‹ጥሩ ነው፤ግን የእጅ ስራ ነው፤ብቻ በልብህ ሳላት›› የሚል ወደ መገዳደር ያጋደለ ምላሽ መስጠታቸውን ስናነብ በመነሻ አቋማቸው ላይ ጥርጣሬ ያድርብናል፡፡በአንድ አጋጣሚ ጳጳሱ ፊት ለውግዘት ቀርበው ሳለም ‹‹ከአሁን በፊት ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ እሰግዳለሁ ሲባል እንጅ ለማርያም እሰግዳለሁ ሲባል አልሰማንም›› የሚል የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ ጳጳሱ ‹‹ለማርያም ባትሰግዱ ስሕተት አይሆንባችሁም፤ብትሰግዱም ኃጢኣት አይሆንባችሁም›› የሚል ማግባቢያ ቃል ነግረዋቸው ‹‹አንተ አባታችን ነህ!በመንፈስ ስትነግረን መልካም ነው፤አባት ሆይ!በፊትም ለማርያም አንሰግድም ያልነው አቃልለን አይደለም›› ብለው አምነው ከጳጳሱ ጋር ለእመቤታችን እንደሰገዱ በገድለ አበው ወአኃው ተጠቅሷል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.149)፡፡ይሕን የደቂቀ እስጢፋኖስ ድርጊትና ክርክራቸውን ስናጤን ከዚያ ቀን በፊት በነበረ ሕይወታቸው ‹‹ለማርያም መስገድ አይገባም›› በሚል አስተምህሮ ይጓዙ እንደነበር መጠርጠር አይከብድም፡፡እንዲያ ከተጓዙ ደግሞ እነሱ ለእመቤታችን እጅ እንዲነሱ ለማግባባት ሲጥሩ የምናያቸው ጳጳስ በቁርጡ ሰዓት መስቀላቸውን ለውግዘት ማንሳታቸው አይቀሬ ነው ብለን መላ እንመታለን፡፡ይሕን መላ ምት የሚያጠናከር ንባብ እንይ!

  (2.3.3) እላይ ከተጠቀሰው ገጽ ወረድ ብለን ስናነብ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከአቡነ ገብርኤል ውግዘት ያመለጡበት አጋጣሚ ጳጳሱ ‹‹እነዚህን ቅዱሳን የማወግዝበት ምክንያት አላገኘሁባቸውም፡፡ሃይማኖታቸው የቀናች ሥርዓታቸውም መልካም ነው፡፡ማርያምን ያምናሉ፤ይሰግዱላታልም›› የሚል ምላሽ ለዘርዐያዕቆብ በመስጠቱ ነው (ዝኒ ከማሁ፡ገ.151)፡፡ይሕ ከሆነ ለእመቤታችን ባይሰግዱ ኖሮ ይወገዙ ነበር፤እነሱ ባይነግሩንም አንሰግድም ባሉባቸው የቀደሙ ጊዜያት ውጉዛን የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው፡፡አሁንም ዝቅ እንበል!

  (2.3.4) ደቂቀ እስጢፋኖስ ውግዘት እንደተላለፈባቸው ይጠቁሙንና አውጋዣቸው ግን ጳጳሱ ሳይሆን ደብረወርቅ የተባለ የጳጳሱ ሎሌ (ምን አልባት አስተርጓሚው?) የጳጳሱን እጅ ይዞ ወደላይ በማንሳት ‹‹እነዚህን መነኵሴዎች ክህነታቸውንም፣ምንኵስናቸውንም አግደናል፡፡በእንጀራም በውሃም አትቀበሏቸው፤የሚቀበላቸው የተወገዘ ይሑን›› ስለማለቱ ይገልጻሉ፡፡ሆኖም የጳጳሱ ሎሌ ደብረወርቅ እንጂ ጳጳሱ ‹‹እኔ እንደዚህ አላልኩም፤አላወገዝኩም›› እንዳለ በመግለጽ መከላከያ ያበጃሉ (ዝኒ ከማሁ፡ገ.153)፡፡መቼም እነሱ በገድላቸው ቃል በቃል ‹‹ተሳስተን ተውግዘን ነበር›› እንዲሉ አንጠብቅም፡፡ያሉትን ፍንጮች ተከትለን ማሰሳችንን ግን እንቀጥል!

  (2.3.5) የደቂቀ እስጢፋኖስ ተከታይ የሆነው ብልሁና ጠቢቡ አባ ዕዝራ የእስጢፋኖሳውያን ልዑካን ተሳላሚዎችን እየመራ ቅድስት ሐገር ኢየሩሳሌምን ለመሳለም ሄዶ ነበር፡፡በኢየሩሳሌም የነበሩ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ደቂቀ እስጢፋኖስ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ክስ ያቀርቡባቸዋል፡፡የክሱ ይዘት፡- ‹በሥላሴ አያምኑም፣ለማርያም አይሰግዱም፣ለመስቀልም አይሰግዱም፣ታቦት የላቸውም፣ቁርባን አይቆርቡም፣አቡነ ዘበሰማያትና ጸሎተ ሃይማኖት አይደግሙም፣የኢትዮጵያ ንጉሥ ይገድላቸዋል፣ጳጳሱ ያወግዛቸዋል፣ሕጋቸው እንደ ሕጋችን አይደለም፣አረማውያን ናቸው› የሚል በጥቅሉ ስንቆጥረው 10 የክስ አርእስት ነው(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.289፣ካሕሳይ፡ገ.70)፡፡አባ ዕዝራ ለነዚህ ክሶች አንድ በአንድ መከላከያውን ዘርዝሮ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን በክሱ እንደተገለጸው እንዳልሆኑ ሞግቷል፡፡‹‹ጳጳሱ ያወግዛቸዋል›› ለሚለው ክስ ግን ምላሽ አልሰጠም፡፡አለፋት፡፡በሕግ ቋንቋ እንዲህ እንላለን <>. የአባ ዕዝራን ለውግዘት ክስ መልስ ሳይሰጥ ማለፍ እንዲያ ተረጎምኳት፡፡ውግዘቱን ስላልካደ አምኗል!ያም ሆኖ ፍለጋችን በዚህ አይቆምም!

  ReplyDelete
 16. 2.3.6) አባ ዕዝራ በአጼ ናዖድ (1488-1500) ጊዜ በነበሩት ግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ይስሐቅ ፊት ቀርቦ ሲናገር ‹‹….እንዳይካኑ ጳጳስ አውግዟቸዋል ይሉናል፡፡እኛም በዚህ ጉዳይ ለሁለት ተከፍለናል፤አንዳንዱ ክፍል ነፍስ ስላስገደለ ከሱ [ደቂቀ እስጢፋኖስ ሲሰቃዩና ሲገደሉ ካልተቃወመው ግብጻዊ ጳጳስ] እጅ ክሕነት አንቀበልም ይላሉ፡፡አንዳንዱ ከ81ዱ የሕግ መጻሕፍት አልወጣንም፣አባቶቻችን ከሐዋርያትና ከተከተሏቸው ሊቃውንት የተለየ ትምህርት አላመጣንም፤ስለዚህ ግዝቱ አይነካንም ይላል፡፡አንዳንዱ ደግሞ ግዝት አንጥስም፣ክሕነት አንቀበልም፤ምክንያቱም ሳያጣራ እንዳስገደለን ራሱ ያውቃል››በሚል ለሁለት መከፈላቸውን ገልጾ እሱ ግን ‹‹ክሕነት እንቀበል›› ከሚሉት ወገን እንደሆነ ያስረዳል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.296)፡፡ይችን የቃል ልውውጥ እያየን የቀደመ ውግዘት አልነበረም ማለት ያዳግተናል፡፡ጉዟችን ግን አንድ እርምጃ ይቀጥል!

  (2.3.7) ጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ አባ ዕዝራን ‹‹ይኸንን ሃይማኖት›› ይዞ እስካሁን ሳይናገር ስለመዘግየቱ ጠይቆት አባ ዕዝራ በሚደርስባቸው መሳደድ ሊመጣ እንዳልቻለ ይገልጽለታል፡፡በመቀጠልም ለጳጳሱ ‹‹ሥልጣን ስላለህ የሞቱትንም በሕይወት ያሉትንም ግዛት ፍታ›› ይለዋል፡፡በተጠየቀው መሰረት አቡነ ይስሐቅ 4 ምስክሮችን አቁሞ ‹‹በጠዋት ያሰርኩትን በምሽት እፈታለሁ፤በምሽት ያሰርኩትን በጠዋት እፈታለሁ፤አሁንም በሥሉስ ቅዱስ አፍ የተፈቱ ይሑኑ፡፡የማርያምና የመስቀል ፍቅር ያለባችሁ ዛሬ ጥር 21 ቀን የማርያም በዓል ነው፡፡ለኔም ለእናንተም ምስክር ትሁነን…›› ሲል ግዝቱን በይፋ ይፈታል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.297)፡፡እናስተውል!አቡነ ይስሐቅ ግዝት የፈታው በሕይወት ላሉት ብቻ አይደለም፤የተጠየቀውም በሕይወት ላሉት ብቻ አይደለም፤በሕይወት ለሌሉትም ጭምር እንጂ፡፡ከላይ እንደተጠቀሰው ደቂቀ እስጢፋኖስ እርስ በርሳቸው የጳጳሱ ‹‹ግዝት አይነካንም›› በሚሉና ‹‹ግዝቱን አንጥስም›› በሚል ለሁለት መከፈላቸውን በራሳቸው አንደበት ገልጸዋል፡፡ይሕ ክፍፍል ከገጽ 394-396 በሰፊው እንደተተረከው አባ ዕዝራ ለእመቤታችንና ለመስቀል ሊደረግ ስለሚገባው ሰጊድ በቃሉ በዓደባባይ መስክሮ፣በተግባርም ለስዕለ-ማርያምና ለመስቀል ሰግዶ ግዝቱን ሲያስፈታ ተቋጨ፡፡ከዚያ ወዲያ ንጉሥ ናዖድ ‹‹እኔም ትቻለሁ፤የደቂቀ እስጢፋኖስን ደም ከማፍሰስ አልጨመርም›› ሲል የጳጳሱን ግዝት መፍታት በዐዋጅ አጸናው(ዝኒ ከማሁ፡ገ.301)፡፡አጼ ዘርዐያዕቆብ ከነገሠበት ከ1426 ዓ.ም አካባቢ የጀመረው የደቂቀ እስጢፋኖስና የነገሥታቱ ፍጥጫ ልክ ስምንተኛው ሺህ ገባበት የተባለው 1500 ዓ.ም ከመድረሱ በፊት ባረፉት አጼ ናዖድ ዘመን ከ76 ዓመታት መለያየትና ሰቆቃ በኋላ ተቋጨ፡፡ጠቢቡ አባ ዕዝራ ሰላም አወረደ፡፡አባ እስጢፋኖስን አልተሳደበም፡፡ከእስጢፋኖስ የተማርኩት ትምህርት ኑፋቄ አለበትም አላለም፡፡ዝም!የተጠየቀውን ለመስቀልና ለእመቤታችን የሚገባ የጸጋ ሰጊድ ሥርዓት ግን በቅጡ መጽሐፍ ጠቅሶ ተናገረ፡፡የተናረገረውን አደረገ፡፡ሰላም ሆነ!ነፍሱ ሰላም ትሁን!

  (2.3.8) ይቺን ንዑስ ርእስ እኔም እንደ መምህር ካሕሳይ ለአባ ዕዝራ ያለኝን አክብሮት ለማዘከር የገድሉ ጸሐፊ ስለ አባ ዕዝራ ቀብር ጽፎ ሲጨርስ በገጽ 314 ባሳረገበት መንገድ ላሳርጋት፡፡‹‹ዐጽሙን በሳጥን አስቀመጡት፤ማኅሌት አድርገው በማዕጠንት ዐጠኑት፤መብራት አበሩ፤ወንጌሎችንም አነበቡ፤የሚገባውን ሥርዓት ሁሉ ፈጸሙ፡፡በዕብራውያን ሐሳብ(አቆጣጠር) በታሙዝ 11 ቀን፣በግእዝ በሐምሌ 21 ቀን በማርያም በዓል ዕለት በሕይወቱ በተመኘበት መቃብር ቀበሩት፡፡የማኅበሩ አገልጋይ የአቡነ ዕዝራ ጸሎትና የብርሃን እናት የእመቤታችን ጸሎት ከኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር፤አሜን፣አሜን፤ይሁን፣ይሁን፡፡››(ካሕሳይ፡ገ.75)፡፡አባ ዕዝራን ብቻ አወድሰን አጼ ናዖድን መዘንጋት ደግ አይደለም፡፡ስለ አጼ ናዖድ ይልማ ዴሬሳ የጻፉት ለዚህ ሰላማዊ ውሳኔው መገለጫ መሆን ይችላል፡፡እሳቸው ‹‹አጼ ናዖድ ታላቅ ገዢ ከመሆኑ ሌላ ፍርድም አዋቂ ነበር፡፡በዐደባባይ ፍርድ ማየት ብቻ ሳይሆን፤ለእያንዳንዱ ሰው በዕለት ስራው መጠንና ሚዛን ያለው አስተያየት የሚሰጥ ንጉሥ ነበር›› ይሉታል (ይልማ ዴሬሳ፡ገ.11)፡፡የንጉሣችንን አጼ ናዖድ ነፍስ ጌታ በለምለሙ ቦታ ያሳርፋት!ወደሌላ ቅሬታ ልሻገር፡፡

  ReplyDelete
 17. 2.4 እውን ለእመቤታችን የጸጋ ስግደት መስገድ የተጀመረው ከዘርዐያዕቆብ ወዲህ ነው?!

  ፕ/ር ጌታቸው እና የፕሮፌሰሩን መደምደሚያ እንዳለ እየተቀበሉ የተረኩት መ/ር ካሕሳይ የደቂቀ እስጢፋኖስን በመነሻ ወቅት ‹‹ለማርያምና ለመስቀል አንሰግድም›› የሚል ሃይማኖታዊ አመጻ ለማጽደቅ በሚያስመስል መልኩ ‹‹እሰግድ ለኪ <እሰግድልሻለሁ› የሚለውን ተአምረ ማርያም ውስጥ ያለ ጸሎት ያመጣው አጼ ዘርዐያዕቆብ ነው›› ይሉናል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.149፣የኅዳግ ማስታወሻ (foot note) ቁ.107፡፡ካሕሳይ፡ገ.51)፡፡አረጋውያኑ አልተችለውም!እኔ ግን መንፈራገጤን ልቀጥል!‹‹እሰግድ ለኪ››ለምትለዋ ቃልና ለተያያዥ የጸጋ ስግደቶች ከዘርዐያዕቆብ የቀደመ ትውፊታዊ ማስረጃ ላስስ!

  (2.4.1) ‹‹በሰጊድ ሰላም ለኵሎን መልክኣትኪ ማርያም›› ወይም ‹‹እሰግድ ለኪ ከመ-ኃጢኣትየ ታስተስርዪ…ለኃጢኣቴ ይቅርታን ታሰጪኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ›› የሚሉት ከንጉሥ ዘርዐያዕቆብ የ1426 ዓ.ም ንግስና ቀድመው በ1417 ዓ.ም ባረፉት አባ ጊዘዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ-ሰዓታት ውስጥ ‹‹ስብሐተ-ፍቁር ዘማርያም›› ተሰኝተው የተካተቱ መዝሙራት ናቸው፡፡

  (2.4.2) ለእመቤታችንና ለመስቀል፣ለቤ/ክ እና ለቅዱሳት መካናት ስለሚገባ የጸጋ ስግደት ቅዱስ ያሬድም አዚሞልናል፡፡ስለእመቤታችን ሰጊድ ‹‹ኵሎሙ ነገሥተ-ምድር ይሰግዱ ለኪ፣ወይልሕሱ ጸበለ-እግርኪ፣ማርያም እምነ፣ወእሙ ለእግዚእነ...[ትርጉም]…የጌታችን እናት የኛም እናታችን ማርያም፣የምድር ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱልሻል፣የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ…››ይላታል (ድጓ ዘነሐሴ ኪዳነ ምሕረት፡ገ.382)፡፡አንድ እንጨምር--ስለ እመቤታችን ሰጊድ!በድጓው ሰፍሮ ለታሕሳስ በዓታ ‹‹እስመለዓለም›› ብለን በዜማና በአቋቋም የምንዘምራት ጥዑም ዜማ እንዲህ ትላለች ‹‹በጽሐ ሠናይ ወአልጸቀ ዘመን፣ወበዓላ ለቅድስት ማርያም፣እንተ-በላዕሌሃ ተመርአወ ቃል፣…ዳዊትኒ ይቤላ በአልባሰ-ወርቅ፣ዑፅፍት ወኁብርት፣ይሰግዱ ለኪ ኵሎሙ ነገሥታተ-ምድር፣ወይልሕሱ ጸበለ-እግርኪ…[ትርጉም]…የበጎነት [ጊዜ] ደረሰ፤ዘመኑ መጣ፣ቃል (ወልድ) የተሞሸረባት የቅድስት ድንግል ማያም በዓልም(እንዲሁ ደረሰ)፣…ዳዊት ይላታል፡- (አንች!) ‹በወርቅ አልባሳት የተጌጥሽና የተሸለምሽ፣የምድር ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱልሻል››› ሲል ቅ/ያሬድ በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 44 ቁ 12-13 ላይ ያለውን ኃይለ-ቃል ለእመቤታችን ሰጥቶ ተርጕሞ አቅርቦልናል(ድጓ ዘነሐሴ ኪዳነ ምሕረት፡ገ.384)፡፡ስለመስቀልም፡- ‹‹በሰማይ ፀሐየ አርአየ፣ወበምድር ዕፀ-መስቀል ተረክበ፣ከመ-ይሳለምዎ እምሰማያት ወረደ…[ትርጉም]…በሰማይ ፀሐይን ገለጠ፣በምድርም መስቀል ተገኘ፣ይሳለሙት ዘንድ ወረደ›› ይላል (ድጓ ዘመስቀል፡ገ.111)፡፡‹‹ለመስቀልከ ንሰግድ››ን በኋላ እናምጣት፡፡ቤ/ክ ስለመሳለም፡- ‹‹በሰላም ንጊሣ ለቤተክርስቲያን፣ወበሰላም ንቁም ቅድሜሃ፣ነአምኀ ንበላ በሀ፣ምስትስራየ-ኃጢኣት ይዕቲ፣ቅድስት ደብተራ…[ትርጉም]…(ወደ) ቤተክርስቲያንን በሰላም እንገስግስ፣በፀጥታ ከደጇ እንቁም፣እጅ እንንሳት፤ሰላም(ለኪ) እንበላት፣የኃጢኣት ማስተስረያ፣ቅድስት ድንኳን(ደብተራ) ናት›› (ጾመ ድጓ ዘገብርኄር ሐሙስ፤ገ.136)፡፡ቅድስት ሀገር ሄዶ ጎልጎታን ስለመሳለም፡- ‹‹ወአንቲኒ ቀራንዮ፣መካነ-ጎልጎታ፣እስመ-በኀቤኪ ተሰቅለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ህየ!ህየ!ህየ!ንሰግድ ኵልነ፣ኀበ-ቆመ እግረ-እግዚእነ…[ትርጉም]…አንቺ ቀራንዮ፣የጎልጎታ ምድር፣ክርስቶስ በላይሽ ተሰቅሏልና፣የጌታ እግር በቆመበት፣በ(ዚያ) ስፍራሽ!በስፍራሽ!በስፍራሽ!ሁላችን እንሰግዳለን›› ይላል ሊቁ መዝሙር 131 ቁ 7 ወለል ብሎ እየታየው(ድጓ ዘእሌኒ፡ገ.28)፡፡ለመስቀሉ እንኳን ሰው ጢስም ሰግዷል፡፡ቅ/ያሬድ ይቀጥል!‹‹ዘእጣን አንጸረ ሰገደ ጢስ፣ወተረክበ በኀሢሥ፣መስቀል ቅዱስ…[ትርጉም]…እጣን አመላከተ(አነጣጠረ)፤ጢስ ሰገደ(ለት)፣በፍለጋ ተገኘ፣ቅዱስ መስቀል›› (ዝኒ ከማሁ፡ገ.28)፡፡እነዚህ ማሳያዎች ‹‹ለአብ ወልድ መንፈስቅዱስ ካልሆነ በቀር ሰጊድ የለም›› የሚለውን የ‹‹አምልኮ›› እና የ‹‹ጸጋ›› ስግደት ያቀላቀለ አቋም ይሞግታሉ፡፡

  (2.4.3) አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ‹‹በሥዕል ፊት ቁሞ መጸለይ ከባለ ሥዕሉ ረድኤት በረከት ምልጃ መለመን መማጠን ነው፡፡ ለሥዕል መስገድ ሥዕልን መሳም ደግሞ በፊት የሥዕል ተዋጊዎች ወይም ጸረ ሥዕሎች (ኢኮኖሚኺ) እንደሚሉት ዛሬም ብዙ ጸረ ማርያሞች እንደሚያጥላሉት ለጣኦት መስገድ ጣዖት መሳም አይደለም፡፡…በሥዕሉ አማካይነት ለሥዕሉ ባለቤት ክብርንና ፍቅርን ለመግለጽ ነው፡፡ይኸውም የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ጥንታዊ ትውፊት ነው፡፡ (Tradition) ነው፡፡ በእምነትና በፍቅር የሆነ ነገር ደግሞ ያንፃል እንጂ አይንድም፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት የሚወርሰው በፍጹም እምነት ቅንነት በተሞላበት ፍቅርና ትሕትና እንጂ በተጥባበ ነገር (Rationalism) አይደለምና›› ይላሉ ሶርያዊውን የ8ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የቤ/ክ ሊቅ ዮሐንስ ዘደማስቆን ጠቅሰው(አቡነ ጎርጎርዮስ፡ገ.99)፡፡የእሳቸውን ጥቆማ ተቀብለን ዮሐንስ ዘደማስቆን እንፈልገው!

  ReplyDelete
 18. (2.4.4) ምስጋና ለጎግል ይሑንና በ8ኛው ክ/ዘ የገነነውን ዮሐንስ ዘደማስቆን [St. John of Damascus (675-745)] አገኘነው፡፡ዋይ!ዋይ!እሱ ትንታግ ነው!አጽሙን ያለምልም!ጥሜን ቆረጠልኝ!ከንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ንግስና 700 ዓመታት ገደማ ቀድሞ የተነሳው ሶርያዊ ሊቅ ሰጊድን በሁለት ከፍሎ ሲተነትን፡-

  Worship is the symbol of veneration and of honour. Let us understand that there are different degrees of worship. First of all the worship of latreia, which we show to God, who alone by nature is worthy of worship. When, for the sake of God who is worshipful by nature, we honour His saints and servants, as Josue and Daniel worshipped an angel, and David His holy places, when be says, "Let us go to the place where His feet have stood." (Ps. 132.7) Again, in His tabernacles, as when all the people of Israel adored in the tent, and standing round the temple in Jerusalem, fixing their gaze upon it from all sides, and worshipping from that day to this, or in the rulers established by Him, as Jacob rendered homage to Esau, his elder brother, (Gen. 33.3) and to Pharaoh, the divinely established ruler. (Gen. 47.7) Joseph was worshipped by his brothers. (Gen. 50.18) I am aware that worship was based on honour, as in the case of Abraham and the sons of Emmor.

  ይላል፡፡ ሁለቱ ቃላት ይሰመርባቸው! <> እና <> የሚሉ አገላለጾች በኢኦተቤክ ‹‹የአምልኮ ስግደት›› እና ‹‹የጸጋ ስግደት›› በሚል ይታወቃሉ፡፡ሊቁ አመክንዮ ይደረድራል፡፡‹‹ለመጽሐፍ አንባብያን ፊደሉ፣ለማያነቡ ስእሉ፤ቃሉን ይነግራቸዋል፡፡ቃል ለጆሮ፣ስእል ለዐይን ይናገራሉ›› ይላል ታቦትን ማንጸሪያ አድርጎ፡፡በራሱ አንደበት፡-

  We proclaim Him also by our senses on all sides, and we sanctify the noblest sense, which is that of sight.The image is a memorial, just what words are to a listening ear.What a book is to the literate,that an image is to the illiterate.The image speaks to the sight as words to the ear; it brings us understanding. Hence God ordered the ark to be made of imperishable wood, and to be gilded outside and in, and the tablets to be put in it, and the staff and the golden urn containing the manna, for a remembrance of the past and a type of the future. Who can say these were not images and far-sounding heralds? And they did not hang on the walls of the tabernacle; but in sight of all the people who looked towards them, they were brought forward for the worship and adoration of God, who made use of them. It is evident that they were not worshipped for themselves, but that the people were led through them to remember past signs, and to worship the God of wonders. They were images to serve as recollections, not divine, but leading to divine things by divine power. (Apologia of St John of Damascus Against
  Those who Decry Holy Images:p.7)

  (2.4.5) አቡነ ጎርጎርዮስ እንደሚሉት ከ787 ዓ.ም የ2ኛው ኒቅያ ጉባኤ በኋላ በካቶሊክ፣በምስራቅ ኦርቶዶክስና በኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት ስዕል የጸጋ ስግደት ይደረግለታል፡፡ለእመቤታችን ስዕል፣ክብርና አማላጅነት ደግሞ ሁሉም ከፍ ያለ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ለእመቤታችን ብቻ ሳይሆን ለመስቀልም <> እያሉ እንደሚዘምሩ አነበብን፡፡በተመሳሳይ ይዘትና ድምጸት ቅ/ያሬድ በስቅለት ጾመ-ድጓ ከጌታ ስዕለ-ስቅለት ስር ሆነን እንድንዘምር ስርዓት ሰርቶ ‹‹ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፣ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኵልነ፣ይዕዜኒ ወዘልፈኒ…[ትርጉም]…መምህራችን ሆይ!ለመስቀልህ እንሰግዳለን፣ቅድስት ትንሣኤህን እናወድሳለን፣ዛሬም ዘወትርም›› የሚል ቃል አኑሮልናል (ጾመ-ድጓ፡ገ.176)፡፡

  ReplyDelete

 19. (2.4.6) የሚያሳዝነው በአንድ በኩል በአበው ወአኃው፣በአባ አበከረዙን እና በአባ ዕዝራ ገድላት ውስጥ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለንጉሡ መስገድንና መምህራቸው እስጢፋኖስን መስደብን እምቢ ብለው አያሌ መስዋዕትነት መክፈላቸው እየተነገረ በሌላ በኩል ለማርያምና ለመስቀል መስገድን እየተቀበሉ መሄዳቸው በገድላቸው ተርጓሚ ‹‹የአባትን ፈለግ እንደመተው›› እንጂ ‹‹ወደ ትክክለኛው መንገድ እንደመመለስ›› ሊቆጠርላቸው አልቻለም፡፡ፕ/ር ጌታቸው ‹‹ለቅድስት ማርያም ስዕልና ለክርስቶስ መስቀል አንሰግድም ማለታቸውንም ቢሆን…የኋለኞቹ ልጆች ትተውታል›› ሲሉ ሂደቱን የ‹‹መመለስ›› ሳይሆን የ‹‹መተው›› አድርገው አቅርበውታል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.31)፡፡

  (2.4.7) እስኪ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለእመቤታችንና ለመስቀል ሰጊድ የፈጸሙባቸውን አጋጣሚዎች እንጥቀስ፡፡በገጽ 151 ማርያምን እንደሚያምኑ እና እንደሚሰግዱላት ተጽፏል፡፡በአባ አበከረዙን ገድል ውስጥ ገጽ 232 ቤ/ክ ሲሳለሙና አበምኔት እጅ ሲነሱ እናገኛቸዋለን፡፡በገጽ 286፣294 እና 295 አባ ዕዝራ ለማርያምና ለመስቀል እሱ ብቻ ሳይሆን መምህሮቹም እንደሚሰግዱ ተናግሯል፤ለንግግሩም ከላይ የቀረቡትን መዝ 131 ቁ 7፣ኢሳ 49 ቁ 23 እና የቅ/ያሬድ መዝሙራት ይጠቅሳል፤ጥቅሱን በተግባር አሳይቶ ግዝቱን አስፈትቷል፡፡ይሕ የአባ ዕዝራ ድርጊት ከጫና እና ሰቆቃ ብዛት የመጣ ነው ይባል ይሆናል፡፡ነገር ግን ከላይ በተጠቀሱት ለእመቤታችንና ለመስቀል በሰገዱባቸው ጊዜያት ሁሉ ‹‹ለንጉሡ ስገዱ፤መምህራችሁን ስደቡ›› ሲባሉ ፈቃደኛ ባለመሆን መራር ሰቆቃዎችን ስለመቀበላቸው አንብበናል፡፡በመሆኑም በበኩሌ የነ አባ ዕዝራን የሰጊድ ድርጊት ፕ/ር ጌታቸው እንደሚሉት የቀደመ አባታቸውን መንገድ የ‹‹መተው›› አድርጎ ከማየት ይልቅ ከቀደመ ‹‹ስህተት›› የመመለስ አድርጌ መቀበልን እመርጣለሁ፡፡

  2.5 በመቅድመ ተአምረ ማርያም ዙሪያ…ፕ/ር ጌታቸው ከየት አምጥተው አገናኙት?!

  ፕ/ር ጌታቸው ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ተአምረ ማርያምን ከዐረቢኛ አስተርጉሞ በሀገር ውስጥ የተፈጸሙ ተአምራትን አካቶ ለየገዳማቱ መላኩ አንድ የጭቅጭቅ ምንጭ እንደሆነ ይገልጻሉ(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.25)፡፡በተለይ ‹‹ፍጥረት ሁሉ ስለእመቤታችን ተፈጠረ፣አዳምና ሔዋን ስለእመቤታችን ተፈጠሩ፣ቁርባን መቁረብ ያልቻለ ተአምሯን ሰምቶ ይሂድ፤እንደቆረበ ይቆጠርለታል›› የሚሉ ንባቦችና ‹‹የበላዔሰብእ ታሪክ›› በየገዳማቱ አበምኔቶች ዘንድ ተአምሩን ለመቀበል አስጨናቂ አድርጎት እንደነበር ጽፈዋል፡፡ይሁን እንጂ ደቂቀ እስጢፋኖስ እና ዘርዐያዕቆብ በእነዚህ ምንባባት ስለመጋጨታቸው ከፕ/ር መላምት ውጭ በተረጎሙት ገድል ውስጥ ተጽፎ አናገኝም፡፡ተአምረ ማርያም በገድሉ ገጽ 128 ብቅ ብሎ እናየዋለን፡፡ሆኖም ያን ያህል የውዝግብ ምንጭ ሆኖ አይደለም፡፡የተነሳበት ጥያቄ ሁለት ነው፡- <> የሚልና ለመጽሐፈ-ተአምረ-ማርያም ጉዳይ፡፡የእጅ መንሳት ጥያቄውን ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ወገን የሆነው መነኵሴ ለተአምሩ እጅ በመንሳቱ ሲቋጭ እናገኘዋለን፡፡የተአምረ-ማርያም ንባብ እንደ ቅዱስ ወንጌል፣ግብረ-ሐዋርያት፣መልእክተ-ጳውሎስና ሌሎች የሐዋርያት መልእክታት በቅዳሴ መካከል ሳይሆን ከቅዳሴ ውጭ የሚነበብና የሚሰማ ተደርጎ ሥርዓት በመሰራቱ የንባቡ ሰዓት ለዘለቃው ያጨቃጨቀ አይመስለኝም፡፡ከዚህ ውጭ ተአምረ-ማርያም በደቂቀ እስጢፋኖስና በንጉሥ ዘርዐያዕቆብ መካከል ያለመግባባት ምንጭ ስለመሆኑ በገድሉ ውስጥ አልሰፈረም፡፡ርእሰ-ጉዳዩ ከተነሳ ዘንድ ግን ጥቂት ልናገር!

  ReplyDelete
 20. (2.5.1) መቅድመ-ተአምረ-ማርያምን በሚመለከት በየጉባኤ ቤቱ ጥያቄዎች እንደሚነሱ መካድ የለበትም--ቢያንስ እኔ ስማር ጥያቄውን የሚያነሱ የመጽሐፍ ተማሪዎች አይቻለሁ፡፡በአንድ በኩል ከላይ ፕ/ር ያለቦታቸው ከደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ ጋር ያያዟቸውን ጥያቄዎች እያነሱ መቅድሙ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ለነቀፋ የሚዳርጉ ምንባባት ይዟል የሚሉ አሉ፡፡ምክንያቶቻቸውም፡- የተጠቀሱት ምንባባት ይዘት ከመጻሕፍትና ከቀደመው ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት አይጣጣምም፣በምንም የማይተካውን ስጋ-ወልደ-እግዚአብሔር ተአምር በመስማት የሚፈጸም በማስመሰል ምስጢረ-ቁርባንን ያቃልላል፣የበላዔሰብእ ታሪክም ኃጢኣትንና ኃጢኣተኞችን በማበረታታት አማንያንን ንዝህላል ያደርጋል፣ምንባባቱና ታሪኩ ተአምረ ማርያም መጀመሪያ በተጻፈባት የግብፅ ቤተክርስቲያን የማይገኙ እና እዚሁ የተጨመሩ ስርዋጾች ናቸው የሚሉ ናቸው፡፡መ/ር ካሕሳይም ይኸንኑ የትችት ሀሳብ አንጸባርቀዋል(ካሕሳይ፡ገ.49)፡፡

  (2.5.2) በሌላ በኩል የነቢዩ ኤርምያስ ከእናት ማኅፀን ጀምሮ መመረጥ ሊኖር እንደሚችል የሚያሳይ ጥቅስ (ኤር.1 ቁ 5)፣የቅ/ያሬድ ‹‹ማርያምሰ ተሐቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዐዳ...[ትርጉም]…ማርያም በአዳም ሆድ(ዘር) ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር›› የሚሉ እንዲሁም ‹‹ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር፤ወዘእንበለ ይሣረር ምድረ ገነት፤ሀለወት ስብሕት ቅድስት ወቡርክት ይዕቲ ማርያም….[ትርጉም]…ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ፣የገነት ምድር ሳትመሰረት፣የተመሰገነች፣የተለየች(የተቀደሰች)፣የተባረከች ማርያም ነበረች›› የሚሉ(ድጓ ገ.389) ዜማዎች ስላሉ በተአምሩ መቅድም የሰፈረው ሐሳብ አዲስ አይደለም፤‹‹አጣሞ›› ሳይሆን ‹‹አጣጥሞ›› የሚተረጉም እስካለ ድረስ ነባሩን ንባብ መነካካት አያስፈልግም፤በትርጕም ይቃናል የሚሉ አሉ፡፡ቁርባንን በሚመለከት ‹‹ተአምር ቁርባንን ይተካል›› አልተባለም፤‹‹እንደ›› በሚል ህጹጽ ማንጸሪያ መቁረብ ላልቻሉ ማጽናኛ ነው የተቀመጠው የሚል አተያይ አለ፡፡አተያዩ ሲቀጥል፡- የመቅድሙ ዐላማ ከጸሎተ-ቅዳሴ በኋላ ምዕመናን ተአምሯን ሳይሰሙ እንዳይሄዱ ማድረግ ነው፤ተአምር መስማት ቁርባን ይተካል ተብሎ ቢታሰብማ ከቅዳሴ ውጭ ሳይሆን ከቅዳሴ በፊት ወይም በቅዳሴ መካከል በመስዋዕት ማሳረጊያነት ይነበብ ነበር፤በዚያው ላይ ጥያቄውን የሚገፉት ብዙ ጊዜ በምስጢረ-ቁርባን የማያምኑ ቀሳጥያን ስለሆኑ ዐላማቸው በሰበቡ መላውን ተአምር ማነወር እንጂ ችግራቸው ከመቅድሙ ብቻ ስላልሆነ ከንቱ ላይመለሱ እነሱን ሰምቶ መጽሐፉን መነካካት አያስፈልግም፤የተሐድሶ ባቡራቸው የነገረ-ሃይማኖት መቆሚያ ፌርማታ ስለሌለው ለእነሱ መንገድ አንከፍትም ይላል፡፡የበላዔሰብእ ታሪክ የእመቤታችንን አማላጅነት የወንበዴ ዋሻ ያደርጋል ስለተባለው የሃይማኖት ህጸጽ እንጅ የምግባር ህጸጽ በቅዱሳን አማላጅነት አምኖ ለተማጸንና ቀዝቃዛ ውሃ ላጠጣ ይቅር ስለሚባል(ማቴ 10 ቁ 42)፣ጌታ ከብዙዎች ጻድቃን ይልቅ በአንድ ኃጥዕ መመለስ ደስ ስለሚሰኝ፣በተባለው መልኩ የእመቤታችንን አማላጅነት ማቃለል ጌታን ከመፀብሐን (ቀራጮች) ጋር ካመሳሰሉት ወገኖች (ማቴ 9 ቁ 11)፣ወይም ዘኬዎስ ቤት ገባ ብለው እንዳሙት ሐሜተኞች(ሉቃ 19 ቁ 1)፣ወይም የማርያም መግደላዊትን ሽቱ በመቀባቱ ከዘማውያን ጋር ዋለ(ሉቃ 7 ቁ 38) ብለው እንዳሙት ተጠራጣሪዎች እንደሚያስቆጥር ቀደምት ሊቃውንት ጽፈዋል(መ/ብ አድማሱ ጀንበሬ፡ገ.161)፡፡አሁን ባለው ሁኔታ ጥሬ ንባቡ ላይ ከማተኮር ይልቅ የመቅድሙን ቃላት በማቃናት የሚተረጉመው የኋለኛው አስተሳሰብ ገዥ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

  (2.5.3)ተአምረ ማርያም ከተነሳ በየገዳማት እና አድባራቱ ውስጥ ባሉ የተአምረ ማርያም መጻሕፍት ውስጥ በተአምር ቁጥር መብዛትና ማነስ የተወሰነ ልዩነት እንዳለ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ኅትመቱ ብዙ ጊዜ በግለሰብ ነጋዴዎች ስለሚከናወን አንዳንድ የቅርብ ዘመን ታሪኮች ሳይቀር እየተካተቱበት መታተሙ ዶግማና ቀኖናንን ከማስጠበቅ አንጻር ተገቢ አይመስለኝም፡፡እነዚህ ነጋዴዎች የሚያሳትሙት ትልቁ ተአምረ ማርያም የአጼ ምኒልክንና የአጼ ቴዎድሮስን ታሪክ በተአምሩ ውስጥ አካቶ መጻፉ ብዙዎቻችንን ያሳዘነ ነው፡፡በራዕየ-ማርያም ባለስርዋጽ ኅትመት ቤተክርስቲያንን ባልዋለችበት አውለው ዋጋ ያስከፈሉ ነጋዴ አሳታሚዎች በቅጡ እንዲሆኑ ሊገሰጹ ይገባል፡፡ሃይማኖት-ነክ ጽሑፎች በተለይ ኦሪጅናሌዎቹ ሊቃውንት ሳያዩዋቸው አንድ ቅጂ ብቻ ካንዱ ደብር አንጠልጥሎ ለኅትመት የመሮጥ ድርጊት ፍጹም ‹‹ውንብድና›› ነው እላለሁ!ሊታረም ይገባል!ወደሌላ ርእስ…

  ReplyDelete

 21. ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ አቋም… ባለቺን መነጽር፣እናነጻጽር፤4ቱን አንጻር!
  ክፍል-2

  2.6 እውን ደቂቀ እስጢፋኖስ መጎንበስ ያለበት ሰላምታ አይሰጡም?ለታቦት አይሰግዱም ነበር?!

  ፕ/ር ጌታቸው በገጽ 29 ደቂቀ እስጢፋኖስ ‹‹ስግደትን ከአምልኮ ጋር ስላያያዙት ከሰው ጋር ሰላምታ ሲሰጣጡ እንኳ አንገታቸውን ሰበር አያደርጉም ነበር ›› ይሉናል፡፡በገጽ 100 ኅዳግ እንዲሁ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለታቦት ስለመስገድ ያላቸውን አመለካከት ‹‹ከመስቀል ጋራ ካመሳሰሉት ለታቦት እንደማይሰግዱ መገመት ይቻላል›› ሲሉ በእኔ እምነት አሳሳች ግምት ይሰነዝራሉ፡፡የተረጎሙት ገድል ግን በገጽ 199 ለንጉሥ ዘርዐያዕቆብ መስገድን እንደ ባዕድ አምልኮ የሚመለከቱት ደቂቀ እስጢፋኖስ በገጽ 128 ለተአምረ ማርያም እጅ ሲነሱ፣በገጽ 232 እና 274 ቤ/ክ ሲሳለሙና አበምኔታቸውን እጅ ሲነሱት እናገኛቸዋለን፡፡የእነሱ እጅ መንሳት መጎንበስ የሌለበት ነው እንዳይባል ደቂቀ እስጢፋኖሳዊው አባ ዕዝራ እና የማኅበረ-እስጢፋኖስ አለቃ ሲገናኙ የነበረው የእጅ መነሳሳት አይነት ‹‹ያዕቆብ ያባቱን እጆች እንደሳመ ‹አጎንብሶ› የአባቱን እጅ ሳመ›› በሚል ተገልጹዋል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.310)፡፡ፕ/ር ጌታቸው ግን በመግቢያቸው ያስቀመጡት መደምደሚያ እንዳይፈርስባቸው በሚያስመስል መልኩ ‹‹መጎንበስ›› ያለበትን የአባ ዕዝራ ስግደት በኅዳግ ማስታወሻ ይሞግቱታል--‹‹ማጎንበስ ጀመሩ›› በሚል ስሜት!ታቦትና ደቂቀ እስጢፋኖስ ስላላቸው ግንኙነት ወረድ ብዬ የተወሰኑ ማስረጃዎችን ከገድላቸው አቀርባለሁ፡፡ፕ/ር ጌታቸው በገጽ 100 ኅዳግ የከፈቷትን የጥርጣሬ መስኮት ለመዝጋት ያህል ግን የአባ ዕዝራን ቃል ልዋስ፤‹‹‹አንተ (እግዘኢአብሔር) እንደረዳኸንና እንዳስደሰትከን ጠላቶቻችን ይዩ እና ይፈሩ› (መዝ 85 ቁ 17)አለ፡፡እንደዚህ ብሎ ሰገደ፤ታቦቶቹንም እጅ ነሣ››(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.308) የሚል ንባብ መኖሩን ጠቁሜ ብቻ ልለፍ፡፡

  2.7 እውን የደቂቀ እስጢፋኖስ ስራዎች በንጽጽር የእመቤታችንን ስም እምብዛም አያነሱም?!

  አባ እስጢፋኖስ ለተከታዮቹ በምሳሌያዊ መንገድ ቃለ-ምዕዳን ሲያስተላልፍ ‹‹…እስራኤልን ለበዓሉ ዕለት በብዙ መግለጫ ጋበዛቸው፡፡የግብዣው ጊዜ ሲደርስ በአስደናቂ መገለጥ ያለሰው ዘር ከንጽሕት ድንግል የዳዊት ልጅ ሰው ሆኖ ከዓለም በፊት ያዘጋጃትን ምክሩን ፈጸማት›› ይላል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.86)፡፡ተርጓሚው ፕ/ር ጌታቸው ደግሞ በኅዳግ ማስታወሻ ቁጥር 97 ‹‹ከዘመኑ የቤተክርስቲያን ስነ ጽሑፍ ጋራ ሲተያይ በእስጢፋኖሳውያን ዘንድ የማርያም ስም ብዙም አይታይም›› ይላሉ፡፡በቀደመው ንባቤ ይሕን የፕ/ር መደምደሚያ በየዋህነት እንዳለ ተቀብዬ አንጸባርቄው ነበር፡፡እየቆየ ግን መደምደሚያቸውን እጠረጥረው ጀመር፡፡ስጠረጥር ለማነጻጸር ተነሳሁ፡፡እድሜ ለዳንኤል ክብረት ‹‹አራቱ ኃያላን›› መጽሐፍ!አነጻጸርኩት!እሳቸው ካሉት የተቃረነ መደምደሚያ ላይ ደረስኩ!ላሳይ….

  (2.7.1) በአባ አኖሬዎስ ገድል ውስጥ በእኔ ፍለጋ የእመቤታችን ስም በቀጥታ ሲነሳ ያገኘሁት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤እሱም ጸሎተ-ማርያምን ከሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁ 52 ጋራ በማስተባበር በገጽ 324፡፡በተቀረ በክርስትና ስም መጠሪያነት በገጽ 335 እና 340 የእመቤታችን ስም አገልግሎት ላይ ውሏል፤እንጂ የአባ አኖሬዎስ ገድል ስሟን ደጋገሞ ሲያነሳ አላጋጠመኝም፡፡

  (2.7.2) በአባ ፊልጶስ ገድል (የፍልሰቱን ሳይጨምር) ውስጥ የእመቤታችን ስም በ6 አጋጣሚዎች መጠራቱን አንብቤያለሁ፡፡አባ ፊልጶስ ‹‹እመቤቴ ሆይ ልመናዬን ስሚኝ፣በዚችም ሰዓት ኃጥዕ ባሪያሽን ከተስፋዬ አታሳፍሪኝ…›› እያለ ጠበል በመርጨት በላዩ ላይ ባደረው መንፈስቅዱስ ኃይል ድውያንን ይፈውስ፤አጋንንትን ያወጣ እንደነበር ተጠቅሷል (ዳንኤል ክብረት፡ገ.203)፡፡በተጨማሪም በአባ ፊልጶስ ገድል ውስጥ በገጽ 220፣233፣252፣274 እና 278 የእመቤታችንን ስም እናገኘዋለን፡፡

  ReplyDelete
 22. (2.7.3) ወደ ደቂቀ እስጢፋኖስ ገድላት ስንመለስ ከገጽ 57 እስከ 115 በሚዘልቀው የአባ እስጢፋኖስ ገድል ውስጥ የእመቤታችን ስም በ4 አጋጣሚዎች በራሳቸው አነሳሽነት ቀጥታ በበጎ ተነስቶ እናገኘዋለን፡፡በገጽ 69 አባ እስጢፋኖስ በመንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ ሆኖ ‹‹ቅድስት ድንግል ማርያን እስኪያያትና ቃሏን እስኪሰማ ድረስ የተመሰገነች ሰማያዊ ምስጢር የሚያይ›› ሆኖ እንደነበር ተጽፏል፡፡በገጽ 85 እና 86 አባ እስጢፋኖስ ስለጌታ ሰው መሆን ሲያስተምር ‹‹ከንጽሕት ድንግል ተወለደ›› ይላል፡፡በገጽ 110 ፕ/ር በኅዳግ ማስታወሻ ቢገዳደሩትም የአባ እስጢፋኖስ አስኬማ የእመቤታችን ንጽሕና አምሳል ሆኖ ቀርቧል፡፡ፕር ግን ‹‹አርያም›› ለማለት ፈልጎ ነው ‹‹ማርያም›› ያለው ምክንያቱም አስኬማ በእመቤታችን አይመሰልም የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡እኔ እስከማውቀው በአብነት ተማሪ ቤት ያሉ ደቀመዛሙርትና ሕጋውያን (ባለትዳር) ቀሳውቅስትም ቆብ ያደርጋሉ፡፡ሆኖም እነሱ የሚያደርጉት ቆብ እንደ መነኰሳት ድፍን ሳይሆን መሀሉ ላይ በመሀል አናት ትይዩ ቀዳዳ ሊኖረው ግድ ነው፡፡የመነኰሳት አስኬማ ግን ከላይ ድፍን ነው፡፡የድንግልናቸው ምልክት ነው!የእመቤታችን ንጽሕና እና ድንግልና ከአባ እስጢፋኖስ ኅትምት(ድፍን) አስኬማ ጋር መነጻጸሩም በዚህ መንገድ ከእሷ ንጽህና ተነጻጽሮ ሊታይ ይገባል እንጂ በኅዳግ ማስታወሻ ደቂቀ እስጢፋኖስን ወደ ፀረ-ማርያም ካምፕ መጎተት ደግ አይደለም፡፡

  (2.7.4) በገድለ አበው ወኃው ውስጥ ታሪካቸው በሰፈረው የእነ ንግስተማርያም ገድል የእመቤታችን ስም ከገጽ 146 እስከ 149 በስፋት ይነሳል፡፡እሱ በሰጊድ ዙሪያ በነበረው ክርክር ስለሆነ እንለፈው፡፡ነገር ግን በገጽ 140 ‹‹የአምላክ እናት ሆይ እነሆ ከምሕረትሽ ጥላ ስር ተደግፈናል፤በጭንቅ ጊዜ ልመናችንን አትናቂ›› የሚሉ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ተማጽኖዎች ልቦናችንን ያንሰፈስፉታል፡፡በገጽ 152 እና 154 ‹‹አክሊለ-ምክሕነ--የትምክታችን አክሊል›› እያሉ ስሟን በውዳሴ ሲጠሩት ስንሰማ እንደነግጣለን፡፡ይሄ ማስረጃ 100 በማይሞሉ የገድላቱ ገጾች በዳሰሳ የተገኘ ነው፡፡ከዚህ አንጻር ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ‹‹ከዘመኑ የቤተክርስቲያን ስነ ጽሑፍ ጋራ ሲተያይ በእስጢፋኖሳውያን ዘንድ የማርያም ስም ብዙም አይታይም›› በሚል የደረሱበት መደምደሚያ ተጨባጭ ንጽጽር ተሠርቶ የቀረበ አልመስሎኝም!ቢያንስ የእመቤታችን ስም ከገድለ አባ አኖሬዎስና አባ ፊልጶስ ጋር ሲነጻጸር በደቂቀ እስጢፋኖስ ገድላት በተደጋጋሚ ተነስቷል፡፡በአባ ዕዝራ ገድል ውስጥማ ስለእመቤታችን ክብርና ውዳሴ ያለው ማስረጃ የትየለሌ!

  (2.7.5) በዚህ ረገድ (በሰጊዱና በውግዘቱ ጉዳይ ልዩነት ቢኖረኝም) በእመቤታችንና ደቂቀ እስጢፋኖስ ሁለንተናዊ ግንኙነቶች ዙሪያ መ/ር ካሕሳይ እንደሚባለው ደቂቀ እስጢፋኖስ ‹‹ፀረ-ማርያም›› እንዳልነበሩ ማሳያዎችን በመደርደር አስመስጋኝ ሥራ ሰርተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ከላይ የጠቀስኳቸውን ስሟን የሚያነሳሱ ድርሰቶቻቸውን፣አባ ገ/ማያም የተባለ የደቂቀ እስጢፋኖስ መነኵሴ ‹‹እኔ የማርያም ባሪያ ነኝ›› ማለቱን(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.156)፣የመሰረቷቸው ገዳማት ሁሉ በእመቤታችን ስም መሆናቸውን፣በጻፏቸው መጻሕፍት ሁሉ የምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕል መኖሩን፣አንቀጸብርሃንና ውዳሴማርያም መድገማቸውን፣ወዘተ…በመጥቀስ ፀረ-ማርያም እንዳልሆኑ ተከራክረዋል (ካሕሳይ፡ገ.55)፡፡አባ እስጢፋኖስ ስለ እመቤታችንና ስለመስቀል የደረሰው 38 ገጽ ድርሰት ብለው ከድርሰቱ ቆንጥረው ያቀረቡልን በውብ የግእዝ ቋንቋ የተከሸኑ ምንባባት ምናልባት በትክክል የእሱ ስለመሆናቸውና በገድሉ ላይ ከተንጸባረቀው አቋሙ ጋር ስለመጣጣማቸው ተመሳክሮ የሚቀርብ ሰፋ ያለ ጥናት የሚፈልጉ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ድርሰቶቹ ግን ሲያምሩ! ግእዙ…ንህነሰ ኢኮነ ጸላእያነሃ ለማርያም…ብሎ ነው የሚጀምረው::እሱን ብዙዎች አንባቢዎቻች ለግእዝ ሩቅ ናቸው ብየ ስለምገምት አማርኛውን ብቻ ጥቂት ልጥቀስ፤‹‹….እኛ ከመጠራጠር የተነሳ ሰዎች እንደሚሉን የማርያም ጠላቶች አይደለንም፡፡ ቃላችንም አይደለም፤አይደለም፤አዎን፤አዎን ብቻ ነው፡፡እኛ ፊታችንን እያማተብን የድንግል ማርያም አገልጋዮች ነን፤ባሮቹዋም ነን፤ፊታችንን በስላሴ ስም እያማተብን አበሳችንን የሚደመስስ ስለወለደችልን እንሰግድላታለን፡፡…..እንዲህ እያልን እመ-ብርሃንን እናመሰግናታለን፡፡ አንቺን ከፍ እናደርግሻለን ፤በስብሐትና በውዳሴም እንሰግድልሻለን፡፡ ዓሳ ከውሃ ወጥቶ በየብስ ለመኖር እንዳይችል ነፍስ የተለየው ስጋም እንደማይንቀሳቀስ፣ከግንዱ የተቆረጠ እንጨትም እንደማያፈራና እንደሚደርቅ ክርስቶስን በወለደች ማርያም የማያምንም ከመጽሐፍ የተፋቀ (የተደመሰሰ) ነው፡፡›› ይሏታል ይሉናል (ካሕሳይ፡ገ.54)፡፡

  2.8 እግረ መንገድ ገድላተ ደቂቀ እስጢፋኖስን ከዘመነኞቻቸው ጋራ እናነጻጽር!
  ደቂቀ እስጢፋኖስ ከዘመናቸው ጋራ ተቀራራቢ በሆነ ወቅት ከተነሱ መስተጋድላን ጋራ ማነጻጸር ከጀመርን ተጋድሎአቸውን እና ክርክራቸውን ጥቂት ገፋ አድርገን በንጽጽር እንየው፡፡ንጽጽሩ በወቅቱ የነበረውን ጠንካራ ክርስቲያን የሆኑ ግን አምባገነን ነገሥታትና ከእነሱ ጋር ያበሩ የተባበሩ ካሕናተ ደብተራ ባንድ ወገን ሆነው፤በሌላው ወገን ደግሞ ጥብቅ የምንኵስና ሕይወት የሚከተሉ መነኮሳት ተሰልፈው ተጋድሎ ያደረጉበትን የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ታሪክ ለመረዳት ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ንጽጽሩን እንቀጥል…

  (2.8.1) አጼ አምደጽዮን ዕቁባት ማብዛት አመጣ፡፡ሦስት ሚስት አበጀ፡፡ካሕናተ-ደብተራም ድርጊቱን ከመንቀፍ ይልቅ ‹‹ይደልዎ›› ብለው አጸደቁለት፡፡እነ አባ ፊልጶስ ድርጊቱን ለማውገዝ ከበዓታቸው ገስግሰው ቤተ-መንግሥቱ ሲደርሱም ካሕናተ ደብተራ ስለንጉሡ ሆነው ይሞግቱለት ጀመር፡፡በተለይ ዘአማኑኤል የተባለው የካሕናተ-ደብተራ ወገን ሽንጡን ገትሮ ተከራከረለት--ለንጉሡ፡፡አባ ፊልጶስ ቁጣው ነደደ፡፡ማን ያቁመው!ዘአማኑኤልን ይተገትገው ጀመር፡፡እንዲህ እያለ ‹‹…ዘአማኑኤል ሦስት ሚስት በአንድ ጊዜ እንዲያገባ ለንጉሡ ታዟል አለ እንጂ ለሁሉም አላለም፤በዚህም እግዚአብሔርን ፊት የሚያይ፡፡ስለመንግሥቱ (ንጉሡን) የሚፈራ፤ድኻንም ስለድኻነቱ የተነሳ የሚንቅ አደረገው፡፡በዚህም በአምላካችን ላይ ዋሸ፡፡‹ለነገሥት ሦስት ሚስት ያገቡ ዘንድ ታዝዟል የሚለውን ከየት አገኘው?› ሕግ መሲሓዊት(ክርስቶሳዊት) ከተገለጠች በኋላ?ከመጽሐፈ-ኪዳን ነውን?ወይስ ከወንጌል፣ወይስ ከሐዋርያት መልእክት፣ወይስ ከእነርሱ ጋር ሱታፌ ካለው፣ልሳነ-እፍረትም ከተባለ ጳውሎስ ነውን?ከዲድስቅልያ ነው?ወይስ ከመጽሐፈ-ሲኖዶስ፣ቅድስት ቤተክርስቲያን ከተቀበለቻቸው፡፡…የጽድቅ ቃላትን ከበሚናገሩ መጻሕፍት ሁሉ ይኸንን ትእዛዝ ብንፈልግም አላገኘነውም፡፡…ከሐዲስና ከብሉይ ምስክር በዚህ ነገር ላይ እናመጣ ነበር፤ነገር ግን እንዳይረዝም ብለን ተውነው›› ይላል(ዳንኤል ክብረት፡ገ.268)፡፡በተመሳሳይ አባ እስጢፋኖስ አባ ሲኖዳ የተባለ ዓለማዊነትን የወደደ መነኵሴ ጋር በንጉሥ ዘርዐያዕቆብ የፍርድ አደባባይ ቀርበው ሲከራከሩ ለመነኰሳት ተብሎ የተለየ ሥርዓት አልተሠራም ባለው ጊዜ ‹‹…ምዕመናን በሚስቶቻቸው እንዲጸኑና ልጆቻቸውን በእውነት እንዲያሳድጉ፣ካሕናትም ለመኖሪያቸው አሥራትና በኵራት እንዲወስዱ አዟል›› ሲል ከአባ ፊልጶስ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ መጽሐፈ-ሲኖዶስን ጠቅሶ ይከራከረዋል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.89)፡፡

  ReplyDelete
 23. (2.8.2) ንጉሥ ሠይፈአርእድ አባ ፊልጶስን ‹‹እኔ ከማልገዛው ምድር ልትደርስ ትችላለህን?›› ባለው ጊዜ ሲመልስ ‹‹እኔስ ምድር የአንተ ሳትሆን የእግዚአብሔር እንደሆነች አውቃለሁ፡፡ነገር ግን አባቶቼ ሐዋርያትን እመስላቸው ዘንድ ስደትን እቀበላለሁ›› ይለዋል(ዳንኤል ክብረት፡ገ.292/293)፡፡ተመሳሳይ ጥያቄ ለአባ እስጢፋኖስ ከንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ቀርቦለት ‹‹ቤተክርስቲያን የታነጸችው በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ እንጅ በምድር ንጉሦች ላይ አይደለም፡፡ስለዚህ ሞገዶች በማያናውጹዋት ክርስቶስ በገነባልን ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ እንኖራለን›› ሲል ይመልስለታል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.110)፡፡

  (2.8.3) አባ ፊልጶስ ከሠይፈአርእድ ‹‹የቤተክርስቲያን ሹማምንት ሁሉ ከእኔ ጋር ተባበሩ፤አንተ ብቻ ትእዛዜን ሳትቀበል ቀረህ›› የሚል ቁጣ ደርሶበት ነበር፡፡የአባ ፊልጶስ ምላሽ ግን ‹‹ፈርቼ ሕጉን ከሻርኩማ የመጀመሪያው ገድሌን በከንቱ አደረግሁት፡፡…ዕርፍ ይዞ ወደኋላ የሚያርስ የለም [ሉቃስ 9 ቁ 62]›› የሚል ነበር (ዳንኤል ክብረት፡ገ.291)፡፡በዚሁ መንገድ ለአባ እስጢፋኖስ ከካሕናተ-ደብተራ ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ‹‹…ጌታ ሕይወትን ስለመውረስ ለጠየቀው ባለጸጋ ‹ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ ሂድና ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ ለድኻ ሰጥተህ ና ተከተለኝ› [ማቴ 19 ቁ 21] እንዳለው ቅዱስ ወንጌል ምስክሬ ነው፡፡…ደግሞ ዕርፍ ይዞ ወደኋላ የሚሄድ የለም፤ምክንያቱም መንግስተ-ሰማያት ቀጥታ ናት [ሉቃስ 9 ቁ 62]›› ይላል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.89)፡፡በደቂቀ እስጢፋኖስ ገድል ውስጥ ንግሥተማርያምን የመሳሰሉ ጠንካራ መነኰሳዪያት እንደምናገኘው ሁሉ በአባ ፊልጶስ ገድል ውስጥም መክብዩና ኦርኒ የተባሉ ጽኑኣት መነኰሳይዪያትን እናገኛለን (ዳንኤል ክብረት፡ገ.287)፡፡

  (2.8.4) በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰውን ሰቆቃ እና እጅግ ኢ-ሰብአዊ ቅጣት ምን ጥቅስና አመክንዮ ብንደረድር አሳማኝ ልናደርገው አንችልም፡፡በመጠናቸው እነሱ ላይ ከደረሱት ጋራ ይተካከላሉ ባይባሉም እጅግ መሪር ሊባሉ የሚችሉ ቅጣቶች በዚያው ዘመን አካባቢ በተነሱ የመካከለኛው ዘመን መነኰሳት ላይም ደርሷል--ዳንኤል ክብረት በ‹‹አራቱ ኃያላን›› ከገጽ 92-102 እንደተረከው፡፡ለምሳሌ፡- አባ ፊልጶስ በጅራፍ ተገርፈዋል፣በሽመል ተወቅተዋል፣እርቃናቸውን ተደርገው የጺማቸውና የኀፍረተ-ሥጋቸው ጸጉር ተነጭቷል፣ታስረዋል፣ተግዘዋል፣ከታሰሩ በኋላ እንደ ሮማውያን ግላዲያተር የተራቡ ውሾች ተለቀውባቸዋል፡፡እነ አባ በጸሎተሚካኤል፣አኖሬዎስ፣አሮን፣ተክለሐዋርያት፣ሣሙኤል ዘደብረ ወገግ የነገሥታቱ የጭካኔ በትሮች አርፈውባቸዋል፡፡የእነ አባ ቀውስጦስ የንጉሥ አምደጽዮን የሥጋ ዘመዶች መሆን ተግሳጽ በንጉሡ ላይ በሰነዘሩ ጊዜ 400 ግርፋት ከመቀበል፣ጺማቸውን ከመነጨት፣እጅና እግራቸው እንደ ድንኳን አውታር ተወጥሮ ከመታሰር እና በመጨረሻም ጎናቸውን በጦር ተወግተው የሰማዕትነትን ጽዋ ከመጎንጨት አላዳናቸውም፡፡

  (2.8.5) ሞትን በሚመለከት ንጽጽር ብንሰራ ደቂቀ እስጢፋኖስ በገጽ 221 እንደሚነግሩን በ‹‹ድብፀር››(አጼ ዘርዐያዕቆብ) እጅ ብቻ 1004 ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን በንጉሡ የግድያ ትእዛዝና በግዞት አልቀዋል፡፡በተመሳሳይ 128 የአባ አኖሬዎስ ተከታዮች፣500 የአቡነ አሮን ተከታዮችና በሺህ የሚቆጠሩ የአባ ፊልጶስ ተከታዮች በአጼ አምደጽዮንና ሰይፈአርእድ ዘመን ሲያልቁ እናገኛለን(ዳንኤል ክብረት፡ገ.98፣287 እና 351)፡፡የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ክርስትና እንደዚህ ነበረ፡፡ነገሥታቱ ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ትንሣኤ እጅግ በመጣጣራቸው፣አምልኮ-ባዕድን በማክሰማቸው፣ክርስቲያኑ ግዛት በሙስሊም ጅሀዲስቶች እንዳይዋጥ ከውጭም ከውስጥም ጠንክረው በመከላከላቸው እናደንቃቸዋለን፡፡የምግባር ጉድለታቸውንና ኢ-ክርስቲያናዊ ቅጣታቸውን ስናይ ደግሞ እንሸማቀቃለን፡፡የሆነ ሆኖ ነገሥታቱ ካለፉ በኋላ እነ አባ አኖሬዎስ፣ፊልጶስ፣አሮን፣ወዘተ ያለልዩነት በቅድስና ሲጠሩ ደቂቀ እስጢፋኖስን በሚመለከት ግን ለምን የተለያየ ሐሳብ ተራመደ?ብለን መጠየቃችን አይቀርም፡፡የእኔን አቋም ቀደም ሲል ስለውግዘትና ስግደት ሳነሳ ያንጸባረቅሁ ይመስለኛል፡፡

  (2.8.6) በአጠቃላይ በገድል አጻጻፍ ደረጃ የክርክሩ ጭብጥ ከመለያየቱ በቀር በደቂቀ እስጢፋኖስና በአራቱ ኃያላን ያለው አቀራረብ የተመሳሰለ ሆኖ ይታየኛል፡፡ደጋግመው የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች ማቴ 5 ቁ 10፣ማቴ 10 ቁ 39፣ማቴ 16 ቁ 24፣ማቴ 19 ቁ 21፣ማቴ 22 ቁ 2፣ሉቃ 9 ቁ 23፣ሉቃ 9 ቁ 62፣መጽሐፈ-ሲኖዶስና ዲድስቅልያ እንዲሁም የቅዱስ ዳዊት መዝሙራትና የነአባ እንጦንስና መቃርስ የምናኔ ተጋድሎዎች ናቸው፡፡እነዚህ ጥቅሶች በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ስለምናኔ እና ምንኵስና በአስረጂነት ሲቀርቡ የምናውቃቸው ናቸው (መ/ብ አድማሱ ጀንበሬ፡ገ.44-46)፡፡ገድላቸውን የሚጽፉበትን ምክንያትም የገድለ አበው ወአኃው ግድል ጸሐፊ በገጽ 221 ሲናገር ‹‹ይኸንን ለኛና ከኛ በኋላ ለሚመጡ ማስታወሻ እንዲሆን እንዳገኘነው ጻፍነው›› ያለ ሲሆን በተመሳሳይ የአባ አኖሬዎስ ገድል ጸሐፊም ‹‹በምስክርነት ካልጻፍንና ካልተናገርን የሚመጣ ትውልድ በምን ያውቃል?...እኛማ እንሞታለን፤እንጣላለንም፡፡የሰው ልጅ ሁሉ እንደሳር ያልፋልና›› (ዳንኤል ክብረት፡ገ.325) ሲል ገድሉን ለመጻፍ ያነሳሳውን ምክንያት ይገልጻል፡፡ለማወቅ የሚጓጓው ሀገራዊ ትውልድ አነሰ እንጂ ገድላትን የመጻፍ ዐላማቸውስ ተጋድሏቸውን ለመጪው ትውልድ ለማሳወቅ ነበር!

  ReplyDelete
 24. 2.9 በውኑ ደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍቅዱስ ብቻ--Bible Only ባዮች ነበሩን?

  (2.9.1) በአባ እስጢፋኖስ ገድል ገጽ 65 እንዲህ የሚል ቃል ሰፍሯል፤‹‹ነፍሱን በአምላክ መጻሕፍት ምስከራ በቆመች በጌታ ሥምሪት አሠማራት፡፡ከሰው ጠባይ የሚድንበት ውሳኔዎቻቸውንም መጠበቅ ያዘ፡፡ቅዱሱ ለሚሠራው ሁሉ አስቀድሞ አበምኔቱን ይጠይቅና ፈቃድ ይወስዳል፡፡›› ፕ/ር ጌታቸው ይሕን የገድሉን ጸሐፊ ገለጻ ሲተረጉሙት ‹‹Fundamentalist የሚባሉት እንደሚያደርጉት መጽሐፍ የሚለውን ቃል በቃል መጠበቅና እንደትእዛዞቹ መሄድ ጀመሩ ማለት ነው›› ይሉናል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.65፣ኅዳግ ቁ.35)፡፡ Fundamentalist የሚባሉት እንደ አባ እስጢፋኖስ ‹‹ዕርፍ ይዞ ወደኋላ የሚያርስ የለም›› በሚል እጅግ የጠበቀ የምንኵስና ሕይወት ስለመከተላቸው፣81ዱ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ፍና-ሐዋርያትንና አሰረ-አበውን ስለመከተላቸው፣በአበምኔት ፈቃድ ስለማደራቸው ግን ፕ/ር አልነገሩንም፤እኛም አላነበብንም፡፡

  (2.9.2) አባ እስጢፋኖስ ‹‹ሰንበታትንና ዓላትን በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እንደተጻፈ እያከበራችሁ…የሐዲስና ብሉይ…ምስከራ ለመጠበቅ የተዘጋጃችሁ ሁኑ›› በማለት ከነባሩ ትውፊትና ቁጥሩ ከ81ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ከሆነው መጽሐፈ-ሲኖዶስ ጠቅሶ ሲያስተምር ፕ/ር ጌታቸው በኅዳግ ማስታወሻቸው ‹‹አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ መጽሐፈ-ሲኖዶስን ከተቀበሉ ቅዳሜንም ያከብራሉ፤ገድሉም ይመሰክራል፡፡በመጽሐፈ-ሲኖዶስ ያልተዘረዘሩትን መጻሕፍት ግን በሕግ ደረጃ የሚቀበሉ አይመስልም፡፡›› ሲሉ ለደቂቀ እስጢፋኖስ በመጽሐፋቸው መግቢያ የሰጡትን ሉተራዊ ተዛምዶ ላለማናጋት የሚጥሩ መስለው ይታያሉ(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.77፤ኅዳግ ማስታወሻ ቁጥር 74)፡፡በወጉ በዓል የሚያከብርና መጽሐፈ-ሲኖዶስን የሚቀበል ሉተራዊ ፕ/ር ዐይተው የሚያውቁ ከሆነ መልካም ነው!መጻሕፍትን በሕግ ደረጃ ስለመቀበል ከላይ በተራ ቁጥር 2.8.1 ከሰፈረው የአባ ፊልጶስ አነጋገር መረዳት እንደሚቻለው ኦርቶዶክሳውያን አባቶችን እንኳንስ የሕግ መጻሕፍት በሚባሉት 81ዱ እና በሌሎች አዋልድ መጻሕፍት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት ይቅርና ሐዲስና ብሉይ ያላቸውን አንጻራዊ ሥልጣንም ‹ምሳሌያዊት› እና ‹አማናዊት›፣‹ብሉይ›ና ሐዲስ፣‹የተሻረች›ና ‹ፍጽምት› ሕግ እያሉ የክብራቸውን ደረጃ ደርድረው ተረድተው ነው የሚያስቀምጡት፡፡

  (2.9.3) ፕ/ር በቦሩ ሜዳ ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ የደረሰው መስተበቁዕ ዘማርያም ኑፋቄ አለበት ተብሎ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲስማማ ተደርጎ መስተካከሉን ነግረውናል፡፡እኛም በዚሁ ጉባኤ ሦስት-ልደት ባዮች ተአምረማርያምን ለክርክራቸው ጠቅሰው ሲያቀርቡ ከ81ዱ ካልሆነ በቀር ለነገረ-ሃይማኖት መከራከሪያ ተአምረማርያም ሊጠቀስ እንደማይገባ በአጼ ዮሐንስ ተነግሯቸው መረታታቸውን አንብበናል--ቅሉ ይሕ አባባል የመጻሕፍትን ደረጃ ከመጠቆም በቀር ተአምረማርያም ለማነወር እንዳልተነገረ ብናውቅም(አቡነ ጎርጎርዮስ፡ገ.73)፡፡ስለዚህ በኢኦተቤክ ከ81ዱ መጻሕፍት ውጭ ‹‹የሕግ መጽሐፍ›› ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስን አክሎ እና ተካክሎ የሚጠቀስ መጽሐፍ እንደሌለ መረዳት አያዳግተንም፡፡ፕ/ር ግን በመግቢያቸው ካስቀመጡዋት መደምደሚያ ፈቀቅ ሊሉ አይሹም፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስን Bible Only ባዮች ለማስመሰል የቆረጡ ይመስላሉ፡፡ለነገሩ ለመጽሐፋቸው ርእስም ያለነገር ‹‹በሕግ አምላክ›› የምትል ተቀጽላ አላበጁለትም!ያ!ባልከፋ፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስን አብዮታውያን ለማድረግ ሲሉ ቤ/ክ እንዲያው አዋልድን እና መጽሐፍ ቅዱስን ለይታ የማታውቅ የሚያስመስል አቀራረባቸው ግን ቅር ያሰኛል፡፡እኔ እንዲያ ተሰምቶኝ ቅር ብሎኛል!

  (2.9.4) በሕገ-መጻሕፍት አጠቃቀስ ረገድ ደቂቀ እስጢፋኖስ በወቅቱ ከነበሩት ሌሎች መስተጋድላን አበውም ሆነ በዘርዐያዕቆብ ወገን ከተሰለፉት ተከራካሪዎች የተለየ አቋም ነበራቸው ለማለት የሚያስችል ተጨባጭ መረጃ የለም፡፡ለምሳሌ ንጉሡ አባ እስጢፋኖስን ሲጠራው ‹‹ላገኝሕና ‹በሕጉ ፈለግ› መሰረት ሁሉንም ለእግዚአብሔር ላስተካክል እወዳለሁ›› ብሎት ነበር(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.92)፡፡በገጽ 147 ንጉሡ ‹‹የኢትዮጵያን ሃይማኖት ለምን ለሁለት ትከፍላላችሁ?አሁንም እኛ ዘንድ የጎደለውን እናንተ እየሞላችሁ፤እናንተ ዘንድ የጎደለውን እኛ እየሞላን ‹በመጻሕፍት ይወሰን›…›› ብሎ ነው የሰበሰባቸው፡፡ዘርዐያዕቆብን በተግባሩ እንወቅሰዋለን እንጂ እነሱ ያልተቀበሉን ሕግ ጠቅሷል ብለን አናማውም፡፡ከፋም ለማም እሱም ‹‹ኑና በሕጉ ተዳኙ›› ነው ያለው፡፡እንደሕጉ ሄዷል/አልሄደም ሌላ ጥያቄ ነው!በጥሪው መሰረት እየቀረቡ ባደረጓቸው ክርክሮች 2ቱም ወጎኖች በዋናነት 81ዱን መጽሐፍቅዱስ ነው የሚጠቀሙት፡፡ማሳያ ካስፈለገ በገጽ 88፣185፣186 እና ከ294-297 ያሉ ሞቃት ክርክሮችንና ምልልሶችን መመልከት ይቻላል፡፡በመጽሐፍ ቅዱስና በአዋልድ አጠቃቀስ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባት በገድላቱ ውስጥ አ…ል…ተ…መ…ዘ…ገ…በ…ም፡፡ባልተመዘገበ ቃል ብይን መስጠት ደግሞ አያስኬድም፡፡ስለዚህ ፕ/ር ደቂቀ እስጢፋኖስ ከFundamentalist ወገን እንደነበሩ አድርገው ያቀረቡትን ማስታወሻ የምቀበለው አይደለም፡፡ለማንኛውም ‹‹መፍቀሬ-ደቂቀ-እስጢፋኖስ›› ብለን ረጅሙን የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ሓሳብ ለመሞገት የተንደፋደፍንበትን አማተራዊ ርእስ በዚሁ ቋጭተን ወደሌላ ዕይታ ተሻገርን!

  ReplyDelete
 25. 3. እንቅስቃሴውን ፖለቲካዊ ትርጕም መስጠት!

  ገና ስጀምር የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ ‹‹ለትርጉም የተመቸ ነው›› ብዬ ነበር፡፡የሆነውም እንዲያ ነው፡፡የደቂቀ እስጢፋኖስን ሰቆቃ መብዛት ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ በወቅቱ የገነገነውን ዓለማዊነት የተጫነውን ምንኵስና ለመታገል ከተደረገው ጥረት ጋር ያይዙታል፤መ/ር ካሕሳይ ከንጉሡ አምባገነንነትና መፍቀሬ-ሥልጣን መሆን ጋራ ያቆራኙታል፤ፕ/ር መስፍን ከንግግር ነጻነት ነፋጊነትና ከማሰብ ነጻነት ጋራ ያይዙታል፤Hagos G የተባሉ ጸሐፊ ‹‹The Dekike Estifanos: Towards an Ethiopian Critical theory›› በሚል ርእስ ከሐገራዊ ኂስ(በእሳቸው ቋንቋ ‹‹ሐተታ››) ጋር አገናዝበው ለእኔ የጣፈጠኝ ውብና በተለየ አንጻር የቀረበ ዳሰሳ አድርገውበታል፡፡አቡነ ጳውሎስና Krzysztof Piotr BŁAśEWICZ የተባሉ በደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ ዙሪያ 2ኛ ዲግሪያቸውን የሰሩ ፖሊሽ (ፖላንዳዊ) የቲዎሊጂ ሊቅም የደቂቀ እስጢፋኖስን መሳደድ ወደ ፖለቲካዊ ትርጓሜው አድልተው ዐይተውታል፡፡የሁሉንም ሐሰባ ማስፈር ባይቻልም የተወሰኑትን እናቅርባቸው፡፡

  (3.1) <> በተሰኘ የዶክትሬት ማሙያ ጥናታቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ <<…It seems that much of their opposition was politically motivated,directed at the claims of the Solomonic dynasty>>ሲሉ የደቂቀ እስጢፋኖስን እንቅስቃሴ ሰሎሞናዊ ንግሥናን ከመቀበልና ካለመቀበል ጋር አያይዘውታል(አቡነ ጳውሎስ፡ገ.262)፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስ ሰጥ ለጥ ብለው ለንጉሡ አለመገዛታቸው ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ አንድነትን መሰረት ያደረገ ግዛት ለመመስረት ቆርጦ በተነሳው አጼ ዘርዐያዕቆብ አደባባይ ቅጣታቸውን እንዳከበደባቸው ይከራከራሉ(ዝኒ ከማሁ፡ገ.263)፡፡መ/ር ካሕሳይም ይሄንኑ ሐሳብ ያጠናክራሉ(ካሕሳይ፡ገ.52)፡፡አቡነ ጳውሎስ ከመ/ር ካሕሳይ ለየት የሚሉት ደቂቀ እስጢፋኖስ የቀደምት አይሑዳውያን-ክርስቲያኖች ቅሪቶች ሳይሆኑ አይቀርም የሚለውን የቤተ-እስራኤል ታሪክ ጸሐፊዎች አስተሳሰብ ወደመቀበል በማዘንበላቸው ነው፡፡እሱን ወረድ ብዬ እመለስበታለሁ፡፡

  (3.2) Krzysztof Piotr BŁAśEWICZ በተመሳሳይ የደቂቀ እስጢፋኖስ መከራ መብዛት ከሃይማኖታዊ መነሻው ይልቅ በካሕናተ-ደብተራ የብልጽግና ኑሮ ላይ ባነሱት ተቃውሞ፣ከሚከተሉት በራስ የድካም ፍሬ የማደር የጠበቀ የምንኵስና ሕይወት፣ከጥብቅ የመጽሐፍ ንባብቸውና ያነበቡትን ለመኖር በሚያደርጉት ጥረት፣ከበዐታቸው እየወጡ በመስበካቸውና ለንጉሡ ባለመስገዳቸው ፖለቲካዊ ይዘት ሊኖረው እንደሚችል ሲተርኩ፤<>( BŁAśEWICZ,p.42)ብለዋል፡፡

  (3.3) በዚህ ጎራ ያለውን አስተሳሰብ ሙሉ ለሙሉ መካድ ኢ-ፍትሐዊ ይሆንብኛል፡፡ከበርቴ ካሕናተ-ደብተራ በንጉሡ ዙሪያ መኖራቸው እውነት ነው፡፡ንጉሡ ለሥልጣኑ ያለው ቀናኢነት ልጆቹና ሚስቱ ላይ ሳይቀር ለማስጨከን የሚያስችለው ነበር፡፡ለንጉሥ ሰጊድ እንዲደረግ በይፋ ሕግ ያወጣውና ‹‹አንቱታ››ን ያመጣው እሱ መሆኑ ከዜናመዋዕሉ እና ከታሪክ መጻሕፍት እንረዳለን(ፍስሐ ያዜ፡ገ.252)፡፡በጊዜው ለደገኛው ክርስቲያን ንጉሣዊ አስተዳደር ተገዳዳሪ ከነበሩት ቆለኛ ሡልጣኔቶችና የቤተ-እስራኤላውያን መሳፍንት መነሳሳት አንጻር ንጉሡ ዙፋኑን ያለሃይማኖት አንድነት ማስጠበቅ እንደማይችል ስጋት አድሮበትም ሊሆን ይችላል፡፡ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች ደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ክንዱን አበርትቶባቸው ሊሆን ይችላል ቢባል ተገቢ መላምት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ያም ሆኖ ግን የደቂቀ እስጢፋኖስ ‹‹ለመስቀልና ለእመቤታችን አንሰግድም›› የሚል አቋም ማስተባበያ እስካልተገኘለት ድረስ ሰቆቃቸው ‹‹ፖለቲካን ብቻ››መሰረት ያደረገ ነው ብሎ መደምደም ደግሞ ተአማኒ አይመስለኝም፡፡ጪስ ከሌለ እሳት አይኖርም!የልደት በዓል ‹‹ታሕሳስ 28 ወይስ ታሕሳስ 29?›› ነው መከበር ያለበት በሚል ክርክር ብቻ የብዙኃን ደም በፈሰሰባት ሀገር ለእመቤታችንና ለመስቀል አለመስገድ እንዲህ እንደዋዛ ይታለፋል ማለት ያውካል፡፡ስለዚህ በእኔ እምነት ለእመቤታችንና ለመስቀል ያለመስገዳቸው ጉዳይ መነሻ ሆኖ ከላይ የተጠቀሱት ፖለቲካዊና መደባዊ ጉዳዮች ስቃያቸውን በገድላቱና በተአምረ ማርያም በሰፈረው መልኩ እጅግ ኢ-ሰብአዊ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

  ReplyDelete
 26. (3.4) ደቂቀ እስጢፋኖስ የንጉሡን ሰሎሞናዊ ዝርያ ስላልተቀበሉት ነው መከራ ያወረደባቸው የሚለው አነጋገር ከአባባል ባለፈ በገድሉ ሲንጸባርቅ አናየውም፡፡ነገሥታቱ እስራኤላዊ ዝርያ አለን የሚለውን ትምክህት ባይተውትም ወደኋላ ክርስትናቸውንም ትልቅ የሥልጣን ሕጋዊነት (Legitimacy) ማስገኛና መመኪያ አድርገውታል፡፡ሰሎሞናዊ ነገሥታት እስራኤላዊነተን ትተው በክርስትናቸው መኩራት ስለመጀመራቸው አጼ ይስሐቅ በገጽ 83 ከእስራኤል ስምና ከክርስትና ስም የቱ ይበልጣል ለሚለው ክርክር ‹‹እኛም ትምክህታችን በክርስትና ነው›› ሲል ለአባ እስጢፋኖስ ደግፎ አረጋግጡዋል፡፡ስለጉዳዩ ያለውን የቀደምት ሰሎሞናዊ ነገሥታት ስነ-ልቡና የበለጠ ማወቅ የፈለገ ደግሞ ክብረ ነገሥትን ከገጽ 106-108 ማንበብ ነው፡፡ወይም የዶናልድ ሌቪኒን ታላቋ ኢትዮጵያ ገጽ 90 መመልከት፡፡አሁን ወደ ሌላ ምልከታ…ስርዋጽ እናስገባ…

  4. እንደስርዋጽ፡-ደቂቀ እስጢፋኖስ ነገሥታቱን በተለይ አጼ ዘርዐያዕቆብን እንዴት ያዩታል?

  የታሪክ መዛግብትን ከደቂቀ እስጢፋኖስ ጋር አነጻጽረን ካየን ከአጼ ይስሀቅ (1406-1420) እስከ አጼ ናዖድ (1486-1500) ባለው ጊዜ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥታዊ ዙፋን 10 ነገሥታት ነግሠዋል፡፡ሆኖም ከነዚህ ውስጥ ከደቂቀ እስጢፋኖስ ጋር ስማቸው ተያይዞ በገድላቱ የተነሳው 4ቱ ብቻ ናቸው፡፡አጼ ይስሐቅና አጼ ናዖድን ገድላቱ በበጎ ያነሷቸዋል፡፡አጼ ዘርዐያዕቆብንና ልጁን አጼ በዕደማርያምን በመራር ቋንቋ ቅጽል የክፋት ስም አውጥተው ይጠሯቸዋል፡፡ጥቂት እንሂድበት!

  (4.1) አባ እስጢፋኖስ ለመጀመሪያ ጊዜ አጼ ይስሐቅ ፊት ተከሶ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን ሲመክረው ‹‹…መጽሐፍ ‹እንግዲህ ንጉሦች አስተውሉ፤መሬትን የምትገዟት ሁሉ ተገሰጹ፤ለእግዚአብሄር በፍርሃት ተገዙ› (መዝ 2 ቁ 10) ይላል፡፡…ለእግዚአብሄር መገዛት ማለት ሕጉን በመፈጸም ራስክን እየጠበቅህ ሕዝቡንም በእውነትና በትክክል ማስተዳደርና በቅዱስ ሲኖዶስ እንደተሠራው ሥርዓት ካሕናት መንጋውን በትክክል እንዲጠብቁ፣ሕዝቡም እንደተደነገገው ለእረኞቻቸው እንዲታዘዙ፣መነኵሴዎች ፍጹም ለመሆን ለሚፈልጉ ወንጌል እንዳዘዘው ራሳቸውም በሰጡት ቃል እንዲቆሙ ሁሉንም በየሥርዓቱ ማደራጀት ነው›› በማለት ስለተቋማዊ አደረጃጀት ንጉሡን ያሳስበዋል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.87)፡፡ንጉሡ በሃይማኖት ጉዳይ ጠልቆ እንዳይገባና ስለራሱ ክብርም መጨበቅ እንዳያበዛ ‹‹ንጉሥ ሆይ መንግሥትህን ለእግዚአብሔር አምላክ አገልግሎት አድርገው እንጂ ለራስህ ክብር አይሁን፤…እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ለመንፈሳውያን በመንፈስ፣ለሥጋውያን በሥጋ የሚኖሩበት ሕግ ለሁሉም አወጣ፡፡ከየወሰናቸው እንዳያልፉም ትእዛዝ ሰጠ›› እያለ በለዘብታ ይመክረዋል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.93)፡፡

  (4.2) አባ እስጢፋኖስ የንጉሥ ቃል ገደብ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ገደቡም የእግዚአብሔር ቃል ነው(ገ.81)፡፡ለመነኰሳት በሥጋዊ ፍርድ መደመር እርም ነው ብሎ ይከራከራል፡፡ለሥጋ ገዢዎች ግን መፍረድ እንደተፈቀደላቸው ያምናል፤ያም ቢሆን ታዲያ ‹‹በሕጉ መሰረት በእውነት ፍርድ ነው እንጂ [ከሕግ ውጭ] አይደለም(ማቴ 19 ቁ 25)››(ዝኒ ከማሁ፡ገ.93)፡፡እነዚህንና ከላይ ያነበብናትን ‹‹ለመንፈሳውያን በመንፈስ፣ለሥጋውያን በሥጋ የሚኖሩበት ሕግ ለሁሉም አወጣ፡፡ከየወሰናቸው እንዳያልፉም ትእዛዝ ሰጠ›› የምትል አነጋገር ስናይ ደቂቀ እስጢፋኖስ የሴኩላሪዝም ጽንሰ-ሐሳብ ሳይኖራቸው አይቀርም ብለን እንገምታለን፡፡በሌላ በኩል የአጼ ይስሐቅንና የአጼ ናዖድን በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጡ ፍርዶች በእነሱ ላይ መገፋትን ስላስቀሩ በአዎንታ ሲመለከታቿው እንታዘባለን፡፡ለንጉሡ ሥልጣን መደንገጊያና መገደቢያ ብለው የሚጠቅሱት መዝሙረ ዳዊትን፣ወንጌለ-ማቴዎስንና መጽሐፈ-ሲኖዶስን መሆኑም ጨርሰን የሴኩላሪዝም አራማጆች የሚል ቅጽል እንዳንሰጣቸው ይይዙናል፡፡ከካሕናተ-ደብተራ ጋራ ሲነጻጸሩ ግን የንጉሡ ሥልጣን በእግዚአብሔር ቃልም ቢሆን ሊገደብ እንደሚገባው፣መነኰሳት በዓለማዊ ፍርድ መደብለቅ እንደሌለባቸው፣ማኅበራዊ ግንኙነቱ ሁሉ በተደነገገለት የሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት እንዲሆን ያላቸው አቋም ከዘመናቸው የተራመደ አስተሳሰብ እንደነበራቸው ሊያስቆጥርላቸው ይገባል፡፡የሰጊዷን ጉዳይ ሳንረሳ ንጉሡ በዚህ አስተሳሰብ ካልሄደ እንደንጉሥ ላያዩት እንደሚችሉ መገንዘብ እንችላለን፡፡

  (4.3) ደቂቀ እስጢፋኖስ እስከመጨረሻው ድረስ ለንጉሥ ዘርዐያዕቆብ መስገድን እምቢ እንዳሉ ነው ያለፉት፡፡እጅ መንሳትና አምልኮ ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው አይመስለኝም፡፡እርስ በርስ እጅ ሲነሳሱ አይተናላ!የእሱ አባባልም ቢሆን ‹‹እኔን ለሰጣችሁ አምላክ ስገዱ›› አለ እንጅ ቃል በቃል ‹‹አምልኩኝ›› አላለም፡፡ይሄ የጠፋቸው አይመስለኝም፡፡እነሱ የማይሰግዱለት ‹‹በሕግ የማሠራ አምባገነን ነው››ብለው ስለሚያምኑ ነው የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ማሳያ ላምጣ!በገጽ 185 ስለንጉሡ በነገረ-ፈጅነት የሚከራከሩት ካሕናተ-ደብተራ እና ደቂቀ እስጢፋኖስ ትንፋሽ የሚያቆምና የቅዱሳት መጻሕፍት ጥቅሶች የተዥጎደጎዱበት አስደማሚ ክርክር ያደርጋሉ፡፡በክርክሩ ማኅል ከካሕናተ ደብተራ ወገን የሆነው ነገረ-ፈጅ ‹‹ለንጉሡ ልምን አትሰግዱም፤ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው አክብረውት የለምን?›› ሲል ላቀረበለት ጥያቄ ደቂቀ እስጢፋኖሳዊው ወንድም ሲመልስ ‹‹ንጉሡ በሕግ የሚሠራ ቢሆን እንደምትሉት እናከብረዋለን፤ከሕግ ውጭ የሚሠራ ከሆነ ግን መምዕላይ[Dictator] ነው›› ሲል የማይሰግዱለት ሕግ ተከትሎ ስለማይሠራ እንጅ የአክብሮት ስግደት(እጅ መንሳት) ስለተከለከለ እንዳልሆነ ልባቸው እንደሚያውቅ ይጠቁመናል፡፡በሌላ አጋጣሚ እንዲሁ አንድ የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ሰላይ ስለንጉሡ ክርስትና ያላቸውን አመለካከት ሲጠይቃቸው ‹‹ሕግ ከፈጸመ ክርስቲያን እንለዋለን፤እኛ እንደምናየው ከሆነ ግን አንተም ታየዋለህ›› ይሉታል፡፡እነሱ እንዴት እንደሚያዩት ለማወቅ ይህ ጥቅስ ከሰፈረበት መስመር ዝቅ ብለን ስናነብ ‹‹ከሕግ ውጭ መሆኑ እውነት ነው፤ንጉሥ አይደለም›› ሲሉት እናገኛለን(ገ.156)፡፡በእነሱ ዘመን-የቀደመ ግንዛቤ ከሕግ ውጭ የሆነ ንጉሥ ‹በስም› እንጂ ‹በገቢር› ንጉሥ አይደለም!What an early outstanding conceptualization of rule of law!ሕጓን እንዴት አድርገው በልተዋታል አያ!እጹብ!

  ReplyDelete
 27. (4.4) እንዲህም ሆኖ ደቂቀ እስጢፋኖስ ንጉሡንም ሆነ ስለንጉሡና በእሱ ዘመን ስለተላለፉባቸው ፍርዶችና ውግዘቶች አፈጻጸም የሚያሳድዷቸውን ኃይላት በጭካኔ፣በስግደትና ከንቱ ውዳሴ ፈላጊነት እንጂ በሃይማኖት ህጸጽ ሲከስሷቸው አናይም፡፡ሲወቅሷቸውም ‹‹አሁን ዐውቀዋል፤ተረድተዋል፤ተረድተውም መጽሐፍ እንዳለው ዕውሮች ሆኑ›› በማለት በአውቆ አጥፊነት ነው የሚወቅሷቸው (ገ.155)፡፡ቤተክርስቲያናቸውን ሲያቃጥሉባቸው እንኳ ‹‹የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አጠፉብን፤ክርስቲያን ሆነው ሳለ በእሳት አቃጠሉት›› የሚል የትካዜና የብሶት ቋንቋ ይጠቀማሉ እንጂ የአሳዳጆቻቸውን ክርስትና አይክዱም፣አያነውሩም(ገ.256)፡፡በተረፈ አጼ ዘርዐያዕቆብንና ልጁን (አድማስ በፀር) እንኳንስ በእነሱ ላይ ስላደረሱት የጭካኔ ተግባር በ‹ደስክ› አማኞች ላይ ስለወሰዱት እርምጃ ሳይቀር እያነሱ ስለምግባራቸው ይዘልፏቸዋል(ገ.221)፡፡ያው እሱም በድርሰቶቹ በይሑዲነት እና በፀረ-ማርያምነት ያብጠለጥላቸዋል፡፡አንዳንድ ጎበዞችም የእሱን ክስ እንደወረደ ተቀብለው ደቂቀ እስጢፋኖስ ጋራ ለመዛመድ መከራቸውን ያያሉ፡፡ይቺን ጉዳይ ለብቻዋ በአዲስ ርእስ እንያት!

  5. ስለደቂቀ እስጢፋኖስ አይሑዳውያንና ፕሮቴስታንት ጸሐፍት ያላቸው ዕይታ!

  በእግዜር ስለማያምን ስሙን በዚህ ጽሑፍ የማንጠራለት ፈላስፋ እንዲህ አለ “The worst readers are those who behave like plundering troops: they take away a few things they can use, dirty and confound the remainder, and revile thewhole.” ምሬቱን እጋራዋለሁ!በገድል ጽንሰ-ሓሳብ የማያምኑ ሰዎች ከማያምኑበት ቅጽር ገብተው ጥቂት አርጩሜዎችን ቀጣጥፈው ከቀሰጡ በኋላ አርጩሜውን ተጠቅመው አርጩሜዎቹ ለምልመው የበቀሉባቸውን የግንድ ቅርንጫፎች እየጨፈጨፉ ስለዛፍ ቅርንጫፎ አላስፈላጊነት ሲሰብኩን እንገረማለን፡፡ይሕን ካልኩ በኋላ ወደ ይሑዲና ፕሮቴስታንት ጸሐፍቶቻችን ልመለስ--ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ስለጻፉት!በገድል መጻፍ አስፈላጊነት ሳያምኑ ገድል ጠቅሰው ስለሚከራከሩት!

  5.1 ደቂቀ እስጢፋኖስን እንደ ይሑዲ-ክርስቲያን?!

  (5.1.1) የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ድርሰት ነው ተብሎ በሚታመነውና ንጉሡ ደቂቀ እስጢፋኖስን በ‹‹ይሑዲነት›› እና ‹‹ፀረ-ማርያም››ነት ፈርጆ ጽፎበታል በሚባለው ‹‹መጽሐፈ ብርሃን›› ዙሪያ ሒሳዊ ጽሑፍ እ.ኤ.አ በ1973 ዓ.ም የጻፉት ታዋቂው አትዮጵያዊ-ይሑዲ(ቤተእስራኤላዊ) ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ በ15ኛ ክ/ዘ በሥላሴ የሦስትነት ጉዳይ ጥያቄ ያነሱ ዘሚካኤላውያንን በማየት፣በቀዳሚት ሰንበት አከባበር ዙሪያ ጥያቄ አንስተው ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኘላቸውን እነ አባ ኤዎስጣቴዎስን በማጥናት፣መጀመሪያ አካባቢ በነበራቸው አቋም ለመስቀልና ለእመቤታችን መስገድን እምቢኝ ያሉትን እነ አባ እስጢፋኖስ በመጥቀስ ያለጥርጥር ሁሉም አይሑዳውያን-ክርስቲያኖች ነበሩ እያሉ ይጽፋሉ፡፡ኧረግ!ብንል ‹እንዲያው እመኑኝ አትጠራጠሩ› <>ብለውን እርፍ (Ephraim Issac:p,69)

  (5.1.2) በእርጋታቸው፣በአረጋዊነታቸውና በትሑት አቀራረባቸው የምወዳቸው ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ አልተችለውም!የዘርዐያዕቆብ ዜና-መዋዕል እና የደቂቀ እስጢፋኖስ ገድላትም ይደግፉኛል፤ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ይሑዲነት እርግጠኛ ነኝ፤ስሙኝ ልንገራችሁ፤<<…we now can confirm our original conjecture that the Stephanites formed part of the Ethiopian Jewish Chiristian community that strictly kept the Saturday Sabbath and the law,refusing to worship anyone except God…›› ይሉና የእመቤታችንና የቅዱስ መስቀል ክብር በንጉሥ ዳዊት በኮፕቲክ ቤ/ክ አማካይነት ተዋውቆ በአጼ ዘርዐያዕቆብ ዘመን ተቋማዊ ቅርጽና ይፋዊ ሥርዓት እንዲኖረው መደረጉን ይገልጻሉ (Ephraim Issac:p,69-71)፡፡እንደእሳቸው አዝማሚያ ከሆነ ‹ተሐድሶ› ያመጣው ዘርዐያዕቆብ ሲሆን ደቂቀ እስጢፋኖስ ግን ነባሩን አይሑዳዊ-ክርስትና ለማስጠበቅ የቆሙ ‹ወግ አጥባቂዎች› ናቸው፡፡

  (5.1.3) የፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅን ጽሑፎች በምንጭነት የተጠቀሙት አባታችን ነፍሰኄር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በጥናታቸው <<…they are denounced as ‘Jews’…they may indeed have been followers of older Jewish Chiristian beleifs in Ethiopia which the king wanted to abolish.>>ይላሉ--ዋናው የደቂቀ እስጢፋኖስ ግጭት መንስኤ ‹‹የሥልጣን ነው›› የሚለውን አቋማቸውን ሳይለቁ ‹‹ይሑዲ›› መሆናቸው ግጭቱን አባብሶት ይሆናል የሚል መላምት በማከል(አቡነ ጳውሎስ፡ገ.262)፡፡የአቡነ ጳውሎስ ጥናት የተሠራው በደርግ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1988 ዓ.ም በስደት አሜሪካ ሳሉ በመሆኑ በደቂቀ እስጢፋኖስ በኩል የነበረውን አቋም ገድሎቻቸውን አመሳክሮ ለማገናዘብ እክል ሳይገጥማቸው አልቀረም ብለን በመገመት በርኅራኄ ካላለፍናቸው በቀር ‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስ አይሑዳውያን ነበሩ›› የሚለውን አቋም ሳይሞግቱ በማለፋቸው መውቀሳችን አይቀርም፡፡

  (5.1.4) ዘርዐያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ‹‹አይሑዳውያን›› ማለቱ በነገረ-ሃይማኖት ደረጃ የአይሑዳውያንን የእምነት መርሆዎች ተቀብለዋል ለማለት ሳይሆን የክሕደታቸውን መጠን አጕልቶ ቅጣቱን ለማክበድ፣በሕዝብና አሕዛብ መካከል የተጠሉ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ይሑዲነት ከሐዲስኪዳን በኋላ ያለው ታሪኩ ከጌታ ስቅለት ጋር እየተያያዘ ስለሚተረክ በኦርቶዶክሳውያን ደራስያን ለበጎ ስያሜ እንደማይውል ይታወቃል፡፡ምናልባት በአጼ ዘርዐያዕቆብ ዘመን ሞሶሎኒ እና ሂትለር ቢኖሩ ኖሮ ንጉሡ ደቂቀ እስጢፋኖስን ‹‹ፋሺት›› እና ‹‹ናዚ›› ሊላቸው እንደሚችል መገመት ነው፡፡ለነገሩ እነሱም ስም ለማውጣት አልሰነፉም ከሰብእና አውርደው ‹‹ድብፀር›› እና ‹‹ዝራጐን›› ብለውታል፡፡እነሱ እንዲያ ስላሉት ግን ዘርዐያዕቆብ ጅብ ወይም ደራጎን ነው ብለን ራሳችንን አናቄልም፡፡ለዚህ ነው የእስራኤላውያኑ ጸሐፍት እና ኋላ የምመጣባቸው የፕሮቴስታንት ጸሐፍት መደምደሚያ የሚያስገርመኝ፡፡እንዴት ተከሳሽን በከሳሽ ቃል ብቻ እንበይናለን!ዘርዐያዕቆብ ‹‹አይሑዳውያን ብሎ ስለከሰሳቸው ‹‹አይሑዳውያን ሳይሆኑ አይቀሩም››፤በፀረ-ማርያምነት ስለተከሰሱ ‹‹ፕሮቴስታንት ሳይሆኑ አይቀሩም›› እየተባለ ሲጻፍ ስናይ እንግዲያማ ‹‹እነሱም እሱን አያ ጅቦ፤ዝራጎኑ ስላሉት ጅብና ደራጎን ሳይሆን አይቀርም›› እንደማለት፤ወይም በሉቃስ 3 ቁ 23 አይሑድ የጌታችን አባት እ/ሔር ወልድ መሆኑ ስላልተገለጸላቸው ‹‹የዮሴፍ ልጅ›› እንዳስመሰሉት ይመስልብናል፡፡

  ReplyDelete
 28. 5.1.5) ደግነቱ ይሑዲው የቤተ-እስራኤል ታሪክ ጸሐፊ STEVEN KAPLAN <<… the most common usage of the term ayhud in medieval Ethiopia was as a description of Christian groups viewed … as heretical. This usage was especially popular in the time of the Emperor Zar’a Ya’eqob, who sought to purge the Church of many of its dissident elements as part of his program of religious nationalism.>>ብሎ ካብራራ በኋላ ምሳሌ ሲያቀርብም አጼ ዘርዐያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ‹‹አይሑዳውያን›› ያላቸው ልክ የገዛ ልጁ ዙፋኑን ሊገለብጥ በሞከረበት ወቅት እምነት አጉዳይነቱን ለመግለጽ በ‹‹አይሑዳዊ››ነት በከሰሰበት መልኩ መሆኑን ይነግረናል፤እንዲህ ሲል <>( STEVEN KAPLAN:p,215)::

  (5.1.6) STEVEN KAPLAN ያሰፈረው ፕ/ር ይሥሐቅ ላነሱትና አቡነ ጳውሎስ በቸልታ ላለፉት የደቂቀ እስጢፋኖስን እንቅስቃሴ ከ‹‹ከይሑዲ››ነት ጋር የሚያያዝ አተያይ በቂ ማስተባበያ ይመስለኛል፡፡በተረፈ ከሐዲስኪዳን ጋራ ያልተጣረሱ፣በግልጽ ያልተከለከሉና ከሐዲሱ ጋር ተጣጥመው የቀጠሉ የኦሪት ትውፊቶችን፣ሥርዓታትን፣የቤተመቅደስ መገልገያ ንዋየ-ቅድሳትን፣የአኗኗር ዘይቤዎችን፣የካሕናትና የደባትር የሲመት እና የአለባበስ ይትበሐሎችን የምንጠቃቅስ ከሆነ ደቂቀ እስጢፋኖስን ብቻ ሳይሆን መላዋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ወደ ‹‹አይሑዳዊ››ነት እንዳናወርዳት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡በደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ የገነኑት እነ አባ ዕዝራ የዘር ሐረጋቸውን ‹‹ከጽዮን ጋራ ከወጡ ከሌዊ ነገድ›› ተያይዞ ስለተተረከና (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.283)፣አባ አበከረዙን የጳውሎስን 2ኛ ቆሮ 2 ቁ 11 ጠቅሶ ስለንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ሲናገር‹‹እኔም እንደነሱ እብራዊ ነኝ›› ስላለ(ዝኒ ከማሁ፡ገ.276)፣ቀዳሚት ሰንበትን ስለሚያከብሩና ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምን ለመሳለም ስለሚጓዙ(ዝኒ ከማሁ፡ገ.288 እና 289) ይሑዲ ነበሩ ለማለት መፋጠን፤በግልጽ በቅድስት ሥላሴ እንደሚያምኑ (ገ.289) እየተናገሩ፣ሰጊድንም ቢሆን መጀመሪያ ለመስቀልና ለእመቤታችን ለመስገድ ቢያወላውሉም ኋላ ከመስገዳቸውም በላይ ለሥሉስ ቅዱስ ስዕል ስላለመስገዳቸው ማስረጃ ባልቀረበበት እንዲሁም ከአይሑዳውያን በተለየ ቅዱሳት ስዕላትን በገድሎቻቸው በስፋት ማኖራቸው እየታወቀ አይሑዳውያን ነበሩ ማለት ተአማኒ አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete
 29. እውነቱ ይነገር ይሰማ!November 12, 2015 at 7:36 AM

  ማቆች!!! ይህን ሳይበላ እያበላ ያስተማረንን የዋህ ወገናችንን ማታለለ ትችሉ ይሆናል:: በግብር አባታችሁና የቤ/ከርስቲያናችን ዋና አፍራቪና ጠላት በሆነው በዘርዓያዕቆብ ሙት መንፈስ እየተመራችሁም ችላችሁዋል፤ አሁን ግን ለሕዝባችን የራራው ጌታ በወንጌሉ ጠላት ላይ ጨክኖ ስለተነሳ በክፉው ተነድታችሁ ማታለል ፈጽሞ አትችሉም። ተሐድሶ ማለት ቤ/ክርስቲያናችን ወደ ቀደመው የእግዚአብሔር ወንጌል ጅማሬዋ ትመለስ ማለት እነደሆነ አብዛኛው ሕዝብና ጳጳሳት ሁሉ እየተረዱ ስለሆነ!

  መርዶ ልንገራችሁ እናንተን ይጋልብ የነበረ የህዝባች/ያገራችን ጠላት በወንጌሉ እሳት እየተቃጠለ በመውጣት እናንተም ጭምር ከደብተራ መንፈስ ነጻ ወጥታችሁ የመንግሥቱን ሥራ አብረን በሰማይ ፍቅር በቁጭት እንደምትሠራ በእምነት እንናገራለን። ዓላማችንና ሥራችን ሰው ሁሉ እንዲድን ፈቃዱ/ከጥፋት ልጅ በስተቀር/ የሆነ የፍቅር አምላክ ያዘዘንን ትእዛዝ በመንፈሱ እየተመራን ማድረግ ስለሆነ!የፍቅር ልጆች የፍቅርን ቃል ይናገራሉ በፍቅርም ይሠራሉ!የክፉው ልጆች ደግሞ እንደ አባታቸው የስድብ አፍ ተሰጥቶዋቸው ክፉና የመር ቃል መናገር ባህሪያቸው ነው። ከዚህ ተፈጥሮአችን ካልሆነ የክፋት ባህሪ ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ ይፈውሰን! የገባው አሜን ቢል ይጠቀማል።

  ወደዳችሁም ጠላችሁም እግዜር ራሱ በፈቀደውና በደነገገው መንገደ(ኢየሱስ በሚባል ብቸኛ መንገድ)ይመለካል እንጂ ሰው ሠራቪ በሆነ ሃይማኖትና ባህል ፈጽሞ አይመለክም። በከንቱ ደክማችሁ ሕዝባችንን አታድክሙት ደግሞም ወደ ሞት አትንዱት??? በሚጠፋ ክብርና ሃብት ተመን የሌላትን ነፍስ አትመዝኑ። እስቲ ቆም በሉና መንገዳችሁን ፈትቩ?እስከ መቼ ድረስ መንገዳችሁ የኤማሁስ መንገድ ብቻ ይሆናል? ማስተዋል ይብዛላችሁ ጌታ አእምሮአችሁን ይክፈትላችሁ (ሉቃስ 24፡45)

  በተወደድንበት ፍቅር በእውነት እንወዳችሁአለን
  የክፋታችሁንና የጥላቻችሁን ምንጭና ባለቤት የሆነውን ግን እጅግ እንጸየፈዋለን!
  እስከ ነፍሳችን ህቅታም በጌታ ስም እንዋጋዋለን
  ወዳችሁም እንዳልሆነ ይገባናል።

  ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያናችንን ሙቪራዋ ያግኛት

  እውነቱ ይነገር ይሰማ

  ReplyDelete
 30. MARK ALECHIH ENATIH MESLEWAT ARU BILENEHAL EGREMENGEDE DEBREBIRHAN HIGE BIRHAN YEWEREDEBET BOTA MIKT TEDERGOBET AYEHU YEMEBREK BILCHITA ENGINE BIRHAN WERDO AYAWKIM BETELEY EZABOTA MINIM ALWEREDEM YEAROGITOCH WE'RE NEW NGEREGNI KALKEGN HOD SIYAWK DORO MATA NEW

  ReplyDelete
 31. Maru yetebalkew betikiklegna simh ARU DEKIKE estifanos le,Emebetachinna Lemsekel Ansegdim bemaletachew Ayhudawayan Nachwe Menafikan nachwe bileh Medemdemiya Lemestet Maseregna Bemalet Yakerebekew Yeshewa Debteroch Gitm (Tese yibl Afekrechi We,Eyafekr Teamrechi krstiyanawi Ikrstun wietu Ayhudawi Wesrtse Estifa Hasawi) min AYNET Sigdet New EMBI YALUT LEAWAKIWOCH ( LE,ELU FITURANIN SIGDETE FETARI YIDELWOMU ESMETEAREU BKIBROMU) LEMILEW YEKAHNATE DEBTERA GITM SAYHON YERAYAEKOB KANAT YETESASATE YETEGANENE YETEDERSE DIRSETNEW TEBACHEW METSIHF KIDUSM LEFTURAN SIGDET AYFEKDIM YIFKDAL? KETEAMR WICH Tikes MESKELM MARYAMIM KFETARI GAR EKUL AYDELUM YEFETARI SIGDETIM AYSEGEDLACHEWM (LEEMEBETACHIN YEMISEGEDEW SIGDET Yetsega Yeakbrot Sigdet New Yefetari sigdet Le.and FETARI bicha new LEMSKELM ENSGDALEN MIKNYATUM WENSEGD WISTE MEKAN HABEKOME EGRE EGZIENE SLEMIL MESKEL LAYMA MEKOM AYDELM LEALEM MEDHANIT YEHONECH DEMU SILEFESESEBET NEW SLEZIH MARU SAYHON SIMH ADENKURU.ARU NEH BIZU METSAFIH BIZU ALEMAWEKIH YIGLTSAL DEKIKE ESTIFANOS LEFETARINA LEFITURAN ANDAYNET SIGDETE AYGEBAM LEFETARI YEAMLKOT LEFITURAN YEAKBROT SIGDETE MALETACHEWNA YAZAN GIZE YENE HAILE GIYORGIS MEMHIRAN KFETARI EMEBETACHI TIBELTALCH YEMIL ASTEMHRO ENANTE ENDALACHIHUT BEDEBREBIRHAN YASTEMARU SILENEBER NEW WOY GOOD (LEFETARINA LEFTURAN ANDAYNET SIGDET ASAFARI NEH MARU ORTHODOX NEGN BILEH ATSAF ADIS HAYMANOTE KEHONE YEMITKETELWE LEAMAGNOCHIH TEDEBIKEH TSAF MAFERYA

  ReplyDelete
 32. የሉተራውያን ተረታ ተረት አእምሮህን ያሻገተው ከላይ ለመሳደብ የሞከርከው ሉተራዊ መናፍቅ፣ የፍፃሜ ዘመን ሀሳዊ መሲህን ለመቀበል በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ያለው ሰይጣናዊ ፕሮቴስታንቲዝም አቀንቃኝ የሆነከው በቁምህ ለሞትከው ግብዝ፣ ቢመርህም እውነቱን ዋጠው፣ ያለ ድንግል ክርስቶስ የሚባል የለም። ክርስትና ያለ እመ እግዚአብሄር የለም።

  ReplyDelete
 33. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:30 PM

  ከ፡-በአማን ነጸረ(በሰላማ መድረክ የተሳትፎ ስሜ hiruy)
  ይህች ጽሑፍ በፌስቡክ ገጼ ላይ የለጠፍኳት ነበረች፡፡ወንድም ማሩ ከበደ ወዲህ አምጥቶ በመለጠፉ አልከፋኝም፡፡ደስ ብሎኛል፡፡የበለጠ ደስ እንዲለኝ ስሜን ቢጠቅሰው መልካም ነበር፡፡ሲለጥፍ ዋናውን ክፍል(ክፍል-3ን)ትኩረት ቢያደርግም የበለጠ ጥሩ ነበር፡፡ዞሮ ዞሮ በኦርቶዶክሳዊ ቀና መንፈስ ተነሳስቶ ጽሑፉን በመለጠፉ ደስተኛ መሆኔን ልግለጽ፡፡የድንግል ልጅ ከረዳኝ ይችን ጽሑፍ መጠነኛ ማሻሻያ አድርጌ ከሌሎች ስራዎች ጋራ በመድብል መልክ እንድትወጣ መሞከሬ አይቀርም፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስ ፕሮቴስታንት እንዳልነበሩ፣በአሁን ዘመን በስማቸው ከሚነግዱ ተሐድሶዎች ጋራ የመንፈስም ሆነ የመርህ ቁርኝት ፈጽሞ እንደሌላቸው አያሌ ማስረጃዎች ስላሉ እሱን ገሐድ ለማድረግ የፈጠረን እስከፈቀደልን ድረስ እንሄድበታለን፡፡ለአሁኑ ግን ከማሩ ከበደ የተረፈውንና በፌስቡክ ገጼ ላይ ያለውን ጽሑፍም አንባብያን ሳይታክቱ እንዲመለከቱት በኦርቶዶክሳዊት ትሕትና ልጋብዝ፡-
  ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ አቋም… ባለቺን መነጽር፣እናነጻጽር፤4ቱን አንጻር!!
  ክፍል-3፤የመጨረሻው ክፍል!
  5.2 ደቂቀ እስጢፋኖስ ፕሮቴስታንት ነበሩ?በአይቴ ሐሊፈኪ?
  ይሄኛውን ርእስ ጥበብ በተሞላበት ንግግሩ ነፍሴን ፍጹም በተመስጦ የሚወስዳትና የቋንቋ አገላለጽ ውበቱ ጥሜን የሚቆርጥልኝ አባ አበከረዙን በገድሉ ገጽ 216 በተናገራት ፍጽምት ኦርቶዶክሳዊት ቃል ልጀምር፡፡እሱ ‹‹ከድካማቸው ጋር ሳትደክም ቅዱሳን አባቶቻችንን ለመምሰል አትድከም›› ይላል፡፡ይቺ ቃል ምናኵስናን እና የምናኔ ሕይወትን እያጣጣሉ መነኰሳቱን (ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን) አባቶቻቸው ለማድረግ ለሚታገሉ የዘመኑ ፕሮቴስታንት ወንድሞች አካሄድ ሸጋ ተግሳጽ ናት፡፡የአባ አበከረዙንን አባባል በቅዱስ ጴጥሮስ አባባል አጥብቀናት እንለፍ፡ቅዱስ ጴጥሮስ በ2ኛ መልእክቱ ምዕራፍ 3 ቁጥር 16 ‹‹ወእለሰ አልቦሙ ትምህርት፤ወእለ ኢለበው ይመይጥዎ ለቃለ መጽሐፍ….ያልተማሩና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎች መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ››ይላል፡፡የገድል አጻጻፍ መውጫና መግቢያ ሊያውቁ ቀርቶ ጆሮአቸውን ቢቆርጡዋቸው ልሳነ-ግእዝ የማይሰሙ ፕሮቴስታንት ጸሐፍት ገድለ-ደቂቀ-እስጢፋኖስን እንዳይሆን አድርገው ቆነጸሉት፡፡ሳያምኑበት ተርጕመው ለአጀንዳቸው ማቀጣጠያ አደረጉት፡፡ዓለምአቀፉ ሚዲያም በእነሱ ስፖንሰሮች የተቃኘ ነውና መነኰሳቱን ባልዋሉበት የሉተር ሜዳ አዋሏቸው፡፡እግዜር ይይላቸው!
  የፕሮቴስታንት ጸሐፍት ሲደንቀን የግእዝ ዘይቤ ተምረናል የሚሉና በኢኦተቤክ ጉባኤ ቤቶች አልፈው ዛሬ ማሊያ ቀይረው ለተቀናቃኝ ቡድን መጫወት የጀመሩ ‹‹ስመ-ተሐድሶ ቁንጽሎች››ም ታማኝነታቸውን ለማሳየት ሲሉ ፍጹም ኢ-ስነምግባራዊ ቃላት እየተጠቀሙ ያደጉባትን፣እስልምና በገነነበት የምስራቅ አፍሪካ ተራሮች መካከል በአስደናቂ መንገድ ተጋድሎ ፈጽማ ከነክብሯ የኖረችውን፣ቅዱስ መጽሐፍ በምልዐት ተርጕማ ያቆየቻቸውን እናት ቤተክርስቲያን በሎሌነት ለአዲስ ጌታ አድረው ለማነወር አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ዐይኖቻችን ዐዩ፡፡ደቂቀ እስጢፋኖስን ተገን አድርገው ብዙ ጸያፍ ቃላት ሰነዘሩ፡፡በበራሪ ጽሑፍ፣በመጽሐፍና በብሎግ ታማኝነታቸውን ለማሳየት ከፕሮቴስታንታውያን በላይ ፕሮቴስታንት ሆነው ግዳይ ጣሏት፡፡ይሁና!ግዴለም!ከmessanger boys ጋር ንግግር የለንም፡፡ጌቶቻቸውን ግን እንደሚከተለው መረር ብለን እንሞግታለን፡፡
  (5.2.1)በwikipedia፣በአፍሪካ ፕሮቴስታንታዊ ክርስቲያኖች ዙሪያ በሚዘግበው dacb.org፣በቃለሕይወት ቤ/ክ የታሪክ መጽሐፍ ደቂቀ እስጢፋኖስ ሉተርን ያስናቁ ቀዳምያን ፕሮቴስታንቶች ተደርገው ቀርበዋል፡፡በተለይ የቃለሕይወት ቤ/ክ የቲዎሎጂ ኮሌጅ በሆነው በEthiopian Graduate School of Theology (EGST) ውስጥ "Biography of 'Hadege Anbesa' (Abba Stephanos) of the Orthodox Church,” በሚል ርእስ ወረቀት የሰሩ ‹‹መስፍን ሸጉየ›› የተባሉ ግለሰብና ቀደም ሲል በአ/አ/ዩ ፕሮፌሰር ሆነው ከጡረታ በኋላ ለdacb.org ጽሑፍ ሲያዋጡ የነበሩ ‹‹ድርሻዬ መንበሩ›› የተባሉ እንስት ምሁር ‹ደቂቀ እስጢፋኖስ ፕሮቴስታንታውያን ነበሩ› የሚለው አነጋገር ወንዝ የተሻገ አሉባልታ እንዲሆን ደክመዋል፡፡ድካማቸው ህጸጽ በዛበት እንጅ!
  (5.2.2) የደቂቀ እስጢፋኖስን ታሪክ ‹‹ተቀጣጥሎ የከሰመ ወንጌላዊ መነቃቃት›› በሚል ርእስ አንድ ምዕራፍ ሰጥተው ልክ እንደራሳቸው ቤ/ክ ታሪክ የጻፉት የኢ/ያ ቃ/ሕይወት ቤ/ክ ታሪክ ጸሐፊዎች የአባታቸውን የማርቲን ሉተር ሲኒየር እንቅስቃሴ በታላቅ አድናቆት ሲተርኩ ከቆዩ በኋላ ‹‹…ከዓለም ቤተክርስቲያን ታሪክ ወደ አገራችን መለስ ስንልም ልማዳዊ ከሆነው አካሄድ ወንጌላዊ ወደሆነው እምነት የተራመደ የጎላ እንቅስቃሴ የተከሰተበት ጊዜ ነበር፡፡…ይሕ እንቅስቃሴ ‹ደቂቀ እስጢፋኖስ› ተሰኝቶ በጀማሪው እስጢፋኖስ ስም ተከታዮቹ ያወጡት መጠሪያ ነበር›› ብለው የራሳቸው ያልሆነውን ታሪክ በቀሳጢነት ለመውረስ ይፋጠናሉ(ወንድዬ ዓሊ፡ገ.23)፡፡በመቀጠልም ‹‹…እንግዲህ እስጢፋኖስ ከሞተ ከ100 ዓመታት በኋላ ነበር የምዕራብ አውሮጳ ተሐድሶ የተጀመረውና ቆይቶም ወንጌላዊ እምነት ወደ አገራችን እንደገና የገባው›› በማለት ምጥ ለእናት ማስተማር የማይታክታቸው ወንድሞቻችን አባ እስጢፋኖስ ከመነሳቱ በፊት ወንጌል እንዳልተሰበከ የሚያስመስል የተለመደ መመጻደቅ ያስንብቡናል (ወንድዬ ዓሊ፡ገ.28)፡፡‹‹ወግ ወጉስ ተይዟል›› አሉ አለቃ ገብሐና!
  (5.2.3) ከላይ ፕ/ር ጌታቸው በኅዳግ ማስታወሻቸውና በመግቢያቸው ደቂቀ እስጢፋኖስን ከሉተራውያን ፕሮቴስታንቶች ጋር ለማዛመድ የሚቃጣቸው አገላለጾች ሳነሳ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፕሮቴስታንት ጸሐፍት ስለደቂቀ እስጢፋኖስ የሚያነሷቸውን የተሳሳቱ ነጥቦች ነካክቻቸዋለሁ፡፡በተለይ ስለስግደቱ እና ስለሰሎሞናዊ ዘር ጉዳይ አልመለስበትም፡፡የተቀሩትን በስሱ ልያቸው፡፡ፕሮቴስታንቶች በዋናነት ደቂቀ እስጢፋኖስን ‹‹አባት›› ለማድረግ የሚያነሷቸው ነጥቦች ደቂቀ እስጢፋኖስ ልክ እንደፕሮቴስታንት፡- (1)ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያሉ አዋልድን አይቀበሉም/አይጠቀሙም፣(2) መዳን ‹‹በማመንና በምግባር ሳይሆን ‹‹በማመን በሚገኝ የእ/ሔር ጸጋ ብቻ ነው›› ብለው ያስተምሩ ነበር፣(3)ታቦት አይቀበሉም፣(4)አረማውያን ቤ/ክ እንዲገቡ ይፈቅዳሉ፣(5)በሞተ-ሥጋ ለተለዩ ቅዱሳን አይጸልዩም የሚሉ ናቸው፡፡እንዲህ አድርገው ካመቻቹ በኋላ አባ እስጢፋኖስን "the first African Protestant" እያሉ መፎከሪያ ያደርጉታል፡፡ውይይይ!አሁንስ ነደደኝ!እነዚሕን ድውያን መደምደሚያዎች እናበጥራቸው!ለነዚህ አነጋገሮች መጽሐፍቅዱስ አልጠቅስም፡፡ሰዎቹ ያለሜዳቸው ገብተው ዘባርቀዋል፡፡በተጠቀሙት ገድል ተጠቅመን ሓሳበቸውን በክብር ለመሞገት እናነጣጥራለን!ስለዚህ ፕ/ር ጥቂት ቢያስቀይሙኝም ስለትርጕማቸው የማያቋርጥ ምስጋናዬን እየቸርኩ ከገድላተ-ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚመዘዙ የመልሶ ማጥቂያ አጸፋዊ ፍልጻዎቼን ላስወንጭፍ--እንዳቅሚቲ!ሰው ባለው ነው!

  ReplyDelete
 34. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:32 PM

  5.2.4 እውን ደቂቀ እስጢፋኖስ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ›› ባዮች ነበሩን?
  (5.2.4.1) በአዋልድ አጠቃቀም ረገድ ሲጀመር ደቂቀ እስጢፋኖስ እንደ ፕሮቴስታንት መጽሐፍ ቅዱሳቸው 66 ብቻ አይደለም፡፡81ዱ ነው(ገ.296)፡፡በአቡነ እስጢፋኖስ ገድል በገጽ 66 መጽሐፈ ሲራክ፣በገጽ 77 መጽሐፈ ሲኖዶስ፣በገጽ 78 መጽሐፈ ሄኖክ ተጠቅሰው እናገኛለን፡፡አባ እስጢፋኖስ በገጽ 93 ስለሳጥናኤል ከክብሩ መውረድ ለማስረዳትና የአባ ሲኖዳን የምንኵስና ኪዳን ሻሪነት ለማሳየት ተአምረ ኢየሱስን ይጠቅሳል፡፡ፕሮቴስታንት ጸሐፍት አባ እስጢፋኖስ ‹‹Bible Only›› የሚል ነው ሲሉ በሌለ ተዛምዶ ሊዛመዱ ሲጎትቱት ደግሞ ‹‹የአበው መጽሐፍ ለመነኵሴ ሞትንና ስቅለትን ተስፋ ከማድረግ የሚበልጥበት የለም ያለውን አልሰማህምን?›› ይላቸዋል (ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.102)፡፡እነሱ አያ!ኧረ!አልሰምተውም!አባ እስጢፋኖስ ምን አጩዋጩዋኸው!እነ እንትናዬ ‹‹የአበውን መጽሐፍ›› የት ያውቁትና፤ባይሆን እኛው እንስማው!
  (5.2.4.2) እኔ ያነበብኳቸው ሁሉም ፕሮቴስታንታዊ ጽሑፎች በደምሳሳው ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ቢተርኩም ብዙ ጊዜ ከገድለ እስጢፋኖስ ተራምደው አይሄዱም፤በጣም ጎበዝ ነን ያሉት ወይም ዘርዐያዕቆብን በቅጣቱ መሪርነት ሰበብ ለማጣጣል ብቻ አልመው የሚነሱት ደግሞ ከገድለ አበው ወአኃው አልፈው አያነቡም፡፡የአባ አበከረዙንና የአባ ዕዝራ ገድላት አንድ መስመርም አያነቧቸውም፡፡ቢያነቧቸውም ስለይዘታቸው ትንፍሽ አይሉም፡፡ገድላቱ በፍጹም ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎች የተሞሉ ናቸዋ!ለቁንጸላ አይመቹም!2ቱን ገድላት በተለየ ሁኔታ ሊደፍሯቸው የሚሞክሩት አይሑዳውያን ጸሐፍት ናቸው፡፡ፕሮቴስታንቶቹ ያውቃሉ!አባ አበከረዙንን ‹ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ መጽሐፍ ያስፈልጋል?› ብለው ምስክርነት ቢጠሩት ከአቤል ጀምሮ እስከ ጌታችን የተነሱ የታላላቅ አበውን ዜና መጽሐፈ ኩፋሌን እያጣቀሰ ሲዘክር ይቆይና ‹‹…‹ከጌታችንም በኋላ…ጴጥሮስ ተሾመ፤ከሱ ቀጥሎ ቀሌምንጦስ…ከጳውሎስ በኋላ ጢሞቴዎስ…ከነሱ በኋላ ሊቃውንትና የቤተክርስቲያን መምህራን ተነሡ፡፡ጽድቅ እንደዚህ በየትውልዱ ከጻድቃን ወደ ጻድቃን ነፍስ ትሸጋገራለች፡፡የእግዚአብሔር ነፍስ ለትውልደ-ትውልድ ነች እንጂ ያንድ ጊዜ ብቻ አይደለችም፡፡ከነሱ በኋላ ደግሞ በዘመናችን በትግላችን ጊዜ ረዳት እንዲሆነን እግዚአብሔር አቡነ እስጢፋኖስን አስነሳልን፡፡› ይኸንን ካለ በኋላ ዝክራቸውን ያነሳው ጻድቃን ያሉባቸውን መጻሕፍት አንብቡ አለ››ይላቸዋል(ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.271)፡፡ዘመዶቻችን ‹‹የጻድቃን ዝክር ያለባቸውን መጻሕፍት›› ማንበብ የሚያበረታታ አባት ‹‹Bible Only›› የሚያምን ብለው ከተቀበሉ ‹ወንዶች በጭብጨባ፤ሴቶች በእልልታ› ታላቅ አቀባበል እናደርግላቸዋለን!
  (5.2.4.3) በአባ አበከረዙን ገድል ገጽ 273 ከፊልክስዩስ ገጽ 219 የተወሰዱ 3 የነፍስ በረከት የሚያስገኙ ተጋድሎዎች ተጠቅሰዋል፡፡ምንኵስና፣ሰማዕትነት እና ጽሞና!በገጽ 276 የአባ መቃርስ ሕይወት ለማስተማሪያነት ሲያገለግል እናነባለን፡፡በገጽ 264 ስለሥርዓተ-ምንኵስና ‹‹የሥርዓታችሁ መጀመሪያ [1]ነፍስን መጣል፣[2]ፍላጎትን መተው፣[3]ገንዘብን አለማከማቸት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡እነዚህ 3ቱ የነፍስ ሕንጻ መሰረቶች ናቸው››ይላል አባ አበከረዙን፡፡ዘመዶቻችን ሥርዓትና ወግ ለሚሉ ቃላት ብዙም ቁብ ያላቸው አይመስለኝ!በ66ቱ መ/ቅዱስ ያልተጻፈ ሁሉ ‹‹ተረት›› አይደል!አባ አበከረዙን ይህን ስብከት የወሰደው በኢትዮጵያ ገዳማዊ ሕይወት ከግብጻውያን ይልቅ እጅግ የበረታ አሻራ አላቸው ተብሎ ከሚገመቱት የሶርያ ጽኑኣን/ጽኑኣት ማኅበረ-መነኰሳት ነው ብለን መከራከር ይቻላል፡፡ምክንያቱም እነሱም <>እንደሚሉ ከዌብሳይታቸው ያነበብን ሲሆን ስለበጎ ተጽእኖአቸው ደግሞ የኢ/ያን ምንኵስና ያጠኑ ሁሉ ተናግረዋል፡፡ፊልክስዩስም አመጣጡ ከሶርያ ነው፡፡ጓዶች ይህን የመሳሰለ የመጽሐፈ-መነኰሳት አጠቃቀስ ካላቸው ደስታ መሞታችን ነው!ግን አልመስሎኝም!ለተጨማሪ መረጃ ቅድስተ አርሴማን የሚያነሳሳውን የንግስተማርያም ተጋድሎ ከገጽ 127፤እንዲሁም ህጻኑን ቅዱስ ቂርቆስን አርአያ አድርገው ገድላቸውን በጥብዐት ለመፈጸም የተዘጋጁትን አኃው ምንባባት ከገጽ 199 ጋብዘን እንለፍ!

  ReplyDelete
 35. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:35 PM

  5.3.5 ደቂቀ እስጢፋኖስ ስለመዳን ትምህርት ምን ይላሉ?
  (5.3.5.1) weak-ፒዲያዎች (weak የምትለዋን ጽርፈታዊ ቅጽል እኔ ነኝ የሰጠኋቸው) ‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስ ስለነገረ-ድኅነት ሲያስተምሩ መዳን የሚገኘው በእ/ሄር ጸጋ እንጅ በምግባረ-ሠናይ እንዳልሆነ ይናገሩ ስለነበር sola gratia-መዳን በእምነት ብቻ ከሚለው ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ጋር ይዛመዳሉ›› ብለው ባልዋሉበት አውለዋቸዋል፡፡ምንጫቸው ፕሮቴስታንታዊቷ የቃለሕይወት ቤ/ክ ጸሐፍት ናቸውና አይገርመንም!አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ!አባ እስጢፋኖስን ‹‹አባታችን›› ቢሉት ‹‹ልጆቼ›› አይላቸውም፡፡ያላለውን ነዋ የሚሉት!እሱ ስለመንኖ ጥሪት ‹‹ወፎች ሲያባርሯቸው በቀላል ይበራሉ፤ምክንያቱም የሸክም ክብደት የለባቸውም፡፡እናንተም እንደዚሁ…ሳታከማቹ ነሩ›› እያለ ይሰብክ ነበር(ገ.77)፡፡እንጂ ‹‹አምኛለሁ፤ጸድቄያለሁ›› ብሎ ተዘልሎ እና ተደላድሎ ጫንቃውን ሲያሳብጥ አልኖረም!
  (5.3.5.2) በእሱ እምነትማ ለመዳን ማመን ብቻ ሳይሆን መታዘዝም ግድ ነው፡፡አባ እስጢፋኖስ እንዲህ ያለስሙ ስም ሰጥተው በስሙ ስለሚነግዱ አስተማሪዎች የተናገረው የሚመስለኝ ስብከት አለው፡፡እስኪ እንስማው፡- ‹‹እነሱ ራሳቸውን ለእግዚብአሄር ትእዛዝ ለማስገዛት ካልፈለጉ ሌላው ለእግዚአብሔር እንዳይጠመድ ለምን ይከለክላሉ? ‹ልጆቻችን ናቸው› የሚሉት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሳያስተምሯቸውና ከኃጢኣት የመዳኛ ጸጋ ሳይሰጡዋቸው እንዴት ልጆቻቸው ሆኑ?እነሱስ ቢሆኑ ራሳቸውን ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለተከታዮቻቸው ለመነኰሳት አባቶች ለእንጦንዮስና ለመቃርስ ትእዛዝ ሳያስገዙ የአባትነትን ስም እንዴት ወለዱ?››ይላል(ገ.81)፡፡እንዲያው ዘመዶቻችን ገድል ጠቅሰው ለመጻፍ ሲጥሩ ለምን አናግዛቸውም ብለን እንጂ ነገሩማ ‹‹ሃይማኖት ያለምግባር ያድናል›› ብሎ ቢያምን ኖሮ ዱር ለዱር ምን አደከመው?!‹‹ልጆቹ ከወጣላቸው ቀኖና ጋራ ልባቸው በሚዛን ላይ እኩል እስኪሆን ድረስ ኑሯቸው በቃልም በምግባርም ትክክል እንዲሆን›› በመጎብኘት ለምን ደከመ(ገ.96)!?
  (5.3.5.3) ኧረ እኔስ ምን አደከመኝ!እነ sola gratiaን ደቂቀ እስጢፋኖሳዊው አባ አበከረዙን ቀንድ ቀንዳቸውን ይልልኝ የለ!‹‹ጣሊያን ተፈጠመ ባመጣው እርሳስ›› አለ አቅራሪው!ቀጥልማ ጠቢቡ መንኵሴ--የ‹አዋኪ አዋቂዎቻችን›ን ቁልል ትምክህት አፍርስልኝ፡- ‹‹…ዕውቀት ብቻውን ሰውን አይጠቅመውም፣ምግባርም ያለመዓዛ አይጠቅምም፡፡ዕውቀት በምግባር ሲጣፍጥ ብዙዎች በመዓዛዋ ይሰበሰባሉ፡፡የክርስቶስ መንጋዎች ልብ ስላላቸው መዓዛ ያለውን እረኛ ይከተላሉ፡፡አሁንም በመጀመሪያ መዓዛችሁን አሳዩ፤አለዚያ በከንቱ አትድከሙ፤ለሰውም እንቅፋት አትሁኑ፤የጽድቅ ሥርዓት በሥራ እንጂ በነገር አይታነጽም፡፡….መጀመሪያ ስለሃይማኖት ስለምግባር ስለመፈቃቀር አስቡ፡፡ሃይማኖት ትረዳለች፣ምግባር ታስችላለች፣ፍቅር ፍጹም ታደርጋለች፡፡››(ገ.264)፡፡እዚህ ላይ ከቶ ምን እንጨምራለን!እሱ እንዳለው ‹‹የጽድቅ ሥርዓት በሥራ እንጂ በነገር አይታነጽም›› እና ነገር አናበዛም፡፡
  (5.3.5.4) በ‹‹ኰኵሐ ሃይማኖት›› መጽሐፋቸው የመናፍቃን መዶሻው መልአከብርሃን ዓድማሱ እንደተናገሩት እነ አባ አበከረዙን ክርስቶስን የተከተሉት ‹‹በእግር›› አይደለም፤‹‹በግብር›› እንጂ!የአባቶቻቸውን መሰረት እየናዱ አይደለም፤ባለው ላይ እያነጹ እንጂ!ናማ!አባ አበከረዙን ናማ!ንገርልኝ፤ለሥርዓት ዘንጣዮች ሥርዓት አስተምርልኝ፤መድረኩ ያንተ ነው፤አንተ ተናገር፤እኛ እንስማ፤ስሙ፡- ‹‹ መነኵሴዎችም ሆናችሁ መነኵሲቶች በመንፈሳዊ አባታችሁ ሥርዓት እንዳላችሁ ብትሞቱ ይሻላችኋል፡፡መጽሐፍ ‹ካብ የሚንድን እባብ ይነክሰዋል› ይላል፡፡እንደዚሁ አሁንም ወደ ፈተና እንዳትገቡና የመንፈሳዊ አባታችሁን ሥርዓት እንዳትንዱ››(ገ.268)፡፡በዚህ ቃለ-ምዕዳን ላይ ሌላ ነገር መጨመር ድፍረት እንደሆነ ይገባኛል!ቢሆንም ስለአባ አበከረዙንና ስለተወለደበት ማ/ሰብ ክብር አንዲት የትግርኛ አባባል ልጥቀስ፡-‹‹ሃይማኖት ብዘይ ግብሪ፣ጸሎት ብዘይ ፍቕሪ፣አይፈቱን ፈጣሪ…ትርጉም…ሃይማኖት ያለምግባር፣ጸሎት ያለፍቅር፣አይወደውም እግዜር!››ይቺን አባባል በአንድ ጥንታዊ የግእዝ መወድስ ቅኔ እናትማት፡፡የቅኔው ይዘት፡- ‹‹ጥርስ ያለከንፈር፣ጣት ያለጥፍር›› አያምርም፤በዚህ አምሳል ‹‹ጸሎት ያለፍቅር፣ሃይማኖት ያለምግባር›› አይሰምርም የሚል ነው፡፡ሊቁ ይቀጥሉ…
  መወድስ!
  ጠፈረ-ምሳሌ፡ሰማይ፡እምከመ-ርኢኩ፤
  ኢያጸድቆ፡ለሰብእ፡ጸሎት፡እንበለ-ፍቅር፣
  ወኢይበቊዖ፡አሚን፡አመ-ኀበ-አልቦ፡ምግባር፣
  ዓዲ፡ኢይደልዎ፤
  ትዕቢት፡ፀሩ፡ለክርስቶስ፡በኵር፣
  ፍና-ትሕትና፡ዘየሐውር፣
  እስመ-ኀበ-ሀሎ፡ትዕቢት፡ህየ፡ሀሎ፡ኀሣር፣
  አኃውየሂ፡ከመ-ታእምሩ፡ምሳሌ-ዝንቱ፡ነገር፣
  አእዳው፡ኢይበቊዑ፡እንበለ-አፃብዕ፡ወአጽፋር፣
  ወኢየሤንዩ፡ምንተ፡በኀበ-ኩሉ፡ፍጡር፣
  አሥናን፡ባህቲቶሙ፡እምኀበ-አልቦሙ፡ከንፈር፡፡
  የዚህን ቅኔ ምስጢር ለመረዳት ‹‹ሃይማኖት እንበለ-ምግባር ምውት ይእቲ…ሃይማኖት ያለምግባር ሙት ነው›› የሚለውን የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ 2 ከቁ 17 ጀምሮ መዝለቅ!ወዳጆቻችን በዚያ ስትዘልቁ እኛ ደግሞ በዚህ ታቦታችንን ፍለጋ እንዝለቅ!

  ReplyDelete
 36. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:35 PM

  5.3.6 ደቂቀ እስጢፋኖስ የኪዳኑን ታቦት አይቀበሉም?
  (5.3.6.1) ይህን ርእስ ቤ/ክ በሰማናት ገጠመኝ እንጀምር!ተማሪው ጀማሪ ነው፡፡አትሮንስ ተዘርግቶ ለንባብ ቀረበ፡፡ጀመረ፡፡‹‹ወአውስአ ኢየሱስ--ኢየሱስም ተናገረ›› የሚለውን ንባብ ‹‹ወአውሰበ ኢየሱስ--ኢየሱስም አገባ›› ብሎት አረፈ፡፡መምህሩ ጮክ ብለው ‹‹ኧረረረ!በዚህስ አይሑድም አላሙት›› አሉት ይባላል፡፡አይሑድ ጌታን ምን ቢከሱት ከዝሙት ጋራ በተያያዘ ስሙን አንስተውት አያውቁም!‹‹የዳቪንቺ ኮድ›› የተሰኘ መጽሐፍ የጻፈ ፈረንጅ ግን የአይሑድን ሪከርድ አሻሻሎ አሳየን መሰል!ወደቀደመ ነገራችን እንመለስ!አጼ ዘርዐያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ‹‹ታቦት አይቀበሉም›› ብሎ ሲከስ አልሰማንም፡፡በዚህ እሱም አላማቸው!እርግጥ እሱ ካለፈ በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መነኰሳት ይህን አይነት ክስ አቅርበውባቸው ነበር፡፡ለክሱ የአባ ዕዝራ መልስ፡- ‹‹ታቦት የላቸውም ስለሚሉት ቅድስት ኦሪት የምትለውን ስማ ‹ከማይነቅዝ እንጨት ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ወርዱ አንድ ከሩብ የሚሆን ታቦት ስራ›(ዘፀ 25 ቁ23)፡፡ታቦት የሁላችን መመኪያ፣የመላእክትም መመኪያ ማርያም ነች›› ይላል ‹‹ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኵለሄ ዘግቡር እምእጽ ዘኢይኔቅዝ›› የምትለዋን የቅ/ኤፍሬም የእሑድ ውዳሴ ማርያም እያሰበ(ገ.290)፡፡ይህንማ ስለእመቤታችን ለመግለጽ ነው የተናገረው እንዳይባል በገጽ 308 በአባ ዕዝራ ጥረት ግዝት ተነስቶ ሰላም ከወረደ በኋላ ደቂቀ እስጢፋኖስ ጳጳሱ ፊት ቀርበው 80 ታቦታትን እንዳስባርኩ እና አባ ዕዝራ ለታቦቱ እጅ እንደነሳ ተጽፎ እናነባለን፡፡
  (5.3.6.2) አባ ዕዝራ አፈንግጦ ነው ይኸን ያደረገው እንዳይባል አባ እስጢፋኖስ በገጽ 100 ‹‹ታቦት የሚሆነውም ቅዱስ ሜሮን የተቀባ እንጨት›› ሲል እናገኘዋለን፡፡በገድለ አበው ወአኃው እንዲሁ ስለታቦት እንዲህ የሚል ንባብ አለ፡- ‹‹ሲመሽ መልእክተኛ መጣና ‹ካሕናቱን ዲያቆናቱን ታቦቶቹን አምጡ› አለ፡፡‹አንሰጥህም› አሉት፡፡ታቦታቸውንና ቅዱሳት እቃቸውን ነጥቋቸው ሄደ››(ገ.150)፡፡ደቂቀ እስጢፋኖሳዊው አባ አበከረዙን ለደቀመዛሙርቱ ከሚሰጣቸው ምክሮች አንዱ ‹‹በደረሳችሁበት ሁሉ የእግዚአብሔርን ታቦቶች ሳትይዙ አትሂዱ፡፡እናንተም በጉዟችሁ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ይረዳችኋል››የሚል ነበር(ገ.257)፡፡ፕ/ር ጌታቸው በተረጐሟቸው 4ቱም ገድላት ደቂቀ እስጢፋኖስ ስለታቦት ተቃውሞ ሳይሆን ፍቅርና ሰጊድ ሲያደርጉ ነው የምናየው፡፡ብቻ የቃለ ሕይወት ቤ/ክ ሰዎች እኛ ያላገኘነው የደቂቀ እስጢፋኖስ ገድል ሳያነቡ አልቀሩም!ወይም ‹‹ወይመስሎሙ ወልደ-ዮሴፍ›› የተባለውን የወንጌል ቃል በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ለመተርጎም እየታተሩ ነው መሰል፤‹‹Abba Estifanos objected to the worldly authority of the monks. He denied the presence of the Ark of the Covenant in Ethiopia and conducted worship services without the presence of a Tabot (a replica of the Ark of the Covenant) which is mandatory in every Orthodox Church.›› እያሉ ስፖንሰሮቻቸውን ያስደስታሉ--ያልተጻፈ እያነበቡ፤ያልተባለ እየተረጎሙ!ድብትርና በእንግሊዝኛ እንዴት ያዋጣል አያ!ፐፐፐ!
  (5.3.6.3)<>ሆሆሆ!‹‹በአይቴ ኀሊፈኪ፤ድጓ ተምህርኪ›› አሉ አባቶች!‹‹አባ›› የሚለው መዓርግ ከየት ተገኘና?ሆ!በሉ አባ እስጢፋኖስን በገጽ 59 ለካሕን ሲናዘዝ፣በገጽ 72 ቅስና ሲቀበል ታገኙታላችሁ፡፡አንብቡት!ልጆቹን በሚመለከት አባ ገብረክርስቶስ ከአባ ተወልደመድኅን ንስሐ ሲቀበል በገጽ 121፣በገጽ 129 ቃል በቃል በጳጳስ እንደሚያምኑ ሲናገሩ ታገኙዋቸዋላችሁ!ይነበብ!ስለበዐላት እና ሰንበታት አከባበር በገጽ 77፣የቅዱሳን አባቶችን ገድላት መጻፍ፣ማስጻፍ፣ማንበብ፣መስማት ስለሚያስገኘው ጸጋና በረከት ገጽ 115፣ለሙታን ቊርባን ስለማስቆረብ በገጽ 133፣ለሙታን ተዝካር ስለማውጣት በገጽ 131 ስላለ ደቂቀ እስጢፋኖስን ከፕሮቴስታንታውያን ደምሮ ማሰብን ሕሊና እሺ ብሎኝ አያውቅም!ወንድሞቻችን ግን የኛን ቤ/ክ ታሪክ ለመጻፍ ሲሉ ደከሙብን! ላይ ቤትና፤ታች ቤት ተራወጡ!ለድካማቸው አንዲት ተረትና ምሳሌ እናበርክት፡- ‹‹ሁለት ዛፍ ላይ ያረፈች ወፍ፤ሁለት ክንፏን ትነደፍ!››ጓዶች ተሰብሰቡ!
  5.2.7 ደቂቀ እስጢፋኖስ ያልተጠመቁ አረማውያንን ቤ/ክ ያስገቡ ነበር?
  ‹‹ወይመስሎሙ ወልደ-ዮሴፍ›› የምትለዋ ፋላሲ ሂደቷን ቀጥላለች፡፡ዘመዶቻችን በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ በተቀዋሚዎቻቸው የተሰነዘረውን ክስ እንዳለ እየወሰዱ ስም መስጠቱን ቀጥለውበታል፡፡‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስ ያልተጠመቁ አረማውያንን ቤ/ክ ያስገቡ ነበር›› ይሉናል እነ dacb.org፡፡ይሄንን ጥያቄ አጼ ዘርዐያዕቆብ ነበር በክስ መልክ ለአባ እስጢፋኖስ ያቀረበለት፡፡ጥያቄውንና መልሱን ከገድሉ ገጽ 100 እንደወረደ እናቅርብ፤‹‹አረማውያን ከቤተክርስቲያን እንደምታስገቡ ሰማሁ…እውነት ነው ወይስ ውሸት?››ብሎ ንጉሡ ጠይቆት አባ እስጢፋኖስ ሲመልስ ‹‹አረሚ ቀርቶ በአፋቸው ክርስቲያን ነን የሚሉትን እንኳን በሕጉ ፈለግ ካልሄዱ ከምሥዋዐችን አናካፍልም›› ነው ያለው፡፡ይሕ በፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን የእንግሊዝኛ አንድምታ ሲተረጎም ‹‹He allowed heathens to enter the church building.›› ተብሎ መሆኑ ሳቅ ስላቃችንን አመጣው!ኡኡቴ!‹‹አናካፍልም= allowed››!ትርጕም በእንብርክ ሄደች!

  ReplyDelete
 37. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:36 PM

  5.2.8 ደቂቀ እስጢፋኖስ (ባረፉ) ቅዱሳን ስም አይማጸኑም?
  (5.2.8.1) ይቺን ጥያቄ መልሶ በጥያቄ መመለስ ይቻላል፡፡ላረፉ ቅዱሳን ስም ካልተማጸኑ ገድሎቻቸው በሙሉ ለምን ‹‹አባ እከሌ መስዋዕትነትን ተቀበለ፤እማሆይ እከሊት፤አረፈች በረከት ረድኤታቸው ይደርብን!››ይላሉ?ገድላቱ ከጫፍ እስከጫፍ በዚህ አይነት መደምደሚያዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ያነበባቸው ይፍረደኝ!ማስረጃ ግድ ከተባለ ግን በገጽ 140 “…የአምላክ እናት ማርያም ሆይ እነሆ ከምሕረትሽ ጥላ ስር ተደግፈናል፤በጭንቀታችን ጊዜ ልመናችንን አትናቂ…”ተብላ የሰፈረችውን ንባብ እንጠቅሳለን፡፡ያም ሆኖ እነ ዊኪፒዲያ ከአባ እስጢፋኖስ ትምህርቶች አንዱ ‹‹Rejection of prayer to dead saints and angelic beings.››ይሉናል!
  (5.2.8.2) ዘመዶቻችንን አውቀው በተኙበት ወይም ሳያውቁ በሳቱበት ትቻቸው ይኸንን ስለዝንጋኤያቸው ዘለፋ እንዲሆንባቸው በሚመስል መልኩ የገድለ አበው ወአኃው ጸሐፊ የእመቤታችንን፣የመላእክትን፣የቅዱሳንና እና ሰማዕታትን ተራዳኢነት እየተማጸነ በአራኅራኂ ቃል ገድሉን ባሳረገበት ፓራግራፍ ልደመድመው!‹‹በድብ ፀር ዘመን…ሰማዕትነታቸውን በመልካም ሰማዕትነትና በመንፈሳዊ ገድል ከፈጸሙት ውስጥ ቁጥራቸውን ያወቅነው የቅዱስ ብፁዐዊ እስጢፋኖስ ወንድና ሴት ልጆች ሰማዕታትና ጻድቃን ጠቅላላ ድምር 1004 ነው፡፡የማናውቀውን እሱ ንብረቱን ይሰብስብ፡፡…ይኸንን ለኛና ከኛ በኋላ ለሚመጡ ማስታወሻ እንዲሆን እንዳገኘነው ጻፍነው፡፡በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ልመና፣በትጉሃን መላእክት ሁሉ ጸሎት፣በቅዱሳንና በሰማዕታት ሁሉ ጸሎት እግዚአብሔር የረድኤታቸውን በረከት ይስጠን፤አሜን፣አሜን፣አሜን፡፡››
  6. መደምደሚያና አስተያየት!
  6.1 የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ ቢነቀፍም ቢወደስም የኢኦተቤክ ታሪክ ነው ብዬ አምናለሁ!ስለሆነም ታሪኩን አይሑዳዊ ወይም ፕሮቴስታንታዊ ገጽታ መስጠት ፍጹም በደል ነው እላለሁ!
  6.2 እርግጥ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከመነሻቸው በ1426 ዓ.ም ገደማ ለእመቤታችንና ለመስቀል መስገድን ይቃወሙ እንደነበር በሁሉም ወገን አልተካደም!በመሆኑም ውግዘት ተላልፎ ነበር የሚለውን አመለካከት እቀበላለሁ፤እናገራለሁ!
  6.3 ነገር ግን ውግዘቱ በሊቀ ጳጳሳችን አቡነ ይስሐቅ በአጼ ናዖድ ዘመን በ1500 ዓ.ም መዳረሻ አካባቢ ከተፈታ በኋላ ደቂቀ እስጢፋኖስ በፍጹምነት ለኦርቶዶክሳዊት እምነት ቆመዋል፤ይህንንም በግራኝ ዘመን ካሕናተ-ደብተራን ሳይቀር በትግራይ ተራሮች ጉያ በተመሰረቱ የእመቤታችን ገዳማቶቻቸው በማስጠለል ቂሙን ሽረውታል ብዬ አምናለሁ!
  6.4 ለ70 ዓመታት አካባቢ የቆየውን ውግዘት መቀበሌ እንዳለ ሆኖ ንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ስመ-መንግሥቱ ቆስጠንጢኖስ ሆኖ ሳለ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ አርዮስን በመሰለ መናፍቅ ላይ ያላደረገውን እጅግ አስጸያፊ ቅጣት በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ መፈጸሙ ታሪካችን የሚያጠቁር ድርጊት ነው ብዬ አምናለሁ!ከውግዘት ባለፈ የሚፈጸምን አካላዊ ቅጣት አለመቃወም ድርጊቱ ዛሬም ቢፈጸም ሊበረታታ እንደሚችል ጠቋሚ አድርጌ አያዋለሁ!
  6.5 ቀደምት አባቶቻችን ቢችሉ የዘርዐያዕቆብን ድርጊት ‹‹ከውግዘት ወዲያ አካላዊ ቅጣት የለም›› ሲሉ ቢቃወሙ፣ተተኪዎችም በአካል ባይደርሱበትም ታሪኩን ቢተቹት ኖሮ በ1878 ዓ.ም በቦሩ ሜዳ ጉባኤ በነዙርዓምቤ እንግዳ ላይ የታየው ምላስ የመቁረጥ ድርጊት አይፈጸምም ነበር ብዬ ስለምገምት በአባቶች አርምሞ ቅር ይለኛል!
  6.6 ከዚህም ባለፈ አባቶቻችን ታሪኩን ከግራቀኝ አጣርተው ከመጻፍ ይልቅ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ያለውን እየሰሙ ሲተርኩ መኖራቸው፣እንዲሁም ስም አሰጣጥ ላይ ሳይጠነቀቁ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለእመቤታችንና ለመስቀል ለመስገድ እምቢተኛ ስለሆኑ ብቻ ‹‹አይሑዳውያን›› እና ‹‹ፕሮቴስታንት›› እንደነበሩ አድርገው ባገኙትና ስማቸውን ያከፋልናል ባሉት ስም ሁሉ ለመጥራት መራወጣቸው የኋላ ኋላ እነዚህ ሁለት ኃይላት ታሪኩን እንዳሻቸው ያለሀይ ባይ እንዲቆነጻጽሉት በር ከፍቷል ብዬ አምናለሁ!
  6.7 በዚህ ረገድ ምንም እንኳ በመግቢያቸውና በአንዳንድ የኅዳግ ማስታወሻዎቻቸው የገድላቱን አረዳድ አዛብተዋል የሚል ቅሬታ ቢኖረኝም አረጋዊው ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ገድላቱን በመተርጎም ግራቀኝ ዐይተን ታሪኩን በባለቤትነት መንፈስ ለመረዳትና ለመተረክ በማመቻቸት ታላቅ ውለታ ሰርተዋል እላለሁ!ድርሻቸውን ተወጥተዋል!ከጓሯችን የተቆረጠውን ዛፍ የማስመለስ ድርሻ የእኛ የአዳዲሶቹ ውሉድ እና አዋልድ ይሆናል!
  6.8 የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ በሀገራችን በቅጡ በባለቤትነት ስሜት አልተጠናም፡፡በመሆኑም ከአንዳንድ የቤ/ክ የቅርብ ሰዎች እንዲህ አይነት ጸሐፍት ሲወጡ ገንቢ ትችት ሳይዘነጋ ቢበረታታ የተገባ ይሆናል፡፡ታላላቅ የሚባሉ አበው ፕ/ር ጌታቸውን እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎች ዳንኤል ክብረትን የመካከለኛው ዘመን ቅዱሳንን ገድላት ሲተረጉሙ የነገሥታቱን ክብር አጣጥለዋል የሚል ክስ እናነባለን፡፡አልስማማበትም!ቅዱስ ዳዊትንና ንጉሥ ሰሎሞንን ያክል ታላላቅ ነገሥታትም ከጠንካራ ጎናቸው ጎን ለጎን ደካማ ታሪካቸው ሰፍሯል፡፡የኛ ነገሥታትም ታሪክ በዚያ መልኮ በጎና ጸያፍ ተግባራቸው መጻፍ አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡
  6.9 ታሪኮቹን ከሚያነቡና ከሚሰሙ ሰዎችም በተቻለ መጠን ታሪኩን ግራቀኙን ለማገናዘበ ቢሞከር ደስ ይለኛል፡፡እንደማየው ታሪኩ በ2ቱም ጽንፍ ያለው አቀራረብ ሕሊናን የሚፈታተን ነውና በተቻለ መጠን የተገናዘበ አመለካከት ቢኖረን!
  6.10 ታሪኩ መንፈሳዊ ይዘቱ እስኪጠፋ ድረስ እጅግ ፖለቲካዊ እንዲሆን መደረጉ ከቶም አያስደስተኝ!ምናልባት የተርጓሚው የፕ/ር ጌታቸው ሲቪ ከፍ ማለት የእሳቸው የግል አመለካከት ልሂቃንን ታሪኩን ገደብ ባለፈ መልኩ እጅግ ፖለቲካዊ እንዲያደርጉት የገፋፋ ይመስለኛልና ጉዳዩ ያለው ሃይማኖታዊ ገጽታ ቸል ባይባል ደስ ይለኛል፡፡

  ReplyDelete
 38. በአማን ነጸረNovember 15, 2015 at 10:38 PM

  ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡በአማን ነጸረ፡፡ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
  ማጣቀሻዎቼ!
  ሀ. መጻሕፍት(ሃርድ ኮፒ)
  1.ጌታቸው ኃይሌ(ፕ/ር)፣ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ፣1996፣ኮሊጅ ቪል ሚኒሶታ
  2.ዳንኤል ክብረት(ዲያቆን)፣አራቱ ኃያላን፣2006፣አግዮስ ኅትመት
  3.ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር፣ምንኵስና በኢትዮጵያ ዛሬና ትናንትና፣2000፣
  4. ድጓ፣1988 ዓ.ም ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት
  5.ወንድዬ ዓሊ፣በመከራ ውስጥ ያበበች ቤተክርስቲያን፡የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤ/ክ ታሪክ፣1990፣የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሥነ ጽሑፍ አገልግሎት
  6. መልአከብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ኰኵሐ ሃይማኖት፣1949
  7. ፍስሐ ያዜ፣የኢትዮጵያ የ5ሺህ ዓመት ታሪክ፣2004
  8.ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ(M.A)፣የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣1986 ዓ.ም፣2ኛ እትም፣ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት
  9.በኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትና ጳጳሳት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻(2000 ዓ.ም)፣በ2000 ዓ.ም፣ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት
  10. ይልማ ደሬሳ፣የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣3ኛ እትም፣2007
  11. ሉሌ መላኩ(ረ/ፕ/ር)፣የቤተክርስቲያን ታሪክ፣1986
  12. አለባቸው ኬዕሚሶ እና ሳሙኤል ሀንዳሞ፣ሐዲያ ሕዝብ ታሪክና ባህል፣ሐምሌ 2002
  13. ጾመድጓ፣1988፣ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት
  14.ክብረ ነገሠት፡ግእዝና አማርኛ፡ትርጉምና ኣርትዖት በስርግው ገላው(ዶ/ር)፣1994፣አ/አ/ዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል
  15. ዶናልድ ሌቪን (ትርጉም በሚሊዮን ነቅንቅ)፣ትልቋ ኢትዮጵያ፣2007 ዓ.ም፣አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ

  ለ. ከኢንተርኔት የተገኙ ማጣቀሻዎች (ሶፍት ኮፒ)
  1. ስእልና እስጢፋኖሳውያን http://art.thewalters.org/detail/31403
  2. ከእስጢፋኖሳውያን ገዳማት አንዱ የኾነው ጕንዳጕንዲ ማርያም ገዳም በቅርብ ጊዜ ስለነበረበት አሳዛኝ ሁኔታ በማኅበረቅዱሳን የተሰራ አጭር ቪዲዮ የማኅበረቅዱሳን ዶክመንተሪ ዘገባ ስለጉንዳዱንዲ ታሪክ https://www.youtube.com/watch?v=dvpf61YFDMU
  3. Hagos G The Dekike Estifanos: Towards an Ethiopian Critical theory January 22, 2013 ethiopiawinote https://ethiopiawinote.wordpress.com/2013/01/22/the-dekike-estifanos-towards-an-ethiopian-critical-theory/
  4. ፐሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይሑዲነት https://books.google.com.et/books?id=itUUAAAAIAAJ&pg=PA68&lpg=PA68&dq=the+cause+of+stephanites&source=bl&ots=-gvPu5R1LL&sig=DsIx8qNEtGn4PSQagwXJ8lcJrWE&hl=en&sa=X&ved=0CCYQ6AEwAmoVChMI3I-YovPNyAIVzA8aCh11cAVv#v=onepage&q=the%20cause%20of%20stephanites&f=false
  5. ለመስቀል ስለመስገድ ያሉ ኦርቶዶክሳዊ የውጭ ተሞክሮዎች https://oca.org/reflections/fr.-steven-kostoff/before-thy-cross-we-bow-down-in-worship
  6. ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ ደቂቀ እስጢፋኖስን በምንኵስና ሕይወት አርአያነት ጠቅሰዋቸዋል፡፡ http://eotcssd.org/ethiopian-orthodox-tewahedo-church-monasteries/55-2011-03-31-12-45-49/385-2014-07-04-05-56-58.html
  7. አጼ ዘርዐያዕቆብን ወደመከላከል ያጋደለች ጽሑፍ ይቻትና http://www.ahatitewahedo.com/2011/01/blog-post_21.html
  8. የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አተያይ ስለደቂቀ እስጢፋኖስ በጨረፍታ https://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2012/04/02/2-april-2012-1855/
  9. በልጅግ ዓሊ የተባሉ ሰው ከአብዮትና ለውጥ ጋር በማያያዝ ለእንቅስቃሴው ፖለቲካዊ ገጽታ የሰጡበት አጭር ጽሑፍ http://www.ethiomedia.com/augur/yemecheresha_qal.pdf
  10. እንቅስቃሴው ከሙስሊሞች ድምጻችን ይሰማ ጋርም ተነጻጽሮ ለማነሳሻነት ተሞክሯል http://sebiawi.blogspot.com/2013/08/blog-post_2191.html
  11. የዊኪፒዴያ ዘገባ https://en.wikipedia.org/wiki/Abba_Estifanos_of_Gwendagwende
  12. ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ያለው ፕሮቴስታንታዊ ዕይታ ባጭሩ http://www.dacb.org/stories/ethiopia/estifanos_.html
  13. የሶርያ ኦርቶዶክክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ሥርዓተ-ምንኵስና ባጭሩ http://www.suryoyo.uni-goettingen.de/library/monastic.html
  14. እንግሊዝኛ የአጼ ዘርዐያዕቆብ የተመጠነ ዜናመዋዕል ፓንክረስት እንደተረጎሙት https://tezetaethiopia.wordpress.com/2005/06/01/the-chronicle-of-the-emperor-zara-yaqob-1434-1468/

  15. Krzysztof Piotr BŁAśEWICZ, ETHIOPIAN MONASTICISM,1999,Institute of Oriental Studies Warsaw University
  16. STEVEN KAPLAN,INDIGENOUS CATEGORIES AND THE STUDY OF WORLD RELIGIONS IN ETHIOPIA: THE CASE OF THE BETA ISRAEL (FALASHA),1992, (The Hebrew University, Jerusalem)
  17. የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የዶክትሬት ማሙያ ጥናት,Filsata: The Feast of the Assumption of the Virgin Mary and the Mariological tradition of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church, 1988,unpublished,Princeton Theological Seminary
  18. ዮሐንስ ዘደማስቆ ስለ ክብረ-ስዕል http://www.documentacatholicaomnia.eu/03d/0675-0749,_Ioannes_Damascenus,_Apologia_Against_Those_Who_Decry_Holy_Images,_EN.pdf
  19. ካቶሊካውያን ስለ ስእል ያላቸው አመለካከት ከኛ ጋር ተመሳሳይ ነው፤እነሱ የተቀረጸ ምስልም ከመጠቀማቸው በቀር http://www.newadvent.org/cathen/07664a.htm
  20. የሶርያ(አንጾኪያ) ኦርቶዶክስ ቤ/ክ(ከ6ቱ ኦሪየንታል አንዷ እኅት ቤ/ክ) አቋም ስለስዕል http://www.antiochian.org/content/no-graven-image-icons-and-their-proper-use
  21. በቅርብ ጊዜ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን በመሰረቷቸው ገዳማት ዙሪያ በውጭ ምሁር የተደረገ ጥናት፤ጥናቱ ገዳማቱ በአሁኑ ጊዜ በኢኦተቤክ ስር ያሉና በዶግማ፣ቀኖና ትውፊት የተለየ አቋም እንደሌላቸው ያሳያል http://www1.uni-hamburg.de/www/ethiostudies/ETHIOSPARE/Publications/Nosnitsin%202013%20Stephanites.pdf

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአማን ነፀረ ለፃፈውና ሊሚፅፈው አስተያየት አድናቆትና ክብር አለኝ፡፡ እንዲህ ስል ግን እርሱ በሚለው ሁሉ እስማማለሁ ማለቴ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን በዚህ የጽሑፍ ርዕስ ዋናው ነገር የሰማዕቱ የአባ እስጢፋኖስ ነገር ቢሆንም በጎን የገድል መጽሐፎቻቸውን መሠረት አድርገህ አንዳንድ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ጠቅሰሃል፡፡ ሆኖም የጠቀስካቸው ነገሮች በአብዛኛው ለአንተ አመለካከለት እንዲደግፍ አድርገህ እንጂ የደቂቀ እስጢፋኖስን ማንነት አስተምህሮና አኗኗር አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማእከል ያደረገ ነው ማለት አልችልም፡፡ እንደሚታወቀው እነርሱ የኦርቶሶክስ ቤተክርስቲያን ፀረ ማርያምና ፀረ መስቀል ብላ የማትቀበላቸው፣ “በክህደታቸው” የተቀጡ እንጂ ስለ ክርስቶስ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሰማዕታት አድርጋ የማትቆጥራቸው ናቸው፡፡ አባ እስጢፋኖስ ሰማዕትነትን ሲቀበል እንኳ ሦስት ጊዜ “ክርስቶስ ክርስቶስ ክርስቶስ” ብሎ እንዳልቀላፋ በገድሉ ተጽፏልና አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ምክንያተ ሞቱን ሌላ ቢያደርገውም እርሱ ግን ስለ ክርስቶስ እንደሞተ ይህም እንኳ አንድ ምስክር ነው፡፡
   ስለሆነም ደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ አሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ ተቀባይነትን ያላገኙና ተገልለው ያሉ ሲሆኑ፣ (እንዲህ ስል ገዳማቶቻቸው ዛሬ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥር አይደሉም እያልኩ አይደለም፤ አባ እስጢፋኖስና ደቀ መዛሙርቶቻቸው ግን አሁንም ድረስ እንደ መናፍቃን የሚታዩ ናቸው ለማለት ነው) አብዛኛው የእምነት አቋማቸው ደግሞ ወደወንጌል የቀረበ በመሆኑ ደግሞ ተሐድሶአዊ አቋም ያላቸው ተደርገው ስለ ተቆጠሩ ተሐድሶ አድርገው ቢቆጥሯቸው ትክክል እንጂ ስሕተት አይሆንም፡፡ በተሐድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ እነርሱን ተሐድሶ ለማድረግ የሚጥሩትን ያህል አንተም በዐጼ ዘርአ ያእቆብ አስተምህሮ የተቀረጸች (የዕንጨት መስቀልን በአክብሮት ሰበብ የምታመልክ፣ ተአምረ ማርያምን የምታነብና የምታስነብብ (ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን የሚለውን ተመልከት) ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ለማስመሰል ጥረት አድርገሃል፡፡ እነርሱ ግን እንዲህ አልነበሩም፡፡ ተአምረ ማርያምን ከገዳማችን አናስገባም ያሉ ነበሩ፡፡ ከዚህ አንጻር ደቂቀ እስጢፋኖስን ወገን በማድረግ የቀደሙት በተሐድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉት ናቸው እንጂ የዘርዓ ያዕቆብ ኦርቶዶክስን ትምህርት የሚከተሉት አይደሉም፡፡
   ስለእነርሱ በጥቅሉ ይህን ካልኩ በዋናነት ላነሳ ወደፈለግኩት ነጥብ ልለፍ፡፡ አንተ በተለይም ስለ ፅድቅ ጉዳይ በክርስቶስ ብቻ ፀድቄያለሁ ማለት መንዘላዘልና ትምህክት እንደሆነ አድርገህ የፃፍከው እጅግ የተሳሳተና ዋናውን እውነት የሚቃወም ነው፡፡ እውነት በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ያልተመዘነና የክርስቶስን ደም በከንቱ የሚያስቀር ስለመሰለኝ ከእግዚአብሔር ቃል ትንሽ ለመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡
   ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ፅድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል እርሱም ለሚያምን ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው ልዩነት የለምና ሁሉም ኃጢአት ሰርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በፀጋው ይፀድቃሉ ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው እርሱ ቀርቶአል በየትኛው ሕግ ነው በሥራ በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም! ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲፀድቅ እንቆጥራለንና፡፡” (ሮሜ 3፥21-28)
   “ለሚሠራ ደመወዝ እንደዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፡፡ ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያፀድቅ ለሚያምን እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል፡፡” (ሮሜ 4፥5)፡፡
   “እንግዲህ ምን እንላለን ፅድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ፅድቅን አገኙ፡፡ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ፅድቅ ነው፡፡ እስራኤል ግን ወደ ጽድቅ አልደረሱም ይህስ ስለ ምንድን ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ፅድቅን ስላልተከተሉ ነው” (ሮሜ 9፥30-33)፡፡
   “የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ” (ገላ. 2፥21)
   እነዚህ ጥቅሶች ከያዕቆብ መልእክት ጋር የሚጋጩ አይደሉም ያዕቆብ የማይሠራ እምነት የሞተ ነው አያድንም አለ እንጂ ሰው የሚድነው በሥራው ነው እንዳላለ ሁሉ ከላይ የተገለጠው የመዳን መንገድ በሚሠራ እምነት የሚገኝ መሆኑን ሐዋርያው ጳውሎስ “በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።” ከብዙ በጥቂቱ ከእግዚአብሔር ቃል እነዚህን የጠቀስኩት ለማሳያ ያህል ነው፡፡ በአማን ነጸረ ሰው የፀደቀው በእግዚአብሔር ፀጋና ቸርነት ነው እንጂ በእኛ መንገድ ጽድቅ ይገኝበታል ወደተባለ ቦታ እየሄድን አግኝተን አይደለም፡፡ የተቀበለን የእኛ ፅድቅ የመርገም ጨርቅ ሆኖ እያለ ነው፡፡ መፅደቃችን ከፀጋው ከምሕረቱ የተነሣ ነው ልጁን የሰጠን፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለ ጸደቅንበት ነገር በግልፅ ተቀምጦ እያለ በክርስቶስ ፀድቄያለሁ የክርስቶስ ደም ለእኔ ኃጢአት በቂ ነው ፅድቅም እሱ ነው ብሎ በክርስቶስ መመካት ኃጢአት ሊሆን፣ በራሳችን ነው የምንፀድቀው በሥራችን ነው ብሎ መመካት ትክክል ሊሆን ማለት ነው፡፡ የእኛ ፅድቅ እኮ የመርገም ጨርቅ ነው ተብሎአልና ወንዝ አያሻግርም፡፡
   በክርስቶስ ብቻ ነው የምፀድቀው ብሎ ማመን መንዘላዘል ነው ትምክህት ነው ያሉት በአማን ነፀረ በእውነት መጽሐፍ ቅዱስን አይተዋል ፈትሸዋል ለማለት ያስቸግረኛል፡፡ እንደ ገና የእግዚአብሔርን ቃል መርምረውና ፈትሸው ቢመለከቱት መልካም ነው እላለሁ፡፡ ምክንያቱም በክርስቶስ ብቻ ነው የምጸድቀው ብሎ ማመን ትህትና እንጂ ትምክህት አይደለም፡፡ እርስዎ እንዳሉት ለመፅደቅ ሥራ አያስፈልግም፤ ይልቁንም የፀደቀ ሰው ሥራ ይሠራል፡፡ ለምሳሌ አንድ ተክል ሲተከል በመጀመሪያ መፅደቅ አለበት እንጂ ለመፅደቅ ፍሬ ማፍራት የለበትም፡፡ ስለ ጸደቀ ግን ፍሬ ያፈራል፡፡ አምኖ የመጽደቁ ማረጋገጫ ነውና፡፡ እርስዎ በቅኔ የገለጡትን ሐሳብ እዚህም ላይ በቅኔ ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡
   ወላድያኒነ ቀድሞት ድህረ በኃጢአት ወደቁ
   ፍትሐ ሞት መጽኦሙ ላዕለ አዳም ወደቂቁ
   እስከነ ወረዱ ውስተ ሲኦል ዘአይትረከብ ዕመቁ
   ኖኅ ወአብርሃም ወካልአንሂ አለ በግብሮሙ ተዐውቁ
   ኢበቁኦሙ ጽድቆሙ ዳእሙ በመርገመ አዳም ወሞት ኩሎሙ ተሐንቁ፡፡
   በጽድቀ ርእስክሙ ቀዊመ እለ ትጽሕቁ
   እም ጸጋ መድኃኒት ኀበ ደይን ከመ ኢትደቁ
   መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ በአስተሐይጾ ጠይቁ
   እንበለ ክርስቶስ በርእሶሙ ከመ ኢድኅኑ በሕቁ
   አብርሃም በምግባሩ ወኢዮብ በጽድቁ

   ትርጉም
   አዳምና ሔዋን በኃጢአት ሲወድቁ
   ወደ ሲኦል ጉድጓድ ወርዱ ጠለቁ
   ሁላችን ተወለድን ከእነርሱ በሩቁ
   ከእኛም መሃል አሉ እነኖኅ በበጎነታቸው የታወቁ
   በአዳም መርገም ሞት እነርሱም ታነቁ
   ዕዳ ሊከፍል አልበቃም የሰው ሁሉ ጽድቁ
   በሥራ ለመጽደቅ የምትናፍቁ
   ከመዳን ጸጋ ፎቅ ቁልቁል እንዳትወድቁ
   ብሉይን ሐዲስን መርምሩ ዕወቁ
   በሥራው አልዳነም አብርሃም ታላቁ ደገኛው ኢዮብም አልዳነም በጽድቁ

   Delete
 39. እውነቱ ይነገር ይሰማNovember 16, 2015 at 7:18 AM

  እውነትን ለማወቅና ነጻ ለመውጣት ምናለበት በቃሉ ላይ ብቻ ብናተኩር???
  1)1ኛ ጴጥ 4፡11
  2)1ኛ ጢሞ 4፡7
  3)ኢዮብ 37፡19
  4) ኢዮብ 36፡26
  5)ሆሴዕ 6፡3
  6)ሆሴዕ 4፡6
  7)ዮሃንስ 13፡17
  8)ዮሃንስ 15፡1-11
  9)ዮሃንስ 17፡16
  10)መዝ (119)፡9_11
  11)ኢሳ 66፡2
  12)ሰቆ ኤር 3፡26

  ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ለእኛም፤ እንወዳታለን ለምንላት ኦርቶዶክ ቤ/ክም፤ ለሕዝባችንም፤ ለኣገራችንም፤ ፈጽሞ ፈጽሞ አይጠቅምምና እባካችሁ ቆም ብለን እንድናስተውልና እውነተኛ የሆነውን በመረዳት እናድርግ (ፊልጵ 4፡8 9)

  ማቆች!ወገኖቼ ስለሆናችሁ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣችሁ እላለሁ።

  በተወደድንበት ሰማያዊ ፍቅር
  የሥጋ ብቻ ወንድማችሁ፡

  እውነቱ ይነገር ይሰማ!

  ReplyDelete
 40. እውነቱ ይነገር ይሰማNovember 16, 2015 at 7:19 AM

  እውነትን ለማወቅና ነጻ ለመውጣት ምናለበት በቃሉ ላይ ብቻ ብናተኩር???
  1)1ኛ ጴጥ 4፡11
  2)1ኛ ጢሞ 4፡7
  3)ኢዮብ 37፡19
  4) ኢዮብ 36፡26
  5)ሆሴዕ 6፡3
  6)ሆሴዕ 4፡6
  7)ዮሃንስ 13፡17
  8)ዮሃንስ 15፡1-11
  9)ዮሃንስ 17፡16
  10)መዝ (119)፡9_11
  11)ኢሳ 66፡2
  12)ሰቆ ኤር 3፡26

  ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ለእኛም፤ እንወዳታለን ለምንላት ኦርቶዶክ ቤ/ክም፤ ለሕዝባችንም፤ ለኣገራችንም፤ ፈጽሞ ፈጽሞ አይጠቅምምና እባካችሁ ቆም ብለን እንድናስተውልና እውነተኛ የሆነውን በመረዳት እናድርግ (ፊልጵ 4፡8 9)

  ማቆች!ወገኖቼ ስለሆናችሁ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣችሁ እላለሁ።

  በተወደድንበት ሰማያዊ ፍቅር
  የሥጋ ብቻ ወንድማችሁ፡

  እውነቱ ይነገር ይሰማ!

  ReplyDelete
 41. Le beaman NETSERE egnam yemnilew Dekike estifa Menfkan AYDELUM Haimanotachew Godolo Metsihafkidusacwe mulue 81 never silezih orthodoksawyan enji menafkanm alneberum Seytanm libalu Aygebam new ORTHODOKSAWINETA HEW KAMENACHIHU NABKEDENETSER ENA ZERAYAEKOB LEMSLACHEW YEMIYASEGDU NEBERU NABKEDENETSER YEMISADEBU ANDEBETOCH zerataekob chekayu yeswen MILAS yemikort yesewn afncha yemikort yezemnu ISIS HAYMANOTE HA NEBERE LEMALET ?????

  ReplyDelete